Account
Addis Insight -አዲስ እይታ

Addis Insight -አዲስ እይታ

እርሶ ቻናላችንን Subscribe ሲያደርጉ ወቅታዊና ሁሉን አቀፍ መረጃዎችን ያገኛሉ። Link👇 https://t.me/AddisInsight23

Username
@addisinsight23
Category
News and media
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers3,180
Avg views per post, 7d316last 7 days
ERR9.94%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 20, 2026527
Nov 21, 2026441
Nov 22, 2026352
Nov 23, 2026341
Nov 24, 2026293
Nov 25, 2026231
Nov 26, 202621

Most viewed this month

  1. 01
    Views527
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—
  2. 02
    Views473
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—
  3. 03
    Views448
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—
  4. 04
    Views442
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—

Latest posts

#14906Photo
Views282−11%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#14905Text

በሰቆጣ ከተማ የተጣለው ቅጣት‼️ አማራ ክልል ዋግኸምራ ሰቆጣ ከተማ አላስፈላጊ ወጪዎችንና ጎጂ ልማዶችን ለመቀነስ አዳዲስ ክልከላዎችና ለማስቆም የተወሰኑ ውሳኔዎች። ​1. ከጋብቻ (ሰርግ) ጋር የተያያዙ ውሳኔዎች ​በእጮኝነት ጊዜ ልብስ ለማልበስ ከ5 ሰዎች በላይ ይዞ መሄድ በሴቷም በወንዱም ወገን እያንዳንዳቸው 50,000 ብር፤ የባረከ ቄስ 10,000 ብር ቅጣት። ​በሰርግ ዋዜማ ለጥሎሽ/ልብስ ከ5 ሰዎች በላይ ይዞ መሄድ በሴቷም በወንዱም ወገን እያንዳንዳቸው 50,000 ብር፤ የባረከ ቄስ 10,000 ብር ቅጣት። ​ከሰርግ በኋላ ለትውውቅ/ምላሽ (ቅልቅል) ከሰርግ ያልተናነሰ ድግስ መደገስ በሴቷም በወንዱም ወገን እያንዳንዳቸው 50,000 ብር፤ የባረከ ቄስ 10,000 ብር ቅጣት። ​በሰርግ ጊዜ ከ25 ሰው በላይ መዝመት ወይም ለተለያዩ ፕሮግራሞች ዩኒፎርም (ተመሳሳይ ልብስ) መልበስ ዋናው ባለጉዳይ 30,000 ብር፤ ለብሰው የሚገኙ አካላት እያንዳንዳቸው 10,000 ብር ቅጣት። ​ለሰርግ በኪራይ ወይም በግዥ የሚዘጋጅ ስቴጅ (መድረክ) እና ከልክ ያለፈ ዲኮሬሽን መጠቀም 20,000 ብር ቅጣት የማይገኝ ሀብት/ማጫ በሐሰት መናገር ማጫ በተጨባጭ ታይቶ መባል አለበት (በዳስ አባቶች ይረጋገጣል)። ​2. ከልዩ ልዩ ድግሶችና በዓላት ጋር የተያያዙ ​በሠርግ እና በክርስትና ዕለት ቡፌ እና ኬክ ማዘጋጀት 50,000 ብር ቅጣት ​የተማሪዎች ከKG ጀምሮ እስከ ዩኒቨርስቲ ድረስ የምረቃ ድግስ ማዘጋጀት 30,000 ብር ቅጣት። ​የቤቢ ሻወር (Baby Shower) እና የጋብቻ ዓመታዊ በዓል (Anniversary) ማክበር 10,000 ብር ቅጣት የጽዋ ማህበራት ዩኒፎርም መልበስ እና ታይታ ያለበት ድግስ ማዘጋጀት እያንዳንዱ አባል 10,000 ብር ቅጣት። ​በማንኛውም ፕሮግራም (ክርስትና፣ ልደት፣ ምንኩስና፣ ቤት ሲሰራ ወዘተ) አረቄ ይዞ መሄድ  ፈጽሞ የተከለከለ ነው፤ ተቀብሎ ያስተናገደ ባለቤት 20,000 ብር ይቀጣል። ​3. ከሀዘንና ከፍትሃት ጋር የተያያዙ ​በፍትሃት ጊዜ ከፍተኛ ድግስ መደገስ፣ በ40 ቀን መቃብር ላይ ሻማ ማብራትና ዳቦ መቁረስ 20,000 ብር ቅጣት በሃዘን ጊዜ ውሃ ይዞ መሄድ የተከለከለ ነው (በምትኩ ገንዘብ፣ ስኳር እና ቆሎ ጋብቻ እንዲወስዱ ተገልጧል። ይሄ ውሳኔ የመንግስት ውሳኔ ሳይሆን ማህበረሰቡ ከሁሉም ሀይማኖት አባቶች እና ከአገር ሽማግሌዎች ጋር በመምከር መጤ ባህሎችን መከላከል እና የማህበረሰቡን አላስፈላጊ ወጭዎች ለመከላከል የተወሰነ የስምምነት ውሳኔ መሆኑን ምንጮቻችን ገልፅዋል ። በተለይ አሁን ላይ ሽምግልና፣ ቅልቅልና መልስ ከሰርግ ያልተናነሰ ወጭ እያስወጡ ማህበሰቡን እያማረሩ ያሉ ጎጂ ባህሎች ናቸው። ከመጤ ባህል ራሳችንን ለመከላከል የተደረገ በጎ አላማ ያለው የማህበረሰብ ውሳኔ መሆኑን ምንጮች ገልፅዋል ። በሰቆጣ ከተማ የተጣለው ከ10,000 እስከ 50,000 ብር ቅጣት ሚዛናዊ ነው ብለው ያስባሉ?

Open in Telegram
Views283−10%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#14902Photo

በዘረመል የተሻሻለ የአሳማ ኩላሊት የተተከለለት ሰው ለ271 ቀናት ያለ ዳያሊሲስ ቆየ፤ በኋላም የሰው ኩላሊት ተተከለለት!   የሕክምናው ዓለም የሚያወራለት ታሪክ፡- የእንስሳት ኩላሊት የሰው ኩላሊት እስኪገኝ ድረስ ታካሚዎችን ለጊዜው እንዴት ሊታደግ እንደሚችል አሳይቷል።   በማሳቹሴትስ ጠቅላላ ሆስፒታል በዘረመል የተሻሻለ የአሳማ ኩላሊት የተተከለለት ቲም አንድሪውስ (Tim Andrews)፣ ለ271 ቀናት ያህል ዳያሊሲስ ሳያስፈልገው ዕለታዊ ሕይወቱን መምራት ችሎ ነበር።   ይህ ሂደት የአሳማ ኩላሊት ቋሚ መፍትሔ ባይሆን እንኳ፣ የሰው ኩላሊት ንቅለ ተከላ እስኪደረግ ድረስ በጠበቃ ዝርዝር ውስጥ ያሉ ታካሚዎችን ለጊዜው እንደ ድልድይ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል ተስፋ ሰጥቷል። ቲም በመጨረሻ የተለገሰ የሰው ኩላሊት ማግኘት ችሏል።   የአሳማው ኩላሊት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት መሥራት ቢያቆምም፣ የቲም አንድሪውስ ተሞክሮ ሳይንስ ምን ያህል እንደተራመደ እና በዚህ ሙከራ ዙሪያ አሁንም መፍታት ያለባቸው ፈተናዎች እንዳሉ በግልጽ ያሳያል ነው የተባለው።  

Open in Telegram
Views302−4%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—

All posts

Connections