ዘገባው የሚለው እንዲህ ነው፦ ቀብሩ ተቆፍሮ የውስጠኛው ክፍል (ለሕድ) ሲደረስ፣ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በገዛ እጃቸው አፈሩን አስተካክለው፣ ፋጢማ ገና ወደ ቀብሩ ሳትወርድ በፊት እራሳቸው ወደ ባዶው ቀብር ገብተው ጋደም አሉና እንዲህ ብለው ዱዓ አደረጉ፦
«አላህ ሆይ! ሕይወትን የምትሰጥና የምትገድል ጌታ ሆይ! እናቴን ፋጢማ ቢንት አሰድን ማራት፣ መልሷን አግራላት፣ መግቢያዋንም (ቀብሯንም) አስፋላት...»
አስተውሉ! ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቀብሩ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ «እናቴን ፋጢማ ቢንት አሰድን ማራት» እያሉ ነው! ታዲያ በራሱ በዚህ ሐዲስ ውስጥ «እናቴ» ብለው እየጠሯት፣ ቄሱ ከየት አምጥቶ ነው «ሚስቱ እንድትሆን» ብሎ የቀጠፈው?! ሆን ብሎ ይህንን ክፍል ቆርጦ የደበቀው ቅጥፈቱ እንዳይጋለጥበት ነው።
ሎጂክ፣ ታሪክ እና የኢስላም ሕግ የሚመሰክሩት እውነት
ከቋንቋው ባለፈ የቄሱ ክስ በአንድ ጤነኛ አእምሮ ፊት እንመዝነው!
ሀ/በአሊይ ኢብን አቢ ጧሊብ ፊት? የቀብር ሥነ-ሥርዓት የሚፈጸመው በብዙ መቶ ሰዎች ፊት በጠራራ ፀሐይ ነው። በፋጢማ ቀብር ላይ ደግሞ ጀግናው ልጇ አሊይ (ረ.ዐ)፣ ሌሎች ልጆቿ፣ ሙሃጂሮችና አንሷሮች በሙሉ ቆመው እያዩ ነበር። አንድ ሰው የገዛ እናቱን ያሳደገችውን እንስት በድን፣ በጀግናው ልጇ በአሊይና በሕዝብ ፊት እንዲህ ያለ አጸያፊ ተግባር ፈጸመ፣ አሊይም ዝም ብሎ አይቶ በኩራት አስተላለፈ ብሎ ማሰብ ምን ዓይነት የታመመ ጭንቅላት ይጠይቃል?!
ለ/ የወቅቱ ጠላቶች የት ነበሩ? በመዲና ውስጥ ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ለማዋረድ ትንሽ ቀዳዳ የሚጠባበቁ ሙናፊቆች፣ የቁረይሽ ጣዖት አምላኪዎችና አይሁዳውያን ነበሩ። እንዲህ ያለ ነገር በሕዝብ ፊት ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ከ21ኛው ክፍለ ዘመን ቀጣፊ ቄስ በፊት እነርሱ ዓለምን ባናወጡት ነበር!
ሐ/የኢስላም ሕግ፣ የሟች ክብር እና የቀብር አቆፋፈር፦ በኢስላም ጋብቻ «የጠበቀ ቃል ኪዳን» (ቁርኣን፣ ሱረቱ አን-ኒሳእ 4፡21) ሲሆን የሚጸናውም በሕይወት ባሉ ሰዎች መካከል በፈቃደኝነት ነው፤ በሞት ደግሞ ጋብቻ ይቋረጣል። የሟች አካል ክብር እጅግ የተጠበቀ በመሆኑ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) «የሞተን ሰው አጥንት መስበር ልክ በሕይወት እያለ እንደመስበር ነው» ብለዋል (ሱነን አቢ ዳውድ፣ ሐዲስ ቁ. 3207)።
መ/ ከዚህም በላይ በኢስላም የቀብር ጉድጓድ (ለሕድ) የሚቆፈረው ለአንድ ሰው አካል ብቻ በጠባቡ እንጂ ሁለት ሰው አስተኝቶ የሚያስቀምጥ አይደለም (ሶሒሕ ሙስሊም፣ ሐዲስ ቁ. 966)።
በሰፈሩት ቁና ይሰፈሩ
የሚገርመው ነገር፣ ዘካሪያ ቡትሮስ ኢስላም ላይ ሲሆን «ወሲብ» ብሎ የሚተረጉመው ይኸው «ኢድጠጀዐ» የሚለው የዐረብኛ ቃል፣ በራሱ በዐረብኛው መጽሐፍ ቅዱስ (Smith-Van Dyke Arabic Bible) ውስጥ እንዴት እንደተቀመጠ ስናይ ነው!
2ኛ ነገሥት 4፡32-34 ላይ ነቢዩ ኤልሳዕ የሞተውን ሕፃን ለማስነሳት ያደረገውን እንመልከት፦ «ኤልሳዕም ወደ ቤት በገባ ጊዜ እነሆ፥ ሕፃኑ ሞቶ በአልጋው ላይ ተጋድሞ (ሙድጠጂዐን) ነበር... ወጥቶም በሕፃኑ ላይ ተጋደመ (ወ-ኢድጠጀዐ ፈውቀስ-ሶቢይ)፥ አፉንም በአፉ ላይ፥ ዓይኖቹንም በዓይኖቹ ላይ፥ እጆቹንም በእጆቹ ላይ አደረገ፥ በእርሱም ላይ ተዘረጋ፤ የሕፃኑም ሥጋ ሞቀ።» (መጽሐፍ ቅዱስ፣ የ1954 ትርጉም)።
ተመልከቱ! 2ኛ ነገሥት 4፡34 ላይ ነቢዩ ኤልሳዕ በሞተ ሕፃን ላይ ተጋደመ ሲል የዐረብኛው መጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀመው ቃል ልክ ያንኑ «ኢድጠጀዐ» የሚለውን ቃል ነው! ያውም አፉን በአፉ ላይ፣ ዓይኑን በዓይኑ ላይ አድርጎ! ታዲያ ለነቢዩ ኤልሳዕ ሲሆን «ኢድጠጀዐ» ማለት «ተጋደመ» ሆኖ፣ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሲሆን ግን እንዴት ወደ አጸያፊ ተግባር ተቀየረ?! ይህ ዓይን ያወጣ ጥላቻ የፈጠረው መረዳት ብቻ ነው!
አዲስ የተጨመረ የሐሰት ማጣፈጫ
የብረት መዝጊያና ቁልፍ ያላቸው መቃብሮች የሐሰት ወሬ (Hoax)፦ «ሙስሊሞች የነቢዩን ሱና ተከትለው ሬሳ ስለሚደፍሩ ወላጆች የሴት ልጆቻቸውን ቀብር በብረት ቆለፉ» እያሉ ያሳዩት ፎቶ በሚያዝያ/ግንቦት 2023 በዓለም አቀፍ የመረጃ አጣሪዎች (AFP Fact Check፣ Alt News እና Boom Live) ውሸትነቱ የተጋለጠ የማኅበራዊ ሚዲያ ፈጠራ ነው! ያ ታዋቂው በብረት የታጠረ ቀብር ፎቶ የተነሳው ሕንድ፣ ሀይደራባድ (Darab Jung Colony, Hyderabad) ውስጥ ሲሆን፣ ቤተሰቦቹ ብረቱን የሠሩት በተጨናነቀው መቃብር ውስጥ ሌሎች ሰዎች በላይ ላይ እንዳይረግጡትና ሌላ አስከሬን እንዳይቀብሩበት ለመከላከል እንጂ ከሬሳ መድፈር ጋር አንዳችም ግንኙነት እንደሌለው ራሳቸው የቀብሩ ባለቤቶችና የመስጊዱ ኮሚቴ ለመረጃ አጣሪዎቹ መስክረዋል። ከሁሉ የሚያስገርመው በቪድዮ ሲያሳዩት የነበረው ፎቶ ላይ« Fact Check » የሚል ፅሁፍ ነበረው። በዚሁ ክስ ምክንያት ለተሰራጨ ምስል ማስተባበያ የሰጡ ሰዎችን ምስል በድጋሚ ለክስ ማቅርባቸው ምን ያህል ለውሸት ህሊናቸውን እንዳዘጋጁ የሚያጋልጥ ነው። በአንዳንድ የገጠር አካባቢዎችም መቃብር በብረት ወይም በድንጋይ የሚታጠረው ከጅብና ከመቃብር ዘራፊዎች ለመከላከል ነው። እንዲህ ያለውን የሐሰት ፎቶ አምጥቶ ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና ጋር ማያያዝ የመጨረሻው የቅጥፈት ደረጃ ነው። ይህን ሊንክ ተጠቅመው ያረጋግጡ (https://newsmeter.in/hyderabad/ground-report-uncovering-truth-behind-hyderabad-grille-covered-grave-711710)።
ማጠቃለያ
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሳዳጊ እናታቸው በመሞቷ ካላቸው ጥልቅ ፍቅርና ውለታ የተነሳ በቀሚሳቸው ከፍነዋት፣ ቀብሯ ውስጥ ገብተው በረከትና ምሕረት ለምነውላት ህዝብ በተሰበሰበበት እንደሸኟት እንጂ፣ ጠላቶች እንደሚቀጥፉት ጸያፍ ነገር ፈጽሞ አልተከሰተም። እንዲህ ያለው ቅጥፈት ከታመመ አእምሮና ከጥላቻ ብቻ የሚፈልቅ ነው።
በስተመጨረሻም የማከብረው ኡስታዝ አቡ ሐይደር (ሳዲቅ መሐመድ) በዚህ ጉዳይ ላይ በአንድ ውይይት ወቅት የሰጠውን ድንቅና ሳቅ አጫሪ ምላሽ አስታውሼ ልቋጭ፦
ከሳሽ፦ "I SLEPT with her in her grave..." ይላል!
ኡስታዝ አቡ ሐይደር፦ «ቆይ 'I SLEPT' ማለት ሴክስ አደረግኩ ማለት ነውን? »
ከሳሽ፦ «አዎ!»
ኡስታዝ አቡ ሐይደር፦ «እስቲ እንግዲያውስ 'እኔ ተኛሁ' የሚለውን በእንግሊዝኛ ጻፍልኝ!» ብሎ በሳቅ ገሎናል።
እውነትም እኮ ነው! በእነዚህ ሰዎች የቋንቋ ቀመር «ተኛሁ / ጋደም አልኩ» (I slept / ኢድጠጀዕቱ) ማለት ሁሉ ሴክስ ከሆነ፣ ታዲያ ነገ ጠዋት ተነስተው «ትላንት ማታ አልጋዬ ላይ በደንብ ተኛሁ» ወይም «ሶፋው ላይ ጋደም ብዬ ነበር» ሲሉ ከአልጋውና ከሶፋው ጋር ምን ሲያደርጉ አደሩ ልንል ነው?! እንኳንስ የሃይማኖት ሊቅ፣ የአንደኛ ደረጃ የቋንቋ ተማሪ እንኳ የማይሳሳተውን ቃል እያጣመሙ ሕዝብን ለማደናገር መሞከር፣ ኪሳራ እንጂ እውቀት አይደለም።
https://t.me/Abuyusra3