Account
AHADU RADIO FM 94.3

AHADU RADIO FM 94.3

የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ! Your source for top local and international news and analysis. You can follow us on: Facebook:- facebook.com/ahadutelevision X: -x.com/ahaduradiotv TikTok: - tiktok.com/@ahadutv.official

Username
@ahaduradio
Category
News and media
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers17,419
Avg views per post, 7d441last 7 days
ERR2.53%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 25, 20261,123
Nov 26, 2026313

Most viewed this month

  1. 01

    የኢትዮጵያና እስራኤል የ70 ዓመታት ትብብር ወደ ሰው ኃይል ልማትና ቴክኖሎጂ እየተሸጋገረ መሆኑ ተገለጸ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የኢትዮጵያና የእስራኤል የ70 ዓመታት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በግብርናና በጤና ዘርፎች ከነበረው ትብብር ባለፈ በሰው ኃይል ልማት፣ በእውቀትና በቴክኖሎጂ ሽግግር እየተጠናከረ መሆኑ ገልፀዋል ። በኢትዮጵያ የእስራኤል ኢምባሲ ምክትል አምባሳደር ሲቫን ኖይማርክ፣ የሁለቱ ሀገራት የቆየ ወዳጅነት ወደ አዲስ የትብብር ምዕራፍ እየተሸጋገረ መሆኑን በ70ኛ ዓመት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መታሰቢያ መድረክ ላይ ተናግረዋል። እስራኤል ውስን የተፈጥሮ ሀብትና የውሃ እጥረት ቢኖርባትም በሰው ኃይል ልማትና በቴክኖሎጂ ፈጠራ ችግሮቿን ለመቅረፍ መቻሏን ምክትል አምባሳደሯ ጠቅሰዋል። በተለይም በመስኖ እርሻ፣ በውሃ ጨው ማስወገድና በምግብ ምርት ቴክኖሎጂ ያካበተችው ልምድ ለኢትዮጵያ ጠቃሚ የትብብር ዕድል መፍጠር እንደሚችል አመልክተዋል። በቴክኖሎጂና በስታርትአፕ ዘርፍ እስራኤል እያስመዘገበች ያለው ውጤትም ለእውቀት ሽግግሩ አስፈላጊ መሠረት መሆኑን ጠቅሰዋል። ባለፈው ዓመት 775 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ስታርትአፕ ኩባንያዎች በእስራኤል የተቋቋሙ ሲሆን፣ 14.6 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት መሳባቸው ጠቁመዋል ። በ2026 የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራትም የእስራኤል ስታርትአፕ ኩባንያዎች 11 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት መሳባቸውንና ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ50 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አስረድተዋል። በደረጀ መንግስቱ #አሐዱ_ሬዲዮ_94.3 #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

    Photo
    Views1.16K
    Forwards—
    Reactions3
    Comments—
  2. 02

    በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራ 12 ቢሊዮን ብር ማዳን መቻሉ ተገለፀ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የፌዴራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአስቸኳይ የሙስና ቅድመ መከላከል ስራ ኢትዮጵያ ልታጣ የነበረውን 12 ቢሊዮን ብር በአምስት ዓመት ውስጥ ማዳን መቻሉን አስታውቋል። የፀረ ሙስና ህጎች እና አለም አቀፍ ስምምነት ማስተባበር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀረጎት አብረሃ እንደገለፁት ፣ ሀገሪቱ ልታጣ የነበረውን ብር ማዳን የተቻለው በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራ መሆኑን ገልፀዋል። ዘንድሮ የሚከበረው 23ኛው የዓለም ዓቀፍ የፀረሙስና ቀን “ሥውር ትስስሮችን በማጋለጥ፤ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ!” በሚል መሪ ቃል እየተገበረ ይገኛል ። ኢትዮጵያም የተባበሩት መንግስታት የፀረ-ሙስና ስምምነት አባል ሀገር እንደመሆኗ፣ ይህንኑ 23ኛ ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ከህዳር 1 እስከ 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እየተከበረ ይገኛል ። ሙስና በተናጠል ወይም በግልጽ ሁኔታ የማይከሰት ፤ ከሌሎች ወንጀሎች እና ከጥቅም ተጋሪዎች ጋር በድብቅ የሚፈጠር ውስብስብ ወንጀል መሆኑን አስረድተዋል። ሙስና በድንገት የሚፈጸም ሳይሆን፣ በጥቅምና በአሠራር የተሳሰሩ አካላትን የሚያካትት የተደራጀ መረብ ወይም ስውር ትስስሮች ያለው ወንጀል መሆኑ ገልፀዋል። አክለውም ይህን የህግ ስራ ለመከላከል የፍትህ አካላት በፀረ-ሙስና ትግሉ ተቀናጅተው በመንቀሳቀስ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን በጋራ መግታት ይኖርባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል። በህይወቴ ጌትነት #አሐዱ_ሬዲዮ_94.3 #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

    Photo
    Views1.12K
    Forwards—
    Reactions3
    Comments—
  3. 03
    Views1.09K
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—
  4. 04

    በኢትዮጵያ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 24 ዓመት ባሉ ታዳጊና ወጣት ሴቶች ላይ አዲስ በኤችአይቪ የመያዝ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ጥናት አመላከተ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ኤድስ ሄልዝኬር ፋውንዴሽን እ.ኤ.አ. በ2025 ባካሄደው ሀገራዊ ጥናት በኢትዮጵያ ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር 660 ሺህ ገደማ መሆኑን ገልጿል። በ5ኛውን የአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና ጉባኤ ላይ የኤች አይቪ ስርጭት እንደ ሀገር ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ በጥናት አስደግፈው የተናገሩት የኤድስ ሄልዝኬር ፋውንዴሽን ተቋም የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ቶለሳ ኦላና ናቸው ፡፡ ስራ አስኪያጁ፡ እንደ ሀገር በበሽታው ከተጠቁ በኋላ ተመርምረው ራሳቸውን ያወቁ ሰዎች 80 በመቶ ያህሉ ብቻ ሲሆኑ ቀሪዎቹ 20 በመቶ የሚሆኑት ገና ያልተለዩ መሆናቸውን ተናግረዋል። በየዓመቱ ከኤችአይቪ ጋር በተያያዘ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ10 ሺህ በላይ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ቶለሳ፣ በተለይም ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 24 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ታዳጊና ወጣት ሴቶች ላይ አዲስ በቫይረሱ የመያዝ ሁኔታ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በታች ባሉ ሕፃናት መካከል በቫይረሱ ተይዘዋል ተብለው ከሚገመቱት ውስጥ ተመርምረው የተለዩትና ሕክምና ላይ የሚገኙት 40 በመቶ አካባቢ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በተለይም በታዳጊና ወጣት ሴቶች እንዲሁም በአጠቃላይ ማኅበረሰቡ ዘንድ አዲስ የመያዝ ሁኔታ እንዲጨምር ምክንያት ከሆኑት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት መስፋፋት፣ በወጣቶች ዘንድ ስለ ቫይረሱ ያለው ግንዛቤና የምርመራ ባህል ዝቅተኛ መሆን ይጠቀሳል ፡፡ በተጨማሪም ለኤችአይቪ መከላከል የሚሰጠው ትኩረትና የድጋፍ መዋቅር መቀዛቀዝ፣ የአልኮልና አደንዛዥ ዕፆች ተጠቃሚነት መጨመር እና ኢኮኖሚያዊ ተጋላጭነትና መሰል ችግሮች መሆናቸው ጠቁመዋል ። ይህንን የበሽታ ስርጭት ለመከላከል ኢትዮጵያ እንደ አፍሪካ የህብረተሰብ የጤና ጉባኤ ያሉ ጉባኤዎችን ማዘጋጀት መቻሏ ትልቅ እድል እንዳለውም ተናግረዋል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የጤና ሚኒስቴር በጋራ በ2025 ባወጡት ሪፖርት በሀገሪቱ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 595 ሺህ 447 ገደማ መሆኑን ያሳያል። በዚህ ሪፖርት መሰረት በዓመት የሚከሰት አዲስ የመያዝ መጠን 7 ሺህ 545 ሲሆን፣ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ደግሞ በዓመት 9 ሺህ 560 አካባቢ መሆኑን የተቋማቱ መረጃዎች ያመላክታሉ። በደረጀ መንግስቱ #አሐዱ_ሬዲዮ_94.3 #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

    Text
    Views573
    Forwards—
    Reactions2
    Comments—

Latest posts

#26077Text

“የኤርትራ መንግሥት ጊዜያዊ ነው፤ በመዝገበ ቃላቱ ውስጥ ልማትና ዕድገት የሚባል ነገር የለም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ፣ ኢትዮጵያ ከኤርትራ መንግሥት ጋር በጋራ ለመልማት ተደጋጋሚ ጥረት ብታደርግም፤ የኤርትራ መንግሥት ግን ለልማትና ለዕድገት ፍላጎትም ሆነ ግንዛቤ የሌለው መሆኑን ገልጸዋል። “የኤርትራ መንግሥት በመዝገበ ቃላቱ ውስጥ ልማትና ዕድገት የሚባል ጽንሰ ሐሳብ የለም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዚህም ምክንያት መንገድ እንሥራ ወይም በጋራ እንልማ ሲባል እንደ አለማወቅና ቂልነት አድርጎ እንደሚመለከተው ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በጋራ ከተሠራ ትልቅ የዕድገት አቅም መኖሩን በማመን ከኤርትራ ጋር አብሮ ለመልማት ከፍተኛ ጥረት ማድረጓን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰዋል። ለአብነትም በኤርትራ ያለውን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ለመቅረፍ ፣ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩን በኢትዮጵያ ወጪ በመዘርጋት በሀገር ውስጥ ተመን ኃይል ለማቅረብ ጥያቄ ቀርቦ እንደነበር አስታውሰዋል። በተጨማሪም ሁለቱን ሀገራት የሚያስተሳስሩ መንገዶችንና ወደቦችን በጋራ ለመገንባት ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ብትጠይቅም በኤርትራ መንግሥት በኩል ፈቃደኝነት አለመገኘቱን አስረድተዋል። ሁለቱ ሀገራት በትብብር ቢሠሩ ኖሮ አስመራን ከኢትዮጵያ ልምድ በመውሰድ በኮሪደር ልማት ማሳደግ ይቻል እንደነበር የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህ አለመሆኑ የኤርትራ መንግሥት ትልቅ ድክመት መሆኑን ገልጸዋል። አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያ ለጋራ ልማት ሐሳቧን ፣ ገንዘቧንና ጉልበቷን በሙሉ ለማዋጣት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠው የኤርትራ መንግሥት ምንም ዓይነት ገንዘብም ሆነ ሐሳብ ሳይጠበቅበት ተባባሪ ብቻ በመሆን በሰላምና በጋራ ዕድገት ጎዳና እንዲጓዝ ጥሪ አቅርበዋል። በወልደሐዋርያት ዘነበ #አሐዱ_ሬዲዮ_94.3 #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

Open in Telegram
Views281−36%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#26074Photo

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ለወጣቶች ዕድል የሚፈጥር የ 10 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በስሩ የሚገኙ ስምንት የልማት ድርጅቶች ያሉባቸውን ችግሮች በመለየት ወጣት ስራ ፈጣሪዎች መፍትሔ እንዲያመነጩ ዕድል የሚያመቻች እና 10 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተመደበለት "ካማ" የተሰኘ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል። ፕሮጀክቱ ለአንድ ዓመት ያህል የሚቆይ ሲሆን ካማ በመባል የሚጠራው ይህ ፕሮጀክት ሀገር በቀል መፍትሔዎችንና ስታርት አፕዎችን በማገዝና ወደ ገበያ የማሻገር ሂደትን ለማፍጠን ያለመ እንደሆነ ተቋሙ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ይህን ፕሮጀክት ተግባራዊ የሚያደርገው ከኤ.ኤል.ኤክስ ኢትዮጵያ ከተሰኘ ተቋም ጋር በመተባበር ሲሆን መርሐ ግብሩም በአራት ዙሮች የሚተገበር መሆኑን ተገልጿል። "ካማ" ሀገር በቀል መፍትሔዎችንና ስታርትአፕዎችን በማገዝና ወደ ገበያ የማሸጋገር ሂደትን ከማፍጠን በተጨማሪም የሀገር ውስጥ የፈጠራ ባለሙያዎችን የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ የሚያሳድጉ ዲጂታል እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እንዲያበለጽጉ እንዲሁም በተግባር እንዲውሉ ዕድል በመፍጠር ለ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ግቦች መሳካት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ተጠቁሟል። የ"ካማ" የመጀመሪያ ዙር ማመልከቻ ከህዳር 17 እስከ ታህሳስ 29 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን መስፈርቱን የሚያሟሉ ኢንተርፕርነሮች ፣ ስታርትአፕዎችና የፈጠራ ባለሙያዎች እንዲሁም የልማት ድርጅቶች ያቀረቧቸውን የፈጠራ ፍላጎቶች ማመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል። በተመስገን ተጋፋው #አሐዱ_ሬዲዮ_94.3 #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

Open in Telegram
Views379−14%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#26073Photo

ትግራይን ጨምሮ የተሟላ ሰላም ሲኖር የህዝብ ቆጠራ እንደሚደረግ ተገለጸ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ትግራይን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ የተሟላ ሰላም ሲሰፍን እና ነገሮች መልክ ሲይዙ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ እንደሚካሄድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። የምክር ቤት አባላት የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ለሀገሪቱ የልማት ዕቅዶች ፣ ለፍትሐዊ የበጀት ድልድል እንዲሁም ለምርጫ ክልሎች አከላለል ወሳኝ መሠረት መሆኑን አንስተው ቆጠራው እንዲካሄድ ጠይቀዋል። በተጨማሪም ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 13 እና 14 ዓመታት የአካባቢ ምርጫ ሳይካሄድ መቆየቱን የገለጹት አባላቱ ምርጫው የሚካሄድበት የጊዜ ሰሌዳ በመንግስት አቅጣጫ ውስጥ እንዲካተት ፣ ለሕዝብ ግልጽ እንዲደረግና አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እንዲከናወን ጥያቄ አቅርበዋል። ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሕዝብ ቆጠራው ትግራይን ጨምሮ በሁሉም አካባቢዎች የተሟላ ሰላም ሲኖር መካሄድ እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተው "ነገሮች መልክ ሲይዙ ይደረጋል" ብለዋል። የአካባቢ ምርጫን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ የአካባቢ ምርጫ በዋናው ምርጫ መካከል የሚደረግ መሆኑን ጠቁመው የዘንድሮው የመንግስት ዕቅድ ቀደም ሲል ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች ላይ የማሟያ ምርጫ ማካሄድ መሆኑን አስረድተዋል። አያይዘውም የማሟያ ምርጫው ከተጠናቀቀ በኋላ ምናልባት ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ አካባቢ ምርጫ እንደሚገባ ገልጸዋል። በፋሲል አረጋይ #አሐዱ_ሬዲዮ_94.3 #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

Open in Telegram
Views491+11%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#26072Text

35 ሺሕ የህጻናት መዋያ ተቋማት በፌዴራልና በክልል መንግስታት መገንባታቸው ተገለጸ 👉 5 ሚሊዮን ተማሪዎች ከመነሻው መሰረታዊ እውቀት እንዲያገኙ መደረጉ ተነስቷል ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ማብራሪያና ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ፣ ከትምህርት ጋር በተያያዘ ፍኖተ ካርታውና የትምህርት ስርዓቱ መቀየሩን ተከትሎ በዘርፉ ለውጥ እየመጣ መሆኑን አስታውቀዋል። በመንግስት የትምህርት ፖሊሲና ስርዓት ላይ የተደረገው ለውጥ ህጻናትን ከመጀመሪያው በመሰረታዊ እውቀት ለማብቃት ያለመ ነው ብለዋል። በዚህም መሰረት በፌዴራልና በክልል መንግስታት 35 ሺሕ የህጻናት መዋያ ተቋማት መገንባታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በእነዚህ ተቋማት አማካኝነት 5 ሚሊዮን ተማሪዎች ከመነሻው ጀምሮ መሰረታዊ እውቀትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት እንዲያገኙ መደረጉን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ መሰረታዊ ስራ ከ20 ዓመታት በኋላ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተጨባጭና ዘላቂ ለውጥ እንደሚያመጣ ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪ የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የሞዴል ቦርዲንግ ትምህርት ቤቶችን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር 50 ሞዴል አዳሪ ትምህርት ቤት መገንባቱ ጠቁመዋል። የፈተና ስርዓትን ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር ለማዘመን በተያዘው አቅጣጫም ከጥቂት ዓመታት በኋላ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና 90 በመቶ በዲጂታል እንደሚሰጥ ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የመምህራንን የማስተማር አቅም ለማሳደግ የስልጠና ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆናቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የፍኖተ ካርታና የስርዓት ለውጡ በትምህርት ዘርፉ አዎንታዊ ለውጥ ማስገኘቱን ለምክር ቤቱ አስገንዝበዋል። በወልደሐዋርያት ዘነበ #አሐዱ_ሬዲዮ_94.3 #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

Open in Telegram
Views432−2%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#26070Text

በጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ መስራትና በአንድ ቋንቋ መቆም እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)   አሳሰቡ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ የጸጥታ ችግሮች ቢኖሩም ከቀደመው ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ መሻሻልና እድገት መኖሩን ገልጸው፣ የቀሩ ጉዳዮችን በጋራና በትብብር ለመፍታት መስራት እንደሚያስፈልግ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኃላፊነት በሚሰማው አካል ልክ በጉዳዩ ላይ «አንድ ቋንቋ» መናገር እንደሚገባ ያነሱ ሲሆን፣ ጥፋትና ጥቃት ሲከሰት የፖለቲካ አጀንዳ ከማድረግ ይልቅ በጋራ ማውገዝና መታገል እንደሚገባ አመልክተዋል። በንግግራቸውም በቅርቡ በአርሲ አካባቢ ሕዝብን ለማዳን ሲሉ የሕይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የፖሊስና የሚሊሻ አባላት መኖራቸውን ጠቅሰው፣ ቤተሰብና ልጆች ላሏቸው እነዚህ አካላት ተገቢው እውቅናና ክብር ካልተሰጣቸው ወደፊት ሕይወቱን የሚሰጥ አካል እንደማይገኝ አስጠንቅቀዋል። በአርሲ የአመራር ለውጥ መደረጉን፣ ሕዝባዊ ውይይቶች መካሄዳቸውን፣ ራስን ከጥቃት የመጠበቅ አሰራር መዘርጋቱን  እንዲሁም ወንጀለኞችን ለሕግ ለማቅረብ ጥረት መደረጉን ገልጸው፣ የጸጥታ ኃይሎችም ዋጋ መክፈላቸውን ጠቁመዋል። በተመሳሳይ በአማራ ክልል በጎጃም አካባቢም የአካባቢ ሚሊሻና ፖሊስ ሕዝብን ለመጠበቅ ሲሉ ሕይወታቸውን እያጡ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሕዝብን የሚጠብቀው ራሱ ሕዝብና የጸጥታ ኃይሉ እንጂ ከሌላ ቦታ መጥቶ የሚሞት እንደማይኖር ተናግረዋል። ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በሚኖርበትና በመንደር በተበታተነ ሀገር ውስጥ በእያንዳንዱ ቀበሌና ቤት መቆም እንደማይቻል የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ዘላቂ መፍትሔው ሕዝቡና የጸጥታ ተቋማት ተናበውና መረጃ ተለዋውጠው ጥቃት የሚፈጽሙ አካላትን በጋራ መከላከል መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህንንም በ«አውቶኢሚዩን ዲዚዝ» (በሰውነት ውስጥ ሆኖ የሚያጠቃ በሽታ) በመምሰል ገልጸውታል። አክለውም በብሔር የተሞከረው ሙከራ እንዳልተሳካ ሁሉ በእምነትም ሊሳካ እንደማይችል ጠቅሰው፣ የጸጥታ ኃይሎች ጥፋተኛን ሲገድሉ «ጥፋተኛ ነው፣ አሸባሪ ነው፣ ሕዝብን ይጎዳል» በሚል በአንድ ድምጽ መቆም እንደሚገባ አሳስበዋል። የትኛውም ሀገር መንግሥት የጸጥታ ችግሮችን ሙሉ በሙሉ ብቻውን ሊቆጣጠር እንደማይችል በምሳሌ ጠቅሰዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጨረሻም በትብብርና በቅንጅት በመስራት ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ተስፋቸውን ገልጸዋል። በሊዲያ አበበ #አሐዱ_ሬዲዮ_94.3 #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

Open in Telegram
Views409−7%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#26067Photo

ሚኒስትሮች ወደ ሁርሶ ስልጠና የገቡት ሰው ለመሆን፣ ሀገርን ለመውደድና ሰንደቅ ዓላማን ለማክበር እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ሹመትና ሥልጣን የሰውን ጠባይ ሊቀይር እንደሚችል የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ስልጠናው አገልጋይነትን ለማስረጽ፣ ቀላል የሚመስሉ ስራዎችን ጨምሮ መሠረታዊ ሕይወትን ለመለማመድ እንዲሁም በአካልና በስትራቴጂ ለመዘጋጀት የተሰጠ መሆኑን አስረድተዋል። የሁርሶ ስልጠና ዋና ዓላማ ዜጎችን ማዋጋት ሳይሆን ዜጎች «ሰው» እንዲሆኑ ማድረግ መሆኑን ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ወላጆችም ልጆቻቸው የተበላሸ ትውልድ እንዳይሆኑ በወታደራዊና በሥነ-ምግባር አሰልጥነው እንዲያሳድጓቸው መክረዋል። አክለውም አንዳንድ ባለሥልጣናት በስልጠናው ካገኙት ልምድና በሀገር ፍቅር ስሜት ባህሪያቸውን ማስተካከላቸውን ገልጸው፣ ጉዳዮችን ከሌሎች ሀገራት የግዳጅ ወታደራዊ ሰልጠናዎች ጋር ማቀራረብ ብዙም ፋይዳ እንደሌለው አመልክተዋል። በሊዲያ አበበ #አሐዱ_ሬዲዮ_94.3 #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

Open in Telegram
Views395−10%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#26066Photo

"ዐድዋን እንደግመዋለን" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ኢትዮጵያ የሱ 35 የጦር ጄቶችን የታጠቀችው ሉዓላዊነቷንና የቀጣናውን ደህንነት ለማስጠበቅ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "አድዋን እንደግመዋለን ሲሉ ገለፀው፣ ማንም ሲሉ የጠሩትን ኃይል ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መጥቶ በክብር መመለስ እንደማይችል" ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። ኢትዮጵያ የራሷን ሉዓላዊነትና የቀጣናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ዘመናዊ የሱ-35 የጦር ጄቶችን መታጠቋንም አስታውቀዋል። እነዚህን ዘመናዊ የአየር ኃይል ቴክኖሎጂዎች የታጠቀችው በዋናነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ደህንነቷንና እና ሉዓላዊነቷን ለማስከበር እንዲሁም ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማረጋገጥ መሆኑን ተናግረዋል። ይህም ማንኛውንም የውጭ ጥቃት አስቀድሞ ለመከላከል ፣ የሀገሪቱን የአየር ክልል በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ እና ለአፍሪካ ቀንድ የጋራ ሰላምና ደህንነት አስተዋጽኦ ለማበርከት መሆኑን ገልጸዋል። ዘመናዊ የጦር ጄቶችን ከመታጠቅ ባሻገር ይህን አቅም በዘላቂነት ለመጠቀምና ውጤታማ ለማድረግ ኢትዮጵያ በቀጣይ ትኩረት ሰጥታ ልትሰራባቸው የሚገቡ ቁልፍ ተግባራት መኖራቸውንም ጠቁመዋል። በደረጀ መንግስቱ #አሐዱ_ሬዲዮ_94.3 #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

Open in Telegram
Views368−17%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—

All posts

Connections