🚨 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አክሱም የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከነገ ኅዳር 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር አስታወቀ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የቆየውን ወደ አክሱም ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ የበረራ አገልግሎት፣ ከነገ ዓርብ ኅዳር 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በድጋሚ የሚጀምር መሆኑን ይፋ አድርጓል። አየር መንገዱ በይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ፣ መደበኛ በረራው ዳግም መጀመሩን ለተጓዦች አሳውቋል። 📌 Ankuar News Network ለታመኑ እና ወቅታዊ መረጃዎች ቤተሰብ ይሁኑ! ልዩ መረጃዎችን ለወዳጅ ዘመድዎ ለማድረስ ቻናላችንን ሼር ያድርጉ 👇 👉 AnkuarNews.t.me 👉 AnkuarNews.t.me
Открыть в Telegram
አንኳር ዜና | Ankuar News Network
📌 Ankuar News Network | አንኳር ዜና የተረጋገጡ፣ ሚዛናዊና ፈጣን የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ የዜና መረጃዎች የሚቀርቡበት አምድ። • እውነተኛና ገለልተኛ ዜናዎች • ወቅታዊ የሀገራችን ጉዳዮች • ትንታኔዎችና አበይት ሁነቶች 📩 ለጥቆማ እና ማስታወቂያ፦ @MrTadios https://telega.io/c/AnkuarNews
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 25 нояб. 2026 г. | 5 563 |
| 26 нояб. 2026 г. | 4 239 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры5,73 тыс.Пересылки—Реакции33Комментарии—
- 02Просмотры5,57 тыс.Пересылки—Реакции39Комментарии—
- 03Просмотры5,56 тыс.Пересылки—Реакции39Комментарии—
- 04Просмотры5,55 тыс.Пересылки—Реакции50Комментарии—
Новые посты
🚨 ደቡብ ሱዳን፣ ኤርትራ፣ ሱዳንና ናይጄሪያ ለሕፃናት ሁለንተናዊ ዕድገት ምቹ ያልሆኑ የአፍሪካ ሀገራት ተባሉ በአዲስ አበባ መቀመጫውን ያደረገው የአፍሪካ የሕፃናት ፖሊሲ ፎረም ዛሬ ኅዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ይፋ ባደረገውና 52 የአፍሪካ ሀገራትን በመዘነ ሪፖርት፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኤርትራ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳን፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ካሜሩን እና መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ለሕፃናት ሁለንተናዊ ዕድገት አመቺ ያልሆኑ ሀገራት መሆናቸው ተመላክቷል። በአንጻሩ ሲሸልስ፣ ኬፕ ቬርዴ፣ ሞሪሸስ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቱኒዚያ እና ናሚቢያ ለሕፃናት ዕድገት ይበልጥ ምቹ በመሆን ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ያለውን ደረጃ የያዙ ሲሆን፣ ደቡብ ሱዳን በተከታታይ የመጨረሻውን ደረጃ ስትይዝ ሱዳን፣ ናይጄሪያና ቡሩንዲ ደረጃቸው ማሽቆልቆሉ ተገልጿል። «ለሕፃናት የተሟላ ዕድገትና ደኅንነት ቤተሰቦቻቸውን መደገፍ» በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ይህ ሪፖርት በአፍሪካ ቢያንስ አንድ የማኅበራዊ ጥበቃ ድጋፍ የሚያገኙት 19.1 በመቶ ገደማ ብቻ መሆናቸውን ጠቁሞ፣ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ቤተሰቦች ውስጥ ከሚኖሩና ዕድሜያቸው ከ2 እስከ 5 ዓመት ከሆኑ ሕፃናት መካከል 60 በመቶ የሚጠጉት የሚጠበቅባቸውን የአእምሮና አካላዊ ዕድገት እያሳዩ አለመሆኑን አስታውቋል። የፎረሙ ዋና ዳይሬክተር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) መንግሥታት ኃላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው ቤተሰቦች ከአቅማቸው በላይ ጫና ተሸክመው ሕፃናት ለጥቃትና ለእንክብካቤ እጦት መጋለጣቸውን ገልጸው፣ የአፍሪካ መንግሥታት ፖሊሲዎቻቸው ቤተሰቦችን ማዕከል ያደረጉ እንዲሆኑና ለአፈጻጸማቸው በቂ ሀብት እንዲመድቡ ጥሪ አቅርበዋል። 📌 Ankuar News Network ለታመኑ እና ወቅታዊ መረጃዎች ቤተሰብ ይሁኑ! ልዩ መረጃዎችን ለወዳጅ ዘመድዎ ለማድረስ ቻናላችንን ሼር ያድርጉ 👇 👉 AnkuarNews.t.me 👉 AnkuarNews.t.me
Открыть в Telegram🚨 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትግራይ የፖለቲካ ልሂቃን አሮጌውን የግጭት አካሄድ ትተው ፈጣንና ሰላማዊ ምርጫ እንዲደግፉ አሳሰቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ኅዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር፣ አንዳንድ የትግራይ የፖለቲካ መሪዎች ከጦርነቱ በኋላ የተጀመረውን የፖለቲካ ሂደት በመቃወምና የራሳቸውን ፖለቲካዊ ተፈላጊነት ለማራዘም ሲሉ በሕዝቡ ኪሳራ ግጭትን እያራዘሙ መሆኑን ገልጸዋል። እነዚህ አካላት ቀጣይነት ያለውን ታጣቂነትና የቅራኔ ምልክቶችን እንደ ጀግንነት በመቁጠር የትግራይን ወጣቶች በከፍተኛ ደረጃ እየሰዉ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መፍትሔው ፈጣን ምርጫ ማካሄድ መሆኑን አስገንዝበዋል። በመሆኑም የክልሉ የፖለቲካ ልሂቃን አሮጌውን የግጭት አካሄድ በመተው ሰላማዊ ምርጫን እንዲደግፉና የትግራይ ነዋሪዎች የራሳቸውን አመራር በነፃነት እንዲመርጡ ዕድል እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። 📌 Ankuar News Network ለታመኑ እና ወቅታዊ መረጃዎች ቤተሰብ ይሁኑ! ልዩ መረጃዎችን ለወዳጅ ዘመድዎ ለማድረስ ቻናላችንን ሼር ያድርጉ 👇 👉 AnkuarNews.t.me 👉 AnkuarNews.t.me
Открыть в Telegram🚨 ዜጎች በባንክ በኩል ቤት ገዝተው በየወሩ የሚከፍሉበት የሞርጌጅ ሥርዓት በቅርቡ እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ኅዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፣ የዜጎች የገቢ አቅም ውስን በመሆኑ በባንክ በኩል ቤት ገዝተው በየወሩ እየከፈሉ የሚኖሩበትን የሞርጌጅ ሥርዓት ለመዘርጋት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንና በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ አስታወቁ። በቤት ግንባታው ዘርፍ የቱርክ፣ የቻይናና የኮሪያ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ቤቶችን የሚገነቡ የፋብሪካ ሂደቶች እየተሞከሩ መሆናቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከ10 እስከ 15 ወለል ያላቸውን ሕንፃዎች መገንባትና በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ቪላ ቤቶችን ማምረት የሚችሉ ፋብሪካዎችን ወደ ሀገር ለማስገባት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ፋብሪካዎችን መግዛት፣ የግንባታ ግብዓቶችን ወደ ቦታው ማድረስና የፍሳሽ መስመርን ጨምሮ ተጓዳኝ መሠረተ ልማቶችን ማሟላት ተግዳሮት መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በሙከራ ግንባታዎች የታዩ ችግሮችን በመገምገም ማስተካከያ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል። 📌 Ankuar News Network ለታመኑ እና ወቅታዊ መረጃዎች ቤተሰብ ይሁኑ! ልዩ መረጃዎችን ለወዳጅ ዘመድዎ ለማድረስ ቻናላችንን ሼር ያድርጉ 👇 👉 AnkuarNews.t.me 👉 AnkuarNews.t.me
Открыть в Telegram🚨 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአርሲ ስለሚፈጸሙ ጥቃቶችና መንግሥት ስለወሰዳቸው እርምጃዎች በፓርላማ ማብራሪያ ሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ኅዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፣ በአርሲ አካባቢ ንጹሐን ዜጎች ሲገደሉ ሁሉም በጋራ ሊያወግዘው እንደሚገባና በጋራ በመታገል ጥቃት ፈጻሚዎችን ማጥፋት እንደሚቻል አስታውቀዋል። በአካባቢው የንጹሐንን ሕይወት ለመታደግ በርካታ ሚሊሻዎችና ፖሊሶች መስዋዕትነት መክፈላቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለእነዚህ የጸጥታ አካላት ተገቢው ዕውቅናና ምስጋና ካልተሰጠ ነገ ለሀገርና ለሕዝብ የሚቆም አካል ሊጠፋ እንደሚችል አሳስበዋል። መንግሥት የአካባቢውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት የአመራር ለውጥ ማድረጉንና ሕዝቡን በማወያየት የማስታጠቅ ሥራ መሥራቱን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ መንግሥት በሁሉም ቦታ በአንድ ጊዜ መገኘት ስለማይችል ሕዝቡም ራሱን በመጠበቅ ረገድ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። 📌 Ankuar News Network ለታመኑ እና ወቅታዊ መረጃዎች ቤተሰብ ይሁኑ! ልዩ መረጃዎችን ለወዳጅ ዘመድዎ ለማድረስ ቻናላችንን ሼር ያድርጉ 👇 👉 AnkuarNews.t.me 👉 AnkuarNews.t.me
Открыть в Telegram🚨 ሕገ መንግሥቱን ቀዶ ከመጣል ይልቅ የሚስተካከሉ አንቀጾችን አሻሽሎ ማቅረብ ይመረጣል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ኅዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፣ በሥራ ላይ ያለውን ሕገ መንግሥት እንደቀደሙት ሥርዓቶች ቀዶ እንደ አዲስ ከመጻፍ ይልቅ ጠቃሚ ሐሳቦችን ጠብቆ የሚስተካከሉትን ማሻሻል የተሻለ አማራጭ መሆኑን አስታወቁ። በተለይም በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 ላይ የተካተተው የብሔረሰቦች በቋንቋቸው የመጠቀምና ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ሊከበር እንደሚገባ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የመገንጠል ጉዳይ ግን መስተካከል እንዳለበት አመልክተዋል። ከሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጋር የተያያዘው የባለሙያዎች ሥራ መጠናቀቁን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ቀጣዩ ሂደት በምክክር ተጠናቆ ለሕዝብ እንደሚቀርብ ገልጸዋል። 📌 Ankuar News Network ለታመኑ እና ወቅታዊ መረጃዎች ቤተሰብ ይሁኑ! ልዩ መረጃዎችን ለወዳጅ ዘመድዎ ለማድረስ ቻናላችንን ሼር ያድርጉ 👇 👉 AnkuarNews.t.me 👉 AnkuarNews.t.me
Открыть в Telegram🚨 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሀገሪቱ እየተባባሰ የመጣውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና የንጹሐን ግድያ አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥያቄ አቀረቡ ዛሬ ሐሙስ ኅዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም በተካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ተወካይ ዶ/ር አወቀ ሀምዛዬ እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አዴን) ተወካይ አቶ ገብረመስቀል አደመ፣ በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸመ ያለውን የንጹሐን ግድያና መፈናቀል አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን አንስተዋል። ዶ/ር አወቀ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ግኝቶችን ዋቢ በማድረግ፣ በመንግሥት ኃይሎች፣ በታጣቂ ቡድኖችና በተለያዩ አንጃዎች በሚፈጸም ግድያና ዘረፋ ምክንያት በአማራ፣ በኦሮሚያ (ወለጋ፣ አርሲ፣ ሞያሌ)፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ (ሶዶና አበሽጌ) እንዲሁም በኮሬና ቡርጂ ዞኖች የዜጎች በሕይወት የመኖር መብት አደጋ ላይ መውደቁን ገልጸዋል፤ በተለይም የኮሬ ሕዝብ ላለፉት 11 ዓመታት የህልውና አደጋ ተጋርጦበት መቆየቱን በመጥቀስ መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። አቶ ገብረመስቀል አደመ በበኩላቸው በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም በአርሲ የተፈጸመውን ጥቃትና መፈናቀል ጨምሮ በአማራ፣ በኦሮሚያና በትግራይ ያለውን የጸጥታ መደፍረስ አንስተው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየአካባቢው ያለውን የመንግሥት አስተዳደራዊ መዋቅር እንዲፈትሹ፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው እንዲመልሱና በወንጀለኞች ላይ ፈጣን ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ አሳስበዋል። ከጸጥታና ከሰብአዊ መብት ጉዳዮች በተጨማሪ ሌሎች የምክር ቤቱ አባላት የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክትን፣ የታክስ ማሻሻያዎችን፣ ሙስናን፣ የቱሪዝም ፕሮጀክቶችንና ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት የተመለከቱ ጥያቄዎችን ማቅረባቸው ተመላክቷል። 📌 Ankuar News Network ለታመኑ እና ወቅታዊ መረጃዎች ቤተሰብ ይሁኑ! ልዩ መረጃዎችን ለወዳጅ ዘመድዎ ለማድረስ ቻናላችንን ሼር ያድርጉ 👇 👉 AnkuarNews.t.me 👉 AnkuarNews.t.me
Открыть в Telegram🌴ኮንቬንሽን ሴንተር ከባለ1-ባለ3 ከቴምር ፕሮፐርቲስ✨ 🌴ከ73 እስከ 145ካሬ ከ5,365,500ብር አጠቃላይ ክፍያ ጀምሮ መኖሪያ ቤቶችን በ40/60 አከፋፈል ዘዴ እየሽጥን እንገኛለን። 📍40 ፐርሰንቱን ብቻ አሁን ከፍላቹ ቀሪውን 60 ፐርሰንት ያለ ምንም የዋጋ ጭማሪ የቤታችሁን ካርታ እና ቁልፍ ስትረከቡ የምትከፍሉበት አማራጭ አዘጋጅተናል። 100% መክፈል የምትፈልጉ ደንበኞች የ30% ቅናሽ ከሼባ ማይልስ ስጦታጋ ይጠብቃችሗል✈️🔥 ለበለጠ መረጃ ብስራት ብለው ይደውሉ! ☎️ 09-98-04-18-67
Открыть в Telegram🚨በግብፅ ካይሮ በነዳጅ መኪና ላይ በተነሳ እሳት ቢያንስ 21 ሰዎች ህይወታቸውን አጡ በአደጋው ቢያንስ 15 ሰዎች መቁሰላቸውን የግብፅ ጤና ሚኒስቴር ለስፑትኒክ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። የቆሰሉት ሰዎች በካይሮና ጊዛ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች ሕክምና ማግኘታቸውን የግብፅ ቀይ ጨረቃ ገልጿል። ለታመኑ እና ወቅታዊ መረጃዎች ቤተሰብ ይሁኑ! ልዩ መረጃዎችን ለወዳጅ ዘመድዎ ለማድረስ ቻናላችንን ሼር ያድርጉ 👇 👉 AnkuarNews.t.me 👉 AnkuarNews.t.me
Открыть в Telegram🚨 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ለመስጠት በጉባኤው ተገኙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ኅዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም በተካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው፣ የምክር ቤቱ አባላት የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ማድመጥ ጀምረዋል። ውይይቱ ያተኮረው ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን ባቀረቡት የመንግሥት ዓመታዊ ዕቅድ ዙሪያ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአባላቱ ለሚነሱ ጥያቄዎች ዝርዝር ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። 📌 Ankuar News Network ለታመኑ እና ወቅታዊ መረጃዎች ቤተሰብ ይሁኑ! ልዩ መረጃዎችን ለወዳጅ ዘመድዎ ለማድረስ ቻናላችንን ሼር ያድርጉ 👇 👉 AnkuarNews.t.me 👉 AnkuarNews.t.me
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
DW Amharic@dw_amharicНовости и СМИ56,8 тыс.
ሰሌዳ | Seleda@seledadotioНовости и СМИ53,6 тыс.
Zehabesha@zehabeshanewsНовости и СМИ53,5 тыс.
BBC News Afaan Oromoo@bbcafaanoromooНовости и СМИ51,5 тыс.
Muktarovich Ousmanova@muktarovichousmanovaНовости и СМИ59,5 тыс.
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ@sputnik_ethiopiaНовости и СМИ50,8 тыс.
4-3-3 World News@ethionews433Новости и СМИ50,3 тыс.
"ኡማ ቲቪ " Tv@ethioomahtvchannleНовости и СМИ44,3 тыс.