Posts of FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

newest first

#61549Link preview

ደጀናችን ለሆነው ህዝብ አጋርነታችን አይለይም የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ሬጅመንት ለግዳጅ በተሰማራበት የትግራይ ክልል አካባቢ የሚገኙና አዝመራቸውን በወቅቱ ለማንሳት አቅም ያነሳቸውን አርሶአደሮች ሰብል ሰብስቧል። የሬጅመንቱ የሠራዊት አባላት በማንኛውም ግዳጆቻቸው ውስጥ ደጀን ለሆነን የአካባቢው ማህበረሰብ አጋርነታችን አይለየውም ብለዋል። የሬጅሜንቱ አዛዥ ሻምበል ሀይሌ የራንጎ እንዳሉት ክፍሉ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጣና ሁሉ በህዝባዊ ተግባሩ የሚታወቅና በመልካም ምግባሩ የሚመሰገን በመሆኑ የህዝብ ደጀንነት ያልተለየው ብቻ ሳይሆን እርሱም ለህዝብ አጋርነቱን በተግባር እያረጋገጠ የመጣ ህዝባዊ ሠራዊት ነው።    የአርሶ አደሮችን ሰብል በመሰብሰብ ተግባር ላይ የተሳተፉ የሬጅመንቱ አባላት በሰጡት አስተያየት መለያ ባህሪያችን የሆነውን ህዝባዊ ድጋፎች አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። ድጋፍ ከተደረገላቸው አርሶ አደሮች መሀከል አቶ በየነ ደመወዝ በበኩላቸው የሠራዊት አባላቱ ሠብላቸውን በመሰብሰብ ላደረጉላቸው ድጋፍ የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል። ዘገባ የክፍለጦሩ የሠራዊት ስነ ልቦና ግንባታ ነዉ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

Open in Telegram
Views524−78%vs avg
Forwards0
Reactions7
Comments—
#61543Link preview

የቅድመ መከላከል ጥገና ለተሽከርካሪዎች አግልግሎትና ደህንነት ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም በመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የሜንተናንስ መምሪያ በአመት አንድ ጊዜ በሠራዊት ክፍሎች እየተንቀሳቀሰ ተሽከርካሪዎች ላይ የቅድመ መከላከል ጥገና እና ፍተሻ ስራ ያካሂዳል። የዋና መምሪያው ሜንተናንስ ሙያተኞችም የመከላከያ ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ማዕከል በሚገለገልባቸው ተሽከርካሪዎች ላይ የቅድመ መከላከያ ጥገና እና ፍተሻ  ስራዎችን አከናውነዋል። በመከላከያ ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ማዕከል የሰው ሀብትና ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ታሪኩ ተረፈ የቅድመ መከላከል ሙያተኞቹ በማዕከሉ ተሽከርካሪዎች የምርመራ ፣ ማጽዳት ፣ ቅባት መስጠት፣ ማስተካከል ፣የመሞከር እና የኤሌክትሪክ ሲስተም የማረጋገጥ ስራዎች የተካተቱበት የቅድመ መከላከልና ፍተሻ ስራዎችን በብቃትና በጥራት መስራት መቻላቸውን አስረድተዋል። የቅድመ መከላከል ጥገና ስራ የተሽከርካሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ጉልህ ጠቀሜታ እንዳለው የገለፁት ሌተናል ኮሎኔል ታሪኩ ተረፈ የጥገና ሥራው የአገልግሎት ጊዜያቸውን ለማራዘም እንደሚያስችልም አስገንዝበው የሜንተናንስ መምሪያ እያከናወናቸው ያሉትን ችግር የመፍታት ተግባር አድንቀዋል። ተሽከርካሪዎች የሰርቪስ ጊዜያቸው ሲደርስ ወደ ጥገና ማዕከል ገብተው አስፈላጊው የጥገና አገልግሎት እንደሚሠጣቸው የተናገሩት ሌተናል ኮሎኔል ታሪኩ ተረፈ የመከላከያ ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ማዕከል ያልተቋረጠ የዕለት ተዕለት የሚዲያ ሥራ የሚሠራ በመሆኑ ያሉት ተሽከርካሪዎችን ዝግጁነት የማረጋገጥና ደህንነታቸውን የመፈተሽ ሥራ መተግበሩንም ገልፀዋል። በሜንተናንስ መምሪያ የመከላከል ጥገና ሾፕ ኃላፊ ሻለቃ ሰላም ካሳሁን በበኩላቸው በተሽከርካሪዎች ላይ የሚካሄደው የቅድመ መከላከል ፍተሻና ጥገና ስራ ተሽከርካሪዎችን ከተለያዩ ጉዳቶች ለመጠበቅ እንደሚያግዝ ገልፀው ወደ ጋራዥ ሲገቡም ለሚሰራው የተሟላ ጥጋና ስራ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተናግረዋል። ዘጋቢ በላቸው ክንዴ ፎቶ ግራፍ አብዱልወሀብ ሙህዲን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

Open in Telegram
Views1,114−53%vs avg
Forwards0
Reactions10
Comments—
#61537Link preview

ስልጠና የሠራዊቱን ሙያዊ አቅም ለማሣደግ ወሳኝ መሆኑ ተመላከተ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም ዘመናዊና ወቅቱን የጠበቀ ስልጠና መሰጠቱ  የሰራዊቱን የውጊያ አስተሳሰብ እና ተዋግቶ የማሸነፍ ብቃቱን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጨምር የመከላከያ ሠራዊት አባላት ገልፀዋል። የመከላከያ ሠራዊት አባላት በየትኛውም የአየር ንብረት እና ሁኔታ ግዳጃቸውን እንዲወጡ ተደርጎ መሰልጠናቸው ተልዕኳቸውን በራስ መተማመን እየፈፀሙ መሆናቸውን ተናግረዋል። ተዋግቶ ማሸነፍ የአንድ ሠራዊት አባል ግዳጅ መሆኑን የገለፁት የሠራዊት አባላት፤ የአገራቸውን ክብርና ነፃነት ለማስጠበቅ በንፁህ የአገር ፍቅር ስሜት ተልዕኳቸውን እንደሚፈፅሙ ገልፀዋል። ከሀገርና ከህዝብ የተቀበልነውን የቃል-ኪዳን አደራ በፅኑ ቁርጠኝነትና ታማኝነት ግዳጃችንን እንፈፅማለን ያሉት የሠራዊት አባላት በቀጣይም ህዝባዊ እሴታችንን ጠብቀን የሀገርን ክብር እናስጠብቃለን ብለዋል። የዘገበው የበላቸው ካሳሁን ነው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

Open in Telegram
Views1,142−52%vs avg
Forwards0
Reactions13
Comments—
#61533Link preview

የሠራዊቱን የግዳጅ አፈጻጸም ለማሳለጥ የጥገና ቡድኑ ያለውን አቅም ሁሉ እየተጠቀመ ነው። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር የጥገና ቡድን፣ ሠራዊቱ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት እንዲፈጽም የጦር መሣሪያዎችንና ተሽከርካሪዎችን በወቅቱ በመጠገን የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑ ተገለጸ። የኮሩ የጥገና ቡድን ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ደጀኔ ተፈራ እንደገለጹት፣ ሠራዊቱ በተለያዩ አስቸጋሪና ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ ሆኖ ተልዕኮውን በላቀ ብቃት እንዲወጣ የጥገና ቡድኑ ያለውን የሰው ኃይል፣ የሙያ እውቀትና የቴክኒክ አቅም ሁሉ እየተጠቀመ ይገኛል። ቡድኑ ተዋጊው ኃይል በሚንቀሳቀስባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ተገኝቶ፣ ከቡድን እስከ የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎች የሚያጋጥሙ ብልሽቶችን እንዲሁም በጉዞና በሥራ ላይ የሚበላሹ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በፍጥነት በመጠገን ወደ ሥራ እንዲመለሱ እያደረገ መሆኑንም አብራርተዋል። የሠራዊቱን አሁናዊ ግዳጅ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ቡድኑ ከመደበኛው የጥገና ሥራ ባለፈ የፈጠራ ሥራዎችንና የባለሙያዎቹን ብቃት በመጠቀም ለተዋጊው ኃይል የማያቋርጥ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። ከኮሩ የጥገና ክፍል ሻምበል ጌትነት ገብረ ማርያም በበኩላቸው፣ ክፍሉ በርካታ ዓመታት በሙያው ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎችን ያቀፈ በመሆኑ ለተዋጊው ኃይል ፈጣንና ሁለገብ የጥገና አገልግሎት በመስጠት የግዳጅ አፈጻጸሙን ለማሳለጥ የራሱን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ለረጅም ዓመታት በአገልግሎት ላይ የቆዩ የተቋሙ ተሽከርካሪዎችና በግዳጅ ላይ የተበላሹ ፓትሮሎች የቦዲ ሞዲፊኬሽንና አስተማማኝ ጥገና በማድረግ እንደገና ለሥራ እንዲበቁ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህም ያሉትን ሀብቶች በአግባቡ በመጠቀም የሠራዊቱን የሥራ አቅም ከማሳደግ አንጻር ጉልህ ሚና እንዳለው አስረድተዋል። ዘጋቢ ቻላቸው አዱኛ ፎቶግራፍ ነበረ ተሾመ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

Open in Telegram
Views1,479−38%vs avg
Forwards0
Reactions20
Comments—
#61528Link preview

ተልዕኮን በብቃት ለመፈፀም ቀጣይነት ያለው ስልጠና ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ሴክተር ሶስት በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ የተሰማራው የኢትዮጵያ ሰራዊት፣ ከሞተራይዝድ ሻለቆችና ከተለያዩ ክፍሎች ለተውጣጡ ሙያተኞች በድሮን ቴክኖሎጂና በአካባቢ ጥበቃ ዘርፎች ስልጠና ሰጥቷል። በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ተገኝተው ለሰልጣኞች ሰርተ-ፊኬት የሰጡት የሴክተር ሶስት ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ሃሺም መሃመድ፣ ስልጠናውን ለሰጡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሶማሊያ ድጋፍ አገልግሎት (UNSOS) አመራርና አባላት ምስጋና አቅርበዋል። ስልጠናው በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ያለውን የሰራዊቱን ሙያዊ የአፈጻጸም አቅም ከማጎልበት ባሻገር፣ ለሚሰጡ ማናቸውም ተልዕኮዎች በብቃትና በዝግጁነት ምላሽ ለመስጠት እንደሚያግዝ ገልጸዋል። የሰራዊቱን የማድረግ አቅም የሚያጎለብቱ ስልጠናዎች እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ሰልጣኞች ባገኙት እውቀትና ክህሎት መሰረት ግዳጃቸውን በአግባቡ እንዲወጡ፣ በተሰማሩበት አካባቢ ማህበረሰቡንና ሰራዊቱን በቅንነት፣ በታማኝነትና በጀግንነት እንዲያገለግሉ አሳስበዋል። ሠልጣኞች በተማሩት ሙያ ተተኪ ሙያተኞችን በማፍራት ረገድ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መልዕክት አስተላልፈዋል። ዘጋቢ መዝገቡ ያረጋል ፎቶግራፍ ሙላቱ በየነ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

Open in Telegram
Views1,302−45%vs avg
Forwards0
Reactions14
Comments—
#61523Link preview

ክፍለጦሩ በሽብር ቡድኑ ሸኔ ላይ ጠንካራ እርምጃ እየወሠደ መሆኑ ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም በማዕከላዊ ዕዝ የጋሻ ኮር ፅናት ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ሻለቃ መለስ አስማማው አሸባሪው የኦነግ ሸኔ ቡድን በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ዳኖ ሮጌ ቀበሌ በሠላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ሲያደርስ መቆየቱን ገልፀው ክፍለጦሩ ባደረገው የተጠናከረ ዘመቻ የሽብር ቡድኑ ሸኔ ላይ አሥፈላጊውን እርምጃ በመውሠድ ከነጦር መሣሪያቸው መማረክ መቻሉን ገልፀዋል። ሠራዊቱ ህዝብና መንግስት የሠጠውን ታላቅ ሃገራዊ ግዳጅ እየተዋጣ መገኘቱን የገለፁት ምክትል አዛዡ መንግስት ተደጋጋሚ ለሠላም እጁን ቢዘረጋም አሻፈረኝ ብሎ በህዝብ ላይ ጉዳት ሲያደርስ የቆየው ሸኔ እየተማረከ መሆኑን አሥረድተዋል። ሻምበል አለሙ ታደሰ በበኩላቸው የሠላም አመራጭን ትቶ የህዝብን ማህበራዊ ህይወት የሚያናጋው እና ሠላምን እያደፈረሠ የሚገኘው የሸኔ ቡድን በህዝብ ላይ የሚያስከትለው ስቃይ እና እንግልት እንዲያከትም ሠራዊቱ እስከ ህይወት መስዋዕትነት በመክፈል የቀጠናውን ሠላም እያረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል። ዘጋቢ አትርሴ ወንዴ ፎቶግራፍ ለሚ ተስፋዬ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

Open in Telegram
Views1,511−37%vs avg
Forwards1
Reactions13
Comments—
#61520Link preview

የደቡብ ጎንደር ዞን ሕዝብ ለምስራቅ ዕዝ ክፍለ ጦር የእርድ ሰንጋ ድጋፍ አደረገ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም የሠራዊቱን ተልዕኮ ስኬታማ ለማድረግና ህብረተሰቡ ከሰራዊቱ ጎን መሆኑን ለማረጋገጥ በደቡብ ጎንደር ዞን የሚገኙ የስማዳ፣ የአንዳቤት፣የእስቴ ወረዳ ሕዝብ ፣የመካነ እየሱስ ከተማ አሰተዳደር እና የወገዳ ከተማ አስተዳደር በቀጣናው ተሰማርቶ ለሚገኘው ሰራዊት 04 የእርድ ሰንጋ እና የበግ ድጋፍ አድርገዋል። የእስቴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማንተፋርዶ ሞላ እና የስማዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳልክ ጥላሁን ሰራዊቱ እየፈፀመ ያለው አኩሪ ጀግንነትና ተጋድሎ ሀገርና ወገንን ያሚያኮራ በመሆኑ መስተዳደሮቹ እና ህዝቡ ሠራዊቱን ለማበረታታት በማንኛውም ሁኔታ ከሰራዊቱ ጎን መሆናችን ለማመላከት የተደረገ ድጋፍ ነው ብለዋል። ድጋፉን የተረከቡት የምሰራቅ ዕዝ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ሌተናል ኮሎኔል መሐመድ ኢንድሪሰ በፅንፈኛው ቡድን ላይ የምናስመዘግበው ድል ህዝቡ ከጎናችን በመሆኑ ነው ሲሉ ገልፀዋል።  የወረዳዎቹ አመራሮች እና የከተማ አስተዳደሮች የሚመሩትን ህዝብ ወክለው ላደረጉልን ህዝባዊ ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል። ዘገባው የክፍለ ጦሩ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

Open in Telegram
Views1,751−26%vs avg
Forwards0
Reactions9
Comments—