Account
Ethiopian Orthodoxs Daily

Ethiopian Orthodoxs Daily

በቤተ ክርስቲያናችን በየቀኑ የሚታሰብ ቅዱሳን፤ የመፅሐፍ ቅዱስ ምንባባት ፤ ብሂለ አበው እና አስተማሪ የሆኑ መንፈሳዊ ፅሁፎች ያገኙበታል::Share https://t.me/ethiopianorthodoxs //like page on facebook fb.me/ethiopianorthodxs ለሀሳብ አስተያየትዎ @Yakob520

Username
@ethiopianorthodoxs
Category
Religion
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers5,130
Avg views per post, 7d384−45.5% vs prev 7d
ERR7.49%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Oct 31, 20261,020
Nov 6, 2026995
Nov 12, 2026739
Nov 15, 2026705
Nov 21, 2026481
Nov 24, 2026287

Most viewed this month

  1. 01

    No text

    Photo
    Views1.02K
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—
  2. 02

    ✝መድኃኔዓለም በአበው አንደበት📖 ጽሐፉ የተወሰደው፡-ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከብሂለ አበው ነው። "ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።”        ዮሐንስ 1 : 2 “እኛ ወደ እርሱ መውጣት ሲያቅተን መድኃኔ ዓለም ወደኛ ወረደ” (አቡነ ሺኖዳ) “ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው” (ዮሐ 3፡13) “ከእባብ ማሳት ምክንያት በበደልን ጊዜ ከዘለዓለማዊ ሕይወት ራቅን፣ ደስታ ካለበት ከገነትም ወጣን፣ አንተ ግን ለዘለዓለሙ አልጣልኸንም፤ … በኋላ ዘመንም በጨለማና በሞት ለምንኖር ለእኛ ታየህልን፣ በመንፈስ ቅዱስ ከድንግል ማርያም ሰው የሆነ የአንድ ልጁንም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን በእኛ ላይ አኖርህ” (ባስልዮስ ዘቂሳርያ) “ማዳኑም ከወደረኞቻችንና ከሚጠሉን ሁሉ እጅ ነው ይህም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው፡፡ ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል” (ካህኑ ዘካርያስ በሉቃ 1፡71-79) “የሰው ልጅ በወደቀ ጊዜ እግዚአብሔር መምሰል ተነጥቆ ነበር፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው ያጣነውን መልክ ሊመልስልን ነው” (ቅዱስ ሚናስ) “ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአል” (ቅዱስ ጳውሎስ ሮሜ 8፡29) “ባለመታዘዝ የእንጨት ፍሬን በመብላት ምክንያት የመጣውን ሞት፣ መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በመታዘዝ በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞትን አስወግዶ ሕይወትን ሰጠን” (ቅዱስ ሄሬኔዎስ) “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ” (ፊልጵ 2፡8) “እኛ ሁላችን አምላካችን እግዚአብሔር መሆኑንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ የለበሰው ቃል መሆኑን እናምናለን፡፡ እርሱ በመለኮቱና ሰው በመሆኑ ፍጹም እንደሆነ እናምናለን፡፡ አምላክነቱ ከሰውነቱ ለቅጽበት እንኳ እንዳልተለየም እናምናለን፡፡ ሰው መሆኑ ከመለኮተ ጋር ያለ መቀላቀል ያለ መለወጥ፣ ያለ መከፋፈልና መለያየት የሆነ ነው” (ቅዱስ ቄርሎስ) “የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ” (ቅዱስ ጳውሎስ 1ኛ ቆሮ 8፡9) “እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፡፡ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ” (ቅዱስ ጳውሎስ ፊልጵ 2፡6-7) “ሔዋንን ዲያብሎስ አሳታት የሞት ምክንያት የሚሆን ቃልን ወለደች፡፡ ድንግል ማርያም ግን መልአክ በአበሠራት ጊዜ ሁሉን ወደ ዘለዓለም ሕይወት የሚመራ አካላዊ ቃልን በሥጋ ወለደች” (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) “መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል” (ሉቃ 1፡35) “የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ” (ገላ 4፡4) “የጠፋ በግ አዳምን የፈለገው ባገኘውም ጊዜ የተሸከመው እውነተኛ ቸር ጠባቂያችን ክርስቶስ ነው” (ተአምረ ማርያም) “መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?…ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል…የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል” (ሉቃ 15፡ 4-6) “ማንም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የማያምን ፀረ ክርስቶስ ነው፡፡ በመስቀል ላይ መከራን በመቀበል ኃጢአታችንን ተሸከመ” (ቅዱስ ፖሊካርፐስ) “ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና፡፡ እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ…ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ” (1ኛ ጴጥ 2፡22-24) “በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል…እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ፡፡ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቾቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም” (ኢሳ53፡1-12) “ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለእኛ ንስሐ ለገባነው ክቡር የሆነ ሰማያዊ አክሊልን ታቀዳጀን ዘንድ የእሾህ አክሊል ደፋህ” (ቅዱስ በርተሎሚዎስ) “ኢየሱስ ክርስቶስ ድል አድራጊ ንጉሥ ነው የምንለው ተሰቅሎ ሞቶ ስለተነሣ ስላየሁት ብቻ አይደለም፤ እርሱ ለዘመናት ድል አድራጊ ነውና” (ዮሐንስ አፈወርቅ) ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።1ዩሐ.1፥9 “አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል” (ራእይ 5፡5) “በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል” (ራእይ 17፡14) “ኢየሱስ ክርስቶስ የማይጠልቅ ፀሐይ፣ የማይጠፋ መብራት፣ በቅዱሳን ላይ ዘወትር የሚያበራ ፀሐይ ነው” (ባስልዮስ ዘቂሳርያ) “እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህንእንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ” (ራእይ 22፡16) "ክርስቶስ በስጋ መጣ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው" ሮሜ 9-5 ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️

    Text
    Views995
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—
  3. 03

    No text

    Photo
    Views739
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—
  4. 04

    #ኅዳር_6 #ደብረ_ቁስቋም ኅዳር ስድስት በዚህች ዕለት ክብርት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ከስደት በሚመለሱበት ጊዜ ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ዐረፉ፡፡ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ከስደት በተመለሰች ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ልጇን ይዛ ከእነ ዮሴፍ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ግብፅ ደርሰው በዚያ ቢቀመጡም ነገርን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ እንዲያውም በምድረ ግብፅ ብዙ ተሠቃይተዋል፡፡ ከግብፅም ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሰላምና በፍቅር ተቀበላቸው፡፡ ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና የኢትዮጵያ ሰዎች እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡ ‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..›› ብለው እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም አደረጉላቸው፡፡ እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር›› አለችው፡፡ ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡ በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤ የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡ እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም እጅግ ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡ ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…›› እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለክብርት እናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትለው የተወደደ ልጇ ግን ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡ ተመልሰውም ሊሄዱ ሲነሡ የኢትዮጵያ ሰዎች ልዩ ልዩ አምሐ እጅ መንሻ ሰጧቸው፡፡ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ ሽቱ እና ሥንቀቸውን በግመሎች ላይ ጭነው እመቤታችንንና የተወደደ ልጇንም በበቅሎ ላይ አስቀምጠው በክብር ሸኟቸው፡፡ እመቤታችንም ልጇን ታቅፋ በበቅሎ ተቀምጣ በበረሃው በመጓዝ ወደ መጣችበት አገር ሄደች፡፡ ኢትዮጵያንም የሰጧትን ብዙ እጅ መንሻዎች በግመሎች ጭና ይዛ ወደ አገሯ በተመለሰች ጊዜ ከአንድ ባሕር ዳር ደረሰች፡፡ ከዚያም የጀልባውን ባለቤት ‹‹እግዚአብሔርን ስለመውደድ አሻግረኝ›› ብላ ለመነችው፡፡ ባለጀልባውም ‹‹እነሆ ዕቃ የተጫኑ አምስት ግመሎችና ከአንቺ ጋር ከዚህም ሕፃን ጭምር አምስት ሰዎች እመለከታለሁ፣ አንቺ የተቀመጥሽባት በቅሎም አለች፡፡ ጀልባዋም ታናሽ ናት፣ የመቀመጫ ክፍሏም በውስጧ የተሳፈሩት ሰዎችም ተጨናንቀው ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ እንዴት ላሻግርሽ እችላለሁ? ነገር ግን እመቤቴ ሆይ! ይቅርታ አድርጊልኝ ይህን በክፋት አላደረግሁትምና›› አላት፡፡ ክብርት እመቤታችንም የጀልባው ባለቤት ሊያሻግራት እንዳልቻለ በተረዳች ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆንህ ይህን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር የአምላክነትህን ሥራ ትሠራ ዘንድ እለምንሃለሁ›› ስትል ማለደችው፡፡ ያንጊዜም ጌታችን ክብርት እናቱን ‹‹የወለደሽኝ እናቴ ሆይ! አትዘኝ›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእኔ ፈቃድ በአባቴ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ካንቺ ሰው ሆኛለሁና ሰው መሆኔንም ከአባቴ በቀር መስተፍሥሒ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም በቀር ያወቀ የለም፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለው ዘንድ እመጣለሁ፡፡ ያችንም ሰዓት የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የአዳም ልጆችም ቢሆኑም ከእኔና ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስም በቀር የሚያውቃት የለም፡፡ ያንጊዜ ‹ዐመፅን የሚናገር አንደበት ሁሉ ይዘጋል› ብሎ አባትሽ ዳዊት እንደተናገረ እከራከራለሁ የሚል አንደበት እንደድዳ ምላሽ ያጣል›› አላት፡፡ ክብርት እመቤታችን ማርያምም ይህንን ሁሉ ምሥጢር የተወደደ ልጇ የነገራትን ታስተውለው በልቧም ትጠብቀው ነበር፡፡ ጌታችንም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለክብርት እናቱ ይህንን ከነገራት በኋላ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ከወንዙ ማዶ ጢር በሚባል ተራራ ያሉትን ድንጋዮች ጠቀሳቸው፡፡ ያንጊዜም እነዚህ ድንጋዮች እየተገለባበጡ መጥተው እንደ ጀልባ ሆነው በወራጁ ወንዝ ላይ ተንሳፈፉ፡፡ ከዚያም እመቤታችንን ከሕፃኑ ጋር ከነቤተሰቧና ከነጓዟ አሻገረሯት፡፡ እነዚህንም ድንጋዮች ያዩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አድንቀው ‹‹ብቻውን ድንቅ ተአምራት ያደረገ፣ እስራኤልን የፈጠረ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ነው›› እያሉ አመሰገኑ፡፡ እነዚህም የተባረኩ ሰዎች ወንዙን ከተሻገሩ በኋላ በዚህች አገር ለስምንት ቀን ተቀመጡ፡፡ ከዚህም በኋላ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለደረገላት መልካም ሥራ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽማ እያመሰገነች ወደ አባቷ ወደ ዳዊት አገር ተመለሰች፡፡ ዳግመኛም በኋለኛው ዘመን ጌታችን በዚህ በደብረ ቍስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸውና ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ የቍርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነገር የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮቹ ሆኑ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን ። ( ስንክሳር ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ገጽ)

    Text
    Views705
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—

Latest posts

#3990Text
Views287−59%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3989Text

በዓለ ሢመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ‹ሚካኤል ሥዩም በዲበ ኃይላት፤ በኃይላት ላይ የተሾምክ ሚካኤል› ሲል ያመሰገነው ቅዱስ ሚካኤል በኃይላት መላእክት ላይ የተሾመ ሊቀ መላእክት እንደመሆኑ በዓለ ሢመቱ ኅዳር ፲፪ ቀን በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ይከበራል፡፡ (መጽሐፈ አክሲማሮስ) ኃይላት የተባሉት መላእክትም ሰዎች በዓለም ፈተና ውስጥ ሆነው ሰይጣን ሊያደክማቸው ሲፈልግ ኃይልን ብርታትን የሚሰጡ፣ ይህን ዓለም ንቀው በበርሃ ወድቀው ከሥጋ ምኞት ጋር የሚጋደሉትን፣ በከተማም እየኖሩ መንፈሳዊ ትሩፋት የሚያደርጉትን ደግሞ የሚያበረቱ ናቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በመልእክቱ ‹እርሱም ወደ ሰማይ ያረገ እግዚአብሔርም ተቀምጦ ያለ መላእክትና ሥልጣናት ኃይላትም የተገዙለት ነው…› ሲል  ‹ኃይላት› በማለት ያነሣቸው በኢዮር አራተኛይቷ  ከተማ  የሚኖሩትን  ነው፡፡ በእነዚህ ላይ እግዚአብሔር  ቅዱስ ሚካኤልን አለቃቸው አድርጎ ሾሞታል፡፡ (፩ኛጴጥ.፫፥፳፪) የቅዱስ  ሚካኤል  ሢመት  በነገደ  መላእክት  ላይ ብቻም ግን  አይደለም፤  የእግዚአብሔር  ሕዝብ  በሆኑት  ላይም ጭምር ነው፡፡ ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ትርጓሜ በዕብራይስጥ ‹‹እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!›› ማለት እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠቅሳሉ፤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ላይ እንዳሰፈሩት ደግሞ የስሙን ፊደላት በመተንተን እንዲህ ተርጉመውታል፤ ሚ-መኑ፣ ካ-ከመ፣ ኤል-አምላክ፤ ‹‹መኑ ከመ አምላክ፤ እንደ አምላክ  ማን ነው!›› (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ) የሰማይ ሠራዊት ሁሉ አለቃቸው  ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ  ይህ ኃያል መልአክ  ቅዱስ  ሚካኤል በብሉይ  ኪዳን  የእግዚአብሔር  ሕዝብ  የተባሉትን  እስራኤል  ዘሥጋን  ሲረዳና  ሲጠብቅ  እንደነበረ ተጽፎልን  እናገኛለን፡፡  ለምሳሌ  መልአኩ  ቅዱስ  ሚካኤል  ለኢያሱ  በኢያሪኮ  ምድረ  በዳ  እንደተገለጠለት  ‹‹… ዐይኑን  አንሥቶ  ተመለከተ፤  እነሆም፥  የተመዘዘ  ሰይፍ  በእጁ የያዘ  ሰው  በፊቱ  ቆሞ አየ፤  ኢያሱም  ወደ  እርሱ  ቀርቦ፥  “ከእኛ  ወገን  ወይስ  ከጠላቶቻችን  ወገን  ነህ?”  አለው፡፡  እርሱም “እኔ  የእግዚአብሔር  ሠራዊት  አለቃ  ነኝ፤  አሁንም  ወደ  አንተ መጥቼአለሁ፡፡” ሲል ተናግሯል፡፡ (ኢያ.፭፥፲፫) እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ‹‹ በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ፥ ወዳዘጋጀሁልህም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ ፥እኔ መልአኬን በፊትህ እልካለሁ››  እንዲል፤  ሹመቱ  በእግዚአብሔር  ሕዝብ  ላይም  በመሆኑ  ስለ  እነርሱ ከእግዚአብሔር ምሕረትን ይለምንላቸው  ነበር፡፡ (ዘፀአት.፳፫፥፳) ነገር ግን ኃጢአት ሲሠሩ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ይቀጣልና ሕዝቡን  ‹‹ራስህን ጠብቅ፤ ስማው፤ እንቢም አትበለው፤ ስሜ በእርሱ ስለሆነ ይቅር አይልምና›› ብሎ  አስጠንቅቋቸው  ነበር፤   ይህም   ቅዱስ  ሚካኤል  በእግዚአብሔር  ሕዝብ  ላይ  መሾሙን  ያስረዳናል፡፡  (ዘፀ.፳፫፥፳፩) ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር  ሕዝብ  ላይ  ቅዱስ ሚካኤል  ስለመሾሙ ሲመሰክር ‹‹በእውነት   በመጽሐፍ   የተጻፈውን   እነግርሃለሁ፤   በዚህም  ነገር  ከአለቃችሁ  ከሚካኤል  በቀር   የሚረዳኝ  ማንም  የለም›› ብሎአል፡፡  ስለዚህም  ለኢያሱ   የተገለጠውና  እስራኤላውያንንም  የመራው  መልአክ  ቅዱስ  ሚካኤል  መሆኑን እንረዳለን፡፡ (ዳን.፲፥፳፩) የቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት በሐዲስ ኪዳንም እንደነበር ይህ ነቢይ በትንቢቱ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ  ልጆች  የሚቆመው  ታላቁ  ሚካኤል  ይነሣል›› በማለት  ተናግሮለታል፡፡   ስለዚህም   ቅዱስ  ሚካኤል   እኛን  ከሰይጣን  አሽክላና  ወጥመድ  ይጠብቀንና  በጸሎቱ  በእግዚአብሔር  ፊት  ይቆምልን  ዘንድ  በእኛም  ላይ  ሹም  ነው፡፡ ምክንያቱም  እኛ  የእግዚአብሔር  ሕዝቦችና  የርስቱ ወራሾች ነንና፡፡  (ዳን.፲፪፥፩) በመጽሐፈ ስንክሳርም ተመዝግቦ እንደምናኘው ቅዱስ ሚካኤል በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠርቶለታል፤ እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙም በጊዜው እንዲወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲያደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲያደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልዳልና፡፡ (ስንክሳር ኅዳር ፲፪) ስለሆነም በኃጢአት ባርነት ተይዘን በችግር እና በመከራ ውስጥ ተዘፍቀን ለምንኖር ሰዎች ስለ  ሕዝበ  እስራኤል  በእግዚአብሔር  ፊት  የቆመው  ሊቀ  መላእክት  ቅዱስ  ሚካኤል  ለእኛም  ያማልደንና ተራዳኢ ይሆነን ዘንድ በጸሎት እንማጸነው።  አምላካችን  እግዚአብሔርም  የምሕረት  ፊቱን  ወደ  እኛ  በመመለስ በጸብና  በጦርነት  ምትክ  ፍቅርን፣  ሰላምንና  መግባባትን፤  በመለያየት  ምትክ አንድነትን እንዲሰጠን በቅዱስ ሚካኤል ስም እንለምን። የሊቀ መላእክት  ቅዱስ  ሚካኤል  አማላጅነትና ተራዳኢነት  አይለየን፤  አሜን፡፡ ምንጭ፤ መጽሐፈ አክሲማሮስ፣ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ፣መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኀ ኅዳር

Open in Telegram
Views481−32%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3988Text

#ኅዳር_6 #ደብረ_ቁስቋም ኅዳር ስድስት በዚህች ዕለት ክብርት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ከስደት በሚመለሱበት ጊዜ ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ዐረፉ፡፡ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ከስደት በተመለሰች ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ልጇን ይዛ ከእነ ዮሴፍ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ግብፅ ደርሰው በዚያ ቢቀመጡም ነገርን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ እንዲያውም በምድረ ግብፅ ብዙ ተሠቃይተዋል፡፡ ከግብፅም ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሰላምና በፍቅር ተቀበላቸው፡፡ ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና የኢትዮጵያ ሰዎች እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡ ‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..›› ብለው እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም አደረጉላቸው፡፡ እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር›› አለችው፡፡ ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡ በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤ የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡ እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም እጅግ ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡ ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…›› እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለክብርት እናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትለው የተወደደ ልጇ ግን ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡ ተመልሰውም ሊሄዱ ሲነሡ የኢትዮጵያ ሰዎች ልዩ ልዩ አምሐ እጅ መንሻ ሰጧቸው፡፡ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ ሽቱ እና ሥንቀቸውን በግመሎች ላይ ጭነው እመቤታችንንና የተወደደ ልጇንም በበቅሎ ላይ አስቀምጠው በክብር ሸኟቸው፡፡ እመቤታችንም ልጇን ታቅፋ በበቅሎ ተቀምጣ በበረሃው በመጓዝ ወደ መጣችበት አገር ሄደች፡፡ ኢትዮጵያንም የሰጧትን ብዙ እጅ መንሻዎች በግመሎች ጭና ይዛ ወደ አገሯ በተመለሰች ጊዜ ከአንድ ባሕር ዳር ደረሰች፡፡ ከዚያም የጀልባውን ባለቤት ‹‹እግዚአብሔርን ስለመውደድ አሻግረኝ›› ብላ ለመነችው፡፡ ባለጀልባውም ‹‹እነሆ ዕቃ የተጫኑ አምስት ግመሎችና ከአንቺ ጋር ከዚህም ሕፃን ጭምር አምስት ሰዎች እመለከታለሁ፣ አንቺ የተቀመጥሽባት በቅሎም አለች፡፡ ጀልባዋም ታናሽ ናት፣ የመቀመጫ ክፍሏም በውስጧ የተሳፈሩት ሰዎችም ተጨናንቀው ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ እንዴት ላሻግርሽ እችላለሁ? ነገር ግን እመቤቴ ሆይ! ይቅርታ አድርጊልኝ ይህን በክፋት አላደረግሁትምና›› አላት፡፡ ክብርት እመቤታችንም የጀልባው ባለቤት ሊያሻግራት እንዳልቻለ በተረዳች ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆንህ ይህን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር የአምላክነትህን ሥራ ትሠራ ዘንድ እለምንሃለሁ›› ስትል ማለደችው፡፡ ያንጊዜም ጌታችን ክብርት እናቱን ‹‹የወለደሽኝ እናቴ ሆይ! አትዘኝ›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእኔ ፈቃድ በአባቴ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ካንቺ ሰው ሆኛለሁና ሰው መሆኔንም ከአባቴ በቀር መስተፍሥሒ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም በቀር ያወቀ የለም፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለው ዘንድ እመጣለሁ፡፡ ያችንም ሰዓት የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የአዳም ልጆችም ቢሆኑም ከእኔና ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስም በቀር የሚያውቃት የለም፡፡ ያንጊዜ ‹ዐመፅን የሚናገር አንደበት ሁሉ ይዘጋል› ብሎ አባትሽ ዳዊት እንደተናገረ እከራከራለሁ የሚል አንደበት እንደድዳ ምላሽ ያጣል›› አላት፡፡ ክብርት እመቤታችን ማርያምም ይህንን ሁሉ ምሥጢር የተወደደ ልጇ የነገራትን ታስተውለው በልቧም ትጠብቀው ነበር፡፡ ጌታችንም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለክብርት እናቱ ይህንን ከነገራት በኋላ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ከወንዙ ማዶ ጢር በሚባል ተራራ ያሉትን ድንጋዮች ጠቀሳቸው፡፡ ያንጊዜም እነዚህ ድንጋዮች እየተገለባበጡ መጥተው እንደ ጀልባ ሆነው በወራጁ ወንዝ ላይ ተንሳፈፉ፡፡ ከዚያም እመቤታችንን ከሕፃኑ ጋር ከነቤተሰቧና ከነጓዟ አሻገረሯት፡፡ እነዚህንም ድንጋዮች ያዩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አድንቀው ‹‹ብቻውን ድንቅ ተአምራት ያደረገ፣ እስራኤልን የፈጠረ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ነው›› እያሉ አመሰገኑ፡፡ እነዚህም የተባረኩ ሰዎች ወንዙን ከተሻገሩ በኋላ በዚህች አገር ለስምንት ቀን ተቀመጡ፡፡ ከዚህም በኋላ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለደረገላት መልካም ሥራ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽማ እያመሰገነች ወደ አባቷ ወደ ዳዊት አገር ተመለሰች፡፡ ዳግመኛም በኋለኛው ዘመን ጌታችን በዚህ በደብረ ቍስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸውና ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ የቍርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነገር የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮቹ ሆኑ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን ። ( ስንክሳር ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ገጽ)

Open in Telegram
Views7050%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3986Text

✝መድኃኔዓለም በአበው አንደበት📖 ጽሐፉ የተወሰደው፡-ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከብሂለ አበው ነው። "ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።”        ዮሐንስ 1 : 2 “እኛ ወደ እርሱ መውጣት ሲያቅተን መድኃኔ ዓለም ወደኛ ወረደ” (አቡነ ሺኖዳ) “ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው” (ዮሐ 3፡13) “ከእባብ ማሳት ምክንያት በበደልን ጊዜ ከዘለዓለማዊ ሕይወት ራቅን፣ ደስታ ካለበት ከገነትም ወጣን፣ አንተ ግን ለዘለዓለሙ አልጣልኸንም፤ … በኋላ ዘመንም በጨለማና በሞት ለምንኖር ለእኛ ታየህልን፣ በመንፈስ ቅዱስ ከድንግል ማርያም ሰው የሆነ የአንድ ልጁንም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን በእኛ ላይ አኖርህ” (ባስልዮስ ዘቂሳርያ) “ማዳኑም ከወደረኞቻችንና ከሚጠሉን ሁሉ እጅ ነው ይህም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው፡፡ ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል” (ካህኑ ዘካርያስ በሉቃ 1፡71-79) “የሰው ልጅ በወደቀ ጊዜ እግዚአብሔር መምሰል ተነጥቆ ነበር፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው ያጣነውን መልክ ሊመልስልን ነው” (ቅዱስ ሚናስ) “ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአል” (ቅዱስ ጳውሎስ ሮሜ 8፡29) “ባለመታዘዝ የእንጨት ፍሬን በመብላት ምክንያት የመጣውን ሞት፣ መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በመታዘዝ በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞትን አስወግዶ ሕይወትን ሰጠን” (ቅዱስ ሄሬኔዎስ) “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ” (ፊልጵ 2፡8) “እኛ ሁላችን አምላካችን እግዚአብሔር መሆኑንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ የለበሰው ቃል መሆኑን እናምናለን፡፡ እርሱ በመለኮቱና ሰው በመሆኑ ፍጹም እንደሆነ እናምናለን፡፡ አምላክነቱ ከሰውነቱ ለቅጽበት እንኳ እንዳልተለየም እናምናለን፡፡ ሰው መሆኑ ከመለኮተ ጋር ያለ መቀላቀል ያለ መለወጥ፣ ያለ መከፋፈልና መለያየት የሆነ ነው” (ቅዱስ ቄርሎስ) “የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ” (ቅዱስ ጳውሎስ 1ኛ ቆሮ 8፡9) “እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፡፡ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ” (ቅዱስ ጳውሎስ ፊልጵ 2፡6-7) “ሔዋንን ዲያብሎስ አሳታት የሞት ምክንያት የሚሆን ቃልን ወለደች፡፡ ድንግል ማርያም ግን መልአክ በአበሠራት ጊዜ ሁሉን ወደ ዘለዓለም ሕይወት የሚመራ አካላዊ ቃልን በሥጋ ወለደች” (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) “መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል” (ሉቃ 1፡35) “የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ” (ገላ 4፡4) “የጠፋ በግ አዳምን የፈለገው ባገኘውም ጊዜ የተሸከመው እውነተኛ ቸር ጠባቂያችን ክርስቶስ ነው” (ተአምረ ማርያም) “መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?…ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል…የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል” (ሉቃ 15፡ 4-6) “ማንም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የማያምን ፀረ ክርስቶስ ነው፡፡ በመስቀል ላይ መከራን በመቀበል ኃጢአታችንን ተሸከመ” (ቅዱስ ፖሊካርፐስ) “ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና፡፡ እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ…ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ” (1ኛ ጴጥ 2፡22-24) “በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል…እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ፡፡ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቾቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም” (ኢሳ53፡1-12) “ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለእኛ ንስሐ ለገባነው ክቡር የሆነ ሰማያዊ አክሊልን ታቀዳጀን ዘንድ የእሾህ አክሊል ደፋህ” (ቅዱስ በርተሎሚዎስ) “ኢየሱስ ክርስቶስ ድል አድራጊ ንጉሥ ነው የምንለው ተሰቅሎ ሞቶ ስለተነሣ ስላየሁት ብቻ አይደለም፤ እርሱ ለዘመናት ድል አድራጊ ነውና” (ዮሐንስ አፈወርቅ) ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።1ዩሐ.1፥9 “አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል” (ራእይ 5፡5) “በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል” (ራእይ 17፡14) “ኢየሱስ ክርስቶስ የማይጠልቅ ፀሐይ፣ የማይጠፋ መብራት፣ በቅዱሳን ላይ ዘወትር የሚያበራ ፀሐይ ነው” (ባስልዮስ ዘቂሳርያ) “እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህንእንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ” (ራእይ 22፡16) "ክርስቶስ በስጋ መጣ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው" ሮሜ 9-5 ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️

Open in Telegram
Views995+41%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3984Text
Views1,230+75%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3983Text

ቅዱስ ፊልጶስ:- አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት ዐሥራ አራት በዚች ቀን ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የሆነ አንዱ ቅዱስ ሐዋርያ ፊልጶስ አረፈ:: ጌታችንም በቂሣርያ አገር ውስጥ በአለፈ ጊዜ በውስጧ አስተማረ:: ትምህርቱንም ሰምቶ ክብር ይግባውና ጌታችንን አምኖ ተከተለው ከሰባ ሁለቱ አርድዕትም ጋር ተቆጠረ:: ጌታችን ይሰብኩ ዘንድ ሁለት ሁለት አድርጎ በላካቸው ጊዜ ከእርሳቸው አንዱ ይህ ደቀ መዝሙር ፊልጶስ ነው:: ከመድኃኒታችንም ዕርገት በኋላ ሐዋርያት ከሾሟቸው ከሰባቱ ዲያቆናት ውስጥ የተቆጠረ ነው:: እርሱም ወደ ሰማርያ ወርዶ አስተማረ:: ብዙዎችንም አሳምኖ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው:: ከዚህም በኋላ የተጎዳውን ሥራየኛ ሲሞንንም አጥምቆት ነበር:: እርሱ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በገንዘብ ሊገዛ አስቧልና:: ፊልጶስ ግን ይህን ሲሞን ገሰጸው። የእግዚአብሔርን ፀጋ በገንዘብ ሊገዛ ሽታልና። ከዚህም በኋላ ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ይሔድ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ፊልጶስን አዘዘው:: በሔደም ጊዜ ለኢትዮጵያ ንግሥት ለህንደኬ በጀሮንዷ የሆነ ጀንደረባውን አገኘው:: "እርሱም እንደ በግ ሊታረድ መጣ" የሚለውን የነቢይ ኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር:: ፊልጶስም ጀንደረባውን "የምታነበውን ቃል ታስተውላለህን?" አለው:: ጀንደረባውም "ያስተማረኝ ሳይኖር እንዴት አውቃለሁ አለ::" ፊልጶስም ስለ ጌታችን ስለ መከራው ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት ስለሆነው ሞቱ እንደተነገረ ተረጎመለት:: ጀንደረባውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አመነ:: ያን ጊዜም በፊልጶስ እጅ ከወንዝ ውኃ ውስጥ ተጠመቀ:: ከውኃውም በወጣ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ፊሊጶስን ነጥቆ ወሰደው:: ጀንደራባውም ሁለተኛ አላየውም:: ፊልጶስም ወደ አዛጦን ከተማ ደረሰ እያስተማረም  እስከ ቂሣርያ ሔደ በከተሞችም ሁሉ በመዞር ወንጌልን ሰበከ:: ከአይሁድና ከሳምራውያንም ብዙዎችን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን መልሶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው:: ለሐዋሪያ ፊልጶስም ከእርሱ ጋር ወንጌልን የሚሰብኩ አራት ሴቶች ልጆች ነበሩት:: አገልግሎቱንም ፈጽሞ በሰላም አረፈ:: በዛሬው መልዕክት የምንማረው የኢትዮጵያ ጀንደረባ ትኅትና በተለይም መፅሐፍ ቅዱስ አንባቢነቱን ነው። መፅሐፍትን ማንበብ ያልገባንን መምህራነ ቤተ ክርስቲያንን መጠየቅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ መገለጫ መሆኑን እንረዳለን። እኛንም በቅዱስ ሐዋርያው ፊልጶስ ጸሎት ይማረን:: በአባታችን አቡነ ሐረጋዊና ገብረ ክርስቶስ ጸሎትና ምልጃ ይጠብቀን:: በረከታቸውም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን:: 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️

Open in Telegram
Views1,100+56%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3982Text

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት አምስት በዚህች ቀን ተአምራቱና ትሩፋቱ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ የእግዚአብሔር ማደርያ የሆነ ቅዱስ አባት ተጋዳይ የአባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የመታሰቢያ ቀኑ ነው:: ይህ ጻድቅ ዕረፍቱ በመጋቢት ሲሆን ቃል-ኪዳን የተቀበሉበት ቀን በጥቅምት ነው:: በመጋቢት ወር በስፋት እና በጥልቀት መልእክቱን ልኬ ክብር ይግባውና ከቃል-ኪዳኑ በረከት ተካፋይ ሆነናል:: ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን በማንበብ በረከትና ቃል-ኪዳኑን በእምነት መቀበል ነው:: ይባረኩበታል:: ይቀደሱበታል:: ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስን በማንበቦ ወይ ሲነበብ በመስማቶ: በስማቸው የታነጸ ቤተ ክርስቲያን ሔደው በመሳለሞ: ማኅሌቱን ቆመው: ቅዳሴ አስቀድሰው: ቃለ ወንጌሉን ሰምተው: ዕጣን ጧፍ ሰጥተው: ለነዳያን እንደ አቅሞ መጽውተው ጻድቁ የተሰጣቸው ቃል-ኪዳን በእምነት ይቀበላሉ:: በዛሬው ቀን ጥቅምት አምስት ቀን እንድናከብረው መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ያዘዙን በመጋቢት ወር ዐቢይ ጾም ምክንያት ወደዚህ የዞረ ባዓል ነው:: ለበረከት ያህል ግን እንሆ......             ++++ ለበረከት +++++ ይህም ቅዱስ አባት በተወለደበት ቀን ድንቅ የሆነ ሥራን ሠራ:: እንደተወለደ ተነሥቶ ከእናቱ እቅፍ ወርዶ ከጨለማ ወደ ብርሃን ላወጣኽኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን እያለ ለሥላሴ ሰግዷል ምስጋናም አቅርቧልና:: በበረሀም ብዙ ዘመናት ሲኖር:: ነፍሱን ነፍስ ሆይ ዕወቂ በእግዚአብሔር ፊት ራቁትሽን ትቆሚ ዘንድ እንዳለሽ እንግዲህስ ጽኚ በርቺ ታገሺ ይላት ነበር:: ከብዙ ዘመናት በኋላም ለአባታችን ለገብረ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ አለው:: ከእንግዲህ በዓለም ካሉ ሰዎች ከካህናት ከመነኰሳት ወይም ከምእመናን ሕዝባውያን እንዳያውቁህ አደርግሃለሁ:: እንዳንተ ካሉ በቀረ አንተ ራስህ ብትፈቅድ እንጂ መላእክትም ይጎበኙሃል:: የብርሃን ሠረገላም ይሁንል መድረስ ወደምትሻበት ሁሉ ብረር:: እኔንም ማየት በምትፈልግበት ጊዜ አባቴን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሦስትነቴ ታየኛለህ:: ስልሳ አንበሶች ስልሳ ነብሮች በፊት በኋላ አጅበውት ወደ ኢትዮጵያ ምድር ተጓዙ:: የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ገብርኤልም ከአንበሶችና ከነብሮች ጋር በነፋስ ሠረገላ አሳፍሮ ይመራው ነበር:: ወደ ምድረ ከብድም አደረሰው ከዚያም ወደ ልዩ ተራራ ወደ ደብረ ዝቋላ ወሰደው:: አባታችን መላው ኢትዮጵያን ያስማረ ፈጣሪም አብዝቶ ቃል ኪዳን የሰጠው ነው:: ስለ ሕዝቡ ምሕረት ልመና መቶ ዓመት በባሕር ኖረ:: በሽተኞችን እንዲፈውስ ሙታንን እንዲያስነሳ አምላካችን ሥልጣን ሰጥቶታል:: ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ እስከ አሥራ አምስት ትውልድ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጠው:: የጸሎቱ ኃይል ሁላችንን የክርስቲያን ወገኖች ይጠብቀን ለዘለዓለሙ አሜን:: ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የአባታችንም የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ምልጃ ቃል ኪዳንና በረከት አይለየን ለዘላለሙ አሜን:: 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️

Open in Telegram
Views1,160+65%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—

All posts

Connections