ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ከማረፉ በፊት ምን ተፈጠረ? ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በወልቂጤ ከተማ ጉብሬ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የዘቢዳር ቢራ ፋብሪካ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በተጋባዥ ድምፃዊነት በተገኘበት ወቅት ማረፉን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል። የቅርብ የሥራ አጋሮቹ ለዳጉ ጆርናል እንደገለጹት፣ ሚኪያስ በዕለቱ ጠዋት ከሙዚቃ ሥራው በፊት ሕመም እየተሰማው እንደነበር ለአጋሮቹ ተናግሮ ነበር። ሆኖም የመድረክ ሥራውን ለመወጣት በማሰብ ሁለት ሙዚቃዎችን ለማቅረብ ወደ መድረክ ወጥቷል። በመድረክ ላይ ሙዚቃውን እያቀረበ ሳለ ራሱን ሊስት ሲቃረብ፣ በአጠገቡ የነበረ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች ደግፎ ይዞታል። ከዚያም ከመድረክ እንዲወርድ ተደርጎ ወደ አቅራቢያው የጤና ማዕከል ተወስዷል። አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ለመስጠት ጥረት ቢደረግም ሕይወቱን ማዳን አልተቻለም። ዳጉ ጆርናል እንደገለጸው፣ የዕረፍቱን መረጃ ቤተሰቦቹ እስኪያውቁ ድረስ ይፋ ሳያደርግ ቆይቷል። ለድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና አድናቂዎች መጽናናትን እንመኛለን። ምንጭ፦ ዳጉ ጆርናል
Open in Telegram
ጣና ሚዲያ Tana Media
ጣናዊነት አዳማዊነት ኖኃዊነት!!! https://telega.io/channels
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 16, 2026 | 775 |
| Nov 22, 2026 | 491 |
Latest posts
"እኔም ለወገኔ" We Stand for Humanity! Join the Global Fundraising Telethon Organized by the Coalition of Amhara Associations in America (CAAA). 🗓 Dates: November 28–29, 2026 ⏰ Time: 10:00 AM EST (Live Online & On TV) Amhara Guard invites all its followers, collaborators and partners to participate in the fundraising event that is organized by the Coalition of Amhara Associations in America (CAAA). Amhara Guard is a member of CAAA and endorses the effort CAAA is undertaking to alleviate the suffering Amhara people are facing due to war and genocide.
Open in Telegramየፈረንሳይ አቢዮት ከተነሳ አይቀር... 1787 ላይ የነበረው የፈረንሳይ አቢዮትን በተመለከተ ኦሾ አንዲት መፅሐፉ ላይ ያሰፈራት ተረክ አለችው። በርግጥ የታሪክ መዛግብት ከፃፉት በእጅጉ ይለያል... "ንጉስ በቃን፤ አሁንስ በዛ! " በሚል የተነሳው አብዮት ተቀጣጥሎ አቢዮተኞቹን ከአደባባይ "ባስቲል" ወደ ተባለ እስር ቤት አደረሳቸው። ባስቲል ሰዎች ገብተው የማይወጡበት እና በየእስረኞች እጅና እግር ላይ ሰንሰለት የሚቆለፍበት እስር ቤት ነው። እዚህ እስር ቤት የገባ ሰው የሚወጣው ሬሳ ሆኖ ብቻ ነው... እናማ እስረኞች ሰንሰለትና ጨለማን አለማቸው አድርገው ሞታቸውን ይጠባበቃሉ። የፈረንሳይ አብዮተኞች ታዲያ የአደባባዩን ሲጨርሱ እስረኞቹን ሊያስለቅቁ እስር ቤቱን ሰብረው ገቡ፤ እስረኞቹንም ከነሰንሰለታቸው ሲንከሻከሹ አገኟቸው። በስኬታቸው እየተፍነከነኩ "በሉ ውጡ፤ ነፃነታችሁን አግኝታችኃል" አሏቸው:: እስረኞቹ መጀመሪያ ደነገጡ፤ ከዚያ ማልቀስ ጀመሩ። አብዮተኞቹ ግራ ገባቸው... "ለቅሶው የደስታ ነው? " እስረኞቹ ከእንባቸው ጋር ተንበርክከው ይለምኑ ጀመር:: "ውይ ሰንሰለቱን እንድንፈታላቸው ይሆናል" አሉና ቁልፍም ሳያስፈልጋቸው ሰንሰለቱን በመጥረቢያ ቆረጡላቸው... የእስረኞቹ ለቅሶና ጩኸት ግን ባሰ... "እኛ መውጣት አንፈልግም... የእኛ አለም ይሄ ነው ፤ እግራችን መራመድ የሚችለው በሰንሰለቱ ልክ ነው፤ አይናችን የሚያውቀው ጨለማን ነው፤ በብርሀን አይናችንን ልታጠፉት ነው እንዴ?" አሉ። አብዮተኞቹ ትዕግስታቸው ተሟጠጠ... ሲጀምር በአንድ ጊዜ ትዕግስተኛ እና አብዮተኛ የሆነ ሰው በአለም ላይ የለም። ትዕግስቱን ጨርሶ ነዋ አብዮተኛ የሚሆነው.... "አይ በጣም ተሞላቀቃችሁ..." አሏቸውና እየጎተቱ ማስወጣት ጀመሩ። አስበኸዋል ሰው ከእስር ቤት ተጎትቶ ሲወጣ? ብቻ በትነዋቸው እስር ቤቱን ቆልፈው ሄዱ። በማግስቱ... እስረኞቹ ከየሄዱበት ተመልሰው እስር ቤቱ ጋ ተኮልኩለው ተገኙ። አብዮተኞቹ "እንዴ ጤነኞች አይደላችሁም እንዴ?" "እናንተ ከዚህ እስክታስወጡን ጤነኛ ነበርን፤ ስንወጣ ነው ያመመን" "ቆይ ምን ሆንን ነው የምትሉት?" "ምንም! መልሳችሁ አስገቡን፤ ሰንሰለቱንም መልሱልን... እኛ የሰንሰለቱ ክብደት ሳይጫነን እንቅልፍም አይወስደን..." አብዮተኞቹ አንገታቸውን ነቅንቀው እያዘኑ ወደ እስር ቤታቸው መለሷቸው። ያው አንዴ በሆነ ነገር አትታሰር ለማለት ነው ታሪኩን የነገርኩህ... ገመድህን ከለመድከው፣ እግርና እጅህን ለሰንሰለቱ እያስማማህ ከኖርክ፣ ሰንሰለቱን አምባር ማጌጫ ነው የምታደርገው... ሰንሰለትህን ቢያወልቁልህ ጌጥህን እንደተነጠቅህ መጮህህ ተጠባቂ ነው... ጌታዬ የአሜሪካ የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት አብርሃም ሊንከንን ለአሳዳሪዎቻቸው ተደርበው የወጉ ጥቁሮች አሉ አሉ እኮ... 'ከአሳዳሪዎቻችን አስወጥቶ ምናባቱ ሊያደርገን ነው?' ብለው ማለት ነው በእርግጥ ይሄንንም የተሰነዱ የታሪክ መጻሕፍት ላይ አታገኘውም... በአፍ የሚነዳ ታሪክ ላይ እንጂ... ብቻ ዋናው ነገር ነፃነት ተሰፍሮም ተዘግኖም ቢሰጥህ ዋጋ የለውም:: መጀመሪያ የምትወስድበትን ከረጢት ሰፍተህ ካላዘጋጀህ ልልህ ነው። #everyonefollowers #viralpost ©️Etsegenet Kebede
Open in Telegramየሰው ክብደት የሚመዘነው ለእኛ በሆነልን መሆን አይደለም... ለሌላውም በሚያሳየው ልኩ እንጂ... መንግሥትም እንደዛው... ድህነቴን ታሪክ አደረገልኝ ተብሎ "ድህነትን ታሪክ አድራጊ መንግስት" አይባልም፤ አንድ ሰው ምሳ ጋበዘኝ ተብሎ " ውይ...እሱ እኮ ደግ ነው፤ ከበር መልስ እኮ ነው የሚጋብዘው..." እንደማይባለው... ማለቴ ነው:: በጥቅማችሁ ሚዛናችሁን ባትቀያይሩ...🤨 ይቅርታ ተመላለስኩባችሁ🙄😁 ©️Etsegenet Kebede
Open in Telegram🕊 🌺 🕊 💛 [ በመስቀሉ ገነትን ከፈተ ! ] 💛 🕊 🌺 🕊 ❝ ተስፋ ላጡ ተስፋ የሆነው መስቀል ለዓለም ሁሉ ሕይወትን አስገኘ ፣ ለምናምን ለኛ ደስታችን ነው ፣ ለነገሥታት ታላቅነታቸው ግርማቸው ነው ፣ የቤተ ክርስቲያን መሠረት የባሕር መረጋጋት ለመርከቦች ወደብ ነው መስቀል። በመስቀሉ ገነትን ከፈተ ፣ በመስቀሉ መድኃኒትን አደረገ ፣ [ በመስቀሉ ] አጋንንትን አባረረ ፣ ከመስቀሉ ወርዶ ቤዛ ሆነን ፣ ለዕረፍትም ሰንበትን መሠረተ። ❞ [ ድጓ ዘዮሐንስ ] 🕊 🕊 ❝ በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል።❞ [ ቆላስ.፪፥፲፬ ] ❝ በመስቀሉም ደም ሰላምን አደረገ ፤ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ አስታረቀ ❞ [ ቆላ.፩፥፳ ] እንጎሮጎባሽ!!! እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!!! 🌸 🌸 ††† ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊 💖
Open in Telegram"ወትባርክ አክሊል ዓመተ ምሕረትከ ፥ በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ መዝ. ፷፬፥፲፩ እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ማርቆስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ሉቃስ፣በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን። 🙏 እንቁጣጣሽ 🌻🌼🌻 #ምርቃት በሰለሞን አያሌው እነሆ፦ -ዓመቱ ግጥማችን ይሁን፤ -ሆሳው ይነሳ፤ -እማይበጀን ገለል ይበል፤ -ለከርሞው በአማን ያድረሰን፤ -ለአገርና ለህዝብ ደግደጉን ያምጣልን፤ -እንደበሬ ሻኛ ከሰው በላይ ያውላችሁ፤ -የእድሜ ጎዳና ይስጥልን፤ -አገሩ ጥጋብ ቀየው ሰላም፤ -አበባውን ፍሬአማ ያድርግልን፤ አሜን!!! መልካም ዘመን መልካም አዲስ ዓመት። ይኩን💚💛❤ይኩን!!!
Open in Telegramሰላም እንዴት ናችሁ!! 👉#ለደብረታቦር ፬ቱ ጉባኤያት ቤተመጽሐፍት መጻሕፍትን እያሰባሰብን ስለሆነ ማንኛውም ሳይንሳዊ፣ፍልስፍናዊና ሃይማኖታዊ መጽሐፍት ድጋፍ ማድረግ ከፈለጋችሁ እንድታመጡልን ስል ጥሪየን አቀርባለሁ። 0927688782 -ደውሉልኝ ወይም በውስጥ ጻፉልኝ!!! 👏👏👏 💚💛❤
Open in TelegramConnections
Similar channels
Hule Addis Media ( HAM)@hulaadissNews and media2.07K
ግዮን-ፎረም@amarawiyanNews and media2.26K
Wanaw Media - ዋናው ሚዲያ@wanawmediaNews and media2.5K
ASCENTIG | TIGRAY@ascentigNews and media1.84K
Benjamin Media 📡🌎@jirraamalleeNews and media2.54K
ኮከብ ጋዜጣ@ethiozodiacNews and media1.82K
𝙱𝚄𝙻𝙱𝚄𝙻𝙰 𝙽𝙴𝚆𝚂⏰@bbn_infoNews and media2.63K
Biiroo Industiriifi Intarpiraayizii Oromiyaa@oromia_eibureauNews and media1.5K