ጭራሽ ሽልማት? (አሌክስ አብርሃም) መምህርነት ክቡር ሙያ ነው፤ በሕይወት ዘመኔ የሚገራርሙ ጥሩ መምህራን አጋጥመውኛል። ግን አንዳንድ ወንድ መምህራን የሆነ ነገራቸው ልክ አልነበረም። እስከአሁንም ባስታወስኳቸው ቁጥር ጤነኝነታቸውን እጠራጠራለሁ። በአጋጣሚ መንገድ ላይ እንኳን ሳያቸው ሰላም ላለማለት መንገድ አቋርጨ ነው የምሄደው። ደግሞ ሰው አይረሱም። "ቲቸር እንትኒት" የሚባል አስተማሪ ነበረን። "እንትኒት" የተባለው በሚጋረፍባት የእንጨት ብትር ስም ነው። እንደደህና ነገር ገና የመጀመሪያ ቀን ዱላውን በስም ለተማሪወች ያስተዋውቃል። ወጥ ማማሰያ የመሰለ ጫፏ ቀይ የተቀባ ብትር። መዳኒት ናት ምናምን እያለ ይሟዘዝና በአየር ላይ እንደሰይፍ እየሰነዘረ ያስቦካናል። የመጀመሪያ ቀን በቃ ይነጅሰናል። ከእኛ በፊት ያስተማራቸው "ዝናውን" ስለሚነግሩን ባያስፈራራንም ፈርተን ነው የምንጀምረው። ሌላውን ተውት ይሄ ሰውየ ገና መስከረም ላይ ሲገባ እንደሆስፒታል የሰርጀሪ አልጋ ከፊት ወንበር አንድ ጠረጴዛ ያመቻቻል። እዛ ጠረጴዛ ላይ የስንት ህፃን ቂ* በደረቅ እንጨት ሰንበር በሰንበር አድርጓል። ሴቶቹን መግረፍ ነፍሱ ነበር። በተለይ ደግሞ እታፈራሁን ካልገረፈ እንደሆነ ሱስ ያዛጋዋል። እታፈራሁ ሚስኪን የደሀ ልጅ ናት፣ ምን ሆንሽ ባይ የሌላት። ሁልጊዜ ፀጉሯ የሚንጨባረር (ቅጫም) ነው የሚላት ቅጫማም አይደለም... ቅጫም! አንድ ቀን ወላጅ አምጭ ተብላ እናቷን ይዛ መጣች...ገና አስተማሪው የቤት ስራ አትሰራም ከማለቱ እናቲቱ የእታፈርን ፀጉር ጨምድዳ "ስታርሽ ነው ስትጎለጉይ" እያለች ትቀጠቅጣት ጀመር ፣ ያ ክፉ አስተማሪ እንኳን "አቁሚ ህፃን አይደለች እንዴ" እስኪል። በነገራችን ላይ በቀጥታ ገርፎኝ አያውቅም ግን ዱላውና ትሮውማው በተዘዋዋሪ ደርሶኛል። አንድ ቀን ይችኑ እታፈራሁን ምን እንዳደረገች ትዝ አይለኝም (መልስ አልመለሽም ብሎ ይመስለኛል) እዛ ጠረጴዛ ላይ በሆዷ አስተኛት። ቀሚስሽን ግለቢ አለ (ሲሪየስ አሁን ይሄ ምንድነው) ልጅቱ ነፍሷ ተጨነቀ። ገና ሳትገረፍ ሽንቷን ለቀቀችው...እንደተደፋ የብርጭቆ ውሃ ሽንቷ ከጠረንጴዛው እየተንኳለለ ስሚንቶው ወለል ላይ ሲያርፍ ድምፁ እስከአሁን ይታወሰኛል። ፊት ወንበር ነበር እኔ የምቀመጠው። "ና አንተ " አለኝ። እየተንቀጠቀጥኩ ሄድኩ። "እዚህ ወገቧ ላይ ግጥም አርገህ ያዝ" አለና በብትሩ ጠቆመኝ። አጥንታም የህፃን ወገቧን ከተገለበ ቀሚሷ ጋር ያዝኩ ። ብቻ የመጀመሪያው ብትር እያፏጨ ሰውነቷ ላይ ሲያርፍና ደም የመሰለ መስመር ሲያጋድምባት ያች ትንሽ ፍጥረት የሷ በማይመስል ሃይልና ጩኸት ገፈታተረችኝ " ሁለተኛው ብትር ሲምዘገዘግና ያመለጠኝን የቀሚሷን ጫፍ ለመያዝ እጀን ስዘረጋ የብትሩ ጫፋ ትንሿ የቀኝ እጀ ጣት አንጓ ላይ አረፈ። ቋ ነው ያለው እንደረቅ እንጨት። ለአመታት ህመሙ ይሰማኝ ነበር ። በተለይ መዳፌን ስጨብጥ። እታፈራሁን ሁልጊዜ አስባት ነበር። የት ሄዳ ይሆን እያልኩ። ምንዱባንን ሳነብ እነ ኤፖኒን ፣አዜልማ፣ ኮዜትን ሁሉ በእርሷ እየተካሁ ትዝ ትለኝ ነበር። ሰውየው ያልገረፈው ህፃንና ያልተለማመደብን አገራረፍ የለም። አለኮ አባታዊ ቅጣት፣ የሆነ ፍቅር ያለው... ልጆች በባህሪም በትምህርትም እንዳይበላሹ መስመር ለማስያዝ ያህል ዘመኑ ይፈቅደው የነበረ ቅጣት። ይሄ ወንዶቹ ላይ ሃይላንድ ያላንጠለጠለብንም በዘመኑ ቅጣቱ ባለመለመዱ ይመስለኛል። በጣት መሃል እስክርቢቶ አስገብቶ ማጣበቅ፣ በማስመሪያ ጠርዝ የጣት ጫፍ መምታት፣ አስጎንብሶ ጆሮ ማስያዝ፣ ተማሪ ፊት ማዋረድ ፣ ጆሮን አፍንጫ ላይ የሚያመጣ ኩርኩም ማጋጨት፣ አይን የሚያንሸዋርር ድንገተኛ ጥፊ፣ በእንብርክክ ስሚንቶ ላይ ማስኬድ፤ በካልቾ መጠለዝማ በረከት ነበር.... ግርርርርም ያለኝ ባለፈው የድሮ ተማሪወቹ ተሰብስበው "ቲቸርን ልንሸልም ነው ተቀላቀለን" አሉኝ። ጭራሽ ሽልማት? ደግሞ በጣም የገረመኝ ሸላሚወቹን ሰብሳቢ ማን ብትሆን ጥሩ ነው? እታፈራሁ! "የቀለም አባታችን" ምናምን እያለች። ምኗ ቅጫም ናት አልኩ በንዴት😀
Open in Telegramኮከብ ጋዜጣ
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 21, 2026 | 746 |
| Nov 22, 2026 | 560 |
| Nov 23, 2026 | 486 |
| Nov 24, 2026 | 414 |
Most viewed this month
- 01Views793Forwards—Reactions29Comments—
- 02Views698Forwards—Reactions27Comments—
- 03Views595Forwards—Reactions14Comments—
- 04Views526Forwards—Reactions26Comments—
Latest posts
አያ ሙሄ [በውቀቱ ስዩም] አያ ሙሄ የተባለ ገበሬ ልጁ ሞቶበት ፥ ጎጆው በርንዳ ላይ ኩርትም ብሎ ይቆዝማል። ባለንጀራው አዋ ይመር አጠገቡ ተቀምጧል። አዋ ይመር ወዳጁን በቃል ማጽናናት በቂ ሆኖ አላገኘውም። የወዳጁን ልጅ የቀሰፈውን ፈጣሪ ለመበቀል ስለፈለገ ፥ ጠመንጃውን አነጣጥሮ ወደ ሰማይ ተኮሰ፤ ተኩሱ በረድ ሲል ሀዘንተኛው አያ ሙሄ ወዳጁን እያየ እንዲህ አለ :- “ካገኘከው ገላገልኸን፤ ከሳትኸው ግን አስፈጀኸን” 🙂
Open in Telegramየኛ ፖለቲካ የብሄር ሆነ ብለህ ሰፍ ብለህ ዘርህን መቁጠር ስትጀምር እጥፍ ይልና የሀይማኖት ይሆናል። በቃ አርፌ ሀይማኖቴ ላይ መረር ልበል ከብሄሩ እሱ ይሻላል ስትል ደሞ መልሶ የብሄር ይሆናል። በዚህ ምክንያት ህዝቡ ጠቅላላ ቶክሲክ ሪሌሽን ላይ ነው ያለው። በብሄር ተጣልቶ ብሎክ ይደራረግና መልሶ በሀይማኖት ጉዳይ አንድ ሲሆን ፎሎው ይደራረካል። ከዛ ድጋሜ ብሎክ... ፎሎ ያረገኛል አንፎሎ ያረገኛል ፖለቲካ።
Open in Telegramአከራይ ተከራይ ሲባል ምንጊዜም ትዝ የሚለኝ አስቂኝ ነገር... (አሌክስ አብርሃም) አንድ ሰፊ የግለሰብ ግቢ ውስጥ ተከራይቸ እኖር ነበር። ብዙ ነበርን ተከራዮቹ ፤ ከእኔ ቤት ቀጥሎ የሚኖረው ተከራይ አንድ አስተማሪ ሲሆን ቅዳሜ ቅዳሜ ብቻ ጢንቢራው እስኪዞር ከመስከርና "ገንዘብ አለያየን ደሃ በመሆኔ" እያለ ከመዝፈን ውጭ ሽቁጥቁጥ፣ የግቢውን በር እንኳን ሲያልፍ ጫማውን ሊያወልቅ የሚዳዳው ትሁት ሰው ነበረ። አንድ ቅዳሜ ግን ምናባቱ...ማለቴ ምን ጠጥቶ እንደመጣ እንጃ ግቢውን በአንድ እግሩ አቆመው። የሆነ ለማሽቃበጥ የሚረዳ መጠጥ ይመስለኛል የጠጣው። ገና ከመግባቱ "ሁላችንም ኪራይ መጨመር አለብን " ብሎ ጮኸ። "አከራዮቻችን ዝም ስላሉ ብቻ ዝም ማለት ልክ ነው? አይደለም! ቤት መስራት ብዙ ዋጋ ያስከፍላል ካርታ አለ...ፕላን አለ...ለመሃንዲስና ምናምን ጉቦ አለ...ብሎኬት አለ...ሲሚንቶ አለ...ለአከራይ ማን ያስብለት?... መሯቸው ሸጠውት ቢሄዱስ? እኔ ከነገ ጀምሮ ሃምሳ ብር ጨምሪያለሁ...ሁልሽም ኪራይ ጨምሪ...እንትና መቶ ብር...እንትና ስልሳ ብር ... አንተ አብርሃም ሰባ ብር ፣ የውሃም እኛ መክፈል አለብን.....(በቃ ይሄ ሰው ራሱን ሊያጠፋ ወስኗል ማለት ነው ብየ አሰብኩ) አከራያችን ጋቢያቸውን ለብሰው ብቅ አሉና እንደወትሮው "እንዲህ ከረበሽክ ከነገ ጀምሮ ቤት ፈልግ" ይሉታል ብለን ስንጠብቅ ፍቅር በሆነ ድምፅ "መምህር ና እራት ብላ እስቲ... " ወሬ ልመለከት ስንወጣ አከራየ ጋር እንደመጋኛ ተገጣጠምን። ወደእኔ እያዮ "የሚጠጣ ሰውኮ በሆዱ ክፋት የለም..." 🤔 እና ልጠጣልወት?
Open in Telegramበችግር ጊዜ የሚሸሹ የዞዲያክ ኮከቦችና ምክንያቶቻቸው እነዚህ ኮከቦች በተፈጥሯቸው አሉታዊነትን፣ ድብርትን ወይም ከባድ ሸክምን መሸከም አይችሉም። ማህበራዊ ክብራቸውን፣ ደስታቸውን ወይም ነፃነታቸውን ስለሚመርጡ ችግርህን ሲያዩ ሮጠው ያመልጣሉ። Gemini (ጀሚናይ) እና Sagittarius (ሳጁታሪየስ): ችግርህን መስማት አሰልቺና ነፃነታቸውን የሚነጥቅ ስለሚመስላቸው፣ Libra (ሊብራ) እና Leo (ሊዮ): ስምህ እና ክብርህ ሲወድቅ አብረው እንዳይጠለሹ በመፍራት፣
Open in Telegramበዚህ ሰዓት የሐይማኖት ሰወች ከአምላካቸው በላይ መንጋቸውን ያመልካሉ። ይህን ለማረጋገጥ ከፈለክ ብዙ መንጋ ያለውንና የሌለውን አነፃፅር። ባለብዙው የበዛ ኮንፊደንስ ሲኖረው ትንሽ መንጋ ያለው አንገቱን ደፍቶ ይቅለሰለሳል። መንጋው ሲበዛለት ተነስቶ ይደነፋል። መንጋ ያድናል፣ መንጋ ሀይል ነው፣ የሚመካ በመንጋው ይመካ ነው መንፈሱ። በዚህ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ የመንጋ እንጅ የሐይማኖት ፀብ አለ ብሎ ለማመን ይቸግራል። ሐይማኖት ከብሔርና ፖለቲካ ተዳቅሎ ዲቃላ ሐይማኖተኞችን ወልዷል።ዲቃላ በባህሪው መንገደኛው ሁሉ አባቱ ይመስለዋል። እናቱን ያገባ ሁሉ አባቱ ይመስለዋል። መንጋ የሐይል፣ መንጋ የገቢ ምንጭ ነው። አማኝ ሳይሆን መንጋ ማብዛት የሐይማኖቶች ዋና ስራ ሁኗል!! ((መንጋ)) በአምላኩ ስም ወደየትም የሚነዳ ግዑዝ የሰው ስብስብ ሲሆን ፣((አማኝ)) ግን በእምነት ወደአምላኩ ብቻ የሚራመድ ሰው ነው!
Open in Telegramአባ (በእውቀቱ ስዩም) አባ ገብረማርያም የአምሳ ስምንት አመት መነኩሴ ናቸው፤ አንድ ማታ፣ ከምሽቱ አምስት ሰአት ተኩል ላይ፣ የንስሀ ልጃቸው ለሆነቸው ወይንሸት ደወሉ፤ “ሀሎ! ወለተማርያም” “አቤት አባ” “ይቅርታ ተመሸ ደወልኩ” “በሰላም ነው አባ?” “ባለቤትሽ ቤት አለ፤? “የለም ፊልድ ወጥትዋል” “ልጆችስ ?” “ተኝተዋል” “በይ ያለሸበትን ክፍል በር ዝጊው” “እ! ዘጋሁት” “ስልክሽን በምን እጅሽ ነው የያዝሽው?” “በቀኝ እጄ ” “ወደ ግራ እጅሽ አዛውሪው” “ማለት ?” “በማንኩሳው ሚካኤል፤ በውስጠጉልቱ ጊዮርጊስ የምልሽን አድርጊ” “እሺ አንዳሉት አድርጊያለሁ” “በቀኝ እጅሽ እስኪብርቶ ይዘሽ ማስታወሻ ትመዘግቢልኛለሽ” “ምንድነው ?” “የሆነ ጊዜ ላይ ሎንዶን የመሄድ እድል ገጥሞኝ፣ ብሪትሽ ላይብራሪ ላይ ከመቅደላ የተዘረፉ ብራናዎችን ሳገላብጥ አንድ ጥንታዊ መጽሀፍ አገኘሁ፤ የመጽሀፉ አስራ ሰባተኛ ገጽ ተገንጥሎ ስመለከት ከነከነኝ ፤ አገር ቤት ስመለስ የብራናውን ቅጂ በየገዳሙ ማፈላለግ ጀመርኩ፤ በመጨረሻ ዲማ ውስጥ አገኘሁት፤ የሚገርምሽ መጽሀፉ በግእዝ የተጻፈ ቢሆንም የተገነጠለው ክፍል ለብቻው በጋፋትኛ ነበር የተጻፈው፤ ታድያ እኔ አባትሽ ጋፋትኛን ለአምሳት አመት አጥንቸ፤ ትርጉሙን ደረስኩበት” “ይቀጥሉ” “ያ ገጽ ታላቅ ምስጢር አዝሉዋል፤ ንጉስ ላሊበላ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሳጥን ሙሉ ወርቅ አልማዝ፤ ዩራኒየም ታንታለም እና ሌሎች የከበሩ ማእድኖችን አንድ ዋሻ ውስጥ አንደደበቀ ይጠቁማል ፤ ይህ ብቻ አይደለም ፤መቅደሶቹን የፈለፈለበት ማሽን ሳይቀር በዚያ ይገኛል፤ ማሽኑ ትልልቅ አለቶችን በቀላሉ አንደ እርሳስ መቅረጽ የሚችል ነው፤ እየሰማሽኝ ነው ?” “አዎ! ይቀጥሉ አባ!” “የብራናውን ጥቆማ መሰረት አድርጌ ስሄድ አገኘሁት፤ ዋሻው ተደብቆ የሚገኘው በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ የሚገኝ ተራራ ግርጌ ነው፤ ” “ይህንን ለኔ ለምንድነው የሚነግሩኝ አባ” አለች ወይንሸት፤ “ሰሞኑን ትንሽ ሲያመኝ አልነበር፤ አንድ የታወቀ ዶክተር ጋር ሂጄ ነበር ዛሬ ጠዋት! በቅርቡ! በሰአታት ጊዜ ውስጥ የመዘንጋት በሽታ አእምሮህን ይቆጣጠረዋል ብሎ አረዳኝ፤ እናም ትውስታየ ሳይከዳኝ ይህንን አገራችንን ከድህነት መንጥቆ የሚያወጣ ሚስጥር አንቺ ጋር ባደራ ላስቀረው ብየ ነው” አሉ አባ ትካዜ በተላበሰ ድምጽ፤ “እሺ የተራራው ስም ምንድነው አባ ?” አለች ወይንሸት፤ አባ በረጅሙ ተነፈሱና መለሱ፤ “የምን ተራራ;?” (ከምናለሽ ተራ እስከ ምንትሴ ተራራ ከሚለው ልብ ሰቃይ መፅሐፍ የተቀነጨበ)
Open in Telegramየምታውቁት እና የምወደው " ሲሪየስ"ቀልድ (አሌክስ አብርሃም) ፖይለቱ ሶስት ሰወችን አሳፍሮ በበረራ ላይ እያለ የአውሮፕላኑ ሞተር ስራ አቆመ። እና ለተሳፋሪወቹ "አዝናለሁ አውሮፕላኑ መከስከሱ ነው፣ እኛ አራት ነን፣ ያለን ግን ሶስት ፖራሹት ብቻ ነው፣ ስለዚህ አንድ ሰው መሞቱ ግድ ነው" አለና አንዱን ፓራሹት አዝሎ ዘለለ። ከሶስቱ አንዷ ተወርውራ አንዱን ፓራሹት አፈፍ አድርጋ በጀርባዋ አዘለችና "አዝናለሁ አገራችን ካሏት ጂኒየስና ስማርት ሰወች አንዷ እኔ ነኝ መሞት የለብኝም" ብላ ዘለለች። ቀሪወቹ አባትና የአስር አመት ልጁ ነበሩ። አባት በሐዘንና በፍቅር እንዲህ አለ " ልጀ እኔ በቂ ኑሪያለሁ አንተ ፓራሹቱን ይዘህ ሂድ ይቅናህ" ልጅ "ዳዲ ሁለት ፓራሹትኮነው ያለን ተመልከት" እውነትም ሁለት ነበር። አባት ተገርሞ "አንዱ ከየት መጣ? ሶስት ብቻ አልነበር ያለው ፓይለቱ?" ልጅ እየሳቀ " ልክነው ዳዲ! ሶስት ብቻ ነው፣ ግን ያች 'ጂኒየስና ስማርት' ሴትዮ ፓራሹት መስሏት የእኔን የትምህርት ቤት ቦርሳ ነው አዝላ የዘለለችው"😀 በእነዚህ ጥቂት ዓመታት ስንቱ ፓራሹት መስሎት ቦርሳችንን እየያዘ ዘለለ! ቦርሳችን ውስጥ የነበረ ፍቅርና እምነት አብሮ ቢወሰድም መሬት ያረፍን ቀን ተፈጥፍጦ የምናገኘው ብዛቱ። መቸስ ቦርሳችን አይፈጠፈጥ አቧራውን አራግፈን እናነሳዋለን። አሁን ሁላችንም አየር ላይ ነን! #Share
Open in Telegramዘመም ይላል እንጂ (በእውቀቱ ስዩም) እንደ ጊዜው መክፋት እንደ ግፉ መስፋት እንዳገሩ ክስመት እንዳገሬው ጥመት እንደሰው ጭካኔ፥እንደ ልቡ ፍሬ ታምር ነው መትረፍሽ፥ ታምር ነው መኖሬ:: የበጎ ሰው ሀሳብ፥ ሲካድ እለት በእለት ጉድጓድ ተምሶለት፥ ሰብእና ሲቀበር በዚህ ዓለም መኖር፥አያስመኝም ነበር :: ምድሩ ሳር ቅጠሉ፥ በስጋት ተሞልቶ የማለዳው ሰማይ፥ እንዳንቀልባ ቀልቶ ታረደ ነደደ ከዘብጥያ ወጥቶ ዘብጥያ ወረደ የሚል ዜና ብቻ ፥ አየሩን ሲሞላው ሰው በገዛ ጥላው ፥ በርግጎ ሲሸበር በዚህ ምድር መኖር፥ አያስመኝም ነበር ፤ አዎ ለጊዜውም ቢሆን ግፍ ያደነዝዛል በደል ያስተክዛል ጊዜም ጠብን ሽሮ፥ ወደ ፊት ይጓዛል በልብ ሰሌዳ ላይ፤ ቂም ይደበዝዛል በነገ ያመነ ልጁን ቀብሮ መጥቶ ፥ ሚስቱን ያስረግዛል :: ይቅርታና ምህረት ፍቅርና ህብረት ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው፥ ቢሆን የሞት ሽረት ዳገት ይወጣሉ፥ በንጥፍጣፊ አቅም የመኖር ፍላጎት ዘመም ይላል እንጂ ፥ተገርስሶ አይወድቅም :: ( አዳምኤል )
Open in Telegram👁️በድብቅ የህይወትህን አስከፊ ድራማ የሚያቀነባብሩልህ 4 አደገኛ ኮከቦች "እኔ ማስመሰል አልወድም..." ይህን ንግግር ስንት ጊዜ ሰምተኸዋል? ምናልባትም ከቅርብ ጓደኛህ፣ ከፍቅረኛህ፣ ወይም አብሮህ ከሚሠራው ሰው? በ Dark Psychology ጥናት መሠረት፣ "ድራማ እጠላለሁ! ማስመሰል አይመቸኝም!" ብለው ጮክ ብለው የሚናገሩ ሰዎች፣ ብዙውን ጊዜ ራሳቸው የፈጠሩትን እሳት እያቀጣጠሉ ከጀርባ ሆነው የሚስቁ አደገኛ የስነ-ልቦና መሐንዲሶች ናቸው። አንዳንድ ሰዎች ደም አያፈሱም። ነገር ግን በስውር የሰዎችን ስሜት እርስ በእርስ በማጋጨትና እሳት በመፍጠር ሙቀቱን የሚመገቡ የአዕምሮ ጥገኛ (Emotional Vampires) ናቸው። አንተን በውጥረት ውስጥ ዘፍቀው፣ አንተ ሰላምህን ስታጣ፣ እነሱ ግን በዚያ ሁከት ውስጥ የህይወታቸውን ትርጉም ያገኛሉ። በኮከብ ቆጠራው አለም ከ12ቱ ኮከቦች መካከል አራቱ በዚህ ባህርያቸው ይታወቃሉ... ውጫዊ ገጻቸው መልአክ፣ ውስጣቸው ግን የረቀቀ የስሜት ጦርነት ሜዳ ነው። ከአራቱ ውስጥ ምናልባት የምትወደው ሰው እንዳለ ስትረዳ ማመን ሊከብድህ ይችላል። የከፋው ደግሞ... ምናልባት ያ አራተኛው ሰው ራስህ ልትሆን መቻልህ ነው? 👇 ሙሉውን አስደናቂ ትንታኔ ለማንበብ 👇 https://mistre-kewakbt.blogspot.com/2026/11/4.html
Open in TelegramConnections
Similar channels
Hule Addis Media ( HAM)@hulaadissNews and media2.08K
Biiroo Industiriifi Intarpiraayizii Oromiyaa@oromia_eibureauNews and media1.5K
ትኩስ መረጃ@tikuswereNews and media1.19K
Addis Insight -አዲስ እይታ@addisinsight23News and media3.18K
Ethiopian Media Authority@ethmediaauthNews and media3.25K
Russian House in Addis Ababa / Русский дом в Аддис-Абебе@rcscethiopiaNews and media4.56K
Warka Times@warkatimesofficialNews and media4.65K- The Urban Center ( Kebet Eske Ketema)@theurbancenterNews and media5.65K