ሴትና ብልሃት **** ሚስቱን ጂን ይዟታል ተባለና ሊያስቀራባት የሆነ ሸይኽ ዘንድ ይዟት ሄደ፡፡ ሸይኹ ጥቂት እንደቀሩባት ጂኑ መናገር ጀመረ፡፡ “ለመውጣት ዝግጁ ነኝ ግን መስፈርት አለኝ፡፡” አላቸው፡፡ ሸይኹ ጂኑን ታገሉት “ያለ አንዳች መስፈርት በግድህ ትወጣታለህ!” አሉት፡፡ ጂኑ ግን እንቢ አለ፡፡ በመጨረሻም ሸይኹ “እሺ መስፈርትህ ምንድነው?” ብለው ጠየቁት፡፡ “ከዚህ ከወጣሁ ቀጥታ ወደባሏ እንድገባ ይፈቀድኝ፡፡” አላቸው፡፡ ቀድሞዉኑ ሲፈራ ወደ ሩቃው ቤት የሄደው ባሏ ተሸበረ፣ ተንቀጠቀጠ፡፡ ሸይኹም “በፍፁም አይሆንም፣ አይደረግም፡፡ ወደርሱ የመግባት መብት የለህም፡፡” አሉት፡፡ ግና ትንሽ ካሰላሰሉ በኋላ ቆይተው ለምን ወደባሏ መግባት እንደፈለገ ጠየቁት፡፡ ጂኑም መለሰ “እሱ የኛ ተመሳሳይ ነው አይሰግድም፡፡ ማረፊያችንና መናኸሪያችን መሆን አለበት” አላቸው፡፡ ሸይኹም ወደ ሰውዬው ዞረው ጠየቁት፤ “አትሰግድም እንዴ!” በማለት ጠየቁት፡፡ “ አረ እሰግዳለሁ፡፡” አላቸው እየተደናበረ፡፡ ሸይኹ ከጂኑ ጋር ተደራደሩ፡፡ እንዲህ አሉት- “በል አሁን ከሷ ዉጣ፡፡ ነገርግን እሱን ግን እዚያው ቤታቸው አካባቢ ሆነህ ተከታተል፡፡ በርግጥ የማይሰግድ ከሆን እንድትገባበት ፈቅጄልሃለሁ፡፡” አሉት፡፡ ጂኑም በሀሳቡ ተስማማና ለቀቃት፡፡ ቀናት አለፉ፡፡ ሴትዮዋ ለሸይኹ ደዉላ ባደረጉት መልካም ነገር አመሰገነቻቸው፡፡ “አሁን ቀጥብሎ እየሰገደ ነው፡፡ እንዲያዉም የመስጂድ በር ከፋች ሆኗል፡፡” አለቻቸው፡፡ ሸይኹም “ አይ ሰው አላህን ሳይፈራ ጂንን ይፈራ!” አሉና ፈገግ አሉ፡፡ እርግጥ ነው ሴትዮዋ ምንም ጂን አልነበረባትም፡፡ ባሏ አልሰግድ ብሎ ቢያስቸግራት ከሸይኹ ጋር ተመካክራ ነው ይህን ያደረገችው፡፡ ሴት ልጅ መላ አታጣም ይባል የለ፡፡ በዚህ መልኩ ባሏ እውነተኛ የአላህ ባርያ ሆኖ ኖረላት፡፡ @heppymuslim29
Открыть в Telegram
HAppy Mûslimah
አጫጭር ኢስላማዊ ታሪኮች ብቻ ONLY SHORT ISLAMIC STORY‼️ Fôr Any Cømments👉 @NihalllAb
Новые посты
ባለቤቴ ሲበዛ እብድ ናት(እኔ ጋር ብቻ)። በዚህ እብደቷ የተነሳ በቀን ውስጥ የሆነ ነገር ሳታጠፋ አታልፍም። ልክ የሆነ ነገር ስታጠፋ አጠገቤ መጥታ ትቀመጥና ልክ እንደ ህፃን ልጅ በነዛ ውብ እና ቅልልቅ ዐይኖቿ ቁልጭ ቁልጭ እያለች ታየኛለች። እኔም ይሄ ድርጊቷ ምንን እንደሚያመላክት ስለማወቅ፦ "በይ ቶሎ ምን እንዳጠፋሽ ተናገሪ ?" እላታለሁ። እርሷም እንደለመደቺው የታቺኛውን ከንፈሯን ጣል በማድረግ፦"እንዴዴዴዴ አባቴ የምር ምንም አላጠፋሁም" ትላለች (እንደዚህ ስታደርግ ግን ልቤን ቅልጥ አርጋው ከሙታኖች ጋር ትቀላቅለኛለች)። እኔም፦ "ሆሆሆሆ ቶሎ ተናገሪ ብዬሻለው" እላታለው እንደምንም ሰቄን ተቆጣጥሬ። እርሷም፦ "እኔ ምንም አላረኩም እራስህ ነህ ድመት እንደማልወድ እያወቅ ይዛሀት የመጣሀው" ትላለች ጥፋቷን ወደ እኔና ወደ ድመቴ እያላከከኝ አለች። እኔም፦ "ፎዙ (የድመቴ ስም ነው) ደሞ ምን አደረገችሽ?" አልኳት። እርሷም፦ "እቃ አጥቤ እንደጨረስኩኝ ይዤው ልደረድረው ስሄድ ፎዙ መጥታ እግሬን ስትተሻሸኝ ደንግጬ እቃዎቹን እንዳለ ወረወረኳቸው ከዛም ተሰበሩ" አለቺ። እኔም፦ አውቄ እንደ ተናደደ ሰው ዝም አልኳት(ዝም ስል አቶድም)። እርሷም፦ "እህህህህ ለምንድነው ዝም የምትለው እንደዚህ ዝም ስትለኝ እንደማልወድ ታቅ የለ እንዴ" ትላለች። እኔም፦ ዝምታዬ እጸናለው። እርሷም፦ "አባቴ ባአላህ በቃ እሺ ይቅርታ እንዴዴ" ብላ ጉንጭዋን ትነፋቸዋለች። እኔም፦ ከዚህ በላይ ስለማልችል ዘልዬ አቅፋታለሁ ። @heppymuslim29
Открыть в Telegramከ ዝሙት አፅዱኝ… ~ • ማዒዝ ኢብኑ ማሊክ የሰው ልጅ ነውና ተሳሳተ፤ ሸይጧን አሸነፈውና ዝሙት ላይ ወደቀ። ወንጀሉን ማንም አላየበትም፤ ሌሊቱ ሰወረው፣ አላህም ነውሩን ሸፈነለት። ነገር ግን የማዒዝ ህሊና ሰላም ሊሰጠው አልቻለም። ምድሪቱ በሰፊው ጠበበችው። «እንዴት አላህን በዚህ ወንጀል እገናኘዋለሁ?» የሚለው ሀሳብ እንቅልፍ ነሳው። የማዒዝ ነፍስ መዳንን ፈለገች። ዱኒያ ላይ ተቀጥቶ አሊያም ነፅቶ ወደ አኼራ መሄድን መረጠ። እግሮቹ ወደ ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) መስጂድ እየመሩት፣ ልቡ ግን በፍርሃት እና በተስፋ መሃል ትናወጥ ነበር። ማዒዝ ወደ ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) ገባ። ከፊታቸው ቆመ። የውስጡን እሳት ለማብረድ እንዲህ ሲል ተማፀነ፡- «يَا رَسُولَ اللَّهِ طَهِّرْنِي» «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አፅዱኝ(ከ ወንጀል)» አላቸው። የእዝነቱ ነብይ ግን ማዒዝን ማጣት አልፈለጉም ነበር። ፊታቸውን አዞሩበት። አልሰሙ እንደሆነ በማስመሰል ወደ ቀኝ ፊታቸውን መለሱ። ማዒዝ ግን አልተወም። አሁንም በዚያ በኩል ሄዶ ደገመው። ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) አሁንም ፊታቸውን አዞሩ። እንዲህም አሉት፡- «وَيْحَكَ! ارْجِعْ فَاسْتَغْفِرِ اللَّهَ وَتُبْ إِلَيْهِ» «ወዮልህ! ተመለስ (ሂድ)፤ አላህን ምህረት ጠይቅ፣ ወደርሱም ተመለስ።» አሉት። ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) በሩን ከፈቱለት። በራሱና በፈጣሪው መሃል ይሁን፣ ተውበት ያድርግና ይተወው በሚል ስሜት አሰናበቱት። ማዒዝ ግን ወንጀሉ ውስጡን እየበላው ነው። ዝም ብሎ መሄድ አልቻለም። ለሶስተኛና ለአራተኛ ጊዜ ተመላለሰ። «ዝሙት ፈፅሚያለሁ »እያለ መሰከረ። ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) ማጣራት ነበረባቸው። እንዲህ ብለው ጠየቁ፡- «أَبِهِ جُنُونٌ؟» «እብደት አለበት እንዴ?» ሰዎችም «አይደለም ጤነኛ ነው» አሉ። አሁንም ጠየቁ፡- «أَشَرِبَ خَمْرًا؟» «ኸምር ጠጥቶ (ሰክሮ) ይሆን?» አንድ ሰዉ ተነስቶ አፉን አሸተተው፤ ምንም አልጠጣም። ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) ግልፅ በሆነ የአረብኛ ቃል ወንጀሉን መፈፀሙን አረጋገጡ። ማዒዝም ምንም ሳይሸሽግ «አዎ!»አለ። ማዒዝ ራሱ በጠየቀው መሰረት ፍርዱ ተወሰነ። ወደ ቅጣት ቦታው ተወሰደ። ድንጋይ ሲወረወርበት ህመሙ ሲሰማው እንደማምለጥ አለ። ሆኖም የዱኒያው ቅጣት ተፈፀመና ማዒዝ ወደ አላህ ሄደ። ይህ ክስተት በሰዎች መካከል መነጋገሪያ ሆነ። አንዳንዶች በልበ ሙሉነት ስለ ማዒዝ ተውበት ሲያወሩ፣ ሁለት ሰዎች ግን በመሃከላቸው እንዲህ ተባባሉ፡-«ይህንን ሰው አያችሁት አይደል? አላህ ነውሩን ሸፍኖለት ነበር፤ እሱ ግን እንደ ውሻ በድንጋይ ተወግሮ እስኪገደል ድረስ ነፍሱን ከመወንጀል አልተወገደም።» አሉ። ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) የነዚያን ሰዎች ንግግር ሰሙ። ዝም ብለው ጉዞአቸውን ቀጠሉ። መንገድ ላይ የሞተ አህያ (በክት) ተጥሎ አዩ። ያኔ እነዚያን ሰዎች ጠሩና እንዲህ አሉ፡- «كُلَا مِنْ جِيفَةِ هَذَا الْحِمَارِ» «ከዚህ የአህያ በክት ብሉ!» ሰዎቹ ደነገጡ። «አንቱ የአላህ ነብይ ሆይ! ይህን ማን ይበላል?» አሉ። ነብዩም ልብን የሚሰብር ምላሽ ሰጡ፡- «ቅድም በወንድማችሁ ክብር ላይ የሰነዘራችሁት ቃል ከዚህ በክት ከመብላት ይበልጥ የከፋ (የቆሸሸ) ነው።» አሏቸው። ከዚያም ስለ ማዒዝ ታላቅ ተውበት ሲናገሩ እንዲህ አሉ፡- «لَقَدْ تَابَ تَوْبَةً لَوْ قُسِّمَتْ بَيْنَ سَبْعِينَ مِنْ أَهْلِ الْمَدِينَةِ لَوَسِعَتْهُمْ» «በ እርግጥም ለመዲና ነዋሪዎች ለ70 ሰዎች ቢከፋፈል ለሁሉም ይበቃቸው ነበር።» ብለው መሰከሩለት። @heppymuslim29
Открыть в Telegramበአውስትራሊያ የሚኖር አንድ አዛውንት በሰላም ተኝተው ሳለ፣ የኢድ አል-ፊጥር የተክቢራ ድምፅ ከእንቅልፋቸው ይቀሰቅሳቸዋል። አዛውንቱ በድምፁ ተረብሸውና ተበሳጭተው፣ ድምፁን እንዲያጠፉ ቅሬታቸውን ለማቅረብ ወደ መስጂዱ አመሩ። ▪️መስጂዱ እንደደረሱ ግን ያልጠበቁት ነገር ገጠማቸው። የመስጂዱ ኢማምና የጀመዓው አባላት በታላቅ አክብሮትና ትህትና ተቀበሏቸው። እንዲህም አሏቸው፦ "ስላስቸገርንዎት በጣም ይቅርታ እንጠይቃለን፤ ከዚህ በኋላ እንዲህ ዓይነት ችግር እንዳይደገም ቃል እንገባልዎታለን።" አዛውንቱ በዚህ መልካም አቀባበልና ትህትና ልባቸው ተነካ። ወዲያውኑ ስለ እምነቱ የበለጠ ለማወቅ ፈልገው ከኢማሙ ጋር ለመቀመጥ ጠየቁ። ኢማሙም ስለ እስልምና ምንነት፣ ስለ መቻቻል፣ በሁሉም ነቢያት ስለማመንና ወደፊት ስለሚከሰቱ ነገሮች አስቀድሞ ስለሚተነብየው የቁርዓን ተአምራት በሰፊው አስረዷቸው። ሽማግሌው በሰሙት ነገር እጅግ ተደንቀው እያለቀሱ እንዲህ አሉ። "እኔ አሁን የ85 ዓመት አዛውንት ነኝ፤ ወደ እስልምና ለመግባት ዕድሉ ያለኝ አይመስለኝም። *ኢማሙም ሲመልሱ፦ "ወደ እስልምና ለመግባት የቀረዎት አንድ ሰከንድ ቢሆን እንኳ፣ አላህ መሐሪና አዛኝ ስለሆነ ወንጀልዎን ይምርልዎታል።" አሏቸው። በመጨረሻም መጀመሪያ ቅሬታ ለማቅረብ የመጡት አዛውንት፣ በመልካም ስነ-ምግባር ተማርከው የእስልምናን እምነት ተቀበሉ። ሱብሃን አላህ!! ▪️ከአረብኛ ፅሁፍ የተወሰደ @heppymuslim29
Открыть в Telegramኸውለት ቢንት አል-አዝወር **** ኻሊድ ኢብን ወሊድ (ረ.ዐ) በአንድ ወቅት ከሮማውያን ጋር በተደረገው ውጊያ የሙስሊሞችን ሰልፍ በማስተካከል ላይ ሳለ አንድ ሙሉ ሰውነቱን እና ፊቱን በአረንጓዴ ጨርቅ የተሸፈነ ተዋጊ ከሰልፉ ፊት ለፊት ተመለከተ፡፡ የሙስሊሞችንም ሰልፍ እየመራ የሮማውያኑን ጦር ከፍተኛ ጉዳት ያደርስበት ጀመር፡፡ ከሙስሊሞች ጦር ውስጥም የተሸፋፈነውን ሰው የሚያውቀው አንድም ሰው አልተገኝም፡፡ በውጊያው መሃልም ከሙጃሂድ ወንድሞቹ አይን ተሰወረ፡፡ ውጊያው ሲቀዘቅዝም ከሮማውያኑ መሃል በደም የተነከረ ሰይፉን ይዞ ወጣ፡፡ ራፊዕ ኢብን ኡመይራ (ረ.ዐ) በወቅቱ ከሙስሊሞች ጦር ጋር ነበር፡፡ ክስተቱንም እንዲህ ሲል ይተርካል፡- “በውጊያ ውስጥ እያለን የተሸፋፈነውን ሰው ጀብዱ ስንመለከት የጦር መሪያችን ኻሊድ ኢብን ወሊድ (ረ.ዐ) ፊቱን ሽፍኖ ገብቶ ይሆናል ብለን ገምተን ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ጀግና ጦርነቱ ሲቀዘቅዝ ከሮማውያን መሀል ሲወጣ ከቀኙ በኩል ኻሊድ ኢብን ወሊድን (ረ.ዐ) ተመለከትነው፡፡ ለኻሊድም (ረ.ዐ) “ይህ ከፊት ለፊትህ ሆኖ አስገራሚ የጀግና ውጊያ የሚዋጋው ሰው ማን ነው?” ብለን ጠየቅነው ኻሊድም (ረ.ዐ) “እኔም እንደናንተ ላውቀው አልቻልኩም” አለን፡፡ ውጊያውም እንደ አዲስ ሊጀመር ነው፡፡ ኻሊድም “የሙስሊም ጦር ሆይ! በጀግንነት ተዋጉ፣ ከእምነታቹሁም ላይ የጠላትን ወረራ ተከላከሉ” በማለት ሙስሊሞችን አበረታታ፡፡ የተሸፋፈነውም ሙጃሂድ ጦሩን ከፊት ለፊት ሆኖ መምራቱን እንደቀጠለ ነው፡፡ ውጊያውም ከተጀመረ በኋላ ወደ ጠላት ስብስብ ገስግሶ ስለሚገባ ሙጃሂድ ወንድሞቹ ከሰልፋቸው ውስጥ አይመለከቱትም ነበር፡፡ ጦርነቱም ሲጠናቀቅ ልብሶቹ በደም የተነከሩ ሆነው ወደ ሙስሊሞች ካምፕ መጣ፡፡ ኻሊድ እና ሙጃሂዶቹም “ለአላህ ስትል ፊትህን ግለጥና አሳየን” ብለው ተናዘዙት፡፡ እርሱ ግን ለንግግራቸው ቦታ ሳይሰጥ ጅርባውን ሰጥቷቸው ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ከሰውዬው የሚታየው ሁኔታ ጉዳዩ አላህ ዘንድ ብቻ እንዲታወቅለት የፈለገ ይመስላል፡፡ ሙስሊም ተዋጊዎችም “አንተ የተሸፋፈንክ ሰው ሆይ! የጦር መሪህ እያዘዘህ ነው ፊትህን አሳየን” እያሉ ከየአቅጣጫ መጮህ ጀመሩ፡፡ ኻሊድም የሰውዬውን እምቢተኝነት በተመለከተ ጊዜ ከፊት ለፊት ቀደመው፡፡ “ወዮልህ! በተግባርህ የሰዎችን ትኩረት ሳብክ” በማለትም ደጋግሞ ጠየቀው፡፡ ጀግናው ሙጃሂድም የጥያቄው መደጋጋም ሲበዛበት “እስካሁን መልስ ያልሰጠሁህ ከአንተ ፊት ድምፄን ለማውጣት ሐያእ (ሀፍረት) ይዞኝ ነው፡፡ እኔም የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ፊታችንን ላልተፈቀደልን ወንዶች እንዳናሳይ ካስተማሩን የሙስሊም ሴቶች ውስጥ አንዷ ነኝ” ስትል በእንስታዊ ድምፅ መለሰችለት፡፡ ኻሊድም በጉዳዩ ተደንቆ “እሺ አላህ ይባርክሽና ስምሽን ንገሪን” ሲል ጠየቃት፡፡ “ኸውለት ቢንት አዝወር ነኝ” ብላ መንገዷን ቀጠለች፡፡ @heppymuslim29
Открыть в Telegramሸይኹ በሚያስተምርበት መስጂድ ውስጥ ሰዎች የሚሰጡትን ክብር እንድትመለከት ሚስቱን አስከትሎ ሄደ። በምላሷ ትወጋው ስለነበር አዛዋን ለማስቆም መሆኑ ነው።….. መስጂድ ውስጥ ሚንበር ላይ ቆሞ ሲያስተምር ዋለ። እቤት ሲመለሱ ሃሳቧን ጠየቃት። «ሁሉም ሰው ዝም ብሎ በዒባዳ ተመስጦ ነበር። አንተ ብቻ ስትለፈልፍና ስትንቀለቀል ነበር።ሰዎች በተዋዱዕ መሬት ላይ ሲቀመጡ ጉረኛው አንተ ግን ከፍታ ቦታ ላይ ራስህን ቆልለህ ቆመሀል!»…ልክ ልኩን ነገረችዋ¡ @heppymuslim29
Открыть в Telegram‹‹መሞትህ ነው›› አሉት ገጠሬውን። ‹‹ከዝያ የት ነኝ?›› ብሎ ጠየቀ። ‹‹እጌታህ ዘንድ›› ቢሉት... ‹‹ታድያ መልካም ሁላ ተሱ ዘንዳ ይገኝ የለ! ምን አስፈራኝ!›› #ተስፋ ‹‹ዱዓው ተቀባይ የሆነን ሰው ታውቃለህ›› ብለው ጠየቁት። ‹‹አላውቅም፤ ግና ዱዓን የሚቀበል ጌታ አውቃለሁ›› አላቸው። #እምነት ሰሓቢዩ ዘንዳ አንዱ መጥቶ ጠየቀ፦‹‹ቂያም ቀን ማን ነው ሞጋቻችን?›› ‹‹አላህ›› ሰሐቢዩ መለሰ። ‹‹እንግዲህ ድነናላ!›› ብሎት ሄደ። #ጥልቅ_ተስፋ ወጣቱ ሞት አፋፍ ላይ ሁኖ ሲያጣጥር እናት ታለቅሳለች፦‹‹እማ! የቂያም ለት ሂሳብ ተሳሳቢዬ አንች ብትሆኚስ፤ ምን ታደርጊኛለሽ? ›› ጠየቃት። ‹‹ስለማዝንልህ ይቅር እልሀለው !›› ‹‹ካንቺ በላይ ወደሚያዝንልኝ ጌታ እየሄድኩ ነው'ና አታልቅሺ›› #ፍቅር @heppymuslim29
Открыть в Telegramከኢሻ ሶላት ቡሀላ ወደ ቤቱ ተመለሰ ልጆቹም ተኝተው አየ፣ ለሚስቱም ልጆቹ ሰግደዋል? እንዴ ብሎ ጠየቃት እሷም፦ምግብ ስላልነበረ አባብዬቸው ተኙ አልሰገዱም እሱም፦ ቀስቅሻቸው አላት እሷም፦ የእገሌ አባት ሆይ …!!ከቀሰቀስኳቸው ከረሀብ የተነሳ ያለቅሳሉ የሚበላ ደሞ የለም! አለቺው እሱም፦ አድምጪኝ: ከኔ የሚጠበቀው እንዲሰግዱ ማዘዝ ነው…እርዚቃቸው ከኔ አይደለም ፣ቀስቅሻቸው እርዚቃቸው ከአላህ ነው ! አላህም እንዲህ ይላል (ቤተሰቦችህንም በስግደት እዘዝ ፣በእሷም ላይ ዘውትር ፅና ፣ሲሳይን አንጠይቅህም ፣እኛ እንሰጥሀለን ፣ መልካሚቱ መጨረሻ ለጥንቅቆቹ ናት ) እናቲቱም እጅ ሰጠችና ቀሰቀሰቻቸው ሰግደው እንደጨረሱም የቤታቸው በር ተንኳኳ ፣ ከዛም ሲከፍቱት ከከተማው አንድ ከበርቴ ከማእዱ ጣፋጭ ከሆነው ግማሹን ይዞ ቆሞ ነበር ፣ ሰውየውም ፦ ውሰድ ላንተ እና ለቤተሰቦችህ ነው አለው እሱም ፦እንዴት ሲለው ሰውየውም፦«አንድ ባለ ስልጣን እንግዳዬ ነበር ማእዱን ከመመገባችን በፊት ተጣላን እና ምግቡን ላይበላ ምሎ ሄደ » ምግቡንም ይዜ እንዲህ አልኩ "እግሬ ለቆመበት ሰው እሰጣለሁ ,በአላህ እምላለሁ አንተ ደጃፍ ስር እንጂ እግሬ አልቆመም ነበር ! በአላህ ይሁንብኝ ምን ወደዚህ ይዞኝ እንደመጣ አላውቅም "አለው !! 《 ጌታዬ ሆይ ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ ፣ከዘሮቼም አድርግ! ጌታችን ሆይ ፀሎቴንም ተቀበለኝ፤ 》 @heppymuslim29
Открыть в Telegramተራዊሕ አምሽተን ስንገባና ደክመን ስንወድቅ ዘጠኝ እና አሥር ሰዓት አካባቢ ገላን ከፍራሽ ማላቀቅ ትልቅ ጉልበት ይጠይቃል። ለሱሑር እንደመነሳት የሚከብድ ነገር የለም። በመሆኑም ብዙዎቻችን ያለ ሱሑር መፆምን በወደድን። ግና ሱናዉን አስበንና በረካዉን ለማግኘት ብለን እየታገልን እንነሳለን። ዐይናችን ሳንከፍት የምንበላ ሁሉ አለን። ከሱሑር በኋላ እስከ ሱብሒ ያለው ሰዓት አጭር ቢሆንም ለብዙዎቻችን ይረዝምብናል። ግና ከፊቱ ያለዉን የግዴታ ሶላት ሳይሰግዱ መተኛት ቁጭትን የሚያስከትል በመሆኑ እንቅልፋችንን እየታገልን በኢስቲግፋርና ቁርአን በመቅራት እንቆያለን ። ገና ለሱብሒ ሶላት እንደቆምን ከሶላቱ በኋላ ያለው ጣፋጭ እንቅልፍ ይታወሰናል። ያ እንቅልፍ ዱንያ ላይ ካሉ ጣፋጭ ነገሮች ሁሉ መካከል ቀዳሚው ሳይሆን አይቀርም። ግና ከሱብሒ በኋላ መተኛት አይመከርም ። ሰዓቱ አላህን የማውሳትና የዱዓ ሰዓት በመሆኑ ወደ አላህ መቅረብንና በርሱ ዘንድ መወደድን አስበልጠው ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ ዚክርና ዱዓ እያደረጉ የሚቀመጡ ብርቱዎችንም አሉ። ኢማን ማለት ይህ ነው። የማይታየዉን የአላህ ቃልኪዳን እንደሚታይ አድርጎ ማመን። እኛ ከምንፈልገው በላይ አላህ የሚወደዉን ማስቀደም። ነፍሲያችን ከምትመርጠው አላህ የሚመርጠዉን መምረጥ። ጀነት ዉድ ናት ። ነፍሲያን መጫንን ፣ ፍላጎትን መጨቆንን ትጠይቃለች ። ጀነት ለነፍሲያ በሚከብዱ ነገሮች የተከበበች ናት። እንቅልፍ መቁረጥን፣ ድካምን መርታትን፣ ስንፍናን ማሸነፍን ፣የምንወደዉን አላህ በሚወደው መተካትን ትሻለች። አላህ ያበርታን። @heppymuslim29
Открыть в Telegramረመዷን ውስጥ የሚደረግ ዑምራ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሐጅ ሲመለሱ ለኡሙ ሲናን (ረ.ዐ.) “ለምንድነው ከኔ ጋር ሐጅ ያላደረግሽው?” አሏት። “ባለቤቴ ሁለት ግመሎች ነበሩት። አንዱን ተሳፍሮ ሐጅ ሄደበት፤ ሁለተኛው ደግሞ አገልጋያችን ውሃ የሚያመላልስበት ነው፡፡” አለቻቸው። እንዲህ አሏት፡- “በረመዷን ውስጥ የምትደረግ ዑምራ ከኔ ጋር ሐጅ ማድረግን ትስተካከላለች። ” የሐጅ ምንዳን ትስተካከላለች ማለታቸው ነው። ነገር ግን ሰውዬው ሐጅ አደረገ ማለት አይደለም። አላህ ምንዳን የሚያነባብራቸው ጊዜያት አሉ። ልብ ብላችሁ ተጠቀሙባቸው። @heppymuslim29
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር@meazahaymanotРелигия5,59 тыс.
Ethiopian Orthodoxs Daily@ethiopianorthodoxsРелигия5,13 тыс.
🔊KEYRAL-UMMA-TUBE@keyralummaРелигия5,76 тыс.
ተንቢሃት Tenbihat – ኢስላማዊ ህግጋት እና ተግሳፃት@tenbihatРелигия5,77 тыс.
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹@ortodox_27Религия5,06 тыс.- መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጋብቻ@biblicalmarriageРелигия5,82 тыс.
Fuad Mohammed@fuadorodurusРелигия4,94 тыс.
AASTU-ECSF@aastuecsfРелигия4,92 тыс.