
Addis Insight -አዲስ እይታ
እርሶ ቻናላችንን Subscribe ሲያደርጉ ወቅታዊና ሁሉን አቀፍ መረጃዎችን ያገኛሉ። Link👇 https://t.me/AddisInsight23
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 20 нояб. 2026 г. | 527 |
| 21 нояб. 2026 г. | 441 |
| 22 нояб. 2026 г. | 352 |
| 23 нояб. 2026 г. | 341 |
| 24 нояб. 2026 г. | 293 |
| 25 нояб. 2026 г. | 234 |
| 26 нояб. 2026 г. | 76 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры527Пересылки—Реакции—Комментарии—
- 02Просмотры473Пересылки—Реакции—Комментарии—
- 03Просмотры448Пересылки—Реакции—Комментарии—
- 04Просмотры442Пересылки—Реакции—Комментарии—
Новые посты
Динамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 21 |
| 3 ч | 97 |
- Через 1 час21
- Всего сейчас97
Динамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 23 ч | 257 |
| 26 ч | 277 |
- Через 24 часа257
- Всего сейчас277
📰 የአንድ ብር ሳንቲምና የ5 እና 10 ብር ኖቶች በገበያ ውስጥ እየጠፉ ነው፤ ኢኮኖሚው ላይ ጫና እየፈጠረ ነው ተባለ በኢትዮጵያ የአንድ ብር ሳንቲም እንዲሁም የ5 እና የ10 ብር ኖቶች በዕለት ተዕለት ግብይት ውስጥ እየቀነሱ መምጣታቸውንና የመግዛት አቅማቸውም እየተዳከመ መሆኑን የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ለአራዳ ኤፍ ኤም ገልጸዋል። ይህም በኢኮኖሚው ላይ ጫና እየፈጠረ ነው ተብሏል። እነዚህ ገንዘቦች በችርቻሮ ንግድ፣ በሕዝብ መጓጓዣና በገበያ ግብይት ውስጥ ጉልህ ሚና አላቸው። መመናመናቸው ትክክለኛውን ዋጋ ለመክፈልና የዕለት ተዕለት ግብይትን ለማከናወን ችግር እየፈጠረ መሆኑ ተመልክቷል። ችግሩ ሸማቾችንም ነጋዴዎችንም እየተፈታተነ ይገኛል። ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርኸ ተስፋ እንዳሉት የሳንቲሞቹ አቅም መዳከም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች በይበልጥ ይጎዳል። ወደ ዲጂታል ክፍያ እየተደረገ ያለው ሽግግርም ለችግሩ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ተናግረዋል። *አዲስ ኢንሳይት ዓለምን በአዲስ እይታ
Открыть в Telegramበሰቆጣ ከተማ የተጣለው ቅጣት‼️ አማራ ክልል ዋግኸምራ ሰቆጣ ከተማ አላስፈላጊ ወጪዎችንና ጎጂ ልማዶችን ለመቀነስ አዳዲስ ክልከላዎችና ለማስቆም የተወሰኑ ውሳኔዎች። 1. ከጋብቻ (ሰርግ) ጋር የተያያዙ ውሳኔዎች በእጮኝነት ጊዜ ልብስ ለማልበስ ከ5 ሰዎች በላይ ይዞ መሄድ በሴቷም በወንዱም ወገን እያንዳንዳቸው 50,000 ብር፤ የባረከ ቄስ 10,000 ብር ቅጣት። በሰርግ ዋዜማ ለጥሎሽ/ልብስ ከ5 ሰዎች በላይ ይዞ መሄድ በሴቷም በወንዱም ወገን እያንዳንዳቸው 50,000 ብር፤ የባረከ ቄስ 10,000 ብር ቅጣት። ከሰርግ በኋላ ለትውውቅ/ምላሽ (ቅልቅል) ከሰርግ ያልተናነሰ ድግስ መደገስ በሴቷም በወንዱም ወገን እያንዳንዳቸው 50,000 ብር፤ የባረከ ቄስ 10,000 ብር ቅጣት። በሰርግ ጊዜ ከ25 ሰው በላይ መዝመት ወይም ለተለያዩ ፕሮግራሞች ዩኒፎርም (ተመሳሳይ ልብስ) መልበስ ዋናው ባለጉዳይ 30,000 ብር፤ ለብሰው የሚገኙ አካላት እያንዳንዳቸው 10,000 ብር ቅጣት። ለሰርግ በኪራይ ወይም በግዥ የሚዘጋጅ ስቴጅ (መድረክ) እና ከልክ ያለፈ ዲኮሬሽን መጠቀም 20,000 ብር ቅጣት የማይገኝ ሀብት/ማጫ በሐሰት መናገር ማጫ በተጨባጭ ታይቶ መባል አለበት (በዳስ አባቶች ይረጋገጣል)። 2. ከልዩ ልዩ ድግሶችና በዓላት ጋር የተያያዙ በሠርግ እና በክርስትና ዕለት ቡፌ እና ኬክ ማዘጋጀት 50,000 ብር ቅጣት የተማሪዎች ከKG ጀምሮ እስከ ዩኒቨርስቲ ድረስ የምረቃ ድግስ ማዘጋጀት 30,000 ብር ቅጣት። የቤቢ ሻወር (Baby Shower) እና የጋብቻ ዓመታዊ በዓል (Anniversary) ማክበር 10,000 ብር ቅጣት የጽዋ ማህበራት ዩኒፎርም መልበስ እና ታይታ ያለበት ድግስ ማዘጋጀት እያንዳንዱ አባል 10,000 ብር ቅጣት። በማንኛውም ፕሮግራም (ክርስትና፣ ልደት፣ ምንኩስና፣ ቤት ሲሰራ ወዘተ) አረቄ ይዞ መሄድ ፈጽሞ የተከለከለ ነው፤ ተቀብሎ ያስተናገደ ባለቤት 20,000 ብር ይቀጣል። 3. ከሀዘንና ከፍትሃት ጋር የተያያዙ በፍትሃት ጊዜ ከፍተኛ ድግስ መደገስ፣ በ40 ቀን መቃብር ላይ ሻማ ማብራትና ዳቦ መቁረስ 20,000 ብር ቅጣት በሃዘን ጊዜ ውሃ ይዞ መሄድ የተከለከለ ነው (በምትኩ ገንዘብ፣ ስኳር እና ቆሎ ጋብቻ እንዲወስዱ ተገልጧል። ይሄ ውሳኔ የመንግስት ውሳኔ ሳይሆን ማህበረሰቡ ከሁሉም ሀይማኖት አባቶች እና ከአገር ሽማግሌዎች ጋር በመምከር መጤ ባህሎችን መከላከል እና የማህበረሰቡን አላስፈላጊ ወጭዎች ለመከላከል የተወሰነ የስምምነት ውሳኔ መሆኑን ምንጮቻችን ገልፅዋል ። በተለይ አሁን ላይ ሽምግልና፣ ቅልቅልና መልስ ከሰርግ ያልተናነሰ ወጭ እያስወጡ ማህበሰቡን እያማረሩ ያሉ ጎጂ ባህሎች ናቸው። ከመጤ ባህል ራሳችንን ለመከላከል የተደረገ በጎ አላማ ያለው የማህበረሰብ ውሳኔ መሆኑን ምንጮች ገልፅዋል ። በሰቆጣ ከተማ የተጣለው ከ10,000 እስከ 50,000 ብር ቅጣት ሚዛናዊ ነው ብለው ያስባሉ?
Открыть в Telegramበዘረመል የተሻሻለ የአሳማ ኩላሊት የተተከለለት ሰው ለ271 ቀናት ያለ ዳያሊሲስ ቆየ፤ በኋላም የሰው ኩላሊት ተተከለለት! የሕክምናው ዓለም የሚያወራለት ታሪክ፡- የእንስሳት ኩላሊት የሰው ኩላሊት እስኪገኝ ድረስ ታካሚዎችን ለጊዜው እንዴት ሊታደግ እንደሚችል አሳይቷል። በማሳቹሴትስ ጠቅላላ ሆስፒታል በዘረመል የተሻሻለ የአሳማ ኩላሊት የተተከለለት ቲም አንድሪውስ (Tim Andrews)፣ ለ271 ቀናት ያህል ዳያሊሲስ ሳያስፈልገው ዕለታዊ ሕይወቱን መምራት ችሎ ነበር። ይህ ሂደት የአሳማ ኩላሊት ቋሚ መፍትሔ ባይሆን እንኳ፣ የሰው ኩላሊት ንቅለ ተከላ እስኪደረግ ድረስ በጠበቃ ዝርዝር ውስጥ ያሉ ታካሚዎችን ለጊዜው እንደ ድልድይ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል ተስፋ ሰጥቷል። ቲም በመጨረሻ የተለገሰ የሰው ኩላሊት ማግኘት ችሏል። የአሳማው ኩላሊት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት መሥራት ቢያቆምም፣ የቲም አንድሪውስ ተሞክሮ ሳይንስ ምን ያህል እንደተራመደ እና በዚህ ሙከራ ዙሪያ አሁንም መፍታት ያለባቸው ፈተናዎች እንዳሉ በግልጽ ያሳያል ነው የተባለው።
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
Russian House in Addis Ababa / Русский дом в Аддис-Абебе@rcscethiopiaНовости и СМИ4,56 тыс.
Warka Times@warkatimesofficialНовости и СМИ4,65 тыс.
Hule Addis Media ( HAM)@hulaadissНовости и СМИ2,08 тыс.
Biiroo Industiriifi Intarpiraayizii Oromiyaa@oromia_eibureauНовости и СМИ1,49 тыс.
LinkUp Premium@linkuppremiumНовости и СМИ7,51 тыс.
Borkena@borkenaНовости и СМИ7,52 тыс.
ትኩስ መረጃ@tikuswereНовости и СМИ1,19 тыс.
Odeffannoo adda addaa Afan Oromon@kuusaa_kitaabaaНовости и СМИ9,17 тыс.