ርዕስ፦ የትምህርተ ሥላሴ መሠረታውያን ጸሐፊ፦ ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ 🚨 ለወዳጆቹ በማጋራት አብረውን ወንጌልን ይስሩ! Join us ═══◉❖◉════ ◉⇲@Christ_mossion ⇲◉ ◉⇲@Christ_mossion ⇲◉ ⇲◉@Christ_mossion ⇲◉ 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Открыть в Telegram
🗣ወንጌል ለአለም ሁሉ
ዮሐንስ1፥5 ብርሀንም በጨለማ ይበራል፥ጨለማም አላሸነፈውም ይህ channel እግ/ርን የምናመልክበት አብረን ተያይዘን ተደጋግፈን ይህን ዘመን የምናልፍበት ወንጌልን ላልሰሙት የምስራጅ የምናበስርበት channel ነው። ሀሳብ/አሰተያየት; @Gospel_Worldbot ዝማሬዎች በየቀኑ ማግኘት ከፈለጉ👇👇 @Enamelkw_tube
Новые посты
የሳኦል ጥፋቱ🧑🦯 ሳኦል ከዘሩ ትንሽ ከሆነው ከቢንያም ነገድ የሆነ አህያ ሊፈልግ ወጥቶ አንተ የእስራኤል የመጀመርያ ንጉስ ነህ የተባለለት እግዛብሄር ልቡን አይቶ ለሱ የቀና ለህዝቡ ስለሚጠቅም ንግስና የሰጠው ግን ሳኦል ልቡን ከእግዜር አንስቶ በቅራቅንቦ ላይ አረገ አጥፋ ሲባል እንቢ ማለት ጀመረ ሁሉንም ነገር አጥፋ ሲለው ለአንተ ይሁኑልኝ የሰቡ ናቸው ልሰዋልህ አለ ለካ ሳኦል ልቡን ከሰማይ አንስቶ ወደምድር መመልከት ጀምሮዋል እግዜርም እንደ ልቡ ወደ ሆነው ወደ ዳዊት ፊቱን አዞረ እኛም ልባች በጌታ ዘንድ ይሁን
Открыть в Telegram🥠 መና 🥠 ከሰማይ የወረደ እንጀራ እሱም ክርስቶስ ነው ዩሐ 6 ÷ 31 ይበሉ ዘንድ ከሰማይ እንጀራ ሰጣቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ አባቶቻችን በምድረ በዳ መና በሉ፡ አሉት። አይሁድ እንጀራ ለመብላት ተከተሉት እውነተኛ እንጀራ እኔ ነኝ ሲላቸው እኔን ብሉኝ ሲላቸው ሊቀበሉት አልቻሉም እኛ ግን ከሰማይ ለኛ እንደ ወረደልን አምነናል ከሰማይ የወረደልን መና እየሱስ ነው SHARE 💯SHARE 💯SHARE💯 💠💠 JOIN US 💠💠 💠@christ_mossion💠 💠@christ_mossion💠 💠@christ_mossion💠
Открыть в Telegram✍️ ባልወድሽ ነው ወይ ** በቃ አይወደኝም ፣ ትያለሽሳ በቃ ጠልቶኛል ፣ ትያለሽሳ እስኪ መልሺ ፣ በይ ልጠይቅሽ በሀዘን ሳይሆን ፣ በመውደዴ አልቅሽ በይማ አንቺዬ...... ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ክብሬን መጣሌ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ መመሳቀሌ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ችንካር የበሳኝ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ስቃይ ያስገሳኝ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ መንገላታቴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ዝም ማለቴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ይማርሽ ያልኩት ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ግፍ የታገስኩት ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ውርደት መጥገቤ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ፍቅር ማንገቤ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ጥም ያነደደኝ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ አባቴ ያረደኝ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ልሙት ማለቴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ መቁሰል መድማቴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ሲዖል መውረዴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ግርዶሽ መቅደዴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ሞትን መርታቴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ድሉን መስጠቴ እስኪ መልሺ ፣ ልጠይቅሽ ቆይ ሁሉን መሆኔ ፣ ላንቺ አይደለም ወይ በቃ አይወደኝም ፣ ትያለሽ ምነው በቃ ጠልቶኛል ፣ ትያለሽ ምነው እንዲያ መሆኔ ፣ ባልወድሽን ነው በይ ራስሺን ፣ ጠይቂ ራስሽ እንድትመለሽ ፣ በገዛ መልስሽ በስስት አይኖች ፣ በማይዝሉ እጆች እንደ ውድ ሚስት ፣ ልክ እንደ ልጆች ዕቅፍፍፍፍፍ ያረገሽ ፣ ያቀማጠለሽ ሞትሽን ወስዶ ፣ በሞቱ ያዳነሽ አለሽ ወይ ሌላ ፣ እንዲህ 'ወዳጅ ሰው የሞተ ላንቺ ፣ በተደገሰው የሷን ሞት ልሙት ፣ ብሎ ያለልሽ ነፍሱ ላይ ቆርጦ ፣ የጨከነልሽ እና አይወድኝም ፣ ማለትሽ ምነው እኔ 'ምወደው ፣ አንቺን ብቻ ነው ስሚ ይልቅስ አድምጭኝማ ፣ ልንገርሽ ውዴ በአንቺነትሽ ፣ በሥራሽ ሳይሆን በ'ኔነቴ ነው ፣ አንቺን መውደዴ ይሄው ለዚህ ነው በቃ አይወደኝም ፣ እያልሽኝ እንኳን አንደምወድሽ ፣ መንገር 'ማይደክመኝ ባንቺ ተክዬ ፣ የፍቅሬን ድንኳን!! እወድሻለሁ❤❤❤❤❤ ገጣሚ #✍ሄኖክ_አሸብር✍
Открыть в Telegram. ✞#የማለዳ_ጥቅስ✞ (መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 124) ---------- 1፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል። 2፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥ 3፤ ቍጣቸውን በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፤ 4፤ በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ፈሳሽ ባለፈ ነበር፤ 5፤ በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር። 6፤ ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ። 7፤ ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች። ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን። 8፤ ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ በእግዚአብሔር ስም ነው። #ሰናይ_ቀን SHARE 💯SHARE 💯SHARE💯 💠💠 JOIN US 💠💠 💠@christ_mossion💠 💠@christ_mossion💠 💠@christ_mossion💠
Открыть в Telegram📚ራስን ማሸነፍ መኖር ስትጀምር ትልቁን እውነት መጋፈጥ ትጀምራለህ። ራስን ማሸነፍ የምናባዊ ስራ ውጤት ነው። እራስህን የማሸነፍ ጎዳናን የምትጀምረው ግዑዝ ከሆነው የሚታይ አለም ወጠህ የሀሳብ ፍልሚያ ወደሆነው ሜዳ ውስጥ ገብተህ ነው። ራስን ማሸነፍ የአስተሳሰብ ለውጥ ነው። ይህ የፍልሚያ ሜዳ መጉዳትና መጎዳት፤ ማሸነፍና መሸነፍ እንዲሁም መውደቅና መነሳት ያለበት ሚዛናዊ ስፍራ ነው። አድሎ ከእውነተኛ ማንነት ያፋታሃልና በዚህ ሜዳ አድሎ አትጠብቅ። ራስህን ለማሸነፍ የምትጀምረው ግጥሚያ ራስህን ወደ መሆን የታላቅነት ስፍራ ያወጣሃል! ራስህን መሆን ማለት አምላክ በራሱ አምሳል የፈጠረውን ንፁህ ማነነት ያለው ሰዎች አንዲሆን የሚፈልጉትን ሳይሆን አምላኩ አንዲሆን የሚፈልገውን ለመሆን የሚጥርና የተስተካከለ ስብዕና ያለውን ፍጥረታዊ ሰው መሆን ማለት ነው። ➲ራስህን እንዳትሆን ካንተ ጋር የሚፋለሙት ቂም፤ ጥላቻ፤ ከባድና የማይረሱ የሚመስሉ የህይወት አስከፊ ገፅታዎችና ቁስሎች ናቸው። ከነዚህ ሁሉ ጋር ታግሎ ለማሸነፍ የየእለት ልምምድ ይቅር ባይነትና አፍቃሪ ማንነት መሆን አለባቸው። ➲ራስህን ከመሆን ማንነት ምንም ነገር አያሰቆምህም ምክንያቱም ራስህን መሆን የተፈጠርክበት እውነት ነውና። ራስህን ሳትሆን ራስህን ለማሸነፍ መሞከር ደመናን ለመያዝ መድከም ነው። ራስን በመሆን ማንነት ውስጥ ራስን የማሸነፍ ድል ይገኛል። Share👇👇👇👇👇 @christ_mossion @christ_mossion @christ_mossion
Открыть в Telegramወሳኝ የሆኑ የሶቅራጠስ 3ቱ ጥያቄዎች! ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ➜አንድ ሰው ወደ ሶቅራጠስ ሄዶ እንዲህ አለው፡፡ ‹‹ሶቅራጠስ ወዳጄ፣ እገሌ ስለተባለው ወዳጅህ የሰማሁት ደስ አይልም›› አለው፡፡ ሶቅራጦስ ግን ዝም አለ፡፡ ➠ሠውየውም እንደገና፡- ‹‹ይገርማል ከእርሱ አይጠበቅም፤ በጣም ገርሞኛል›› አለ፡፡ ሶቅራጦስም ይህ ሰው እንደማይለቀው ስለተረዳ አንድ መደራደሪያ አቀረበለት፡፡ ‹‹ስለ ወዳጄ ልትነግረኝ የፈለግከውን ልሠማው የምችለው ሶስት ጥያቄዎች አሉኝ፤ እነርሱን ስትመልስልኝ ብቻ ነው›› አለው፡፡ ሠውየውም ተስማማ፡፡ ‹‹የመጀመሪያው ጥያቄዬ የእውነት ጥያቄ ነው፡፡ ስለወዳጄ የሠማኸው መቶ በመቶ እውነት ነው ወይ?›› አለው፡፡ ሠውየውም፡- ‹‹መቶ በመቶ እንኳን እርግጠኛ መሆን አልችልም›› አለው፡፡ ➾ሶቅራሶቅራጦስም‹‹ልትነግረኝ የፈለግከው እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው ማለት ነው፡፡ እሺ ሁለተኛው ጥያቄዬ የመልካምነት ነው፡፡ የምትነግረኝ መልካም ነገር ነው ወይ?›› አለው፡፡ ሠውየውም፡- ‹‹እርሱማ መልካም አይደለም›› አለው፡፡ ➾ሶቅራጦስም፡- ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠና መልካም ያልሆነ ነገር ልትነግረኝ ፈልገሃል፡፡ እሺ ሶስተኛውና የመጨረሻው ጥያቄዬን ልጠይቅህ?›› አለው፡፡ ➠ሠውየውም፡- ‹‹እሺ›› አለ፡፡ ➾ሶቅራጦስም፡- ‹‹የምትነግረኝ ነገር ለእኔ የሚጠቅመኝ ነገር አለው ወይ?›› አለው፡፡ ➠ሰውየውም፡- ‹‹የለም›› ብሎ መለሠ፡፡ ሶቅራጦስም በመጨረሻ፡- ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፤ መልካም ያልሆነ፤ ለእኔ የማይጠቅም ነገር አልሠማም›› አለው ይባላል፡፡ ✍ስንቶቻችን ነን ሰው የሚነግረን ነገር እውነት፣ መልካምና ጠቃሚ መሆኑን አጣርተን የምንሰማው? ስንቶቻችን ነን ለሰው ቁምነገር ብለን ልንናገር ስንል ከሶስቱ አንዱን ማሟላቱን የምናረጋገጠው? አሁን እኮ ሰው ዝም ብሎ የተነገረውን ስለሚሰማ በቀላሉ እንደ እንስሳ የሚነዳ ሆኗል፡፡ ✍በየሶሻል ሚዲያው ላይ ፖስት የሚደረጉት ብዙዎቹ መረጃዎች እውነት ያልሆኑ፣ መልካምነት የሌላቸው እና ለእኛ ምንም ጥቅም የማይሰጡ ናቸው፡፡ ✍በተቃራኒው የውሸት መረጃዎች ሆነው ስንቱን ያጭበረበሩ፣ ሰይጣናዊ ርምጃ ለመውሰድ የሚገፋፉ ሆነው ሳለ ያለማቅማማት እንሰማቸዋለን፡፡ አሁን አሁን እውነት ከሚናገሩት ሰዎች በላይ በመርዝ የተለወሰ ውሸት የሚናገሩ ሰዎች የተሻለ ብዙ #ተከታይ አላቸው፡፡ መልካም መልካሙን ከሚሰብኩ ሰዎች ይልቅ የጥፋት ሰባኪዎች ብዙ ደጋፊ አላቸው፡፡ ፍለጠው/ቁረጠው ባዮች ናቸው የጀገኑት፡፡ እነሱን ማስቆም አይቻል ይሆናል፤ ነገር ግን እነሱን አለመስማት/አለመከተል ቀላል ነው፡፡ እነዚህን የሶቅራጠስ 3ቱ ጥያቄዎችን እንደ ወንፊት ተጠቅመን ማጣራት ብቻ በቂ ነው፡፡ 💠💠 JOIN US 💠💠 @christ_mossion @christ_mossion @christ_mossion
Открыть в Telegram. 🚨በፍቅሩ የምትነኩበት ፀሎት😭 ━━━━━⊱✿⊰━━━ 💫በመንፈስ ሆናችሁ ይህን ፀሎት አብራችሁኝ ፀልዩ መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስን ፍቅር በልባችሁ ያፈሰዋል!🔥🔥🔥 🔸መልካሙ ሙሉጌታ .........……▪️•°○.................... 🚨 #ረሀቦን የሚጨምሩ #የፀሎት እና #የትምህርት ጊዜያትን በየእለቱ ለማግኘት አሁኑኑ ይቀላቀሉ👇👇 ✨ @christ_mossion ✨ ✨ @christ_mossion ✨ sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
"ቃለ እግዚአብሔር "@kaleegziabeherРелигия6,83 тыс.
🌹ኒቃቢስቷ ንግስት👑 🌹نحن السلفيين@nikabistuwanigistРелигия6,57 тыс.
አዶናይ@thedayofpentecostРелигия7,1 тыс.
ራዕይ ዮሐንስ 20 በልዩ ልዩ የዓለም ቋንቋዎች መልዕክቱን የሚያገኙበት@rayyohanes20Религия6,49 тыс.
Isaiah 48 Apologetics@thetriuneРелигия7,19 тыс.
Galmee Seenaa Qulqulloota!@qulqullootaРелигия7,2 тыс.
KENNAA@kennaapostРелигия6,34 тыс.
AbulAbasNasir (አቡል ዓባስ)@abulabasРелигия6,33 тыс.