Кабинет
ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus 2009

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus 2009

ዳዕዋ ሰለፍያ በአርባ ምንጭ AMUጫሞ ካምፓስ ሃቅን ፍለጋ ከቁርዓንንና ከትክክለኛ ሃድስ በነዚያ ደጋግ ቀደምቶች ( በሰለፉነ–ሷሊሂን) አረዳድ ! "ከሃቅ በሗላ ጥሜት እንጅ ምን አለ! ? " ስለዚህ ሃቅን ብቻ ተከተል ! ማሳሰቢያ: –ለማንኛውም አስተያየትዎ ከታች ባለው ቦት ያስቀምጡልን ጀዛኩሙላህ ኸይር @JemalEndro33

Юзернейм
@daewaselefiyaarbaminch
Категория
Религия
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики1 893
Просмотров на пост, 7 дн.145−54,4% к пред. 7 дн.
ERR7,64 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
10 нояб. 2026 г.154
12 нояб. 2026 г.280
13 нояб. 2026 г.355
14 нояб. 2026 г.516
15 нояб. 2026 г.157
16 нояб. 2026 г.178
17 нояб. 2026 г.286
21 нояб. 2026 г.163
24 нояб. 2026 г.254
25 нояб. 2026 г.86
26 нояб. 2026 г.92

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01
    Просмотры516
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—
  2. 02
    Просмотры463
    Пересылки—
    Реакции6
    Комментарии—
  3. 03
    Просмотры451
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—
  4. 04

    ከዛሬው ደርስ የተወሰዴ ~ «ተውሒድ» (የአላህ አንድነት) እና ብቼኛ ተመላኪነትን በአጭሩ ይህ ርዕስ የመልዕክተኞችም ዋናው የተላኩበት አጀንዳ እንደሆነ በሚከተለው መልክ ተብራርቷል ። ​1. የተውሒድ ትርጉም (وَالْمَعْنَى...): ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የነብያት እና የመልእክተኞች ጥሪ ሁሉ ወደ አላህ ብቻ መገዛት እና ለእርሱ ምንም አጋር እንደሌለው ማመን እንደሆነ ይገልጻል። ከየትኛውም መልክተኛ ጋር አላህን ከሌላ አካል ጋር አብሮ ማምለክን የሚሰብክ አልነበረም። ​2. አመክንዮአዊ እና አዕምሯዊ ማሳያ (وَنَبَّهَ اللَّهُ...): አላህ የአጋሪዎችን (ሙሽሪኮችን) እምነት የሚያፈርስ አዕምሯዊ ማስረጃን ከቁርአን ጠቅሷል። በሱረቱ አል-አሕቃፍ አንቀጽ 4 ላይ ያለው «(መሐመድ ሆይ!) በሉ፦ እነዚያ ከአላህ ውጪ የምትገዟቸውን አጋሮቻችሁን አያችሁን? ከምድር ምንን እንደፈጠሩ አሳዩኝ፤ ወይስ በሰማያት ውስጥ ለእነርሱ ድርሻ አላቸውን? ከዚህ መጽሐፍ በፊት ያለን መጽሐፍ ወይም የቀረውን የዕውቀት ቅሪት (አስረጃ) አምጡልኝ፤ እውነተኞች ከሆናችሁ» የሚለውን ቃል በማስረጃነት ያቀርባል። ​3. የአምልኮ ውድቀት (فَهَذَا دَلِيلٌ عَقْلِيٌّ...): ይህ አንቀጽ ከአላህ ውጪ ያሉ አካላት ማናቸውንም ነገር ስላልፈጠሩ፣ በምንም ነገር ፍጥረት ላይ ድጋፍ ወይም ሽርክና ስለሌላቸው ከርሱ ውጪ የሚደረግ አምልኮ ሁሉ ከንቱ እና ውሸት መሆኑን የሚያሳይ ቁጭ ያለ አዕምሯዊ ማስረጃ መሆኑን ይገልጻል። ፈጣሪው አላህ ብቻ ከሆነ ታዲያ ሌሎችን ማምለክ ምን ፍቺ አለው? በማለት ይጠይቃል። ​4. የማስረጃ እጦት (ثُمَّ نَفَى اللَّهُ...): አላህ ከአጋሪዎች (ሙሽሪኮች) ጎን ሆኖ የሚሟገትላቸው ከወረዱ መጻሕፍትም ሆነ ከነብያት የተገኘ ምንም ዓይነት ትክክለኛ ማስተላለፊያ (ነቅል) ማስረጃ እንደሌለ አረጋግጧል። በመሆኑም ሙሽሪኮች በምንም መልኩ መከራከሪያ ወይም ማስተባበያ የላቸውም፤ በዚህም ምክንያት ለዘላለም በገሃነም እሳት ውስጥ ከሚኖሩት እንደሚሆኑ እና መመለሻቸውም ምንኛ የሰፋ መጥፎ መድረሻ እንደሆነ ይናገራል። ​5. የዚህ ጉዳይ አጽንኦት (وَمِمَّا تَقَدَّمَ...): ከቀረቡት ማብራሪያዎች በመነሳት ይህ የተውሒድ ጽንሰ-ሀሳብ ከግዴታዎች ሁሉ ቀዳሚው እና ከጉዳዮች ሁሉ ዋናው እንደሆነ፣ አላህ ከማንም ሰው ከእርሱ ውጪ ያለ ሃይማኖት ፈጽሞ እንደማይቀበለው በማጠቃለያው ይገልጻል። ከአልሙቅተቀዱ ሶሂሃ ኪታብ ከገፅ 19 በግርድፉ የተተረጎመ ህዳር 03/2019 E.E ወረኢሉ ፉርቃን መስጅድ 🎙 ከዛሬው ከመጝሪብ እስከ ኢንሻ ደርስ የተወሰዴ @Jemalendro33 https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/16581

    Текст
    Просмотры395
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—

Новые посты

#16598Текст
Просмотры67−72%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч34
4 ч67
  1. Через 1 час34
  2. Всего сейчас67
#16597Фото

#ለሁሉም_ጩኸት_መልስ_አትስጥ 🎙 ሸህ በርበሃሪ— አላህ ይዘንላቸው — እንዲህ አሉ፦ «አላህ ይዘንልህና አስተውል፤ ከዘመንህ ሰዎች ንግግሩን የሰማኸው ሁሉ — በተለይም — አትቸኩል፤ ጠይቀህ እና አስተውለህ እስክታረጋግጥ ድረስ በምንም ነገር አትግባ፦ ከነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ባልደረቦች ወይም ከዐሊሞች (ከምሁራን) መካከል በዚህ ነገር የተናገረ አለ ወይ? በዚያ ጉዳይ ላይ ከእነርሱ የተላለፈ አስተያየት ወይም ዘገባ ብታገኝ አጥብቀህ ያዘው፤ ከእነርሱ አትለፍ (በምንም አትለፈው)፤ በእነርሱ ላይም የራስህን ምርጫ አታስቀድም፤ አለበለዚያ በእሳት ውስጥ ትወድቃለህ።» ሸርሁ ሱና ገፅ:49 ከዚህ የሚወሰዴው ቁም ነገር 👉ጥንቃቄ እና ማረጋገጥ (ተሰቡት )፦ አዲስ ንግግር ወይም አድስ ጉዳይ ሲያጋጥም ሳይጣደፉ ቀድመው ያለፉ የነቢዩ ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ሶሃቦች እና የዑለሞችን አቋም መኖሩን ማጣራት እንደሚገባ ያስገነዝባል። 👉​በቀደምት ምሁራን አስተያየት መጽናት (እስቲቃማ )፦ የሰሃቦች ረድየላሁ ዓንሁም ወይም የዖለሞች ዘገባ ሲገኝ በዚያ መጽናትና ከእነርሱ አልፎ የራስን አስተያየት አለማስቀደም የስህተት መከላከያ መሆኑን ያመላክታል። 👉ሁልጊዜም ከኛ የግል አስተያየት ይልቅ የኦለሞች ተውጅሃት እንደሚቀደም ማንም የቀደመን በሌለበት ጉዳይ ላይ መግባት እንደሌለብን ያስጨብጣል አላሁ አዕለም ✍️ መልካም የዒባዳ ቀን ይሁንላችሁ 🤲 @highlight ህዳር17/2019 E.C @Jemalendro33 https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/16597

Открыть в Telegram
Просмотры116−51%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
5 ч85
8 ч116
  1. Через 6 часов85
  2. Всего сейчас116
#16596Текст
Просмотры86−64%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#16595Текст

«🔖ዒልም ማለት ተቅዋን ያላበሰ ነው። ተቅዋ የሌላቸው ሰዎች ኢልም ቢኖራቸውም እንኳን ጃሂሎች ናቸው ተቅዋ ያላቸው ሰዎች ኢልማቸው ያነሰ፣የቀለለ ቢሆኑም አሊሞች ናቸው !ምክንያት...... የኢልም አላማው ምንድን ነው «ተቅዋ » ስለሆነ !!» ምንጭ ኡስታዝ  @Ibnumunewor ~ ተቅዋ ማለት :-ተቅዋ (تقوى) በመሰረቱ የአረብኛ ቃል ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙ «ጥንቃቄ ማድረግ»፣ «መከላከል» ወይም «ራስን መጠበቅ» ማለት ነው። በእስልምና እና በዕለት ተዕለት የሕይወት ፍልስፍና ውስጥ ግን ከዚህም ሰፋ ያለ ጥልቅ ትርጉም አለው። ከነዚህም ውስጥ አላህን መፍራትና መጠንቀቅ: በግልጽም ሆነ በድብቅ፣ በብቸኝነትም ሆነ በሰዎች ፊት አላህ እንደሚያይና እንደሚቆጣጠር በማሰብ እርሱን ከማስቀየምና ከቅጣቱ ራስን መጠበቅ ነው። ​በአላህና በቅጣቱ መካከል መከላከያ ማበጀት: ብዙ ሊቃውንት ተቅዋን የሚገልጹት አንድ ሰው በእሾህ ወይም በጭቃ በተሞላ መንገድ ሲሄድ ልብሱን ሰብስቦና ተጠንቅቆ እንደሚራመድ ነው። የሰው ልጅም በዱንያ ሕይወት ውስጥ ከኃጢአትና ከጥፋት ራሱን በመጠበቅ ለራሱ መከላከያ የሚያበጅበት መንገድ ነው። ​ትዕዛዛትን መፈጸምና ክልከላዎችን መራቅ: አላህ ያዘዛቸውን መልካም ነገሮች በአቅም ልክ መፈጸም እና የከለከላቸውን መጥፎ ነገሮች መተው ነው። ​የልብ ንጽሕናና ራስን መመርመር: ባህሪን ማስተካከል፣ ትህትናን መላበስ፣ ሰዎችን ይቅር ማለት፣ ሐቀኛ መሆን እና ከራስ ጋር ታማኝ መሆንን ያጠቃልላል። ​ተቅዋ ከ«ዒልም» (እውቀት) ጋር ያለው ትስስር ​ቀደም ባለው ጥቅስ ላይ እንደተገለጸው የዒልም ዋና ዓላማው ተቅዋ ነው። ምክንያቱም፦ ​እውቀት ብቻውን ካለ ተቅዋ ባህሪን ወደ ትዕቢት፣ ወደ ውድድር ወይም ለግል ጥቅም ወደ ማዋል ሊያመራ ይችላል። ​የተቅዋ ባለቤት የሆነ ሰው ያለው እውቀት ትንሽ እንኳ ቢሆን በሕይወቱ ስለሚተገብረውና ስለሚጠነቀቅበት የእውቀቱን ፍሬ ያገኛል። ​በአጭሩ ተቅዋ ማለት እውቀትን ወደ መልካም ሥነ-ምግባር፣ ወደ ራስ ገዢነት እና ወደ ጥንቃቄ የምንቀይርበት የሕይወት መንገድ ነው። አላህ ኸእነሱ ከተቅዮች ያድርገን ✍️ መልካም የዒባዳ ቀን ይሁንላችሁ 🤲 ህዳር 15/2019 E.C @Jemalendro33 https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/16595

Открыть в Telegram
Просмотры254+6%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#16594Превью ссылки
Просмотры193−19%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#16593Превью ссылки

Переслано из Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

በአንዴ የተፈፀመ ሶስት ፍች እንደ አንድ ነው ወይስ እንደ ሶስት የሚቆጠረው = አቋም አንድ፦ እንደ ሶስት ነው የሚቆጠረው። ስለሆነም ሌላ ሰው አግብታ ካልተለያየች በስተቀር ሶስቴ የፈታት ሰው ሊመልስ አይፈቀድለትም። ይሄ የብዙሃን ምሁራን አቋም ነው። ማስረጃዎቻቸው ከፊሉ ''ሶሪሕ" አይደሉም። ከፊሉ ሶሒሕ አይደሉም። ፅሁፌን ለማሳጠር ስል አላሰፍራቸውም። መሞገት የሚፈልግ ከስር በአደብ ሃሳብ መለዋወጥ ይቻላል። አቋም ሁለት፦ በአንድ ቃልም ይሁም በተለያየ ቃል በአንድ ጊዜ የተፈፀመ ሶስት ፍቺ እንደ ሶስት ሳይሆን እንደ አንድ ነው የሚቆጠረው የሚል ነው። ማስረጃቸው፦ ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- "كَانَ الطَّلَاقُ عَلَى عَهْدِ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، وَأَبِي بَكْرٍ، وَسَنَتَيْنِ مِنْ خِلَافَةِ عُمَرَ، طَلَاقُ الثَّلَاثِ وَاحِدَةً، فَقَالَ عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ: إِنَّ النَّاسَ قَدِ اسْتَعْجَلُوا فِي أَمْرٍ قَدْ كَانَتْ لَهُمْ فِيهِ أَنَاةٌ، فَلَوْ ‌أَمْضَيْنَاهُ عَلَيْهِمْ، فَأَمْضَاهُ عَلَيْهِمْ " “በአላህ መልእክተኛ (ﷺ) ዘመን፣ በአቡበክርና ከዑመር ዘመንም ሁለት አመት ጊዜ (በአንዴ የተፈፀመ) ሶስት ፍቺ እንደ አንድ ነበር የሚቆጠረው። ዑመር ብኑል ኸጧብ፡ ‘ሰዎች ቀድሞ ፋታ በነበራቸው ነገር ላይ በርግጥም ቸኮሉ። ስለዚህ እሱኑ (አንዴ የተናገሩትን) ብናፀናባቸውስ?’ አሉ። ከዚያም አፀኑት።” [ሙስሊም፡ 1472] * ከዚህ ዘገባ ቀጥሎ ኢማም ሙስሊም እንዲህ የሚል አስከትለዋል፦ أَنَّ أَبَا الصَّهْبَاءِ، قَالَ لِابْنِ عَبَّاسٍ: أَتَعْلَمُ « أَنَّمَا كَانَتِ الثَّلَاثُ تُجْعَلُ وَاحِدَةً عَلَى عَهْدِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، وَأَبِي بَكْرٍ، وَثَلَاثًا مِنْ إِمَارَةِ عُمَرَ»؟ فَقَالَ ابْنُ عَبَّاسٍ: «نَعَمْ» “አቡ ሶህባእ ለኢብኑ ዐባስ ‘በነብዩ ዘመን፣ በአቡበብክርም እንዲሁ እና ከዑመርም ዘመነ ሹመት ውስጥ ሶስት አመት ያክል (በአንዴ የተፈፀመው) ሶስቱ ፍቺ አንድ ይደረግ እንደነበር ታውቃለህን?’ ሲሏቸው ‘አዎ’ ብለው መልሰዋል።” * አሁንም አልኢማም ሙስሊም ከዚህ ዘገባ ቀጥሎ እንዲህ የሚል አስከትለዋል፦ أَلَمْ يَكُنِ الطَّلَاقُ الثَّلَاثُ عَلَى عَهْدِ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، وَأَبِي بَكْرٍ وَاحِدَةً»؟ فَقَالَ: «قَدْ كَانَ ذَلِكَ، فَلَمَّا كَانَ فِي عَهْدِ عُمَرَ تَتَايَعَ النَّاسُ فِي الطَّلَاقِ، فَأَجَازَهُ عَلَيْهِمْ “ 'በአላህ መልእክተኛና በአቡበክር ዘመን ሶስቱ ፍቺ አንድ አልነበረምን?' በማለት አቡ ሶህባእ ኢብኑ ዐባስን ሲጠይቁ ‘እንደሱ ነበር። በዑመር ዘመነ ሰዎች ፍቺ ላይ በተቻኮሉ (ባበዙ) ጊዜ አፀኑባቸው’ አሉ።” አስተውሉ! ከዚህ ገለፃ የምንረዳው ዑመርም ለሆነ ፋይዳ ብለው ቢቀይሩም የሳቸው ውሳኔ ጊዜያዊ አስተያየት እንጂ ቋሚው ህግ እንዳልሆነ አነጋገራቸው ይጠቁማል። ስለዚህ እንደ ሶስት ይቆጠራል የሚለው ለሰዎች መቀጣጫና መማሪያ እንዲሆን ኋላ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ያወጁት እንጂ ነባር ህግ አይደለም ማለት ነው። ነባሩ ህግ ሶሒሕ ሙስሊም ውስጥ በግልፅ እንደሰፈረው መሀል ላይ መመለስ ሳይኖር በአንዴ ከተፈፀመ እንደ አንድ ይቆጠራል የሚለው ነው። ይሄ አቋም የኢብኑ ተይሚያ አቋም ነው። በዚህ የተነሳ "ኢጅማዕ ጥሷል" ተብለው ታስረው ወህኒ ቤት ውስጥ ነው የሞቱት። "ኢጅማዕ ጥሷል" የሚለው ክስ ከእውነት ያፈነገጠ ነው። ምክንያቱም፦ 1. "እንደ ሶስት ነው የሚቆጠረው" የሚለው ፈፅሞ ኢጅማዕ የለበትምና። ለዚህም የኢብኑ ሐጀርንና የነወዊይን ምስክርነት ማቅረብ ይቻላል። ኢብኑ ሐጀር እንደ ሶስት ሳይሆን እንደ አንድ ነው የሚቆጠረው ያሉ ምሁራንን ከዘረዘሩ በኋላ “እንዳየኸው ልዩነት በተጨባጭ ከመከሰቱ ጋር ኢብኑ ቲን እንደ ሶስት በመቆጠሩ ላይ ‘ልዩነት የለም’ ማለቱ የሚደንቅ ነው” ብለዋል። [ፈትሑል ባሪ፡ 9/363] ነወዊይም በጉዳዩ ላይ የተንፀባረቁ የተለያዩ ሀሳቦችን ባሰፈሩበት “እንደ አንድ ብቻ ነው የሚቆጠረው” ያሉትን ከመጥቀሳቸው ጋር “እንዲያውም ከነጭራሹ እንደ ፍቺም አይቆጠርም” የሚል ሀሳብ ከሐጃጅ ብኑ አርጧህ፣ ሙቃቲልና ሙሐመድ ብኑ ኢስሓቅ እንደተንፀባረቀ ጠቅሰዋል። [ሸርሑ ሙስሊም፡ 10/325] 2. ይሄ ''እንደ አንድ ነው የሚቆጠረው" የሚለው አቋም የዐልይ፣ የኢብኑ መስዑድ፣ የዐብዱረሕማን ብን ዐውፍ፣ የዙበይር፣ የሰዒድ ብኑል ሙሰይብ፣ የጣውስ፣ የዒክሪማ፣ የዐምር ብኑ ዲናር፣… የሙሐመድ ብኑ ኢስሓቅ፣ የኢብኑ ወዷሕ፣ የኢብኑ መኽለድ፣ ወዘተ ምርጫ ነው። እነዚህን ሁሉ ታላላቆች ያገለለ አቋም በምን ስሌት ነው እንደ ኢጅማዕ የሚቆጠረው? 3. ይሄ አቋም የዟሂሪያ መዝሀብ አቋምም ነው። ከአቡ ሐኒፋ፣ ከማሊክና ከአሕመድ ተከታዮችም ውስጥ የደገፉት በተጨባጭ አሉ። ስለዚህ ከቀደምቶቹም ከኋለኞቹም መሁራን የተጓዙበት ቀላል አይደሉም። ይህን ሁሉ ያላካተተ ኢጅማዕ ምን አይነት ኢጅማዕ ነው?! ይሄ ሁሉ ዑለማእ የተጓዙበትን አቋም ያስተጋባ ሰው እንዴት ኢጅማዕ ጥሰሃል ይባላል?! የሸውካኒይና የሶንዓኒይ አቋምም ይሄው ነው። ሸይኹል አልባኒይ ቀደም ብሎ በኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ ከተላለፈው "እንደ አንድ ነበር የሚቆጠረው'' ከሚለው ሐዲሥ ስር እንዲህ ይላሉ፡- “ይሄ መረጃ በአንዴ የተፈፀመ ሶስት ፍቺ እንደ አንድ እንደሚቆጠር ፅኑና አስተማማኝ ህግ ነው። ከነብዩ (ﷺ) ህልፈት በኋላም በአቡበክር አስተዳደርና በዑመር የመጀመሪያ ዘመን የተሰራበት ስለሆነ አልተሻረም። በዚያ ላይ ደግሞ ዑመር በኢጅቲሃዳቸው እንጂ በሌላ መረጃ አልተፃረሩትም። ለዚህም ነው መጀመሪያ ላይ ጥቂት ያመነቱት። ‘ሰዎች ተቻኮሉ’ እና ‘ብናፀናባቸውስ?’ የሚለው አነጋገራቸው ይህን ይጠቁማል። አንድ ዳኛ መረጃ ቢኖረው በዚህ መልኩ ሊጠይቅና ሊያመነታ ይፈቀድለታል’ንዴ? ደግሞም ‘ሰዎች ቸኮሉ’ ማለታቸው ቀድሞ ያልነበረ መቻኮል እንደተከሰተ ይጠቁማል። ለዚህም ነው ቅኑ ኸሊፋ በቅጣት መልክ ሶስቱንም ያፀኑባቸው። ከዚህ ሁሉ ጋር በአቡበክርና በዑመርም የመጀመሪያ ዘመን የነበረው በሙስሊሞች ኢጅማዕ የፀና ህግ ለዑመር ግላዊ እይታና ኢጅቲሃድ ሲባል ይተዋልን? እሳቸው ራሳቸው የአላህ መልእክተኛን (ﷺ) እና አቡበክርን ተከትለው በመጀመሪያ ዘመናቸው የሰሩበትን ትተን ኢጅቲሃዳቸውን እንወስዳለን?! በእውነት ይሄ በኢስላማዊ ፊቅህ ውስጥ ከተከሰቱ አስገራሚ ነገሮች ውስጥ ነው!! ምሁራን ሆይ! እባካችሁን ፍንትው ወዳለው ሱና ተመለሱ። በተለይ ደግሞ በዚህ አስደንጋጭ በሆነ መልኩ ፍቺ እንደጉድ ተንሰራፍቶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች አደጋ ባንዣበበባቸው ዘመን!!” [አሶሒሐህ፡ 3/272] የፈለገ ሙሉውን ይየው። በጣም ጠቃሚ ነው።

Открыть в Telegram
Просмотры172−28%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#16592Фото

Переслано из Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры124−48%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#16588Текст
Просмотры208−13%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—

Все посты

Связи