ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአርሲ ስለሚፈጸሙ ጥቃቶችና ስለ መንግሥት እርምጃ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው በአርሲ አካባቢ ስለሚደርሰው ተደጋጋሚ የንጹሐን ዜጎች ሞትና መንግሥት ስለወሰዳቸው እርምጃዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በአርሲ ንጹሐን ዜጎች ሲገደሉ ሁሉም በጋራ ሊያወግዘው እንደሚገባ በማሳሰብ፤በጋራ ከታገልን ችግሩንና ፈጻሚዎቹን ማጥፋት እንደሚቻል ገልጸዋል። በአካባቢው የንጹሐንን ሕይወት ለማዳን ሲሉ በርካታ ሚሊሻዎችና ፖሊሶች መስዋዕትነት መክፈላቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ነገር ግን ስለእነዚህ የጸጥታ አካላት መስዋዕትነት የሚናገር አካል አለመኖሩን ጠቁመዋል። እነዚህን ሕይወታቸውን የሰጡ ጀግኖች የማናመሰግን ከሆነ ነገ ለሀገርና ለሕዝብ የሚሞት ሰው ይጠፋል ሲሉም አስጠንቅቀዋል። በአካባቢው ያለውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት መንግሥት የአመራር ለውጥ ማድረጉንና ሕዝቡን አወያይቶ የማስታጠቅ ሥራ መሥራቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስታውቀዋል። አክለውም ጥቃቱ በሚፈጸምበት ወቅት ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት የት አለ?›› የሚሉ ጥያቄዎች እንደሚነሱ በመጥቀስ፤መንግሥት በሁሉም ቦታ በአንድ ጊዜ መገኘት እንደማይችልና ሕዝቡ ራሱን በመጠበቅ ረገድ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። አቤል እስጢፋኖስ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም
Открыть в Telegram
Ethio Fm 107.8
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 25 нояб. 2026 г. | 1 101 |
| 26 нояб. 2026 г. | 618 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры1,29 тыс.Пересылки—Реакции2Комментарии—
- 02Просмотры1,07 тыс.Пересылки—Реакции1Комментарии—
- 03Просмотры1,07 тыс.Пересылки—Реакции—Комментарии—
- 04Просмотры974Пересылки—Реакции—Комментарии—
Новые посты
ምክር ቤቱ የቀረበለትን የድጋፍ ሞሽን አፀደቀ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የቀረበውን የ2019 የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫ የድጋፍ ሞሽን አጽድቋል። 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል። በፕሬዚዳንቱ የቀረበውን ሞሽን መነሻ በማድረግ ከምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተውባቸዋል። ምክር ቤቱም የቀረበለትን የድጋፍ ሞሽን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ኀዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም
Открыть в Telegramበ12 የኢትዮጵያ ወረዳዎች የተተገበረው የሰላም ግንባታ ፕሮጀክት ተጨባጭ ውጤት ማምጣቱ ተገለጸ በትግራይ፣ በአማራ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በሚገኙ 12 ወረዳዎች ባለፉት ሁለት ዓመታት የተተገበረው ‹‹ውጥረቶችን የማርገብ ፕሮጀክት››በግጭት የተጎዱ ማህበረሰቦች እንዲያገግሙና ሰላማዊ አብሮ መኖር እንዲጠናከር ማስቻሉ ተገልጿል። በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍና በዎርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ አስተባባሪነት የተከናወነው ይህ ፕሮጀክት፤ከ16 ሺህ በላይ ዜጎች የስነ-ልቦና ማገገሚያ ድጋፍ እንዲያገኙ ሲያደርግ፣ ለ4መቶ60 ተጎጂዎች ደግሞ የ4.8 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል ተብሏል። በተጨማሪም 1 ሺህ 2መቶ የወጣት የሰላም አምባሳደሮችን በማሰልጠንና 36 የውይይት መዋቅሮችን በማቋቋም ዘጠኝ የጋራ መገልገያ ተቋማት በህብረተሰቡ ትብብር እንዲገነቡና እንዲታደሱ ማስቻሉ ተጠቅሷል። የዎርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ዳይሬክተር ካርመን ቲል ‹‹ማህበረሰቦች የሰላም ተቀባዮች ብቻ ሳይሆኑ የሰላም መሃንዲሶች ናቸው›› ሲሉ የተፈጠሩት መዋቅሮች ዘላቂ ሰላምን ለማስቀጠል እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል። ሐመረ ፍሬዉ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም
Открыть в Telegramኪም ጆንግ ኡን ሰሜን ኮሪያ የታክቲካል ኒውክሌር ጦር መሣሪያዎችን ስርጭት እንድታሰፋ መመሪያ ሰጡ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፤ሀገራቸው የታክቲካል ኒውክሌር ጦር መሣሪያዎችን ለተለያዩ ወታደራዊ ተልዕኮዎች በተለያዩ የጦር ዘርፎች በማሰማራት ላይ እንድታተኩር ጥሪ ማቅረባቸውን የሀገሪቱ ብሔራዊ የዜና ወኪል ዘግቧል። መሪው የኒውክሌር ቁሳቁስ ማምረቻ እና የጦር መሣሪያ ምርምር ተቋማትን በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት፤የሀገሪቱ የኒውክሌር ቁሳቁስ የማምረት አቅም በስርዓት እየተስፋፋ ይገኛል። ሰሜን ኮሪያ በ2023 በሕገ መንግሥቷ ያጸደቀችው የኒውክሌር ባለቤትነት አቋም ‹‹ፈጽሞ የማይደፈር›› መሆኑን ያነሱት ኪም፤ ይህንን ዕውቅና ለመንፈግ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ እንደ ‹‹ግልጽ የጦርነት አዋጅ›› እንደሚቆጠር አስጠንቅቀዋል። በተጨማሪም የታክቲካል ኒውክሌር መሣሪያዎችን አጠቃቀም ማስፋፋት በድንበር አካባቢ ከተጋረጠው ወታደራዊ ስጋት አንጻር ‹‹አንገብጋቢ እና ወቅታዊ ተግባር››መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህ ማስጠንቀቂያ የተሰማው መስከረም 21 በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ በሆነው ቀጣና በደረሰ የፈንጂ ፍንዳታ ሦስት የደቡብ ኮሪያ ወታደሮች መቁሰላቸውን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት ባየለበት ወቅት ነው። የደቡብ ኮሪያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጋራ አጣሪ ኮሚቴ ፈንጂዎቹ በሰሜን ኮሪያ መቀበራቸውን ካረጋገጠ በኋላ ሴኡል ይፋዊ ይቅርታ ብትጠይቅም፤ ፒዮንግያንግ ክሱን ውድቅ በማድረግ ወደ ጃፓን ባሕር 10 ያህል የአጭር ርቀት ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏ ተገልጿል። ሳራ ዮሐንስ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም
Открыть в Telegram«አብዛኞቹ ነጋዴዎች ጊዜያቸውን በግብር ስወራ ላይ ያሳልፋሉ» - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የሚገኙ አብዛኞቹ ነጋዴዎች ብዙውን ጊዜያቸውን በግብር ስወራ እንደሚያሳልፉ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ፣ የገቢ ግብር በዝቷል ሲሉ ከምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው። በሀገሪቱ ግብር የሚከፍሉት ጥቂት ሰዎች ብቻ መሆናቸውን ያነሱት ዶ/ር ዐቢይ፣ ይህ አካሄድ ትክክል አለመሆኑን አስገንዝበዋል። የነጋዴዎች ቁጥርም ከመንግሥት ሠራተኛው ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ ዋነኛ ግብር ከፋዮች የመንግሥት ልማት ድርጅቶች መሆናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው ተናግረዋል። የንግዱ ማኅበረሰብ ግብር መክፈልን የሥልጣኔ መገለጫ አድርጎ መውሰድ እንዳለበት ያሳሰቡት ዶ/ር ዐቢይ፣ ማንኛውም ዜጋ ሥራ በሠራ ቁጥር ግብር መክፈልን ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባው አመልክተዋል። የሀገሪቱን የልማት ፍላጎት ለማሟላትም የገቢ ግብር አሰባሰቡ አሁን ካለበት ደረጃ ይበልጥ መስፋትና መጠናከር እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። ለዓለም አሰፋ ኀዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 230 |
| 3 ч | 687 |
- Через 1 час230
- Всего сейчас687
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ግብር አከፋፈልና ገቢ መሰወር ተናገሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በሚኖርባት ኢትዮጵያ ግብር የሚከፍሉ ሰዎች ቁጥር 10 ሺህ እንኳ እንደማይሞላ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ፣ ስለ ነጋዴው ማኅበረሰብ የግብር ጫና ቅሬታና ገቢን ስለሚሸሽጉ ነጋዴዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ ነው። ግብር የማይከፍሉ ኃይሎች ጥቂቶች መሆናቸውን የጠቀሱት ዶ/ር ዐቢይ፣ አርሶ አደሮችም እስካሁን በቂ ግብር እየከፈሉ እንዳልሆነ ጠቁመዋል። ማንኛውም ሰው ለሠራው ሥራ እንደየደረጃው ግብር መክፈል እንዳለበት ያሳሰቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ግብር መክፈል ክብር መሆኑን ዜጎች ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል። ተጨማሪ ሥራ በሠሩ ልክ የሚጋራ የሀብት መጠንም እንዳለ ማወቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። አብዛኞቹ ነጋዴዎች ግብር በመሰወር ሥራ ላይ እንደሚሰማሩ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ ችግር በአሠራር ሊስተካከል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። አቤል እስጢፋኖስ ኀዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 309 |
| 3 ч | 680 |
- Через 1 час309
- Всего сейчас680
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከሰሃራ በታች ሦስተኛ ሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ሁለት መቶ አስር ቢሊየን ዶላር መድረሱን አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው። በዚህም ኢትዮጵያ በቀጠናው ትልቋ ኢኮኖሚ ስትሆን፣ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ደግሞ ከደቡብ አፍሪካና ከናይጄሪያ ቀጥሎ ሦስተኛ ሆናለች። ቁጥሩ የተገኘው ከአሥራ አንድ ዓመታት በኋላ በተደረገ የኢኮኖሚ ክለሳ ነው። ክለሳው ከዓለም ባንክና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ጋር በቅርብ በመሥራት የተከናወነ ሲሆን፣ ቀደም ሲል ያልተቆጠሩ የዲጂታል ኢኮኖሚን፣ የሞባይል ገንዘብን፣ የኮሪደር ልማትን፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን፣ የታዳሽ ኃይልንና የኮንፈረንስ ቱሪዝምን አካትቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከቀረቡት ሦስት አማራጮች እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት መመረጡንና አሁንም ሰፊ መደበኛ ያልሆነ ኢኮኖሚ እንዳለ ጠቁመዋል። ልዑል ወልዴ ኀዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 361 |
| 4 ч | 686 |
- Через 1 час361
- Всего сейчас686
Динамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 338 |
| 4 ч | 644 |
- Через 1 час338
- Всего сейчас644
የኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽን ትርፉ ከ3.4 ቢሊየን ብር ወደ 43 ቢሊየን ብር ማደጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ የኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽን ከጥቂት ዓመታት በፊት ያመጣው ከነበረው 3 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር አካባቢ ትርፍ ዛሬ ወደ 43 ቢሊየን ብር ማደጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ7ኛው የምክር ቤቱ 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ከሁለትና ሦስት ዓመታት በፊት በውጭ ማኔጅመንት ኮንትራት ይተዳደር የነበረው ኮርፖሬሽኑ ዕዳውን መክፈል ቀርቶ የሠራተኛ ደሞዝ መክፈል የማይችልበት ደረጃ ላይ እንደነበር አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድን የምታስተዳድር ሀገር የባቡር ኮርፖሬሽኗን ማስተዳደር አይሳናትም በሚል በተካሄደው የሪፎርም ሥራም፣ የኤሌክትሪክና የነዳጅ ባቡር ጎታች ሞተሮች ከ11 ወደ 36፣ ጋሪዎች ከ560 ወደ ከአንድ ሺህ በላይ ማደጋቸውን አስረድተዋል። በዚህም በዓመት ይስተናገድ የነበረው የመንገደኞች ቁጥር ከ198 ሺህ ወደ 588 ሺህ፣ የጭነት አቅሙም ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ቶን ወደ 4 ነጥብ 3 ሚሊየን ቶን ከፍ ማለቱንና የባቡሩ ፍጥነትም በሰዓት ከ37 ወደ 55 ኪሎ ሜትር ማደጉን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ቢያንስ 95 በመቶ የቡና ወጪ ንግድ እና 25 በመቶ ገደማ የማዳበሪያ ገቢ ንግድ በባቡር እየተከናወነ መሆኑንም አክለዋል። በተጨማሪም ሰበታ አካባቢ ከ15 ኪሎ ሜትር በላይ የባቡር መንገድና የመጫኛ ማውረጃ ወደብ በራስ አቅም መገንባቱን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ እንዲሁም ከኮምቦልቻ እስከ ሃራ ገበያ ያሉ መስመሮችን በሁለት የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች የመገንባትና የመጠገን ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል። በመተሐራ አካባቢ በመሬት መንቀጥቀጥና በዝርፊያ የፈረሱ ድልድዮችንና መስመሮችን ጨምሮ እስካሁን ወደ 100 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ሥራ መጠናቀቁንና ቀሪውም ከአንድ ዓመት ተኩል ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ተናግረዋል። ልዑል ወልዴ ኀዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 364 |
| 4 ч | 703 |
- Через 1 час364
- Всего сейчас703
Динамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 332 |
| 4 ч | 569 |
- Через 1 час332
- Всего сейчас569
Связи
Похожие каналы
Capitalethiopia@capitalethiopiaНовости и СМИ18,1 тыс.
Addis Standard@addisstandardengНовости и СМИ19,2 тыс.
AHADU RADIO FM 94.3@ahaduradioНовости и СМИ17,4 тыс.
The Reporter (Ethiopian Reporter English)@thereporterethiopiaНовости и СМИ17,2 тыс.
CHANNEL 29@channel29newsНовости и СМИ20,5 тыс.
FIDEL POST NEWS@tesfaget55Новости и СМИ15,5 тыс.
Addis Standard Amharic@addisstandardamhНовости и СМИ21,9 тыс.
Ethiopian News Agency@ethiopiannewsaНовости и СМИ22,4 тыс.