Кабинет

Посты канала HAppy Mûslimah

сначала новые

#7595Текст

ሴትና ብልሃት **** ሚስቱን ጂን ይዟታል ተባለና ሊያስቀራባት የሆነ ሸይኽ ዘንድ ይዟት ሄደ፡፡ ሸይኹ ጥቂት እንደቀሩባት ጂኑ መናገር ጀመረ፡፡ “ለመውጣት ዝግጁ ነኝ ግን መስፈርት አለኝ፡፡” አላቸው፡፡ ሸይኹ ጂኑን ታገሉት “ያለ አንዳች መስፈርት በግድህ ትወጣታለህ!” አሉት፡፡ ጂኑ ግን እንቢ አለ፡፡ በመጨረሻም ሸይኹ “እሺ መስፈርትህ ምንድነው?” ብለው ጠየቁት፡፡ “ከዚህ ከወጣሁ ቀጥታ ወደባሏ እንድገባ ይፈቀድኝ፡፡” አላቸው፡፡ ቀድሞዉኑ ሲፈራ ወደ ሩቃው ቤት የሄደው ባሏ ተሸበረ፣ ተንቀጠቀጠ፡፡ ሸይኹም “በፍፁም አይሆንም፣ አይደረግም፡፡ ወደርሱ የመግባት መብት የለህም፡፡” አሉት፡፡ ግና ትንሽ ካሰላሰሉ በኋላ ቆይተው ለምን ወደባሏ መግባት እንደፈለገ ጠየቁት፡፡ ጂኑም መለሰ “እሱ የኛ ተመሳሳይ ነው አይሰግድም፡፡ ማረፊያችንና መናኸሪያችን መሆን አለበት” አላቸው፡፡ ሸይኹም ወደ ሰውዬው ዞረው ጠየቁት፤ “አትሰግድም እንዴ!” በማለት ጠየቁት፡፡ “ አረ እሰግዳለሁ፡፡” አላቸው እየተደናበረ፡፡ ሸይኹ ከጂኑ ጋር ተደራደሩ፡፡ እንዲህ አሉት- “በል አሁን ከሷ ዉጣ፡፡ ነገርግን እሱን ግን እዚያው ቤታቸው አካባቢ ሆነህ ተከታተል፡፡ በርግጥ የማይሰግድ ከሆን እንድትገባበት ፈቅጄልሃለሁ፡፡” አሉት፡፡ ጂኑም በሀሳቡ ተስማማና ለቀቃት፡፡ ቀናት አለፉ፡፡ ሴትዮዋ ለሸይኹ ደዉላ ባደረጉት መልካም ነገር አመሰገነቻቸው፡፡ “አሁን ቀጥብሎ እየሰገደ ነው፡፡ እንዲያዉም የመስጂድ በር ከፋች ሆኗል፡፡” አለቻቸው፡፡ ሸይኹም “ አይ ሰው አላህን ሳይፈራ ጂንን ይፈራ!” አሉና ፈገግ አሉ፡፡ እርግጥ ነው ሴትዮዋ ምንም ጂን አልነበረባትም፡፡ ባሏ አልሰግድ ብሎ ቢያስቸግራት ከሸይኹ ጋር ተመካክራ ነው ይህን ያደረገችው፡፡ ሴት ልጅ መላ አታጣም ይባል የለ፡፡ በዚህ መልኩ ባሏ እውነተኛ የአላህ ባርያ ሆኖ ኖረላት፡፡ @heppymuslim29

Открыть в Telegram
Просмотры3280%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7594Текст

ባለቤቴ ሲበዛ እብድ ናት(እኔ ጋር ብቻ)። በዚህ እብደቷ የተነሳ በቀን ውስጥ የሆነ ነገር ሳታጠፋ አታልፍም። ልክ የሆነ ነገር ስታጠፋ አጠገቤ መጥታ ትቀመጥና ልክ እንደ ህፃን ልጅ በነዛ ውብ እና ቅልልቅ ዐይኖቿ ቁልጭ ቁልጭ እያለች ታየኛለች። እኔም ይሄ ድርጊቷ ምንን እንደሚያመላክት ስለማወቅ፦ "በይ ቶሎ ምን እንዳጠፋሽ ተናገሪ ?" እላታለሁ። እርሷም እንደለመደቺው የታቺኛውን ከንፈሯን ጣል በማድረግ፦"እንዴዴዴዴ አባቴ የምር ምንም አላጠፋሁም" ትላለች (እንደዚህ ስታደርግ ግን ልቤን ቅልጥ አርጋው ከሙታኖች ጋር ትቀላቅለኛለች)። እኔም፦ "ሆሆሆሆ ቶሎ ተናገሪ ብዬሻለው" እላታለው እንደምንም ሰቄን ተቆጣጥሬ። እርሷም፦ "እኔ ምንም አላረኩም እራስህ ነህ ድመት እንደማልወድ እያወቅ ይዛሀት የመጣሀው" ትላለች ጥፋቷን ወደ እኔና ወደ ድመቴ እያላከከኝ አለች። እኔም፦ "ፎዙ (የድመቴ ስም ነው) ደሞ ምን አደረገችሽ?" አልኳት። እርሷም፦ "እቃ አጥቤ እንደጨረስኩኝ ይዤው ልደረድረው ስሄድ ፎዙ መጥታ እግሬን ስትተሻሸኝ ደንግጬ እቃዎቹን እንዳለ ወረወረኳቸው ከዛም ተሰበሩ" አለቺ። እኔም፦ አውቄ እንደ ተናደደ ሰው ዝም አልኳት(ዝም ስል አቶድም)። እርሷም፦ "እህህህህ ለምንድነው ዝም የምትለው እንደዚህ ዝም ስትለኝ እንደማልወድ ታቅ የለ እንዴ" ትላለች። እኔም፦ ዝምታዬ እጸናለው። እርሷም፦ "አባቴ ባአላህ በቃ እሺ ይቅርታ እንዴዴ" ብላ ጉንጭዋን ትነፋቸዋለች። እኔም፦ ከዚህ በላይ ስለማልችል ዘልዬ አቅፋታለሁ ። @heppymuslim29

Открыть в Telegram
Просмотры2 030+519%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7593Текст

ከ ዝሙት አፅዱኝ… ~ • ማዒዝ ኢብኑ ማሊክ የሰው ልጅ ነውና ተሳሳተ፤ ሸይጧን አሸነፈውና ዝሙት ላይ ወደቀ። ወንጀሉን ማንም አላየበትም፤ ሌሊቱ ሰወረው፣ አላህም ነውሩን ሸፈነለት። ነገር ግን የማዒዝ ህሊና ሰላም ሊሰጠው አልቻለም። ምድሪቱ በሰፊው ጠበበችው። «እንዴት አላህን በዚህ ወንጀል እገናኘዋለሁ?» የሚለው ሀሳብ እንቅልፍ ነሳው። የማዒዝ ነፍስ መዳንን ፈለገች። ዱኒያ ላይ ተቀጥቶ አሊያም ነፅቶ ወደ አኼራ መሄድን መረጠ። እግሮቹ ወደ ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) መስጂድ እየመሩት፣ ልቡ ግን በፍርሃት እና በተስፋ መሃል ትናወጥ ነበር። ማዒዝ ወደ ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) ገባ። ከፊታቸው ቆመ። የውስጡን እሳት ለማብረድ እንዲህ ሲል ተማፀነ፡- «يَا رَسُولَ اللَّهِ طَهِّرْنِي» «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አፅዱኝ(ከ ወንጀል)» አላቸው። የእዝነቱ ነብይ ግን ማዒዝን ማጣት አልፈለጉም ነበር። ፊታቸውን አዞሩበት። አልሰሙ እንደሆነ በማስመሰል ወደ ቀኝ ፊታቸውን መለሱ። ማዒዝ ግን አልተወም። አሁንም በዚያ በኩል ሄዶ ደገመው። ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) አሁንም ፊታቸውን አዞሩ። እንዲህም አሉት፡- «وَيْحَكَ! ارْجِعْ فَاسْتَغْفِرِ اللَّهَ وَتُبْ إِلَيْهِ» «ወዮልህ! ተመለስ (ሂድ)፤ አላህን ምህረት ጠይቅ፣ ወደርሱም ተመለስ።» አሉት። ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) በሩን ከፈቱለት። በራሱና በፈጣሪው መሃል ይሁን፣ ተውበት ያድርግና  ይተወው በሚል ስሜት አሰናበቱት። ማዒዝ ግን ወንጀሉ ውስጡን እየበላው ነው። ዝም ብሎ መሄድ አልቻለም። ለሶስተኛና ለአራተኛ ጊዜ ተመላለሰ። «ዝሙት ፈፅሚያለሁ »እያለ መሰከረ። ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) ማጣራት ነበረባቸው። እንዲህ ብለው ጠየቁ፡- «أَبِهِ جُنُونٌ؟» «እብደት አለበት እንዴ?» ሰዎችም «አይደለም ጤነኛ ነው» አሉ። አሁንም ጠየቁ፡- «أَشَرِبَ خَمْرًا؟» «ኸምር ጠጥቶ (ሰክሮ) ይሆን?» አንድ ሰዉ ተነስቶ አፉን አሸተተው፤ ምንም አልጠጣም። ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) ግልፅ በሆነ የአረብኛ ቃል ወንጀሉን መፈፀሙን አረጋገጡ። ማዒዝም ምንም ሳይሸሽግ «አዎ!»አለ። ማዒዝ ራሱ በጠየቀው መሰረት ፍርዱ ተወሰነ። ወደ ቅጣት ቦታው ተወሰደ። ድንጋይ ሲወረወርበት ህመሙ ሲሰማው እንደማምለጥ አለ። ሆኖም የዱኒያው ቅጣት ተፈፀመና ማዒዝ ወደ አላህ ሄደ። ይህ ክስተት በሰዎች መካከል መነጋገሪያ ሆነ። አንዳንዶች በልበ ሙሉነት ስለ ማዒዝ ተውበት ሲያወሩ፣ ሁለት ሰዎች ግን በመሃከላቸው እንዲህ ተባባሉ፡-«ይህንን ሰው አያችሁት አይደል? አላህ ነውሩን ሸፍኖለት ነበር፤ እሱ ግን እንደ ውሻ በድንጋይ ተወግሮ እስኪገደል ድረስ ነፍሱን ከመወንጀል አልተወገደም።» አሉ። ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) የነዚያን ሰዎች ንግግር ሰሙ። ዝም ብለው ጉዞአቸውን ቀጠሉ። መንገድ ላይ የሞተ አህያ (በክት) ተጥሎ አዩ። ያኔ እነዚያን ሰዎች ጠሩና እንዲህ አሉ፡- «كُلَا مِنْ جِيفَةِ هَذَا الْحِمَارِ» «ከዚህ የአህያ በክት ብሉ!» ሰዎቹ ደነገጡ። «አንቱ የአላህ ነብይ ሆይ! ይህን ማን ይበላል?» አሉ። ነብዩም ልብን የሚሰብር ምላሽ ሰጡ፡- «ቅድም በወንድማችሁ ክብር ላይ የሰነዘራችሁት ቃል ከዚህ በክት ከመብላት ይበልጥ የከፋ (የቆሸሸ) ነው።» አሏቸው። ከዚያም ስለ ማዒዝ ታላቅ ተውበት  ሲናገሩ እንዲህ አሉ፡- «لَقَدْ تَابَ تَوْبَةً لَوْ قُسِّمَتْ بَيْنَ سَبْعِينَ مِنْ أَهْلِ الْمَدِينَةِ لَوَسِعَتْهُمْ» «በ እርግጥም ለመዲና ነዋሪዎች ለ70 ሰዎች ቢከፋፈል ለሁሉም ይበቃቸው ነበር።» ብለው መሰከሩለት። @heppymuslim29

Открыть в Telegram
Просмотры2 700+723%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7524Текст

በአውስትራሊያ የሚኖር አንድ አዛውንት በሰላም ተኝተው ሳለ፣ የኢድ አል-ፊጥር የተክቢራ ድምፅ ከእንቅልፋቸው ይቀሰቅሳቸዋል። አዛውንቱ በድምፁ ተረብሸውና ተበሳጭተው፣ ድምፁን እንዲያጠፉ ቅሬታቸውን ለማቅረብ ወደ መስጂዱ አመሩ። ▪️​መስጂዱ እንደደረሱ ግን ያልጠበቁት ነገር ገጠማቸው። የመስጂዱ ኢማምና የጀመዓው አባላት በታላቅ አክብሮትና ትህትና ተቀበሏቸው። እንዲህም አሏቸው፦ "ስላስቸገርንዎት በጣም ይቅርታ እንጠይቃለን፤ ከዚህ በኋላ እንዲህ ዓይነት ችግር እንዳይደገም ቃል እንገባልዎታለን።" ​አዛውንቱ በዚህ መልካም አቀባበልና ትህትና ልባቸው ተነካ። ወዲያውኑ ስለ እምነቱ የበለጠ ለማወቅ ፈልገው ከኢማሙ ጋር ለመቀመጥ ጠየቁ። ኢማሙም ስለ እስልምና ምንነት፣ ስለ መቻቻል፣ በሁሉም ነቢያት ስለማመንና ወደፊት ስለሚከሰቱ ነገሮች አስቀድሞ ስለሚተነብየው የቁርዓን ተአምራት በሰፊው አስረዷቸው። ​ሽማግሌው በሰሙት ነገር እጅግ ተደንቀው እያለቀሱ እንዲህ አሉ። "እኔ አሁን የ85 ዓመት አዛውንት ነኝ፤ ወደ እስልምና ለመግባት ዕድሉ ያለኝ አይመስለኝም። *​ኢማሙም ሲመልሱ፦ "ወደ እስልምና ለመግባት የቀረዎት አንድ ሰከንድ ቢሆን እንኳ፣ አላህ መሐሪና አዛኝ ስለሆነ ወንጀልዎን ይምርልዎታል።" አሏቸው። በመጨረሻም መጀመሪያ ቅሬታ ለማቅረብ የመጡት አዛውንት፣ በመልካም ስነ-ምግባር ተማርከው የእስልምናን እምነት ተቀበሉ። ሱብሃን አላህ!! ▪️ከአረብኛ ፅሁፍ የተወሰደ @heppymuslim29

Открыть в Telegram
Просмотры5 450×17к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7522Текст

ኸውለት ቢንት አል-አዝወር **** ኻሊድ ኢብን ወሊድ (ረ.ዐ) በአንድ ወቅት ከሮማውያን ጋር በተደረገው ውጊያ የሙስሊሞችን ሰልፍ በማስተካከል ላይ ሳለ አንድ ሙሉ ሰውነቱን እና ፊቱን በአረንጓዴ ጨርቅ የተሸፈነ ተዋጊ ከሰልፉ ፊት ለፊት ተመለከተ፡፡ የሙስሊሞችንም ሰልፍ እየመራ የሮማውያኑን ጦር ከፍተኛ ጉዳት ያደርስበት ጀመር፡፡ ከሙስሊሞች ጦር ውስጥም የተሸፋፈነውን ሰው የሚያውቀው አንድም ሰው አልተገኝም፡፡ በውጊያው መሃልም ከሙጃሂድ ወንድሞቹ አይን ተሰወረ፡፡ ውጊያው ሲቀዘቅዝም ከሮማውያኑ መሃል በደም የተነከረ ሰይፉን ይዞ ወጣ፡፡ ራፊዕ ኢብን ኡመይራ (ረ.ዐ) በወቅቱ ከሙስሊሞች ጦር ጋር ነበር፡፡ ክስተቱንም እንዲህ ሲል ይተርካል፡- “በውጊያ ውስጥ እያለን የተሸፋፈነውን ሰው ጀብዱ ስንመለከት የጦር መሪያችን ኻሊድ ኢብን ወሊድ (ረ.ዐ) ፊቱን ሽፍኖ ገብቶ ይሆናል ብለን ገምተን ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ጀግና ጦርነቱ ሲቀዘቅዝ ከሮማውያን መሀል ሲወጣ ከቀኙ በኩል ኻሊድ ኢብን ወሊድን (ረ.ዐ) ተመለከትነው፡፡ ለኻሊድም (ረ.ዐ) “ይህ ከፊት ለፊትህ ሆኖ አስገራሚ የጀግና ውጊያ የሚዋጋው ሰው ማን ነው?” ብለን ጠየቅነው ኻሊድም (ረ.ዐ) “እኔም እንደናንተ ላውቀው አልቻልኩም” አለን፡፡ ውጊያውም እንደ አዲስ ሊጀመር ነው፡፡ ኻሊድም “የሙስሊም ጦር ሆይ! በጀግንነት ተዋጉ፣ ከእምነታቹሁም ላይ የጠላትን ወረራ ተከላከሉ” በማለት ሙስሊሞችን አበረታታ፡፡ የተሸፋፈነውም ሙጃሂድ ጦሩን ከፊት ለፊት ሆኖ መምራቱን እንደቀጠለ ነው፡፡ ውጊያውም ከተጀመረ በኋላ ወደ ጠላት ስብስብ ገስግሶ ስለሚገባ ሙጃሂድ ወንድሞቹ ከሰልፋቸው ውስጥ አይመለከቱትም ነበር፡፡ ጦርነቱም ሲጠናቀቅ ልብሶቹ በደም የተነከሩ ሆነው ወደ ሙስሊሞች ካምፕ መጣ፡፡ ኻሊድ እና ሙጃሂዶቹም “ለአላህ ስትል ፊትህን ግለጥና አሳየን” ብለው ተናዘዙት፡፡ እርሱ ግን ለንግግራቸው ቦታ ሳይሰጥ ጅርባውን ሰጥቷቸው ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ከሰውዬው የሚታየው ሁኔታ ጉዳዩ አላህ ዘንድ ብቻ እንዲታወቅለት የፈለገ ይመስላል፡፡ ሙስሊም ተዋጊዎችም “አንተ የተሸፋፈንክ ሰው ሆይ! የጦር መሪህ እያዘዘህ ነው ፊትህን አሳየን” እያሉ ከየአቅጣጫ መጮህ ጀመሩ፡፡ ኻሊድም የሰውዬውን እምቢተኝነት በተመለከተ ጊዜ ከፊት ለፊት ቀደመው፡፡ “ወዮልህ! በተግባርህ የሰዎችን ትኩረት ሳብክ” በማለትም ደጋግሞ ጠየቀው፡፡ ጀግናው ሙጃሂድም የጥያቄው መደጋጋም ሲበዛበት “እስካሁን መልስ ያልሰጠሁህ ከአንተ ፊት ድምፄን ለማውጣት ሐያእ (ሀፍረት) ይዞኝ ነው፡፡ እኔም የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ፊታችንን ላልተፈቀደልን ወንዶች እንዳናሳይ ካስተማሩን የሙስሊም ሴቶች ውስጥ አንዷ ነኝ” ስትል በእንስታዊ ድምፅ መለሰችለት፡፡ ኻሊድም በጉዳዩ ተደንቆ “እሺ አላህ ይባርክሽና ስምሽን ንገሪን” ሲል ጠየቃት፡፡ “ኸውለት ቢንት አዝወር ነኝ” ብላ መንገዷን ቀጠለች፡፡ @heppymuslim29

Открыть в Telegram
Просмотры4 640×14к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7521Текст
Просмотры3 090+842%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7520Текст
Просмотры3 940×12к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7519Текст

ከኢሻ ሶላት ቡሀላ ወደ ቤቱ ተመለሰ ልጆቹም ተኝተው አየ፣ ለሚስቱም ልጆቹ ሰግደዋል? እንዴ ብሎ ጠየቃት እሷም፦ምግብ ስላልነበረ አባብዬቸው ተኙ አልሰገዱም እሱም፦ ቀስቅሻቸው አላት እሷም፦ የእገሌ አባት ሆይ …!!ከቀሰቀስኳቸው ከረሀብ የተነሳ ያለቅሳሉ የሚበላ ደሞ የለም! አለቺው እሱም፦ አድምጪኝ: ከኔ የሚጠበቀው እንዲሰግዱ ማዘዝ ነው…እርዚቃቸው ከኔ አይደለም ፣ቀስቅሻቸው እርዚቃቸው ከአላህ ነው ! አላህም እንዲህ ይላል (ቤተሰቦችህንም በስግደት እዘዝ ፣በእሷም ላይ ዘውትር ፅና ፣ሲሳይን አንጠይቅህም ፣እኛ እንሰጥሀለን ፣ መልካሚቱ መጨረሻ ለጥንቅቆቹ ናት ) እናቲቱም እጅ ሰጠችና ቀሰቀሰቻቸው ሰግደው እንደጨረሱም የቤታቸው በር ተንኳኳ ፣ ከዛም ሲከፍቱት ከከተማው አንድ ከበርቴ  ከማእዱ ጣፋጭ ከሆነው ግማሹን ይዞ ቆሞ ነበር ፣ ሰውየውም ፦ ውሰድ ላንተ እና ለቤተሰቦችህ ነው አለው እሱም ፦እንዴት ሲለው ሰውየውም፦«አንድ ባለ ስልጣን እንግዳዬ ነበር ማእዱን ከመመገባችን በፊት ተጣላን እና ምግቡን ላይበላ ምሎ ሄደ » ምግቡንም ይዜ እንዲህ አልኩ "እግሬ ለቆመበት ሰው እሰጣለሁ ,በአላህ እምላለሁ አንተ ደጃፍ ስር እንጂ እግሬ አልቆመም ነበር ! በአላህ ይሁንብኝ ምን ወደዚህ ይዞኝ እንደመጣ አላውቅም "አለው !! 《 ጌታዬ ሆይ ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ ፣ከዘሮቼም አድርግ! ጌታችን ሆይ ፀሎቴንም ተቀበለኝ፤ 》 @heppymuslim29

Открыть в Telegram
Просмотры3 670×11к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7518Текст

ተራዊሕ አምሽተን ስንገባና ደክመን ስንወድቅ ዘጠኝ እና አሥር ሰዓት አካባቢ ገላን ከፍራሽ ማላቀቅ ትልቅ ጉልበት ይጠይቃል። ለሱሑር እንደመነሳት የሚከብድ ነገር የለም። በመሆኑም ብዙዎቻችን ያለ ሱሑር መፆምን በወደድን። ግና ሱናዉን አስበንና በረካዉን ለማግኘት ብለን እየታገልን እንነሳለን። ዐይናችን ሳንከፍት የምንበላ ሁሉ አለን። ከሱሑር በኋላ እስከ ሱብሒ ያለው ሰዓት አጭር ቢሆንም ለብዙዎቻችን ይረዝምብናል። ግና ከፊቱ ያለዉን የግዴታ ሶላት ሳይሰግዱ መተኛት ቁጭትን የሚያስከትል በመሆኑ እንቅልፋችንን እየታገልን በኢስቲግፋርና ቁርአን በመቅራት እንቆያለን ። ገና ለሱብሒ ሶላት እንደቆምን ከሶላቱ በኋላ ያለው ጣፋጭ እንቅልፍ ይታወሰናል። ያ እንቅልፍ ዱንያ ላይ ካሉ ጣፋጭ ነገሮች ሁሉ መካከል ቀዳሚው ሳይሆን አይቀርም። ግና ከሱብሒ በኋላ መተኛት አይመከርም ። ሰዓቱ አላህን የማውሳትና የዱዓ ሰዓት በመሆኑ ወደ አላህ መቅረብንና በርሱ ዘንድ መወደድን አስበልጠው ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ ዚክርና ዱዓ እያደረጉ የሚቀመጡ ብርቱዎችንም አሉ። ኢማን ማለት ይህ ነው። የማይታየዉን የአላህ ቃልኪዳን እንደሚታይ አድርጎ ማመን። እኛ ከምንፈልገው በላይ አላህ የሚወደዉን ማስቀደም። ነፍሲያችን ከምትመርጠው አላህ የሚመርጠዉን መምረጥ። ጀነት ዉድ ናት ። ነፍሲያን መጫንን ፣ ፍላጎትን መጨቆንን ትጠይቃለች ። ጀነት ለነፍሲያ በሚከብዱ ነገሮች የተከበበች ናት። እንቅልፍ መቁረጥን፣ ድካምን መርታትን፣ ስንፍናን ማሸነፍን ፣የምንወደዉን አላህ በሚወደው መተካትን ትሻለች። አላህ ያበርታን። @heppymuslim29

Открыть в Telegram
Просмотры2 720+729%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7517Текст
Просмотры5 520×17к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7515Текст
Просмотры2 630+702%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7514Текст

ልጅ እያለሁ ነው ያው ልጅ እያለሁ ማለት በደምብ ልጅ እያለሁ...የረመዳን ወር ከመግባቱ በፊት መስጂድ ላይ ባለው ወከባ እና ርብርብ ብቻ የወሩን ክቡርነት ተረድተናል፤ እናም ይህ ክቡር ወር ከመግባቱ ቀናቶች ሲቀሩት ኡስታዛችን ሰብሰብ አደረገን እና ስለ ፆም ህግጋትን በልጅኛ አንደበት ያብራሩልን ጀመር "ማንኛውም  የሚበላና የሚጠጣ ነገር ፆምን ያጠፋል እሺ፣ያው ረስታቹ ከበላችሁ ግን ችግር አይኖረውም" ውብ ፈገግታ እየቸሩን ስለ ወሩ በደምብ ያወጉና እኛም ስንናፍቀው ቀናቶች የአመታት ያህል እየረዘሙብንም ቢሆን  ከወሩ ዘለቅን ረመዳን 1 ብሎ በተራዊህ ጅማሮውን አበሰረ ኢላሂ!! የዛን ግዜ ደስታ የሆነ ለየት ያለ ስሜት  ነበረው። ተራዊሁ ተገባዶ ወደ መፆም አለፍን። ሱሁር እንዲያነሱኝ ባስጠነቀኳቸው መሰረት ሱህሬን ተመግቤ የፆመኛን ክብር በእጄው ያዝኩ (ፆመኛው እኔ) ቀኑን እንደምንም እስከ ዙህር እየተንገዳገድኩም ቢሆን ከፆምኩ ቡሀላ  ዙህርን ከጓደኞቼ ጋር  ሰግደን ከመውጣታችን ነው አንድ ሸንኮራ አዟሪ ባይናችን እልፍ ያለው እህእእ ሸንኳራ ግን ፆም ያጣፋል እንዴ፤ እርስ በእርስ አንሾካሾክን " አረ ኡስታዝ እኮ የሚበላ ወይም  የሚጠጣ ነው ያሉት ሸንኮራ ደግሞ እንጨቱ ይተፋላ እንዴ!!!" አዎ አዎ ሁላችንም ተንጫጫን (የልጅነት ፈትዋ)እናሳ ተርበናል እኮ ያልፆመ ደግሞ ፍጡር ላይ የሚደርስበት መገለል ይታወቃል። ያለችንን 25፣50ም ሳንቲምን እያዎጣን ቁርስ ምሳችንን ለቀናት በሸንኮራ ያለ ከልካይ ፁመናል     #ዝምታ ቢበዛም ጥቂቶች ትዝታቸውን አስቃኝተውናል የረመዳን ትዝታውን ያጋራንን የወንድማችንን ፅሁፍ አንካችሁ ብያለሁ!! ትዝታ! እና ረመዷን @heppymuslim29

Открыть в Telegram
Просмотры2 320+607%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7513Превью ссылки

👉  ተራዊሕ ላይ ቁርአን ይዞ መከታተል የሸይኽ ፈውዛን ፈትዋ ↙️ https://t.me/AbuImranAselefy/8443 ➲ ብዙ ሰዎች በተራዊሕ ሶላት ላይ ኢማሙ ሲያሰግድ ቁርኣን ይዘው ይከታተላሉ። ይህ ተግባር በሶላት ውስጥ አንድ ሰው ማድረግ ያለበትን ተግባሮች ይቃረናል። ➪ አንድ ሰው በሚሰግድ ጊዜ የቀኝ እጁን መዳፍ በግራ እጁ ሳአት ማሰሪያ ላይ ደርቦ ደረቱ ላይ ማድረግ ይኖርበታል። ይህ ከሶላት ሱናዎች አንዱ ነው። እንደዚሁ በሚቆምበት ጊዜ ስጁድ የሚያደርግበትን ቦታ መመልከት አለበት ይህም ሱና ነው። ➧ ኢማሙ በሚቀራበት ጊዜ ማዳመጥ አለበት ይህም ዋጂብ ካልሆነ ሱና ነው። ሌላው ሶላት ላይ ሆኖ አላስፈላጊ እንቅስቃሴ ማድረግ የለበትም። ቁርኣን ይዞ የሚከታተል ሰው እነዚህን ሁሉ ሱናዎች ይቃረናል። ለእነዚህና ለመሳሰሉት ምክንያቶቸ አብዛኛዎች የኢስላም ሊቃውንቶች ይከለክላሉ። ምናልባት ቁርኣንን የሸመደደና ኢማሙ ቢሳሳት ሊመልስ የሚችል ከሌለ አንድ ሰው ከኋላው ቁርኣን ይዞ ይከታተለው ይላሉ። ➽ ከነጭራሹ ሶላቱ ባጢል ነው የሚሉም አሉ። በተቃራኒው ይቻላል ብለው አነስ ኢብኑ ማሊክ በሚያሰግድ ጊዜ ከኋላው አንድ ወጣት ቁርኣን ይዞ ከተሳሳተ ይመልሰው ነበር የሚሉ አሉ። ነገር ግን ሌሎች ዑለሞችም ሐፊዝ በሌለ ጊዚ አንድ ሰው ይከታተለው ያሉትም ለዚህ ነው ደሩራ ስለሆነ።    ➾ ከዚህ ውጪ አሁን ባለው መልኩ በነብዩም ይሁን በሶሐቦች ዘመን አልተገኘም። በዚህ ዙሪያ ያሉትን የዑለሞች አቋም የሚከተለውን ይመስላል:– — ኢማሙ አቡ ሐኒፋ ክልክል ነው ይላሉ። –  ኢማሙ ማሊክ ይጠላል ይላሉ። – ኢማሙ አሕመድና ኢማሙ ሻፍዕይ ይቻላል ይላሉ። – ኢብኑ ሐዝም ሶላቱ ባጢል ነው ይላል። –  ከዘመናች ዑለሞች ኢማሙ ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ዑሰይሚንና ሸይኽ አልባኒ ሱናን ስለሚቃረን ለደሩራ ካልሆነ አይቻልም ይላሉ። ➧ ከላይ ለተጠቀሱት ሙኻለፋዎች ምክንያት ለደሩራ ካልሆነ አይቻልም የሚለው አመዛኝ ነው። ዒባዳችንን ከሙኻለፋ መጠበቅ የኛ ድርሻ ነው።      አላህ ለመልካሙ ይወፍቀን። @heppymuslim29

Открыть в Telegram
Просмотры2 390+629%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7511Текст
Просмотры3 970×12к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7508Текст

ግርም ከሚሉኝ የሕይወት ታሪኮች መካከል አንዱ የእናታችን የዓኢሻ ነው፡፡ በስንት ዓመቷ አገባች በሚለው ላይ ዉዝግብ ስላለ ልለፈው፡፡ ግና በ18 ዓመቷ ﷺ ተለዩዋት፡፡ አሥር ዓመት እንኳን ከነቢዩ ጋር አልኖሩም፡፡  ዓኢሻ ገና በአፍላ ወጣትነቷ ነበር ያዉም በእጅጉ የምትቀናባቸዉን ተወዳጅ ባለቤቷን ያጣችው፣ ልጅ አልነበራትም፡፡የሚገርመው “ልጅ ይኖረኝ ዘንድ ዱዓ አድርጉልኝ” ብላ ነቢዩን ወትዉታለች የሚል ሐዲሥ አልተገኘም፡፡ ልብ በሉልኝ። ከርሣቸው ህልፈት በኋላ 47 ዓመታትን ብቻዋን ነው የኖረችው፡፡ አዎ ብቻዋን። አላህ ለዓኢሻ ልጅ ያልሰጣት ስለሚጠላት ነው የሚል ይኖር ይሆን?? አላህ ምንን ለምን እንደዳደረገ የሚያውቅ ጌታ ነው፣ አንችን ባርያዉን አይጠላም እሺ። እናታችን ዓኢሻ አላህ ሱ.ወ ልጅ ስላልሰጣት መፈጠሯን አልጠላችም፣ በአምላኳም አላማረረችም። እምነቷን አልቀየረችም። 'የኔስ ተለየ' አላማረረችም። የሷ ባልሆነው ልጅ 'ኡሙ ዐብደላህ' ተብላ እየተጠራች ሙሉ ሕይወቷን በዒባዳ፣ በዕውቀትና በጂሃድ አሳለፈች፡፡ ትላልቅ ሶሐቦች ከሷ ተምረዋል፣ ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን ለብዙዎች ታስረዳ ነበር፡፡ ከዚህ ምን እንማራለን መሰለሽ ... ልጅ ስለጠፋ፣ ትዳር ስለጠፋ፣ ቤት ስለጠፋ፣ መኪና ስለጠፋ … ሕይወት አትቆምም ትቀጥላለች፡፡ @heppymuslim29

Открыть в Telegram
Просмотры4 800×15к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7507Текст
Просмотры4 380×13к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7504Текст

ከኡሙ ደርዳእ ምክሮች - ኡሙ ደርዳእ ከበኒ ተሚም ጎሣ ለሆነ አቡ ሂዛር ለሚባል አንድ ታላቅ ሰው ‹የሂዛር አባት ሆይ ! በሞት አልጋ ላይ ያለ ሰው ምን እንደሚል ልንገርህን?› አለችው። ‹ምን ይላል ?› አላት። ‹እንዲህ ሲል የሚጣራ ይመስለኛል፡፡› አለችው፡፡ ‹ ጎረቤቶቼ ሆይ! የአስከሬኔ ተሸካሚዎች ሆይ! ይህች ዓለም እኔን እንዳታለለችኝ እናንተንም እንዳታታልላችሁ ። በኔ እንደተጫወተችብኝ በናንተም አትጫወትባችሁ። ቤተሰቦቼ ሆይ! ወንጀሌ ሁሉ ሸክሙ በኔ ላይ ነው። ከኔ ወንጀል ቅንጣት ታህል አትሸከሙም።› ኡሙ ደርዳእ ረ.ዐ አሁንም ትመክራለች። ድንገተኛውን እና ጥፍጥና ቆራጩን ሞት ታስታውሰናለች። ሰዎች የሞተን ሰው ገላ ሲሸከሙ ኃጢኣቱን አብረው አይሸከሙም፡፡ ቢሸከሙማ ኖሮ በተለይ የመጥፎ ሰው በድን እንዴት ይከብድ ነበር በአላህ!፡፡ ሰዎች አንድ የሞተን ሰው ቀደ መቃብር ሲሸከሙ ወንጀሉ የራሱ እዳ ነውና አብረው አይሸከሙም፡፡ ቢሸከሙማ ኖሮ በተለይ የእኩይ ሰው አስከሬን ስንቶችን ባጎበጠ ነበር፡፡ እንደሞተ ሰው የሚያሣዝን ማን አለ!፡፡ ለነፍሱ ለመሥራት እድል የለውም። መልካም ሥራዎቹን ለማብዛት ዕድሜ አይኖረውም፡፡ የቆይታ ጊዜው አብቅቷልና። የተሠጠውን እድሜ ጨርሷልና፡፡ የመልካምም ሆነ የመጥፎ ሥራ ባለቤት የሰው ልጅ ዱኒያን ሲሰናበት የጎደለበት ሆኖ ነው። መቆጨቱም የማይቀርና የግድ ነው። የመልካም ሥራ ባለቤት መሥራት የሚገባኝን ያህል አልሠራሁም ብሎ ይቆጫል። የመጥፎ ሥራ ባለቤት ደግሞ የገዛ መጥፎ ሥራው መልሦ እሾህ ሲሆንበት እጁን ይነክሣል። ኡሙ ደርዳእ የዋዛ ሴት አልነበረችም። መሞቷን በርግጠኝነት አወቀች። በመሆኑም በብዙ ቦታዎች ላይ በተደጋጋሚ ከራሷ ጋር አውርታለች። መጨረሻዋንም አርቃ ለማየት ሞክራለች። እጣ ፈንታዋንም ፈርታለች። ስለሆነም ወደ መቃብር መንገድ የጀመሩ ሙታኖችን በሀሣብ ለማነጋገር አሠበች። እንዲህ የሚሏት ይመስላታል - የፈለጋችሁትን ያህል ብትኖሩ መሞታችሁ ግድ ነው። የቱን ያህል ብትሮጡ ሩጫችሁ ፌርማታ አለው። ፌርማታውም ወደ እውነተኛውና ቋሚው ዓለም መሸጋገሪያ ነው። ረጃጅም ጉዞዎች፣ አስፈሪ መሰናክሎችና አቀበቶች ከፊት ለፊታችሁ አሉ። ነገ ረጅም ጉዞ እንዳለበት ያወቀ ሰው ደግሞ ዛሬን በአንድ ልብ ማረፍ የለበትም። ለዚያኛው ሀገር መዘጋጀት ይኖርበታል። በቂ ስንቅም ያስፈልገዋል። ኡሙ ደርዳእ በእምቅ ቃላቶቿ ትመክራለች….. በዚህች ዓለም ጥቅም አትዘናጉ። ለአስፈሪው ቀን ስንቅ ያዙ። ከፊታችሁ ብዙዎች ቀድመዋችኋል፡፡ እናንተም ትሄዳላችሁ፡፡ የተቀሩትም ይከተሏችኋል። በፍፁም አትታለሉ። ዘላለም እንደሚኖር ሰው አትገንቡ። እድሜ ልክ እንደሚከርም ሰው አታከማቹ። ቋሚ አይደላችሁም ትሄዳላችሁ። የቀኑ ጨዋታችሁ ያልቃል። የለሊቱም እንቅልፋችሁ ያበቃል። ዛሬን ለአላህ ሱ.ወ ስገዱ፡፡ ካለፋችሁ በኋላ የሚሰግድላችሁ/ መልካም ሥራ የሚሠራላችሁ የለም። ዛሬውና ሞልታችሁ ሥሩ፤ ነገ የሚሞላላችሁ አታገኙም። ዛሬውኑ ፍጠኑ፤ ቆሞ የሚጠብቃችሁ አታገኙም። የመዘናጋትን ጥላ ከላያችሁ ላይ ግፈፉ። ያልሠራ ሰው በርትቶ ከሠራው ሊቀድም አይችልም። የሚራመደውም የሚሮጠውን ይቀድማል ተብሎ አይታሠብም። ይህች ዓለም አታታልላችሁ። ውድድሩን የሚያቋርጥ ሰነፍ ሰው ከመወዳደር አያዘናጋችሁ። ዛሬ ሥራ ነው ዉጤት የለም። ነገ ደግሞ ውጤት ነው ሥራ የለም። @heppymuslim29

Открыть в Telegram
Просмотры4 300×13к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7503Текст

"አስተውለህ ታውቃለህ ግን?  "አስተውሎ ከጨረሰ በኋላ የሚጠይቀኝ ጥያቄ ነው .. " ምኑን?" " አጥብቀን የምንፈልጋቸው ነገራቶች እንደማይገኙ ?" " እኔንጃ ለምሳሌ ምን ምን ?" ቀለል የሚሉ ጥያቄዎችን የሚያበዛ ቢሆንም መመለስ አልወድም.. የሚለውን ባደምጥ ምላሼን እዛ ውስጥ እንደማገኘው አውቃለው " ብዙ ጊዜ ቸኩለን አልያ ደግሞ በጣም ፈልገነው ያለ እቃ ከጠፋ ለማግኘት እንቸገራለን « አሁን በጣም ስለፈለኩት ነው'ጂ በቀላሉ አገኘው ነበር» እንላለን እና ይህ አጋጥሞህ አያውቅም ?" ሁሌ ቁልፍ እየጣልኩ የምንከራተተው ነገር ትዝ ብሎኝ ፈገግ አልኩ " አዎ ሁሉም ሰው ላይ ያለ ነገር ይመስለኛል" "አዎ ሁሉም በሚባል ደረጃ አሳልፎታል...እና ካስተዋልክ እንደዛ ላይ ታች የምንልባቸው እና መጮህ እስኪያሰኘን የሚያለፉን እቃዎች መጨረሻ ላይ ግን ግልፅ ቦታ ላይ ነው የምናገኛቸው " እዚ ሆኖ ነው የለፋነው ?" እንላለን ብዙ ጊዜ ...ለምን ይመስልሀል ?" "እኔንጃ ለምንድነው ?" " አላውቅም ግን ሲመስለኝ በዛ ሰዓት ማግኘት እንዳለብን እንጂ እንዴት ማግኘት እንዳለብን አናስብም ። ቦታ የተባለ ነገር ሁሉ እቃን ማስቀመጥ ስለሚችል ሁሉን ቦታ እናስሳለን ደሞም አይተነው ልናልፈው እንችላለንኮ...ግን በዛ ሰዓት የጠፋብን እቃ የት ሊቀመጥ ይችላል የሚለውን ብናስብ ብዙ ልፋት እናድን ነበር ...እና እኛ የሰው ልጆች አሁን የጠፋብን ነገር እነዚ ደስታ ፣ ሀሴት እና ፍቅር የምንላቸው ነገራቶች ናቸው ። ሁሉም ሰው ደግሞ አጥብቆ እየፈለጋቸው ነው ....ለምን አላገኘነውም ?" " እኔንጃ !" " ሁሉም ቦታ በችኮላ እየፈለግናቸው ይመስለኛል ! ሁሉም ሰው አድካሚ በሆነ ፍጥነት ነገራቶችን እያዘበራረቀ እየፈለገ ቢሆንም ሊያገኘው አልቻለም ቅድም እንዳልኩህ ማግኘት እንዳለብን እንጂ የት ማግኘት እንደምንችል አላወቅንም ። ሁሉም በሌሎች ተፅዕኖ እና ግፊት ሁሉንም መንገድ ቢጠቀምም ሊያገኛቸው አልቻለም ።" "እና የት እንፈልጋቸው ? እንዴት ?" " ቀላል ነው ! ወደውስጣችን ...ሰፊ ወደሆነው የራስ አለማችን እይታችንን ማዞር ነው ። ነፍሳችን ውስጥ ነው ሚስጥሩ ። " ልክ ይሁን ? እንጃ @heppymuslim29

Открыть в Telegram
Просмотры3 460×11к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7502Текст

አንድ ቀን አባቴ ለሁለታችን የሚሆን ምግብ አዘጋጀና በሁለት ሳህን ከፍሎ የምግብ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው። የተዘጋጀው ምግብ ፓስታ በእንቁላል ነበር። አባቴ ፓስታውን ሲያስቀምጠው በአንደኛው ሳህን ከፓስታው በተጨማሪ የተቀቀለ አንድ እንቁላል ከአናቱ አድርጎበታል። በሌላኛው ሳህን ግን ከፓስታው በላይ እንቁላል የሚባል ነገር የለበትም። ከዚያ አባቴ ወደ እኔ እየተመለከተ፣ “ልጄ! የትኛውን ትፈልጋለህ? አንዱን ሳህን ምረጥና አንሳ...” አለኝ። በጊዜው እንቁላል እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ ምግብ አልነበረም። ድህነቱ፣ ገንዘብ ማጣቱ በሁላችንም ቤት ጫን ያለ ስለነበረ አዲስ ዓመት ካልመጣ ወይም ዓመትባል ካልደረሰ በቀር እንቁላል መብላት ዘበት ነው። ታዲያ እኔ፣ አንዱን ሳህን መርጬ እንድወስድ አባቴ ሲጠይቀኝ ፈጥኜ እንቁላል ያለበትን ሳህን መረጥኩ። እንዴ ማን ይሞኛል? እንቁላል ተገኝቶ ነው? በሰዓቱ እንቁላል ያለበትን ሳህን ሳነሳ ቅንጣት ታህል አላመነታሁም ነበር። ደስ እያለኝ ፓስታ በእንቁላሌን መብላት ጀመርኩ። አባቴ ሁለተኛውን ሳህን አንስቶ መመገብ ሲጀምር ግን ዐይኔን ማመን አቃተኝ። አባቴ ከሚበላበት ሳህን ውስጥ ሁለት የተቀቀሉ እንቁላሎች በፓስታው ተሸፍነው ኖሯል። አቤት እንዴት እንደተናደድኩ! ቆጨኝ በጣም! ቸኩዬ በመወሰኔ ራሴን ወቀስኩት። ምናልባትም በሕይወት ዘመኔ እንደዚያ ቀን የተበሳጨሁበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም። ይኼን ጊዜ አባቴ እየሳቀ፣ “የእኔ ልጅ… ዐይኖችህ የሚያዩት ነገር ሁሉ እውነት እንዳልሆኑ መቼም እንዳትረሳ! ደግሞ በሰዎች ላይ ብልጣብልጥ ለመሆን ስትሞክር ትጎዳለህ!!” አለኝ። @heppymuslim29

Открыть в Telegram
Просмотры3 720×11к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7501Текст

እኔ ግን እጠይቀዋለሁ . . ይህች ምኗ ደፋር፣ ምኗ ዐይናውጣ ናት አሏት ጠየቀችው ተብሎ መወራቱን ሲሰሙ፡፡ ‹እኔ እሞታታለሁ እንጂ አልጠይቀውም፡፡› አለች አንደኛዋ፡፡ ‹እኔ ግን እጠይቀዋለሁ› አልኳት ኮስተር ብዬ፡፡ ‹አዎ እኔ ግን ባንቺ ቦታ ቢሆን እጠይቀዋለሁ፡፡› አልኳት፡፡ ‹እንዴት?› አለች ማነሽ ብርቄ ነይማ እስቲ … ምን መሰለሽ … ጉዳዩ ቀልድ አይደለማ፣ ጉዳዩ የቁምነገር ጉዳይ ነው፡፡ ጉዳዩ የዲን ጉዳይ ነው፤ ጉዳዩ ዱንያ አኺራን የማሳካት ጉዳይ ነው፡፡ ጉዳዩ ኢስላማዊ ቤተሰብን የመመሥረት ጉዳይ ነው፡፡ በጉዳዩ ዉስጥ ከራስ እስከ ማኀበረሰብ አርቆ የማሰብ ዓላማ አለበት፡፡ ለዚህ ነው እፍረቴን ገፍፌ እጠይቀዋለሁ ያልኩሽ፡፡ እንዲሁም ጉዳዩ ሌላ ጉዳይም አለው፡፡ ጉዳዩ ከሚወዱት ጋር የመኖር ጉዳይ ነው፡፡ ከሚወዱት ጋር መኖር ደግሞ ፀጋ ነው፤ ከሚወዱት መውለድ ደግሞ ሌላ ፀጋ ነው፡፡ የወደዱትን ማግኘት እንዴት ደስ ይላል መሠላችሁ! ዱንያ ሁለቴ አይኖርባትም። አስቦኝ ይሆናል ብዬ ካሰብኩ፣ ሰው እንደሌለው ከገመትኩ፣ ለኔ ጥሩ አመለካከት እንዳለው ካስተዋልኩ፣ አብሮ የሚሄድ ቀለም አለን ብዬ ካሰላሰልኩ የምሬን ነው የምላችሁ ዐይኔን በጨው አጥቤ እጠይቀዋለሁ፡፡ እናንተ እፈሩ እንጂ እኔ አላፍርም፡፡ ‹የትዳር አጋሩ እንድትሆኚው ያሰበሽ ሰው አለ› ቢለኝ ‹አንተስ ለምን አትሆነኝም?› እለዋለሁ ኮስተር ብዬ፡፡ ‹እስቲ ሚስት ምናምን ፈልጊ› ካለኝ ‹ ሚስት እኮ በዙሪያችን ሞልቷል› እለዋለሁ😁፡፡ ታሞ እንጂ ፈርቶ የሞተ ማን አለ!፡፡ ማን ያውቃል ደፍሮ መጠየቅ አቃተው እንጂ እሱም አስቦኝ ይሆናል፡፡ : : ‹ አረ ጥንቅር ብሎ ለምን አይቀርም!› አለች፡፡ ‹ ጥንቅር ብሎ ለምን ይቀራል?› አልኳት፡፡ ‹ ምን ይቀርብኛል?› አለች፡፡ ‹ ጥሩ ባል ሊቀር ይችላል፡፡ አላህን የሚፈራና የሚያመልክ ጥሩ ቤተሰብ ሊቀር ይችላላ አልኳት. እናም እጠይቀዋለሁ እንጋባ ማለት ቅሌት አይደለም መውረድም፣ መቅለልም መዋረድም አይደለም፣ ሐያእ ማጣትም አይደለም፡፡ ሐያእ ማለት ሐቅን መሸሽ ማለት አይደለም፡፡  መውደድም ወንጀል አይደለማ፡፡ መንፈሳዊ ሕይወቱ ከሳበኝ፣ ታማኝነቱ፣ ኢማኑና ለዲን ያለው ትጋቱ ከማረከኝ ለምን ብዬ ነው የማፍረው እጠይቀዋለሁ፡፡ ሐሳቤ መልካም ነውና፣ ዓላማዬ ትልቅ ነውና፣ የዉስጤን አምላኬ ያውቃልና እጠይቀዋለሁ ብጠይቀው ምንድነው ጥፋቴ!፡፡ ባማክረውና ጥቅሙ የጋራችን ነው ብለው የት ላይ ነው ክፋቴ!፡፡ እሱን በማሰቤ ምንድነው ኃጢኣቴ፡፡ አትጠይቁ የሚል አስተምህሮ አለ እንዴ!፡፡ ለሚጠቅም ነገር መሽቀዳደም ጠቃሚ አይደለም እንዴ! እናታችን ኸዲጃ ነቢዩን የመሰለ ታላቅ ሰው ከእጇ ያስገባችው ጠይቃ አይደለም እንዴ!! ሆ … . እጠይቀዋለሁ ስል ታዲያ ኩሽማንኩሹን አይደለም፡፡ ትኩረቴም ፊቱና ኪሱ አይደለም፡፡ ትኩረቴ ኢማኑና ዲኑ ነው፡፡ ትኩረቴ ስብእናውና ዓላማው ነው፡፡ የሚኮራውንና የሚያስወራውን አይደለም የምጠይቀው፡፡ ኋላ ላይ ‹ጠይቃኝ፣ ወትውታኝ፣ አቻኩላኝ፣ መቆም መቀመጥ ነስታኝ፣ መግባት መውጣት ከልክላኝ … እኮ ነው ያገባኋት› ብሎ ሊመፃደቅ ይችላል ብዬ የገመትኩትን አይደለም የምጠይቀው፡፡ ቁምነገር ያለውን፣ ለምን እንደጠየቅኩት ከኔ በላይ የሚገባውን ነው የምጠይቀው፡፡ ስንቱ ሐራም ፍለጋ ብሎ ከቦሌ እሰከ ጉለሌ እየሄደ አይደለም እንዴ! እኔሰ ለሐላሉ ምን አሳፈረኝ?፤ ቢሳካ መልካም ነው፣ ባይሳካም አይከፋኝም፡፡ እንቢ ተባልኩ ብዬም አልሸማቀቅም፡፡ የሆነው ሁሉ አላህ ያለው ነውና፡፡ ለወንጀል አይደለም የጠየቅኩት፡፡ ለዝሙት አይደለም ያሰብኩት እና አልፈራም አላፍርም …. እጠይቀዋለሁ። ‹ሆ … እናንተ ፀሃፊዎች እኮ እማታመጡት የለ› አለች እታለሜ ሀሳቡን ሳነሳባት ጊዜ አፍጥጣ እያየችኝ፡፡ . . እኔ ይሄን አልፃፍኩም🙄፡፡ ሀሳቡ ግን የኔም ነው፤ መስማማት ያለመስማማት ደግሞ የግል ጉዳይ ነው😊 @heppymuslim29

Открыть в Telegram
Просмотры4 670×14к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—