Кабинет
AMU ግቢ ጉባኤ ቤተ-መፅሀፍት

AMU ግቢ ጉባኤ ቤተ-መፅሀፍት

ይህ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ main ካምፓስ ግቢ ጉባዔ የቤተ-መፃህፍት ጥያቄ ና መልስ እንዲሁም ወቅታዊ መረጃዎች የሚተላለፍበት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው ማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት ካላቹ በዚህ @AMUlibrary_bot ያድርሱን።

Юзернейм
@gebigubae_library
Категория
Религия
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Создан
, 3 года
Подписчики1 652
Просмотров на пост, 7 дн.208−52% к пред. 7 дн.
ERR12,59 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
7 нояб. 2026 г.568
16 нояб. 2026 г.560
18 нояб. 2026 г.306
21 нояб. 2026 г.208

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01

    Без текста

    Фотоальбом
    Просмотры598
    Пересылки1
    Реакции—
    Комментарии—
  2. 02

    Без текста

    Фотоальбом
    Просмотры587
    Пересылки0
    Реакции—
    Комментарии—
  3. 03

    Без текста

    Фотоальбом
    Просмотры568
    Пересылки0
    Реакции—
    Комментарии—
  4. 04

    Без текста

    Фотоальбом
    Просмотры567
    Пересылки0
    Реакции—
    Комментарии—

Новые посты

#1749Фото

✝እንኳን አደረሳችሁ ! ☞ወርኀ ኅዳር ቡሩክ፤ ወአመ ፲ወ፪፦ ✝በዓል ዐቢይ ወክቡር ለዘመደ ክርስቲያን፦ በእንተ ዕበዩ ወክብሩ ለመልአክ ንጹሕ፥ ዐቢይ ወክቡር፥ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት፥ ሊቆሙ ለኃይላት ሰማያውያን፥ መሐሪ ወርኅሩኅ ለዘመደ እጓለእመሕያው፥ ኃያል ወልዑለ መንበር (ረዳኤ ምንዱባ፥ ወሰዋቄ ትንቱናን) ✝ተዝካረ ተአምር ዘገብረ፥ መልአክ ክቡር፥ ሚካኤል ሊቅ፥ ሊቀ መላእክት፥ ርዕሰ ኩሎሙ ኃይላት ሰማያውያን፥ ርኅሩኀ ልብ ወመስተሣህል፥ ለነገደ ያዕቆብ እስራኤል፥ ዘመርሆሙ መዓልተ በዐምደ ደመና፥ ወኩሎ ሌሊተ በብርሃነ እሳት (ዘረድኦ ለኢያሱ እስከ አጥፍኦሙ ለነግሥተ ከነዓን) ✝ወተዝካረ በዓሎሙ ለቅዱሳን፦ ማቴዎስ ሐዋርያ ወወንጌላዊ፥ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ወሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ላሊበላ ጻድቅ ወመስቀል ክብራ፥ ወሠምራ ክርስቶስ ብጽዕት፥ ማር ቴዎድሮስ በናድሌዎስ ምሥራቃዊ፥ ወማር ድሜጥሮስ ድንግል ❖ ወበዓለ ቅዱሳን አበው፦ ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ ወነቢይ፥ ወወልደ ነዌ፥ ኢያሱ/አውሴ መስፍን፥ መድኀኒቶሙ ለእስራኤል፥ ዘቀተለ ነገሥተ፥ ወአውረሶሙ ርስተ ለሕዝቡ፥ ወዓዲ ዘአቀመ ፀሐየ በገባዖን፥ ወወርኀ በቆላተ ዔሎም፥ ረድኡ ለቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት (ዘርዕዮ ለሚካኤል በኢያሪኮ)

Открыть в Telegram
Просмотры222−52%к среднему
Пересылки1
Реакции—
Комментарии0
#1748Текст

+አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ ወድንግል፥ ኃያል ወመስተጋድል፥ ወብእሴ እግዚአብሔር፥ ማር ዮሐንስ ወልደ ዘካርያስ፥ መጥምቀ መለኮት፥ ወጸያሔ ፍኖት፥ ወነቢየ ልዑል፥ ሐዋርያ ወካህን ወሰማዕት፥ ባሕታዊ መምህር ወመገሥጽ፥ ዘኢያደሉ ለገጽ፥ ወዘየዐቢ እምትውልደ አንስት፥ ዘወደሶ እግዚኡ (አስተርእዮተ ርዕሱ በደብረ ማኅው፥ በምድረ ግብጽ) ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ ወድንግል፥ ጽሙድ ወመስተጋድል፥ ብእሴ እግዚአብሔር፥ ማር አባ ፊላታዎስ ጠቢብ፥ ሊቀ ጳጳሳት ዘሀገረ እስክንድርያ፥ ሰባኬ ሃይማኖት፥ ወመምህረ ወንጌል፥ ወመተርጉመ መጻሕፍት ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጽሙድ ወመስተጋድል፥ ጻድቅ ወንጹሕ ወድንግል፥ ማር አባ ዳንኤል ዘአስቄጥስ፥ ጳጳስ ዘብሔረ ኢትዮጵያ ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ፥ ጽሙድ ወመስተጋድል፥ ብእሴ እግዚአብሔር፥ ማር አባ ባሕራን ቀሲስ፥ ብእሲ የዋህ፥ መፍቀሬ ጸሎት ወምጽዋት(ፍቁረ ቅዱስ ሚካኤል) ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ፥ ፍቁር ወመስተጋድል፥ ወመፍቀሬ እግዚአብሔር፥ ማር ዱራታዎስ ቡሩክ፥ ዘሀገረ ቆሎንያ፥ ዘያፈቅር ምጽዋተ (ዘአስተርአዮ ሚካኤል) ✝ቅድስት ወቡርክት፥ ስብሕት ወብጽዕት፥ ክብርት ወልዕልት፥ መፍቀሪተ ክርስቶስ መድኅን፥ ቴዎብስታ ጻድቅት (ብእሲቱ) ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ፥ ጽሙድ ወመስተጋድል፥ ማር ሐፄ በዕደ ማርያም ጻድቅ፥ መፍቀሬ እግዚአብሔር ልዑል፥ ወመፍቀሬ እሙ ድንግል፥ ወርቱዓ ሃይማኖት፥ ወንጉሠ ኢትዮጵያ፥ ዘሐነጻ ለአትሮንሰ ማርያም (ወልዱ ለጻድቅ ዘርዓ ያዕቆብ፥ ወአቡሁ ለማር ናዖድ) ✝ቅድስት ወቡርክት፥ ስብሕት ወብጽዕት፥ ክብርት ወልዕልት፥ መፍቀሪተ ክርስቶስ መድኅን፥ ዕሌኒ ንግሥት፥ ዘብሔረ አግዓዚ (ብእሲቱ) ✝ክቡራን ወዐቢያን፥ መፍቀርያነ ክርስቶስ፥ ጻድቃን ንጹሐን (ሰብአ ቤቱ ለማር በእደ ማርያም) ❖ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ። ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

Открыть в Telegram
Просмотры194−58%к среднему
Пересылки0
Реакции1
Комментарии0
#1747Текст

በዘመናችን ያሉ ሐሰተኛ ነቢያትን እንዴት መለየት ይቻላል? በብሉይ ኪዳን ነቢያተ ሐሰትና ነቢያተ ጽድቅ የሚለዩበት መገለጫ ነበራቸው። ከመገለጫዎቹ አንዱ የተናገሩት የትንቢት ቃል ሳይፈጸም ከቀረ ነቢያተ ሐሰት እንደሆኑ ይታወቃል። ይህ ግልፅ የሆነ መለያቸው ነበር፤ ነቢዩ ዮናስ ነነዌ ሄዶ መስበክ ያልፈለገበት ምክንያት አንዱ ይህ ነበር፤ ይኸውም የነነዌ ሀገር በሦስት ቀን ውስጥ ትቃጠላለች ትገለበጣለች ብዬ ብሰብክና እግዚአብሔር ምሕረት አድርጎላቸው የተናገርኩት ቃል ሳይፈጸም ቢቀር፤ ነቢየ ሐሰት ልባል አይደለምን ብሎ ለስሙ ተጠንቅቆ አልሰብክም ያለበት ምክንያት ለዚሁ ነበር (ዘዳ ፲፰፥፳ ፤ ዮና ፩፥፩)። ባዕድ አምልኮን የሚከተል፤ ሕዝብን የሚሸነግል፤ በክፉ መንፈስ የሚመራ፤ ስለራሱ የሚያወራ ሲሆንና አካሄዱ ክፉ ከሆነ ያ ነቢይ ነቢየ ሐሰት ነው፡፡ ዛሬ በዘመናችን የምናያቸው ነቢያት ከእነዚህ ይመደባሉ፤ ለሕዝቡ የማይራሩ እነርሱ ቁርጥና ክትፏቸውን በልተው ጠጃቸውን ጠጥተው በባዶ አንጀቱ ሊሰማቸው የተሰበሰበውን ሕዝብ "ጌታ እንዲህ ብሎኛልና እንዲህ አድርግ" እያሉ በጠራራ ፀሐይ የደሀውን ገንዘብ እየመዠገጉና የዋሁን ማኅበረሰብ በኀጢአት እያስወጉ የራሳቸውን ክብር እየቆለሉ ሌላውን እያቃለሉ፤ ግብዝ ሕዝባቸውን እያታለሉ የሚኖሩ ነቢያተ ሐሰት ናቸው — (ዘዳ ፲፫፥፩ ፤ ፩ኛ ነገ ፳፪፥፲፱ ፤ ኤር ፳፫፥፱)። ኀጢአት በበዛ ጊዜ ስለፍርድ ስለሰላም የሚተነብይ ከሆነ ይህ ማለት ኀጢአት እየሠሩ ጣዖት እያመለኩ የእግዚብሔር ቁጣ እንደሚመጣ በመናገር ፋንታ ሰላምና ደስታ ይሆንላችኋል፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው እያለ ሕዝቡን የሚያታልል ከሆነ ያ ነቢይ ሐሰተኛ ነቢይ ነው፡፡ የትንቢቱ ቃል ከመንፈሳዊነቱ ይልቅ ሥጋዊነቱ የሚያመዝን ከሆነ ለምሳሌ ሥራ ታገኛለህ፤ ትዳር ታገኛለህ፤ ውጭ ሀገር ትሔዳለህ፤ ሀብታም ትሆናለህ እነዚህን የመሳሰሉት ነገሮች፤ ትንቢት ከሚባሉ ይልቅ ሟርት ይባላሉ። ሕዝ ፲፫፥፫ ፤ ኤር ፳፫፥፲፮ ፤ ኤር ፮፥፲፫)። ግለሰቡ ከራሱ ጥቅምና ክብር አንጻር የሚናገር ከሆነ ወይም ዛሬ በየመናፍቃኑ አዳራሽ እንደምናየው ትንቢት እናገራለሁ ባዩ የሚናገረው ትንቢት የራሱን ጥቅም ለማሟላት ክብሩን ለማስጠበቅ የሚናገር ከሆነ፤ ለምሳሌ «ዕገሊትን ታገባለህ ተብያለሁ» በማለት የፈለጉትን ማድረግ፤ ወይም ይህን ያህል ብር ታገኛለህ ተብያለሁና አድርጉ የሚል ከሆነ ያ ነቢይ ሐሰተኛ ነቢይ ነው (ሚክ ፫፥፲፩) ምክንያቱም ከእውነተኞች ነቢያት እንዲህ ዐይነት ጠባይና ዓመል ታይቶ አይታወቅም፤ እንዲያውም አብዛኞቹ ነቢያት እነኤልያስ፣ እነኢሳይያስ፣ ሌሎችም ነቢያት እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሕጉን የሚያከብሩ ለእግዚአብሔር ያደሩ ምንም ሀብት ጥሪት የሌላቸው እግዚአብሔርን ሀብት ጥሪት አድርገው የኖሩ ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ አንድም ቦታ ስለ ራሱ ታሪክና ክብር የተናገረ ነቢይ የለም። ጉዳዩ (የትንቢቱ መልእክት) ከእግዚአብሔር ጋራ በምንም መልኩ የማይገናኝ ከሆነ ለምሳሌ አምልኮተ እግዚአብሔርን ከማስፋፋት፤ ነገረ ሃይማኖትን ከማስተማር፤ ወደ እግዚአብሔር መንገድ ከመመለስ፤ የንስሐ ሕይወትን ከመስበክ የራቀ ከሆነ ይህ ትንቢት አይባልም። ምክንያቱም የትንቢት መጨረሻ ግቡ ሰውን ወደ ሃይማኖት ማምጣት፤ ከእግዚአብሔር ጋር ማገናኘትና ንስሐን መስበክ ነው (ኢሳ ፴፭፥፭)። ትንቢቱ ከሰው መንፈሳዊ ሕይወት ጋር ፍጹም ግንኙነት የሌለው ከሆነ ያ ሰው ያለምንም ጥርጥር ነቢየ ሐሰት ነው፤ ዛሬ መናፍቃን እንደሚያደርጉት በዓለም ስለሚደረጉ ሁነቶችና ወቅታዊ ጉዳዮች ማንነታቸውንና ተቀባይነታቸውን ለማጉላት ሲሉ የሚተነብዩ (የሚያሟርቱ) ሰዎች አሉ። ለምሳሌ በዓለም ዋንጫ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ የዓለም ሕዝብ ትኩረት የሚስቡ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫዎች ሊሆን ይችላል አስቀድሞ ዕገሌ ያሸንፋል ዕገሌ አያሸንፍም የሚባሉት ነገሮች እነዚህንና የመሳሰሉ ሁሉ «ሟርት» ይባላሉ እንጂ ትንቢት አይባሉም፤ እንዲሁም ግለሰቡ ያለበትን ሁኔታና ፍላጎቱን በማየት ግምት መስጠት፤ ለምሳሌ የጤና ጉድለትን በሚመለከት የኑሮ ደረጃን፣ ሀብትን፣ ሥልጣንን በሚመለከት አስቀድሞ ግምት በመውሰድ የሚነገሩ ሁሉ ይህ ትንቢት አይባልም (ኤር ፭፥፴) ስለዚህ ዛሬ ትንቢት እንናገራለን ነቢያት ነን የሚሉ ሁሉ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ የሐሰት ነቢያት መሆናቸውን በዚህ ቃል መዝኖ ማወቅ ይቻላል። ዳግመኛም ሐሰተኞች ነቢያት እንደሚነሡ ክርስቶስ ለሐዋርያት፣ ሐዋርያት ለሰብአ አርድእት ከዚያም በኋላ ተላውያነ ሐዋርያት በየዘመናቸው አስጠንቅቀዋል (ማቴ ፯፥፲፭ ፤ ፪ኛ ጴጥ ፪፥፩ ፤ ፩ኛ ዮሐ ፬፥፩)። ስለዚህ ከኅሊናቸው ሰሌዳ ከልቡናቸው ጓዳ አንቅተው የሚናገሩ፤ ሳይላኩ ተልከናል ብለው ራሳቸውን ነቢያት አድርገው የሾሙትን ነቢያተ ሐሰት እንዳንቀበል የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ያዝዘናል፦ ❝እኔ የቅርብ አምላክ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ትንቢት የሚናገሩላችሁን የነቢያትን ቃል አትስሙ፤ እነሆ ከምላሳቸው ትንቢት አውጥተው እርሱ ይላል በሚሉ ነቢያት ላይ ነኝ፤ እነሆ ሐሰት በሚያልሙ በሚናገሩም በሐሰታቸውና በድፍረታቸው ሕዝቤን በሚያስቱ በነቢያት ላይ ነኝ፤ ይላል እግዚአብሔር እኔም አላኳቸውም አላዘዝኳቸውም ለእነዚህ ሕዝብ በማናቸውም መልኩ አይረቧቸውም❞ — በማለት የሐሰት ነቢያት ለሕዝብ ደኅንነት ጠንቅ ለሀገር ሰላም ጭንቅ መሆናቸውን ተናግሯል። በተለይ በዘመናችን በየመናፍቃን አዳራሽ እንደምንሰማው "ነገ ሀብታም ትሆናለህ፤ እንዲህ የሚባል ድርጅት ያንተ ይሆናል" እያሉ በኑሮ ሂደት ሳይሠሩ ሳይደክሙ መበልጸግን የሚያስመኙ ሕዝብን መረን የሚያደርጉ፤ ስንፍናን የሚያስተምሩ ዘረፋን የሚያስፋፉ፣ የደሀን ገንዘብ የሚገፉ በአዕምሮ የሰነፉ ዳተኞች ነቢያት መሆናቸውን አውቀን ከእነዚህ ሐሰተኛ ነቢያት እንድንርቅ ያስጠነቅቀናል (ኤር ፳፫፥፳፫)። እኛም ቤት በስመ አጥማቂ፣ በስመ ሰባኪ ክርስቶስን እንዲሰብኩ ታምነው በተሰጣቸው ዐውደ ምሕረትና መንጋ ላይ "እኔ እንዲህ ሆኜ፣ እንዲህ አድርጌ ..." እያሉ ራሳቸውን ብቻ የሚያገንኑ 'አገልጋዮች' ቁጥራቸው ብዙ ነው። ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ! ዲ/ን ኃይለራጉኤል

Открыть в Telegram
Просмотры306−33%к среднему
Пересылки2
Реакции5
Комментарии0
#1743Фотоальбом

Переслано из አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры598+31%к среднему
Пересылки1
Реакции—
Комментарии—
#1742Фотоальбом

Переслано из አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры567+24%к среднему
Пересылки0
Реакции—
Комментарии—
#1741Фотоальбом

Переслано из አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры587+28%к среднему
Пересылки0
Реакции—
Комментарии—
#1740Фотоальбом

Переслано из አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры568+24%к среднему
Пересылки0
Реакции—
Комментарии—
#1739Фотоальбом
Просмотры522+14%к среднему
Пересылки0
Реакции2
Комментарии0
#1738Текст

Переслано из ያሬዳውያን

🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 የጥቅምት 8 የሁለተኛው ሳምንት ማኅሌተ  ጽጌ በዓለ ፬ቱ እንስሳ ወኪሮስ ገዳማዊ ሥርዓተ ማኅሌት አማርኛ ትርጓሜ ክፍል ፪ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ማኅሌተ ጽጌ እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተኣምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ @EOTCmahlet ትርጉም ነጭ እና ቀይ የሆንሽ ጽጌ በንጽሕናና በተኣምር ቀን ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ  ልጅሽን ታቅፈሽ ነዪ ። ርግቤ ሆይ ከሀዘን ታረጋጊኝ ዘንድ ነዪ ። መልካም የሆንሽልኝ ሆይ ከደስተኛ መልአክ ከገብርኤል ጋራ እና እንዳንቺ ሩኅሩኅ ከሆነ ከመልአኩ ከቅዱስ ገብርኤል ጋራ ነዪ ። @EOTCmahlet ወረብ፦ ንዒ ርግብየ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/ ወንዒ ሰናይትየ ወንዒ ሰናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ/፪/ ትርጉም፦ ርግቤ ሆይ ነዪ ከሚካኤል ጋራ ነይ።  መልካም የሆንሽልኝ ሆይ ከደስተኛ መልአክ ከገብርኤል ጋራ እና እንዳንቺ ሩኅሩኅ ከሆነ ከመልአኩ ከቅዱስ ገብርኤል ጋራ ነዪ ። ዚቅ በሰላም ንዒ ማርያም፤ትናዝዝኒ ኃዘነ ልብየ፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሚካኤል ወገብርኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሱራፌል ወኪሩቤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ኲሎሙ ቅዱሳን፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ወልድኪ አማኑኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ለናዝዞ ኩሉ ዓለም። ትርጉም፦ ማርያም!! ከልቤ ኀዘን ታረጋጊኝ ዘንድ በፍቅር አንድነት ( በሰላም) ነይ፤ ማርያም!! ከሚካኤል እና ከገብርኤል ጋር በፍቅር አንድነት ( በሰላም) ነይ፤ ማርያም!! ከሱራፌል እና ከኪሩቤል ጋር በፍቅር አንድነት ( በሰላም) ነይ፤ ማርያም!! ከቅዱሳን ሁሉ ጋር በፍቅር አንድነት ( በሰላም) ነይ፤ ማርያም!! ከልጅሽ ከአማኑኤል ጋር በፍቅር አንድነት ( በሰላም) ነይ፤ ማርያም!! ዓለምን ሁሉ ለማረጋጋት በፍቅር አንድነት ( በሰላም) ነይ። ማኅሌተ ጽጌ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡ ትርጉም የስሙና የሞቱ መታሰቢያ ባንቺ የተጻፈብሽ የሚያበራ ከሆነ ዕንቈ ባሕርይ ይልቅ የጠራ ወርቅ ክበብ ያለው የራስ ቊር የተባለ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ የራስ ልብስ ጌጥ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ለእርሱ ሁሉን ታሰግጅለታለሽ (ታንበረክኪለታለሽ) እርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል ። ወረብ፦ ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየሐቱ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/ ማርያም አክሊለ ጽጌ ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ/፪/ ትርጉም፦ ከዕንቈ ባሕርይ ይልቅ የጠራ ወርቅ ክበብ ያለው የራስ ቊር የአበባ አክሊል ማርያም የጊዮርጊስ የመንግሥቱ የራስ ልብስ ጌጥ ሽልማት ነሽ ። ዚቅ፦ ይእቲ ተዓቢ እምአንስት እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት መድኃኒቶሙ ለነገሥት አክሊል ንጹሕ ለካህናት ብርሃኖሙ ለከዋክብት @EOTCmahlet ትርጉም፦ ከሴቶች ይልቅ ከፍ ከፍ ትላለች ። የሰማዕታት እናታቸው ነች ። የመላእክት እኅታቸው ነች ። የነገሥታት መድኃኒታቸው ነች ።  ለካህናት ንጹሕ አክላለቸው ነች ። የከዋክብት ብርሃናቸው ነች ። ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ። @EOTCmahlet ወረብ፦ ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም /፪/ ማርያም ከመ ዖፍ ተዓይል ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ/፪/ @EOTCmahlet ትርጉም ማርያም ማረፊያ እንዳጣች ወፍ ብቻዋን በግብፅ ተራሮች ውስጥ ትንከራተታለች፤ የሕፃናትም ደም በመንገዷ ሁሉ ይፈሳል። @EOTCmahlet ዚቅ፦ አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤ አድባራተ ኤልኪ ከመ ዖፍ፤ እንዘ ከመ ዝናም ያንደፈድፍ፤እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ። @EOTCmahlet ትርጉም ልጅሽን አቅፈሽ ከሰይፍ ባሸሸሽ ጊዜ፤ ከዓይኖችሽ እንባ ከጉንጮችሽም ወዝ እንደ ዝናም እየወረደ ተራሮችን እንደ ወፍ ዞርሽ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ፤ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ ለዘሀሎ መልእልተ አርያም።አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ።ዘከለሎ ለሰማይ በከዋክብት ብሩህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወለምድርኒ አሠርገዋ በጽጌያት ንፁህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወሠርዓ ሰንበተ ለነባረ ያዕርፉ ባቲ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌ:ማ- መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት። ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ። @EOTCmahlet ትርጉም ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ከአርያም በላይ ያለ የአምላክ የጥበቡ ብዛት  እጅግ የሚያስደንቅ ነው ። የጥበቡ ብዛት እጅግ የሚያስደንቅ ነው ። ምሕረቱን በእኛ ላይ ገለጠ ። ሰማይን በሚያበሩ  ከዋክብቶች ያስዋበ /የከለለ / ምሕረቱን በእኛ ላይ ገለጠ ። ምድርንም ንጹሕ በሆኑ አበባዎች አስዋባት ። ምሕረቱን በእኛ ላይ ገለጠ ። በእርሷ ያርፉባት ዘንድ ሰንበትን ሠራ ። ምሕረቱን በእኛ ላይ ገለጠ ።   @EOTCmahlet አመላለስ፦ መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት/፪/ ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ/፬/ @EOTCmahlet ትርጉም የቅዱሳን መዓዛቸው በሸለቆዎች ውስጥ እንዳለ እንደ ሱፍ አበባ ነው ። ቀንሞስ የተባለ ሽቱን ናርዶስ ከተባለ ሽቱ ጋር አፈሩ ። 👇👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCmahlet👈                  👉@EOTCmahlet👈 👉@EOTCmahlet👈 🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹       @EOTCmahlet   #ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ

Открыть в Telegram
Просмотры1 026+124%к среднему
Пересылки3
Реакции2
Комментарии0

Все посты

Связи