Account
አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

የአቡ ዩስራ ንጽጽራዊ ሀይማኖት ላይ ያተኮሩ የፁሁፍና የድምጽ ስራዎች ይቀርቡበታል።

Username
@abuyusra3
Category
Religion
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers5,460+8 in 1 day
Avg views per post, 7d653−76.4% vs prev 7d
ERR11.95%last 7 days

Subscribers, 30 days

Nov 27 – Nov 28+8 (+0.1%)

Show as table
DateSubscribers
Nov 27, 20265,452
Nov 28, 20265,460

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 10, 20263,020
Nov 11, 20262,280
Nov 12, 20262,145
Nov 14, 20262,003
Nov 19, 20261,430
Nov 21, 20264,100
Nov 23, 2026719
Nov 24, 2026585
Nov 28, 2026589

Most viewed this month

  1. 01

    ክርስቲያን ወገኖቻችን፣ በዚህ የቲዎሎጂ ትንታኔ በእውነት ትስማማላችሁን? ​ሰሞኑን እኔና ወንድሜ የሕያ «የጽልመቱ ጥላ» ለተባለው መጽሐፍ ምላሽ እንዳዘጋጀን ይታወቃል። ጸሐፊው መጽሐፉን ያዘጋጀው እስልምናን ለመተቸትና ለማጥቃት አስቦ ቢሆንም፣ በሒደቱ ግን ባላሰበው መንገድ የራሱን የክርስትና እምነት መሠረታዊ አስተምህሮዎች ደጋግሞ ገደል ሲከታቸው ታዝበናል። ​ከእነዚህም ውስጥ አንዱን ለክርስትና እምነት ተከታዮች ለሚዛናዊ ፍርድ (ለጥያቄ) ማቅረብ ወደድን። ​በዮሐንስ ወንጌል 1፡29 ላይ «የእግዚአብሔር በግ» የሚለው ቃል ለድኅነት፣ ለሕይወት እና ለኃጢአት ስርየት የሚውል መሆኑን እንደምታምኑ ይታወቃል። ነገር ግን በእናንተ ስም ይሟገታል የተባለው ይህ "አፖሎጂስት"፣ ይህንን ክርስቶስ የተመሰለበትን «ቅዱስ በግ»፣ አንዲት አይሁዳዊት ሴት ነቢዩን ሙሐመድን (ﷺ) ለመግደል በቂም በቀል ካዘጋጀችውና በመርዝ ከተለወሰው የበግ ሥጋ ጋር አመሳስሎታል! ​ያቀረበውን ሎጂክ ስንመለከት፣ «ኢየሱስም የእግዚአብሔር በግ ተብሏል፣ ሴትዮዋም ያመጣችው የበግ ሥጋ ነው» ከሚል እጅግ የወረደ የቃላት ማነጻጸሪያ የመነጨ ነው። በእሱ መነጽርና ትንታኔ፣ ለዓለም ቤዛ ነው ተብሎ የሚታመነው «የእግዚአብሔር በግ»፣ ሰውን ገድሎ ከሚያሰቃይ የቂም በቀል መርዝ ጋር አንድ ዓይነት አምሳያ ተደርጎ ቀርቧል ማለት ነው። ​እዚህ ላይ ክርስቲያን ወገኖቻችንን በጨዋነት መጠየቅ የምንፈልገው፦ በእውነት ይህ ሰው እናንተንና የክርስትናን ቲዎሎጂ ወክሎ ነው የሚሟገተው? እናንተስ ለድኅነት ነው ብላችሁ የምታምኑትን «የክርስቶስን የማዳን ሥራ» ከሴረኛ መርዝ ጋር አመሳስሎ የሚያቀርብን አስተምህሮ ትቀበላላችሁን? ወይስ እስልምናን ለመተቸት ሲባል ብቻ የራሳችሁን እምነት ክብር ዝቅ ሲያደርግ ዝምታን ትመርጣላችሁ? ​ይህ ሰው በዚህ የተንሸዋረረ ሎጂኩ ከቀጠለ፣ ነገ በ«ቅዱስ ቁርባን» ጊዜ "የአምላክ ሥጋ ነው" ተብሎ ለምእመኑ የሚሰጠውን ቅዱስ ነገር፣ ከገዳይ መርዝ ጋር እንዳያመሳስልባችሁ ሥጋት አለን። እንዲህ ያለ የራሱን መሠረት የሚያፈርስ ጠበቃ ላለው እምነት፣ በእውነት ሌላ የውጭ ተቺ አያስፈልገውም። https://t.me/Abuyusra3 ​

    Text
    Views6.54K
    Forwards—
    Reactions39
    Comments—
  2. 02

    «መጽሐፉ የሚለውን ነው የተናገርነው»! - ከግብጹ ዘካርያስ ቡትሮስ እስከ ዛሬ የቲክቶክ ተሳዳቢዎች፤ ራሳቸው የቀሰቀሱት የዕውቀት ማዕበል! ታሪክ ራሱን ይደግማል፤ ሞኞች ግን ከታሪክ አይማሩም! ከዓመታት በፊት በግብፅ ምድር ዘካርያስ ቡትሮስ የተባለ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቄስ ተነሥቶ ነበር። እስከዚያን ጊዜ ድረስ የግብፅ ሙስሊሞች ጠንካራ የኦርቶዶክስ ማኅበረሰብ ባለበት ሀገር ውስጥ ቢኖሩም፣ በንጽጽራዊ ሃይማኖት ጥናት ላይ ብዙም ገፍተው የሚታወቁ አልነበሩም። ዘካርያስ ቡትሮስ ግን በቴሌቪዥን መስኮት እየወጣ እስልምናን እጅግ ጸያፍና ባለጌ በሆነ መንገድ መሳደብ ጀመረ። የግብፅ ሙስሊም ምሁራንና የሀገር ሽማግሌዎች ወደ ቤተክርስቲያኗ አባቶች ሄደው «ይህንን ሰውዬ ሥርዓት አስይዙት» በሚል ሲጠይቁ የቤተ ክርስቲያኗ ሰው የሰጡት ትዕቢት የተሞላበት ምላሽ አንድ ነበር፦ «እርሱ መጽሐፉ የሚለውን ነው የተናገረው እንጂ አዲስ ነገር አልተናገረም፤ መልስ ስጡት!» ያቺ ቀን በግብፅ ታሪክ ውስጥ ትልቅ የዕውቀት አብዮት የፈነዳባት ዕለት ሆነች! በዚያ ትዕቢት የተቀሰቀሱት የግብፅ ሙስሊሞች ከቋንቋቸው ተሻግረው መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎበታል የሚባልበትን ጥንታዊ ቋንቋ ዕብራይስጥን እና ግሪክን ጭምር አጥንተው በመውጣት፣ የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እያንዳንዱን ድርሳናት በማጥናት ቃል በቃል በትነው አደባባይ ላይ አሰጡት! ዛሬ በግብፅ ምድር አንድም የኦርቶዶክስ ሰባኪ በሙለ የራስ መተማመን ስለ እስልምና መተንፈስ ወደ ሚቸገርበት ደረጃ ተሸጋገሩ። በምዕራቡ ዓለም (በአሜሪካና በእንግሊዝ) የታየውም ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለም። እንደ ዴቪድ ዉድ እና ጄይ ስሚዝ ያሉ የምዕራቡ ዓለም ጸረ-ኢስላም ሰባኪያን በአብያተ ክርስቲያናት ድጋፍ «መረጃውን ነው የጠቀስነው» እያሉ እስልምናን ሲያንቋሽሹ፣ ምላሹ የሆነው በዓለም አቀፍ መድረኮች (እንደ Speakers' Corner ባሉ) የመጽሐፍ ቅዱስን ቴክስችዋል ክሪቲሲዝም እና የሥላሴን መሠረት-አልባነት የሚያጋልጡ ኃያላን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዳዒዎችና ተመራማሪዎች መፍለቅ ነው! ዛሬ በሀገራችን እየሆነ ያለውም የዚሁ ታሪክ ግልባጭ ነው! ጥቂት መድረኩ ላይ የተኮለኮሉ የቤተ ክርስቲያኗ ሰዎች እስልምናን በጸያፍ ቃላት ሲሳደቡ፣ ተከላካዮቻቸው የሚሰጡት ምላሽ ያው የግብጾቹን ቃል የኮረጀ ነው፦ «መጽሐፉን ነው የተናገረው እንጂ አዲስ ነገር አልተናገረም!» እውነቱን ለመናገር ይህንን የምጽፈው ስለ ጥቂት ተራ ባለጌ ግለሰቦች ተጨንቄ አይደለም፤ ነገር ግን እኛ የነዚህን ግለሰቦች ብልግና ችላ ብለን ባለፍንበት ሰዓት፣ የእነርሱ አክቲቪስትና መንጋ ግን ይህንን ጸያፍ ተግባር እንደ ታላቅ ጀግና አንሥቶ ሲወራጭበት አይቼ በመደመሜ ነው! የቤተክርስቲያኗ ምእመናን ምን ያህል በጥልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እየኖሩ እንዳሉ የሚያሳብቀውም ይኸው ነው፤ ተስፋ ከመቁረጣቸው የተነሣ ያገኙትን ይህንን የብልግና ዕድል ላለማባከን መከራቸውን እየበሉ መሆኑ በግልጽ ያስታውቃል። ነገር ግን እነዚህ ወገኖች የቀሰቀሱትን እሳት አላወቁትም! እኛ ወደ ኋላ የምንልበት አንዳችም ምክንያት የለም። ከዚህ በኋላ የቤተክርስቲያኗን ሥርዓተ ትምህርትና ጥንታዊ ድርሳናት (ከግእዝ የተተረጎሙትንም ያልተተረጎሙትንም) አደባባይ ላይ በማውጣት፣ ለተራ ስብከት ሳይሆን ከጥልቅ ምርምር ጋር አያይዞ ለምእመኑ እውነቱን የሚገልጥ፣ በእስልምና ዙሪያ የሚነሣውንም ማንኛውንም የሐሰት ክስ ቃል በቃል በትኖ መልስ የሚሰጥ ኃያል ትውልድ የሚነሣበት ዘመን ይመጣ ዘንድ ግን መደላድል እየፈተጠረ ነው! ከዚያ በኋላ ራሳቸው ያስነሡትን ይህንን የዕውቀት ማዕበል በደንብ መቋቋም ከቻሉ አብረን የምንመለከተው ይሆናል። ለወገኖቻችን የምነግራችሁ ትልቁ እውነት ግን አንድ ነው፦ ይህ የዛሬው ሁካታ ለመጪው ጊዜ እጅግ ትልቅ መደላደል፣ መነሻና የማንቂያ ደወል መሆኑን ፈጽሞ እንዳትረሱ! https://t.me/Abuyusra3

    Text
    Views4.61K
    Forwards—
    Reactions59
    Comments—
  3. 03

    No text

    Photo
    Views4.5K
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—
  4. 04

    No text

    Photo
    Views3.59K
    Forwards—
    Reactions13
    Comments—

Latest posts

#599Text
Views589−71%vs avg
Forwards—
Reactions64
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
3 h373
11 h589
  1. Total to date589
#597File
Views612−70%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#596Text

ዘገባው የሚለው እንዲህ ነው፦ ቀብሩ ተቆፍሮ የውስጠኛው ክፍል (ለሕድ) ሲደረስ፣ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በገዛ እጃቸው አፈሩን አስተካክለው፣ ፋጢማ ገና ወደ ቀብሩ ሳትወርድ በፊት እራሳቸው ወደ ባዶው ቀብር ገብተው ጋደም አሉና እንዲህ ብለው ዱዓ አደረጉ፦ «አላህ ሆይ! ሕይወትን የምትሰጥና የምትገድል ጌታ ሆይ! እናቴን ፋጢማ ቢንት አሰድን ማራት፣ መልሷን አግራላት፣ መግቢያዋንም (ቀብሯንም) አስፋላት...»   አስተውሉ! ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቀብሩ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ «እናቴን ፋጢማ ቢንት አሰድን ማራት» እያሉ ነው! ታዲያ በራሱ በዚህ ሐዲስ ውስጥ «እናቴ» ብለው እየጠሯት፣ ቄሱ ከየት አምጥቶ ነው «ሚስቱ እንድትሆን» ብሎ የቀጠፈው?! ሆን ብሎ ይህንን ክፍል ቆርጦ የደበቀው ቅጥፈቱ እንዳይጋለጥበት ነው።   ሎጂክ፣ ታሪክ እና የኢስላም ሕግ የሚመሰክሩት እውነት   ከቋንቋው ባለፈ የቄሱ ክስ በአንድ ጤነኛ አእምሮ ፊት እንመዝነው! ሀ/በአሊይ ኢብን አቢ ጧሊብ ፊት? የቀብር ሥነ-ሥርዓት የሚፈጸመው በብዙ መቶ ሰዎች ፊት በጠራራ ፀሐይ ነው። በፋጢማ ቀብር ላይ ደግሞ ጀግናው ልጇ አሊይ (ረ.ዐ)፣ ሌሎች ልጆቿ፣ ሙሃጂሮችና አንሷሮች በሙሉ ቆመው እያዩ ነበር። አንድ ሰው የገዛ እናቱን ያሳደገችውን እንስት በድን፣ በጀግናው ልጇ በአሊይና በሕዝብ ፊት እንዲህ ያለ አጸያፊ ተግባር ፈጸመ፣ አሊይም ዝም ብሎ አይቶ በኩራት አስተላለፈ ብሎ ማሰብ ምን ዓይነት የታመመ ጭንቅላት ይጠይቃል?! ለ/ የወቅቱ ጠላቶች የት ነበሩ? በመዲና ውስጥ ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ለማዋረድ ትንሽ ቀዳዳ የሚጠባበቁ ሙናፊቆች፣ የቁረይሽ ጣዖት አምላኪዎችና አይሁዳውያን ነበሩ። እንዲህ ያለ ነገር በሕዝብ ፊት ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ከ21ኛው ክፍለ ዘመን ቀጣፊ ቄስ በፊት እነርሱ ዓለምን ባናወጡት ነበር! ሐ/የኢስላም ሕግ፣ የሟች ክብር እና የቀብር አቆፋፈር፦ በኢስላም ጋብቻ «የጠበቀ ቃል ኪዳን» (ቁርኣን፣ ሱረቱ አን-ኒሳእ 4፡21) ሲሆን የሚጸናውም በሕይወት ባሉ ሰዎች መካከል በፈቃደኝነት ነው፤ በሞት ደግሞ ጋብቻ ይቋረጣል። የሟች አካል ክብር እጅግ የተጠበቀ በመሆኑ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) «የሞተን ሰው አጥንት መስበር ልክ በሕይወት እያለ እንደመስበር ነው» ብለዋል (ሱነን አቢ ዳውድ፣ ሐዲስ ቁ. 3207)። መ/ ከዚህም በላይ በኢስላም የቀብር ጉድጓድ (ለሕድ) የሚቆፈረው ለአንድ ሰው አካል ብቻ በጠባቡ እንጂ ሁለት ሰው አስተኝቶ የሚያስቀምጥ አይደለም (ሶሒሕ ሙስሊም፣ ሐዲስ ቁ. 966)። በሰፈሩት ቁና ይሰፈሩ   የሚገርመው ነገር፣ ዘካሪያ ቡትሮስ ኢስላም ላይ ሲሆን «ወሲብ» ብሎ የሚተረጉመው ይኸው «ኢድጠጀዐ» የሚለው የዐረብኛ ቃል፣ በራሱ በዐረብኛው መጽሐፍ ቅዱስ (Smith-Van Dyke Arabic Bible) ውስጥ እንዴት እንደተቀመጠ ስናይ ነው! 2ኛ ነገሥት 4፡32-34 ላይ ነቢዩ ኤልሳዕ የሞተውን ሕፃን ለማስነሳት ያደረገውን እንመልከት፦ «ኤልሳዕም ወደ ቤት በገባ ጊዜ እነሆ፥ ሕፃኑ ሞቶ በአልጋው ላይ ተጋድሞ (ሙድጠጂዐን) ነበር... ወጥቶም በሕፃኑ ላይ ተጋደመ (ወ-ኢድጠጀዐ ፈውቀስ-ሶቢይ)፥ አፉንም በአፉ ላይ፥ ዓይኖቹንም በዓይኖቹ ላይ፥ እጆቹንም በእጆቹ ላይ አደረገ፥ በእርሱም ላይ ተዘረጋ፤ የሕፃኑም ሥጋ ሞቀ።» (መጽሐፍ ቅዱስ፣ የ1954 ትርጉም)።   ተመልከቱ! 2ኛ ነገሥት 4፡34 ላይ ነቢዩ ኤልሳዕ በሞተ ሕፃን ላይ ተጋደመ ሲል የዐረብኛው መጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀመው ቃል ልክ ያንኑ «ኢድጠጀዐ» የሚለውን ቃል ነው! ያውም አፉን በአፉ ላይ፣ ዓይኑን በዓይኑ ላይ አድርጎ! ታዲያ ለነቢዩ ኤልሳዕ ሲሆን «ኢድጠጀዐ» ማለት «ተጋደመ» ሆኖ፣ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሲሆን ግን እንዴት ወደ አጸያፊ ተግባር ተቀየረ?! ይህ ዓይን ያወጣ ጥላቻ የፈጠረው መረዳት ብቻ ነው!   አዲስ የተጨመረ የሐሰት ማጣፈጫ   የብረት መዝጊያና ቁልፍ ያላቸው መቃብሮች የሐሰት ወሬ (Hoax)፦ «ሙስሊሞች የነቢዩን ሱና ተከትለው ሬሳ ስለሚደፍሩ ወላጆች የሴት ልጆቻቸውን ቀብር በብረት ቆለፉ» እያሉ ያሳዩት ፎቶ በሚያዝያ/ግንቦት 2023 በዓለም አቀፍ የመረጃ አጣሪዎች (AFP Fact Check፣ Alt News እና Boom Live) ውሸትነቱ የተጋለጠ የማኅበራዊ ሚዲያ ፈጠራ ነው! ያ ታዋቂው በብረት የታጠረ ቀብር ፎቶ የተነሳው ሕንድ፣ ሀይደራባድ (Darab Jung Colony, Hyderabad) ውስጥ ሲሆን፣ ቤተሰቦቹ ብረቱን የሠሩት በተጨናነቀው መቃብር ውስጥ ሌሎች ሰዎች በላይ ላይ እንዳይረግጡትና ሌላ አስከሬን እንዳይቀብሩበት ለመከላከል እንጂ ከሬሳ መድፈር ጋር አንዳችም ግንኙነት እንደሌለው ራሳቸው የቀብሩ ባለቤቶችና የመስጊዱ ኮሚቴ ለመረጃ አጣሪዎቹ መስክረዋል። ከሁሉ የሚያስገርመው በቪድዮ ሲያሳዩት የነበረው ፎቶ ላይ« Fact Check » የሚል ፅሁፍ ነበረው። በዚሁ ክስ ምክንያት ለተሰራጨ ምስል ማስተባበያ የሰጡ ሰዎችን ምስል በድጋሚ ለክስ ማቅርባቸው ምን ያህል ለውሸት ህሊናቸውን እንዳዘጋጁ የሚያጋልጥ ነው። በአንዳንድ የገጠር አካባቢዎችም መቃብር በብረት ወይም በድንጋይ የሚታጠረው ከጅብና ከመቃብር ዘራፊዎች ለመከላከል ነው። እንዲህ ያለውን የሐሰት ፎቶ አምጥቶ ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና ጋር ማያያዝ የመጨረሻው የቅጥፈት ደረጃ ነው። ይህን ሊንክ ተጠቅመው ያረጋግጡ (https://newsmeter.in/hyderabad/ground-report-uncovering-truth-behind-hyderabad-grille-covered-grave-711710)።   ማጠቃለያ   ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሳዳጊ እናታቸው በመሞቷ ካላቸው ጥልቅ ፍቅርና ውለታ የተነሳ በቀሚሳቸው ከፍነዋት፣ ቀብሯ ውስጥ ገብተው በረከትና ምሕረት ለምነውላት ህዝብ በተሰበሰበበት  እንደሸኟት እንጂ፣ ጠላቶች እንደሚቀጥፉት ጸያፍ ነገር ፈጽሞ አልተከሰተም። እንዲህ ያለው ቅጥፈት ከታመመ አእምሮና ከጥላቻ ብቻ የሚፈልቅ ነው።   በስተመጨረሻም የማከብረው ኡስታዝ አቡ ሐይደር (ሳዲቅ መሐመድ) በዚህ ጉዳይ ላይ በአንድ ውይይት ወቅት የሰጠውን ድንቅና ሳቅ አጫሪ ምላሽ አስታውሼ ልቋጭ፦ ከሳሽ፦ "I SLEPT with her in her grave..." ይላል! ኡስታዝ አቡ ሐይደር፦ «ቆይ 'I SLEPT' ማለት ሴክስ አደረግኩ ማለት ነውን? » ከሳሽ፦ «አዎ!» ኡስታዝ አቡ ሐይደር፦ «እስቲ እንግዲያውስ 'እኔ ተኛሁ' የሚለውን በእንግሊዝኛ ጻፍልኝ!» ብሎ በሳቅ ገሎናል።   እውነትም እኮ ነው! በእነዚህ ሰዎች የቋንቋ ቀመር «ተኛሁ / ጋደም አልኩ» (I slept / ኢድጠጀዕቱ) ማለት ሁሉ ሴክስ ከሆነ፣ ታዲያ ነገ ጠዋት ተነስተው «ትላንት ማታ አልጋዬ ላይ በደንብ ተኛሁ» ወይም «ሶፋው ላይ ጋደም ብዬ ነበር» ሲሉ ከአልጋውና ከሶፋው ጋር ምን ሲያደርጉ አደሩ ልንል ነው?! እንኳንስ የሃይማኖት ሊቅ፣ የአንደኛ ደረጃ የቋንቋ ተማሪ እንኳ የማይሳሳተውን ቃል እያጣመሙ ሕዝብን ለማደናገር መሞከር፣ ኪሳራ እንጂ እውቀት አይደለም። https://t.me/Abuyusra3

Open in Telegram
Views798−61%vs avg
Forwards—
Reactions33
Comments—
#594Text

ቀጣፊው ግብፃዊ ቄስ ዘካሪያ ቡትሮስ እና የፋጢማ ቢንት አሰድ (ረ.ዐ) እውነተኛ ታሪክ   አንዳንድ ሰዎች አዲስ ነገር ያገኙ ይመስል፣ ዛሬ ላይ  ያረጀና ያፈጀ የውሸት ክስ እንደ አዲስ ሲያራግቡና ሕዝብን ለማደናገር ሲሞክሩ ተመልክቻለሁ። ይህ ቅጥፈት የዛሬ 10 ዓመት ገደማ በቂና የማያዳግም ምላሽ የተሰጠበት፣ አቧራ የለበሰ የግብፃዊው ቄስ ዘካሪያ ቡትሮስ ፈጠራ ነው። ሆኖም «ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል» እንደሚባለው፣ አዳዲስ አንባቢያንና ተመልካቾች በዚህ ተራ ቅጥፈት እንዳይታለሉ በማሰብ፣ የዛሬ 10 ዓመት የጻፍኩትን ምላሽ የተሟሉ የመጻሕፍት ማስረጃዎችን በማካተት አሻሽዬ እንደገና አቅርቤላችኋለሁ፤ መልካም ንባብ!   ዛሬ ስለ አንዲት ታላቅ ሙስሊም እንስት ጥቂት ላወጋችሁ ወደድኩ። እግረ መንገዴንም ከእርሷ ታሪክ ጋር ተያይዞ በነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ለሚነዛው አሳፋሪ ቅጥፈት የማያዳግም ምላሽ እንሰጣለን። ይህ ክስ በቀደምት የኢስላም ጠላቶችም ሆነ ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሕልፈት በኋላ በነበሩ ክፍለ ዘመናት አንድም ቀን ተሰምቶ የማይታወቅ፣ ነገር ግን በዚህ ዘመን «ዘካሪያ ቡትሮስ» በተባለ የውሸት ቁንጮ ግብፃዊ ቄስ ተቀምሞ የተለቀቀ መርዝ ነው።   ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) በሕፃንነታቸው እናትና አባታቸውን በሞት እንዳጡ ሁላችንም የምናውቀው ሐቅ ነው። ታዲያ ከአያታቸው ከአብዱል ሙጠሊብ ሕልፈት በኋላ፣ አላህ (ሱ.ወ) ለእርሳቸው ከገዛ ልጆቿ አስበልጣ የምትወዳቸውንና ልክ እንደ እናት ሆና የምትንከባከባቸውን ድንቅ እንስት ሰጣቸው። ይህች እንስት ፋጢማ ቢንት አሰድ ኢብን ሃሺም (ረ.ዐ) ትባላለች። የአጎታቸው የአቡ ጧሊብ ባለቤትና የአራተኛው ኸሊፋ የአሊይ (ረ.ዐ) እንዲሁም የጀዕፈርና የዐቂል እናት ናት (ኢብን ሰዕድ፣ አጥ-ጠበቃቱል ኩብራ፣ ቅጽ 8፣ ገጽ 222)።   ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በአቡ ጧሊብ ቤት ውስጥ እንደ ገዛ ልጅ ሆነው ሲያድጉ፣ ፋጢማ ቢንት አሰድ በፍቅርና በእዝነት ኮትኩታ አሳደገቻቸው። እርሳቸውም እስከ ዕለተ ሞቷ ድረስ እጅግ ይወዷትና ያከብሯት ነበር፤ ሁልጊዜም «እናቴ» እያሉ ነበር የሚጠሯት። ኢስላምንም ከመጀመሪያዎቹ ቀደምት ሰዎች ተርታ ሆና ተቀብላ ወደ መዲና የተሰደደች ታላቅ ሰሐቢት ናት (ኢብን ሐጀር አል-ዐስቀላኒ፣ አል-ኢሷባህ ፊ ተምዪዚስ-ሰሐባህ፣ ቅጽ 8፣ ገጽ 269)።   ስለ እርሷ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የነበራቸውን ጥልቅ ፍቅር ሰሐባው አነስ ኢብን ማሊክ (ረ.ዐ) እንዲህ ይተርክልናል፦ «የአሊይ እናት ፋጢማ ቢንት አሰድ ባረፈች ጊዜ፣ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ ቤቷ ገብተው በራስጌዋ ተቀመጡና እንዲህ አሉ፦ "የአላህ እዝነት በአንቺ ላይ ይሁን እናቴ ሆይ! አንቺ ከእናቴ ቀጥሎ እናቴ ነበርሽ። አንቺ እየተራብሽ እኔን አብልተሽኛል፤ አንቺ እየታረዝሽ እኔን አልብሰሽኛል፤ የአላህን ውዴታና የመጨረሻውን ዓለም (ጀነትን) ከጅለሽ ለራስሽ የሚገባውን መልካም ነገር ሁሉ ለእኔ አስቀድመሽ ሰጥተሽኛል።"» (አጥ-ጠበራኒ፣ አል-ሙዕጀም አል-ከቢር፣ ቅጽ 24፣ ገጽ 351)   በቀብር ሥነ-ሥርዓቷም ዕለት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከነበራቸው ከፍተኛ ውለታና ፍቅር የተነሳ፣ ለብሰውት የነበረውን ቀሚሳቸውን አውልቀው እንዲከፍኗት ሰጡ። ቀብሩ ተቆፍሮ እንዳለቀም፣ እርሷ ወደ ቀብሩ ሳትወርድ በፊት ቦታው የተባረከ እንዲሆንላትና የቀብር ጭንቀት እንዲቀልላት በማሰብ እራሳቸው ቀብሩ ውስጥ ገብተው ለጥቂት ጊዜ ጋደም አሉና ከልብ ዱዓ አደረጉላት (አቡ ኑዐይም፣ ሒልየቱል አውሊያእ፣ ቅጽ 3፣ ገጽ 121)።   አላህ ለዚህች ታላቅ እናት ጀነቱል ፊርደውስን ይወፍቃት! አሚን።   ቅጥፈቱ ምንድን ነው?   የኢስላም ጠላቶች ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ለማጥላላት ጤነኛ አእምሮ ሊቀበላቸው የማይችሉ ተራ ዘለፋዎችን ሲቀጥፉ ማየት ልብን የሚያደማ ቢሆንም፣ ጌታችን አላህ ግን ቀድሞውኑ እንዲህ ብሎ አጽናንቶናል፦ «ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል።» (ቁርኣን፣ ሱረቱ አል-ሒጅር 15፡95)   ታዲያ ቄስ ዘካሪያ ቡትሮስ እና የእርሱን ጽሑፍ ሳያጣሩ የሚያራግቡ ሰዎች የሚነዙት አጸያፊ ክስ ምን ይላል? (አላህ ይቅር ይበለን!)   «ከንዙል ዑማል» (ቅጽ 12፣ ሐዲስ ቁ. 34424) ላይ ተዘገበ የሚሉትን የኢብን ዐባስ ዘገባ ጠቅሰው፦ «ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በፋጢማ ሞት አዝነው፣ የቀብር ቅጣት እንዲቀንስላትና የ'ሙእሚኖች እናት' የሚለውን የሚስትነት ክብር እንድታገኝ ከሞተው በድኗ ጋር በቀብሯ ውስጥ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸሙ» ይላሉ! ለዚህም ዋና «ማስረጃ» አድርገው የሚያቀርቡት በዘገባው ውስጥ ያለችውን «ኢድጠጀዕቱ መዐሃ ፊ ቀብሪሃ» (ከእርሷ ጋር በቀብሯ ውስጥ ጋደም አልኩ/ተኛሁ) የምትለዋን ቃል ነው። «ዲሜትሪየስ» የተባለ ማንነቱ የማይታወቅ የዐረብኛ ምሁር «ኢድጠጀዐ ማለት ለወሲብ መተኛት ማለት ነው» ብሎ ተርጉሞታል እያሉም ያላዝናሉ።   እስቲ ይህን ዓይን ያወጣ ቅጥፈት አንድ በአንድ እንመለከተው!   የምንጩ ተአማኒነት   ከሳሾቹ እንደ ዋና ማስረጃ የጠቀሱት «ከንዙል ዑማል» የተባለው መጽሐፍ ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሕልፈት ከ900 ዓመታት በኋላ በኖሩት አል-ሙተቂ አል-ሂንዲ (የሞቱት 975 ሂጅራ / 1567 እ.ኤ.አ.) የተሰበሰበ ሲሆን፣ እርሳቸውም ዘገባዎቹን ያጠናቀሩት ከኢማም አስ-ሱዩጢ «ጀምዑል ጀዋሚዕ» ከተሰኘው ከ45 ሺህ በላይ ሐዲሶችን ከያዘው መጽሐፍ ነው።   «ከንዙል ዑማል» እንደ ሶሒሕ አል-ቡኻሪ ትክክለኛ (ሶሒሕ) ሐዲሶችን ብቻ አጣርቶ የያዘ መጽሐፍ አይደለም፤ በውስጡ ሶሒሕም፣ ደዒፍም ዘገባዎች አሉበት። የዚህ ዘገባ የመጀመሪያ ምንጭ የሆነው የአጥ-ጠበራኒ ዘገባ እንኳ በሰንሰለቱ ውስጥ «ረውሕ ኢብን ሶላሕ» የተባለ ዘጋቢ ስላለበት፣ እንደ ኢብን ዐዲይ (አል-ካሚል ፊ ዱዐፋኢር-ሪጃል፣ ቅጽ 3፣ ገጽ 146) እና አድ-ዳረቁጥኒ ያሉ ታላላቅ የሐዲስ ሊቃውንት ዘገባውን ደካማ ብለውታል።   የቃሉ ትክክለኛ የዐረብኛ ትርጉም («ኢድጠጀዐ» ምን ማለት ነው?)   ዘገባው ሙሉ በሙሉ ትክክል ነው ብለን እንኳ ብንወስደው፣ የዘካሪያ ቡትሮስ ቅጥፈት የሚፈርሰው በራሱ በዐረብኛው ቃል ነው። ቄሱ «ኢድጠጀዐ» የሚለውን ቃል «ግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ» ብሎ መተርጎሙ ዓይን ያወጣ የቋንቋ ማጭበርበር ነው።   - በታዋቂው የዐረብኛ መዝገበ-ቃላት «ሊሳኑል ዐረብ» (ኢብን መንዙር፣ «ደጀዐ» ሥር) ውስጥ «ኢድጠጀዐ» ማለት በቀላሉ «በጎን መጋደም፣ ጋደም ማለት፣ ዐረፍ ማለት» (to lie down / recline) ማለት እንጂ በፍጹም «ወሲብ መፈጸም» ማለት አይደለም! በዐረብኛ ቋንቋ የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ለመግለጽ የሚያገለግሉ ቃላት «ጃመዐ»፣ «ዋቀዐ» ወይም «ደኸለ ቢሃ» እንጂ «ኢድጠጀዐ» አይደለም። - ይህ ቃል በተከበረው ቁርኣን ውስጥም መጥቷል። አላህ ስለ ሌሊት ሰጋጆች ሲናገር፦ «ጎኖቻቸው ከመጋደሚያዎቻቸው (አል-መዳጂዕ) ይራራቃሉ» (ቁርኣን፣ ሱረቱ አስ-ሰጅዳህ 32፡16) ይላል። - በሶሒሕ አል-ቡኻሪ (ሐዲስ ቁ. 1160) ላይ ደግሞ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የፈጅርን ሱና ሰግደው ሲጨርሱ በቀኝ ጎናቸው ጋደም ይሉ (የድጠጂዑ) እንደነበር ተዘግቧል። ታዲያ በቄሱና በዚያ ማንነቱ በማይታወቀው «ዲሜትሪየስ» አመክንዮ፣ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከፈጅር ሱና በኋላ ብቻቸውን ጋደም ሲሉ ወሲብ አደረጉ ሊሉን ነው እንዴ?!   በራሱ በሐዲሱ ውስጥ የተገለጸው ቅደም ተከተል እና ዱዓ   ቄሱ ሆን ብሎ የቆረጠውን የአጥ-ጠበራኒ ሙሉ ዘገባ (አል-ሙዕጀም አል-አውሰጥ፣ ሐዲስ ቁ. 189) ስናነበው ቅጥፈቱ ወዲያውኑ ይጋለጣል።

Open in Telegram
Views723−64%vs avg
Forwards—
Reactions10
Comments—
#592Text

«መጽሐፉ የሚለውን ነው የተናገርነው»! - ከግብጹ ዘካርያስ ቡትሮስ እስከ ዛሬ የቲክቶክ ተሳዳቢዎች፤ ራሳቸው የቀሰቀሱት የዕውቀት ማዕበል! ታሪክ ራሱን ይደግማል፤ ሞኞች ግን ከታሪክ አይማሩም! ከዓመታት በፊት በግብፅ ምድር ዘካርያስ ቡትሮስ የተባለ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቄስ ተነሥቶ ነበር። እስከዚያን ጊዜ ድረስ የግብፅ ሙስሊሞች ጠንካራ የኦርቶዶክስ ማኅበረሰብ ባለበት ሀገር ውስጥ ቢኖሩም፣ በንጽጽራዊ ሃይማኖት ጥናት ላይ ብዙም ገፍተው የሚታወቁ አልነበሩም። ዘካርያስ ቡትሮስ ግን በቴሌቪዥን መስኮት እየወጣ እስልምናን እጅግ ጸያፍና ባለጌ በሆነ መንገድ መሳደብ ጀመረ። የግብፅ ሙስሊም ምሁራንና የሀገር ሽማግሌዎች ወደ ቤተክርስቲያኗ አባቶች ሄደው «ይህንን ሰውዬ ሥርዓት አስይዙት» በሚል ሲጠይቁ የቤተ ክርስቲያኗ ሰው የሰጡት ትዕቢት የተሞላበት ምላሽ አንድ ነበር፦ «እርሱ መጽሐፉ የሚለውን ነው የተናገረው እንጂ አዲስ ነገር አልተናገረም፤ መልስ ስጡት!» ያቺ ቀን በግብፅ ታሪክ ውስጥ ትልቅ የዕውቀት አብዮት የፈነዳባት ዕለት ሆነች! በዚያ ትዕቢት የተቀሰቀሱት የግብፅ ሙስሊሞች ከቋንቋቸው ተሻግረው መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎበታል የሚባልበትን ጥንታዊ ቋንቋ ዕብራይስጥን እና ግሪክን ጭምር አጥንተው በመውጣት፣ የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እያንዳንዱን ድርሳናት በማጥናት ቃል በቃል በትነው አደባባይ ላይ አሰጡት! ዛሬ በግብፅ ምድር አንድም የኦርቶዶክስ ሰባኪ በሙለ የራስ መተማመን ስለ እስልምና መተንፈስ ወደ ሚቸገርበት ደረጃ ተሸጋገሩ። በምዕራቡ ዓለም (በአሜሪካና በእንግሊዝ) የታየውም ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለም። እንደ ዴቪድ ዉድ እና ጄይ ስሚዝ ያሉ የምዕራቡ ዓለም ጸረ-ኢስላም ሰባኪያን በአብያተ ክርስቲያናት ድጋፍ «መረጃውን ነው የጠቀስነው» እያሉ እስልምናን ሲያንቋሽሹ፣ ምላሹ የሆነው በዓለም አቀፍ መድረኮች (እንደ Speakers' Corner ባሉ) የመጽሐፍ ቅዱስን ቴክስችዋል ክሪቲሲዝም እና የሥላሴን መሠረት-አልባነት የሚያጋልጡ ኃያላን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዳዒዎችና ተመራማሪዎች መፍለቅ ነው! ዛሬ በሀገራችን እየሆነ ያለውም የዚሁ ታሪክ ግልባጭ ነው! ጥቂት መድረኩ ላይ የተኮለኮሉ የቤተ ክርስቲያኗ ሰዎች እስልምናን በጸያፍ ቃላት ሲሳደቡ፣ ተከላካዮቻቸው የሚሰጡት ምላሽ ያው የግብጾቹን ቃል የኮረጀ ነው፦ «መጽሐፉን ነው የተናገረው እንጂ አዲስ ነገር አልተናገረም!» እውነቱን ለመናገር ይህንን የምጽፈው ስለ ጥቂት ተራ ባለጌ ግለሰቦች ተጨንቄ አይደለም፤ ነገር ግን እኛ የነዚህን ግለሰቦች ብልግና ችላ ብለን ባለፍንበት ሰዓት፣ የእነርሱ አክቲቪስትና መንጋ ግን ይህንን ጸያፍ ተግባር እንደ ታላቅ ጀግና አንሥቶ ሲወራጭበት አይቼ በመደመሜ ነው! የቤተክርስቲያኗ ምእመናን ምን ያህል በጥልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እየኖሩ እንዳሉ የሚያሳብቀውም ይኸው ነው፤ ተስፋ ከመቁረጣቸው የተነሣ ያገኙትን ይህንን የብልግና ዕድል ላለማባከን መከራቸውን እየበሉ መሆኑ በግልጽ ያስታውቃል። ነገር ግን እነዚህ ወገኖች የቀሰቀሱትን እሳት አላወቁትም! እኛ ወደ ኋላ የምንልበት አንዳችም ምክንያት የለም። ከዚህ በኋላ የቤተክርስቲያኗን ሥርዓተ ትምህርትና ጥንታዊ ድርሳናት (ከግእዝ የተተረጎሙትንም ያልተተረጎሙትንም) አደባባይ ላይ በማውጣት፣ ለተራ ስብከት ሳይሆን ከጥልቅ ምርምር ጋር አያይዞ ለምእመኑ እውነቱን የሚገልጥ፣ በእስልምና ዙሪያ የሚነሣውንም ማንኛውንም የሐሰት ክስ ቃል በቃል በትኖ መልስ የሚሰጥ ኃያል ትውልድ የሚነሣበት ዘመን ይመጣ ዘንድ ግን መደላድል እየፈተጠረ ነው! ከዚያ በኋላ ራሳቸው ያስነሡትን ይህንን የዕውቀት ማዕበል በደንብ መቋቋም ከቻሉ አብረን የምንመለከተው ይሆናል። ለወገኖቻችን የምነግራችሁ ትልቁ እውነት ግን አንድ ነው፦ ይህ የዛሬው ሁካታ ለመጪው ጊዜ እጅግ ትልቅ መደላደል፣ መነሻና የማንቂያ ደወል መሆኑን ፈጽሞ እንዳትረሱ! https://t.me/Abuyusra3

Open in Telegram
Views4,610+127%vs avg
Forwards—
Reactions59
Comments—
#589Photo

አልሐምዱሊላህ! በአላህ ፈቃድ በነቢዩ (ﷺ) ስብዕና ላይ ለሚነሱ ብዥታዎች ምላሽ ለመስጠት ያዘጋጀነው «ጽልመቱን የገፈፈው ብርሃን» መጽሐፍ፣ ለንባብ ይበልጥ ምቹ እንዲሆን ታስቦ ሳይዙ ተቀንሶ በሞባይል አፕሊኬሽን ቀርቧል። በኪስዎ ይዘው በቀላሉ እንዲጠቀሙበት ተደርጎ የተዘጋጀው ይህ አፕሊኬሽን፦ • መጠኑ አነስተኛ የሆነ፦ በስልክዎ ላይ ብዙ ቦታ ሳይዝ በፍጥነት የሚጫን። • ያለ ኢንተርኔት የሚሠራ፦ አንዴ ካወረዱት በኋላ በማንኛውም ቦታ ዳታ ሳይፈጅ የሚያገለግል። • ለንባብ ምቹ፦ ከማውጫው ላይ የሚፈልጉትን ርዕስ ነክተው በቀጥታ ወደ ገጹ የሚወስድና ቃላትን ለመፈለግ (Search) የሚያስችል። • አጋዥ አማራጮች ያሉት፦ ያቆሙበትን ገጽ ራሱ የሚያስታውስና ቁልፍ ነጥቦችን ማስታወሻ መጻፍ የሚያስችል። ይህንን ሥራ አውርደው እንዲያነቡትና ለሌሎችም በማጋራት የአጅሩ ተቋዳሽ እንዲሆኑ በትህትና እንጋብዛለን። አፑን የሰራው ወንድማችንንም አላህ መልካም ስራውን ይቀበለው! ⬇️ አፑን ለማውረድ ይህንን ይጫኑ፦ 🔗 https://t.me/kasimApp/173 #ጽልመቱን_የገፈፈው_ብርሃን #ንጽጽር #ኢስላም

Open in Telegram
Views1,150−43%vs avg
Forwards—
Reactions65
Comments—

All posts

Connections