Account
ማርያም ድንግል maryam dngil tube21

ማርያም ድንግል maryam dngil tube21

https://youtube.com/@orthodox-i2l?si=W_azZ4XHUIxrA76C ዩቱብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ"ብበድልህም እንኳ አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው፡፡ እየተጓተትሁምቢሆን የምጓዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው" ለአስተያየት @OrthodoxsuggetionBot

Username
@orthodoxfilm_mezmur
Category
Religion
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers2,142
Avg views per post, 7d—last 7 days
ERR18.35%30-day average

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 8, 2026583
Nov 18, 2026203

Latest posts

#1347Text
Views203−48%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#1345Text
Views583+48%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#1344Text

እንኳን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤አደረሰን🙏 መላእክትም ነፍሱን በታላቅ ዝማሬ አሳርገዋታል ትውልዳቸው ግብጽ ንሒሳ ውስጥ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ 33 ዓመት በትዳር ሲቆዩ ልጅ ለማግኘት ሲሉ ሦስት ቀን ብቻ በሩካቤ ስጋ ቀዋውቀዋል፡፡ በመልአክ ብስራትም መጋቢት 29 ተጸንሰው ታኅሣሥ 29 በጌታችን ልደት ቀን ተወለዱ፡፡ ሕጻኑ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በተወለደበት ቅጽበት ቅድስት ሥላሴን አመሰገነ፤ የእናቱን ጡት ሳይጠባም ቅዱስ ገብርኤል ወሰደው፡፡ እግዚአብሔርም መልአኩን “ወደ እናቴ ወደ ማርያም ውሰደውና ትባርከው” አለው፡፡ ወስዶት እመቤታችንም ባረከችው፡፡ ከዚህም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሕፃኑን አባ ዘመደ ብርሃን የተባሉ አባት ላሉበት ገዳም ወስዶ ምግቡ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ነግሮ ሰጣቸው፡፡ አባ ዘመደ ብርሃንም ሕፃኑን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማረ አሳድጎ ዲቁና ሰጠው፡፡ እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስም ጸጋንና ሞገስን የተመላ ሥራው የተቃና ሆነ፡፡ አባ ዘመድ ብርሃንም እንደ ቅዱስ እንጦንስ አስኬማን ሰጠው፡፡ ከዚህ በኋላም አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቅስናን ተቀብለው በጾም በጸሎትና በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ እንደ ሐዋርያትም የተአምራትና የፈውስ ሀብት ተሰጣቸውና ድውያንን የሚፈውሱ፣ ሙታንን የሚያነሡ፣ አጋንንትን የሚያወጡ ሆኑ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዳግመኛ ተገልጦላቸው ወደ ሰማይ አሳረጋቸው፡፡ እግዚአብሔርም ከባረካቸው በኋላም ከሰው ተለይተው ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመር፡፡ ሰውነታቸውም ሁሉ በጠጉር ተሸፈነ፡፡ በፍጹም ተጋድሎም በቀንና በሌሊት የክርስቶስን መከራ እያሰቡ ስለ ኃጥአንም ጥፋት እንባቸውን እያፈሰሱ ይጸልዩ ነበር፡፡ በጸሎታቸውም ብዙ እልፍ ነፍሳትን አስምረዋል፡፡ በ300 ዓመታቸውም ከ60 አንበሶችና ከ60 ነብሮች ጋር ወደ ኢትዮጵያ ያመጣቸው ቅዱስ ገብርኤል ምድረ ከብድንና ዝቋላን አሳይቷቸዋል፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማርልኝ ብለው ለአንድ መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው ስጋቸው እስኪያልቅ ጸልየው  ጥቅምት 5 ቀን ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል፡፡ በሀገራችንም 262 ዓመታት በጸሎትና በትምህር እየቀዱሱዋት፣ አጋንንትን እያሳደዱ ኖረው በተወለዱ በ562 ዓመታቸው መጋቢት 5 ቀን ምድረ ከብድ ላይ አርፈዋል፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ነፍሳቸውን በታላቅ ዝማሬ አሳርገዋታል፡፡ የቅዱሳኑ በረከት እንዲድርብን ገዳማውያንን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡   ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

Open in Telegram
Views694+77%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#1343Text

የምስክርነት ቀን ይህችን ቀን ስለኛ ያለውን ፍቅር በመስቀል ሞት የገለጠ ፥ ጠላቶቹ ሳለን እዳችንን በደሙ መፍሰስ ያስቀረልን ፥ የተረሳን ስንሆን በስሙ ያከበረን ፥ የወደቅን ስንሆን በትንሳኤው ያስነሳን ቸሩ መድኃኔዓለም ስለእኛ ያደረገው ውለታው እንዴት ይታሰባል?? እንዴት ይነገራል?? ከዚህ የተነሳ ፈጣሪን አምላኬና መድኃኒቴ ማለት ኃይልና ብርታት ሲሆን በእርሱ በፈጣሪ ግን የማላፍርበት ልጄ መባል ትልቅ መመረጥና ቅድስና ነው። በሰው ዘንድ የተለዩ መባልን መርጠው ፈጣሪ ግን አላውቃችሁም የሚላቸው ግን እንዴት አይነት ምስኪኖች ናቸው?? ውበቴ ክርስቶስ ብለው የሚኖሩና ራሳቸውን ከዓለም ከሚገኝ እድፍ የሚጠብቁ እነርሱን ግን ኅሩያን ናቸው። በእርሱ ፊት የሚያደርጉትን የፍቅር አገልግሎትና ስርዓተ አምላኮ ከሰው ሸሽገው በትሕትና ራሳቸውን የሚገዙ እነርሱ የተመረጡ ናቸው። ውበታቸው ያላታለላቸው ፥ ማግኘታቸው ያስታበያቸው ፥ ማጣታቸውን ለክህደት ያላበቃቸውን ፥ የተሰጣቸውን መክሊት አትርፈውን ለጌታቸው እጥፍ አድርገው የሚመልሱ ንዑዳን ናቸው። ጸሎት የቅድስት አርሴማ አምላክ መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለበጎ ሥራ የሚተጋ ልብ ፥ አንተ ብቻ የሚያይ ዓይን ፥ የአንተን ቃል ብቻ የሚያዳምጥ ጆሮ ስጠኝ። በኃጢያት የጠቆረን ገፄንና የጎሰቆለውን ማንነቴን በቅዱስ መንፈስ አድስልኝና ከፊቴ ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንድሮጥ አትጋኝ !!

Open in Telegram
Views651+66%vs avg
Forwards—
Reactions8
Comments—
#1342Text

"....ሀብታምን ዕድለኛ ድሀን ደግሞ ዕድለ ቢስ ብለን መጥራት እንደሌለብን ከአልዓዛር እንማር፡፡እዉነቱን ለመናገር ግን ባለጸጋዉ ጥቂት ንብረቶችን የሚፈልገው እንጂ ብዙ ንብረቶችን የሰበሰበው አይደለም፡፡ ድሀ የሚባለው ደግሞ ምንም ንብረት ሳይኖረዉ ብዙ ፍላጎቶች ያለዉ ነዉ፡፡ የሀብትና የድህነት መገለጫዉም ይህ እንደሆነ ልናዉቅ ይገባናል፡፡ ለብዙ ነገሮች የሚስገበገብና የሁሉንም ሀብት በእጁ ያስገባዉን ሰዉ ብትመለከቱ እንዲህ ዓይነቱ ሰዉ የመጨረሻው ደሀ ሰዉ መሆኑን እወቁ፡፡ በአንጻሩ ምንም ባያገኝ እንኳ ጥቂት ፍላጎቶች ያሉትን ሰዉ ብትመለከቱ እንዲህ ያለዉን ሰዉ የባለጸጎች ሁሉ ባለጸጋ አድርጋችሁ ቁጠሩት፡፡ ድህነትንና ሀብታምነትን በአንድ ሰዉ ዉጫዊ መገለጫ መጠን ሳይሆን እንደ አዕምሯችን ሚዛናዊነት ማስቀመጥ ልማዳችን አድርገነዋል፡፡ በቅምጥልነት ቢደሰትና በወንዞችና በምንጮች አጠገብ ቢኖር እንኳ ሁልጊዜ የሚጠማን ሰዉ ጤነኛ ነዉ ብለን አንጠራዉም፡፡ በባለጸጎችም ዘንድ ያለዉ ልክ እንደዚህ ነዉ፡፡ የሌሎች ሰዎችን ንብረት ለማግኘት ሁልጊዜ የሚጓጉና የሚጠሙ ሰዎችን ጤነኞች ብለን አንጠራቸዉ፡፡ እንደዚህ ያሉ ሰዎች የተትረፈረፈ ነገር ቢያገኙ እንኳ ይረካሉ ብለን አንዳናስብ፡፡ አንድ ሰዉ የሰዎችን ሁሉ ንብረት ለራሱ አድርጎ እየወሰደ የራሱን ስስት መቆጣጠር ካልቻለ እንዴት ባለጸጋ ሊሆን ይችላል? ነገር ግን ዓይኖቻቸዉን ከሌሎች ንብረት ላይ ሳይጥሉ ባላቸዉ ረክተዉና የራሳቸው በሆነ ንብረት ደስ ተሰኝተዉ የሚኖሩት እነዚህ ሰዎች የድሆች ሁሉ ድሀ ቢሆኑም እንኳ የባለጸጋዎች ሁሉ ባለጸጎች ናቸዉ፡፡ በሌሎች ንብረት ላይ ምንም ዓይነት ፍላጎት የሌለውና ራሱን በመቻሉ ደስተኛ የሆነዉም ሰዉ የባለጸጎች ሁሉ ባለጸጋ ነዉ፡፡" (ሀብታምና ድሀ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገፅ 27-28 ➛ በአያሌው ዘኢየሱስ የተተረጎመ)

Open in Telegram
Views500+27%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1341Text

#ወርኃ_ፆመ_ፅጌ / #የፅጌ_ፆም #እንኳን_አደረሰን ፡አደረሳችሁ !! የእመቤታችን ስደት በጾም በጸሎት የምታስቡ ወይም የምታሳልፉ የእመቤታችን የድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁ ለጽጌ ጾም ካላቸው ፍቅር የተነሳ አንዳንድ ምዕመናን ጽጌ ጾም መቼ ነው የሚገባው እያሉ የሚጠይቁ ስላሉ ከወዲሁ ለማስታወስ ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያለው አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጸጌ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡ የፍስክ መብላት የሚቻለው እስከ መስከረም 25 ነው በዛውም ዘመነ ክረምት የሚያበቃውም መስከረም 25 ነው ዘመነ መኸር ደግሞ ከመስከረም 26 እስከ ታሕሳስ 25 ነው ••• ስደት ሲነሳ ሐዋርያት በወንጌል የተነሳ ተሰደዋል፣ ሞተዋል፡፡ ቅዱሳን ስለ ክርስቶስ ፍቅር በየገዳሙ ተሰደዋል፡፡ እነዚህና ሌሎችም ስለ ስሙና በስሙ ምክንያት ሲሰደዱ የእመቤታችን ስደት ግን ከእነሱ ልዩ ነው፡፡ ተወዳጅ ልጅዋን ቅዱስ አማኑኤልን ይዛ ነው የተሰደደችው፡፡ ቅዱሳን በአምላካቸው ስም ሲሰደዱ እመቤታችን ደግሞ አምላክን ይዛ ተሰዳለች፡፡ . ስድት የማይገባት የእኛ እናት ወላዲተ አምላክ የእኛን የኃጢአተኞችን ፈንታ ተሰደደች፡፡ እመቤታችን በመሰደድዋ ከገነት እንድንሰደድ ያደረገን ሰይጣንን አሳደደችው፡፡ እመቤታችን በስደትዋ ወቅት በቀላሉ የማይነገር ከሕሊና በላይና ልብ ሰባሪ መከራ ተቀብላለች፡፡ በዚህም ቅድስተ ቅዱሳን ፣ ንፅሂተ ንፁሃን ወላዲተ አምላክ ክብር ምስጋና ይገባታል። . በፅጌ ፆም ግርም የሚለኝ ጾም ሲባል መጾሙ ላይ እንጨቃጨቃለን መብላቱ ላይ ግን እንስማማለን፡፡ ይህ የሚሆነው ለነፍሳችን ሳይሆን ለሥጋችን ስለምናደላ ነው፡፡ ለስንት ዘመን ስንበላ የከረምነው ዓሳ ‹‹ይበላል አይበላም›› እያልን የምንጨቃጨቀው የመጾም ሳይሆን የመብላት ፍላጎታችንን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡  ለዚህም ነው የፅጌ ፆምን አንዴ የመነኮሳት አንዴ የቄሶች ነው እያልን የምንጨቃጨቀው። . ጾም አንዱና ዋኛው የጸጋ መንገድ ነው፡፡ የትኛውንም ገድለ ቅዱሳን ብንመለከት አባቶቻቸን በልተው ሳይሆን ጾመው ነው የበቁት የተሰወሩት፡፡ ለዚህም ነው ጾሞ እንጂ በልቶ የበቃ ቅዱስ እስከ ዛሬ ያልተገኘው፡፡ ስለዚህ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ከመሄዳችን በተጨማሪ የምንችለውን ያህል እየፆምን ብንማፀናት እናተርፋለን እንጂ አናጎድልም። . ዛሬ እንኳን በልተን፣ጾም ትተን ቀርቶ ጾመንም ጸልየንም ሰይጣን ከእኛ አልርቅ፣ፈተናችን አልላቀቅ ብሎናል፡፡ . ወገኖቼ እውነት እንነጋገር ከተባለ ጾመ ነነዌ የአዋጅ ጾም ነው፡፡ ጾመ ነነዌን የምንጾመው የታላቅዋ የነነዌ ሕዝብ ጾመው የእግዚብሔር መቅሰፍት ስለራቀላቸው እኛ እንደ እነሱ የእግዚአብሔር ቁጣ እንዲርቅልን እንጾማለን፡፡ ግን ለነነዌ ሕዝብ ከተደረገላቸው ነገር በላይ ለእኛ በእመቤታችን በኩል የተደረገልን የመዳናችን ምስጢር እና ውለታ አይበልጥምን? በተለይ ለእኛ ለኢትዮጲያውያን! ታዳ ምናለበት ፍቅሯን እና ውለታዋን እያሰብን ብንፆም። . እንደምታውቁት መከራ ወደ ምድር የመጣው በጾም ሳይሆን በመብል ነው፡፡ የቻልን በርትተን ብንጾም ብሎም ሱባኤ ገብተን ብንጠይቃት መልስ አናጣም፡፡ ካልቻልን ግን አለመቻላችንን የመነኮሳት እና የቄሶች ነው በሚል መደለያ እራሳችንንም ሌሎችንም አንሸውድ። አንዳነድ ሰነፎች ‹‹ፅጌ ጾምን ያልጾመ ችግር የለውም ባለመጾሙ አይኮነንም ›› ይላሉ፡፡ በእርግጥ ልክ ነው፡፡ ግን በእመቤታችን የፍቅር ሚዛን ላይ ተመዝኖ እንደ ገለባ መቅለል እንዳለ መርሳት የለብንም፡፡ . በነገራችን ላይ እንኳን የፅጌ ፆምን ከአብይ ፆም እና ከፍልሰታ ፆም ውጭ ያሉትን አፅዋማት እንደ ፈቃድ ፆም የሚቆጥሩ ሰዎችም አጋጥመውኛል። ይህ ግን ፍፁም ስህተት ነው። ለዚህም ነው ታላቁ መፅሐፍ ሲያጠቃልለው በ1ኛ ቆሮ 6 :12 - 13 ‹‹መብል ለሆድ ነው ሆድም ለመብል ነው ፣ እግዚአብሔር ግን ይህንንም ያንንም ያጠፋቸዋል›› ያለው። . በጽጌ ጾም  ከመስከረም 26 እስከ ሕዳር 6 ባሉት  ቀናት በየቤተክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባቦች፣ የሚዘመሩት መዝሙሮች፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐት እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋክብት ምድር በጽጌያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡ ወርኃ ጽጌ ለሚከናወነው መንፈሰዊ አገልግሎት መነሻው "መልአኩ ሕፃኑንና እናቱን ወደ ግብፅ ይዘሃቸው ሽሽ፣ የሕፃኑን ነፍስ ሊገድሉት ይፈልጋሉና" ሲል ለዮሴፍ በሕልሙ በነገረው መሠረተ ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብፅ መሰደዱና እመቤታችንና ሕፃኑ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ /ራእይ.12፣6/ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት የመመለሳቸው መታሰቢያ ነው፡፡ /ማቴ 2፣13-23፣ ት.ኢሳ.19፣1፣ እንባቆም 3፣6-7፣ መዝ.83፣3/፡፡ ይህንንም በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡ አባ ጽጌ ብርሃን ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ሁሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመለሰ በሚያስረዳው ድርሰታቸው እንዲህ በማለት ገልጸውለታል፡፡ "አፈወ ሮማን ማርያም ጽጌ ቀናንሞ ወአበሜ፣ እስከ ተጸምሐየየ በጾም ዘመልክዕኪ ጊዜ ድክታሜ፣ እምተመነይኩ ተሳትፎ ከመ አኅትኪ ሰሎሜ፣ ወፍሥሓኪ ዘአልቦ ፍጻሜ"፡፡ ሲተረጎምም የሮማን ሽቱ የቀናንሞ አበባ የምትሆኚ ማርያም ሆይ፣ በርሃብ በጾም አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪጠወልግ ድረስ በስደትና በልቅሶ የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እኅትሽ እንደ ሰሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህ ፍጻሜ የሌለውን ደስታሽን እሳተፍ ነበር፡፡ እንዲሁም አባ አርክ ሥሉስ በስደቷ የደረሰባትን ኀዘን ፣ ልቅሶና ሰቆቃ አስመልክተው በደረሱት "ሰቆቃወ ድንግል" በሚለው ድርሰታቸው እንዲህ አሉ፣ ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር” የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝክር ነው፡፡ በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጠዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ከማኅሌት ጽጌና ከሰቆቃው ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው፡፡ ዝክሩም፣ በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ እየተረሳ ቢመጣም፣ ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢ ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባስበው በእመቤታችን ስም የሚዘክሩት ነው፡፡ ዐቅመ ደካሞች፣ ድሆችና መንገደኞች ተጠርተው በእመቤታችን ስም እንዲበሉና እንዲጠጡ ይደረጋል፡፡ ይህም ትውፊት እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ኢትዮጵያውያን አባቶችና እናቶች ያደረጉላትን መስተንግዶ ለማሰብ ነው፡፡ ዘመነ ጽጌ ለሐገራችን ለሕዝባችን ለቤተክርስቲያን ለዓለም ሁሉ ሰላም የሚወርድበት አንድነታችን ፍቅራችን የሚመለስበት ይህ ክፉ ጊዜ የሚያበቃበት ያድርግልን አሜን

Open in Telegram
Views538+37%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1340Text
Views340−13%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1339Text
Views386−2%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1338Text

ተግሣጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም "በባልንጀራህ ላይ የምትቆጣ ከሆነ የአንተ ቁጣ በእግዚአብሔር ላይ ነው፡፡ በባልንጀራህ ላይ ቂምን በልብህ የያዝክ ከሆነ ቂምህ በጌታህ ላይ ነው፡፡ ባልንጀራህን በከንቱ የምትቆጣው ከሆነ ኃጢአት በአንተ ላይ ይሠለጥንብሃል፡፡ ነገር ግን ልብህን የፍቅር ማደሪያ ካደረግኸው በምድር ላይ አንዳች ጠላት አይኖርብህም፡፡ አንተ እውነተኛ የሰላም ሰው ከሆንክ በሌላ ሰው ላይ የክፋት ወጥመድን አትዘረጋም፡፡ አንተ በእውነት ጻድቅ ከሆንክ በባልንጀራህ ላይ ከፋትን አታደርግም። ነገር ግን ቁጣን የምታፈቅራት ከሆነ በኃጢአትህ ላይ ተቆጣ፡፡ ይህ ተገቢ የሆነ ቁጣ ነውና፡፡ ጦር መግጠም ከፈለግህ እነሆ ሰይጣን ጠላትህ፤ በእርሱ ላይ ጦርነትህን ከፈት፡፡ ማመፅም ካማረህ፣ ለመርከስህ ምክንያት በሆኑ አጋንንት ላይ አምፅ። በእግዚአብሔር አርዓያ የተፈጠረውን የምትሰድብ ከሆነ የነፍሰ ገዳዩ እጣ ፈንታ ይደርስብሃል፡፡ በሰው ላይ በአመፃ የምትነሣሣ ከሆነ በእግዚአብሔር ላይ እንደተነሣሣህ ቁጥር ነው፡፡ ለባልንጀራህ አክብሮትን የቸርከው ከሆነ እነሆ እግዚአብሔር አከበረህ፡፡ ነገር ግን ባልንጀራህን የምታዋርድ ከሆነ የባልጀራህ ቁጣ በአንተ ላይ እንዲነሣሣ እወቅ፡፡ “እግዚአብሔር አምላክህን፣ በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኃይልህ (እንደችሎታህ መጠን) ውደድ” (ዘዳግ.6፥4-6) የሚለው ሕግ እርሱ የመጀመሪያው ሕግ ነው። እግዚአብሔርንም ስለማፍቀርህ ምልክቱ ባልጀራህን እንደራስህ መውደድህ ነው፡፡ ነገር ግን ባልንጀራህን የምትጠላው ከሆነ የአንተ ጥላቻ በእግዚአብሔር ላይ ይሆናል፡፡ ከባልንጀራህ ጋር በጠብ እየኖርህ በእግዚአብሔር ፊት ለጸሎት የምትቆም ከሆነ፣ እርሱን እንደመሳደብ ይቆጠርብሃል፡፡ በከንቱ ቃላትን እያበዛህ እንደሆነ የገዛ ሕሊናህ ይመሰክርብሃል፡፡ ሕሊናህም ከጸሎትህ አንዳች ፍሬ እንደማታገኝ ያስታውቅሃል፡፡ አምላከህ ክርስቶስ ስለገዳዮቹ በመስቀሉ ላይ ሳለ ይቅርታን ለመነ፤ እንዴት አንተ ፍጥረትህ ከትቢያ የሆነ ቁጣን በፈቃድህ በራስህ ላይ ታቀጣጥላለህ? በወንድምህ ላይ ቂምን ይዘህ ሳለ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ዘንድ ተወዳጅ የሚሆን ይመስልሃልን? በአንተ ምክንያት ከአንተ ጋር ያለ፣ ነገር ግን በኃጢአትህ ተባባሪ ያልሆነው ሰው ድንኳን መተላለፍህ ያገኘዋል፡፡ በአንተ ምክንያትም ጸሎቱ አይሰማለትም። መራርነትን ከሰውነትህ አርቅ ከዛም ጸሎትህን አቅርብ፡፡ ባልንጀራህ በቁጣ ውስጥ ከሆነ፣ ምንም ቁጣው በአንተ ላይ ባይሆን፣ ቁጣን ከሰውነቱ ያርቀው ዘንድ እርዳው፤ ምክንያቱም በሰውነቱ ርኩሰት ይነግሥበታልና፡፡ አንተ መንፈሳዊ ተፈጥሮ አለህ፡፡ ነፍስህም የእግዚአብሔር አርዓያና አምሳል ናት፡፡ እናም ከሰው ሁሉ ጋር በፍቅር በመኖር የእግዚአብሔር አርዓያ የሆነችውን ነፍስህን አክብራት፡፡ በምትኖርባቸው ዘመኖችህ ሁሉ በተቻለህ መጠን ሰውነትህን ከቁጣ ጠብቅ፡፡ ያለበለዚያ አንተን ወደ ሲአል ታወርድሃለች፤ ጎዳናዎቿም ወደ ገሃነም የሚያመሩ ናቸው፡፡ እናም ቁጣን በልብህ አታኑራት፡፡ መራርነትንም በነፍስህ አታሳድር፡፡ በነፍሰህ ላይ አንዳች ሥልጣን የለህምና ነፍስህን መልካም በማድረግ ጠብቃት፡፡" (ስብከት ወተግሣጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም ገጽ ሶርያዊ 66-67 - በመምህር ሽመልስ መርጊያ የተተረጎመ)

Open in Telegram
Views420+7%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#1337Text

ከዓለማዊ ሕይወት የተመለስን ብዙዎች  አዘውትረን ከሚያስጨንቀን ነገር አንዱ "እውነት እግዚአብሔር ኃጢያቴን ዐይቶ ከሕዝቡ ነጥሎ ይለየኝ ይሆንን ?? ለርስቱስ ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ጋርስ ይደምረኛልን ??" የሚል እንደሆነ ግልፅ ነው። እንደዚህ አይነቱ ስሜት ቅዱስ ጴጥሮስ እንኳን በአንድ ወቅት ተሰምቶት ነበር ሉቃ ፭ ፥ ፰ ። ይህ አይነቱ ፍርሃት ግን ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚቀዳና የሚፈስ አይደለም። በእርግጥ በማቴ ፳፪ ፥ ፪ - ፲፬ ላይ አንድ ንጉስ ለልጁ ሰርግን ባደረገ ግዜ ለልጁ ሰርግ የማይመጥን ልብስን የለበሰ ሰው "ወዳጄ ሆይ የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ? አለው " በማለት ጠይቅ መልስ ሲያጣ ከሰርጉ ድግስ መሃከል ከደስታው ለይቶ ወደ ውጪ ጨለማ ወዳለበት ስፍራ እንደጣለው ተጽፎ እናነባለን  !! ይህ ግን የተነገረው በፍርድ ግዜ ሃይማኖት ኖሯቸው ምግባር ለጎደላቸው ከንጉሱ ክርስቶስ ግብዣ ከቅዱስ ስጋውና ከክቡር ደሙ እንዲበሉ ፥  እንዲጠጡ ቢጋበዙም ንስሐ ሳይገቡ የሞቱ ኃጥአን ምሳሌ እንጂ በምድር ላለን ኃጥአን ምሳሌ አይደለም ። እውነተኛው እረኛ ክርስቶስ "ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ" አለ እንጂ "ከሌላ ቦታ መጥተው የተቀላቀሉ ሌሎች በጎች በበረቴ ገብተዋል አላለም" ዮሐ ፲ ፥ ፲፪ ።" ስለ እኛ ወደ ቅድስት በረቱ መመለስ ጌታ በጠፋው በግ ፣ በጠፋችው ድሪምና በጠፋው ልጅ ታሪክ መስሎ የእኛን ወደ እርሱ መመለስ እንደሚጠብቅ አስተምሮናል ። እርሱ የተገፋትን የሚቀበል ርህሩህ ፣ የተጨቆኑትን ነፃ የሚያወጣ አቸናፊ ፣ የታመሙትን የሚፈውስ መድኃኒት ፣ የተራቡትን የሚያጠግብ እንጀራ ፣ የተጠሙትን የሚያረካ ምንጭ ነውና እንዴት ብሎ ወደ እርሱን የመጡትን እንዴት ተነሳህያን ያስወጣቸዋል ?? በዕለተ አርብ እንኳን ያን ሁሉ መከራ እየተቀበለ ሃዘንተኞቹን ፥ የሚያለቅሱትን ቸል ሳይል "ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ " ብሎ በቃሉ አፅናንቷል። በሌላ ቦታ ደግሞ በመልካም እርሻ መካከል እንክርዳድ በቅሎ በተገኘ ግዜ"ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ አለ።" ማቴ ፲፫ ፥ ፴ እንጂ ወዲያው ይነቀሉ አላለም ስለሆነ ምንም አይነት እንክርዳድ የመሰለ ሕይወት ቢኖረን መከር የተባለ ሞት ወይም  ዳግም ምጽአት መቶ አጫጆች መላእክት ወደ ልዑል እግዚአብሔር እስኪወስዱን ድረስ ዘለላ ባላቸው ስንዴ በተመሰሉ ጻድቃን ጋራ በእርሻው በአባታችን ቤት እንኖራለና በተሰጠን እድሜ የሚያጸድቀንን ፍሬ እናፍራ !! ማቴ ፫ ፥ ፲ "ቤተክርስቲያንን አየኋት ፥ አወኳት ፥ ወደድኳት"

Open in Telegram
Views463+18%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—

All posts

Connections