Account
ፍሬ ሃይማኖት

ፍሬ ሃይማኖት

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአ/አ ሐገረ ሥብከት የመ/ደ/ገ/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እና ሥርዓት የጠበቁ መዝሙሮች እና ወረቦች ግጥማቸው ከነዜማ የሚገኝበት ቻናል ነው፡፡ ® ለማናኛውም ሃሳብ አስተያየት ጥያቄና ጥቆማ @Frehaymanoteebot

Username
@frehaymanote
Category
Religion
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers1,900
Avg views per post, 7d284last 7 days
ERR14.95%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 21, 2026409
Nov 24, 2026315
Nov 25, 2026255
Nov 26, 2026122

Most viewed this month

  1. 01
    Views453
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—
  2. 02

    No text

    Photo
    Views365
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—
  3. 03

    ጾመ ነቢያት፤ ተስፋውን ማሰብ፣ ለበዓሉ መዘጋጀት 🕯 ዛሬ ዓለማችን በፍጥነት ትንቀሳቀሳለች፤ ሁሉም ነገር በቅጽበት ይከወናል፡፡ በዚህ ሁሉም ነገር በቅጽበት በሚለዋወጥበት ዓለም፣ አንድን ነገር ይሆናል ብሎ በተስፋ መጠበቅ በዘመናችን የሚደገፍ ነገር አይደለም፡፡ ለክርስቲያኖች ግን በተስፋና በትዕግሥት መጠበቅ የሕይወታችን ዘይቤ ነው፡፡ ይህን ደግሞ ጾመ ነቢያት የበለጠ አጉልቶ ያሳየናል። ምክንያቱም ጾሙ የመጠበቅ እና የማግኘት ስለሆነ፡፡ ጾመ ነቢያት ቆም ብለን የምናስብበትና ልባችንን የምናዘጋጅበት ወቅት ነው፡፡ የነቢያት ተስፋ ተፈጽሟል፤ ክርስቶስ መጥቷል፤ ታዲያ ለምን እንጾማለን? ቅዱሳን ነቢያት ለብዙ ዘመናት የመድኃኒቱን መምጣት ተስፋ አድርገው በጾምና በጸሎት ጠብቀዋል፡፡ “ከሰማይ ይወርዳል፤ ከድንግል ይወለዳል፤ ሰውን ያድናል” የሚለው ተስፋ ለአዳም ተሰጥቶ ነበር፤ ያ ተስፋ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተፈጽሟል፡፡ ዛሬ እኛ የምንጾመው ክርስቶስ እንዳልመጣ ሆነን አይደለም፡፡ በጾማችን ነቢያት የጠበቁትንና የጾሙትን እናስባለን፤ በዚህም ለነፍስና ለሥጋ በረከት እናገኛለን፡፡ ጾማችን የምስጋና፣ የመታሰቢያና የዝግጅት ጾም ነው፡፡ ጾሙ ሦስት ትርጕም አለው፡- 1. ማሰብ፡- የተስፋውን ረጅም ጉዞና የተስፋውን ፍጻሜ እናስታውሳለን፡፡ በዚህም ልባችን በምስጋና ይሞላል፡፡ 2. መዘጋጀት፡- የጾሙ ፍጻሜ የጌታችን የልደት በዓል ነው፡፡ ጾሙ በንስሓናና በንጽሕና ለበዓሉ እንድንዘጋጅ ያደርገናል፡፡ 3. በትጋት መኖር፡- ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን ዳግም መምጣት በናፍቆት ትጠብቃለች፡፡ ስለዚህ ጾሙ ዘወትር በንቃት መኖርን ያስተምረናል፡፡ የጾሙ ጊዜና ሰንበታት ጾሙ ከኅዳር 15 እስከ ታኅሣሥ 28 ድረስ ይዘልቃል (በዘመነ ዮሐንስ ደግሞ እስከ ታኅሣሥ 27)፡፡ በዚህ ወቅት ሦስት ሰንበታት ይታሰባሉ፡- • ስብከት (ከታኅሣሥ 7 እስከ 13)፡- ነቢያት ስለ ክርስቶስ መምጣት የሰበኩት ይታሰባል፡፡ • ብርሃን (ከታኅሣሥ 14 እስከ 20)፡- ክርስቶስ እውነተኛ የዓለም ብርሃን መሆኑ ይሰበካል፡፡ • ኖላዊ (ከታኅሣሥ 21 እስከ 27)፡- ክርስቶስ መልካም እረኛና ጠባቂያችን መሆኑ ይታሰባል፡፡ ጾማችን እንዴት ይሁን? • 📱 ትኩረታችንን ከሚወስዱ ነገሮች ራሳችንን ገተን ጊዜያችንን ለጸሎት እናድርግ፡፡ • 🤝 የተጣላነውን ይቅር እንበል፤ ይቅርታም እንጠይቅ፡፡ • 💛 በጾም የተውነውን ቁርሳችንን ለተቸገረ እናካፍል፡፡ • 📖 በየቀኑ አንድ የመዝሙረ ዳዊት ክፍል እናንብብ፡፡ • ⛪️ ትምህርተ ወንጌልን ለመስማት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሒድ፡፡ • ⛪️ ቅዳሴ እናስቀድስ፡፡ • ⛪️ ከምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን እንሳተፍ፡፡ መደምደሚያ ነቢያት ጠበቁ፤ ተስፋቸውም ተፈጸመ፡፡ እኛ ደግሞ ያንን ተስፋ እያሰብን፣ ልባችንን እያዘጋጀን የልደቱን ብርሃን በደስታ እንቀበላለን፡፡ እግዚአብሔር ይህንን ጾም በበረከት እንድናሳልፍ ይርዳን፤ ለሀገራችን ሰላምን የሚሰጥበት ያድርግልን፡፡ አሜን፡፡

    Text
    Views315
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—
  4. 04

    No text

    Photo
    Views282
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—

Latest posts

#8966Text

.       ዝክረ ተክለ ጻድቅ(ዳዊት አየለ) በደረጀ እሸቴ(ወልደ ሥላሴ) "የዘመኔን አነስተኛነት ንገረኝ በዘመኔ እኩሌታ አትውሰደኝ ዓመቶችህ  ለልጅ ልጅ ናቸው።"  መዝ. 101 ፥23-24 በአንድ ወቅት  በሕይወት ለሌለ ለአንድ አንጋፋ የአገራችን የኪነ ጥበብ ሠው በተዘጋጀ  የመታሰቢያ ዝግጅት ላይ የተጋበዙት ታዋቂው የማስታወቂያ  ባለሙያ  ሰው ጋሽ ውብ እሸት ወርቅ ዓለማሁ(ነፍስ ኄር) እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው "የሠው ልጅ የጋማ ከብት አይደለም።ሞተ ተብሎ የትም አይጣልም።"  ከትልቅ ሰው የሚጠበቅ ዘመን ተሻጋሪ አባባል። እኔም እላለሁ  ሰው ስለሞተ ብቻ  መረሳት የለበትም።በሠራው ደግም ይሁን ክፉ ሥራ ሲዘከር(ሲታወስ) ይኖራል። ቅዱሳት መጻሕፍትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም የሚያረጋግጡት ይህንኑ ነው እንጂ አንዳንድ አላዋቂዋች እንደሚናገሩት እንዲህ መዋተታችን ሥራ ፈቶች ሆነን እንዳይደለ ልብ ይባልልን።                       እንቀጥል ዕለተ እሁድ ጥር  10 ቀን 2007ዓ.ም  በበዓለ ጥምቀቱ ዋዜማ(በከተራው  ዕለት) ነው።  ሠርክ ሰዓት አካባቢ ታቦታተ ሕጉን በክብር አጅበን ወደ ባሕረ ጥምቀት ስንወርድ በአገልግሎት ይተጉ ከነበሩ ወጣት የሰ/ት/ቤታችን አባላት መኻል አንደኛው በብሩህ ገጽ (በፈገግታ  ተሞልቶ)  በትህትናና በአክብሮት ወደ እኔ ዘንድ ቀረበ። ልጁን በመልክ እንጂ በስም አላውቀውም።እንዲህም አለኝ "እኔ እኮ የካሣሁን አየለ ወንድም ነኝ.......አንተ የፈረምክበት የምሥክር  ወረቀት ከቤታችን ይገኛል" አለኝ እየተሽቆጠቆጠ። ካሣሁን አየለ??? ዓመታቱ  ወደ ኋላ ዘለግ ቢሉም ወንድሙን ማስታወስ ብዙም አላዳገተኝም።በ1992ዓ.ም ህጻናት ክፍል ካስተማርኳቸውና በጣም ከማቀርባቸው(ልጆቼ  ከምላቸው)  ህጻናት አንደኛው ነው ወንድሙ ካሣሁን። እያናገረኝ  ያለው ወጣት ታናሽ ወንድሙ  ሲሆን ዳዊት አየለ በስመ ጥምቀቱ ተክለ ጻድቅ ይባላል። ካናገረኝ በኋላ  በአገልግሎት መባከኑን ቀጠለ።የታላቅና የታናሽ  ወንድማማችነታችን ከዚያች ቅጽበት  ጀምሮ ተጠናክሮ ቀጠለ። ሰንበት ት/ቤት ለጉባኤም ሆነ ለአገልግሎት ስሄድ ባገኘኝ ቁጥር ከተቀመጠበት በመነሳት ከቆመበት ሸብረክ  በማለት በፍጹም ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ሰላም ይለኛል። እኔን ብቻ ግን አይደለም ሁሉንም ነው። ኃብተ ትህትናና ፍቅረ ቢጽ ተችሮታልና። ይህ መልካም ወጣት ከዚያ በኋላ በዚች ከንቱ ምድር የቆየው ለአጭር ጊዜ(ለአንድ ዓመት ከአስር ወራት ብቻ ነው።) ዕለተ አርብ ህዳር 16 ቀን 2009ዓ.ም ድንገት የተሰማው ዜና(ወሬ) ልብን በኃዘን ሰይፍ ለሁለት ክፍል የሚያደርግ ነበር። ትሁቱ፣ሽቁጥቁጡ፣ሰው አክባሪውና ትጉሁ አገልጋይ ዳዊት አየለ (ወልደ ጻድቅ) በዚያች ጥቁር ዕለት ይህችን ዓለም በሞተ ሥጋ ተሰናበታት። የተወለደው ደብረ ገነት በተተከለ፤ ፍሬ ሃይማኖትም በተመሠረተች በቀጣዩ ዓመት ሚያዝያ 26  ቀን 1986 ዓ.ም ሲሆን በዚች የኮንትራት ዓለምም የቆየው ለ23 ዓመታት ብቻ(ያውም አልሞላም) ነው።   እሁድ ህዳር 18 ቀን 2009ዓ.ም በወቅቱ የካቴድራሉ አስተዳዳሪ የነበሩት መልአከ ብርሃናት ቆሞስ አባ ሄኖክ ተክለ ጊዮርጊስ(የአሁኑ ብጹዕ አቡነ ሕርያቆስ)፣ ማኅበረ ካሕናቱ፣ ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ እና ይልቁኑም የመንፈስ ወንድሞቹና እህቶቹ የፍሬ ሃይማኖት አባላት በተገኘንበት እንባ እንደ ሐምሌ ዝናም እየወረደ(እየጎረፈ)  በምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል መካነ መቃብር ሥርዓተ ቀብሩ ተፈጽሟል። ወንድማችን  ሲታወስ(ስሙ ሕያው ሆኖ) እንዲኖር በማሰብም በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ  ውስጥ ዘወትር ቃለ እግዚአብሔር የሚነገርበት  አትሮንስ  በስሙ ተበርክቶለታል።እኛም  በአትሮንሱ ላይ የተጻፈውን ሕያው ስም በማየት እና መልካም ሥራውን በማስታወስ የጥሪ ጊዜያችን ደርሶ እስከምንከተለው ድረስ ውሉደ ፍሬ ሃይማኖት በሙሉ ስንዘክረው እንኖራለን። ኦ እግዚኦ አዕርፍ ለነፍሰ ገብርከ ተክለ ጻድቅ። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። ተጻፈ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም ማለዳ 3:00 ሰዓት

Open in Telegram
Views266−6%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#8965Text

ጾመ ነቢያት፤ ተስፋውን ማሰብ፣ ለበዓሉ መዘጋጀት 🕯 ዛሬ ዓለማችን በፍጥነት ትንቀሳቀሳለች፤ ሁሉም ነገር በቅጽበት ይከወናል፡፡ በዚህ ሁሉም ነገር በቅጽበት በሚለዋወጥበት ዓለም፣ አንድን ነገር ይሆናል ብሎ በተስፋ መጠበቅ በዘመናችን የሚደገፍ ነገር አይደለም፡፡ ለክርስቲያኖች ግን በተስፋና በትዕግሥት መጠበቅ የሕይወታችን ዘይቤ ነው፡፡ ይህን ደግሞ ጾመ ነቢያት የበለጠ አጉልቶ ያሳየናል። ምክንያቱም ጾሙ የመጠበቅ እና የማግኘት ስለሆነ፡፡ ጾመ ነቢያት ቆም ብለን የምናስብበትና ልባችንን የምናዘጋጅበት ወቅት ነው፡፡ የነቢያት ተስፋ ተፈጽሟል፤ ክርስቶስ መጥቷል፤ ታዲያ ለምን እንጾማለን? ቅዱሳን ነቢያት ለብዙ ዘመናት የመድኃኒቱን መምጣት ተስፋ አድርገው በጾምና በጸሎት ጠብቀዋል፡፡ “ከሰማይ ይወርዳል፤ ከድንግል ይወለዳል፤ ሰውን ያድናል” የሚለው ተስፋ ለአዳም ተሰጥቶ ነበር፤ ያ ተስፋ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተፈጽሟል፡፡ ዛሬ እኛ የምንጾመው ክርስቶስ እንዳልመጣ ሆነን አይደለም፡፡ በጾማችን ነቢያት የጠበቁትንና የጾሙትን እናስባለን፤ በዚህም ለነፍስና ለሥጋ በረከት እናገኛለን፡፡ ጾማችን የምስጋና፣ የመታሰቢያና የዝግጅት ጾም ነው፡፡ ጾሙ ሦስት ትርጕም አለው፡- 1. ማሰብ፡- የተስፋውን ረጅም ጉዞና የተስፋውን ፍጻሜ እናስታውሳለን፡፡ በዚህም ልባችን በምስጋና ይሞላል፡፡ 2. መዘጋጀት፡- የጾሙ ፍጻሜ የጌታችን የልደት በዓል ነው፡፡ ጾሙ በንስሓናና በንጽሕና ለበዓሉ እንድንዘጋጅ ያደርገናል፡፡ 3. በትጋት መኖር፡- ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን ዳግም መምጣት በናፍቆት ትጠብቃለች፡፡ ስለዚህ ጾሙ ዘወትር በንቃት መኖርን ያስተምረናል፡፡ የጾሙ ጊዜና ሰንበታት ጾሙ ከኅዳር 15 እስከ ታኅሣሥ 28 ድረስ ይዘልቃል (በዘመነ ዮሐንስ ደግሞ እስከ ታኅሣሥ 27)፡፡ በዚህ ወቅት ሦስት ሰንበታት ይታሰባሉ፡- • ስብከት (ከታኅሣሥ 7 እስከ 13)፡- ነቢያት ስለ ክርስቶስ መምጣት የሰበኩት ይታሰባል፡፡ • ብርሃን (ከታኅሣሥ 14 እስከ 20)፡- ክርስቶስ እውነተኛ የዓለም ብርሃን መሆኑ ይሰበካል፡፡ • ኖላዊ (ከታኅሣሥ 21 እስከ 27)፡- ክርስቶስ መልካም እረኛና ጠባቂያችን መሆኑ ይታሰባል፡፡ ጾማችን እንዴት ይሁን? • 📱 ትኩረታችንን ከሚወስዱ ነገሮች ራሳችንን ገተን ጊዜያችንን ለጸሎት እናድርግ፡፡ • 🤝 የተጣላነውን ይቅር እንበል፤ ይቅርታም እንጠይቅ፡፡ • 💛 በጾም የተውነውን ቁርሳችንን ለተቸገረ እናካፍል፡፡ • 📖 በየቀኑ አንድ የመዝሙረ ዳዊት ክፍል እናንብብ፡፡ • ⛪️ ትምህርተ ወንጌልን ለመስማት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሒድ፡፡ • ⛪️ ቅዳሴ እናስቀድስ፡፡ • ⛪️ ከምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን እንሳተፍ፡፡ መደምደሚያ ነቢያት ጠበቁ፤ ተስፋቸውም ተፈጸመ፡፡ እኛ ደግሞ ያንን ተስፋ እያሰብን፣ ልባችንን እያዘጋጀን የልደቱን ብርሃን በደስታ እንቀበላለን፡፡ እግዚአብሔር ይህንን ጾም በበረከት እንድናሳልፍ ይርዳን፤ ለሀገራችን ሰላምን የሚሰጥበት ያድርግልን፡፡ አሜን፡፡

Open in Telegram
Views315+11%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#8954Photo
Views453+59%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—

All posts

Connections