ኅዳር ዐሥራ ሰባት ኅዳር ፲፯ (ኅዳር ዐሥራ ሰባት) የዓለሙ ሁሉ መምህር የሆነው የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ቅዱስ ሥጋው ከዕረፍቱ ከ፴፭ (ሠላሳ ዐምስት) ዓመታት በኋላ በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን፣ ወደ ቁስጥንጥንያ የፈለሰበት (የተዛወረበት) ዕለት ነው። . የአርቃዴዎስ ልጅ ታናሹ፣ ቴዎዶስዮስ በነገሠ ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ፣ . #የቅዱስ #ዮሐንስን ሥጋ በመዘመር እና በማመስገን በታላቅ ክብር ወደ ቍስጠንጥንያ አፍልሶ አስመጣው። . ይኽም ከዕረፍቱ በኋላ በሠላሳ አምስት ዓመቱ ነው። . የዕንቍ ፈርጦች ባሉት የዕብነ በረድ ሳጥን ውስጥ አድርገው፣ ወደ ቤተ መቅደስ አስገቡት፤ . ከሥጋውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተኣምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይኹን፤ እኛንም በዚኽ በከበረ አባት ጸሎት ይማረን፤ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር፤ ለዘለዓለሙ አሜን።
Открыть в Telegram
ቤተ መጻሕፍት
"መጻሕፍት፡ ለሰው ልጅ መድኀኒት የታዘዘባቸው የማዘዣ ወረቀት መኾናቸዉን ተገንዝባችኊ አንቡቧቸው።" ('ርጢን' ገጽ ፲፫)፧፧፧፧ የ'ቤተ መጻሕፍቱ' ሊንክ https://t.me/betemetsihaf ለማንኛውም አስተያየት https://t.me/getnetfekadu
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 30 окт. 2026 г. | 630 |
| 31 окт. 2026 г. | 752 |
| 7 нояб. 2026 г. | 672 |
| 21 нояб. 2026 г. | 401 |
| 26 нояб. 2026 г. | 146 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры916Пересылки—Реакции24Комментарии—
- 02Просмотры755Пересылки—Реакции18Комментарии—
- 03Просмотры692Пересылки—Реакции8Комментарии—
- 04Просмотры670Пересылки—Реакции14Комментарии—
Новые посты
#ቅድስትኄራኒ #ኹሌምየማልለይሽ #ጠባቂመልኣክሽ #ነኝ የሥራ ምድቤ፣ ከበኣቴ ራቅ ያለ ቦታ ነበር፤ ሌሊት በዐሥር ሰዓት ተነሥቼ፣ ሄጄ ሥራዬን ስሠራ እውልና፥ ማታ በዐምስት ሰዓት ወደ በኣቴ ስመለስ፣ ከባድ ድካም ና የሰውነት ዝለት እየተሰማኝ ነው። ልተኛ ስዘጋጅም፥ " አኹን እንዴት ብዬ ነው ለጸሎት መነሣት የምችለው? ቀሪው ሰዓቴ ለዕረፍት እና ለጸሎት በቂ ይኾናልኛል? " ብዬ አስባለኊ። እያንዳንዷ መነኲሲት፣ ያለ ቀስቃሽ ራሷ መነሣት ስላለባት፣ " ዕንቅልፍ ይጥለኝ ይኾን " ብዬም እጨነቃለኹ፤ ያኔ ጊዜ ሰዓትም ሆነ፣ ለነገህ ጸሎት የሚያነቃ ደውል አልነበረንም፤ ኾኖም ረድኤተ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነውና፣ ልክ ሲነጋ ሦስት ጊዜ " ኄራኒ ኄራኒ ኄራኒ! ተነሽ ጸልዪ " የሚለኝ ድምፅ እሰማለኊ። ታድያ ስነቃ የሚሰማኝ ለአራት ብቻ ሳይኾን ለስምንት ሰዓታት እንደተኛው ሆኖ ነው። ልክ ከዕቅልፌ ነቅቼ ዐይኖቼን ስገልጥ፣ ከበላዬ ሊቀ መላእክት ይታየኛል፤ ከነቃሁ በኋላ ደግሞ፣ በመኝታዬ ግርጌ በኲል ይዞርና ይቆማል፤ ልክ ከአልጋዬ ስወርድ ይሰወራል። ከዚህ በኋላ ምንም ዐይነት ድካም ሳይሰማኝ ጸሎቴን አደርሳለኹ፤ በዚህ ሁኔታ በየዕለቱ በተመሳሳይ ሰዓት እና መንገድ መልኣኩ ያነቃኛል፤ አንድ ቀን አንተ ማን ነኽ ስለው "እኔ ኹሌም የማልለይሽ ጠባቂ መልኣክሽ ነኝ" አለኝ። [ ዝክረ ቅዱሳት አንስት ዘተዋሕዶ ቅጽ ፩፤ ትርጒም በአዜብ በርሄ፤ ገጽ ፻፶፬/154፤ ፳፻፰/2008 ዓ.ም. ]
Открыть в Telegram#ቅድስትኄራኒ . ራሷን ዝቅ ስለ ማድረጓ እና ስለ ትሕትናዋም፣ ብዙዎች ተማርከዋል፤ ብዙዎችም መስክረውላታል። . እግዚአብሔር ድክመቷን እና ታናሽነቷን ተመልክቶ ብቻ፣ ክብሩን በርሷ እንደሚገልጥ እንጂ፣ ከርሷ የኾነ አንዳች ነገር እንደሌለ በንጹሕ ልብ እና አንደበት ትናገራለች። . ሊያወድሳት ወይም ምስጋና ሊያቀርብላት የሚያስብ ሰው ካለ "በፍቅሩ የያዘንን የሰማዩን አምላካችንን አመስግኑ" በማለት ራሷን ከውዳሴ ከንቱ ታሸሻለች። . ይኽ ኹሉ የሚያሳየው፦ የማያልቅ ጸጋው አብዝቶ እንደ ሰጣትና፣ ርሷም ይኽነን መክሊቷን፣ በግብርም(በሥራም) በቃልም ለኹሉ እንደምታካፍል ነው።
Открыть в Telegram#ቅድስትኄራኒ . የልቧ ንጽሕና፣ ለሰዎች የምታሳየው አክብሮት፣ ራሷን ዝቅ ማድረጓ፣ እያንዳንዷ እንቅስቃሴዋ እና ንግግሯ ኢየሱስ ክርስቶስን ይሰብካል። . ... ድምጿን የሰማ ኹሉ፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ይሳባል። . ኹሉን በፍቅር የሚቀበል ፈጣሪም፣ ወደ ቤቱ ያስገባቸዋል፤ በዚኽም እግዚአብሔር ይወደሳል፤ ይመሰገናል። 🔆💡#የገዳምመብራት፣ #እማሆይኄራኒ በረከቷ፣ ፍቅሯ፣ ምልጃዋ፣ .... በእውነት ይደርብን
Открыть в Telegramእንኳን ለተወዳጇ ለቅድስት ኄራኒ እረፍት አደረሳችኹ። ስለ ቅድስት ኄራኒ ሕይወቷን፣ ተጋድሎዋን፣ ... እያነሣሣን እንዘክራት። መልካም ቀን ይኹንላችኊ።
Открыть в Telegramጉባኤ አርድእት ዐውደ ተዋስኦ ዕለተ ቀዳሚት ጥቅምት ፳፩ ቀን ፳፻፲ወ፱ ዓመተ ምሕረት ጊዜ ሠርክ (ምሽት)፦ ፲፩ - ፩ (11:00 - 1:00) ቦታ፦ በተምሮ ማስተማር ሰንበት ት/ ቤት አዳራሽ ⏱️ : በሰዓቱ ስለምንጀምር፣ እባክዎ ሰዓት አክብረው ቢገኙልን። በዕለቱ ከፍልስፍናዊ ይዘት ውጪ ማንኛውንም ያሎትን ጥያቄ መጠይቅ ይችላሉ፤ አስተዳላዊ:- በተምሮ ማስተማር ሰንበት ት/ቤት በትምህርት ሥራ አስፈጻሚ የአብነት እና አርድእት ት/ት ክፍል
Открыть в Telegramአንድ ሰው በቁጣ ሲናገር፣ በውስጡ የቆሰለ እና የታመመ ነፍስ እንዳለው ተረዳ እንጂ፣ አንተም በቁጣ አትመልስለት፡፡ የታመመ ሰው በሕመሙ ብዛታ፣ ቃሉ ቢመርበት አትፍረድበት፤ ይልቁንም በይቅርታ እለፈው፡፡ ቁጣን በቁጣ መመለስ፡ የራስን ሰላም አሳልፎ ለጠላት መስጠት ነው፡፡ [ቅዱስ ባ ስልዮስ ዘቂሣርያ]
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
ፍሬ ሃይማኖት@frehaymanoteРелигия1,9 тыс.
ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus 2009@daewaselefiyaarbaminchРелигия1,89 тыс.
ተውጂሃት ሊል ሙእሚናት...🌹@tewjihatРелигия1,92 тыс.
ኒሳኡል መሻሪዕ@nisaulmesharieРелигия1,86 тыс.
abduleaziz ali@abduleazizaliРелигия1,99 тыс.
Ibn Yahya Ahmed@ibnyahya777Религия1,72 тыс.
AMU ግቢ ጉባኤ ቤተ-መፅሀፍት@gebigubae_libraryРелигия1,65 тыс.
💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!@tibyaan54Религия1,62 тыс.