▪️ነጋዴና ማጭበርበር 1. 🔻አብዛኛው ኤሌክትሮኒክስ ሱቆች ላይ ከገዢዎች እና ከተለያዩ ሰዎች የሰማዋቸውን እና እኔም ማውቃቸውን የነጋዴዎች ማጭበርበርያዎች እንድትጠነቀቁ ዘንድ በከፊሉ ላካፍላችሁ 1ኛ ማወቅ ያለባችሁ ነገር አብዛኛው.ነጋዴ መሸጥ ሚፈልገው በእጁ ያለውን ወይም በቅርቡ ከአከፋፋይ ሱቅ ማግኘት የሚችለውን እቃ ነውና ያ እቃ መጥፎም ይሁን ምን .. ሊገዛ የመጣውን ሰው ሚያሳምነው በዛ እቃ ብቻና ብቻ ነው። ለዚህም ° 2.ያንን እቃ ለማሳመን የተለያየ ዘዴ ይጠቀማል ከነሱም ውስጥ ገዢው የጠየቀውን እቃ አለ ይለውና ወንበና ውኃ አስይዞ ካስቀመጠው በኋላ ገዢው ያዘዘውን እቃ ለሰራተኛው ያዘዋል ፤ እሱም ይመጣልኛል ብሎ ይጠብቃል በዚ መሀል ብዙ ጊዜ ያስጠብቀውና ገዢው ስለጠየቀው እቃ መጥፎነት እና በእጁ ላይ ስላለው እቃ ጥሩነት ማውራት ይጀምራል ... ይሄም ማስከርበት ይሉታል ° እንቀጥላላን .. @ibnyahya777
Open in Telegram
Ibn Yahya Ahmed
የተለያዩ ዲናዊ ፅሑፎችን ብቻ የማስተላልፍበት ቻናሌ ነው።
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 2, 2026 | 315 |
| Nov 6, 2026 | 277 |
| Nov 9, 2026 | 277 |
| Nov 16, 2026 | 210 |
| Nov 26, 2026 | 86 |
Most viewed this month
- 01Views315Forwards—Reactions—Comments—
- 02Views277Forwards—Reactions—Comments—
- 03Views277Forwards—Reactions—Comments—
- 04Views210Forwards—Reactions—Comments—
Latest posts
▪️መዲና እና እስልምና 2. 🔻ከ"በይዐተል-ዐቐበተል ኡላ" ከመጀመርያው ስምምነት በኋላ ነብያችን ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም ለመዲና ሰዎች እስልምናን እንዲያስተምር ሙስዐብ ቢን ዑመይር - ረዲየሏሁዐንሁን - ላኩት። እሱም ከመዲና በመጀመርያ ከሰለሙት ሰዎች መካከል ወደ አስዐድ ቢን ዙራራ ጋር በሆን እስልምናን ዳዕዋ ማድረግ ጀመረ ፤ ከዳዕዋው ፍሬ ውስጥም ትላልቅ መሪዎች ከነበሩት ውስጥ ኡሰይድ ቢን ሑደይር እና ሰዐድ ቢን ሙዓዝን ማስለም ቻለ። እነሱም ከሙስዐብ ጋር በመሆን ለህዝባቸው ኢስላምን አስተማሩ አብዛኛው ሰውም ሰለመ። ° 🔻ቀጣዩ የሐጅ አመት ሳይደርስ ሙስዐብ ወደ ረሱል በመመለስ ያሳለፈውን የዳዕዋ ሁኔታ ነገራቸው። የሐጅ አመት ሲደርስ(ማለትም 13ተኛው አመትላይ) ከመዲና ሰዎች 73 ወንዶች እና 2 ሴቶች ሚና "ዐቐባህ" በሚባል ቦታ ላይ በምሽት በድብቅ ረሱላችን ጋር ቃል ለመግባባት ተሰባሰቡ። እሳቸውም በችግርም በድሎትም ጊዜ አሏህን እንዲታዘዙ ፤ ሰደቃ እንዲሰጡ በመልካም እንዲያዙ ከመጥፎ እንዲከለክሉ ፤ በነፍሶቻቸው እና በንብረታቸው ረሱልን እንዲከላከሉ ይሄን ካደረጉ ደግሞ አሏህ ጀነት እንደሚሰጣቸው ቃል ገቡላቸው። ነብያችንም በጣም ተደሰቱ ... << እኔ ከናንተ ነኝ እናንተም ከኔ ናችሁ .. >> አሏቸው። አንሷሮችም በዚህም ተስማሙ ፤ ይሄም "በይዐተል-ዐቐበተ-ሳኒያ/ኩብራ" ወይም ሁለተኛው ስምምነት በመባል ይታወቃል። ይህም ስምምነት ለወደፊቱ እስልምና ማማር ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል። ሙሽሪኮችንም በቁጭት አስከፍቷል። ረሒቑል-መኽቱም ፥ 134 - 136 @ibnyahya777
Open in Telegram▪️ኢስራእና ሚእራጅ 🔻ኢስራእ ፡ ከመስጂደልሐራም ወደ በይተልመቅዲስ የተደረገ ጉዞ ሲሆን ሚእራጅ ደግሞ ከበይተልመቅዲስ ወደ ሰማይ የተደረገው ጉዞ ነው። ° 🔻ነብያችን - ሰለሏሁዓለይሂወሰለም - በጂብሪል ጓደኝነት ቡራቅን ጋልበው ኢስራእ አደረጉ ከዛም ሚእራጅ .. በመጀመርያው ሰማይ ላይ አደም - ዐለይሂሰላምን - አገኙ ፣ 2ተኛው ላይ የሕያ ቢን ዘከርያ እና ዒሳ ዐለይሂማሰላምን አገኙ ፣ 3ተኛው ላይ ዩሱፍን 4ተኛው ላይ ኢድሪስን ፣ 5ተኛው ላይ ሀሩን ቢን ዒምራንን አገኙ ሁሉንም ሰላም እያሉ እነሱም በነበይነታቸው እያረጋገጡ አለፉ። ° 🔻በ6ተኛው ሰማይ ላይ ሙሳ ዐለይሂሰላምን እና በ7ተኛው ሰማይ ደግሞ ኢብራሂም ዐለይሂሰላምን አግኝተዋል። ከዛ ሲድረተል ሙንተሃ እስኪደርሱ ድረስ ተጉዘዋል። ከዛም ወደጌታቸው ተጠግተው 50ሰላትን በግዴታነት ደነገገባቸው እሳቸውም ተቀብለው ሲመለሱ በሙሳ - ዐለይሂሰላም - ጥቆማ እያስቀነሱ ጌታቸውን እስከሚያፍሩ ድረስ ወደ 5አስቀንሰዋል። ጀነትና ጀሀነምን ያዩ ሲሆን ሌሎች ብዙ ተዓምራቶችንም አይተዋል .. ዐለይሂ አፍደሉሰላቲ ወትተስሊም መቼ አደረጉ የሚለው ልዩነት ያለበት ሲሆን የአብዛኛዎቹ ዑለማዎች አስተያየት ከኑቡዋ በ12 ወይም በ13ተኛ አመት የሚለው ያመዝናል። ጌታቸውን በዐይናቸው አይተዋል አላዩም የሚለውም ልዩነት ያለበት ሲሆን አላዩም የሚለው ትክክለኛው አቋም ነው። ~~~~ ረሒቑል መኽቱም ፥ 127 - 129 @ibnyahya777
Open in Telegram▪️መዲና እና እስልምና 🔻መዲና ውስጥ እስልምና እንዲስፋፋ መሰረት ከጣለው ትልቅ ነገር ከነቡዋ በ11ኛው አመት የ6ሰሓባዎች መስለም ነበር። እነሱም 1.አስዐድ ቢን ዙራራ 2.ዐውፍ ቢን ሓሪስ 3.ራፊዕ ቢን ማሊክ 4.ቑጥባህ ቢን ዓሚር 5.ዑቕባህ ቢን ዓሚር እና 6.ጃቢር ቢን ዐብዲሏህ ናቸው። እነሱ ከሰለሙ በኋላ ወደመዲና በመመለስ እስልምናን አስተረዋል። ከዛም ከነቡዋህ በ12ኛው አመት ላይ እንደተለመደው ለሐጅ ሲመጡ ሌሎች 7 ሰሓባዎች እስልምናን ተቀበሉ እነሱም 1.ሙዓዝ ቢን ሓሪስ 2.ዘክዋን ቢን ዐብድቀይስ 3.ዑባደቱ ቢን ሷሚት 4.የዚድ ቢን ሰዕለባህ 5.ዓባስ ቢን ዑባደት ቢን ነድላህ 6.አቡልሐይሰም 7.ዑወይም ቢን ሳዒድደህ 🔻ከነዚህ 13 ሰዎች ውስጥ ጃቢር ቢን ዐብዲሏህ ሲቀር 12ቱ ረሱልን ሙባየዓህ ወይም ቃለመሃላ ፈፀሙ። ማለትም በአሏህ ላይ ማንንም ላያጋሩ ፣ ላይሰርቁ ፣ ዝሙት ላይሰሩ ... ቃለ መሃላ ሚና ላይ ፈፀሙ። ይህም በይዐተል ዐቀበተልኡላ በመጣል ይታወቃል። ~~~ ረሑቑል መኽቱም ፥ 126 - 132 @ibnyahya777
Open in Telegram▪️ጧኢፍና አዛኙ ነብያችን 🔻ነብያችን - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - የመካ ሙሽሪኮች ዳዕዋቸውን አልቀበልም በማለት ሲያስቸግሯቸው ነብይ ከሆኑ በ10ኛው አመት ከዘይድ ቢን ሓሪስ ጋር በመሆን ወደጧኢፍ ተጓዙ። እዛም የባሰ ነገር እንጂ አልገጠማቸውም። ጫማቸው በደም እስኪጨማለቅ ድረስ ደበደቧቸው። አሏህንም ደካማነቴን ወደአንተ ስሞታ አቀርባለው .. አንተ አትቆጣብኝ እንጂ ግድ የለኝም በማለት ተማፀኑ ..አሏህም ዱዓቸውን ሰምቶ ቀርነል-መናዚል የተባለ ቦታ ሲደርሱ የተራራ መላኢካ ላከላቸው ፤ አንተ ከፈለግክ በሁለቱ ተራራ መካከል ላጣብቅልህም አላቸው እሳቸው ግን የእዝነት ነብይ ናቸውና አይሆንም! ከነሱ ዝርያ አሏህን በብቸኝነት የሚያመልኩ ባርያዎች ይፈጠሩ ይሆናል በማለት መለሱለት። (ረሒቁል መኽቱም ፥ 119 - 120) @ibnyahya777
Open in Telegram▪️ኸዲጃህ ረዲየሏሁዓንሃ 🔻ነብያችን ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም ስለኸዲጃህ ውለታ ሲናገሩ ይህን አሉ ፦[ ሰዎች በካዱኝ ጊዜ በኔ አመነች ፤ ሰዎች በዋሹኝ ጊዜ እውነተኛ መሆኔን አረጋገጠች ፤ ሰዎች ገንዘባቸውን በከለከሉኝ ጊዜ ከንብረቷ አጋራችኝ ፤ አሏህ ከሷ ልጆችን ረዘቀኝ .. ] (ኢማሙ አሕመድ ሙስነድ ላይ ዘግበውታል) @ibnyahya777
Open in Telegram▪️በዲን ፈተና ላይ መታገስ 🔻ኸባብ ኢብን አረስ ከእለታት አንድ ቀን ነብያችን ሰለሏሁዐለይሂወሰለም ጋር መጣና ከሙሽሪኮች ስለሚያጋጥማቸው መከራ በመንገር አሏህን አትለምንልም እንዴ በማለት በምሬት ሲጠይቃቸው .. እሳቸውም በቁጣ ፊታቸው ቀላ ብሎ ይህን አሉ ፦ [ ከእናንተ በፊት የነበሩት ህዝቦችኮ በጋለ ብረት ከአጥንቱ ስጋው እስኪለያይ ድረስ ያበጥሯቸው ነበር ግን ይህ ተግባራቸው ከዲኑ ንቅንቅ አያደርገውም ነበር። .. ] (ቡኻሪ) @ibnyahya777
Open in Telegram▪️የመጀመርያ ሒጅራ 🔻ነብዩ ሰለሏሁዓለይሂወሰለም የመካ ሙሽሪኮች ሲያስቸግሯቸውና ስቃዩ ሲበረታባቸው ነብይ ከመሆኑ በ5ተኛው አመት በረጀብ ወር የመጀመርያው ቡድን 12ወንድ እና 4ሴቶች ሆነው ወደሐበሻ እንዲሰደዱ አደረጉ። ከነሱም ውስጥ ዑስማን ቢን ዓፋን እና ባለቤታቸው ሩቅያ ይገኙበታል። ከኢብራሂም እና ከሉጥ ዐለይሂሰላም በኃላ በአሏህ መንገድ ላይ የተሰደዱ የመጀመርያ ቤተሰብ ናቸው በማለት ነብያችን ተናግረዋል። ~~~ ዛዱልመዓድ ፥ 1/24 .. ረሒቁልመኽቱም ፥ 92
Open in Telegram#በቁርአን_አስታውስ قُلْ إِنِّي أَخَافُ إِنْ عَصَيْتُ رَبِّي عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ «እኔ በጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ» በላቸው፡፡ (አንዓም ፥ 15)
Open in Telegram▪️መጀመርያ የሰለሙት - 🔻ነብያችን - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - በመጀመርያ የእስልምና ጥሪያቸው የሰለሙት ኸዲጃህ , ዐሊይ ቢን አቡጧሊብ ፣, ዘይድኢብንሓሪስ እና አቡበክር አስሲዲቅ ናቸው። ከዛ አቡበክር ዳዕዋ አድርገው ኡስማን ቢን ዐፋን ፣ ዙበይር ቢን ዐዋም ፣ ዐብዱረሕማን ቢን ዐውፍ ፣ ሰዕድ ቢን አቢወቃስ እና ጠልሓህ ቢን ዑበይዱላህ ሰልመዋል። ---- ረሒቁልመኽቱም ፥ 74 @ibnyahya777
Open in TelegramConnections
Similar channels
ኡስታዝ አቡየሕያ አብዱልዋሲዕ | قناة أستاذ أبي يحيى عبدالواسع@menhajadamaReligion3.87K
AMU ግቢ ጉባኤ ቤተ-መፅሀፍት@gebigubae_libraryReligion1.65K
💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!@tibyaan54Religion1.62K
መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች@recordingytReligion1.6K
ኒሳኡል መሻሪዕ@nisaulmesharieReligion1.86K
ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus 2009@daewaselefiyaarbaminchReligion1.89K
ቤተ መጻሕፍት@betemetsihafReligion1.9K
ፍሬ ሃይማኖት@frehaymanoteReligion1.9K