«አብዛኞቹ ነጋዴዎች ጊዜያቸውን በግብር ስወራ ላይ ያሳልፋሉ» - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የሚገኙ አብዛኞቹ ነጋዴዎች ብዙውን ጊዜያቸውን በግብር ስወራ እንደሚያሳልፉ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ፣ የገቢ ግብር በዝቷል ሲሉ ከምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው። በሀገሪቱ ግብር የሚከፍሉት ጥቂት ሰዎች ብቻ መሆናቸውን ያነሱት ዶ/ር ዐቢይ፣ ይህ አካሄድ ትክክል አለመሆኑን አስገንዝበዋል። የነጋዴዎች ቁጥርም ከመንግሥት ሠራተኛው ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ ዋነኛ ግብር ከፋዮች የመንግሥት ልማት ድርጅቶች መሆናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው ተናግረዋል። የንግዱ ማኅበረሰብ ግብር መክፈልን የሥልጣኔ መገለጫ አድርጎ መውሰድ እንዳለበት ያሳሰቡት ዶ/ር ዐቢይ፣ ማንኛውም ዜጋ ሥራ በሠራ ቁጥር ግብር መክፈልን ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባው አመልክተዋል። የሀገሪቱን የልማት ፍላጎት ለማሟላትም የገቢ ግብር አሰባሰቡ አሁን ካለበት ደረጃ ይበልጥ መስፋትና መጠናከር እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። ለዓለም አሰፋ ኀዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም
Open in Telegram
Ethio Fm 107.8
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 25, 2026 | 1,101 |
| Nov 26, 2026 | 371 |
Most viewed this month
- 01Views1.29KForwards—Reactions2Comments—
- 02Views1.07KForwards—Reactions1Comments—
- 03Views1.07KForwards—Reactions—Comments—
- 04Views974Forwards—Reactions—Comments—
Latest posts
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ግብር አከፋፈልና ገቢ መሰወር ተናገሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በሚኖርባት ኢትዮጵያ ግብር የሚከፍሉ ሰዎች ቁጥር 10 ሺህ እንኳ እንደማይሞላ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ፣ ስለ ነጋዴው ማኅበረሰብ የግብር ጫና ቅሬታና ገቢን ስለሚሸሽጉ ነጋዴዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ ነው። ግብር የማይከፍሉ ኃይሎች ጥቂቶች መሆናቸውን የጠቀሱት ዶ/ር ዐቢይ፣ አርሶ አደሮችም እስካሁን በቂ ግብር እየከፈሉ እንዳልሆነ ጠቁመዋል። ማንኛውም ሰው ለሠራው ሥራ እንደየደረጃው ግብር መክፈል እንዳለበት ያሳሰቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ግብር መክፈል ክብር መሆኑን ዜጎች ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል። ተጨማሪ ሥራ በሠሩ ልክ የሚጋራ የሀብት መጠንም እንዳለ ማወቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። አብዛኞቹ ነጋዴዎች ግብር በመሰወር ሥራ ላይ እንደሚሰማሩ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ ችግር በአሠራር ሊስተካከል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። አቤል እስጢፋኖስ ኀዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም
Open in Telegramየኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከሰሃራ በታች ሦስተኛ ሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ሁለት መቶ አስር ቢሊየን ዶላር መድረሱን አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው። በዚህም ኢትዮጵያ በቀጠናው ትልቋ ኢኮኖሚ ስትሆን፣ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ደግሞ ከደቡብ አፍሪካና ከናይጄሪያ ቀጥሎ ሦስተኛ ሆናለች። ቁጥሩ የተገኘው ከአሥራ አንድ ዓመታት በኋላ በተደረገ የኢኮኖሚ ክለሳ ነው። ክለሳው ከዓለም ባንክና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ጋር በቅርብ በመሥራት የተከናወነ ሲሆን፣ ቀደም ሲል ያልተቆጠሩ የዲጂታል ኢኮኖሚን፣ የሞባይል ገንዘብን፣ የኮሪደር ልማትን፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን፣ የታዳሽ ኃይልንና የኮንፈረንስ ቱሪዝምን አካትቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከቀረቡት ሦስት አማራጮች እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት መመረጡንና አሁንም ሰፊ መደበኛ ያልሆነ ኢኮኖሚ እንዳለ ጠቁመዋል። ልዑል ወልዴ ኀዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም
Open in Telegramየኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽን ትርፉ ከ3.4 ቢሊየን ብር ወደ 43 ቢሊየን ብር ማደጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ የኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽን ከጥቂት ዓመታት በፊት ያመጣው ከነበረው 3 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር አካባቢ ትርፍ ዛሬ ወደ 43 ቢሊየን ብር ማደጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ7ኛው የምክር ቤቱ 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ከሁለትና ሦስት ዓመታት በፊት በውጭ ማኔጅመንት ኮንትራት ይተዳደር የነበረው ኮርፖሬሽኑ ዕዳውን መክፈል ቀርቶ የሠራተኛ ደሞዝ መክፈል የማይችልበት ደረጃ ላይ እንደነበር አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድን የምታስተዳድር ሀገር የባቡር ኮርፖሬሽኗን ማስተዳደር አይሳናትም በሚል በተካሄደው የሪፎርም ሥራም፣ የኤሌክትሪክና የነዳጅ ባቡር ጎታች ሞተሮች ከ11 ወደ 36፣ ጋሪዎች ከ560 ወደ ከአንድ ሺህ በላይ ማደጋቸውን አስረድተዋል። በዚህም በዓመት ይስተናገድ የነበረው የመንገደኞች ቁጥር ከ198 ሺህ ወደ 588 ሺህ፣ የጭነት አቅሙም ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ቶን ወደ 4 ነጥብ 3 ሚሊየን ቶን ከፍ ማለቱንና የባቡሩ ፍጥነትም በሰዓት ከ37 ወደ 55 ኪሎ ሜትር ማደጉን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ቢያንስ 95 በመቶ የቡና ወጪ ንግድ እና 25 በመቶ ገደማ የማዳበሪያ ገቢ ንግድ በባቡር እየተከናወነ መሆኑንም አክለዋል። በተጨማሪም ሰበታ አካባቢ ከ15 ኪሎ ሜትር በላይ የባቡር መንገድና የመጫኛ ማውረጃ ወደብ በራስ አቅም መገንባቱን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ እንዲሁም ከኮምቦልቻ እስከ ሃራ ገበያ ያሉ መስመሮችን በሁለት የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች የመገንባትና የመጠገን ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል። በመተሐራ አካባቢ በመሬት መንቀጥቀጥና በዝርፊያ የፈረሱ ድልድዮችንና መስመሮችን ጨምሮ እስካሁን ወደ 100 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ሥራ መጠናቀቁንና ቀሪውም ከአንድ ዓመት ተኩል ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ተናግረዋል። ልዑል ወልዴ ኀዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም
Open in Telegramያልተካሄደው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ጊዜ እንዲገለጽ እና የፕሬስ ነጻነት ትኩረት እንዲያገኝ በምክር ቤቱ ጥያቄ ቀረበ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበ ጥያቄ፣ በሕገ-መንግሥቱ መሠረት በየአሥር ዓመቱ መካሄድ የነበረበትና ያልተካሄደው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ መቼ እንደሚደረግ እንዲገለጽ፣ እንዲሁም የፕሬስና የፖለቲካ ነጻነት መስፋት ጉዳይ በፕሬዝዳንቱ ንግግርና ሞሽን ውስጥ እንዲካተት ተጠየቀ። የምክር ቤት አባሉ በንግግራቸው፣ ሕገ-መንግሥቱ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በየአሥር ዓመቱ እንዲካሄድ ቢደነግግም ከ1997 ዓ.ም በኋላ በ2007 ዓ.ም መካሄድ የነበረበት ቆጠራ አለመካሄዱን አስታውሰዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የበጀት ቀመር ለማውጣት፣ ፍትሐዊ የበጀት ድልድል ለማድረግ፣ የልማት ዕቅዶችን ለመንደፍ እና የምርጫ ክልሎችን አከላለል ለመወሰን መነሻ የሚያደርገው ይህንኑ ቆጠራ መሆኑን የገለጹት ተናጋሪው፤ ቆጠራው አለመካሄዱ ፍትሐዊነትን እንደሚያጓድልና የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታውን እንደሚያቀጭጭ አስገንዝበዋል። በመሆኑም ቆጠራው መቼ እንደሚካሄድ በፕሬዝዳንቱ ንግግርና ሞሽን ውስጥ ተካቶ ምላሽ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል። በተያያዘም በቅርቡ የተካሄደው ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በጥሩ ሁኔታ ቢጠናቀቅም በርካታ ሕጸጾች እንደነበሩበት ተናጋሪው ጠቅሰዋል። የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ከፖለቲካና ከፕሬስ ነጻነት መስፋት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ መሆኑን አንስተው፣ ነጻው ፕሬስ እንደ አራተኛ መንግሥት የመብት ጥሰቶችን በማጋለጥና የመንግሥት ተጠያቂነት እንዲኖር በማድረግ ረገድ ድርሻውን እንዲወጣ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል። ይሁን እንጂ የመንግሥት ወይም የፐብሊክ ሚዲያዎች መንግሥትን ከመቆጣጠርና ዲሞክራሲን ከመገንባት ይልቅ የመንግሥት አፈ ቀላጤ ሆነው መቀጠላቸው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ እንዳይጎለብትና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ጥረቱ እንዳይጠናከር እያደረገ ነው ሲሉ ተችተዋል። ስለሆነም የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ፣ የፖለቲካ ነጻነትና የፕሬስ ነጻነት መስፋት ጉዳይ በፕሬዝዳንቱ ንግግር ተካቶ የመንግሥት የትኩረት ማዕከል እንዲሆን ጠይቀዋል። ልዑል ወልዴ ኀዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም
Open in Telegramበተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚታዩ የጸጥታ ችግሮች እና የኮሬ ሕዝብ ጉዳይ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው በምክር ቤቱ ተጠየቀ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ዶ/ር አወቀ አምዛዬ በምክር ቤቱ ባደረጉት ንግግር፣ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተባባሱ የመጡ የጸጥታ ችግሮችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ በተለይም የኮሬ ሕዝብ እያጋጠመው ያለው አደጋ በፕሬዝዳንቱ ንግግርና ሞሽን ውስጥ ተካተው አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠየቁ። የምክር ቤት አባሉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከሰኔ 2017 እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ገጽ 21 ላይ የሰፈረውን መረጃ በመጥቀስ፣ በበጀት ዓመቱ የሕገ-መንግሥቱ ምዕራፍ ሦስት አንቀጽ 14፣ 15፣ 16 እና 17 ተጥሰው የዜጎች በሕይወት የመኖር መብት አደጋ ላይ መውደቁን አንስተዋል። በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ ኢመደበኛ ታጣቂ ቡድኖችና ጸረ-ሰላም ኃይሎች የሚፈጸሙ የንጹሐን ግድያዎች፣ የአካል ጉዳቶች፣ የንብረት ዝርፊያ እና የመንገድ መዝጋት ድርጊቶች የዜጎችን ሰላማዊ ኑሮና ህልውና ማናጋታቸውን ገልጸዋል። እነዚህ ችግሮች በአማራ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ፣ አርሲ፣ ሞያሌ እና የምዕራብ ጉጂ አዋሳኝ አካባቢዎች፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሶዶና አበሽጌ እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ (አማሮ) እና ቡርጂ ዞኖች በከፍተኛ ደረጃ መባባሳቸውን ጠቁመዋል። በተለይም አነስተኛ ቁጥር ያለው የኮሬ ሕዝብ ላለፉት 11 ዓመታት በተከታታይ በጽንፈኛ ታጣቂዎች እየተወረረ ህልውናው አደጋ ላይ መውደቁን የገለጹት ዶ/ር አወቀ፣ የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ የተሰማሩ የደቡብ ክልል ፖሊስና የጸጥታ አካላትም ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈሉ መሆኑን አስረድተዋል። የምክር ቤት አባሉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት ቀጥተኛ ጥያቄም፣ የኮሬ ሕዝብ ለ11 ዓመታት ሲጨፈጨፍና ህልውናው አደጋ ላይ ሲወድቅ መንግሥት ጉዳዩን ለምን ችላ እንዳለ እና የሕዝቡ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ምን እንደሆነ ማብራሪያ ጠይቀዋል። ልዑል ወልዴ ኀዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም
Open in TelegramConnections
Similar channels
Capitalethiopia@capitalethiopiaNews and media18.1K
Addis Standard@addisstandardengNews and media19.2K
AHADU RADIO FM 94.3@ahaduradioNews and media17.4K
The Reporter (Ethiopian Reporter English)@thereporterethiopiaNews and media17.2K
CHANNEL 29@channel29newsNews and media20.5K
FIDEL POST NEWS@tesfaget55News and media15.5K
Addis Standard Amharic@addisstandardamhNews and media21.9K
Ethiopian News Agency@ethiopiannewsaNews and media22.4K