#Album_Release_Event ወገንታትስ ሰላም ይብዛላችሁ 🤗 👉🏼ለአልበም ምርቃት መረሃ ግብር ቀን የምትመጡትን ልጆች ቁጥር በውል ለማወቅ እንዲመቸን ከታች ያለውን Google Form እንዲሞሉ በጌታ ፍቅር እናሳስባችኋለን።🙏🏻 👉🏼ይገባሃል የአልበም ምርቃት Google Form👈🏼 ✨✨ለመረሃ ግብሩም ወዳጅ ቤተሰቦቻችሁን እንድትጋብዙ እናሳስባችኋለን ✨✨ 📌አደራ ለኹሉም ነገር ግን መጸለይን እንዳንረሳ ተባረኩ!!! Follow AASTU ECSF On : Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
Open in Telegram
AASTU-ECSF
Evangelical Christian Students' Fellowship at AASTU CBE: 1000805392529 Fikat Alemu And/Or Dagim Mengiste Telebirr: 0931106178 Daniel Kebede Stay tuned via: @galleryaastuecsfBot @souceoflifeBot @AASTU_Anony_Counseling_bot @i4u_contact_bot
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 22, 2026 | 1,153 |
| Nov 23, 2026 | 1,020 |
| Nov 24, 2026 | 993 |
| Nov 25, 2026 | 850 |
Most viewed this month
- 01Views1.26KForwards—Reactions35Comments—
- 02Views1.13KForwards—Reactions29Comments—
- 03Views1.07KForwards—Reactions10Comments—
- 04Views1.06KForwards—Reactions21Comments—
Latest posts
📌ወገኖች ብዙ ግራ መጋባት እያየን ነው እናም Challengeኡን በተመለከተ Screenshot የምትልኩት በእነዚህ Account ነው እሺ Telegram: @aastuecsfcontact Instagram: AASTU ECSF Tiktok: AASTU ESCF
Open in Telegram✨✨✨#General_Fellowship✨✨✨ ✨✨✨#Devotional_Teaching_Night✨✨ ሰላም ወገንታትስ Mid እንዴት ይዟቹአል ባካችሁ 😁... ምንም ይሁን ጌታ ግን መልካም ነው ዛሬ የምንወደው የህብረት ጊዜ ይኖረናል 🧎➡️የፀሎት ጊዜ 🎹 የዝማሬ ጊዜ 🗣ስለ ፀሎት በስፋት እንማራለን 🤩እንዲሁም ወሳኝ ማስታወቂያዎች ይኖሩናል 📌 የጥሞና ጊዜ ከ11:30 ስለሚጀምር መገኘታችሁን እንዳትረሱ እንላለን። 📌 ልብ በሉ ባለፈው እንደተነገረው በፌሎሺፓችን የተዘጋጀው Wristband የደረሰ በመሆኑ ሁላችሁም ለዚያ ተዘጋጅታችሁ እንድትመጡ ይሁን ተባረኩ🙌 #የመንግስቱ_ተስፋ #በማየት #በመኖር #በመመስከር Follow AASTU ECSF On : Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
Open in Telegram🔥🔥 #DIGITAL_CHALLENGE 🔥🔥 ባለፈው እሮብ እንደተነገረው፣ ዛሬ ከ4:00 ጀምሮ DIGITAL CHALLENGE ይኖረናል! 🤩 3 አሸናፊዎች፣ 3 ልዩ ሽልማቶች! 👀🎁 እናንተም ከአሸናፊዎቹ መካከል ለመሆን ዝግጁ ናችሁ? እንዴት መሳተፍ ትችላላችሁ? 📲 የFellowship የማህበራዊ ሚዲያ ገጻችንን Follow አድርጉ። 🔁 የአልበም ምርቃት ማስታወቂያ ቪዲዮውን Repost አድርጉ። 📩 ቪዲዮውን ከ5 ሰዎች በላይ ላኩ፤ እነሱም ገጻችንን Follow እንዲያደርጉ ጋብዙ። 📸 ያጋራችሁትን ማስረጃ (Screenshot) ወደ የFellowship Instagram ,Telegram ወይም TikTok ገጻችን ላኩ። Telegram: @aastuecsfcontact Instagram: AASTU ECSF Tiktok: AASTU ESCF 🏆 ቪዲዮውን ለብዙ ሰዎች ያጋሩ 3 ተሳታፊዎች አሸናፊ ይሆናሉ! ⏰ የሚያበቃበት ሰዓት: ረቡዕ ማታ 2:00! 🔥 አሁኑኑ ይሳተፉ! ያጋሩ! ከ3ቱ አሸናፊዎች አንዱ ይሁኑ! ቪዲዮውን ለማግኘት: Instagram: ALBUM RELEASE DIGITAL CHALLENGE Tiktok: ALBUM RELEASE DIGITAL CHALLENGE Follow AASTU ECSF On : Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
Open in Telegram🎓🎓🎓#GC_Batch_Program 🎓🎓🎓 ሰላም እንዴት ናችሁ GCያንስ 🤗 ቤተሰቦቻችን🧑🎓 👉🏼ዛሬ ዘወትር ማክሰኞ 12:00 የሚኖረን የGC batch ፕሮግራም እንደቀጠለ ነው። በሰዓቱም አብረን የምንፀልይበት ፣ በዝማሬ የምናመልክበት አንዲሁም ከ እግዚአብሔር ቃል የምንማርበት ጊዜ ይኖረናል። 👉🏼ስለዚህ 12:00 ጀምሮ GC የሆንን ሁላችንም በቂሊንጦ መካነየሱስ ቤተክርስቲያን (Fellow በሚደረግበት ቦታ) በጊዜ ሳናረፍድ ፣ ከወንድም እህቶቻችን ጋር ተጠራርተን በጊዜ እንገኝ። #የመንግስቱ_ተስፋ #በማየት #በመኖር #በመመስከር Follow AASTU ECSF On : Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
Open in Telegram#OLD_TESTAMENT_READING_CHALLENGE 👉 ...በሕዝቡ መካከል መኖር የእግዚአብሔር ፍላጎትና ዓላማ ነው። ሆኖም ፍጹም ቅዱስ የሆነው አምላክ ቅዱስ ባልሆነ ሕዝብ መካከል እንዴት ሊኖር ይችላል? በዘጸአት 32 ላይ የተረከው የወርቅ ጥጃ ዓመጽ፣ እስራኤል ራሷ ለክፋትና አመፅ መሠረታዊ ችግር የተጋለጠች መሆኗን ፍንትው አርጎ ያሳያል። እስራኤል የምትኖረው በበሽታ፣ በውድቀትና በሞት በተሞላ የወደቀ ዓለም ውስጥ ነው፣ እናም የእርሱ አካል ናት። እኩይነት (ርኩሰት) ሁሉንም ነገር ይበክላል፣ እናም ቅድስና እና ርኩሰት መቼም ቢሆን መገናኘት የለባቸውም። ሲገናኙም ውጤቱ አስከፊ ይሆናል ። እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የሚኖር ከሆነ፣ ወደ ፊት የሚቀጥለው በምን መንገድ ነው?... 👉የብሉይ ኪዳን የንባብ ንቅናቄያችን እንደቀጠለ ነው! ቀጣዩ ንባባችን የሚሆነው የኦሪት ዘሌዋውያን መጽሃፍ ነው። 📌ምንም የፈተና ወቅት ላይ ብንሆን የእግዚአብሄርን ቃል ለማንበብ ጥቂት ደቂቃዎችን በቀን መመደብ ድርድር ሊኖረው ሚገባ ነገር አይደለም። 📌እነሆ የኦሪት ዘሌዋውያን መግቢያ 🫴 👉ኦሪት ዘሌዋውያን👈 (ማስፈንጠርያውን ይጫኑ) 📖✏️መልካም የንባብ ጊዜ 📖✏️ Follow AASTU ECSF On : Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
Open in Telegram✨✨ #First_year_batch_program ✨✨ ባለዓደራዎች ከጌታ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ 🤗 👉በዛሬው ፕሮግራማችንም ላይ ፦ 🙏 በፀሎት የጌታን ፊት እንፈልጋለን 🎹 ጌታን በዝማሬ እናመልካለን የጋራ የህብረት ጊዜ ይኖረናል 📍 ቂልንጦ መካነ ኢየሱስ ትወደዳላችሁ🥰 አታርፍዱ #የመንግስቱ_ተስፋ #በማየት #በመኖር #በመመስከር Follow AASTU ECSF On : Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
Open in Telegramሰላም የጌታ ልጆች እንዴት ናችሁ😊 በዚህ ሳምንት በምሥራቅ አፍሪካ ለሚኖሩ የአፋር (Afar) ሕዝቦች እንፀልያለን። 🙏 የአፋር ሕዝቦች በምሥራቅ አፍሪካ 🙏 የአፋር ሕዝቦች በኢትዮጵያ፣ በጅቡቲና በኤርትራ በተለይም እጅግ ሞቃታማና አስቸጋሪ በሆነው የአፋር በረሃ የሚኖሩ ኩሩ አርብቶ አደሮች ናቸው። አብዛኛዎቹ በግ፣ ፍየል፣ ከብትና ግመል እያረቡ በዘላንነት የሚኖሩ ሲሆን፣ በእሾህ አጥር በተከበበ ሰፈር "አሪ" በሚባሉ ተንቀሳቃሽ ጎጆዎች ይኖራሉ። በዋናነት የእስልምና ተከታዮች ቢሆኑም፣ ከእስልምና በፊት የነበሩ ባሕላዊ እምነቶችን (የሙታን መናፍስትንና ክታቦችን) አጥብቀው ይይዛሉ። በድርቅና በንጹሕ ውኃ እጥረት ከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ። መሠረታዊ መረጃ📊 -መኖሪያ : ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና ኤርትራ -የህዝብ ቁጥር : 291,000 -መተዳደሪያ : አርብቶ አደርነት (ከብት፣ ግመል፣ በግና ፍየል እርባታ) -ንዑስ ቡድኖች : አሳእማራ (ቀዮቹ) እና አዳእማራ (ነጮቹ) -ዋና ሃይማኖት : እስልምና (ከባሕላዊ እምነቶች ጋር) -ዋና ፍላጎት : ንጹሕ ውኃ እና የወንጌል ብርሃን 🤲🏽 የጸሎት ርዕሶች 🤲🏽 👉 ሥጋዊ ንጹሕ ውኃንም ሆነ የሕይወት ውኃ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያገኙ እንፀልይ። 👉 ለረዥም ጊዜ አብረዋቸው የሚቆዩ ታማኝ የክርስቶስ ሠራተኞች እንዲላኩላቸው እንፀልይ። 👉 ወንጌል በሬዲዮና ከባሕላቸው ጋር በሚስማማ መንገድ ሲሰራጭ እግዚአብሔር እንዲቀባውና ልባቸውን እንዲከፍት እንፀልይ። የአፋር ሕዝቦች ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ በግል፣ በsmall group፣ በteam እንፀልይ። Follow AASTU ECSF On : Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
Open in Telegramእንዴት ናችሁ ቤተሰቦች?🤗🤗🤗 በጉጉት ስንጠብቀው የነበረዉ Wristband አምና ያልነበሩ የቀለም አማራጮችን ጨምሮ በ 10 የተለያዩ ቀለሞች እና በ2 Size እጅግ ውብ ሆኖ ተሰርቶ መጥቷል። 🎉🎉🎉 የዚህ Wristband አላማዎችም ፦ ➡️ የአመቱ መሪ ሃሳባችንን (Theme) በመያዝ: 👑HOPE OF THE KINGDOM👑 በሚል የተሰራ ሲሆን የአመቱን መሪ ሃሳባችንን እንድናስታውስበት ይሆናል። ➡️ AASTU ECSF ህብረታችንን የምናስታውስበት ወደፊት ከፌሎም ከወጣን በኋላ አሪፍ Memory ይሆንልናል። ➡️ በግቢም ውስጥ ሁላችንም እጃችን ላይ አድርገነው ስንታይ ሌሎች ሰዎች ደግሞ ምን እንደሆነ ይጠይቁናል እናም ስለ መንግስቱ ተስፋ ለማካፈል እንዲሁም ስለ ህብረታችንም ተናግረን ወደ ፌሎ ለመጋበዝ እንጠቀምበታለን። ➡️ ሁላችንም ስንገዛ ደግሞ በተወሰነም መንገድ ህብረታችንን በገንዘብም እናግዛለን። =========================== 🗓 የፊታችን ረቡዕ ህዳር 16 ከፌሎ ፕሮግራም በፊት 11:00 ላይ ቀድመን በመገኘት ሁላችንም እንድንገዛ እንዲሁም ደግሞ መግዛት ለማይችሉም ወንድምና እህቶቻችንም ገዝተን እንድንሰጥ አደራ ማለትን እንወዳለን። 🙏🙏🙏 እንዲሁም Fund Coordinators ጋር እየደወላችሁ በምትፈልጉት ቀለም መርጣችሁ መግዛት ትችላላችሁ። Fund Coordinators: +251961169845.. Selam +251937724006.. Abenezer +251929104747.. Hiwot +251932081652.. Samuel #የመንግስቱ_ተስፋ #በማየት #በመኖር #በመመስከር Follow AASTU ECSF On : Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
Open in Telegram#Sunday_Devotion የምህረት እቅፍ “ነገር ግን ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየው፥ አዘነለትም፥ ሮጦም ሄዶ አንገቱን አቀፈው ሳመውም።” ሉቃስ 15፥20 👉አንዳንድ ጊዜ ከእግዚአብሔር ለመራቃችን ምክንያት የሚሆነው ስህተታችን ብቻ ሳይሆን ወደ እርሱ ለመመለስ ማፈራችንም ጭምር ነው። የሠራነውን ስህተት እያሰብን እንዴት ይቀበለኛል? ብለን እንጠራጠራለን። በዚህ ክፍል ውስጥ የሚያስደንቀው ልጁ ወደ አባቱ መመለሱ ብቻ አይደለም አባቱ ገና ከሩቅ አይቶ ወደ እርሱ መሮጡ ነው። 👉 በዚያ ዘመን በአይሁድ ባህል ወንድ ሆኖ እንደዉም የቤተሰብ አለቃ ሆኖ በአደባባይ መሮጥ በጣም አሳፋሪ እና የተዋረደ ተግባር ነበር። ግን ይህ አባት ልጁን ለመቀበል የራሱን ክብር እንኳን አላሳሰበውም። እንደዉም በግሪክኛው የተጻፈው Dramōn (δραμών) በፍጥነት መሮጥ... የአባቱን ጉጉትና ልጁን ለመቀበል ያለው ፍላጎት ከባህሉ ከክብሩ እና ከማንነቱ እጅግ የላቀ መሆኑን ያሳያል። 👉ከዚያም በተጨማሪ ከልብ በሆነ ጥልቅ ርኅራኄ በድህነት፣ በውርደት እና በውድቀት ተሸፍኖ የመጣውን ልጁን አቅፎ ወደ ልቡ አስጠጋው፣ ሳመው። 👉አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔርን ፍቅር በራሳችን ሁኔታ እንለካዋለን። ግን የአባቱ ፍቅር የልጁን ውድቀት እንደማይበልጥ ያሳየናል። ይህ ማለት ስህተታችን ምንም አይደለም ማለት ሳይሆን ከስህተታችን በኋላም ወደ አባታችን የመመለስ ተስፋ አለን ማለት ነው። 👉ልጁ ከአባቱ ቤት ርቆ ብዙ ነገር አጥቷል ግን ወደ ቤቱ ሲመለስ ያላጣውን አንድ ነገር አገኘ የአባቱን ፍቅር። 👉ምናልባት ብዙ ተሳስተናል፣ ብዙ ጊዜ ወድቀናል፣ የማይገባንንም አድርገናል ብለን ወደ እርሱ ለመመለስ እንፈራ ይሆናል። ግን ከእግዚአብሔር ርቀን ብንቆይ አሁንም ወደ እርሱ ለመመለስ አልረፈደም። ምክንያቱም በንስሐ ወደ እርሱ እንድንመለስ የሚጋብዘን የማይጠፋ ፍቅር ከሩቅ የሚያየን፣ በርኅራኄ የሚቀበለንና በፍቅሩ የሚያቅፈን አባት አለን። ዛሬም እንደተለመደው ከወንድም እህቶቻችን ጋር በመሆን አካባቢያችን በሚገኝ ቤተክርስትያን በተዋረደ ልብ በጌታ ፊት መቅረብ እንድንችል ወደ ጌታ ቤት መገስገሳችሁን አትዘንጉ 🙌🏿። Follow AASTU ECSF On : Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
Open in TelegramConnections
Similar channels
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹@ortodox_27Religion5.06K
Ethiopian Orthodoxs Daily@ethiopianorthodoxsReligion5.13K
የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች@ne_siha_eslamikReligion4.65K
Y4C@youth4christReligion4.48K
መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር@meazahaymanotReligion5.59K
ተንቢሃት Tenbihat – ኢስላማዊ ህግጋት እና ተግሳፃት@tenbihatReligion5.77K
Abdu & Hasu@abduftsemierReligion3.98K
ኡስታዝ አቡየሕያ አብዱልዋሲዕ | قناة أستاذ أبي يحيى عبدالواسع@menhajadamaReligion3.87K