▪️ነጋዴና ማጭበርበር 1. 🔻አብዛኛው ኤሌክትሮኒክስ ሱቆች ላይ ከገዢዎች እና ከተለያዩ ሰዎች የሰማዋቸውን እና እኔም ማውቃቸውን የነጋዴዎች ማጭበርበርያዎች እንድትጠነቀቁ ዘንድ በከፊሉ ላካፍላችሁ 1ኛ ማወቅ ያለባችሁ ነገር አብዛኛው.ነጋዴ መሸጥ ሚፈልገው በእጁ ያለውን ወይም በቅርቡ ከአከፋፋይ ሱቅ ማግኘት የሚችለውን እቃ ነውና ያ እቃ መጥፎም ይሁን ምን .. ሊገዛ የመጣውን ሰው ሚያሳምነው በዛ እቃ ብቻና ብቻ ነው። ለዚህም ° 2.ያንን እቃ ለማሳመን የተለያየ ዘዴ ይጠቀማል ከነሱም ውስጥ ገዢው የጠየቀውን እቃ አለ ይለውና ወንበና ውኃ አስይዞ ካስቀመጠው በኋላ ገዢው ያዘዘውን እቃ ለሰራተኛው ያዘዋል ፤ እሱም ይመጣልኛል ብሎ ይጠብቃል በዚ መሀል ብዙ ጊዜ ያስጠብቀውና ገዢው ስለጠየቀው እቃ መጥፎነት እና በእጁ ላይ ስላለው እቃ ጥሩነት ማውራት ይጀምራል ... ይሄም ማስከርበት ይሉታል ° እንቀጥላላን .. @ibnyahya777
Open in TelegramPosts of Ibn Yahya Ahmed
▪️መዲና እና እስልምና 2. 🔻ከ"በይዐተል-ዐቐበተል ኡላ" ከመጀመርያው ስምምነት በኋላ ነብያችን ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም ለመዲና ሰዎች እስልምናን እንዲያስተምር ሙስዐብ ቢን ዑመይር - ረዲየሏሁዐንሁን - ላኩት። እሱም ከመዲና በመጀመርያ ከሰለሙት ሰዎች መካከል ወደ አስዐድ ቢን ዙራራ ጋር በሆን እስልምናን ዳዕዋ ማድረግ ጀመረ ፤ ከዳዕዋው ፍሬ ውስጥም ትላልቅ መሪዎች ከነበሩት ውስጥ ኡሰይድ ቢን ሑደይር እና ሰዐድ ቢን ሙዓዝን ማስለም ቻለ። እነሱም ከሙስዐብ ጋር በመሆን ለህዝባቸው ኢስላምን አስተማሩ አብዛኛው ሰውም ሰለመ። ° 🔻ቀጣዩ የሐጅ አመት ሳይደርስ ሙስዐብ ወደ ረሱል በመመለስ ያሳለፈውን የዳዕዋ ሁኔታ ነገራቸው። የሐጅ አመት ሲደርስ(ማለትም 13ተኛው አመትላይ) ከመዲና ሰዎች 73 ወንዶች እና 2 ሴቶች ሚና "ዐቐባህ" በሚባል ቦታ ላይ በምሽት በድብቅ ረሱላችን ጋር ቃል ለመግባባት ተሰባሰቡ። እሳቸውም በችግርም በድሎትም ጊዜ አሏህን እንዲታዘዙ ፤ ሰደቃ እንዲሰጡ በመልካም እንዲያዙ ከመጥፎ እንዲከለክሉ ፤ በነፍሶቻቸው እና በንብረታቸው ረሱልን እንዲከላከሉ ይሄን ካደረጉ ደግሞ አሏህ ጀነት እንደሚሰጣቸው ቃል ገቡላቸው። ነብያችንም በጣም ተደሰቱ ... << እኔ ከናንተ ነኝ እናንተም ከኔ ናችሁ .. >> አሏቸው። አንሷሮችም በዚህም ተስማሙ ፤ ይሄም "በይዐተል-ዐቐበተ-ሳኒያ/ኩብራ" ወይም ሁለተኛው ስምምነት በመባል ይታወቃል። ይህም ስምምነት ለወደፊቱ እስልምና ማማር ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል። ሙሽሪኮችንም በቁጭት አስከፍቷል። ረሒቑል-መኽቱም ፥ 134 - 136 @ibnyahya777
Open in Telegram▪️ኢስራእና ሚእራጅ 🔻ኢስራእ ፡ ከመስጂደልሐራም ወደ በይተልመቅዲስ የተደረገ ጉዞ ሲሆን ሚእራጅ ደግሞ ከበይተልመቅዲስ ወደ ሰማይ የተደረገው ጉዞ ነው። ° 🔻ነብያችን - ሰለሏሁዓለይሂወሰለም - በጂብሪል ጓደኝነት ቡራቅን ጋልበው ኢስራእ አደረጉ ከዛም ሚእራጅ .. በመጀመርያው ሰማይ ላይ አደም - ዐለይሂሰላምን - አገኙ ፣ 2ተኛው ላይ የሕያ ቢን ዘከርያ እና ዒሳ ዐለይሂማሰላምን አገኙ ፣ 3ተኛው ላይ ዩሱፍን 4ተኛው ላይ ኢድሪስን ፣ 5ተኛው ላይ ሀሩን ቢን ዒምራንን አገኙ ሁሉንም ሰላም እያሉ እነሱም በነበይነታቸው እያረጋገጡ አለፉ። ° 🔻በ6ተኛው ሰማይ ላይ ሙሳ ዐለይሂሰላምን እና በ7ተኛው ሰማይ ደግሞ ኢብራሂም ዐለይሂሰላምን አግኝተዋል። ከዛ ሲድረተል ሙንተሃ እስኪደርሱ ድረስ ተጉዘዋል። ከዛም ወደጌታቸው ተጠግተው 50ሰላትን በግዴታነት ደነገገባቸው እሳቸውም ተቀብለው ሲመለሱ በሙሳ - ዐለይሂሰላም - ጥቆማ እያስቀነሱ ጌታቸውን እስከሚያፍሩ ድረስ ወደ 5አስቀንሰዋል። ጀነትና ጀሀነምን ያዩ ሲሆን ሌሎች ብዙ ተዓምራቶችንም አይተዋል .. ዐለይሂ አፍደሉሰላቲ ወትተስሊም መቼ አደረጉ የሚለው ልዩነት ያለበት ሲሆን የአብዛኛዎቹ ዑለማዎች አስተያየት ከኑቡዋ በ12 ወይም በ13ተኛ አመት የሚለው ያመዝናል። ጌታቸውን በዐይናቸው አይተዋል አላዩም የሚለውም ልዩነት ያለበት ሲሆን አላዩም የሚለው ትክክለኛው አቋም ነው። ~~~~ ረሒቑል መኽቱም ፥ 127 - 129 @ibnyahya777
Open in Telegram▪️መዲና እና እስልምና 🔻መዲና ውስጥ እስልምና እንዲስፋፋ መሰረት ከጣለው ትልቅ ነገር ከነቡዋ በ11ኛው አመት የ6ሰሓባዎች መስለም ነበር። እነሱም 1.አስዐድ ቢን ዙራራ 2.ዐውፍ ቢን ሓሪስ 3.ራፊዕ ቢን ማሊክ 4.ቑጥባህ ቢን ዓሚር 5.ዑቕባህ ቢን ዓሚር እና 6.ጃቢር ቢን ዐብዲሏህ ናቸው። እነሱ ከሰለሙ በኋላ ወደመዲና በመመለስ እስልምናን አስተረዋል። ከዛም ከነቡዋህ በ12ኛው አመት ላይ እንደተለመደው ለሐጅ ሲመጡ ሌሎች 7 ሰሓባዎች እስልምናን ተቀበሉ እነሱም 1.ሙዓዝ ቢን ሓሪስ 2.ዘክዋን ቢን ዐብድቀይስ 3.ዑባደቱ ቢን ሷሚት 4.የዚድ ቢን ሰዕለባህ 5.ዓባስ ቢን ዑባደት ቢን ነድላህ 6.አቡልሐይሰም 7.ዑወይም ቢን ሳዒድደህ 🔻ከነዚህ 13 ሰዎች ውስጥ ጃቢር ቢን ዐብዲሏህ ሲቀር 12ቱ ረሱልን ሙባየዓህ ወይም ቃለመሃላ ፈፀሙ። ማለትም በአሏህ ላይ ማንንም ላያጋሩ ፣ ላይሰርቁ ፣ ዝሙት ላይሰሩ ... ቃለ መሃላ ሚና ላይ ፈፀሙ። ይህም በይዐተል ዐቀበተልኡላ በመጣል ይታወቃል። ~~~ ረሑቑል መኽቱም ፥ 126 - 132 @ibnyahya777
Open in Telegram▪️ጧኢፍና አዛኙ ነብያችን 🔻ነብያችን - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - የመካ ሙሽሪኮች ዳዕዋቸውን አልቀበልም በማለት ሲያስቸግሯቸው ነብይ ከሆኑ በ10ኛው አመት ከዘይድ ቢን ሓሪስ ጋር በመሆን ወደጧኢፍ ተጓዙ። እዛም የባሰ ነገር እንጂ አልገጠማቸውም። ጫማቸው በደም እስኪጨማለቅ ድረስ ደበደቧቸው። አሏህንም ደካማነቴን ወደአንተ ስሞታ አቀርባለው .. አንተ አትቆጣብኝ እንጂ ግድ የለኝም በማለት ተማፀኑ ..አሏህም ዱዓቸውን ሰምቶ ቀርነል-መናዚል የተባለ ቦታ ሲደርሱ የተራራ መላኢካ ላከላቸው ፤ አንተ ከፈለግክ በሁለቱ ተራራ መካከል ላጣብቅልህም አላቸው እሳቸው ግን የእዝነት ነብይ ናቸውና አይሆንም! ከነሱ ዝርያ አሏህን በብቸኝነት የሚያመልኩ ባርያዎች ይፈጠሩ ይሆናል በማለት መለሱለት። (ረሒቁል መኽቱም ፥ 119 - 120) @ibnyahya777
Open in Telegram▪️ኸዲጃህ ረዲየሏሁዓንሃ 🔻ነብያችን ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም ስለኸዲጃህ ውለታ ሲናገሩ ይህን አሉ ፦[ ሰዎች በካዱኝ ጊዜ በኔ አመነች ፤ ሰዎች በዋሹኝ ጊዜ እውነተኛ መሆኔን አረጋገጠች ፤ ሰዎች ገንዘባቸውን በከለከሉኝ ጊዜ ከንብረቷ አጋራችኝ ፤ አሏህ ከሷ ልጆችን ረዘቀኝ .. ] (ኢማሙ አሕመድ ሙስነድ ላይ ዘግበውታል) @ibnyahya777
Open in Telegram▪️በዲን ፈተና ላይ መታገስ 🔻ኸባብ ኢብን አረስ ከእለታት አንድ ቀን ነብያችን ሰለሏሁዐለይሂወሰለም ጋር መጣና ከሙሽሪኮች ስለሚያጋጥማቸው መከራ በመንገር አሏህን አትለምንልም እንዴ በማለት በምሬት ሲጠይቃቸው .. እሳቸውም በቁጣ ፊታቸው ቀላ ብሎ ይህን አሉ ፦ [ ከእናንተ በፊት የነበሩት ህዝቦችኮ በጋለ ብረት ከአጥንቱ ስጋው እስኪለያይ ድረስ ያበጥሯቸው ነበር ግን ይህ ተግባራቸው ከዲኑ ንቅንቅ አያደርገውም ነበር። .. ] (ቡኻሪ) @ibnyahya777
Open in Telegram▪️የመጀመርያ ሒጅራ 🔻ነብዩ ሰለሏሁዓለይሂወሰለም የመካ ሙሽሪኮች ሲያስቸግሯቸውና ስቃዩ ሲበረታባቸው ነብይ ከመሆኑ በ5ተኛው አመት በረጀብ ወር የመጀመርያው ቡድን 12ወንድ እና 4ሴቶች ሆነው ወደሐበሻ እንዲሰደዱ አደረጉ። ከነሱም ውስጥ ዑስማን ቢን ዓፋን እና ባለቤታቸው ሩቅያ ይገኙበታል። ከኢብራሂም እና ከሉጥ ዐለይሂሰላም በኃላ በአሏህ መንገድ ላይ የተሰደዱ የመጀመርያ ቤተሰብ ናቸው በማለት ነብያችን ተናግረዋል። ~~~ ዛዱልመዓድ ፥ 1/24 .. ረሒቁልመኽቱም ፥ 92
Open in Telegram#በቁርአን_አስታውስ قُلْ إِنِّي أَخَافُ إِنْ عَصَيْتُ رَبِّي عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ «እኔ በጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ» በላቸው፡፡ (አንዓም ፥ 15)
Open in Telegram▪️መጀመርያ የሰለሙት - 🔻ነብያችን - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - በመጀመርያ የእስልምና ጥሪያቸው የሰለሙት ኸዲጃህ , ዐሊይ ቢን አቡጧሊብ ፣, ዘይድኢብንሓሪስ እና አቡበክር አስሲዲቅ ናቸው። ከዛ አቡበክር ዳዕዋ አድርገው ኡስማን ቢን ዐፋን ፣ ዙበይር ቢን ዐዋም ፣ ዐብዱረሕማን ቢን ዐውፍ ፣ ሰዕድ ቢን አቢወቃስ እና ጠልሓህ ቢን ዑበይዱላህ ሰልመዋል። ---- ረሒቁልመኽቱም ፥ 74 @ibnyahya777
Open in TelegramForwarded from ኡስታዝ አቡየሕያ አብዱልዋሲዕ | قناة أستاذ أبي يحيى عبدالواسع
አንድ ወንድም የግድ ሀጂ ኢብራሂም ሰው ፊት ተመልሻለሁ ማለት ይጠበቅባቸዋል ?ብሎ ለጠየቀው መልስ አሏህ በቅዱስ ቃሉ እንዲህ ይላል إِنَّ ٱلَّذِينَ يَكۡتُمُونَ مَآ أَنزَلۡنَا مِنَ ٱلۡبَيِّنَٰتِ وَٱلۡهُدَىٰ مِنۢ بَعۡدِ مَا بَيَّنَّٰهُ لِلنَّاسِ فِي ٱلۡكِتَٰبِ أُوْلَٰٓئِكَ يَلۡعَنُهُمُ ٱللَّهُ وَيَلۡعَنُهُمُ ٱللَّٰعِنُونَ ١٥٩ إِلَّا ٱلَّذِينَ تَابُواْ وَأَصۡلَحُواْ وَبَيَّنُواْ فَأُوْلَٰٓئِكَ أَتُوبُ عَلَيۡهِمۡ وَأَنَا ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ ١٦٠ (159-160) እነዚያ (ስለነብዩ ሙሐመድና ሌሎችም) ከአንቀፆችና ቅን መመሪያዎች ያወረድነውን ለሰዎች በመጽሐፍ ከገለፅነው በኋላ የሚደብቁ ሰዎች ሁሉ አላህ ይረግማቸዋል፡፡ ረጋሚዎችም ሁሉ ይረግሟቸዋል፡፡ እነዚያ ከመደበቅ የተፀፀቱና አካሄዳቸውን ያስተካከሉና የደበቁትን የገለፁ ሲቀሩ፡፡ የእነርሱን ፀፀትንማ እቀበላለሁ፡፡ እኔም ፀፀትን በጣም ተቀባይ (አዛኝ) ነኝ፡፡ (وبينوا) (የገለፁ )የምትለዋ ዐ/ነገር ትክሩት ሊሰጣት ይገባል፤ለምሳሌ ለአንድ ሰው ከሆነ ስህተት ያስተማርከው በግል ትነግረዋለህ ፤ለመስጂድ ጀመኣ ከሆነ መስጂድ ቆመህ ታርማለህ ፤በህዝብ ፊት ከሆነው በህዝብ ፊት ስህተትን ማስተካከል ግድ ነው። በተረፈ ስለ ወልይ ያነሱት ላይ አንዳንድ ሰዎች ወሊይ ማለታቸው ወልየልአምር(ባለስልጣን ) ማለታቸው ነው ብለው ሲያድበሰብሱ ተመልክቻለሁ ፤ይህ በሁለት መንገድ ውሸት ነው፤ 1_ "አብይ ነቢይ የተባለው እዚህ ጎሮ ውስጥ ነው" ብለው ነው ቀጠል አድርገው" ነብይ ባንለውም ወልይ ነው "ያሉት፤ይህ ደግሞ በቀጥታ ግልጽ ነው። 2_አህመዲን በፃፈው ፅሁፍ እራሳቸው ማለትም የፈለጉት እሱን እንደነበረና ስህተት እንደሆነ አምነዋል ። ስለዚህ ወደ ሚዲያ ወጥተው ባለፈው የተናገሩት በስሜት መደበላለቅ ነው ፤ አላህ ይማረኝ ትክክል አልነበረም ማለት ይጠበቅባቸዋል ።
Open in Telegram▪️ሲራ 🔻ነብያችን ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም ሰኞ ቀን ጧት አከባቢ በረቢዓል አወል 9ነኛው ቀን ተወለዱ ፤ እንደተወለዱ ከኪስራ ህንፃዎች ውሥጥ 14ት የሚሆኑት ወድቀዋል እሳት አምላኪዎች የሚያመልኩትም እሳት ጠፍቷል ፤ ቡሐይራህ አከባቢ ያለ ቤተ-ክርስትያንም ወድሟል የሚለውን ጦበሪይና በይሃቂ የዘገቡት ቢሆንም ጠንካራ የሚባል ሰነድ ግን የለውም። አሚና እንደወለደቻቸው ወደአያታቸው ዐብዱልመጦሊብ ጋር ወሰደቻቸው እሱም ሙሐመድ የሚል ስም መረጠላቸው። በ7ቀናቸውም ተገረዙ። እናታቸው ሳምንት ካጠቧቸው በኋላ መጀመርያ ያጠባቻቸው የአቡለሀብ ባርያ ሱወይባህ ትባላለች። የነብያችንን አጎት ሀምዛን አጥብታ ነበር። ----- ረሒቁል መኽቱም ፥ 54-55 @ibnyahya777
Open in Telegram▪️ሶላት ውስጥ ኹሹዕ ለማምጣት ሚረዱ ነጥቦች 1.ከሸይጧን በአሏህ መጠበቅ 2.የምንቀራውን ቁርአን እና ዚክር ማስተንተን 3.የአሏህን ታላቅነት ማምጣት ፣ አሏህን ፊት መቆማችንን ማስታወስ 4.በሩኩዕ እና በሱጁድ ላይ ለአሏሁ ተዓላ መተናነሱን ማስታወስ እና የሰውልጅ ደካማ መሆኑን ማወቅ 5.ወደሱጁድ ቦታ ላይ መመልከት 6.በተለያዩ ስሜት ውስጥ ሆኖ ለምሳሌ ምግብ ርቦት ሽንቱን ወጥሮት ምናምን ወደሰላት አለመግባት ተውዲሑል-አሕካም ፥ 1/404 @ibnyahya777
Open in TelegramForwarded from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የአካል ጉዳት ሊደርስ የሚችልበት፣ ከዚህም አልፎ ህይወት የመጥፋት አደጋ ያለበት ስፖርት በኢስላም የተከለከለ ለመሆኑ የቁርኣንና የሐዲሥ ማስረጃዎች እና አጠቃላይ የሸሪዐ መርሆዎች አጉልተው ያሳያሉ። እንዲህ አይነት ስፖርታዊ ውድድር እንደማይፈቅድ የሚገልፁ የዑለማእ ፈትዋዎችንም ማየት እንችላለን። ይሄ እውነታ በተለያዩ አካላት ሲገለፅ ስለነበር ከሞላ ጎደል ግልፅ ይመስለኛል። ስፖርቱ የሚታወቅባቸው አላስፈላጊ ስድድቦች፣ ጉራዎች፣ ውሸቶች ሲጨመሩ ደግሞ ጥፋቱ ከፍ ይላል። ተወዳዳሪዎቹ ሴቶች ሲሆኑ ደግሞ የበለጠ ይብሳል። እዚህ ድረስ ያለው ሐቅ ለአብዛኛው ሙስሊም የሚሰወር ባይሆንም እጅግ ብዙ ወገን በተለያዩ መንገዶች ለግርግሩ ድምቀት እየሰጠ ነው። ቀላል የማይባል አካል ደግሞ ተሳታፊዎቹ ባልተፈቀደ ተግባር ላይ የተሰማሩ ሳይሆን ትልቅ ገድል የፈፀሙ ያክል ሃይማኖታዊ ውግንና እያሳየ ነው። አንድ ነገር በኢስላም የማይፈቀድ ከሆነ በሃይማኖትም፣ በሃገርም፣ በብሄርም፣ በአካባቢም ፣ በፆታም መነፀር እየተመለከትን ልንወግን አይገባም። የማይፈቀድ ከሆነ በቃ አይፈቀድም። ያልተፈቀደን ነገር ለመመልከት ገንዘብ ማውጣት፣ ያልተፈቀደን ነገር በሚያበረታታ መልኩ ድርጅቶችን ማስተዋወቅ አብሮ የማይፈቀድ ተግባር ነው። ሌላው ጊዜያችንን፣ ገንዘባችንን፣ ትኩረታችንን የምንሰጠው ምሳሌ ለሚሆነንና ከኛ የሚሻል ጉዳይ ላይ ለሚሰማራ አካል ነው። በተረፈ ጤናን ለመጠበቅ እና ከራስ ላይ ለመከላከል አካልን ብቁ የሚያደርጉ የ"ስፖርት" አይነቶችን መሰልጠን ጥሩ ነው። ይሄኛው ቀደም ብዬ ከገለፅኩት የሚለይ ነው። በመጨረሻም በቦክስና መሰል ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ የደረሱ የነፍስ መጥፋቶችና ቋሚ ጉዳቶችን መጥቀስ ፈልጌ ጄሚናይን ጠይቄ ነበር። ያገኘሁት እንደወረደ የሚከተለውን ይመስላል:- በቦክስና በሌሎች መሰል ከባድ የውጊያ ስፖርቶች (እንደ MMA/Mixed Martial Arts ያሉ) ላይ በውድድር እና በልምምድ ወቅት የሚደርሱ የነፍስ ማለፍና ከፍተኛ ቋሚ የአካል/የአእምሮ ጉዳቶች አሉ። የነፍስ መጥፋት (ሞት) * በቦክስ፡ በቦክስ ታሪክ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተወዳዳሪዎች በጨዋታ ወቅት ወይም ከጨዋታ በኋላ በተከሰተ የጭንቅላት ጉዳት ሕይወታቸውን አጥተዋል። ለምሳሌ ያህል፡ * ዱክ ኩ-ኪም (Duk Koo Kim - 1982)፦ የደቡብ ኮሪያው ቦክሰኛ ሬይ ማንሲኒን በተጋጠመበት ጨዋታ ላይ በደረሰበት የጭንቅላት ደም መፍሰስ ምክንያት ሕይወቱ አልፏል። ይህ አደጋ ዓለም አቀፉ የቦክስ ማህበር የዙር ብዛትን ከ15 ወደ 12 እንዲቀንስ ትልቅ ምክንያት ሆኗል። * ፓትሪክ ዴይ (Patrick Day - 2019)፦ አሜሪካዊው ቦክሰኛ በውድድር ወቅት ባጋጠመው ከባድ የጭንቅላት ጉዳት (Traumatic Brain Injury) ምክንያት ሕይወቱ አልፏል። * በሌሎች ስፖርቶች፦ በኤምኤምኤ (MMA)፣ በሙአይ ታይ (Muay Thai) እና በባዶ እጅ ውጊያዎች (Bare-knuckle boxing) ላይም ተመሳሳይ የነፍስ ማለፍ አደጋዎች ተመዝግበዋል። ቋሚ እና የረጅም ጊዜ ጉዳቶች * የአእምሮ እና የነርቭ ጉዳት (Chronic Traumatic Encephalopathy - CTE)፦ በየጊዜው በጭንቅላት ላይ በሚያርፉ ጠንካራ ምቶች ምክንያት የሚከሰት የረጅም ጊዜ የአእምሮ ጉዳት ነው። ይህም የማስታወስ ችሎታ ማጣት፣ ድብርት፣ የባህሪ ለውጥ እና የነርቭ መታወክ ያመጣል። * ቦክሰኛ ዲሜንሽያ (Punch-Drunk Syndrome / Dementia Pugilistica)፦ በብዙ የቦክስ ተወዳዳሪዎች ላይ የሚታይ ሲሆን፣ የመናገር ችግርን፣ የእጅ መንቀጥቀጥን (እንደ ፓርኪንሰን በሽታ) እና የእንቅስቃሴ መዛባትን ያስከትላል። * የዓይን እና የአካል ጉዳቶች፦ * የዓይን ሌንስ መንሸራተት ወይም የሬቲና መቀደድ (Retinal Detachment) እስከ ሙሉ እይታ ማጣት የሚያደርስ ቋሚ ጉዳት ያስከትላል። * የፊት አጥንቶች ስብራት፣ የጆሮ ቅርጽ መበላሸት (Cauliflower Ear) እና የቋሚ መንጋጋ ጉዳቶች። * የውስጥ አካላት (እንደ ኩላሊት እና ጉበት) ደም መፍሰስ እና ስብራት። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
Open in Telegram#በቁርአን_አስታውስ 🔻ስሜትን የመከተል ጉዳት { أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا } [ ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን ] (ፉርቃን ፥ 43) @ibnyahya777
Open in Telegram▪️ሶላት ውስጥ ከአሏህ ፍራቻ ማልቀስ 🔻ከሙጠሪፍ ቢን ዐብዲሏህ ከአባቱ ተይዞ እንደተዘገበው እንዲህ አለ ፡ [ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂወሰለም - እየሰገዱ ከማልቀሳቸው የተነሳ ከልባቸው ውስጥ ልክ ድስት ሲፈላ እንዲፍለቀለቀው ሲያለቅሱ አይቻለው። ] (አቡዳውድ ፣ ነሳኢይ ፣ ቲርሚዚይ እና ኢማሙአሕመድ ዘግበውታል) @ibnyhaya777
Open in TelegramForwarded from ስለ ቀልባችን
ከትዳር በፊት ወደ ዝሙት ገደል የሚጎትትሽ ወንድ ድንግልናሽን ሊነጥቅ የመጣ አዳኝ እንጂ፣ ፈፅሞ ባል አይሆንሽም። ያለ አንዳች ርህራሄ አሁኑኑ ብሎክ አድርጊው! ከህይወትሽም ጠራርገሽ አውጪው!
Open in Telegramቀን ይሰግዱ ይፆሙና ልክ ወንጀል እንደሰራ ሰው ተጨንቀው ደግሞ ለሊት ላይ ተነስተው ጌታችን ሆይ! ማረን ይላሉ የአሏህ ባሮች ... አሏህ ከነሱ ያድርገን @ibnyahya777
Open in TelegramForwarded from ኡስታዝ አቡየሕያ አብዱልዋሲዕ | قناة أستاذ أبي يحيى عبدالواسع
በአሁኑ ጊዜ አንድ ሰው መስጂድ ስላየሀው ብቻ ኢማሙ አህመድ እንዳይመስልህ ፤በዱንያ ጉዳይ ልብነ ድንግል ሊሆን ይችላል ፤ የሰው ሀቅ መጠንቀቅ ዲን እንደሆነ ብዙ ሰው ይዘነጋል
Open in TelegramForwarded from قناة دروس فضيلة الشيخ محمد زين بن آدم الحبشي - Sheikh MuhammedZain Adam - ሸይኽ ሙሐመድዘይን ኣደም
የተጠናቀቁ ዱሩሶች ስብስብ! ------------------------------------ በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ተቀርተው ተጠናቀው የተለቀቁ ዱሩሶችን እነዚህን ሊንኮች በመጫን በቀላሉ ማግኘት ትችላላችሁ። 1, "አድ'ዱሩሱል ሙሂማህ | الدروس المهمة" https://t.me/SheikhMuhammedZain/762 2, "ኡሱሉ'ሱንናህ | أصول السنة" https://t.me/SheikhMuhammedZain/755 3, "ሸርሑ ከሽፊ' ሹቡሀት | شرح كشف الشبهات" https://t.me/SheikhMuhammedZain/970 4, "ሸርሑ መሳኢሊል ጃሂሊያህ | شرح مسائل الجاهلية" https://t.me/SheikhMuhammedZain/994 5, "ሸርሑ ዐቂደቲ 'ጠሐዊያህ | شرح عقيدة الطحاوية" https://t.me/SheikhMuhammedZain/775 6, "ኡሱሉን'ፊ ተፋሲር | أصول في التفسير" https://t.me/SheikhMuhammedZain/912 7, "አር'ረሒቁል መኽቱም | الرحيق المختوم" https://t.me/SheikhMuhammedZain/548 8, "ሙልሐቱል' ኢዕራብ | ملحة اﻹعراب" https://t.me/SheikhMuhammedZain/150 9, "ከሽፉ'ኒቃብ | كشف النقاب" https://t.me/SheikhMuhammedZain/662 10, "አል'ፈዎኪሁል ጀንያህ | الفواكه الجنية" https://t.me/SheikhMuhammedZain/224 11، "አል'ፈዎኪሁል ጀንያህ | الفواكه الجنية" https://t.me/SheikhMuhammedZain/1084 12, "ሙዘኪራ ፊ አሕካሚ አስ-ሲያም | " مذكرة في أحكام الصيام https://t.me/SheikhMuhammedZain/1255 13, "ሸርሑ ኡሱሊ አስ-ሱና | شرح أصول السنة" https://t.me/SheikhMuhammedZain/1281 14, "ደዓኢሙ ሚኒሃጂ ኑቡዋህ | دعائم منهاج النبوة" https://t.me/SheikhMuhammedZain/1310 15, "ሸርሑ ሱንና ሊልበርበሃሪ | شرح السنة للإمام البربهاري" https://t.me/SheikhMuhammedZain/1462 16, "ሱነኑ አቢ ዳውድ / سنن أبي داود" https://t.me/SheikhMuhammedZain/1537 17, አልዑቡዲያህ / العبودية https://t.me/SheikhMuhammedZain/2127 18,ቡሉጉል መራም / بلوغ المرام https://t.me/SheikhMuhammedZain/2181 19,ሙዘኪራ ዐለል ዐቂደቲል ዋሲጢየህ / مذكرة على العقيدة الواسطية https://t.me/SheikhMuhammedZain/2479 20,ሸርሑ ኢብኒ ዐቂል ዐላ አልፊየቲ ኢብኒ ማሊክ/شرح ابن عقيل على ألفية ابن مالك https://t.me/SheikhMuhammedZain/2523 21,አል ቀዋዒዱል ሒሳን አል ሙተዐሊቀቲ ቢተፍሲሪል ቁርኣን/القواعد الحِسان المتعلقة بتفسير القرآن https://t.me/SheikhMuhammedZain/2772 22,ሙስጠለሑል ሐዲሥ/مصطلح الحديث https://t.me/SheikhMuhammedZain/2830 23,ሸርሑ ሙቀዲመቲ ተፍሲር/شرح مقدمة التفسير https://t.me/SheikhMuhammedZain/2849 24,መትኑል አጅሩሚየህ/متن الأجرومية https://t.me/SheikhMuhammedZain/2898 25,ደላሉ ጀማዐቲል አሕባሽ/ضلال جماعة الأحباش https://t.me/SheikhMuhammedZain/3112 📍የሸይኹን የተጠናቀቁ ዱሩሶችን ለማግኘት ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ↓↓↓ https://t.me/SheikhMuhammedZain
Open in Telegram