Кабинет

Посты канала አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

сначала новые

#599Текст
Просмотры589−71%к среднему
Пересылки—
Реакции64
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
3 ч373
11 ч589
  1. Всего сейчас589
#597Файл
Просмотры612−70%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#596Текст

ዘገባው የሚለው እንዲህ ነው፦ ቀብሩ ተቆፍሮ የውስጠኛው ክፍል (ለሕድ) ሲደረስ፣ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በገዛ እጃቸው አፈሩን አስተካክለው፣ ፋጢማ ገና ወደ ቀብሩ ሳትወርድ በፊት እራሳቸው ወደ ባዶው ቀብር ገብተው ጋደም አሉና እንዲህ ብለው ዱዓ አደረጉ፦ «አላህ ሆይ! ሕይወትን የምትሰጥና የምትገድል ጌታ ሆይ! እናቴን ፋጢማ ቢንት አሰድን ማራት፣ መልሷን አግራላት፣ መግቢያዋንም (ቀብሯንም) አስፋላት...»   አስተውሉ! ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቀብሩ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ «እናቴን ፋጢማ ቢንት አሰድን ማራት» እያሉ ነው! ታዲያ በራሱ በዚህ ሐዲስ ውስጥ «እናቴ» ብለው እየጠሯት፣ ቄሱ ከየት አምጥቶ ነው «ሚስቱ እንድትሆን» ብሎ የቀጠፈው?! ሆን ብሎ ይህንን ክፍል ቆርጦ የደበቀው ቅጥፈቱ እንዳይጋለጥበት ነው።   ሎጂክ፣ ታሪክ እና የኢስላም ሕግ የሚመሰክሩት እውነት   ከቋንቋው ባለፈ የቄሱ ክስ በአንድ ጤነኛ አእምሮ ፊት እንመዝነው! ሀ/በአሊይ ኢብን አቢ ጧሊብ ፊት? የቀብር ሥነ-ሥርዓት የሚፈጸመው በብዙ መቶ ሰዎች ፊት በጠራራ ፀሐይ ነው። በፋጢማ ቀብር ላይ ደግሞ ጀግናው ልጇ አሊይ (ረ.ዐ)፣ ሌሎች ልጆቿ፣ ሙሃጂሮችና አንሷሮች በሙሉ ቆመው እያዩ ነበር። አንድ ሰው የገዛ እናቱን ያሳደገችውን እንስት በድን፣ በጀግናው ልጇ በአሊይና በሕዝብ ፊት እንዲህ ያለ አጸያፊ ተግባር ፈጸመ፣ አሊይም ዝም ብሎ አይቶ በኩራት አስተላለፈ ብሎ ማሰብ ምን ዓይነት የታመመ ጭንቅላት ይጠይቃል?! ለ/ የወቅቱ ጠላቶች የት ነበሩ? በመዲና ውስጥ ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ለማዋረድ ትንሽ ቀዳዳ የሚጠባበቁ ሙናፊቆች፣ የቁረይሽ ጣዖት አምላኪዎችና አይሁዳውያን ነበሩ። እንዲህ ያለ ነገር በሕዝብ ፊት ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ከ21ኛው ክፍለ ዘመን ቀጣፊ ቄስ በፊት እነርሱ ዓለምን ባናወጡት ነበር! ሐ/የኢስላም ሕግ፣ የሟች ክብር እና የቀብር አቆፋፈር፦ በኢስላም ጋብቻ «የጠበቀ ቃል ኪዳን» (ቁርኣን፣ ሱረቱ አን-ኒሳእ 4፡21) ሲሆን የሚጸናውም በሕይወት ባሉ ሰዎች መካከል በፈቃደኝነት ነው፤ በሞት ደግሞ ጋብቻ ይቋረጣል። የሟች አካል ክብር እጅግ የተጠበቀ በመሆኑ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) «የሞተን ሰው አጥንት መስበር ልክ በሕይወት እያለ እንደመስበር ነው» ብለዋል (ሱነን አቢ ዳውድ፣ ሐዲስ ቁ. 3207)። መ/ ከዚህም በላይ በኢስላም የቀብር ጉድጓድ (ለሕድ) የሚቆፈረው ለአንድ ሰው አካል ብቻ በጠባቡ እንጂ ሁለት ሰው አስተኝቶ የሚያስቀምጥ አይደለም (ሶሒሕ ሙስሊም፣ ሐዲስ ቁ. 966)። በሰፈሩት ቁና ይሰፈሩ   የሚገርመው ነገር፣ ዘካሪያ ቡትሮስ ኢስላም ላይ ሲሆን «ወሲብ» ብሎ የሚተረጉመው ይኸው «ኢድጠጀዐ» የሚለው የዐረብኛ ቃል፣ በራሱ በዐረብኛው መጽሐፍ ቅዱስ (Smith-Van Dyke Arabic Bible) ውስጥ እንዴት እንደተቀመጠ ስናይ ነው! 2ኛ ነገሥት 4፡32-34 ላይ ነቢዩ ኤልሳዕ የሞተውን ሕፃን ለማስነሳት ያደረገውን እንመልከት፦ «ኤልሳዕም ወደ ቤት በገባ ጊዜ እነሆ፥ ሕፃኑ ሞቶ በአልጋው ላይ ተጋድሞ (ሙድጠጂዐን) ነበር... ወጥቶም በሕፃኑ ላይ ተጋደመ (ወ-ኢድጠጀዐ ፈውቀስ-ሶቢይ)፥ አፉንም በአፉ ላይ፥ ዓይኖቹንም በዓይኖቹ ላይ፥ እጆቹንም በእጆቹ ላይ አደረገ፥ በእርሱም ላይ ተዘረጋ፤ የሕፃኑም ሥጋ ሞቀ።» (መጽሐፍ ቅዱስ፣ የ1954 ትርጉም)።   ተመልከቱ! 2ኛ ነገሥት 4፡34 ላይ ነቢዩ ኤልሳዕ በሞተ ሕፃን ላይ ተጋደመ ሲል የዐረብኛው መጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀመው ቃል ልክ ያንኑ «ኢድጠጀዐ» የሚለውን ቃል ነው! ያውም አፉን በአፉ ላይ፣ ዓይኑን በዓይኑ ላይ አድርጎ! ታዲያ ለነቢዩ ኤልሳዕ ሲሆን «ኢድጠጀዐ» ማለት «ተጋደመ» ሆኖ፣ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሲሆን ግን እንዴት ወደ አጸያፊ ተግባር ተቀየረ?! ይህ ዓይን ያወጣ ጥላቻ የፈጠረው መረዳት ብቻ ነው!   አዲስ የተጨመረ የሐሰት ማጣፈጫ   የብረት መዝጊያና ቁልፍ ያላቸው መቃብሮች የሐሰት ወሬ (Hoax)፦ «ሙስሊሞች የነቢዩን ሱና ተከትለው ሬሳ ስለሚደፍሩ ወላጆች የሴት ልጆቻቸውን ቀብር በብረት ቆለፉ» እያሉ ያሳዩት ፎቶ በሚያዝያ/ግንቦት 2023 በዓለም አቀፍ የመረጃ አጣሪዎች (AFP Fact Check፣ Alt News እና Boom Live) ውሸትነቱ የተጋለጠ የማኅበራዊ ሚዲያ ፈጠራ ነው! ያ ታዋቂው በብረት የታጠረ ቀብር ፎቶ የተነሳው ሕንድ፣ ሀይደራባድ (Darab Jung Colony, Hyderabad) ውስጥ ሲሆን፣ ቤተሰቦቹ ብረቱን የሠሩት በተጨናነቀው መቃብር ውስጥ ሌሎች ሰዎች በላይ ላይ እንዳይረግጡትና ሌላ አስከሬን እንዳይቀብሩበት ለመከላከል እንጂ ከሬሳ መድፈር ጋር አንዳችም ግንኙነት እንደሌለው ራሳቸው የቀብሩ ባለቤቶችና የመስጊዱ ኮሚቴ ለመረጃ አጣሪዎቹ መስክረዋል። ከሁሉ የሚያስገርመው በቪድዮ ሲያሳዩት የነበረው ፎቶ ላይ« Fact Check » የሚል ፅሁፍ ነበረው። በዚሁ ክስ ምክንያት ለተሰራጨ ምስል ማስተባበያ የሰጡ ሰዎችን ምስል በድጋሚ ለክስ ማቅርባቸው ምን ያህል ለውሸት ህሊናቸውን እንዳዘጋጁ የሚያጋልጥ ነው። በአንዳንድ የገጠር አካባቢዎችም መቃብር በብረት ወይም በድንጋይ የሚታጠረው ከጅብና ከመቃብር ዘራፊዎች ለመከላከል ነው። እንዲህ ያለውን የሐሰት ፎቶ አምጥቶ ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና ጋር ማያያዝ የመጨረሻው የቅጥፈት ደረጃ ነው። ይህን ሊንክ ተጠቅመው ያረጋግጡ (https://newsmeter.in/hyderabad/ground-report-uncovering-truth-behind-hyderabad-grille-covered-grave-711710)።   ማጠቃለያ   ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሳዳጊ እናታቸው በመሞቷ ካላቸው ጥልቅ ፍቅርና ውለታ የተነሳ በቀሚሳቸው ከፍነዋት፣ ቀብሯ ውስጥ ገብተው በረከትና ምሕረት ለምነውላት ህዝብ በተሰበሰበበት  እንደሸኟት እንጂ፣ ጠላቶች እንደሚቀጥፉት ጸያፍ ነገር ፈጽሞ አልተከሰተም። እንዲህ ያለው ቅጥፈት ከታመመ አእምሮና ከጥላቻ ብቻ የሚፈልቅ ነው።   በስተመጨረሻም የማከብረው ኡስታዝ አቡ ሐይደር (ሳዲቅ መሐመድ) በዚህ ጉዳይ ላይ በአንድ ውይይት ወቅት የሰጠውን ድንቅና ሳቅ አጫሪ ምላሽ አስታውሼ ልቋጭ፦ ከሳሽ፦ "I SLEPT with her in her grave..." ይላል! ኡስታዝ አቡ ሐይደር፦ «ቆይ 'I SLEPT' ማለት ሴክስ አደረግኩ ማለት ነውን? » ከሳሽ፦ «አዎ!» ኡስታዝ አቡ ሐይደር፦ «እስቲ እንግዲያውስ 'እኔ ተኛሁ' የሚለውን በእንግሊዝኛ ጻፍልኝ!» ብሎ በሳቅ ገሎናል።   እውነትም እኮ ነው! በእነዚህ ሰዎች የቋንቋ ቀመር «ተኛሁ / ጋደም አልኩ» (I slept / ኢድጠጀዕቱ) ማለት ሁሉ ሴክስ ከሆነ፣ ታዲያ ነገ ጠዋት ተነስተው «ትላንት ማታ አልጋዬ ላይ በደንብ ተኛሁ» ወይም «ሶፋው ላይ ጋደም ብዬ ነበር» ሲሉ ከአልጋውና ከሶፋው ጋር ምን ሲያደርጉ አደሩ ልንል ነው?! እንኳንስ የሃይማኖት ሊቅ፣ የአንደኛ ደረጃ የቋንቋ ተማሪ እንኳ የማይሳሳተውን ቃል እያጣመሙ ሕዝብን ለማደናገር መሞከር፣ ኪሳራ እንጂ እውቀት አይደለም። https://t.me/Abuyusra3

Открыть в Telegram
Просмотры798−61%к среднему
Пересылки—
Реакции33
Комментарии—
#594Текст

ቀጣፊው ግብፃዊ ቄስ ዘካሪያ ቡትሮስ እና የፋጢማ ቢንት አሰድ (ረ.ዐ) እውነተኛ ታሪክ   አንዳንድ ሰዎች አዲስ ነገር ያገኙ ይመስል፣ ዛሬ ላይ  ያረጀና ያፈጀ የውሸት ክስ እንደ አዲስ ሲያራግቡና ሕዝብን ለማደናገር ሲሞክሩ ተመልክቻለሁ። ይህ ቅጥፈት የዛሬ 10 ዓመት ገደማ በቂና የማያዳግም ምላሽ የተሰጠበት፣ አቧራ የለበሰ የግብፃዊው ቄስ ዘካሪያ ቡትሮስ ፈጠራ ነው። ሆኖም «ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል» እንደሚባለው፣ አዳዲስ አንባቢያንና ተመልካቾች በዚህ ተራ ቅጥፈት እንዳይታለሉ በማሰብ፣ የዛሬ 10 ዓመት የጻፍኩትን ምላሽ የተሟሉ የመጻሕፍት ማስረጃዎችን በማካተት አሻሽዬ እንደገና አቅርቤላችኋለሁ፤ መልካም ንባብ!   ዛሬ ስለ አንዲት ታላቅ ሙስሊም እንስት ጥቂት ላወጋችሁ ወደድኩ። እግረ መንገዴንም ከእርሷ ታሪክ ጋር ተያይዞ በነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ለሚነዛው አሳፋሪ ቅጥፈት የማያዳግም ምላሽ እንሰጣለን። ይህ ክስ በቀደምት የኢስላም ጠላቶችም ሆነ ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሕልፈት በኋላ በነበሩ ክፍለ ዘመናት አንድም ቀን ተሰምቶ የማይታወቅ፣ ነገር ግን በዚህ ዘመን «ዘካሪያ ቡትሮስ» በተባለ የውሸት ቁንጮ ግብፃዊ ቄስ ተቀምሞ የተለቀቀ መርዝ ነው።   ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) በሕፃንነታቸው እናትና አባታቸውን በሞት እንዳጡ ሁላችንም የምናውቀው ሐቅ ነው። ታዲያ ከአያታቸው ከአብዱል ሙጠሊብ ሕልፈት በኋላ፣ አላህ (ሱ.ወ) ለእርሳቸው ከገዛ ልጆቿ አስበልጣ የምትወዳቸውንና ልክ እንደ እናት ሆና የምትንከባከባቸውን ድንቅ እንስት ሰጣቸው። ይህች እንስት ፋጢማ ቢንት አሰድ ኢብን ሃሺም (ረ.ዐ) ትባላለች። የአጎታቸው የአቡ ጧሊብ ባለቤትና የአራተኛው ኸሊፋ የአሊይ (ረ.ዐ) እንዲሁም የጀዕፈርና የዐቂል እናት ናት (ኢብን ሰዕድ፣ አጥ-ጠበቃቱል ኩብራ፣ ቅጽ 8፣ ገጽ 222)።   ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በአቡ ጧሊብ ቤት ውስጥ እንደ ገዛ ልጅ ሆነው ሲያድጉ፣ ፋጢማ ቢንት አሰድ በፍቅርና በእዝነት ኮትኩታ አሳደገቻቸው። እርሳቸውም እስከ ዕለተ ሞቷ ድረስ እጅግ ይወዷትና ያከብሯት ነበር፤ ሁልጊዜም «እናቴ» እያሉ ነበር የሚጠሯት። ኢስላምንም ከመጀመሪያዎቹ ቀደምት ሰዎች ተርታ ሆና ተቀብላ ወደ መዲና የተሰደደች ታላቅ ሰሐቢት ናት (ኢብን ሐጀር አል-ዐስቀላኒ፣ አል-ኢሷባህ ፊ ተምዪዚስ-ሰሐባህ፣ ቅጽ 8፣ ገጽ 269)።   ስለ እርሷ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የነበራቸውን ጥልቅ ፍቅር ሰሐባው አነስ ኢብን ማሊክ (ረ.ዐ) እንዲህ ይተርክልናል፦ «የአሊይ እናት ፋጢማ ቢንት አሰድ ባረፈች ጊዜ፣ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ ቤቷ ገብተው በራስጌዋ ተቀመጡና እንዲህ አሉ፦ "የአላህ እዝነት በአንቺ ላይ ይሁን እናቴ ሆይ! አንቺ ከእናቴ ቀጥሎ እናቴ ነበርሽ። አንቺ እየተራብሽ እኔን አብልተሽኛል፤ አንቺ እየታረዝሽ እኔን አልብሰሽኛል፤ የአላህን ውዴታና የመጨረሻውን ዓለም (ጀነትን) ከጅለሽ ለራስሽ የሚገባውን መልካም ነገር ሁሉ ለእኔ አስቀድመሽ ሰጥተሽኛል።"» (አጥ-ጠበራኒ፣ አል-ሙዕጀም አል-ከቢር፣ ቅጽ 24፣ ገጽ 351)   በቀብር ሥነ-ሥርዓቷም ዕለት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከነበራቸው ከፍተኛ ውለታና ፍቅር የተነሳ፣ ለብሰውት የነበረውን ቀሚሳቸውን አውልቀው እንዲከፍኗት ሰጡ። ቀብሩ ተቆፍሮ እንዳለቀም፣ እርሷ ወደ ቀብሩ ሳትወርድ በፊት ቦታው የተባረከ እንዲሆንላትና የቀብር ጭንቀት እንዲቀልላት በማሰብ እራሳቸው ቀብሩ ውስጥ ገብተው ለጥቂት ጊዜ ጋደም አሉና ከልብ ዱዓ አደረጉላት (አቡ ኑዐይም፣ ሒልየቱል አውሊያእ፣ ቅጽ 3፣ ገጽ 121)።   አላህ ለዚህች ታላቅ እናት ጀነቱል ፊርደውስን ይወፍቃት! አሚን።   ቅጥፈቱ ምንድን ነው?   የኢስላም ጠላቶች ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ለማጥላላት ጤነኛ አእምሮ ሊቀበላቸው የማይችሉ ተራ ዘለፋዎችን ሲቀጥፉ ማየት ልብን የሚያደማ ቢሆንም፣ ጌታችን አላህ ግን ቀድሞውኑ እንዲህ ብሎ አጽናንቶናል፦ «ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል።» (ቁርኣን፣ ሱረቱ አል-ሒጅር 15፡95)   ታዲያ ቄስ ዘካሪያ ቡትሮስ እና የእርሱን ጽሑፍ ሳያጣሩ የሚያራግቡ ሰዎች የሚነዙት አጸያፊ ክስ ምን ይላል? (አላህ ይቅር ይበለን!)   «ከንዙል ዑማል» (ቅጽ 12፣ ሐዲስ ቁ. 34424) ላይ ተዘገበ የሚሉትን የኢብን ዐባስ ዘገባ ጠቅሰው፦ «ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በፋጢማ ሞት አዝነው፣ የቀብር ቅጣት እንዲቀንስላትና የ'ሙእሚኖች እናት' የሚለውን የሚስትነት ክብር እንድታገኝ ከሞተው በድኗ ጋር በቀብሯ ውስጥ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸሙ» ይላሉ! ለዚህም ዋና «ማስረጃ» አድርገው የሚያቀርቡት በዘገባው ውስጥ ያለችውን «ኢድጠጀዕቱ መዐሃ ፊ ቀብሪሃ» (ከእርሷ ጋር በቀብሯ ውስጥ ጋደም አልኩ/ተኛሁ) የምትለዋን ቃል ነው። «ዲሜትሪየስ» የተባለ ማንነቱ የማይታወቅ የዐረብኛ ምሁር «ኢድጠጀዐ ማለት ለወሲብ መተኛት ማለት ነው» ብሎ ተርጉሞታል እያሉም ያላዝናሉ።   እስቲ ይህን ዓይን ያወጣ ቅጥፈት አንድ በአንድ እንመለከተው!   የምንጩ ተአማኒነት   ከሳሾቹ እንደ ዋና ማስረጃ የጠቀሱት «ከንዙል ዑማል» የተባለው መጽሐፍ ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሕልፈት ከ900 ዓመታት በኋላ በኖሩት አል-ሙተቂ አል-ሂንዲ (የሞቱት 975 ሂጅራ / 1567 እ.ኤ.አ.) የተሰበሰበ ሲሆን፣ እርሳቸውም ዘገባዎቹን ያጠናቀሩት ከኢማም አስ-ሱዩጢ «ጀምዑል ጀዋሚዕ» ከተሰኘው ከ45 ሺህ በላይ ሐዲሶችን ከያዘው መጽሐፍ ነው።   «ከንዙል ዑማል» እንደ ሶሒሕ አል-ቡኻሪ ትክክለኛ (ሶሒሕ) ሐዲሶችን ብቻ አጣርቶ የያዘ መጽሐፍ አይደለም፤ በውስጡ ሶሒሕም፣ ደዒፍም ዘገባዎች አሉበት። የዚህ ዘገባ የመጀመሪያ ምንጭ የሆነው የአጥ-ጠበራኒ ዘገባ እንኳ በሰንሰለቱ ውስጥ «ረውሕ ኢብን ሶላሕ» የተባለ ዘጋቢ ስላለበት፣ እንደ ኢብን ዐዲይ (አል-ካሚል ፊ ዱዐፋኢር-ሪጃል፣ ቅጽ 3፣ ገጽ 146) እና አድ-ዳረቁጥኒ ያሉ ታላላቅ የሐዲስ ሊቃውንት ዘገባውን ደካማ ብለውታል።   የቃሉ ትክክለኛ የዐረብኛ ትርጉም («ኢድጠጀዐ» ምን ማለት ነው?)   ዘገባው ሙሉ በሙሉ ትክክል ነው ብለን እንኳ ብንወስደው፣ የዘካሪያ ቡትሮስ ቅጥፈት የሚፈርሰው በራሱ በዐረብኛው ቃል ነው። ቄሱ «ኢድጠጀዐ» የሚለውን ቃል «ግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ» ብሎ መተርጎሙ ዓይን ያወጣ የቋንቋ ማጭበርበር ነው።   - በታዋቂው የዐረብኛ መዝገበ-ቃላት «ሊሳኑል ዐረብ» (ኢብን መንዙር፣ «ደጀዐ» ሥር) ውስጥ «ኢድጠጀዐ» ማለት በቀላሉ «በጎን መጋደም፣ ጋደም ማለት፣ ዐረፍ ማለት» (to lie down / recline) ማለት እንጂ በፍጹም «ወሲብ መፈጸም» ማለት አይደለም! በዐረብኛ ቋንቋ የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ለመግለጽ የሚያገለግሉ ቃላት «ጃመዐ»፣ «ዋቀዐ» ወይም «ደኸለ ቢሃ» እንጂ «ኢድጠጀዐ» አይደለም። - ይህ ቃል በተከበረው ቁርኣን ውስጥም መጥቷል። አላህ ስለ ሌሊት ሰጋጆች ሲናገር፦ «ጎኖቻቸው ከመጋደሚያዎቻቸው (አል-መዳጂዕ) ይራራቃሉ» (ቁርኣን፣ ሱረቱ አስ-ሰጅዳህ 32፡16) ይላል። - በሶሒሕ አል-ቡኻሪ (ሐዲስ ቁ. 1160) ላይ ደግሞ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የፈጅርን ሱና ሰግደው ሲጨርሱ በቀኝ ጎናቸው ጋደም ይሉ (የድጠጂዑ) እንደነበር ተዘግቧል። ታዲያ በቄሱና በዚያ ማንነቱ በማይታወቀው «ዲሜትሪየስ» አመክንዮ፣ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከፈጅር ሱና በኋላ ብቻቸውን ጋደም ሲሉ ወሲብ አደረጉ ሊሉን ነው እንዴ?!   በራሱ በሐዲሱ ውስጥ የተገለጸው ቅደም ተከተል እና ዱዓ   ቄሱ ሆን ብሎ የቆረጠውን የአጥ-ጠበራኒ ሙሉ ዘገባ (አል-ሙዕጀም አል-አውሰጥ፣ ሐዲስ ቁ. 189) ስናነበው ቅጥፈቱ ወዲያውኑ ይጋለጣል።

Открыть в Telegram
Просмотры723−64%к среднему
Пересылки—
Реакции10
Комментарии—
#592Текст

«መጽሐፉ የሚለውን ነው የተናገርነው»! - ከግብጹ ዘካርያስ ቡትሮስ እስከ ዛሬ የቲክቶክ ተሳዳቢዎች፤ ራሳቸው የቀሰቀሱት የዕውቀት ማዕበል! ታሪክ ራሱን ይደግማል፤ ሞኞች ግን ከታሪክ አይማሩም! ከዓመታት በፊት በግብፅ ምድር ዘካርያስ ቡትሮስ የተባለ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቄስ ተነሥቶ ነበር። እስከዚያን ጊዜ ድረስ የግብፅ ሙስሊሞች ጠንካራ የኦርቶዶክስ ማኅበረሰብ ባለበት ሀገር ውስጥ ቢኖሩም፣ በንጽጽራዊ ሃይማኖት ጥናት ላይ ብዙም ገፍተው የሚታወቁ አልነበሩም። ዘካርያስ ቡትሮስ ግን በቴሌቪዥን መስኮት እየወጣ እስልምናን እጅግ ጸያፍና ባለጌ በሆነ መንገድ መሳደብ ጀመረ። የግብፅ ሙስሊም ምሁራንና የሀገር ሽማግሌዎች ወደ ቤተክርስቲያኗ አባቶች ሄደው «ይህንን ሰውዬ ሥርዓት አስይዙት» በሚል ሲጠይቁ የቤተ ክርስቲያኗ ሰው የሰጡት ትዕቢት የተሞላበት ምላሽ አንድ ነበር፦ «እርሱ መጽሐፉ የሚለውን ነው የተናገረው እንጂ አዲስ ነገር አልተናገረም፤ መልስ ስጡት!» ያቺ ቀን በግብፅ ታሪክ ውስጥ ትልቅ የዕውቀት አብዮት የፈነዳባት ዕለት ሆነች! በዚያ ትዕቢት የተቀሰቀሱት የግብፅ ሙስሊሞች ከቋንቋቸው ተሻግረው መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎበታል የሚባልበትን ጥንታዊ ቋንቋ ዕብራይስጥን እና ግሪክን ጭምር አጥንተው በመውጣት፣ የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እያንዳንዱን ድርሳናት በማጥናት ቃል በቃል በትነው አደባባይ ላይ አሰጡት! ዛሬ በግብፅ ምድር አንድም የኦርቶዶክስ ሰባኪ በሙለ የራስ መተማመን ስለ እስልምና መተንፈስ ወደ ሚቸገርበት ደረጃ ተሸጋገሩ። በምዕራቡ ዓለም (በአሜሪካና በእንግሊዝ) የታየውም ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለም። እንደ ዴቪድ ዉድ እና ጄይ ስሚዝ ያሉ የምዕራቡ ዓለም ጸረ-ኢስላም ሰባኪያን በአብያተ ክርስቲያናት ድጋፍ «መረጃውን ነው የጠቀስነው» እያሉ እስልምናን ሲያንቋሽሹ፣ ምላሹ የሆነው በዓለም አቀፍ መድረኮች (እንደ Speakers' Corner ባሉ) የመጽሐፍ ቅዱስን ቴክስችዋል ክሪቲሲዝም እና የሥላሴን መሠረት-አልባነት የሚያጋልጡ ኃያላን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዳዒዎችና ተመራማሪዎች መፍለቅ ነው! ዛሬ በሀገራችን እየሆነ ያለውም የዚሁ ታሪክ ግልባጭ ነው! ጥቂት መድረኩ ላይ የተኮለኮሉ የቤተ ክርስቲያኗ ሰዎች እስልምናን በጸያፍ ቃላት ሲሳደቡ፣ ተከላካዮቻቸው የሚሰጡት ምላሽ ያው የግብጾቹን ቃል የኮረጀ ነው፦ «መጽሐፉን ነው የተናገረው እንጂ አዲስ ነገር አልተናገረም!» እውነቱን ለመናገር ይህንን የምጽፈው ስለ ጥቂት ተራ ባለጌ ግለሰቦች ተጨንቄ አይደለም፤ ነገር ግን እኛ የነዚህን ግለሰቦች ብልግና ችላ ብለን ባለፍንበት ሰዓት፣ የእነርሱ አክቲቪስትና መንጋ ግን ይህንን ጸያፍ ተግባር እንደ ታላቅ ጀግና አንሥቶ ሲወራጭበት አይቼ በመደመሜ ነው! የቤተክርስቲያኗ ምእመናን ምን ያህል በጥልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እየኖሩ እንዳሉ የሚያሳብቀውም ይኸው ነው፤ ተስፋ ከመቁረጣቸው የተነሣ ያገኙትን ይህንን የብልግና ዕድል ላለማባከን መከራቸውን እየበሉ መሆኑ በግልጽ ያስታውቃል። ነገር ግን እነዚህ ወገኖች የቀሰቀሱትን እሳት አላወቁትም! እኛ ወደ ኋላ የምንልበት አንዳችም ምክንያት የለም። ከዚህ በኋላ የቤተክርስቲያኗን ሥርዓተ ትምህርትና ጥንታዊ ድርሳናት (ከግእዝ የተተረጎሙትንም ያልተተረጎሙትንም) አደባባይ ላይ በማውጣት፣ ለተራ ስብከት ሳይሆን ከጥልቅ ምርምር ጋር አያይዞ ለምእመኑ እውነቱን የሚገልጥ፣ በእስልምና ዙሪያ የሚነሣውንም ማንኛውንም የሐሰት ክስ ቃል በቃል በትኖ መልስ የሚሰጥ ኃያል ትውልድ የሚነሣበት ዘመን ይመጣ ዘንድ ግን መደላድል እየፈተጠረ ነው! ከዚያ በኋላ ራሳቸው ያስነሡትን ይህንን የዕውቀት ማዕበል በደንብ መቋቋም ከቻሉ አብረን የምንመለከተው ይሆናል። ለወገኖቻችን የምነግራችሁ ትልቁ እውነት ግን አንድ ነው፦ ይህ የዛሬው ሁካታ ለመጪው ጊዜ እጅግ ትልቅ መደላደል፣ መነሻና የማንቂያ ደወል መሆኑን ፈጽሞ እንዳትረሱ! https://t.me/Abuyusra3

Открыть в Telegram
Просмотры4 610+127%к среднему
Пересылки—
Реакции59
Комментарии—
#589Фото

አልሐምዱሊላህ! በአላህ ፈቃድ በነቢዩ (ﷺ) ስብዕና ላይ ለሚነሱ ብዥታዎች ምላሽ ለመስጠት ያዘጋጀነው «ጽልመቱን የገፈፈው ብርሃን» መጽሐፍ፣ ለንባብ ይበልጥ ምቹ እንዲሆን ታስቦ ሳይዙ ተቀንሶ በሞባይል አፕሊኬሽን ቀርቧል። በኪስዎ ይዘው በቀላሉ እንዲጠቀሙበት ተደርጎ የተዘጋጀው ይህ አፕሊኬሽን፦ • መጠኑ አነስተኛ የሆነ፦ በስልክዎ ላይ ብዙ ቦታ ሳይዝ በፍጥነት የሚጫን። • ያለ ኢንተርኔት የሚሠራ፦ አንዴ ካወረዱት በኋላ በማንኛውም ቦታ ዳታ ሳይፈጅ የሚያገለግል። • ለንባብ ምቹ፦ ከማውጫው ላይ የሚፈልጉትን ርዕስ ነክተው በቀጥታ ወደ ገጹ የሚወስድና ቃላትን ለመፈለግ (Search) የሚያስችል። • አጋዥ አማራጮች ያሉት፦ ያቆሙበትን ገጽ ራሱ የሚያስታውስና ቁልፍ ነጥቦችን ማስታወሻ መጻፍ የሚያስችል። ይህንን ሥራ አውርደው እንዲያነቡትና ለሌሎችም በማጋራት የአጅሩ ተቋዳሽ እንዲሆኑ በትህትና እንጋብዛለን። አፑን የሰራው ወንድማችንንም አላህ መልካም ስራውን ይቀበለው! ⬇️ አፑን ለማውረድ ይህንን ይጫኑ፦ 🔗 https://t.me/kasimApp/173 #ጽልመቱን_የገፈፈው_ብርሃን #ንጽጽር #ኢስላም

Открыть в Telegram
Просмотры1 150−43%к среднему
Пересылки—
Реакции65
Комментарии—
#588Текст
Просмотры1 710−16%к среднему
Пересылки—
Реакции94
Комментарии—
#587Текст

የምሥራች! ለዳዕዋና ለንጽጽር መድረክ ወሳኝ የሆኑ መጻሕፍት ወደ እናንተ ሊደርሱ ነው! አልሐምዱሊላህ! ከአላህ ፈቃድ ጋር በቀጣይ ጊዜያት እጅግ ጠቃሚ የሆኑ አዳዲስ መጻሕፍትን ከእኛ በኩል ወደ እናንተ እንደምናደርስ ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው! እነዚህ መጻሕፍት የተወለዱት ትናንት አይደለም። ከሁለት ዓመት በፊት በጥቂት መድረሳዎች እና መርከዞች የንጽጽር ኮርሶችን በምንሰጥበት ጊዜ፣ በተበታተነ መልኩ እናዘጋጃቸው ከነበሩ ሞጁሎች የመነጩ ናቸው። በሃገራችን ኢትዮጵያ፣ የክርስትና ኮሌጆች ስለ እስልምና የሚያስተምሩባቸው የተደራጁ ካሪኩለሞችና መጻሕፍት በስፋት ሲኖሩ፣ በኛ በኩል ግን ይህን ትልቅ ክፍተት የሚሞላ ማስተማሪያ ማኑዋል አልነበረም። ስለዚህም፣ የዐረብኛና የእንግሊዝኛ ምንጮችን ወደ አማርኛ እየመለስን ስናስተምር ቆይተናል። ይህንን ክፍተት ለመድፈንና ትምህርቱ በሁሉም ቦታ ተደራሽ እንዲሆን፣ ያዘጋጀናቸውን ሞጁሎች ወደተሟሉ መጻሕፍት አሳድገናቸዋል። ከነዚህ መጻሕፍት መካከል "የታማኙ ቃል፣ የነቢይነት ሕያው ማረጋገጫዎች" (በራሂን አን-ኑቡዋህ) የሚለው በዋናነት ይጠቀሳል። ብዙ ጊዜ፣ "ስለ ነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) እውነተኛነት ማወቅ እፈልጋለሁ" የሚሉ ክርስቲያን ወገኖቻችን ሲያጋጥሙን፣ በግልጽና በተደራጀ መልኩ የምንሰጠው የአማርኛ መጽሐፍ አልነበረም። በኢስላም ታሪክ እንደ ኢማም አል-በይሀቂ፣ አል-ቃዲ ዒያድ እና ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሂመሁላህ)፣ እንዲሁም በዘመናችን እንደ ዶ/ር ሳሚ አሚሪ ያሉ ታላላቅ ዑለሞች በዚህ ርዕስ ዙሪያ (ደላኢሉ አን-ኑቡዋህ / በራሂኑ አን-ኑቡዋህ) ሰፋፊ ሥራዎችን ቢሠሩም፣ ለአማርኛ አንባቢ ተደራሽ አልነበሩም። አሁን ግን፣ ይህንን መጽሐፍ በጥልቀት አዋቅረን አዘጋጅተነዋል! ለአንድ ወገናችሁ ይህን መጽሐፍ ስጦታ ብትሰጡ፣ የዕድሜ ልክ ሂዳያ ሰበብ ሊሆን ይችላል። አዲስ ኪዳን እና ብሉይ ኪዳንን ከፈጣሪ ቃልነት አንጻር የሚፈትሹ መጻሕፍት ሌላኛው አስፈላጊ ስራዎች ናቸው። በኢትዮጵያ የንጽጽር ሀይማኖት ሥነ-ጽሑፍ ታሪክ፣ መጽሐፍ ቅዱስን በጥቅሉ የሚዳስሱና የሚኅይሱ መጻሕፍት ቢኖሩም፣ አብዛኛዎቹ በተወሰኑ የተመረጡ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ እንጂ፣ ጠቅለል ባለ መልኩ ለማስተማሪያነት ታቅደው የተዘጋጁ አልነበሩም። እነዚህ አዳዲስ መጻሕፍት ግን ከምንም በላይ ጥልቀት ያላቸው ናቸው! የሀገራችን አንደምታና ትርጓሜ ጨምሮ የበርካታ ምዕራባውያን የመጽሀፍ ቅዱስ ምሁራን እና የጥንታዊ የክርስትና ሊቃውንትን ሥራዎች መሠረት ያደረጉ፣ እንዲሁም የራሳቸው የክርስትና ምሁራን ጥልቅ ትንታኔዎች የተዳሰሱባቸው ናቸው። ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ደግሞ፣ እስልምና ስለ ቀደምት መለኮታዊ መጻሕፍት የሚያስተምረውን ንጹሕ አቋም ፍጹም በጠበቀ መልኩ ነው! መጽሀፍቱ ብዙ ከመሆናቸው አንጻር መጀመሪያ ላይ ውስን ኮፒዎችን የምናሳትም ሲሆን፣ አንዳንዶቹን ለመርከዞች፣ ቀሪዎቹን ደግሞ ለገበያ እናቀርባለን። እነርሱ ሲሸጡ ደግሞ ተጨማሪ እያሳተምን በስፋት እናዳርሳለን ኢንሻአላህ። አላህ ሥራችንን እንዲባርክልን፣ ይህን ክፍተት ለመድፈን የጀመርነውን ጥረት ከዳር እንዲያደርስልን፣ እናንተም ከጎናችን በመሆን በዱዓችሁ አግዙን! https://t.me/Yahyanuhe

Открыть в Telegram
Просмотры2 140+5%к среднему
Пересылки—
Реакции95
Комментарии—
#584Превью ссылки

​የእግርን መድኃኒት ለራስ‼ ፀሀፊው በገፅ 242-243 ሰለ ሂና ያወራበት ሀሳብ አለ፣ እስኪ ነገሩን ላማብራራት በዝርዝር እንየው:— ጸሐፊው የተጠቀመው የዓረብኛ ጽሑፍ፦ "مَا كَانَ أَحَدٌ يَشْتَكِي إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَجَعًا فِي رَأْسِهِ إِلَّا قَالَ: «احْتَجِمْ» وَلَا وَجَعًا فِي رِجْلَيْهِ إِلَّا قَالَ: «اخْتَضِبْهُمَا»" የጸሐፊው የተሳሳተ ትርጉም፦ "የነቢዩ ባሪያ የነበረችው ሰልማ እንደተናገረችው ማንም ሰው በራስ ወይም በእግር ህመም ከአላህ መልእክተኛ በላይ ታመው ቅሬታ አያቀርቡም ሂና እንዲቀቡም ይነግራቸው ነበር።" ትክክለኛው ትርጉም፦ «ማንም ሰው ወደ አላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መጥቶ የራስ ሕመምን አያማርርም ነበር እርሳቸው፡- "ሒጃማ አድርግ " የሚሉት ቢሆን እንጂ፤ እንዲሁም በእግሮቹ ላይ ሕመምን አያማርርም ነበር እርሳቸው፡- "ሂና ተቀባቸው" የሚሉት ቢሆን እንጂ።» ትክክለኛው  ንባብ የሚያወራው ስለ ሁለት የተለያዩ ሕመሞች እና ስለ ሁለት የተለያዩ መድኃኒቶች ነው። የጸሐፊው ማጭበርበር እና የተንኮሉ ዓላማ ሐዲሱን ሲተረጉም የሰራው ስህተት ባለማወቅ ሳይሆን ሆን ተብሎ የተፈጸመ ነው እንዴት ካሉ ተከታተሉኝ:— 1. እንዴት አጭበረበረ? ቢጫ ከተቀቡትን ቃላት አንዱ «እሕተጂም (احْتَجِمْ)» የሚል  ትእዛዝ አለ ትርጉሙም "ሂጃማ  አድርግ" ማለት ነው። ነገር ግን በአማርኛ ትርጉሙ ላይ ይህንን ቃል ጭራሽ አጥፍቶ በመጣል፣ ሐዲሱ ፈጽሞ ያላዘዘውን «ለራስ ምታትም ሂና ይቀቡ ነበር» የሚል ሐሰተኛ ትርጉም ፈጠረ። ሁለቱን የተለያዩ ሕመሞች (የራስ እና የእግር) አንድ ላይ ደባልቆ፣ መድኃኒቱ አንድ "ሂና መቀባት" ብቻ እንደሆነ አድርጎ አቀረበ። ለምን እንዲህ አደረገ ? ይህን ሁሉ የትርጉም ማጭበርበር  የሰራበት ዋና ዓላማ የራሱን የጥላቻ ድራማ ለማሳመር ብሎ ነው፡- ጸሐፊው  በገጽ 243  "የሂና ቅጠል የሰይጣንን ጭንቅላት ይመስላል" የሚል ቡኻሪ ውስጥ የሌለ የፈጠራ ጽሑፍ ጽፎ ነበር። በመቀጠልም "ስለዚህ ሙሐመድ የሰይጣን ጭንቅላት የሚመስለውን ቅጠል (ሂና) ራሱ ላይ በማድረግ መገለጥ መጣልኝ ይላቸዋል" ብሎ ማገናኘት ፈልገ። ግን አንድ ችግር ገጠመው ሀዲሱ ላይ ሂና ለራስ ህመም የሚል ማግኘት አልቻለም። ታዲያ ይህ ውሸቱ እውነት እንዲመስልለት ግን ነቢዩ (ﷺ) ለራስ ምታታቸው ሂና እንደተቀቡ ማስመሰል ነበረበት። ነገር ግን ሐዲሱን ሲያየው ለራስ ምታት የታዘዘው "ሂጃማ"  እንጂ ሂና አልነበረም። ስለዚህ የፈጠረው "የሰይጣን ቅጠል በጭንቅላት ላይ የማድረግ" ውሸት እንዳይፈርስበት ሲል፣ "ሂጃማ" የምትለዋን ቃል ሰረዛት። ከዚያም የእግር ሕመም መድኃኒት የሆነውን "ሂና" ወደ ራስ ምታት አምጥቶ በመለጠፍ፣ አንባቢን ለማታለል ርካሽ የትርጉም ማጭበርበር ፈጸመ። https://t.me/Abuyusra3

Открыть в Telegram
Просмотры2 450+21%к среднему
Пересылки—
Реакции78
Комментарии—
#582Фото

መልሱን ቆርጦ መልስ የሚፈልገው ፀሃፊ ይህ ጸሐፊ በገፅ 102 ላይ  «ሙሐመድ ሌሊት መቃብር የሚሄዱት ለምንድነው? ጤናማ መንፈስ ነውን?» ብሎ አንባቢን ለማደናገር ሲሞክር ነበር ፣ ሐዲሱ ራሱ የሚሰጠውን ግልጽ ምላሽ ግን ሆን ብሎ ቆርጦ ጥሎታል! በቢጫ የተሰመረበትን ቃል ያስተውሉ 'ፈየቁል (فَيَقُولُ - እንዲህም ይሉ ነበር)' ከሚለው ቃል ቀጥሎ፣ የነበረውን ነቢዩ (ﷺ) መቃብር ላይ ቆመው የተናገሩትንና የሄዱበትን ምክንያት የሚያሰረዳውን  ሀሳብ ሐዲሱ ላይ በግልጽ ተቀምጦ ሳለ ፀሀፊው ሆነ ብሎ ቆረጠው!! የተቆረጠው እንዲህ ይላል፦ السلام عليكم دار قوم مؤمنين، وأتاكم ما توعدون، غداً مؤجلون وإنا إن شاء الله بكم لاحقون، اللهم اغفر لأهل بقيع الغرق «ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን የአማኞች መንደር ነዋሪዎች፤ የተቀጠራችሁት ሞት መጥቶላችኋል፤ (ሙሉ ምንዳችሁ) ለነገ (ለውመል ቂያማ) የተዘገየ ሆኖ ሳለ። እኛም በአላህ ፈቃድ እናንተን ተከታዮች (ተቀላቃዮች) ነን። አላህ ሆይ! ለበቂዕ አል-ገርቀድ (የመቃብር ስፍራ) ሰዎች ምሕረት አድርግላቸው» የሚል ለሟቾች የተደረገ እጅግ አዛኝ የምሕረት ዱዓ ነው። ታዲያ ጸሐፊው ይህንን የጸሎት ቃል ለምን ደበቀው ካላችሁ ? ምክንያቱም ነቢዩ ወደ መቃብር የሄዱት ለሟቾች ጸሎት ለማድረግ መሆኑን ካሳወቀ፣ «ጤናማ መንፈስ አይደለም» ብሎ የገነባው የጥላቻ ትርክት ስለሚፈርስበት ነው። የሌላውን እምነት ለመተቸት መረጃን መቁረጥና መደበቅ፣ የእውነት ፈላጊነት ሳይሆን የስነ ጹሁፍ ክብርን ያልጠበቀ ሌብነት ማሳያ ነው! https://t.me/Abuyusra3

Открыть в Telegram
Просмотры2 280+12%к среднему
Пересылки—
Реакции97
Комментарии—
#579Текст
Просмотры1 510−26%к среднему
Пересылки—
Реакции42
Комментарии—
#578Текст

"በ45 ደቂቃ አፈራረስኩት!" ካልክ... ዛሬ መንጋ ልኮ ሪፖርት ማድረግ ነውር ነው! ባለፉት የቲክቶክ ላይቭ ፕሮግራሞቻችን ላይ ከሦስት ጊዜ በላይ ሪፖርት እየተደረገብን ከላይቭ መውረዳችን ይታወሳል። የ«የጽልመቱ ጥላ» ጸሐፊ የምላሽ መጽሀፉ የፈጠረበትን ድንጋጤ መሸከም አቅቶት፣ ምላሹ እንዳይሰራጭና እውነቱ እንዳይወጣ በማሰብ የሪፖርት ዘመቻዎችን በማሰማራት የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ነው። ኢንሻአላህ! ዛሬ ግን ሙስሊም ወንድሞችና እህቶች በተቻላችሁ መጠን ሼር እና "ኮፒ ሊንክ" በማድረግ ይህንን የፍርሃት ዘመቻ እንደምታከሽፉት ተስፋ እናደርጋለን! የዛሬው ልዩ ፕሮግራም ነው! ዛሬ ምሽት 3፡00 ሰዓት ላይ በወንድማችን ኢብራሂም የቲክቶክ ገጽ ላይ፣ ከ200 በላይ ገጾችና 100 በላይ ዐበይት ርዕሰ ጉዳዮች የተዳሰሱበትን «ጽልመቱን የገፈፈው ብርሃን» የተሰኘውን መጽሐፋችንን በአጠቃላይ የምንዳስስበትና "የምረቃ ፕሮግራም" የምናደርግበት ይሆናል። መጽሐፉን የጻፈው ግለሰብ የገጠመው የስነ-ልቦና ቀውስ ግን በእውነት አሳዛኝ ነው። የ200 ገጽ መጽሐፍን ሙሉ ሐሳብና መረጃ መከላከል ከብዶት፣ የራሱን ተከታዮች የማመዛዘን አቅም በናቀ መልኩ አንዲት "የቅማል/የቱሃን" ነጥብ ፈልጎ በማውጣት፣ በዚያች ብቸኛ አጀንዳ ሙሉውን መጽሐፍ የመለሰ አስመስሎ መንጋውን ለማስደሰት የሄደበት ርቀት... የሰውዬውን የጭንቀት ልክ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። እኛ ጋር እንዲህ ዓይነት ርካሽ የልጆች መደበቂያ አይሠራም፤ እያንዳንዱን የሸሸውን ነጥብ እየነቀስን ነው የምናጋልጠው! እሱ በሄደበት ርካሽ መንገድ ተጉዘን፣ ወደ ኦርቶዶክስ "ገድላት" ውስጥ ገብተን (ቅዱሳን ተብለው ከሚታመኑ አባቶች ሰውነት ላይ ስለሚረግፉ ትሎችና ቅማሎች) ብዙ ነገሮችን መምዘዝ እና መሳለቅ እንችል ነበር። ነገር ግን ሐሳቡን በቅጡ የማያውቁ፣ እውነታውን መረዳት የሚፈልጉና ብዙ ጨዋ ክርስቲያን ወገኖች እንዳሉ እናውቃለን። ከሁሉም በላይ ደግሞ የራሳችን የእስልምና ሥነ-ምግባር ይህንን ርካሽ የንጽጽር መንገድ እንድንከተል ስለማይፈቅድልን፣ ሚዛናችንን ጠብቀንና ለሥነ-ምግባር ቅድሚያ ሰጥተን ማለፍን መርጠናል። አንድ አደራ ለ"45 ደቂቃው ጀግና" አንተ "በ45 ደቂቃ ውስጥ 200 ገጽ አንብቤ ምላሽ ሰጥቻለሁ/አፈራርሻለሁ" ብለህ የምትፎክረው ጸሐፊ ሆይ... አንድ መልእክት አለን! እንግዲህ መጽሐፉን አንብበህ "አፈራርሰኸዋል" አይደል? ታዲያ ከዚህ በኋላ መንጋህን አሰማርተህ የዛሬውን ላይቭ "ሪፖርት" የምታስደርግበት ምንም ዓይነት ሎጂካዊ ምክንያት የለም! ዛሬም ሪፖርት አድርጋችሁ ላይቩን የምታቋርጡ ከሆነ፣ ያው "በ45 ደቂቃ መለስኩት" ያልከው የፈሪ ፉከራ መሆኑንና ሽንፈታችሁን ሕዝቡ ራሱ ይፈርዳል። ቢያንስ ዛሬን እንኳን በራስ መተማመን አሳየን! ሁላችሁም መጽሐፉን አንብቡት! እጅግ ጠቃሚና ዝርዝር መረጃዎችን ይዟል። ዛሬ ምሽት 3፡00 ሰዓት ላይ በወንድማችን ኢብራሂም ቲክቶክ እንገናኝ! ኮፒ ሊንክ ማድረጋችሁን አትርሱ! https://t.me/Yahyanuhe

Открыть в Telegram
Просмотры1 320−35%к среднему
Пересылки—
Реакции45
Комментарии—
#576Текст

ክርስቲያን ወገኖቻችን፣ በዚህ የቲዎሎጂ ትንታኔ በእውነት ትስማማላችሁን? ​ሰሞኑን እኔና ወንድሜ የሕያ «የጽልመቱ ጥላ» ለተባለው መጽሐፍ ምላሽ እንዳዘጋጀን ይታወቃል። ጸሐፊው መጽሐፉን ያዘጋጀው እስልምናን ለመተቸትና ለማጥቃት አስቦ ቢሆንም፣ በሒደቱ ግን ባላሰበው መንገድ የራሱን የክርስትና እምነት መሠረታዊ አስተምህሮዎች ደጋግሞ ገደል ሲከታቸው ታዝበናል። ​ከእነዚህም ውስጥ አንዱን ለክርስትና እምነት ተከታዮች ለሚዛናዊ ፍርድ (ለጥያቄ) ማቅረብ ወደድን። ​በዮሐንስ ወንጌል 1፡29 ላይ «የእግዚአብሔር በግ» የሚለው ቃል ለድኅነት፣ ለሕይወት እና ለኃጢአት ስርየት የሚውል መሆኑን እንደምታምኑ ይታወቃል። ነገር ግን በእናንተ ስም ይሟገታል የተባለው ይህ "አፖሎጂስት"፣ ይህንን ክርስቶስ የተመሰለበትን «ቅዱስ በግ»፣ አንዲት አይሁዳዊት ሴት ነቢዩን ሙሐመድን (ﷺ) ለመግደል በቂም በቀል ካዘጋጀችውና በመርዝ ከተለወሰው የበግ ሥጋ ጋር አመሳስሎታል! ​ያቀረበውን ሎጂክ ስንመለከት፣ «ኢየሱስም የእግዚአብሔር በግ ተብሏል፣ ሴትዮዋም ያመጣችው የበግ ሥጋ ነው» ከሚል እጅግ የወረደ የቃላት ማነጻጸሪያ የመነጨ ነው። በእሱ መነጽርና ትንታኔ፣ ለዓለም ቤዛ ነው ተብሎ የሚታመነው «የእግዚአብሔር በግ»፣ ሰውን ገድሎ ከሚያሰቃይ የቂም በቀል መርዝ ጋር አንድ ዓይነት አምሳያ ተደርጎ ቀርቧል ማለት ነው። ​እዚህ ላይ ክርስቲያን ወገኖቻችንን በጨዋነት መጠየቅ የምንፈልገው፦ በእውነት ይህ ሰው እናንተንና የክርስትናን ቲዎሎጂ ወክሎ ነው የሚሟገተው? እናንተስ ለድኅነት ነው ብላችሁ የምታምኑትን «የክርስቶስን የማዳን ሥራ» ከሴረኛ መርዝ ጋር አመሳስሎ የሚያቀርብን አስተምህሮ ትቀበላላችሁን? ወይስ እስልምናን ለመተቸት ሲባል ብቻ የራሳችሁን እምነት ክብር ዝቅ ሲያደርግ ዝምታን ትመርጣላችሁ? ​ይህ ሰው በዚህ የተንሸዋረረ ሎጂኩ ከቀጠለ፣ ነገ በ«ቅዱስ ቁርባን» ጊዜ "የአምላክ ሥጋ ነው" ተብሎ ለምእመኑ የሚሰጠውን ቅዱስ ነገር፣ ከገዳይ መርዝ ጋር እንዳያመሳስልባችሁ ሥጋት አለን። እንዲህ ያለ የራሱን መሠረት የሚያፈርስ ጠበቃ ላለው እምነት፣ በእውነት ሌላ የውጭ ተቺ አያስፈልገውም። https://t.me/Abuyusra3 ​

Открыть в Telegram
Просмотры6 540+222%к среднему
Пересылки—
Реакции39
Комментарии—