Кабинет

Посты канала 🗣ወንጌል ለአለም ሁሉ

сначала новые

#8628Файл
Просмотры8230%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#8623Текст
Просмотры2 880+250%к среднему
Пересылки—
Реакции45
Комментарии—
#8622Текст
Просмотры2 570+212%к среднему
Пересылки—
Реакции17
Комментарии—
#8620Текст

✍️ ባልወድሽ ነው ወይ ** በቃ አይወደኝም ፣ ትያለሽሳ በቃ ጠልቶኛል ፣ ትያለሽሳ እስኪ መልሺ ፣ በይ ልጠይቅሽ በሀዘን ሳይሆን ፣ በመውደዴ አልቅሽ በይማ አንቺዬ...... ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ክብሬን መጣሌ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ መመሳቀሌ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ችንካር የበሳኝ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ስቃይ ያስገሳኝ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ መንገላታቴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ዝም ማለቴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ይማርሽ ያልኩት ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ግፍ የታገስኩት ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ውርደት መጥገቤ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ፍቅር ማንገቤ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ጥም ያነደደኝ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ አባቴ ያረደኝ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ልሙት ማለቴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ መቁሰል መድማቴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ሲዖል መውረዴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ግርዶሽ መቅደዴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ሞትን መርታቴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ድሉን መስጠቴ እስኪ መልሺ ፣ ልጠይቅሽ ቆይ ሁሉን መሆኔ ፣ ላንቺ አይደለም ወይ በቃ አይወደኝም ፣ ትያለሽ ምነው በቃ ጠልቶኛል ፣ ትያለሽ ምነው እንዲያ መሆኔ ፣ ባልወድሽን ነው በይ ራስሺን ፣ ጠይቂ ራስሽ እንድትመለሽ ፣ በገዛ መልስሽ በስስት አይኖች ፣ በማይዝሉ እጆች እንደ ውድ ሚስት ፣ ልክ እንደ ልጆች ዕቅፍፍፍፍፍ ያረገሽ ፣ ያቀማጠለሽ ሞትሽን ወስዶ ፣ በሞቱ ያዳነሽ አለሽ ወይ ሌላ ፣ እንዲህ 'ወዳጅ ሰው የሞተ ላንቺ ፣ በተደገሰው የሷን ሞት ልሙት ፣ ብሎ ያለልሽ ነፍሱ ላይ ቆርጦ ፣ የጨከነልሽ እና አይወድኝም ፣ ማለትሽ ምነው እኔ 'ምወደው ፣ አንቺን ብቻ ነው ስሚ ይልቅስ አድምጭኝማ ፣ ልንገርሽ ውዴ በአንቺነትሽ ፣ በሥራሽ ሳይሆን በ'ኔነቴ ነው ፣ አንቺን መውደዴ ይሄው ለዚህ ነው በቃ አይወደኝም ፣ እያልሽኝ እንኳን አንደምወድሽ ፣ መንገር 'ማይደክመኝ ባንቺ ተክዬ ፣ የፍቅሬን ድንኳን!! እወድሻለሁ❤❤❤❤❤ ገጣሚ #✍ሄኖክ_አሸብር✍

Открыть в Telegram
Просмотры2 610+217%к среднему
Пересылки—
Реакции27
Комментарии—
#8619Текст
Просмотры2 520+206%к среднему
Пересылки—
Реакции22
Комментарии—
#8618Текст

📚ራስን ማሸነፍ መኖር ስትጀምር ትልቁን እውነት መጋፈጥ ትጀምራለህ። ራስን ማሸነፍ የምናባዊ ስራ ውጤት ነው። እራስህን የማሸነፍ ጎዳናን የምትጀምረው ግዑዝ ከሆነው የሚታይ አለም ወጠህ የሀሳብ ፍልሚያ ወደሆነው ሜዳ ውስጥ ገብተህ ነው። ራስን ማሸነፍ የአስተሳሰብ ለውጥ ነው። ይህ የፍልሚያ ሜዳ መጉዳትና መጎዳት፤ ማሸነፍና መሸነፍ እንዲሁም መውደቅና መነሳት ያለበት ሚዛናዊ ስፍራ ነው። አድሎ ከእውነተኛ ማንነት ያፋታሃልና በዚህ ሜዳ አድሎ አትጠብቅ። ራስህን ለማሸነፍ የምትጀምረው ግጥሚያ ራስህን ወደ መሆን የታላቅነት ስፍራ ያወጣሃል! ራስህን መሆን ማለት አምላክ በራሱ አምሳል የፈጠረውን ንፁህ ማነነት ያለው ሰዎች አንዲሆን የሚፈልጉትን ሳይሆን አምላኩ አንዲሆን የሚፈልገውን ለመሆን የሚጥርና የተስተካከለ ስብዕና ያለውን ፍጥረታዊ ሰው መሆን ማለት ነው። ➲ራስህን እንዳትሆን ካንተ ጋር የሚፋለሙት ቂም፤ ጥላቻ፤ ከባድና የማይረሱ የሚመስሉ የህይወት አስከፊ ገፅታዎችና ቁስሎች ናቸው። ከነዚህ ሁሉ ጋር ታግሎ ለማሸነፍ የየእለት ልምምድ ይቅር ባይነትና አፍቃሪ ማንነት መሆን አለባቸው። ➲ራስህን ከመሆን ማንነት ምንም ነገር አያሰቆምህም ምክንያቱም ራስህን መሆን የተፈጠርክበት እውነት ነውና። ራስህን ሳትሆን ራስህን ለማሸነፍ መሞከር ደመናን ለመያዝ መድከም ነው። ራስን በመሆን ማንነት ውስጥ ራስን የማሸነፍ ድል ይገኛል። Share👇👇👇👇👇 @christ_mossion @christ_mossion @christ_mossion

Открыть в Telegram
Просмотры2 320+182%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#8581Текст

ወሳኝ የሆኑ የሶቅራጠስ 3ቱ ጥያቄዎች! ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ➜አንድ ሰው ወደ ሶቅራጠስ ሄዶ እንዲህ አለው፡፡ ‹‹ሶቅራጠስ ወዳጄ፣ እገሌ ስለተባለው ወዳጅህ የሰማሁት ደስ አይልም›› አለው፡፡ ሶቅራጦስ ግን ዝም አለ፡፡ ➠ሠውየውም እንደገና፡- ‹‹ይገርማል ከእርሱ አይጠበቅም፤ በጣም ገርሞኛል›› አለ፡፡ ሶቅራጦስም ይህ ሰው እንደማይለቀው ስለተረዳ አንድ መደራደሪያ አቀረበለት፡፡ ‹‹ስለ ወዳጄ ልትነግረኝ የፈለግከውን ልሠማው የምችለው ሶስት ጥያቄዎች አሉኝ፤ እነርሱን ስትመልስልኝ ብቻ ነው›› አለው፡፡ ሠውየውም ተስማማ፡፡ ‹‹የመጀመሪያው ጥያቄዬ የእውነት ጥያቄ ነው፡፡ ስለወዳጄ የሠማኸው መቶ በመቶ እውነት ነው ወይ?›› አለው፡፡ ሠውየውም፡- ‹‹መቶ በመቶ እንኳን እርግጠኛ መሆን አልችልም›› አለው፡፡ ➾ሶቅራሶቅራጦስም‹‹ልትነግረኝ የፈለግከው እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው ማለት ነው፡፡ እሺ ሁለተኛው ጥያቄዬ የመልካምነት ነው፡፡ የምትነግረኝ መልካም ነገር ነው ወይ?›› አለው፡፡ ሠውየውም፡- ‹‹እርሱማ መልካም አይደለም›› አለው፡፡ ➾ሶቅራጦስም፡- ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠና መልካም ያልሆነ ነገር ልትነግረኝ ፈልገሃል፡፡ እሺ ሶስተኛውና የመጨረሻው ጥያቄዬን ልጠይቅህ?›› አለው፡፡ ➠ሠውየውም፡- ‹‹እሺ›› አለ፡፡ ➾ሶቅራጦስም፡- ‹‹የምትነግረኝ ነገር ለእኔ የሚጠቅመኝ ነገር አለው ወይ?›› አለው፡፡ ➠ሰውየውም፡- ‹‹የለም›› ብሎ መለሠ፡፡ ሶቅራጦስም በመጨረሻ፡- ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፤ መልካም ያልሆነ፤ ለእኔ የማይጠቅም ነገር አልሠማም›› አለው ይባላል፡፡ ✍ስንቶቻችን ነን ሰው የሚነግረን ነገር እውነት፣ መልካምና ጠቃሚ መሆኑን አጣርተን የምንሰማው? ስንቶቻችን ነን ለሰው ቁምነገር ብለን ልንናገር ስንል ከሶስቱ አንዱን ማሟላቱን የምናረጋገጠው? አሁን እኮ ሰው ዝም ብሎ የተነገረውን ስለሚሰማ በቀላሉ እንደ እንስሳ የሚነዳ ሆኗል፡፡ ✍በየሶሻል ሚዲያው ላይ ፖስት የሚደረጉት ብዙዎቹ መረጃዎች እውነት ያልሆኑ፣ መልካምነት የሌላቸው እና ለእኛ ምንም ጥቅም የማይሰጡ ናቸው፡፡ ✍በተቃራኒው የውሸት መረጃዎች ሆነው ስንቱን ያጭበረበሩ፣ ሰይጣናዊ ርምጃ ለመውሰድ የሚገፋፉ ሆነው ሳለ ያለማቅማማት እንሰማቸዋለን፡፡ አሁን አሁን እውነት ከሚናገሩት ሰዎች በላይ በመርዝ የተለወሰ ውሸት የሚናገሩ ሰዎች የተሻለ ብዙ #ተከታይ አላቸው፡፡ መልካም መልካሙን ከሚሰብኩ ሰዎች ይልቅ የጥፋት ሰባኪዎች ብዙ ደጋፊ አላቸው፡፡ ፍለጠው/ቁረጠው ባዮች ናቸው የጀገኑት፡፡ እነሱን ማስቆም አይቻል ይሆናል፤ ነገር ግን እነሱን አለመስማት/አለመከተል ቀላል ነው፡፡ እነዚህን የሶቅራጠስ 3ቱ ጥያቄዎችን እንደ ወንፊት ተጠቅመን ማጣራት ብቻ በቂ ነው፡፡ 💠💠 JOIN US 💠💠 @christ_mossion @christ_mossion @christ_mossion

Открыть в Telegram
Просмотры8 730×11к среднему
Пересылки—
Реакции34
Комментарии—
#8557Голосовое
Просмотры7 450+805%к среднему
Пересылки—
Реакции12
Комментарии—
#8507Текст
Просмотры15 800×19к среднему
Пересылки—
Реакции29
Комментарии—
#8506Аудио
Просмотры8 950×11к среднему
Пересылки—
Реакции23
Комментарии—
#8505Голосовое

.        🙇‍♂ #በጥሞና_ጊዜያችን🙇‍♂         በህይወታችን የሚሆኑ #7                🔑ቁልፍ🔑ነገሮች             በ #መልካሙ_ሙሉጌታ .          ━━━━━⊱✿⊰━━━━━ ☑️ #ክፍል_3 ☑️ በጥሞና ጊዜዬ የጌታን ፈቃድ ስለ ትምህርቴ ፣ የፍቅር ህይወቴ እና ስለ ስራዬ እንዴት ማወቅ እችላለሁ?🤔 ☑️በመንፈሳዊ ህይወታችሁ ማደግ እና ጌታን አክብሮ መኖሮ የምትፈልጉ ሁሉ ልትሰሙት ይገባል!👆👆👆                                         ☑️ #ክርስቲያን_ወጣቶች ንቁ ራሳችሁን አስመልጡ ሰይጣን ተራ ሊያደርጋችሁ ነው‼️ ☑️በዚህ ትምህርት #መንፈስ_ቅዱስ በእያንዳንዳችሁ ህይወት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ያመጣል! ☑️ #በመንፈስ የተሞላ ትምህርት! 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 🚨 ለሀሳብ አስተያየት እንዲሁም ምስክርነቶቻችሁን ለማድረስ👇👇👇ይህን ይጠቀሙ @melke1211_bot ……………………………………………………… በ youtube ቻናሌም ቤተሰብ በመሆን አገልግሎቴን በስፋት ይከፋፈሉ 👇 https://www.youtube.com/channel/UC7n0Mo4O54Dj66zdQafnilQ Holy Tube Ethiopia                     ........................………………………… #ራስዎን_በቤትዎ_ይገንቡ                     ............▪️•°○.......................... ☑️ #ረሀቦን የሚጨምሩ #የፀሎት እና #የትምህርት ጊዜያትን በየእለቱ ለማግኘት አሁኑኑ ይቀላቀሉ👇👇👇  ✨ @christ_mossion✨  ✨ @christ_mossion✨ sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯

Открыть в Telegram
Просмотры7 800+848%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—
#8504Аудио
Просмотры7 790+847%к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—
#8503Голосовое
Просмотры6 500+690%к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—
#8502Фото

🚨#ውጤት_ለማየት_በመጠባበቅ_ላይ_ያላችሁ #እንዲሁም_ያያችሁ_ውድ_የአባቴ_ልጆች!! አንዲት ነገር ሹክ ልበላች ስሙኝማ " በየትኛውም አይነት መልኩ በህይወታችሁ የጠበቃችሁት ቀርቶ ያልጠበቃችሁት ቢሆን እንኳን አይዟችሁ ምንም አትሆኑም ምክንያቱም የህይወታችሁ #መልህቅ የሆነው ክርስቶስ ሁልጊዜም ቢሆን ከእናንተ ጋር ነውና!! ሀያላን አባታችሁ እግዚአብሔር ሁል ጊዜም ቢሆን ለእናንተ #ምርጥ አለው!! 🚨ጌታ ኢየሱስ ተኝቶበት ስፍራውን ሁሉ ተቆጣጥሮት ማዕበል ቢነሳ ወጀቡ እንዴት ይሰጥማል መርከቡ ( አይዞአችሁ ሁል ጊዜም ስለእናንተ የሚያገደው እርሱ ነገሮችን እንዴት ማመቻቸት እንዳለበት ያውቃል) " እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል። ትንቢተ ናሆም 1 : 7 🚨ውዶች ቀናት ሲያልፉ ወራት ሲደማመሩ እና አመታት ሲቆጠሩ በህይወታችሁ የሆነው ነገር ሁሉ ለበጎ እንደሆነ ያኔ ይገባችኋል። አሁን ላይ እየሆነ ባለው ነገር በፍፁም ልባችሁ እንዳይወርድ ለጠላታችሁም ክፍተት አትስጡት አትርሱ ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ!!   ✨#እግዚአብሔር_መልካም_ብቻ_ነው✨         ✨ #በእናንተ_ህይወት!!✨ 🚨እንዳወራችሁ እና እንድፀልይላችሁ የምትፈልጉ 👉 @melke1211_bot አውሩኝ። እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ወደ ሮሜ ሰዎች 8 : 28 እንዲህም አለ። ራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ነሣ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን። መጽሐፈ ኢዮብ 1 : 21 ✨ አገልጋይ መልካሙ ሙሉጌታ!✨ ✨ @christ_mossion✨ ✨ @christ_mossion✨

Открыть в Telegram
Просмотры6 320+668%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—
#8500Текст
Просмотры5 640+585%к среднему
Пересылки—
Реакции34
Комментарии—