Кабинет
Warka Times

Warka Times

Warka Times is a multi-platform bi-lingual global online media service where credibility is a priority. We will keep you both informed and entertained. The infotainment presented on WT comes from wide variety of sources. FB 👉fb.com/warkatimesofficial

Юзернейм
@warkatimesofficial
Категория
Новости и СМИ
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики4 650
Просмотров на пост, 7 дн.509−41,1% к пред. 7 дн.
ERR10,95 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
11 нояб. 2026 г.1 062
12 нояб. 2026 г.1 091
14 нояб. 2026 г.749
15 нояб. 2026 г.984
16 нояб. 2026 г.972
21 нояб. 2026 г.509

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01
    Просмотры1,26 тыс.
    Пересылки—
    Реакции4
    Комментарии—
  2. 02

    ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ ለኢትዮጵያ መንግሥት መልእክት ላኩ። ********* ይድረስ ካገሬ ኢትዮጵያ የፌደራልና ክልሎች ባለስልጣናት! ኢትዮጵያዊው ሊቅ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ የተናገሩትና እንደ ዋዛ ያለፍነው አንድ ጉዳይ አለ፡፡ እናም እንደገና ማሳታወስ ፈለኩ፡፡ “አንድ ጊዜ ደርግ ጽ/ቤት ተጠርቼ ከመንግሥቱ ኃ/ማርያም ጽ/ቤት ገባሁ፡፡ እኔም እንዲህ አልኩት፡-           ‘ሊቀመንበር መንግሥቱ ያንተና የመንግሥታችሁ ሥራና ታሪክ ዛሬ በአዲስ ዘመንና በሠርቶ አደር ጋዜጣ ላይ እንደሚፃፈው ላይሆን ይችላል፡፡ እውነተኛና ሀቀኛ ታሪካችሁና ተግባራችሁ የሚፃፈው በሚመጣው ዘመንና ትውልድ ነው!’  አልኩት” ብለው እንደተናገሩ ያስታውሳሉ፡፡ የፕሮፌሰር ምክረ ሀሳብ በወቅቱ ሰሚ ባያገኝም ኋላ ላይ እውነት ሆኖ ታዝበናል፡፡ በአዲስ ዘመንና በሠርቶ አደር ጋዜጣ፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን መንግሥቱ ኃ/ማርያምን ‹ቆራጡ አብዮታዊ መሪ፤ መንግሥታቸውን ደግሞ ተራማጅ፣ ለጭቁኖች የቆመ፣ ሶሻሊስት› ብለው ቢያንቆለጳጵሱትም ሥርዓቱ ሲወድቅ ኮሎኔል መንግሥቱን ‹ጨካኝ› መንግሥታቸውም ‹ሰው በላ፣ ፀረ ደሞክራሲ› ተባለ፡፡ ኢህአዴግም እንደዚያው ሆነ፡፡ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ጋዜጣ፣ እፎይታ መፅሔት፣ ዋልታና ፋና እንደዘገቡት ሳይሆን ‹ዘረኛና ከፋፋይ› ዘመኑም ‹የ27 ዓመት ጨለማ ዘመን› ተብሎ ተበየነ፡፡ አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ታሪክም አሁን ላይ ፋናና ኢቢሲ  እንደሚዘግቡት ላይሆን ይችላል፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሥርዓቱ አፈቀላጤዎችና ራሳቸውን ‹አክቲቪስት› ብለው የሚጠሩት እንደሚፅፉትና እንደሚያደንቁት ላይሆን ይችላል፡፡ እውነተኛው የመንግሥት ታሪክ የሚፃፈው ለተረኛዉ ሲያስረክብና ኃይልና ስልጣን ከእነርሱ ስትርቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሲሆኑ ዘግይቶ ነው፡፡ ታሪክ የፍትህ ሚዛን ላይ ሲያስቀምጥህ እርቃንህን ነው፡፡ በብዙ አጀብና የፀጥታ መዋቅር የጠበከው ምሥጢር በአደባባይ ይዘከዘካል፡፡ ምሥክር ይሆኑ ዘንድ በየጫካው በግፍ የተገደሉ የሙታን ድምፅ ግዘፍ ነስቶ ይመጣል፤ እስረኞች እስከ ቂማቸው ይፈታሉ፤ የተሰደዱና የተፈናቀሉ እስከቁጣቸው ይመለሳሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ዘመን ከድቶት ብቻውንና እርቃኑን ለሚቆመው መንግሥታዊ ተግባርህ ተፋራጅ ይሆናሉ፡፡ ኘሮፌሰር መስፍን በመፅሐፋቸው እንደገለፁት ‹አድፋጩ የኢትዮጵያ ሕዝብ› ከየጎሬው ወጥቶ ‹ሌባ ሌባ› ይልኻል፤ እንደ እስጢፋኖስ በድንጋይ ሊወግርህ ይከብኻል፡፡ እናም በወጣትነትህና በጎልማሳነትህ ከነሙሉ ኃይልህና ክብርህ ጋር የሠራኸው ግፍ በኋላ ዘመንህ በሌለህ ጉልበት እንደ መርግ ላይህ ላይ ይጫንብሃል፡፡ ዳፋው ካንተ አልፎ ለልጅ ልጆችህና ለቤተሰቦችህም ይተርፋል፡፡ ታሪክ ለፍርድ ሲያቆምህ ማንገራገር፣ ማስተባበል፣ ማስተካከልም እንዳትችል በአበቃ ጊዜህ ላይ ይሆናል፡፡ እናም የሀገሬ ባለስልጣናት ወንድሞቼና እህቶቼ ዛሬ በሚቀርብላችሁ ውዳሴና የተጋነነ ክዋኔ ሪፖርት እንዳትታለሉ፡፡ ይልቁንም ከሚተቿችሁና ከሚነቅፏችሁ ይልቅ አብዝተው ከሚያወድሷችሁና ከሚያሸበሽቡላችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፡፡ ግፍን ፍሩ፤ የሕዝብን ብሶትናምሬት አዳምጡ፤ የሆነ ቦታ በሆነ ተግባር ቢሳካላችሁ እንኳን ትሩፋቱ ለሁሉም ሕዝብ ስለማይደርስ ተስፋ ለጣው ህብረተሰብ ሞራል ተጨነቁ፡፡ አቅመ ቢስ ዜጎችን ከጥቃት ተከላከሉ፡፡ የዜጎችን ሞት እንደተራ ክስተት አትቀበሉ፡፡ ምናልባት በመረጃ ክፍተትና ባቅም ማነስ በዜጎች ላይ ጥቃት ሲደርስ እንደ ሰው ወጥታችሁ ኃዘናችሁን  ግለጡ ቢቻል በአካል ተገኝታችሁ የተጎጂ ቤተሰቦችን አፅናኑ፤ እንደ መንግሥት ቁጭታችሁን  በግልፅ ቋንቋ ግለፁ  እንጅ የቃላት ቁማር አትጫወቱ፡፡ ያከናወናችሁትን ስኬት በልኩ ግልጹ፤ ችግራችሁንም በግልፅ ለህዝብ አስታውቁ፤ ድክመታችሁን አምርራችሁ ፈትሹ፡፡ በህዝብ ላይ ለደረሰ ጥፋት እስከመጨረሻው መርምራችሁ ተጠያቂዎችን ለይታችሁ ለህግ አቅርቡ እንጅ በደፈናው አትፈረጁ ወይም አታድበስብሱ፡፡ በሲቪሊያን ላይ ማንነትን መሠረት አድርጎ በተደጋጋሚ የሚደርስን ጥቃት ማስቆም ካልቻለ ወይም ተጠያቂዎችን ለይቶ ለፍርድ ካለቀረበ የተጠያቂነቱ  ሸክሙ ከመንግሥት ላይ መውደቁ ግድ ነው፡፡ ስለሆነም የህግ ተጠያቂዎችንና ወንጀለኞችን ዛሬ ለይታችሁ ካለቀረባችሁ ነገ የጋራ ወንጀላችሁ ሆኖ መምጣቱን አትዘንጉ፡፡ ይህን ምክረ ሀሳብ የማቀርበው ለሀገሬ ኢትዮጵያ ካለኝ ፍቅር የተነሳ በተሰጣችሁ ዕድል አንዳች የሚጠቅም አስተዋፅኦ አድርጋችሁ እንድታልፉ ካለኝ በጎ ስሜት ነው፡፡ አብዛኞቻችሁ የዕድሜ እኩዮቼና የዘመን ተጋሪዎቼ በመሆናችሁ ቀሪ ዘመናችሁ መልካም እንዲሆን ማንም ከማያመልጠው የታሪክ ፍርድ ትድኑ ዘንድ ከመጨነቅ የተነሳ የታሪክ መስታዎትን እንድታዩ ለማስታወስ ነው፡፡ በተለይም በዚች ታሪካዊ ሀገር አንድ ልምምድ እውን ሆኖ ማየት ስለምፈልግ ነው፡፡ እሱም የመንግሥት ሹመኞች የሥራ ዘመናችው ሲያልቅ፤ መንግሥታቸውም ሲቀየር በሠላምና በአክብሮት በህብረተሰቡ መካከል ሲኖሩ ማየት ነው፡፡ የቀድሞ ባለሥልጣኖች በየዕድርና ሠርግ ቤቱ፣ በየቤተ እምነቱና  በየመናኸሪያው ስናገኛቸው ‘ስለሰጡን አገልግሎት እናመሰግናለን /Thank you for your service’  ሲባሉ ማየት ስለምናፍቅ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ ዓይነ ልቡናችሁን ያብራላችሁ፤ ቀናውን ያሳስባችሁ! ©ዓለማየሁ ዋሴ

    Фото
    Просмотры1,14 тыс.
    Пересылки—
    Реакции16
    Комментарии—
  3. 03
    Просмотры995
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—
  4. 04
    Просмотры985
    Пересылки—
    Реакции1
    Комментарии—

Новые посты

#20487Фото
Просмотры509−44%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#20486Фото
Просмотры972+7%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#20484Фото
Просмотры995+9%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#20481Фото

Переслано из ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

ልክ የዛሬ አንድ ወር ገደማ ይህን መረጃ አጋርቼ ነበር። ታድያ በወቅቱ አንድ የመንግስት ሹም "ፍፁም ውሸት ነው፣ አንድም የካቢኔ አባል በአምባሳደርነት አይሾምም፣ እንደውም ምርመራ እየተደረገ ነው" ብለው በውስጥ መልዕክት ልከው ነበር። ዛሬ ግን ይፋ የተደረገው እውነታውን አረጋግጧል ⤵️ "ጠ/ሚር አብይ አህመድ በሙስና፣ በሌብነት እና የህዝብን ሀብት በመበዝበዝ የተደረሰባቸው የካቢኔ አባላት አሉ ብለዋል... ይሁንና እነዚህኑ ግለሰቦች መልሶ አምባሳደር እና ዲፕሎማት አድርጎ መሾም ምን ማለት ይሆን? አንድ ወይም ሁለት ሳይሆን በርካታ ከስልጣን ተነሺዎች በዲፕሎማትነት ወደ ውጪ እንደሚላኩ መረጃዎች ደርሰውኛል፣ አንደኛውማ 'ቻይና ልመደብ ስለሆነ እዛው እንቀጥለዋለን' በማለት ለሀገር ውስጥ እና ለቻይና ባለሀብቶች መናገር ጀምረዋል። ሌባ ቢሆኑም ዲፕሎማት ተደርገው ቢላኩ ብዙም ብር ስለሌለው አይሰርቁም በሚል ስሌት ይሆን? ሌባ ለአመሉ እንዲሉ መስረቅ የለመደ የኤምባሲዎችን ጣርያ ነቅሎ ሊሸጥ ይችላል። ከሁሉም በላይ ግን ዲፕሎማትነትን እና ዲፕሎማሲያችንን የሰረቀ የሚላክበት፣ የሚቀጣበት ተደርጎ የሚወሰድበት አግባብ ልክ አይደለም፣ ሀገራቸውን በቅንነት ለሚያገለግሉ ዲፕሎማቶችም fair አይደለም። የሰረቀን ክስ መስርቶ መፋረድ እንጂ በየኤምባሲው ማጨቅ መፍትሄ አይሆንም።" @EliasMeseret

Открыть в Telegram
Просмотры741−18%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#20477Фото

Переслано из TIKVAH-ETHIOPIA

​የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር ልጅ በታጣቂዎች ተገደለ። ​የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ዋና አስፈጻሚ ብርጋዴር ጀነራል ገብረእግዚአብሔር በየነ (ወዲ አንጥሩ) ልጅ የሆነው ወጣት መዋእል ገብረእግዚአብሔር መንገድ ላይ በታጣቂዎች መገደሉን የቅርብ ምንጮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል። ​ምንጮቹ እንደገለጹት፤ ወጣቱ ትናንትና አመሻሽ ከመቐለ በ15 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው ደጉዓ ተምቤን ወረዳ ታጣቂዎች በከፈቱበት ጥቃት ሕይወቱ አልፏል። በ1995 ዓ/ም የተወለደው የ24 ዓመቱ ወጧት መዋእል ገብረእግዚአብሔር የቀብር ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 5 በመቐለ ከተማ ይፈጸማል ተብሏል። ሟቹ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 2017 ዓ.ም የቲዲኤፍ አባል የነበረ ሲሆን ጥር 2017 ዓ.ም የኮር እና ከኮር በላይ አመራሮች በእነ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ሲመራ ለነበረው ህወሓት እውቅና እንደሚሰጡ የወሰኑትን ውሳኔ ተከትሎ ወደ ትግራይ የሰላም ኃይል መቀላቀሉ የትግል ጓዶቹ ያጋሩት መረጃ አመልክቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры748−18%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#20472Фото
Просмотры757−17%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#20471Видео
Просмотры1 260+39%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#20469Фото

ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ ለኢትዮጵያ መንግሥት መልእክት ላኩ። ********* ይድረስ ካገሬ ኢትዮጵያ የፌደራልና ክልሎች ባለስልጣናት! ኢትዮጵያዊው ሊቅ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ የተናገሩትና እንደ ዋዛ ያለፍነው አንድ ጉዳይ አለ፡፡ እናም እንደገና ማሳታወስ ፈለኩ፡፡ “አንድ ጊዜ ደርግ ጽ/ቤት ተጠርቼ ከመንግሥቱ ኃ/ማርያም ጽ/ቤት ገባሁ፡፡ እኔም እንዲህ አልኩት፡-           ‘ሊቀመንበር መንግሥቱ ያንተና የመንግሥታችሁ ሥራና ታሪክ ዛሬ በአዲስ ዘመንና በሠርቶ አደር ጋዜጣ ላይ እንደሚፃፈው ላይሆን ይችላል፡፡ እውነተኛና ሀቀኛ ታሪካችሁና ተግባራችሁ የሚፃፈው በሚመጣው ዘመንና ትውልድ ነው!’  አልኩት” ብለው እንደተናገሩ ያስታውሳሉ፡፡ የፕሮፌሰር ምክረ ሀሳብ በወቅቱ ሰሚ ባያገኝም ኋላ ላይ እውነት ሆኖ ታዝበናል፡፡ በአዲስ ዘመንና በሠርቶ አደር ጋዜጣ፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን መንግሥቱ ኃ/ማርያምን ‹ቆራጡ አብዮታዊ መሪ፤ መንግሥታቸውን ደግሞ ተራማጅ፣ ለጭቁኖች የቆመ፣ ሶሻሊስት› ብለው ቢያንቆለጳጵሱትም ሥርዓቱ ሲወድቅ ኮሎኔል መንግሥቱን ‹ጨካኝ› መንግሥታቸውም ‹ሰው በላ፣ ፀረ ደሞክራሲ› ተባለ፡፡ ኢህአዴግም እንደዚያው ሆነ፡፡ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ጋዜጣ፣ እፎይታ መፅሔት፣ ዋልታና ፋና እንደዘገቡት ሳይሆን ‹ዘረኛና ከፋፋይ› ዘመኑም ‹የ27 ዓመት ጨለማ ዘመን› ተብሎ ተበየነ፡፡ አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ታሪክም አሁን ላይ ፋናና ኢቢሲ  እንደሚዘግቡት ላይሆን ይችላል፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሥርዓቱ አፈቀላጤዎችና ራሳቸውን ‹አክቲቪስት› ብለው የሚጠሩት እንደሚፅፉትና እንደሚያደንቁት ላይሆን ይችላል፡፡ እውነተኛው የመንግሥት ታሪክ የሚፃፈው ለተረኛዉ ሲያስረክብና ኃይልና ስልጣን ከእነርሱ ስትርቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሲሆኑ ዘግይቶ ነው፡፡ ታሪክ የፍትህ ሚዛን ላይ ሲያስቀምጥህ እርቃንህን ነው፡፡ በብዙ አጀብና የፀጥታ መዋቅር የጠበከው ምሥጢር በአደባባይ ይዘከዘካል፡፡ ምሥክር ይሆኑ ዘንድ በየጫካው በግፍ የተገደሉ የሙታን ድምፅ ግዘፍ ነስቶ ይመጣል፤ እስረኞች እስከ ቂማቸው ይፈታሉ፤ የተሰደዱና የተፈናቀሉ እስከቁጣቸው ይመለሳሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ዘመን ከድቶት ብቻውንና እርቃኑን ለሚቆመው መንግሥታዊ ተግባርህ ተፋራጅ ይሆናሉ፡፡ ኘሮፌሰር መስፍን በመፅሐፋቸው እንደገለፁት ‹አድፋጩ የኢትዮጵያ ሕዝብ› ከየጎሬው ወጥቶ ‹ሌባ ሌባ› ይልኻል፤ እንደ እስጢፋኖስ በድንጋይ ሊወግርህ ይከብኻል፡፡ እናም በወጣትነትህና በጎልማሳነትህ ከነሙሉ ኃይልህና ክብርህ ጋር የሠራኸው ግፍ በኋላ ዘመንህ በሌለህ ጉልበት እንደ መርግ ላይህ ላይ ይጫንብሃል፡፡ ዳፋው ካንተ አልፎ ለልጅ ልጆችህና ለቤተሰቦችህም ይተርፋል፡፡ ታሪክ ለፍርድ ሲያቆምህ ማንገራገር፣ ማስተባበል፣ ማስተካከልም እንዳትችል በአበቃ ጊዜህ ላይ ይሆናል፡፡ እናም የሀገሬ ባለስልጣናት ወንድሞቼና እህቶቼ ዛሬ በሚቀርብላችሁ ውዳሴና የተጋነነ ክዋኔ ሪፖርት እንዳትታለሉ፡፡ ይልቁንም ከሚተቿችሁና ከሚነቅፏችሁ ይልቅ አብዝተው ከሚያወድሷችሁና ከሚያሸበሽቡላችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፡፡ ግፍን ፍሩ፤ የሕዝብን ብሶትናምሬት አዳምጡ፤ የሆነ ቦታ በሆነ ተግባር ቢሳካላችሁ እንኳን ትሩፋቱ ለሁሉም ሕዝብ ስለማይደርስ ተስፋ ለጣው ህብረተሰብ ሞራል ተጨነቁ፡፡ አቅመ ቢስ ዜጎችን ከጥቃት ተከላከሉ፡፡ የዜጎችን ሞት እንደተራ ክስተት አትቀበሉ፡፡ ምናልባት በመረጃ ክፍተትና ባቅም ማነስ በዜጎች ላይ ጥቃት ሲደርስ እንደ ሰው ወጥታችሁ ኃዘናችሁን  ግለጡ ቢቻል በአካል ተገኝታችሁ የተጎጂ ቤተሰቦችን አፅናኑ፤ እንደ መንግሥት ቁጭታችሁን  በግልፅ ቋንቋ ግለፁ  እንጅ የቃላት ቁማር አትጫወቱ፡፡ ያከናወናችሁትን ስኬት በልኩ ግልጹ፤ ችግራችሁንም በግልፅ ለህዝብ አስታውቁ፤ ድክመታችሁን አምርራችሁ ፈትሹ፡፡ በህዝብ ላይ ለደረሰ ጥፋት እስከመጨረሻው መርምራችሁ ተጠያቂዎችን ለይታችሁ ለህግ አቅርቡ እንጅ በደፈናው አትፈረጁ ወይም አታድበስብሱ፡፡ በሲቪሊያን ላይ ማንነትን መሠረት አድርጎ በተደጋጋሚ የሚደርስን ጥቃት ማስቆም ካልቻለ ወይም ተጠያቂዎችን ለይቶ ለፍርድ ካለቀረበ የተጠያቂነቱ  ሸክሙ ከመንግሥት ላይ መውደቁ ግድ ነው፡፡ ስለሆነም የህግ ተጠያቂዎችንና ወንጀለኞችን ዛሬ ለይታችሁ ካለቀረባችሁ ነገ የጋራ ወንጀላችሁ ሆኖ መምጣቱን አትዘንጉ፡፡ ይህን ምክረ ሀሳብ የማቀርበው ለሀገሬ ኢትዮጵያ ካለኝ ፍቅር የተነሳ በተሰጣችሁ ዕድል አንዳች የሚጠቅም አስተዋፅኦ አድርጋችሁ እንድታልፉ ካለኝ በጎ ስሜት ነው፡፡ አብዛኞቻችሁ የዕድሜ እኩዮቼና የዘመን ተጋሪዎቼ በመሆናችሁ ቀሪ ዘመናችሁ መልካም እንዲሆን ማንም ከማያመልጠው የታሪክ ፍርድ ትድኑ ዘንድ ከመጨነቅ የተነሳ የታሪክ መስታዎትን እንድታዩ ለማስታወስ ነው፡፡ በተለይም በዚች ታሪካዊ ሀገር አንድ ልምምድ እውን ሆኖ ማየት ስለምፈልግ ነው፡፡ እሱም የመንግሥት ሹመኞች የሥራ ዘመናችው ሲያልቅ፤ መንግሥታቸውም ሲቀየር በሠላምና በአክብሮት በህብረተሰቡ መካከል ሲኖሩ ማየት ነው፡፡ የቀድሞ ባለሥልጣኖች በየዕድርና ሠርግ ቤቱ፣ በየቤተ እምነቱና  በየመናኸሪያው ስናገኛቸው ‘ስለሰጡን አገልግሎት እናመሰግናለን /Thank you for your service’  ሲባሉ ማየት ስለምናፍቅ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ ዓይነ ልቡናችሁን ያብራላችሁ፤ ቀናውን ያሳስባችሁ! ©ዓለማየሁ ዋሴ

Открыть в Telegram
Просмотры1 140+25%к среднему
Пересылки—
Реакции16
Комментарии—

Все посты

Связи