Кабинет
ነገረ ወንጌላውያን

ነገረ ወንጌላውያን

በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ የሚፃፉ ፅሁፎች፣ ዘገባዎችና ዜናዎች ይቀርባሉ! ትምህርቶች፣ መረጃዎችና ምካቴ እምነቶች በዚህ ቻናል ይስተናገዳሉ! በተለያዮ ሶሻል ሚዲያዎች የሚገኙ ፀሐፊያን የሚፅፉቸው ፅሁፎችን እናጋራለን።

Юзернейм
@negere_evangelical
Категория
Религия
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики5 130
Просмотров на пост, 7 дн.328за 7 дней
ERR6,39 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
27 окт. 2026 г.2 140
28 окт. 2026 г.1 080
31 окт. 2026 г.1 885
26 нояб. 2026 г.328

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01

    የዘመናችን ቤተ ክርስቲያን ተሃድሶ ያስፈልጋታል ስል በእውነትና በጸጋው ወደ መሞላት መመለስ ይኖርባታል ማለቴ ነው። ይኽ ደግሞ ሊሆን የሚችለው በአቦሰጥ (randomly) አይደለም። ይኽ እንዲሆን በመጀመሪያ ደረጃ የቤተ ክርስቲያን ትኩረት ወደ ክርስቶስ ማንነትና አገልግሎት ምሳሌነት መመለስ አለበት። ክርስቶስን ምሳሌዋ ያላደረገች ቤተ ክርስቲያን የትም ጥሻ ውስጥ ናት። የሞተላትን እረኛዋን በመተው ሌላ ነገር የምትከተል ቤተ ክርስቲያን ስታለች። ሞቱንና ትንሣኤውን የስብከቷ አንኳር መልዕክት የማታደርግ ቤተ ክርስቲያን የርሱ አይደለችም። ተሃድሶ መንፈሳዊ መነቃቃት እንጂ አዕምሮአዊ ንቃት አይደለም። ለመንፈሳዊ መነቃቃት ደግሞ የሰውን ልብ የሚያዘጋጀው ወይም የሚከፍተው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። የምሁራን ትምህርት፥ የመንፈሳዊያን ልምምድ፥ የታላላቆች ምክር፥ የኃይማኖት መሪዎች ቅንዓት ቤተ ክርስቲያንን ያለ መንፈስ ቅዱስ ሥራ ሊያነቃቃት አይችልም። አሁንም ልድገም ቤተ ክርስቲያንን ወደ ቃሉ ሥልጣን፥ ወደ ክብሩ፥ ሙላት፥ ወደ መንፈሱ አሠራር፥ ወደ ንስሓና ወደ ቅድስና ሕይወት ለመመለስ የሚያስችለው ቅዱሱ የእግዚአብሔር መንፈስ ብቻ ነው። ተሃድሶ ሰዎችን ወደ ሉተራዊነይ፥ ወደ ካልቪንስትነይ፥ ወደ ዌስሊያንነት፥ ወደ ጴንጤቆስጤያዊነት ማዘዋወር አይደለም። ወደ እግዚአብሔር ፍቅር፥ ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አገዛዝ፥ ለጌታ ወደሚኾን ታማኝነት፥ ለቃሉ ወደሚኾን ታዛዥነት ነው። ተሃድሶ ፕሮግራም አይደለም “reformation is not an event” የሚባለው ትክክለኛ መረዳት ነው። yes its not an event. ኮንፈራንስ አይደለም። ዝማሬና የአዳራሽ ውስጥ ጭፈራም አይደለም። ረጅም ጸሎት መቻል አይደለም። አቧራ ማጨስ መድረክ መሙላት አይደለም። የሚዲያ ጋጋታ የደጋፊ ብዛት አይደለም። የወረት ሰሞናዊ ግርግር አይደለም። ተሃድሶ የሕይወት ለውጥ ነው። የአካኼድ የአቅጣጫ ለውጥ ነው። ወደ መለኮታዊ አጀንዳ መመለስ ነው። ወደ እግዚአብሔር ደስታ መመለስ ነው። ቤተ ክርስቲያን በዚህች ምድር ባለችበት ዘመን ሁሉ እንድትሠራው ወደ ተሰጣት የምስዮናዊነት ተልዕኮ ወደ ነቢይነት ሚና መመለስ ነው። ወደ ቀደመው ክብሯ ወደ ነበራት ሥፍራዋ መመለስ ነው። መልካም የተሃድሶ መታሰቢያ ቀን ለፕሮቴስታንት ወንድሞችና እህቶች!! ብዬ ቋጨሁ። ወርቅነህ ዳዊት

    Текст
    Просмотры2,94 тыс.
    Пересылки—
    Реакции14
    Комментарии—
  2. 02

    የዛሬ 509 ዓመት፣ በዛሬዋ ዕለት፣ በኦክቶበር 31፣ 1517 አመተ እግዚ አንድ ብዙም የማይታወቅ የአውገስጢኖስ ገዳም መነኩሴ፣ በአንዲት ትንሽ የጀርመን ዩኒቨርስቲ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ፕሮፌሰር የነበረ ሰው በዩኒቨርስቲው ቅጥር ውስጥ በሚገኘው የቤተ ክርስትያን በሮች ላይ የተወሰኑ ወረቀቶችን ለመለጠፍ መዶሻ አነሳ። እነዚያን ወረቀቶች በቤተ ክርስትያን አደባባይ ላይ የለጠፈበት ምክንያት የቤተ ክርስትያኑ አደባባዩ ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ እንደ ማስታወቅያ ሰሌዳ ያገለግል ስለነበር በርከት ያለ ሰው እንዲመለከተውና ውይይት እንዲያጭር አስቦ ነበር። በለጠፈው ወረቀት ውስጥ 95 አናቅጽት በዋናነት የሰውን ድኅነት እንደ ቁስ መገዛቱን በማውገዝ ነበር። ሰው ከፑርጋቶሪ ይወጣ ዘንድ የኅጢአት ይቅርታ ሰነድ በመኸከለኛ ዘመኗ ካቶሊክ ለጉድ ይቸበቸብ ነበር። ይህ ሰነድ ወይም 'ኢንደንጀልስ' በወረቀት የሰፈረና የቤተ ክርስትያንን ይሁንታ አግኝቶ መግዛት ለቻለ ሁሉ የቀረበ ነበር። ህዝቡም ኢንደልጀንሱን ይገዛ ዘንድ 'በቅቤ አቅልጥ' ደላላ አሻሻጮች ይጎተጎት ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ይሁንታዋን ሰጥታ ነበር። ህዝቡ ለራሱ፣ ለዘመዱና ለወዳጁ ይገዛ ነበር፤ በሞቱት ስም እንኳን ሳይቀር ይቸረቸራል። ሉተር 95 አናቅጽቱን ጽፎ ሲለጥፋቸው ዩኒቨርስቲ ውስጥ ባሉት ፕሮፌሰሮች መሃል ውይይት እንዲፈጥር በማሰብ ነበር። ነገር ግን ዘጠና አምስቱ አናቅጽት ከቪተንበርግ ማኅበረሰብ በዘለለ በመላው የጀርመን ግዛቶችና በጠቅላላው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ዘንድ ታላቅ ሁካታን ለመፍጠር በቃ። በአጭር ጊዜ ውስጥም ብዙ ህዝብ የዚህን መነኩሴ ስም ማወቅ ጀመረ፣ በቪተንበርግ ዩኒቨርስቲ የሥነ መለኮት ዶክተሩን ማርቲን ሉተርን። ህዝብን በማወክና ባለመታዘዝ ቤተክርስትያን ከሰሰቸው፣ በጀርመን ንጉስ ፊትም ራሱን እንዲከላከልና ያደረገው ሃሰት መሆኑን አውቆ እንዲያስወግድ ታዘዘ። ያደረገው ስህተት መሆኑን ባለመቀበሉና ህሊናው ለቅዱሳት መጽሐፍት ተገዢነታቸውን በማጽናቱ ምክንያት የውጤቱን ስሜት 500 አመታትን ተሻግሮ ዛሬ እኛም ይሰማናል። . «ስቻለሁ የምለው አንዳች ነገር የለኝም፤ ኅሊናዬ ከሚያዘኝ ውጪ መሆን ትክክልም ሆነ አግባብ አይደለም። እነሆ፤ እዚሁ ቆሜያለሁ፤ ከዚህ ውጪ ምንም ላደርግም አይቻለኝም። እግዚአብሔር ሆይ እርዳኝ። አሜን።» . ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ እንዳሉት፣ "አሕይዎና ተሐድሶ (Revival and Renewal or Reformation) ተደላድሎና ተመቻችቶ በተቀመጠ ሥርዐት (Establishement) ውስጥ የዛገና የሚራገፍ ነገር የሚያይ የአእምሮ ችሎታና የተፈጥሮ ተሰጥዎ ካላቸው ታላላቅ ሰዎች ዘንድ የሚመጡ ሐሳቦች ናቸው።" በዚህ ሰው ለመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት በታማኝነት መታዘዝና መሰጠት ምክንያት የቤተክርስቲያን መልክ እንደ ቀደሞው ላይሆን ተለውጧል። . ተሐድሶ ብቻ መቆምን ይጠይቃል። ዘመንን መረዳትን፣ መጽሐፍትን መመርመርን፣ ለእግዚአብሔርና ለህሊናችን ታማኝ መሆንን ይጠይቃል። ተሐድሶ ወደ አባቶችና አያቶች ለመንፀሪያ መመልከትን አንደ ቄንጥ አያይም። የድነትን መኸከለኛ፣ የእምነትን ፈፃሚ፣ የእግዚአብሔርን መገለጥ፣ ትምሕርተ ክርስቶስን አደብዛዥን ሁሉ ለመቃወም ሁለቴ አያስብም። ተሐድሶ ቃለ–እግዚአብሔር ማሕደረ–ክርስቶስ በተባለችው ቤተክርስቲያን ሲደፈጠጥ ጥሪውን በማማ ላይ ያሰማል፤ እነሆኝ ለህሊናዬም ለቃሉም ቆሜያለሁ ይላል። እግዚአብሔር ልጁን በገለጠበት ቃል በኩል ለኅሊናዬ ብቻዬን እንኳን ቢሆን እቆማለሁ የሚል እውነትና ፅናት ያድለን። . የዛሬ 509 ዓመት የተለኮሰውን የተሐድሶውን እሳት ነገ በቅዱስ ማቴዎስ አንግሊካን ቤተክርስቲያን ከቀኑ 9:00 ጀምሮ እናስበዋለን! ወደ ተተሓድሶው እሳቤዎች መመለስ ከእምነት ድንጋጌ እና ከእምነት መግለጫዎች ስልጣን ሥፍራ አንጻር እንቃኛለን። መልካም ዕለተ ተሐድሶ ማስታወሻ! አማኑኤል አሰግድ

    Текст
    Просмотры2,27 тыс.
    Пересылки—
    Реакции7
    Комментарии—
  3. 03
    Просмотры2,14 тыс.
    Пересылки—
    Реакции30
    Комментарии—
  4. 04

    “Ecclesia semper reformanda est - ቤተ ክርስቲያን ሁሌም መታደስ አለባት (ይኖርባታል)።” በአሥራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተካኸደው የፕሮቴስታንት ተሃድሶ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን የእምነት አቋምና ልምምድ የፈተነ ወይም የፈተሸ ነበር። ጀርመናዊው ሉተር በ1517ዓ.ም ዘጠና አምስት ነጥቦች ያሉትን የተሃድሶ መግለጫ በዊተንበርግ የለጠፈው በዛሬው ቀን October 31 ነበር። ሉተር ቤተ ክርስቲያን የገባችበትን ግብረገባዊ ውድቀት በተለይም የኃጢአት ይቅርታ እንደ ሸቀጥ ለሽያጭ የሚቀርብበትን ሁኔታ በመቃወም ነበር የተሃድሶ ፈር ቀዳጅ በመኾን የተነሳው። ሁኔታው ተመችቶት ወይም እንደሌሎች መነኩሴዎች ዝምታን መርጦ መቀመጥ ቢችልም ይኽንን ማድረግ ምርጫው አልነበረም። በልዩነት አቋሙን ይዞ ወጣ። እንግዲህ ተሃድሶው በኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነቶችና ልምምዶች ላይ የተወሰደ የተቃውሞ እርምጃ ነበር። የአመጽ እርምጃ ሳይኾን የመንፈሳዊ መነቃቃት እርምጃ ነበር። የግብረገብ ውድቀት (Moral decay) በሚኖርበት ጊዜና ሁኔታ ሁል ጊዜም ተሃድሶ ግድ ነው። በዚያ ዘመን አማኙ ማኅበረሰብ ቃሉን ለማግኘትም ኾነ በቃሉ ሕይወቱን ለመምራት ዕድል አልነበረውም (lack of access to scripture ነበር) መጽሐፍ ቅዱስ ከላቲን ውጭ ባልነበረበት በዚያ ሁኔታ ወደ መጽሐፍ ቅዱሳዊው መንፈሳዊነት ትውልዱን ለመመለስ ሉተር ተነሳ። የሚከፈለውን መሥዋዕት ሁሉ የሚጠይቀውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ራሱን አዘጋጅቶ ወደ ሥራው ገባ። ድኅነት በጸጋው በእምነት አማካይነት ብቻ፥ የበላይ ባለ ሥልጣንና መለኮታዊ መገለጥ ቃሉ ብቻ፥ የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና ክብር ለርሱ ብቻ፥ ለሕትወታችን ድኅነት የተሰጠን ሥጦታ መካከለኛው የሕይወታችን ማዕከል ክርስቶስ ብቻ በሚል መንፈሳዊና ሥነ መለኮታዊ ተጽዕኖ ያሳደሩ አቋሞች በዚህ ወቅት ተገልጸው ነበር። በተለይ በጊዜው በተነሡ ሌሎችም አባቶች ታምነው በሂደት ጥርት ያለው የአምስቱ ብቻ አቋም (five solas) ድንቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዘመን ዘለቅ የእምነት አቋም ነበር። ተሃድሶው ያስከተላቸው ሁለንተናዊ ተጽዕኖዎች ሊዘረዘሩ ይገባል። ቤተ ክርስቲያንን ከነበረችበት ሁኔታ ፈቀቅ ሊያደርግ የቻለ ብቻ ሳይሆን አውሮፓን በሁለንተናው የለወጠ ተሃድሶ ነበር። መንፈሳዊና ሥነ መለኮታዊ በረከቶችን ሁሉ አማኝ በእምነት አማካይነት በግሉ መጎናጸፍ እንደሚችል ያመለከተ & የእግዚአብሔርን ጸጋ ያለግዢ በነጻ በእምነት ቀርቦ መቀበል እንደሚችሉ ያሳየ እንቅስቃሴ ነበር። የቤተ ክርስቲያን እረኞች (የቄሳውስት) አገናኝ ጣልቃ ገብነት አማኝ እግዚአብሔርን በግሉ ማወቅና መከተል እንደ ጌታ ማገልገል እንደ አባት ማናገር እንደሚችል መልሶ ያሳሰበ ክርስቶስን ያመነ ሁሉ የንጉሡ ካሕን መኾኑን ያበሰረ ተሃድሶ ነበር። አማኞች የእግዚአብሔርን ቃል በግላቸው የማንበብ፥ የመረዳት፥ ለቃሉ የመታዘዝ መንፈሳዊ አቅም ያላቸው መኾኑን ያስገነዘበ ነበር። ከዚህ ሁሉ ጋር አማኞች የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ አማኞቹ መረዳት በሚችሉት ቋንቋ እንዲኖራቸው እንዲያጠኑና በሕይወታቸው እንዲተረጉሙ ያደረገ ነበር። ድኅነት ሰው በጥረቱ የሚያገኘው ሳይኾን የእግዚአብሔር ነጻ ሥጦታ መኾኑን በማወቅ እምነቱን በጌታ ብቻ እንዲያደርግ ያደረገ ነበር። መንፈሳዊ ጥገኝነትን ያስወገደ አማኞችን በግላቸው የተዘጋጀላቸውን የድኅነት በረከት እንዲያገኙ ያዘጋጀ የእምነት እጃቸውን ዘርግተው እንዲቀበሉ ያደረገ ነበር። በቄሳውስቶችና ካሕናት ዘንድ የነበረው የባለቤትነት ስሜት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከዛሬው በባሰ ነበር። ቤተ ክርስቲያንን እንደ ባለአደራ ሳይኾን እንደባለቤት ቆጥረው ያሻቸውን ያደርጉ ነበር። ይኽንን አስገባሪ ሁኔታ ተሃድሶው ሽሮአል። አንዳንዶች ራሳቸውን በተለየ ሁኔታ ለእግዚአብሔር የቀረበ በማስመሰል ሕዝቡን እንደ ዛሬው ለሸቀጥ አጋልጠው ያስጨንቁ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ በአውሮፓ ትምህርትና ሥልጣኔ እንዲስፋፋ ምክንያት የሆነ እንቅስቃሴ ነበር። የግለሰብ ነጻነትና ሰብዓዊ መብት በተመለከተም ተሃድሶ የራሱን አሻራ ያስቀመጠ ነበር። ነባሩን የሮማውያንን የፖለቲካ ሥልጣን የበላይነት ወደ ፖለቲካዊ ፕሉራሊዝም ወይም ሌሎች አማራጮችን የማየት ያስቻለ ነበር። መንፈሳዊና ግብረገባዊ ብቻ ሳይኾን የኢኮኖሚያዊ አውታርና የፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ሁሉ ዓይን ከፋች እንቅስቃሴ ነበር። ማኅብረሰቡ ከተለያዩ እሥራቶች በመፈታት ወደ ሕሊና ነጻነት እንዲመጣ የበኩሉን ጉልህ ድርሻ የተወጣ ነበር ተሃድሶው። በጊዜው በነበረው ማኅበረሰብ ዘንድ ብቻም ሳይኾን ሁል ጊዜም በየሥፍራው እውነት፥ እምነት፥ የሕሊና ሕግ ሊታደስ የሚገባ መኾኑን በግልጽ ያመለከተ ድንቅ ንቅናቄ ነበር። በርግጥ ተሃድሶው አዲስና መጤ አስተሳሰብ ሳይኾን ቤተ ክርስቲያንን ወደ ቀደመው አዲስ ኪዳናዊው ትምህርትና ልምምድ የመለሰ ነበር። ምሁራን ስለ ተሃድሶ በሰጡት ምስክርነት:- “The Reformation was essentially a revival of New Testament Christianity.” (J.I. Packer) ብለዋል። ይህ አባባል የማያግባባቸው አንዳንድ ዘመነኞች በዚህ ዘመን የተሃድሶ መሪዎችን ተሃድሶአዊ እንቅስቃሴና እርምጃ ሲያጣጥሉ እየሰማን ነው። ይኽ ደግሞ አሳዛኝ ክስተት ነው። እነዚህ ወጣቶች ወደ ጥንታዊው ክርስትና የመመለስን አስፈላጊነት ቢናገሩም ይኽንን ታላቅ ሥራ ግን የማጣጣል ምንም ሞራል አይኖራቸውም። ይኽንን የተሃድሶ አምድ ሳንለቅ ቅ በዚህ ዘመን የሚያየውን የቤተ ክርስቲያን ችግር እንቅረፍ ማለት እንጂ ይኽንን የተሃድሶ ሥራ በማጣጣል የሚጀመር ምንም እንቅስቃሴ ሊኖር አይገባም ብዬ አምናለሁ። ይህንን ያህል ለመግቢያ ካልኩ ወደ ዋናው ሃሳቤ ልግባ። ቤተ ክርስቲያን ሁሌም ለተሃድሶ ክፍትና ዝግጁ መኾን ይኖርባታል። የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችም ቤተ ክርስቲያንን ወደ እግዚአብሔር ቃል፥ ወደ እግዚአብሔር ጸጋ፥ ወደ እግዚአብሔር ክብር፥ ወደ ክርስቶስ ማዕከልነት፥ ወደ ተልዕኮው ትኩረት መጣራት ይኖርባቸዋል። የአዲስ ኪዳኗ ቤተ ክርስቲያን ዕለት ዕለት የምትታደስ ራሷን በቃሉ መርህ መሠረት የምትፈትሽ ድንገት ከሳተችም አቋሟን የምታስተካክል ናት እንጂ በገባችበት የሥነመለኮታዊና መንፈሳዊ ችግሮች ተውጣ የምትቀመጥ አይደለችም። ቤተ ክርስቲያን በየትኛውም ዘመን የሰው ባሕልና ልምድ የሰው ልምምድና ሥርዓት ሳይኾን ቃሉ በበላይነት የሚመራት በመንፈስ ቅዱስ አሠራር የምታምንና ፈቃዱን የምትከተል መኾን ይኖርባታል። ልኬቷ ተበላሽቶ መርከብ ያለ መሪ እንደሚጓዝ በምድር ባሕር ተለቅቃ መጓዝ የለባትም። ተሃድሶ አማኞችን ከከንቱ ኃይማኖታዊ ሥርዓት ይልቅ ከጌታ ጋር ሊኖር ወደሚገባው ግላዊ ግንኙነት የሚመራ፥ ሰዎች በክርስቶስ አማካይነይ የተዘጋጀላቸውን ጽድቅና ክብር ወደመጎናጸፍ እንዲመጡ የሚያደርግ መኾን ይኖርበታል። አማኞች ከእግዚአብሔር በነጻ ላገኙት ለጸጋው ሥጦታ ካላቸው ክብርና ምሥጋና ተነስተው በሙሉ መሰጠት ተቀድሰው እንዲኖሩ የሚያስችል መኾን ይኖርበታል። ተሃድሶ ከአጉል ወግ አጥባቂነትም ሆነ ከልቅ ለዘብተኛ ማንነት የሚያላቅቅ ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት የሚያስገዛ መሆን ይኖርበታል። በነገራችን ላይ እውነተኛ ተሃድሶ ትርጉሙ አጭርና ግልጽ ነው ይኼውም renewal through truth and grace ሊባል ይችላል። ክርስቶስ የምድርን ሁኔታ ለመለወጥ ሲመጣ የተሞላው በነዚህ በሁለቱ ነበር። truth and grace የማይገነጣጠሉ ነገሮች ናቸው።

    Текст
    Просмотры1,31 тыс.
    Пересылки—
    Реакции7
    Комментарии—

Новые посты

#1827Текст

የስም ማጥፋት ነገር እንደ ስም መጥፋት ክስ ስሙ የጠፋ የሚገኝ አይመስለኝም። ክሱ ገንዘብ ያላቸውና ጡንቸኞች የሚገለገሉበት ሆኗል። ከሰሞኑ “ወንጌላውያን ነን” የሚሉ ሰዎች የተቃወሞቸውንና የተቿቸውን ሰዎች በስም ማጥፋት መክሰስን ደጋግመውታል። ለሦሥተኛ ትዳር የሚያኮበኩቡ፣ በመድረክ በጌታ ስም የሚያላግጡት፣ እኩይ ተቋም መፍጠራቸው ሳያንስ በሙስና የተዘፈቁት ሁሉ ስማቸው እንደጠፋ ማሰባቸው ይደንቃል። የሰው አይን በአደባባይ የሚነርቱ፣ አስገድዶ ደፋሪዎች፣ ሰው የሚያግቱና የሚያስደበድቡ ስማቸው መጥፋቱን ማሰባቸው ይገርማል። እውነታው መሆን የነበረበት ከየትኛው መልካም ስም ነው አዲስ ስም የተለጠፈባችሁ የሚል ነበር። ለመሆኑ የትኛው መልካም ስም ነው የጠፋው? ይሄ ሃሰተኛ ነብያት ክርስትና ያነሳው ስም ይሆን? ወይንስ የብልጸግና ወንጌልና የእምነት ቃል ትምህርትን ወንጌላዊ ያደረገው ፀረ ክርስቲያናዊ ስም? ለስራ ቅጥር ገንዘብ ያስከፈለ ስም ጠፍቶ ይሆን? አልያስ ተቋማዊ ምዝበራን አቋም ያደረገው ስም ጠፍቷል? በእምነት ስም ሰዎችን scam ለማስደረግ ተቋማዊ መደላድል የፈጠረው ስም ይሆን የጠፋው? የትኛው መልካም ስም ነው የጠፋው? ቦታ ለከፈላቸው ሁሉ እንዲሰጣቸው ያሳልጣሉ የሚለው ስም ይሆን የጠፋው? ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ የቄሣር ድምጽ ይሰማሉ የሚለው ስም ጠፍቶ ይሆን? አንድ ሰው ለሌላ ሰው ወይም ተቋም ሊረጋገጥ የማይችል ሃሰተኛና ከእውነታ የራቀ ስም ሲሰጥ ስም ጠፋ ይባላል ሲሉ ሕግ አዋቂዎችን ማድመጤን አስታውሳለሁ። እነዚህ ያለስማችን ስም ተቸረን የሚሉት ሁሉም ሰዎችና ተቋማት ቀረብ ብሎ ለተመለከተ በስማቸውና ግብራቸው ተጠሩ እንጂ ያለ ስም ስም አልተቸራቸው። እንደውም በአግባቡ በስማቸው የጠራቸው ስለመኖሩ ያጠራጥራል። ጥቂት ሰዎች በስማችሁ ስለጠሯችሁ እንጂ ስማችሁ እንዲሆን የፈለጋችሁት ሳይሆን በግብራችሁ የገለጣችሁት ነው። ቴዲ ያደረገው በስም መጥራት ነው። መጠራት በምትሹት ሳይሆን ስራችሁ በሚገልጠው ስም። በጎ ስም እንዳላችሁ ብታምኑ ኖሮ ምግባራችሁ በተለየ ነበር። ባለቤቱ እንዳለችው “ታሳሪዎቹ ከሳሾቹ” ናችሁ። እግዚአብሔር ይፍታችሁ። አማኑኤል አሰግድ

Открыть в Telegram
Просмотры209−85%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#1826Текст

የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከተቋቋመ ወዲህ ባሉት ዓመታት በቀያጭነት እና በመንግሥታዊ ቅርርብ/ድጋፍ ጥርጣሬዎች ውስጥ ሲተች ቆይቷል። ቴዎድሮስ ተጫንን የመሳሰሉ በሚዲያ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችም ይህንን ጨምሮ ብዙ ጉዳዮችን ሲተቹ ኖረዋል። ቴዎድሮስ ተጫን በተለይ ከዚህ ጋር በተያያዘ ብዙ ሰዎችን ተችቷል (በትክክለኛም ይሁን በተሳሳተ ምክንያት)። አንዳንዱ ሲነካ ይመልሳል፤ ሌላው በዝምታ ያልፈዋል። በካውንስሉ ባይሆንም ከእኔ ጋርም ተጋጭተን እናውቃለን። እስከማውቀው ግን ክስ እና እስር ድረስ የደረሰ ምላሽ የሰጠ እንዳለ አላውቅም። አብዛኛው ሰው «ያልተግባባነው ወንድም ነው» ብሎ ቢያልፍ እንጂ ስምን ለማስከበር እና ለማፈን እዚህ ድረስ አይደርስም። ቴዲ አሁን ላይ በካውንስሉ ጉዳይ እስር ላይ እንዳለ እየሰማን ነው። ማንም አካል ወይም ተቋም ሕግ አጣቅሶ ስሙን የማስከበር መብት ቢኖረውም፣ የካውንስሉ ጉዳይ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እንደመሆኑ ከመደበኛ ሕግ በላቀ የሞራል ልዕልና እንዲያዝ እጠብቅ ነበር። በክርስቲያናዊ የሥነ ምግባር ልዕልና ቴዎድሮስ ኑፋቄ አላስተማረ፤ አሊያም የሥነ ምግባር ዝንፈት ውስጥ አልተገኘም ( የሚያደርገውንም ለርካሽ ዝና ያደርጋል ብዬ አላስብም)። ይልቁንም ካውንስሉን በእነዚህ ሁለት ወሳኝ ነገሮች መተቸቱ፣ እንደ አንድ የቤተ ክርስቲያን ልጅ በሚችለው ማስረጃ መምጣቱ፣ ለዚህ እስር ሊዳርገው ይገባል? ቤተ ክርስቲያን በሙስና እና ምዝበራ በልጆቿ ስትተች ምላሿ ይህ መሆን አለበት? መቼስ ቃሉ ነው ለሁሉ መለኪያችን፤ የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን የዘር አድልዎ አለ ስትባል ምን አደረገች (ሐዋ. 6፥1-2)? ጴጥሮስ ሲሰብክ 3,000 የሚድነው፣ ጨርቁ ድውያንን የሚፈውሰው፣ መልአክ ከእስር የሚያስፈታው፣ ሙታንን የሚያስነሳው በቆርኔሌዎስ ጉዳይ በተነቀፈ ጊዜ ምን አደረገ (ሐዋ. 11፥2)? በግልጽነት የሆነውን ሁሉ አስረዳ። ጳውሎስም በ2ኛ ቆሮንቶስ 2፥14–7፥4 ያደረገው ያንኑ ነው፤ በትዕግሥት ንጽሕናን ማስረዳት። ንጹሕ ሆኖ ከተገኘ ደግሞ ለተቃዋሚዎች ሸብረክ አለማለት! ጥያቄው ቤተ ክርስቲያን እና መሪዎች የተነቀፉ ሲመስላቸው ቀድመው ወደ ፖሊስ፣ ደኅንነት እና መደበኛ ሕግ ነው መሄድ ያለባቸው? ክስ የቀረበባቸው መንፈሳዊ መሪዎች ንጹሕ ቢሆኑ እንኳን ንጽሕናቸውን በዋነኝነት የሚያረጋግጥላቸው ማን ነው? በቴዎድሮስ በታየው የካውንስሉ ድርጊት የሚለየው፣ ከማንም በላይ በውስጥ ምርመራ ይቋጫል ተብሎ ሲጠበቅ፣ ስሙን እና ሥልጣኑን ለማስጠበቅ እስከ ብረት እና ሰንሰለት ድረስ እንደሚሄድ ማሳየቱ ነው። ለምን? ክሱ ሐሰት መሆኑ ስለተረጋገጠ በቀል መሆኑ ነው? ወይስ ክሱ ማያወላዳ በመሆኑ ማምለጫ ለማድረግ? ምናልባትም ለቴዎድሮስ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም «ለተናገረኝ እንዲህ አደርጋለሁ» የሚል ማስጠንቀቂያ ለማስተላለፍ ይሆን? ካውንስሉ ተቃዋሚውን ሲያሳስር የመጀመሪያው እንዳልሆነ ሰምቻለሁ። በዚህ አጭር ተቋማዊ ዘመኑ የሰዱቃውያንን አካሄድ መከተሉ—ማለትም ከመንግሥት ጋር ተቀራርቦ ስጋትን የማስወገድ ዘዴ መላበሱ—ይታማል። ገና ከአሁኑ ቀና ብለህ የማታየው እና የማትናገረው አካል እየሆነ ነው። ይህ ድርጊት የካውንስሉን አባል አገልግሎቶች ስለ መብት እና ግዴታ እንዲያስቡ የሚያደርግ ነው (በተለይ ቴዎድሮስ አባል ከሆነ)። አባል አገልግሎቶች ግዴታቸውን ካደረጉ፣ መብታቸው እስከምን ድረስ ነው የሚለውን ማሰብ የሚጀምሩበት ወቅት ነው። ካውንስሉ ነገ ጉዳዩን የት ሊወስደው እንደሚችል ስላሳየ፣ የትኛውም ጥያቄ በሕግ አግባብ መደራጀት እንዳለበትም የሚያመላክት ነው። አባል ካልሆነ ደግሞ፣ እንደ ምክር፣ የካውንስሉ አባል ቢሆን የበለጠ የሚጠቅም ይመስለኛል። የመናገር መብቱን በአባልነት አውድ ውስጥ ቢጠይቅ የበለጠ የሚረዳው ይሆናል። ለማለት የፈለኩት ቴዲን ከመተቸት ጋር በማያያዝ ብቻ፣ መታሰሩን የሚጠበቅ አድርጎ ማየት ወይም ከዚያም ባለፈ «አብዝቶት ነበር፤ ይበለው» የሚል ምላሽ የሚያስከትለው አደጋ በጣም የገዘፈ ነው። ከቴዎድሮስ ጋር ድፍረት እና በግልጽ የመናገር ነጻነት አብረው ታስረዋል። ቴዲ እንደ ግለሰብ ነገ ይወጣል። እሱ ሲወጣ በዝምታ የደገፍነው ወይም ያለፍነው አካሄድ፣ ተቋሙ ነገ «ተራው የእናንተ ነው» (You are next) እያለን እንደሆነ ለማስታወስ ነው። አክሊሉ ኩማ

Открыть в Telegram
Просмотры447−68%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
#1824Текст

የዘመናችን ቤተ ክርስቲያን ተሃድሶ ያስፈልጋታል ስል በእውነትና በጸጋው ወደ መሞላት መመለስ ይኖርባታል ማለቴ ነው። ይኽ ደግሞ ሊሆን የሚችለው በአቦሰጥ (randomly) አይደለም። ይኽ እንዲሆን በመጀመሪያ ደረጃ የቤተ ክርስቲያን ትኩረት ወደ ክርስቶስ ማንነትና አገልግሎት ምሳሌነት መመለስ አለበት። ክርስቶስን ምሳሌዋ ያላደረገች ቤተ ክርስቲያን የትም ጥሻ ውስጥ ናት። የሞተላትን እረኛዋን በመተው ሌላ ነገር የምትከተል ቤተ ክርስቲያን ስታለች። ሞቱንና ትንሣኤውን የስብከቷ አንኳር መልዕክት የማታደርግ ቤተ ክርስቲያን የርሱ አይደለችም። ተሃድሶ መንፈሳዊ መነቃቃት እንጂ አዕምሮአዊ ንቃት አይደለም። ለመንፈሳዊ መነቃቃት ደግሞ የሰውን ልብ የሚያዘጋጀው ወይም የሚከፍተው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። የምሁራን ትምህርት፥ የመንፈሳዊያን ልምምድ፥ የታላላቆች ምክር፥ የኃይማኖት መሪዎች ቅንዓት ቤተ ክርስቲያንን ያለ መንፈስ ቅዱስ ሥራ ሊያነቃቃት አይችልም። አሁንም ልድገም ቤተ ክርስቲያንን ወደ ቃሉ ሥልጣን፥ ወደ ክብሩ፥ ሙላት፥ ወደ መንፈሱ አሠራር፥ ወደ ንስሓና ወደ ቅድስና ሕይወት ለመመለስ የሚያስችለው ቅዱሱ የእግዚአብሔር መንፈስ ብቻ ነው። ተሃድሶ ሰዎችን ወደ ሉተራዊነይ፥ ወደ ካልቪንስትነይ፥ ወደ ዌስሊያንነት፥ ወደ ጴንጤቆስጤያዊነት ማዘዋወር አይደለም። ወደ እግዚአብሔር ፍቅር፥ ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አገዛዝ፥ ለጌታ ወደሚኾን ታማኝነት፥ ለቃሉ ወደሚኾን ታዛዥነት ነው። ተሃድሶ ፕሮግራም አይደለም “reformation is not an event” የሚባለው ትክክለኛ መረዳት ነው። yes its not an event. ኮንፈራንስ አይደለም። ዝማሬና የአዳራሽ ውስጥ ጭፈራም አይደለም። ረጅም ጸሎት መቻል አይደለም። አቧራ ማጨስ መድረክ መሙላት አይደለም። የሚዲያ ጋጋታ የደጋፊ ብዛት አይደለም። የወረት ሰሞናዊ ግርግር አይደለም። ተሃድሶ የሕይወት ለውጥ ነው። የአካኼድ የአቅጣጫ ለውጥ ነው። ወደ መለኮታዊ አጀንዳ መመለስ ነው። ወደ እግዚአብሔር ደስታ መመለስ ነው። ቤተ ክርስቲያን በዚህች ምድር ባለችበት ዘመን ሁሉ እንድትሠራው ወደ ተሰጣት የምስዮናዊነት ተልዕኮ ወደ ነቢይነት ሚና መመለስ ነው። ወደ ቀደመው ክብሯ ወደ ነበራት ሥፍራዋ መመለስ ነው። መልካም የተሃድሶ መታሰቢያ ቀን ለፕሮቴስታንት ወንድሞችና እህቶች!! ብዬ ቋጨሁ። ወርቅነህ ዳዊት

Открыть в Telegram
Просмотры2 940+112%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#1823Текст

“Ecclesia semper reformanda est - ቤተ ክርስቲያን ሁሌም መታደስ አለባት (ይኖርባታል)።” በአሥራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተካኸደው የፕሮቴስታንት ተሃድሶ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን የእምነት አቋምና ልምምድ የፈተነ ወይም የፈተሸ ነበር። ጀርመናዊው ሉተር በ1517ዓ.ም ዘጠና አምስት ነጥቦች ያሉትን የተሃድሶ መግለጫ በዊተንበርግ የለጠፈው በዛሬው ቀን October 31 ነበር። ሉተር ቤተ ክርስቲያን የገባችበትን ግብረገባዊ ውድቀት በተለይም የኃጢአት ይቅርታ እንደ ሸቀጥ ለሽያጭ የሚቀርብበትን ሁኔታ በመቃወም ነበር የተሃድሶ ፈር ቀዳጅ በመኾን የተነሳው። ሁኔታው ተመችቶት ወይም እንደሌሎች መነኩሴዎች ዝምታን መርጦ መቀመጥ ቢችልም ይኽንን ማድረግ ምርጫው አልነበረም። በልዩነት አቋሙን ይዞ ወጣ። እንግዲህ ተሃድሶው በኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነቶችና ልምምዶች ላይ የተወሰደ የተቃውሞ እርምጃ ነበር። የአመጽ እርምጃ ሳይኾን የመንፈሳዊ መነቃቃት እርምጃ ነበር። የግብረገብ ውድቀት (Moral decay) በሚኖርበት ጊዜና ሁኔታ ሁል ጊዜም ተሃድሶ ግድ ነው። በዚያ ዘመን አማኙ ማኅበረሰብ ቃሉን ለማግኘትም ኾነ በቃሉ ሕይወቱን ለመምራት ዕድል አልነበረውም (lack of access to scripture ነበር) መጽሐፍ ቅዱስ ከላቲን ውጭ ባልነበረበት በዚያ ሁኔታ ወደ መጽሐፍ ቅዱሳዊው መንፈሳዊነት ትውልዱን ለመመለስ ሉተር ተነሳ። የሚከፈለውን መሥዋዕት ሁሉ የሚጠይቀውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ራሱን አዘጋጅቶ ወደ ሥራው ገባ። ድኅነት በጸጋው በእምነት አማካይነት ብቻ፥ የበላይ ባለ ሥልጣንና መለኮታዊ መገለጥ ቃሉ ብቻ፥ የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና ክብር ለርሱ ብቻ፥ ለሕትወታችን ድኅነት የተሰጠን ሥጦታ መካከለኛው የሕይወታችን ማዕከል ክርስቶስ ብቻ በሚል መንፈሳዊና ሥነ መለኮታዊ ተጽዕኖ ያሳደሩ አቋሞች በዚህ ወቅት ተገልጸው ነበር። በተለይ በጊዜው በተነሡ ሌሎችም አባቶች ታምነው በሂደት ጥርት ያለው የአምስቱ ብቻ አቋም (five solas) ድንቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዘመን ዘለቅ የእምነት አቋም ነበር። ተሃድሶው ያስከተላቸው ሁለንተናዊ ተጽዕኖዎች ሊዘረዘሩ ይገባል። ቤተ ክርስቲያንን ከነበረችበት ሁኔታ ፈቀቅ ሊያደርግ የቻለ ብቻ ሳይሆን አውሮፓን በሁለንተናው የለወጠ ተሃድሶ ነበር። መንፈሳዊና ሥነ መለኮታዊ በረከቶችን ሁሉ አማኝ በእምነት አማካይነት በግሉ መጎናጸፍ እንደሚችል ያመለከተ & የእግዚአብሔርን ጸጋ ያለግዢ በነጻ በእምነት ቀርቦ መቀበል እንደሚችሉ ያሳየ እንቅስቃሴ ነበር። የቤተ ክርስቲያን እረኞች (የቄሳውስት) አገናኝ ጣልቃ ገብነት አማኝ እግዚአብሔርን በግሉ ማወቅና መከተል እንደ ጌታ ማገልገል እንደ አባት ማናገር እንደሚችል መልሶ ያሳሰበ ክርስቶስን ያመነ ሁሉ የንጉሡ ካሕን መኾኑን ያበሰረ ተሃድሶ ነበር። አማኞች የእግዚአብሔርን ቃል በግላቸው የማንበብ፥ የመረዳት፥ ለቃሉ የመታዘዝ መንፈሳዊ አቅም ያላቸው መኾኑን ያስገነዘበ ነበር። ከዚህ ሁሉ ጋር አማኞች የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ አማኞቹ መረዳት በሚችሉት ቋንቋ እንዲኖራቸው እንዲያጠኑና በሕይወታቸው እንዲተረጉሙ ያደረገ ነበር። ድኅነት ሰው በጥረቱ የሚያገኘው ሳይኾን የእግዚአብሔር ነጻ ሥጦታ መኾኑን በማወቅ እምነቱን በጌታ ብቻ እንዲያደርግ ያደረገ ነበር። መንፈሳዊ ጥገኝነትን ያስወገደ አማኞችን በግላቸው የተዘጋጀላቸውን የድኅነት በረከት እንዲያገኙ ያዘጋጀ የእምነት እጃቸውን ዘርግተው እንዲቀበሉ ያደረገ ነበር። በቄሳውስቶችና ካሕናት ዘንድ የነበረው የባለቤትነት ስሜት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከዛሬው በባሰ ነበር። ቤተ ክርስቲያንን እንደ ባለአደራ ሳይኾን እንደባለቤት ቆጥረው ያሻቸውን ያደርጉ ነበር። ይኽንን አስገባሪ ሁኔታ ተሃድሶው ሽሮአል። አንዳንዶች ራሳቸውን በተለየ ሁኔታ ለእግዚአብሔር የቀረበ በማስመሰል ሕዝቡን እንደ ዛሬው ለሸቀጥ አጋልጠው ያስጨንቁ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ በአውሮፓ ትምህርትና ሥልጣኔ እንዲስፋፋ ምክንያት የሆነ እንቅስቃሴ ነበር። የግለሰብ ነጻነትና ሰብዓዊ መብት በተመለከተም ተሃድሶ የራሱን አሻራ ያስቀመጠ ነበር። ነባሩን የሮማውያንን የፖለቲካ ሥልጣን የበላይነት ወደ ፖለቲካዊ ፕሉራሊዝም ወይም ሌሎች አማራጮችን የማየት ያስቻለ ነበር። መንፈሳዊና ግብረገባዊ ብቻ ሳይኾን የኢኮኖሚያዊ አውታርና የፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ሁሉ ዓይን ከፋች እንቅስቃሴ ነበር። ማኅብረሰቡ ከተለያዩ እሥራቶች በመፈታት ወደ ሕሊና ነጻነት እንዲመጣ የበኩሉን ጉልህ ድርሻ የተወጣ ነበር ተሃድሶው። በጊዜው በነበረው ማኅበረሰብ ዘንድ ብቻም ሳይኾን ሁል ጊዜም በየሥፍራው እውነት፥ እምነት፥ የሕሊና ሕግ ሊታደስ የሚገባ መኾኑን በግልጽ ያመለከተ ድንቅ ንቅናቄ ነበር። በርግጥ ተሃድሶው አዲስና መጤ አስተሳሰብ ሳይኾን ቤተ ክርስቲያንን ወደ ቀደመው አዲስ ኪዳናዊው ትምህርትና ልምምድ የመለሰ ነበር። ምሁራን ስለ ተሃድሶ በሰጡት ምስክርነት:- “The Reformation was essentially a revival of New Testament Christianity.” (J.I. Packer) ብለዋል። ይህ አባባል የማያግባባቸው አንዳንድ ዘመነኞች በዚህ ዘመን የተሃድሶ መሪዎችን ተሃድሶአዊ እንቅስቃሴና እርምጃ ሲያጣጥሉ እየሰማን ነው። ይኽ ደግሞ አሳዛኝ ክስተት ነው። እነዚህ ወጣቶች ወደ ጥንታዊው ክርስትና የመመለስን አስፈላጊነት ቢናገሩም ይኽንን ታላቅ ሥራ ግን የማጣጣል ምንም ሞራል አይኖራቸውም። ይኽንን የተሃድሶ አምድ ሳንለቅ ቅ በዚህ ዘመን የሚያየውን የቤተ ክርስቲያን ችግር እንቅረፍ ማለት እንጂ ይኽንን የተሃድሶ ሥራ በማጣጣል የሚጀመር ምንም እንቅስቃሴ ሊኖር አይገባም ብዬ አምናለሁ። ይህንን ያህል ለመግቢያ ካልኩ ወደ ዋናው ሃሳቤ ልግባ። ቤተ ክርስቲያን ሁሌም ለተሃድሶ ክፍትና ዝግጁ መኾን ይኖርባታል። የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችም ቤተ ክርስቲያንን ወደ እግዚአብሔር ቃል፥ ወደ እግዚአብሔር ጸጋ፥ ወደ እግዚአብሔር ክብር፥ ወደ ክርስቶስ ማዕከልነት፥ ወደ ተልዕኮው ትኩረት መጣራት ይኖርባቸዋል። የአዲስ ኪዳኗ ቤተ ክርስቲያን ዕለት ዕለት የምትታደስ ራሷን በቃሉ መርህ መሠረት የምትፈትሽ ድንገት ከሳተችም አቋሟን የምታስተካክል ናት እንጂ በገባችበት የሥነመለኮታዊና መንፈሳዊ ችግሮች ተውጣ የምትቀመጥ አይደለችም። ቤተ ክርስቲያን በየትኛውም ዘመን የሰው ባሕልና ልምድ የሰው ልምምድና ሥርዓት ሳይኾን ቃሉ በበላይነት የሚመራት በመንፈስ ቅዱስ አሠራር የምታምንና ፈቃዱን የምትከተል መኾን ይኖርባታል። ልኬቷ ተበላሽቶ መርከብ ያለ መሪ እንደሚጓዝ በምድር ባሕር ተለቅቃ መጓዝ የለባትም። ተሃድሶ አማኞችን ከከንቱ ኃይማኖታዊ ሥርዓት ይልቅ ከጌታ ጋር ሊኖር ወደሚገባው ግላዊ ግንኙነት የሚመራ፥ ሰዎች በክርስቶስ አማካይነይ የተዘጋጀላቸውን ጽድቅና ክብር ወደመጎናጸፍ እንዲመጡ የሚያደርግ መኾን ይኖርበታል። አማኞች ከእግዚአብሔር በነጻ ላገኙት ለጸጋው ሥጦታ ካላቸው ክብርና ምሥጋና ተነስተው በሙሉ መሰጠት ተቀድሰው እንዲኖሩ የሚያስችል መኾን ይኖርበታል። ተሃድሶ ከአጉል ወግ አጥባቂነትም ሆነ ከልቅ ለዘብተኛ ማንነት የሚያላቅቅ ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት የሚያስገዛ መሆን ይኖርበታል። በነገራችን ላይ እውነተኛ ተሃድሶ ትርጉሙ አጭርና ግልጽ ነው ይኼውም renewal through truth and grace ሊባል ይችላል። ክርስቶስ የምድርን ሁኔታ ለመለወጥ ሲመጣ የተሞላው በነዚህ በሁለቱ ነበር። truth and grace የማይገነጣጠሉ ነገሮች ናቸው።

Открыть в Telegram
Просмотры1 310−6%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
#1821Текст

የዛሬ 509 ዓመት፣ በዛሬዋ ዕለት፣ በኦክቶበር 31፣ 1517 አመተ እግዚ አንድ ብዙም የማይታወቅ የአውገስጢኖስ ገዳም መነኩሴ፣ በአንዲት ትንሽ የጀርመን ዩኒቨርስቲ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ፕሮፌሰር የነበረ ሰው በዩኒቨርስቲው ቅጥር ውስጥ በሚገኘው የቤተ ክርስትያን በሮች ላይ የተወሰኑ ወረቀቶችን ለመለጠፍ መዶሻ አነሳ። እነዚያን ወረቀቶች በቤተ ክርስትያን አደባባይ ላይ የለጠፈበት ምክንያት የቤተ ክርስትያኑ አደባባዩ ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ እንደ ማስታወቅያ ሰሌዳ ያገለግል ስለነበር በርከት ያለ ሰው እንዲመለከተውና ውይይት እንዲያጭር አስቦ ነበር። በለጠፈው ወረቀት ውስጥ 95 አናቅጽት በዋናነት የሰውን ድኅነት እንደ ቁስ መገዛቱን በማውገዝ ነበር። ሰው ከፑርጋቶሪ ይወጣ ዘንድ የኅጢአት ይቅርታ ሰነድ በመኸከለኛ ዘመኗ ካቶሊክ ለጉድ ይቸበቸብ ነበር። ይህ ሰነድ ወይም 'ኢንደንጀልስ' በወረቀት የሰፈረና የቤተ ክርስትያንን ይሁንታ አግኝቶ መግዛት ለቻለ ሁሉ የቀረበ ነበር። ህዝቡም ኢንደልጀንሱን ይገዛ ዘንድ 'በቅቤ አቅልጥ' ደላላ አሻሻጮች ይጎተጎት ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ይሁንታዋን ሰጥታ ነበር። ህዝቡ ለራሱ፣ ለዘመዱና ለወዳጁ ይገዛ ነበር፤ በሞቱት ስም እንኳን ሳይቀር ይቸረቸራል። ሉተር 95 አናቅጽቱን ጽፎ ሲለጥፋቸው ዩኒቨርስቲ ውስጥ ባሉት ፕሮፌሰሮች መሃል ውይይት እንዲፈጥር በማሰብ ነበር። ነገር ግን ዘጠና አምስቱ አናቅጽት ከቪተንበርግ ማኅበረሰብ በዘለለ በመላው የጀርመን ግዛቶችና በጠቅላላው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ዘንድ ታላቅ ሁካታን ለመፍጠር በቃ። በአጭር ጊዜ ውስጥም ብዙ ህዝብ የዚህን መነኩሴ ስም ማወቅ ጀመረ፣ በቪተንበርግ ዩኒቨርስቲ የሥነ መለኮት ዶክተሩን ማርቲን ሉተርን። ህዝብን በማወክና ባለመታዘዝ ቤተክርስትያን ከሰሰቸው፣ በጀርመን ንጉስ ፊትም ራሱን እንዲከላከልና ያደረገው ሃሰት መሆኑን አውቆ እንዲያስወግድ ታዘዘ። ያደረገው ስህተት መሆኑን ባለመቀበሉና ህሊናው ለቅዱሳት መጽሐፍት ተገዢነታቸውን በማጽናቱ ምክንያት የውጤቱን ስሜት 500 አመታትን ተሻግሮ ዛሬ እኛም ይሰማናል። . «ስቻለሁ የምለው አንዳች ነገር የለኝም፤ ኅሊናዬ ከሚያዘኝ ውጪ መሆን ትክክልም ሆነ አግባብ አይደለም። እነሆ፤ እዚሁ ቆሜያለሁ፤ ከዚህ ውጪ ምንም ላደርግም አይቻለኝም። እግዚአብሔር ሆይ እርዳኝ። አሜን።» . ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ እንዳሉት፣ "አሕይዎና ተሐድሶ (Revival and Renewal or Reformation) ተደላድሎና ተመቻችቶ በተቀመጠ ሥርዐት (Establishement) ውስጥ የዛገና የሚራገፍ ነገር የሚያይ የአእምሮ ችሎታና የተፈጥሮ ተሰጥዎ ካላቸው ታላላቅ ሰዎች ዘንድ የሚመጡ ሐሳቦች ናቸው።" በዚህ ሰው ለመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት በታማኝነት መታዘዝና መሰጠት ምክንያት የቤተክርስቲያን መልክ እንደ ቀደሞው ላይሆን ተለውጧል። . ተሐድሶ ብቻ መቆምን ይጠይቃል። ዘመንን መረዳትን፣ መጽሐፍትን መመርመርን፣ ለእግዚአብሔርና ለህሊናችን ታማኝ መሆንን ይጠይቃል። ተሐድሶ ወደ አባቶችና አያቶች ለመንፀሪያ መመልከትን አንደ ቄንጥ አያይም። የድነትን መኸከለኛ፣ የእምነትን ፈፃሚ፣ የእግዚአብሔርን መገለጥ፣ ትምሕርተ ክርስቶስን አደብዛዥን ሁሉ ለመቃወም ሁለቴ አያስብም። ተሐድሶ ቃለ–እግዚአብሔር ማሕደረ–ክርስቶስ በተባለችው ቤተክርስቲያን ሲደፈጠጥ ጥሪውን በማማ ላይ ያሰማል፤ እነሆኝ ለህሊናዬም ለቃሉም ቆሜያለሁ ይላል። እግዚአብሔር ልጁን በገለጠበት ቃል በኩል ለኅሊናዬ ብቻዬን እንኳን ቢሆን እቆማለሁ የሚል እውነትና ፅናት ያድለን። . የዛሬ 509 ዓመት የተለኮሰውን የተሐድሶውን እሳት ነገ በቅዱስ ማቴዎስ አንግሊካን ቤተክርስቲያን ከቀኑ 9:00 ጀምሮ እናስበዋለን! ወደ ተተሓድሶው እሳቤዎች መመለስ ከእምነት ድንጋጌ እና ከእምነት መግለጫዎች ስልጣን ሥፍራ አንጻር እንቃኛለን። መልካም ዕለተ ተሐድሶ ማስታወሻ! አማኑኤል አሰግድ

Открыть в Telegram
Просмотры2 270+63%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
#1818Фото
Просмотры2 140+54%к среднему
Пересылки—
Реакции30
Комментарии—
#1817Фото

የ16ኛው ክፍለ ዘመን ተሓድሶ አዲስ ሃይማኖት አዋላጅ አልነበረም። የቀደመውን መንገድ ወደ ኋላ አሽቀንጥሮ በተለየ ጎዳና ላይ ክርስትናን የወሰደም ተደርጎ አይቆጠርም። ይልቁንም ተሓድሶው ተመላሽ ነበር። ወደ ሐዋርያዊቷ ቤተክርስቲያንና እምነት፣ ወደ አባቶች አስተምህሮና አቋም ተመላሽ ነው። የእምነት ድንጋጌዎችንም ሆነ የእምነት መግለጫዎችን የተቀዱት ከቅዱሳት መጽሐፍት ምስክርነት መሆኑን እያጸና ወደ ኋላ ይመለሳል። እውነተኛ ተሓድሶ ወደ ኋላ በመመለስ እውነተኛውንና የቀናውን መንገድ ለመያዝ ይጥራል። ቤተክርስቲያን አንድም በሰብዐዊ ድካም ወይም በዘመን ብዛት በሚከሰት ብዥታ አልያም በቸልታ ለእውነተኛው መንገድ ማደር ሲያቅታት እግዚአብሔር በተሓድሶ ንፋስ እያጸዳ በቃሉ ብርሃን ያጸዳታል። የሆነውም ይህ ነው። የፊታችን እሁድ ከቀኑ 9:00 ላይ በቅዱስ ማቴዎስ አንጌሊካን ቤተክርስቲያን ብቅ ብትሉ ተሓድሶውን እያወሳን ስለ እምነት ድንጋጌዎች፣ ስለ እምነት መግለጫዎች እንዲሁም ተዋስኦዊ ሥልጣን በተሓድሶው እንዴት እንደነበር እናያለን። ወደ ተሓድሶው መመለስ አለብን ብለን እንጮኸለን። ከቻላችሁ ተገኙ!

Открыть в Telegram
Просмотры1 820+31%к среднему
Пересылки—
Реакции12
Комментарии—

Все посты

Связи