ደጀናችን ለሆነው ህዝብ አጋርነታችን አይለይም የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ሬጅመንት ለግዳጅ በተሰማራበት የትግራይ ክልል አካባቢ የሚገኙና አዝመራቸውን በወቅቱ ለማንሳት አቅም ያነሳቸውን አርሶአደሮች ሰብል ሰብስቧል። የሬጅመንቱ የሠራዊት አባላት በማንኛውም ግዳጆቻቸው ውስጥ ደጀን ለሆነን የአካባቢው ማህበረሰብ አጋርነታችን አይለየውም ብለዋል። የሬጅሜንቱ አዛዥ ሻምበል ሀይሌ የራንጎ እንዳሉት ክፍሉ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጣና ሁሉ በህዝባዊ ተግባሩ የሚታወቅና በመልካም ምግባሩ የሚመሰገን በመሆኑ የህዝብ ደጀንነት ያልተለየው ብቻ ሳይሆን እርሱም ለህዝብ አጋርነቱን በተግባር እያረጋገጠ የመጣ ህዝባዊ ሠራዊት ነው። የአርሶ አደሮችን ሰብል በመሰብሰብ ተግባር ላይ የተሳተፉ የሬጅመንቱ አባላት በሰጡት አስተያየት መለያ ባህሪያችን የሆነውን ህዝባዊ ድጋፎች አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። ድጋፍ ከተደረገላቸው አርሶ አደሮች መሀከል አቶ በየነ ደመወዝ በበኩላቸው የሠራዊት አባላቱ ሠብላቸውን በመሰብሰብ ላደረጉላቸው ድጋፍ የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል። ዘገባ የክፍለጦሩ የሠራዊት ስነ ልቦና ግንባታ ነዉ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official
Open in Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# ቁልፍ እሴቶች 1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣ 2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣ 3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣ 4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Subscribers, 30 days
Oct 31 – Nov 4−6 (0%)
Show as table
| Date | Subscribers |
|---|---|
| Oct 31, 2026 | 42,959 |
| Nov 1, 2026 | 42,960 |
| Nov 2, 2026 | 42,952 |
| Nov 3, 2026 | 42,951 |
| Nov 4, 2026 | 42,953 |
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Oct 31, 2026 | 3,546 |
| Nov 1, 2026 | 3,411 |
| Nov 2, 2026 | 2,595 |
| Nov 3, 2026 | 2,243 |
| Nov 4, 2026 | 1,668 |
Most viewed this month
- 01Views4.58KForwards1Reactions55Comments—
- 02Views4.46KForwards4Reactions35Comments—
- 03Views4.43KForwards5Reactions—Comments—
- 04Views4.41KForwards2Reactions—Comments—
- 05Views4.36KForwards5Reactions—Comments—
Latest posts
የቅድመ መከላከል ጥገና ለተሽከርካሪዎች አግልግሎትና ደህንነት ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም በመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የሜንተናንስ መምሪያ በአመት አንድ ጊዜ በሠራዊት ክፍሎች እየተንቀሳቀሰ ተሽከርካሪዎች ላይ የቅድመ መከላከል ጥገና እና ፍተሻ ስራ ያካሂዳል። የዋና መምሪያው ሜንተናንስ ሙያተኞችም የመከላከያ ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ማዕከል በሚገለገልባቸው ተሽከርካሪዎች ላይ የቅድመ መከላከያ ጥገና እና ፍተሻ ስራዎችን አከናውነዋል። በመከላከያ ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ማዕከል የሰው ሀብትና ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ታሪኩ ተረፈ የቅድመ መከላከል ሙያተኞቹ በማዕከሉ ተሽከርካሪዎች የምርመራ ፣ ማጽዳት ፣ ቅባት መስጠት፣ ማስተካከል ፣የመሞከር እና የኤሌክትሪክ ሲስተም የማረጋገጥ ስራዎች የተካተቱበት የቅድመ መከላከልና ፍተሻ ስራዎችን በብቃትና በጥራት መስራት መቻላቸውን አስረድተዋል። የቅድመ መከላከል ጥገና ስራ የተሽከርካሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ጉልህ ጠቀሜታ እንዳለው የገለፁት ሌተናል ኮሎኔል ታሪኩ ተረፈ የጥገና ሥራው የአገልግሎት ጊዜያቸውን ለማራዘም እንደሚያስችልም አስገንዝበው የሜንተናንስ መምሪያ እያከናወናቸው ያሉትን ችግር የመፍታት ተግባር አድንቀዋል። ተሽከርካሪዎች የሰርቪስ ጊዜያቸው ሲደርስ ወደ ጥገና ማዕከል ገብተው አስፈላጊው የጥገና አገልግሎት እንደሚሠጣቸው የተናገሩት ሌተናል ኮሎኔል ታሪኩ ተረፈ የመከላከያ ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ማዕከል ያልተቋረጠ የዕለት ተዕለት የሚዲያ ሥራ የሚሠራ በመሆኑ ያሉት ተሽከርካሪዎችን ዝግጁነት የማረጋገጥና ደህንነታቸውን የመፈተሽ ሥራ መተግበሩንም ገልፀዋል። በሜንተናንስ መምሪያ የመከላከል ጥገና ሾፕ ኃላፊ ሻለቃ ሰላም ካሳሁን በበኩላቸው በተሽከርካሪዎች ላይ የሚካሄደው የቅድመ መከላከል ፍተሻና ጥገና ስራ ተሽከርካሪዎችን ከተለያዩ ጉዳቶች ለመጠበቅ እንደሚያግዝ ገልፀው ወደ ጋራዥ ሲገቡም ለሚሰራው የተሟላ ጥጋና ስራ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተናግረዋል። ዘጋቢ በላቸው ክንዴ ፎቶ ግራፍ አብዱልወሀብ ሙህዲን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official
Open in TelegramConnections
Similar channels
Абиссинецъ – የሐበሻ መስኮብ@meskobPolitics1.81K
4-3-3 World News@ethionews433News and media50.1K
Ethiopian News Agency@ethiopiannewsaNews and media22.3K
Fana Media Corporation S.C (FMC)@fanatelevisionNews and media204K
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®@esat_tv1News and media205K
Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ@ayuzehabeshanewsNews and media262K
Витебск. Главное!@vitebskNews and media42.8K
GasGaza (الهيئة العامة للبترول)@gas_gaza1News and media43.2K
Mentioned by
Абиссинецъ – የሐበሻ መስኮብ@meskob1 mention, 5 repostsLatest post