Кабинет

Посты канала ትኩስ መረጃ

сначала новые

#12762Фото
Просмотры64−8%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12761Текст

በቅርቡ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ከእስር ተለቆ (ፍርዱን ሳይጨርስ ወጥቶ) በአንድ ወር ውስጥ 5 ሴቶችን የገ'ደ'ለው ተጠርጣሪ ! • ግለሰቡ አሁን በእስር ላይ ይገኛል። ከቀናት በፊት በትግራይ ሽሬ እንዳስላሰ ከተማ በስራ ቦታዋ ላይ እያለች የሶስት ልጆች እናትን በአሰቃቂ ሁኔታ የገ'ደ'ለና አ'ስ'ክሬኗ ላይ ጾታዊ ጥ'ቃት የፈጸመ ተስፋይ ዮሐንስ የተባለ ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል። ግለሰቡ እሷን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሴቶችንም መ'ግ'ደሉን ከሞ'ቱ በኋላ ጾታዊ ጥ'ቃት መፈጸሙ ተነግሯል። የሰሜን ምዕራብ ዞን ወንጀል ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ገብረሥላሴ አማረ በዚህ ጉዳይ ላይ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል። ምን አሉ ? ግለሰቡ 54 ዓመቱ እንደሆነና በ2015 ዓ/ም አንዲትን ሴት ቡና በርካሽ ዋጋ እንደሚሸጥላት በማታለል ወስዶ ገ'ድ'ሏት የ22 ዓመት እስራት ተፈርዶበት ነበር። አሁን በቅርቡ ጦርነት ሲቀሰቀስ ከእስር ከወጣ በኋላ አምስት ሴቶችን አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በመ'ግ'ደል መጠርጠሩን ኮማንደሩ ተናግረዋል። እንደ ፖሊስ ገለጻ፣ ግለሰቡ አምስቱንም ሴቶች ከገ'ደ'ለ በኋላ ፆታዊ ጥ'ቃት ፈጽሟል። ከአምስቱ መካከል የአንዲትን ሟች የአምስት ዓመት ልጅንም ማገቱን ፖሊስ አስረድቷል። ተጠርጣሪው 5ቱን ሴቶች የገ'ደላቸው ከጥቅምት 19 እስከ ኅዳር 8/2019 ዓ.ም ባሉት 20 ቀናት ውስጥ መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል። - መጀመሪያ የተ'ገ'ደለችው ዮርዳኖስ ሓጎስ ስትባል ጥቅምት 19 ተገ'ድላለች። - የአንድ ልጅ እናት የሆነችው ሟች የሻለም ዘነበ ጥቅምት 25 ተገ'ድላለች። - ሦስተኛዋ ሟች ገነት ደጀን ጥቅምት 30 ተገ'ድላለች። - አራተኛ ሟች ሚሊዮን ገብረእግዚአብሔር ኅዳር 7 ተገ'ድላለች። - አምስተኛዋ ሟች ወሰንየለሽ መኮንን ኅዳር 8 ተገ'ድላለች። ተጠርጣሪው በሴቶቹ ላይ ግድያውን ለመፈጸም ቢ'ላ'ዋ፣ መ'ጥ'ረቢያ እና ድንጋይ እንደተጠቀመ ኮማንደር ገብረሥላሴ ገልጸዋል። ከገ'ደላቸው በኋላ ጾታዊ ጥ'ቃት እንደፈጸመባቸው ተመላክቷል። ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ወንጀሉን እንደፈጸመ ያመነ ሲሆን፣ ወንጀሉን የፈጸመበትን ምክንያት ሲያስረዳ "በተፈጥሮዬ ችግር ስላለብኝ ነው" የሚል ምላሽ እንደሰጠ ፖሊስ አመልክቷል። ኮማንደር ገብረሥላሴ እንዳብራሩት፣ ግ'ድያ መፈጸሙ ለተጠርጣሪው የኩራት እና የእርካታ ስሜት የሚሰጠው እንደሚመስል በምርመራው ተረድተዋል። በተጠርጣሪው ተገ'ድለዋል ከተባሉት መካከል አንዷ የሆነችው የሻለም ዘነበ የአምስት ዓመት ልጅም የት እንዳለች እስካሁን አልታወቀም። ምርመራው እንደሚያሳየው፤ ተጠርጣሪው ልጅቷን ካገተ በኋላ እናቷን 40 ሺህ ብር እንድትሰጠው በመጠየቅ፣ ልጇን እንደሚመልስላት ነግሯት ነበር። የሻለምም ራቅ ወዳለ ወዳለ ቦታ በመምጣት ልጇን እንደምትረከብ ነግሯት ከደረሰች በኋላ እንደገደላት ፖሊስ ገልጿል። ነገር ግን ልጅቷ ያለችበት ቦታ እስካሁን አልታወቀም፤ ጉዳዩም በምርመራ ላይ ይገኛል። ከሟቾቹ መካከል የሆነችው ገነት በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ነበረች ያለው ፖሊስ፣ እሷን ጨምሮ ሁሉም ሟቾች በሻይ ቡና እና በአልኮል መጠጥ ንግድ ላይ ተሰማርተው ነበር። የምርመራው መነሻ የሆነው በኅዳር 7/2019 ዓ.ም የተገደለችው የሚሊዮን ገብረእግዚአብሔር ግድያ ነው። ከሟቿ ጋር ትሠራ የነበረች ሴት፣ ሚሊየን በጠዋት ስልክ ደውላላት፣ ተስፋይ የሚባል ሰው ቡና በርካሽ ዋጋ እንደሚያቀርብላት ነግሯት ወደ ሥራ ቦታዋ እንድትመጣ እንደጠራት አሳውቃት ነበር። አብራት የምትሠራዋ ወደ ሥራ ቦታው ባቀናችበት ወቅት ግን ሚሊየን ሻይ ቡና የምትሠራበት ቦታ በሩ ተዘግቶ ነበር የጠበቃት። በዚህም ምክንያት ጓደኛዋን ፈልጋ ስላጣቻት ቁልፍ አፈላልጋ በሩን ከፍታ ስትገባ አስክሬኗን እንዳገኘች የፖሊስ ምርመራ አመልክቷል። ፖሊስ ከጓደኛዋ በተገኘው መረጃ መሠረት ምርመራ ሲያካሂድ ተስፋይ የሚባል ግለሰብ ከሟቿ ጋር በስልክ ተደዋውሎ እንደነበር ማወቁን ኮማንደር ገብረሥላሴ ገልጸዋል። ከዚያም የተጠርጣሪውን ማንነት፣ አካላዊ ገጽታ እና ልዩ መለያ በማጣራት ወደ ተጠርጣሪው መድረሳቸውን ተናግረዋል። ግለሰቡ ከዚህ ቀደም በሠራው ወንጀል ከተፈረደበት እስር ማምለጡም ፖሊስ ምርመራውን ተስፋይ ላይ እንዲደረግ አስችሏል ሲሉ ኮማንደሩ ይገልጻሉ። ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላም የወንጀሉን እውነተኛ ሁኔታ ለማረጋገጥ ግድያዎቹ ወደ ተፈጸሙባቸው ቦታዎች እንዲመራቸው እንደጠየቁት፣ እሱም እየመራ አምስት የወንጀል ቦታዎችን እንዳሳየ ኮማንደሩ አስረድተዋል። ከሟቾቹ መካከል የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችው ገነት ደጀን ከተገደለች በኋላ የት እንዳለች ሳይታወቅ እንደቆየች እና ቤተሰቦቿም በዚያን ጊዜ ስለመገደሏ እንዳላወቁ ተገልጿል። ተጠርጣሪው ከከተማ ራቅ ወዳለ ቦታ ወስዶ አስክሬኗ የሚገኝበትን ቦታ የጠቆመ ሲሆን፣ የሟቿ መሆናቸውን የሚያመለክቱ የግል ንብረቶች እና የአካል ቅሪቶች እንዳገኙ ኮማንደሩ ገልጸዋል። የሌሎቹ አስክሬን ቀደም ብሎ የተገኘ ቢሆንም በማን እና በምን ምክንያት እንደተገደሉ ለመመርመር በወቅቱ የነበረው የፀጥታ ሁኔታ እንዳላስቻለ ኮማንደሩ ተናግረዋል። ከሟቾቹ መካከል የሻለም ዘነበ እና ገነት ደጀን ከቤት ውጪ ሲገደሉ ቀሪዎቹ በቤታቸው መገደላቸውን ፖሊስ አመልክቷል። ይሁንና ምርመራው ሙሉ በሙሉ አልተጠናቀቀም። በተለይ የአምስት ዓመቷ ሕፃን ያለችበትን ቦታ ለማወቅ እና ሌሎች ተጨማሪ የወንጀል ጥቆማዎች ካሉ ለማጣራት ምርመራው እየቀጠለ እንደሆነ ኮማንደር ገብረሥላሴ አማረ ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ገገልጸዋል። ምንጭ| BBC News Amharic

Открыть в Telegram
Просмотры59−15%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12759Фото
Просмотры65−6%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#12758Фото
Просмотры70+1%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12757Превью ссылки

Переслано из Fund 2 Learn

🇰🇷 KAIST Undergraduate Scholarship 2027 – በደቡብ ኮሪያ ሙሉ የትምህርት ክፍያ እና ወርሃዊ አበል! 12ኛ ክፍልን ጨርሰዋል ወይም በ2027 ይጨርሳሉ? በእስያ ቀዳሚ ከሆኑት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ በሆነው KAIST Bachelor ይማሩ 👇 🎓 የBachelor ቅበላ ለ2027 የበልግ ወቅት (Fall 2027፣ Regular Track)፣ በእንግሊዝኛ 💰 ምን ይሸፍናል? ✅ ለ8 ሴሚስተር ሙሉ የትምህርት ክፍያ ✅ በወር 350,000 የኮሪያ ዎን የኑሮ አበል ✅ የሕክምና መድን (Health Insurance) ⚠️ ከ1ኛ ዓመት በኋላ ከ4.3 ቢያንስ 2.7 GPA መያዝ ያስፈልጋል 👥 ማን ማመልከት ይችላል? 🔹 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እስከ 31 August 2027 የሚያጠናቅቁ 🔹 የኮሪያ ዜግነት የሌላቸው (ወላጆቻቸውም ኮሪያውያን ያልሆኑ) 🔹 ጥሩ እንግሊዝኛ (ለምሳሌ IELTS 6.5 ወይም TOEFL iBT 83 ይመከራል) 📄 ትራንስክሪፕት፣ ፓስፖርት፣ የብሔራዊ ፈተና ወይም SAT ውጤት፣ የእንግሊዝኛ ፈተና እና እስከ 2 Recommendation Letter። የማመልከቻ ክፍያ 80 ዶላር ነው። 📅 የመጨረሻ ቀን፦ ጥር 6 ቀን 2019 ዓ.ም (14 January 2027)፣ ከምሽቱ 6:00 በኮሪያ ሰዓት 💡 ምክር፦ የተለየ የስኮላርሺፕ ማመልከቻ የለም፤ በቅጹ "Statement of Financial Resources" ክፍል "KAIST Scholarship"ን ብቻ ይምረጡ። የብሔራዊ ፈተና ውጤትም ተቀባይነት አለው። 🔗 ኦፊሴላዊ ሊንክ፦ https://admission.kaist.ac.kr/intl-undergraduate/support/scholarships/kaist 📖 ሙሉ መረጃውን በድረ-ገጻችን ያንብቡ፦ https://fund2learn.hahuprime.com/kaist-undergraduate-scholarship-2027/ 🤝 ይህን እድል 12ኛ ክፍል ለሚጨርሱ ጓደኞችዎ ያጋሩ! #Undergraduate #StudyInKorea #Scholarships 📌 ለተጨማሪ እድሎች፦ @fund2learn

Открыть в Telegram
Просмотры67−3%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12756Фото

Переслано из Hahuprime Amharic

ኢትዮጵያ ለግብፅ፦ «መጀመሪያ የራሳችሁን የውኃ ብክነት አስተካክሉ» የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ ማክሰኞ ኅዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ግብፅ ለውኃ ችግሯ ኢትዮጵያን ከመውቀስ ይልቅ የራሷን የውኃ አጠቃቀም ማዘመን አለባት ብለዋል። ሚኒስትሩ ግብፅ በሞቃታማ አየር ንብረት ውስጥ ባህላዊ የጎርፍ መስኖ መጠቀሟን፣ ከ500 ሺህ ሄክታር በላይ ሩዝና ከ100 ሺህ ሄክታር በላይ ሸንኮራ አገዳ ማልማቷን እንዲሁም የዓባይን ውኃ ወደ ቶሽካና ሲና በረሃዎች መቀየሷን ተችተዋል። ግብፅ አዲስ ከተማ ለመገንባት ማቀዷን በመጥቀስም፣ ካይሮ የዓባይን ውኃ የሚነኩ ፕሮጀክቶችን ከመጀመሯ በፊት የኢትዮጵያን ፈቃድ ማግኘትና «የአንድ ወገን እርምጃዎችን ማቆም» አለባት ብለዋል። አስተያየቱ የመጣው ግብፅ፣ ሱዳንና ኤርትራ ቅዳሜ ኅዳር 12 ቀን በአስዋን ባደረጉት ስብሰባ «የአንድ ወገን የውኃ እርምጃዎችን» እንደማይቀበሉ ካስታወቁ ከሦስት ቀናት በኋላ ነው። ግብፅ እስካሁን ምላሽ አልሰጠችም። ሚኒስትሩ ግን ለውይይት በር አልዘጉም፤ በዓባይ ተፋሰስ የጋራ የውኃ መሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ሐሳብ አቅርበዋል። ሙሉውን ያንብቡ: HahuPrime #ዓባይ #ኢትዮጵያ #ግብፅ @hahuprime_et

Открыть в Telegram
Просмотры73+5%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12755Фото
Просмотры77+11%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12754Фото

Переслано из Hahuprime Amharic

ሀገራት በAI «ገዳይ ሮቦቶች» ላይ ደንብ ለማርቀቅ ተስማሙ፤ አስገዳጅ ስምምነት ግን የለም በጄኔቫ እስከ ሌሊቱ 10 ሰዓት ገደማ በዘለቀ ድርድር፣ የተባበሩት መንግሥታት የጦር መሣሪያ ስምምነት አባል የሆኑ 128 ሀገራት ቅዳሜ ኅዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም. አንድ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል። ሀገራቱ ሰው ሳያዝዛቸው ዒላማ መርጠው የሚያጠቁ ገዳይ ራስ-ገዝ የጦር መሣሪያዎችን የሚመለከት ሰነድ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ለማዘጋጀት ተስማምተዋል። ሆኖም ሰነዱ ሕጋዊ አስገዳጅነት ይኖረው እንደሆነ አልተወሰነም። ወደ 100 የሚጠጉ ሀገራት አስገዳጅ ሕግ ቢፈልጉም አሜሪካ፣ ሩሲያና እስራኤል መቃወማቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። የተመድ የትጥቅ ማስፈታት ኃላፊ ኢዙሚ ናካሚትሱ ሁለት ዓመት «በጣም የተጣበበ ጊዜ» መሆኑን ገልጸው፣ አስገዳጅ ስምምነት የማግኘት ዕድል አሁንም ክፍት ነው ብለዋል። የአፍሪካ ሀገራት አስገዳጅ ስምምነት እንዲኖር ሲገፋፉ ቆይተዋል። ድሮኖች በሱዳን፣ በኢትዮጵያና በሶማሊያ ጦርነቶች ውስጥ ከፍተኛ ሚና በያዙበት በዚህ ወቅት፣ መዘግየቱ ሲቪሎችን ለአደጋ ያጋልጣል ሲሉ ዘማቾች አስጠንቅቀዋል። ኢትዮጵያ የስምምነቱ አባል ባትሆንም በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ተመሳሳይ ውሳኔዎችን ደግፋለች። ሙሉውን ያንብቡ: HahuPrime #AI #ገዳይ_ሮቦቶች #ተመድ @hahuprime_et

Открыть в Telegram
Просмотры85+22%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#12753Текст

Переслано из Fund 2 Learn

🇹🇷 Erasmus+ ልውውጥ በMETU፣ ቱርክ 2027 — ለባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ብቻ! ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአንካራ በሚገኘው Middle East Technical University (METU) የ2027 የፀደይ ሴሚስተር ለመማር ወይም ምርምር ለማድረግ የErasmus+ KA171 ጥሪ ከፍቷል። ይህ እድል አሁን በBDU በመደበኛ መርሐ ግብር ለተመዘገቡ ተማሪዎች ብቻ ነው። 👇 🎓 የፀደይ 2026–2027 ሴሚስተር በMETU — ኮርስ ወይም ምርምር። ዋና ሙሉ ድጋፍ የሚያገኙት 2 ቦታዎች ናቸው፤ ተተኪዎችም ይመደባሉ። 💰 በወር €800 የኑሮ አበል፣ አንድ ጊዜ የጉዞ አበል ከ€211 እስከ €1,735፣ እና በMETU የትምህርት ክፍያ ሙሉ በሙሉ ይቀራል። ⚠️ የተመረቁ ወይም ከሌላ ተቋም የመጡ አይመለከቱም። የመጀመሪያው 70% ክፍያ ከደረሱ ከ2–3 ሳምንት በኋላ ስለሚገባ፣ የመጀመሪያውን ወር የኑሮ ወጪ በራስዎ ገንዘብ ለመሸፈን ይዘጋጁ። የካምፓስ መኖሪያ አይረጋገጥም። 👥 ከሁለተኛ ዓመት በላይ፣ ቢያንስ አንድ ሙሉ ዓመት ያጠናቀቁ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ማስተርስ ወይም ፒኤችዲ ተማሪዎች (የድኅረ ምረቃ በጣም ይበረታታል)። ቢያንስ B1 እንግሊዘኛ (CEFR)፣ የሚያገለግል ፓስፖርት፣ እና በMETU ቢያንስ 30 ECTS። ለምርምር የሚሄዱ ማስተርስ/ፒኤችዲ ተማሪዎች የMETU Supervisor Acceptance Letter እና የBDU የአማካሪ ድጋፍ ደብዳቤ ያስፈልጋቸዋል። 📅 የBDU ውስጣዊ የመጨረሻ ቀን፦ ኅዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም (5 December 2026)፣ ከሰዓት በኋላ 5:00 በኢትዮጵያ ሰዓት 💡 ማመልከቻው በነፃ በኦፊሴላዊ ቅጹ ብቻ ነው። ፋይሎች በPDF፣ የተጠየቁትን ብቻ ይጫኑ። ገንዘብ የሚጠይቅ ኤጀንት አይመኑ። 🔗 የማመልከቻ ቅጽ፦ https://forms.gle/zuWWqLw8hwHkJsDUA 📖 ሙሉ መረጃውን በድረ-ገጻችን ያንብቡ፦ https://fund2learn.hahuprime.com/erasmus-exchange-metu-turkiye-2027-bahir-dar/ 🤝 ይህን እድል ለባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጓደኞችዎ ያጋሩ! #ErasmusPlus #METU #BahirDarUniversity 📌 ለተጨማሪ እድሎች፦ @fund2learn

Открыть в Telegram
Просмотры82+18%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12752Фото
Просмотры76+10%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12751Фото
Просмотры63−9%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12750Фото
Просмотры64−8%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#12749Фото

Переслано из Hahuprime Amharic

ካርቱም ላይ ጎህ ሳይቀድ የድሮን ጥቃት፤ የ10 ዓመት ሕፃን ተገደለ፣ የተ.መ.ድ. ሕንፃ ተጎዳ እሑድ ኅዳር 13 ቀን 2019 ዓ.ም. ጎህ ሳይቀድ የሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ከሁለት ሰዓት በላይ በድሮኖች ጥቃት ተፈጽሞባታል። የሠራዊቱ የአየር መከላከያ ተኩስ በአየር ማረፊያው አካባቢ ይሰማ እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል። ከካርቱም በስተደቡብ በጀበል አውሊያ አንድ ድሮን መኖሪያ ቤት በመምታቱ የ10 ዓመት ሕፃን መገደሉን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። የሕክምና ምንጮች ለአልጀዚራ እንደተናገሩት በኦምዱርማን ሦስት ሲቪሎች ተገድለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞቹ በውስጡ የነበሩበት አንድ ሕንፃው መጎዳቱን ገልጾ «ሲቪሎች የጦርነት ሕጋዊ ዒላማ አይደሉም» ብሏል። የአገር ውስጥ አየር መንገዶች ወደ ካርቱም የሚያደርጉትን በረራ አቋርጠዋል። የሱዳን ወታደራዊ ምንጮች ድሮኖቹ ከኢትዮጵያ ግዛት ተነስተዋል ቢሉም ይህ በገለልተኛ ወገን አልተረጋገጠም። ኢትዮጵያ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን (RSF) ትደግፋለች የሚለውን ክስ «መሠረተ ቢስ» በማለት ስታስተባብል ቆይታለች። ሙሉውን ያንብቡ: HahuPrime #ሱዳን #ካርቱም #Sudan @hahuprime_et

Открыть в Telegram
Просмотры61−12%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#12748Фото

Переслано из SPORT GUADA/ስፖርት ጓዳ

የዣቢ አሎንሶ የቼልሲ የጫጉላ ጊዜ አበቃ! ቼልሲ ቅዳሜ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ በሊድስ ዩናይትድ 4-1 ሲሸነፍ፣ የቡድኑ አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ በገዛ ደጋፊዎቹ ተቃውሞ ገጥሞታል። ሊድስ ከ1999 ወዲህ በስታምፎርድ ብሪጅ የመጀመሪያ ድሉን ሲያስመዘግብ፣ ቼልሲ ባለፉት አራት የሊግ ጨዋታዎች ሶስቱን ተሸንፎ ከአምስተኛ ወደ ስምንተኛ ደረጃ ወርዷል። አማካዩ ሞይሰስ ካይሴዶ በጨዋታው መጀመሪያ ላይ በጉዳት መውጣቱን ተከትሎ፣ ጆአዎ ፔድሮ እና ሪስ ጀምስን ጨምሮ የቡድኑ ጉዳተኞች ቁጥር ስድስት ደርሷል። አሎንሶ ከጨዋታው በኋላ "ዛሬ በአእምሮ ደካማ ጊዜ ላይ እንዳለን ተሰምቶኛል፤ ቡጢ ሲያርፍብን በጠንካራ ሁኔታ ማገገም አልቻልንም" ብሏል። የቀድሞው የእንግሊዝ አጥቂ አላን ሺረር በበኩሉ "የአሎንሶ የጫጉላ ጊዜ አብቅቷል፤ ተጫዋቾቹ ከሚጠበቅባቸው በጣም ርቀዋል" ሲል ተችቷል። ቼልሲ በቀጣይ ዓርብ ምሽት 5:00 ሰዓት ወደ ሲቲ ግራውንድ አቅንቶ ኖቲንግሃም ፎረስትን ይገጥማል። በግንቦት ወር የአራት ዓመት ውል የፈረመው አሎንሶ የሚመራው ቼልሲ በ11 ጨዋታ 16 ነጥብ ይዞ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ፎቶ: BBC Sport (Getty Images) #Chelsea #XabiAlonso #PremierLeague @SPORTGUADA

Открыть в Telegram
Просмотры73+5%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12747Фото

Переслано из Hahuprime Amharic

ከ167 ዓመታት በኋላ፦ በClaude AI እገዛ የተሠራው የሪማን መላምት ማረጋገጫ ገለልተኛ ፍተሻዎችን አለፈ ኅዳር 13 ቀን 2019 ዓ.ም. — በአንትሮፒክ ኩባንያ የሚሠሩት የሒሳብ ሊቅ ሌቨንት አልፖጌ ከኩባንያው የAI ሞዴል Claude ጋር በመሆን በዓለም ታዋቂውን የሪማን መላምት (Riemann Hypothesis) ማረጋገጣቸውን ዓርብ ኅዳር 11 አስታውቀዋል። በ1859 እ.ኤ.አ. የቀረበው ይህ መላምት የፕራይም ቁጥሮች በቁጥር መስመር ላይ እንዴት እንደሚሰራጩ የሚመለከት ሲሆን፣ ለመፍታቱ የአንድ ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ተዘጋጅቶለታል። ማረጋገጫው በሰው የሚነበብ ጽሑፍ ሳይሆን 17 ሚሊዮን መስመር ያለው የLean ኮምፒውተር ኮድ ብቻ ነው። ቅዳሜ ኅዳር 12 የLean እና የMathlib ማኅበረሰቦች ማረጋገጫው ትክክል መሆኑን በጋራ መግለጫ አረጋግጠዋል። ታዋቂ የሒሳብ ሊቃውንት ይህን ታሪካዊ ሊሆን የሚችል ስኬት ብለውታል፤ ሆኖም ማረጋገጫውን በሚገባ ለመረዳት ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ ያስጠነቅቃሉ። አንዳንዶች ደግሞ ይፋ የተደረገበትን ጊዜ ተችተዋል። ሙሉውን ያንብቡ: HahuPrime #ሰው_ሰራሽ_አስተውሎት #ሒሳብ #AI @hahuprime_et

Открыть в Telegram
Просмотры64−8%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12746Фото

Переслано из Hahuprime Amharic

ግብፅ፣ ሱዳንና ኤርትራ፦ «የቀይ ባሕር ደኅንነት የባሕሩ ዳርቻ አገሮች ኃላፊነት ነው» የግብፅ፣ የሱዳንና የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቅዳሜ ኅዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም. በግብፅ አስዋን ከተማ ባደረጉት የሦስትዮሽ ስብሰባ የቀይ ባሕርን የማስተዳደርና ደኅንነቱን የመጠበቅ ኃላፊነት «የባሕሩ ዳርቻ አገሮች» እንደሆነ ገልጸዋል። የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ መሠረት ሚኒስትሮቹ በጸጥታም ሆነ በውኃ ደኅንነት ጉዳዮች ላይ የሚወሰዱ «የአንድ ወገን እርምጃዎችን» እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል። መግለጫው የትኛውንም አገር በስም አልጠቀሰም። ይሁን እንጂ አቋሙ ባለፈው ጥቅምት ወር በኒው አላሜይን የተፈረመውን የአራቱ አገሮች መግለጫ የሚደግም ነው። ኢትዮጵያ በወቅቱ በሰጠችው ምላሽ ማንኛውም የቀይ ባሕር ደኅንነት ውይይት የኢትዮጵያን ሕጋዊ ጥቅም ከግምት ማስገባት እንዳለበት፣ ዓባይም ከናይል ወንዝ አጠቃላይ ፍሰት 85 በመቶ ገደማውን እንደሚያበረክት አስታውቃ ነበር። ስብሰባው የተካሄደው ኢትዮጵያና ኤርትራ በድንበራቸው ላይ ሠራዊት በማስፈር ውጥረቱ በተባባሰበት ወቅት ነው። ኢትዮጵያ በአስዋኑ ስብሰባ ላይ እስካሁን ይፋዊ ምላሽ አልሰጠችም። ሙሉውን ያንብቡ: HahuPrime #ቀይባሕር #ኢትዮጵያ #RedSea @hahuprime_et

Открыть в Telegram
Просмотры61−12%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12745Фото

Переслано из SPORT GUADA/ስፖርት ጓዳ

የአርሰናሉ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ ጉዳት አስተናገደ! የአርሰናሉ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ ቅዳሜ ቡድኑ በሴንት ጀምስ ፓርክ ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር 2-2 በተለያየበት ጨዋታ በ70ኛው ደቂቃ ጉዳት ደርሶበት ተቀይሮ ወጥቷል። የ31 ዓመቱ ስፔናዊ ከኒውካስሉ አጥቂ ዊሊያም ኦሱላ ጋር በተጋጨበት ወቅት ትከሻው ላይ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፣ በኬፓ አሪዛባላጋ ተተክቷል። ራያ እስከዚህ ጨዋታ ድረስ በዚህ የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉና በሻምፒዮንስ ሊጉ እያንዳንዱን ደቂቃ ተጫውቷል፤ ዛሬም የኤምአርአይ ምርመራ ይደረግለታል ተብሎ ይጠበቃል። አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከጨዋታው በኋላ "ዴቪድ ለእኛ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እናውቃለን፤ ነገ ተጨማሪ መረጃ ይኖረናል" ሲሉ ተናግረዋል። አርሰናል ማክሰኞ ምሽት 5:00 ቦሩሲያ ዶርትሙንድን በሻምፒዮንስ ሊግ፣ እሁድ ምሽት 1:30 ደግሞ ማንቸስተር ሲቲን በፕሪሚየር ሊግ ያስተናግዳል። ቡካዮ ሳካና ማርቲን ሱቢሜንዲን በጉዳት ያጣው አርሰናል በስድስት ነጥብ ልዩነት የሊጉ መሪ ነው። ፎቶ: BBC Sport (Getty Images) #Arsenal #DavidRaya #PremierLeague @SPORTGUADA

Открыть в Telegram
Просмотры69−1%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12744Фото

Переслано из Hahuprime Amharic

በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት ውጊያው ወደ ዋና ከተማዋ ደማዚን እየተቃረበ ነው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF) እና በአብደልአዚዝ አል-ሒሉ የሚመራው የSPLM-ሰሜን ቡድን ጥምረት ሐሙስ ኅዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም. የባው (Bau) ወረዳ ዋና መሥሪያ ቤትን፣ ዓርብ ኅዳር 11 ደግሞ በጌይሳን ወረዳ የሚገኙ አምስት አካባቢዎችን መቆጣጠሩን አስታውቋል። እነዚህ አካባቢዎች ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰነው የብሉ ናይል ግዛት ዋና ከተማ ደማዚን 40 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ይገኛሉ። የግዛቱ መንግሥት ቃል አቀባይ ሰይፍ አል-ነስር ሚናላህ ግን ተዋጊዎቹ ወደ ከተማዋ እየተጠጉ ነው የሚለውን አስተባብለው፣ ሠራዊቱ አሁንም የበላይነቱን እንደያዘ ገልጸዋል። የሁለቱም ወገኖች የጦር ሜዳ መግለጫዎች በገለልተኛ ወገን አልተረጋገጡም። የባው ወረዳ ኮሚሽነር እንዳሉት የ35 መንደሮች ነዋሪዎች ወደ ደማዚን ተሰደዋል፤ አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎችም መውጣት ጀምረዋል። የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) መረጃ እንደሚያሳየው ከጃንዋሪ እስከ ኦክቶበር 2026 ብቻ በብሉ ናይል ግዛት ወደ 120 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል፤ ደማዚን ቀድሞውንም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችን እያስተናገደች ነው። ኮሚሽነሩ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ግዛቱን በማተራመስ «በቀጥታ ተሳትፈዋል» ብለው ቢከሱም ማስረጃ አላቀረቡም፤ ሁለቱም መንግሥታት ምላሽ አልሰጡም። ሙሉውን ያንብቡ: HahuPrime #ሱዳን #ብሉናይል #Sudan @hahuprime_et

Открыть в Telegram
Просмотры81+17%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12743Фото

Переслано из SPORT GUADA/ስፖርት ጓዳ

ቦርንማውዝ በታሪኩ የመጀመሪያውን ተከታታይ 9 ድል አስመዘገበ! የማርኮ ሮዝ ቦርንማውዝ በፕሪሚየር ሊጉ ኖቲንግሃም ፎረስትን በቫይታሊቲ ስታዲየም 2-0 በማሸነፍ በሁሉም ውድድሮች ያስመዘገበውን ተከታታይ ድል ወደ ዘጠኝ ከፍ አድርጓል። ቡድኑ በ1998-99 እና በ2012-13 ያስመዘገባቸውን የስምንት ተከታታይ ድሎች ክብረወሰን በዚህ ድል አሻሽሏል። ብራዚላዊው አጥቂ ኤቫኒልሰን በ19ኛው ደቂቃ ቀዳሚውን ጎል ሲያስቆጥር፣ ጀስቲን ክላይቨርት በመጀመሪያው አጋማሽ የጭማሪ ሰዓት ሁለተኛውን አክሏል። ኤቫኒልሰን በተከታታይ ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ላይ ጎል በማስቆጠር የውድድር ዘመኑን ጎሎች ስድስት አድርሷል። አሰልጣኝ ማርኮ ሮዝ ለBBC Match of the Day "ስለ ክብረወሰን አናስብም፤ የምናስበው ስለሚቀጥለው ጨዋታ ብቻ ነው" ብለዋል። ቦርንማውዝ ሐሙስ ምሽት 2:45 በዩሮፓ ሊግ ሴልታ ቪጎን በስፔን ይገጥማል፤ እሁድ ቀን 11:05 ደግሞ ከፉልሀም ጋር ይጫወታል። ድሉ ቦርንማውዝን በ18 ነጥብ ወደ ሊጉ አራተኛ ደረጃ ሲያሳድገው፣ ፎረስት በ9 ነጥብ 17ኛ ላይ ቀርቷል። ፎቶ: ESPN #Bournemouth #PremierLeague #Evanilson @SPORTGUADA

Открыть в Telegram
Просмотры82+18%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—