ሦስት የአፍሪቃ ሀገራትን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ-ቫልተር ሽታይንማየር ዛሬ ጠዋት የመጨረሻዋ የሚጎበኟት ሀገር የሆነችው ኬንያ ገብተዋል። ናይሮቢ ሲደርሱም የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አቀባበል አድርገዉላቸዋል። ሽታይንማየር ናይሮቢ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትን ይጎበኛሉ፤ ከሁለቱም ሀገራት የንግድ ዘርፍ ቡድኖች እና ልዑካን ጋርም ይገናኛሉ ተብሎ እቅድ ተይዟል። ጀርመን በጎርጎረሳዉያኑ 2025 ከአፍሪቃ ጋር ያደረገችዉ የንግድ ልውውጥ በ 10.5 በመቶ አድጎ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነግሯል። ከአፍሪቃ ጋር ያለውን የንግድ ትስስር ማጠናከር እንደሚገባ ሰሞኑን ያሳሰቡት ሽታይንማየር ከኬንያ በፊት ጋናን እና አይቮሪ ኮስትን ጎብኝተዋል።
Открыть в Telegram
ትኩስ መረጃ
በ ወቅታዊ፡ ተክኖሎጂ ቢዝነስ ሳይንስ ጆፖለትክስ ሰፋ ያለ ዘገባ እናቀርባለን Share to others!
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 21 нояб. 2026 г. | 82 |
| 22 нояб. 2026 г. | 68 |
| 23 нояб. 2026 г. | 85 |
| 24 нояб. 2026 г. | 72 |
| 25 нояб. 2026 г. | 60 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры85Пересылки—Реакции1Комментарии—
- 02Просмотры82Пересылки—Реакции—Комментарии—
- 03Просмотры82Пересылки—Реакции—Комментарии—
- 04Просмотры81Пересылки—Реакции—Комментарии—
Новые посты
በቅርቡ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ከእስር ተለቆ (ፍርዱን ሳይጨርስ ወጥቶ) በአንድ ወር ውስጥ 5 ሴቶችን የገ'ደ'ለው ተጠርጣሪ ! • ግለሰቡ አሁን በእስር ላይ ይገኛል። ከቀናት በፊት በትግራይ ሽሬ እንዳስላሰ ከተማ በስራ ቦታዋ ላይ እያለች የሶስት ልጆች እናትን በአሰቃቂ ሁኔታ የገ'ደ'ለና አ'ስ'ክሬኗ ላይ ጾታዊ ጥ'ቃት የፈጸመ ተስፋይ ዮሐንስ የተባለ ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል። ግለሰቡ እሷን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሴቶችንም መ'ግ'ደሉን ከሞ'ቱ በኋላ ጾታዊ ጥ'ቃት መፈጸሙ ተነግሯል። የሰሜን ምዕራብ ዞን ወንጀል ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ገብረሥላሴ አማረ በዚህ ጉዳይ ላይ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል። ምን አሉ ? ግለሰቡ 54 ዓመቱ እንደሆነና በ2015 ዓ/ም አንዲትን ሴት ቡና በርካሽ ዋጋ እንደሚሸጥላት በማታለል ወስዶ ገ'ድ'ሏት የ22 ዓመት እስራት ተፈርዶበት ነበር። አሁን በቅርቡ ጦርነት ሲቀሰቀስ ከእስር ከወጣ በኋላ አምስት ሴቶችን አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በመ'ግ'ደል መጠርጠሩን ኮማንደሩ ተናግረዋል። እንደ ፖሊስ ገለጻ፣ ግለሰቡ አምስቱንም ሴቶች ከገ'ደ'ለ በኋላ ፆታዊ ጥ'ቃት ፈጽሟል። ከአምስቱ መካከል የአንዲትን ሟች የአምስት ዓመት ልጅንም ማገቱን ፖሊስ አስረድቷል። ተጠርጣሪው 5ቱን ሴቶች የገ'ደላቸው ከጥቅምት 19 እስከ ኅዳር 8/2019 ዓ.ም ባሉት 20 ቀናት ውስጥ መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል። - መጀመሪያ የተ'ገ'ደለችው ዮርዳኖስ ሓጎስ ስትባል ጥቅምት 19 ተገ'ድላለች። - የአንድ ልጅ እናት የሆነችው ሟች የሻለም ዘነበ ጥቅምት 25 ተገ'ድላለች። - ሦስተኛዋ ሟች ገነት ደጀን ጥቅምት 30 ተገ'ድላለች። - አራተኛ ሟች ሚሊዮን ገብረእግዚአብሔር ኅዳር 7 ተገ'ድላለች። - አምስተኛዋ ሟች ወሰንየለሽ መኮንን ኅዳር 8 ተገ'ድላለች። ተጠርጣሪው በሴቶቹ ላይ ግድያውን ለመፈጸም ቢ'ላ'ዋ፣ መ'ጥ'ረቢያ እና ድንጋይ እንደተጠቀመ ኮማንደር ገብረሥላሴ ገልጸዋል። ከገ'ደላቸው በኋላ ጾታዊ ጥ'ቃት እንደፈጸመባቸው ተመላክቷል። ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ወንጀሉን እንደፈጸመ ያመነ ሲሆን፣ ወንጀሉን የፈጸመበትን ምክንያት ሲያስረዳ "በተፈጥሮዬ ችግር ስላለብኝ ነው" የሚል ምላሽ እንደሰጠ ፖሊስ አመልክቷል። ኮማንደር ገብረሥላሴ እንዳብራሩት፣ ግ'ድያ መፈጸሙ ለተጠርጣሪው የኩራት እና የእርካታ ስሜት የሚሰጠው እንደሚመስል በምርመራው ተረድተዋል። በተጠርጣሪው ተገ'ድለዋል ከተባሉት መካከል አንዷ የሆነችው የሻለም ዘነበ የአምስት ዓመት ልጅም የት እንዳለች እስካሁን አልታወቀም። ምርመራው እንደሚያሳየው፤ ተጠርጣሪው ልጅቷን ካገተ በኋላ እናቷን 40 ሺህ ብር እንድትሰጠው በመጠየቅ፣ ልጇን እንደሚመልስላት ነግሯት ነበር። የሻለምም ራቅ ወዳለ ወዳለ ቦታ በመምጣት ልጇን እንደምትረከብ ነግሯት ከደረሰች በኋላ እንደገደላት ፖሊስ ገልጿል። ነገር ግን ልጅቷ ያለችበት ቦታ እስካሁን አልታወቀም፤ ጉዳዩም በምርመራ ላይ ይገኛል። ከሟቾቹ መካከል የሆነችው ገነት በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ነበረች ያለው ፖሊስ፣ እሷን ጨምሮ ሁሉም ሟቾች በሻይ ቡና እና በአልኮል መጠጥ ንግድ ላይ ተሰማርተው ነበር። የምርመራው መነሻ የሆነው በኅዳር 7/2019 ዓ.ም የተገደለችው የሚሊዮን ገብረእግዚአብሔር ግድያ ነው። ከሟቿ ጋር ትሠራ የነበረች ሴት፣ ሚሊየን በጠዋት ስልክ ደውላላት፣ ተስፋይ የሚባል ሰው ቡና በርካሽ ዋጋ እንደሚያቀርብላት ነግሯት ወደ ሥራ ቦታዋ እንድትመጣ እንደጠራት አሳውቃት ነበር። አብራት የምትሠራዋ ወደ ሥራ ቦታው ባቀናችበት ወቅት ግን ሚሊየን ሻይ ቡና የምትሠራበት ቦታ በሩ ተዘግቶ ነበር የጠበቃት። በዚህም ምክንያት ጓደኛዋን ፈልጋ ስላጣቻት ቁልፍ አፈላልጋ በሩን ከፍታ ስትገባ አስክሬኗን እንዳገኘች የፖሊስ ምርመራ አመልክቷል። ፖሊስ ከጓደኛዋ በተገኘው መረጃ መሠረት ምርመራ ሲያካሂድ ተስፋይ የሚባል ግለሰብ ከሟቿ ጋር በስልክ ተደዋውሎ እንደነበር ማወቁን ኮማንደር ገብረሥላሴ ገልጸዋል። ከዚያም የተጠርጣሪውን ማንነት፣ አካላዊ ገጽታ እና ልዩ መለያ በማጣራት ወደ ተጠርጣሪው መድረሳቸውን ተናግረዋል። ግለሰቡ ከዚህ ቀደም በሠራው ወንጀል ከተፈረደበት እስር ማምለጡም ፖሊስ ምርመራውን ተስፋይ ላይ እንዲደረግ አስችሏል ሲሉ ኮማንደሩ ይገልጻሉ። ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላም የወንጀሉን እውነተኛ ሁኔታ ለማረጋገጥ ግድያዎቹ ወደ ተፈጸሙባቸው ቦታዎች እንዲመራቸው እንደጠየቁት፣ እሱም እየመራ አምስት የወንጀል ቦታዎችን እንዳሳየ ኮማንደሩ አስረድተዋል። ከሟቾቹ መካከል የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችው ገነት ደጀን ከተገደለች በኋላ የት እንዳለች ሳይታወቅ እንደቆየች እና ቤተሰቦቿም በዚያን ጊዜ ስለመገደሏ እንዳላወቁ ተገልጿል። ተጠርጣሪው ከከተማ ራቅ ወዳለ ቦታ ወስዶ አስክሬኗ የሚገኝበትን ቦታ የጠቆመ ሲሆን፣ የሟቿ መሆናቸውን የሚያመለክቱ የግል ንብረቶች እና የአካል ቅሪቶች እንዳገኙ ኮማንደሩ ገልጸዋል። የሌሎቹ አስክሬን ቀደም ብሎ የተገኘ ቢሆንም በማን እና በምን ምክንያት እንደተገደሉ ለመመርመር በወቅቱ የነበረው የፀጥታ ሁኔታ እንዳላስቻለ ኮማንደሩ ተናግረዋል። ከሟቾቹ መካከል የሻለም ዘነበ እና ገነት ደጀን ከቤት ውጪ ሲገደሉ ቀሪዎቹ በቤታቸው መገደላቸውን ፖሊስ አመልክቷል። ይሁንና ምርመራው ሙሉ በሙሉ አልተጠናቀቀም። በተለይ የአምስት ዓመቷ ሕፃን ያለችበትን ቦታ ለማወቅ እና ሌሎች ተጨማሪ የወንጀል ጥቆማዎች ካሉ ለማጣራት ምርመራው እየቀጠለ እንደሆነ ኮማንደር ገብረሥላሴ አማረ ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ገገልጸዋል። ምንጭ| BBC News Amharic
Открыть в TelegramПереслано из Hahuprime English
Somalia Airs Footage Accusing the UAE of Flying Thousands of Colombian Fighters Through Bosaso to Sudan Somali state television has aired a documentary alleging that more than 6,000 Colombian fighters, along with weapons shipments, passed through Bosaso airport and port on their way to Sudan's Rapid Support Forces. Somalia's aviation authority says it logged 969 unauthorised UAE-chartered flights in 2024 and 2025. The figures have not been independently verified. The UAE denies arming any side in Sudan and has called Mogadishu's stance "escalatory and hostile". Read more: HahuPrime #Somalia #UAE #SudanWar @hahuprime
Открыть в TelegramПереслано из Hahuprime English
Abiy Offers to Host Sudan Peace Dialogue in Ethiopia as Khartoum Accuses Addis Ababa of Backing the RSF In a statement issued in Arabic on Tuesday, Prime Minister Abiy Ahmed invited Sudan's army, the Rapid Support Forces and civilian groups to an inclusive dialogue hosted by Ethiopia, aimed at ending the war and forming a broadly accepted national unity government. He promised to keep "an equal distance from all parties". Neither the army nor the RSF responded immediately. Khartoum accuses Addis Ababa of backing the RSF and letting drones fly from its territory, which Ethiopia denies. Read more: HahuPrime #Sudan #AbiyAhmed #HornOfAfrica @hahuprime
Открыть в TelegramПереслано из Fund 2 Learn
🇰🇷 KAIST Undergraduate Scholarship 2027 – በደቡብ ኮሪያ ሙሉ የትምህርት ክፍያ እና ወርሃዊ አበል! 12ኛ ክፍልን ጨርሰዋል ወይም በ2027 ይጨርሳሉ? በእስያ ቀዳሚ ከሆኑት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ በሆነው KAIST Bachelor ይማሩ 👇 🎓 የBachelor ቅበላ ለ2027 የበልግ ወቅት (Fall 2027፣ Regular Track)፣ በእንግሊዝኛ 💰 ምን ይሸፍናል? ✅ ለ8 ሴሚስተር ሙሉ የትምህርት ክፍያ ✅ በወር 350,000 የኮሪያ ዎን የኑሮ አበል ✅ የሕክምና መድን (Health Insurance) ⚠️ ከ1ኛ ዓመት በኋላ ከ4.3 ቢያንስ 2.7 GPA መያዝ ያስፈልጋል 👥 ማን ማመልከት ይችላል? 🔹 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እስከ 31 August 2027 የሚያጠናቅቁ 🔹 የኮሪያ ዜግነት የሌላቸው (ወላጆቻቸውም ኮሪያውያን ያልሆኑ) 🔹 ጥሩ እንግሊዝኛ (ለምሳሌ IELTS 6.5 ወይም TOEFL iBT 83 ይመከራል) 📄 ትራንስክሪፕት፣ ፓስፖርት፣ የብሔራዊ ፈተና ወይም SAT ውጤት፣ የእንግሊዝኛ ፈተና እና እስከ 2 Recommendation Letter። የማመልከቻ ክፍያ 80 ዶላር ነው። 📅 የመጨረሻ ቀን፦ ጥር 6 ቀን 2019 ዓ.ም (14 January 2027)፣ ከምሽቱ 6:00 በኮሪያ ሰዓት 💡 ምክር፦ የተለየ የስኮላርሺፕ ማመልከቻ የለም፤ በቅጹ "Statement of Financial Resources" ክፍል "KAIST Scholarship"ን ብቻ ይምረጡ። የብሔራዊ ፈተና ውጤትም ተቀባይነት አለው። 🔗 ኦፊሴላዊ ሊንክ፦ https://admission.kaist.ac.kr/intl-undergraduate/support/scholarships/kaist 📖 ሙሉ መረጃውን በድረ-ገጻችን ያንብቡ፦ https://fund2learn.hahuprime.com/kaist-undergraduate-scholarship-2027/ 🤝 ይህን እድል 12ኛ ክፍል ለሚጨርሱ ጓደኞችዎ ያጋሩ! #Undergraduate #StudyInKorea #Scholarships 📌 ለተጨማሪ እድሎች፦ @fund2learn
Открыть в TelegramПереслано из Hahuprime Amharic
ኢትዮጵያ ለግብፅ፦ «መጀመሪያ የራሳችሁን የውኃ ብክነት አስተካክሉ» የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ ማክሰኞ ኅዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ግብፅ ለውኃ ችግሯ ኢትዮጵያን ከመውቀስ ይልቅ የራሷን የውኃ አጠቃቀም ማዘመን አለባት ብለዋል። ሚኒስትሩ ግብፅ በሞቃታማ አየር ንብረት ውስጥ ባህላዊ የጎርፍ መስኖ መጠቀሟን፣ ከ500 ሺህ ሄክታር በላይ ሩዝና ከ100 ሺህ ሄክታር በላይ ሸንኮራ አገዳ ማልማቷን እንዲሁም የዓባይን ውኃ ወደ ቶሽካና ሲና በረሃዎች መቀየሷን ተችተዋል። ግብፅ አዲስ ከተማ ለመገንባት ማቀዷን በመጥቀስም፣ ካይሮ የዓባይን ውኃ የሚነኩ ፕሮጀክቶችን ከመጀመሯ በፊት የኢትዮጵያን ፈቃድ ማግኘትና «የአንድ ወገን እርምጃዎችን ማቆም» አለባት ብለዋል። አስተያየቱ የመጣው ግብፅ፣ ሱዳንና ኤርትራ ቅዳሜ ኅዳር 12 ቀን በአስዋን ባደረጉት ስብሰባ «የአንድ ወገን የውኃ እርምጃዎችን» እንደማይቀበሉ ካስታወቁ ከሦስት ቀናት በኋላ ነው። ግብፅ እስካሁን ምላሽ አልሰጠችም። ሚኒስትሩ ግን ለውይይት በር አልዘጉም፤ በዓባይ ተፋሰስ የጋራ የውኃ መሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ሐሳብ አቅርበዋል። ሙሉውን ያንብቡ: HahuPrime #ዓባይ #ኢትዮጵያ #ግብፅ @hahuprime_et
Открыть в TelegramПереслано из Hahuprime English
Africa’s First Nvidia ‘AI Factory’ Is Already Full as Cassava Hunts for $1 Billion in More Chips Cassava Technologies’ AI factory in Cape Town, with just over 2,000 Nvidia GPUs, has been running at full capacity since November 1, Africa Data Centres chief Boyd Chislett told Business Day. Bloomberg reports that the Strive Masiyiwa-founded group is seeking up to $1 billion for more chips, though Cassava declined to comment and the talks may not produce a deal. With Africa holding under 1% of global AI data-centre capacity, most of the continent’s AI work still runs overseas. Read more: HahuPrime #ArtificialIntelligence #AfricaTech #Nvidia @hahuprime
Открыть в TelegramПереслано из Hahuprime Amharic
ሀገራት በAI «ገዳይ ሮቦቶች» ላይ ደንብ ለማርቀቅ ተስማሙ፤ አስገዳጅ ስምምነት ግን የለም በጄኔቫ እስከ ሌሊቱ 10 ሰዓት ገደማ በዘለቀ ድርድር፣ የተባበሩት መንግሥታት የጦር መሣሪያ ስምምነት አባል የሆኑ 128 ሀገራት ቅዳሜ ኅዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም. አንድ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል። ሀገራቱ ሰው ሳያዝዛቸው ዒላማ መርጠው የሚያጠቁ ገዳይ ራስ-ገዝ የጦር መሣሪያዎችን የሚመለከት ሰነድ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ለማዘጋጀት ተስማምተዋል። ሆኖም ሰነዱ ሕጋዊ አስገዳጅነት ይኖረው እንደሆነ አልተወሰነም። ወደ 100 የሚጠጉ ሀገራት አስገዳጅ ሕግ ቢፈልጉም አሜሪካ፣ ሩሲያና እስራኤል መቃወማቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። የተመድ የትጥቅ ማስፈታት ኃላፊ ኢዙሚ ናካሚትሱ ሁለት ዓመት «በጣም የተጣበበ ጊዜ» መሆኑን ገልጸው፣ አስገዳጅ ስምምነት የማግኘት ዕድል አሁንም ክፍት ነው ብለዋል። የአፍሪካ ሀገራት አስገዳጅ ስምምነት እንዲኖር ሲገፋፉ ቆይተዋል። ድሮኖች በሱዳን፣ በኢትዮጵያና በሶማሊያ ጦርነቶች ውስጥ ከፍተኛ ሚና በያዙበት በዚህ ወቅት፣ መዘግየቱ ሲቪሎችን ለአደጋ ያጋልጣል ሲሉ ዘማቾች አስጠንቅቀዋል። ኢትዮጵያ የስምምነቱ አባል ባትሆንም በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ተመሳሳይ ውሳኔዎችን ደግፋለች። ሙሉውን ያንብቡ: HahuPrime #AI #ገዳይ_ሮቦቶች #ተመድ @hahuprime_et
Открыть в TelegramПереслано из Fund 2 Learn
🇹🇷 Erasmus+ ልውውጥ በMETU፣ ቱርክ 2027 — ለባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ብቻ! ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአንካራ በሚገኘው Middle East Technical University (METU) የ2027 የፀደይ ሴሚስተር ለመማር ወይም ምርምር ለማድረግ የErasmus+ KA171 ጥሪ ከፍቷል። ይህ እድል አሁን በBDU በመደበኛ መርሐ ግብር ለተመዘገቡ ተማሪዎች ብቻ ነው። 👇 🎓 የፀደይ 2026–2027 ሴሚስተር በMETU — ኮርስ ወይም ምርምር። ዋና ሙሉ ድጋፍ የሚያገኙት 2 ቦታዎች ናቸው፤ ተተኪዎችም ይመደባሉ። 💰 በወር €800 የኑሮ አበል፣ አንድ ጊዜ የጉዞ አበል ከ€211 እስከ €1,735፣ እና በMETU የትምህርት ክፍያ ሙሉ በሙሉ ይቀራል። ⚠️ የተመረቁ ወይም ከሌላ ተቋም የመጡ አይመለከቱም። የመጀመሪያው 70% ክፍያ ከደረሱ ከ2–3 ሳምንት በኋላ ስለሚገባ፣ የመጀመሪያውን ወር የኑሮ ወጪ በራስዎ ገንዘብ ለመሸፈን ይዘጋጁ። የካምፓስ መኖሪያ አይረጋገጥም። 👥 ከሁለተኛ ዓመት በላይ፣ ቢያንስ አንድ ሙሉ ዓመት ያጠናቀቁ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ማስተርስ ወይም ፒኤችዲ ተማሪዎች (የድኅረ ምረቃ በጣም ይበረታታል)። ቢያንስ B1 እንግሊዘኛ (CEFR)፣ የሚያገለግል ፓስፖርት፣ እና በMETU ቢያንስ 30 ECTS። ለምርምር የሚሄዱ ማስተርስ/ፒኤችዲ ተማሪዎች የMETU Supervisor Acceptance Letter እና የBDU የአማካሪ ድጋፍ ደብዳቤ ያስፈልጋቸዋል። 📅 የBDU ውስጣዊ የመጨረሻ ቀን፦ ኅዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም (5 December 2026)፣ ከሰዓት በኋላ 5:00 በኢትዮጵያ ሰዓት 💡 ማመልከቻው በነፃ በኦፊሴላዊ ቅጹ ብቻ ነው። ፋይሎች በPDF፣ የተጠየቁትን ብቻ ይጫኑ። ገንዘብ የሚጠይቅ ኤጀንት አይመኑ። 🔗 የማመልከቻ ቅጽ፦ https://forms.gle/zuWWqLw8hwHkJsDUA 📖 ሙሉ መረጃውን በድረ-ገጻችን ያንብቡ፦ https://fund2learn.hahuprime.com/erasmus-exchange-metu-turkiye-2027-bahir-dar/ 🤝 ይህን እድል ለባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጓደኞችዎ ያጋሩ! #ErasmusPlus #METU #BahirDarUniversity 📌 ለተጨማሪ እድሎች፦ @fund2learn
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
Biiroo Industiriifi Intarpiraayizii Oromiyaa@oromia_eibureauНовости и СМИ1,49 тыс.
Hule Addis Media ( HAM)@hulaadissНовости и СМИ2,08 тыс.
Addis Insight -አዲስ እይታ@addisinsight23Новости и СМИ3,18 тыс.
Russian House in Addis Ababa / Русский дом в Аддис-Абебе@rcscethiopiaНовости и СМИ4,56 тыс.
Warka Times@warkatimesofficialНовости и СМИ4,65 тыс.
LinkUp Premium@linkuppremiumНовости и СМИ7,51 тыс.
Borkena@borkenaНовости и СМИ7,52 тыс.
Odeffannoo adda addaa Afan Oromon@kuusaa_kitaabaaНовости и СМИ9,17 тыс.