ጭራሽ ሽልማት? (አሌክስ አብርሃም) መምህርነት ክቡር ሙያ ነው፤ በሕይወት ዘመኔ የሚገራርሙ ጥሩ መምህራን አጋጥመውኛል። ግን አንዳንድ ወንድ መምህራን የሆነ ነገራቸው ልክ አልነበረም። እስከአሁንም ባስታወስኳቸው ቁጥር ጤነኝነታቸውን እጠራጠራለሁ። በአጋጣሚ መንገድ ላይ እንኳን ሳያቸው ሰላም ላለማለት መንገድ አቋርጨ ነው የምሄደው። ደግሞ ሰው አይረሱም። "ቲቸር እንትኒት" የሚባል አስተማሪ ነበረን። "እንትኒት" የተባለው በሚጋረፍባት የእንጨት ብትር ስም ነው። እንደደህና ነገር ገና የመጀመሪያ ቀን ዱላውን በስም ለተማሪወች ያስተዋውቃል። ወጥ ማማሰያ የመሰለ ጫፏ ቀይ የተቀባ ብትር። መዳኒት ናት ምናምን እያለ ይሟዘዝና በአየር ላይ እንደሰይፍ እየሰነዘረ ያስቦካናል። የመጀመሪያ ቀን በቃ ይነጅሰናል። ከእኛ በፊት ያስተማራቸው "ዝናውን" ስለሚነግሩን ባያስፈራራንም ፈርተን ነው የምንጀምረው። ሌላውን ተውት ይሄ ሰውየ ገና መስከረም ላይ ሲገባ እንደሆስፒታል የሰርጀሪ አልጋ ከፊት ወንበር አንድ ጠረጴዛ ያመቻቻል። እዛ ጠረጴዛ ላይ የስንት ህፃን ቂ* በደረቅ እንጨት ሰንበር በሰንበር አድርጓል። ሴቶቹን መግረፍ ነፍሱ ነበር። በተለይ ደግሞ እታፈራሁን ካልገረፈ እንደሆነ ሱስ ያዛጋዋል። እታፈራሁ ሚስኪን የደሀ ልጅ ናት፣ ምን ሆንሽ ባይ የሌላት። ሁልጊዜ ፀጉሯ የሚንጨባረር (ቅጫም) ነው የሚላት ቅጫማም አይደለም... ቅጫም! አንድ ቀን ወላጅ አምጭ ተብላ እናቷን ይዛ መጣች...ገና አስተማሪው የቤት ስራ አትሰራም ከማለቱ እናቲቱ የእታፈርን ፀጉር ጨምድዳ "ስታርሽ ነው ስትጎለጉይ" እያለች ትቀጠቅጣት ጀመር ፣ ያ ክፉ አስተማሪ እንኳን "አቁሚ ህፃን አይደለች እንዴ" እስኪል። በነገራችን ላይ በቀጥታ ገርፎኝ አያውቅም ግን ዱላውና ትሮውማው በተዘዋዋሪ ደርሶኛል። አንድ ቀን ይችኑ እታፈራሁን ምን እንዳደረገች ትዝ አይለኝም (መልስ አልመለሽም ብሎ ይመስለኛል) እዛ ጠረጴዛ ላይ በሆዷ አስተኛት። ቀሚስሽን ግለቢ አለ (ሲሪየስ አሁን ይሄ ምንድነው) ልጅቱ ነፍሷ ተጨነቀ። ገና ሳትገረፍ ሽንቷን ለቀቀችው...እንደተደፋ የብርጭቆ ውሃ ሽንቷ ከጠረንጴዛው እየተንኳለለ ስሚንቶው ወለል ላይ ሲያርፍ ድምፁ እስከአሁን ይታወሰኛል። ፊት ወንበር ነበር እኔ የምቀመጠው። "ና አንተ " አለኝ። እየተንቀጠቀጥኩ ሄድኩ። "እዚህ ወገቧ ላይ ግጥም አርገህ ያዝ" አለና በብትሩ ጠቆመኝ። አጥንታም የህፃን ወገቧን ከተገለበ ቀሚሷ ጋር ያዝኩ ። ብቻ የመጀመሪያው ብትር እያፏጨ ሰውነቷ ላይ ሲያርፍና ደም የመሰለ መስመር ሲያጋድምባት ያች ትንሽ ፍጥረት የሷ በማይመስል ሃይልና ጩኸት ገፈታተረችኝ " ሁለተኛው ብትር ሲምዘገዘግና ያመለጠኝን የቀሚሷን ጫፍ ለመያዝ እጀን ስዘረጋ የብትሩ ጫፋ ትንሿ የቀኝ እጀ ጣት አንጓ ላይ አረፈ። ቋ ነው ያለው እንደረቅ እንጨት። ለአመታት ህመሙ ይሰማኝ ነበር ። በተለይ መዳፌን ስጨብጥ። እታፈራሁን ሁልጊዜ አስባት ነበር። የት ሄዳ ይሆን እያልኩ። ምንዱባንን ሳነብ እነ ኤፖኒን ፣አዜልማ፣ ኮዜትን ሁሉ በእርሷ እየተካሁ ትዝ ትለኝ ነበር። ሰውየው ያልገረፈው ህፃንና ያልተለማመደብን አገራረፍ የለም። አለኮ አባታዊ ቅጣት፣ የሆነ ፍቅር ያለው... ልጆች በባህሪም በትምህርትም እንዳይበላሹ መስመር ለማስያዝ ያህል ዘመኑ ይፈቅደው የነበረ ቅጣት። ይሄ ወንዶቹ ላይ ሃይላንድ ያላንጠለጠለብንም በዘመኑ ቅጣቱ ባለመለመዱ ይመስለኛል። በጣት መሃል እስክርቢቶ አስገብቶ ማጣበቅ፣ በማስመሪያ ጠርዝ የጣት ጫፍ መምታት፣ አስጎንብሶ ጆሮ ማስያዝ፣ ተማሪ ፊት ማዋረድ ፣ ጆሮን አፍንጫ ላይ የሚያመጣ ኩርኩም ማጋጨት፣ አይን የሚያንሸዋርር ድንገተኛ ጥፊ፣ በእንብርክክ ስሚንቶ ላይ ማስኬድ፤ በካልቾ መጠለዝማ በረከት ነበር.... ግርርርርም ያለኝ ባለፈው የድሮ ተማሪወቹ ተሰብስበው "ቲቸርን ልንሸልም ነው ተቀላቀለን" አሉኝ። ጭራሽ ሽልማት? ደግሞ በጣም የገረመኝ ሸላሚወቹን ሰብሳቢ ማን ብትሆን ጥሩ ነው? እታፈራሁ! "የቀለም አባታችን" ምናምን እያለች። ምኗ ቅጫም ናት አልኩ በንዴት😀
Open in TelegramPosts of ኮከብ ጋዜጣ
አያ ሙሄ [በውቀቱ ስዩም] አያ ሙሄ የተባለ ገበሬ ልጁ ሞቶበት ፥ ጎጆው በርንዳ ላይ ኩርትም ብሎ ይቆዝማል። ባለንጀራው አዋ ይመር አጠገቡ ተቀምጧል። አዋ ይመር ወዳጁን በቃል ማጽናናት በቂ ሆኖ አላገኘውም። የወዳጁን ልጅ የቀሰፈውን ፈጣሪ ለመበቀል ስለፈለገ ፥ ጠመንጃውን አነጣጥሮ ወደ ሰማይ ተኮሰ፤ ተኩሱ በረድ ሲል ሀዘንተኛው አያ ሙሄ ወዳጁን እያየ እንዲህ አለ :- “ካገኘከው ገላገልኸን፤ ከሳትኸው ግን አስፈጀኸን” 🙂
Open in Telegramየኛ ፖለቲካ የብሄር ሆነ ብለህ ሰፍ ብለህ ዘርህን መቁጠር ስትጀምር እጥፍ ይልና የሀይማኖት ይሆናል። በቃ አርፌ ሀይማኖቴ ላይ መረር ልበል ከብሄሩ እሱ ይሻላል ስትል ደሞ መልሶ የብሄር ይሆናል። በዚህ ምክንያት ህዝቡ ጠቅላላ ቶክሲክ ሪሌሽን ላይ ነው ያለው። በብሄር ተጣልቶ ብሎክ ይደራረግና መልሶ በሀይማኖት ጉዳይ አንድ ሲሆን ፎሎው ይደራረካል። ከዛ ድጋሜ ብሎክ... ፎሎ ያረገኛል አንፎሎ ያረገኛል ፖለቲካ።
Open in Telegramአከራይ ተከራይ ሲባል ምንጊዜም ትዝ የሚለኝ አስቂኝ ነገር... (አሌክስ አብርሃም) አንድ ሰፊ የግለሰብ ግቢ ውስጥ ተከራይቸ እኖር ነበር። ብዙ ነበርን ተከራዮቹ ፤ ከእኔ ቤት ቀጥሎ የሚኖረው ተከራይ አንድ አስተማሪ ሲሆን ቅዳሜ ቅዳሜ ብቻ ጢንቢራው እስኪዞር ከመስከርና "ገንዘብ አለያየን ደሃ በመሆኔ" እያለ ከመዝፈን ውጭ ሽቁጥቁጥ፣ የግቢውን በር እንኳን ሲያልፍ ጫማውን ሊያወልቅ የሚዳዳው ትሁት ሰው ነበረ። አንድ ቅዳሜ ግን ምናባቱ...ማለቴ ምን ጠጥቶ እንደመጣ እንጃ ግቢውን በአንድ እግሩ አቆመው። የሆነ ለማሽቃበጥ የሚረዳ መጠጥ ይመስለኛል የጠጣው። ገና ከመግባቱ "ሁላችንም ኪራይ መጨመር አለብን " ብሎ ጮኸ። "አከራዮቻችን ዝም ስላሉ ብቻ ዝም ማለት ልክ ነው? አይደለም! ቤት መስራት ብዙ ዋጋ ያስከፍላል ካርታ አለ...ፕላን አለ...ለመሃንዲስና ምናምን ጉቦ አለ...ብሎኬት አለ...ሲሚንቶ አለ...ለአከራይ ማን ያስብለት?... መሯቸው ሸጠውት ቢሄዱስ? እኔ ከነገ ጀምሮ ሃምሳ ብር ጨምሪያለሁ...ሁልሽም ኪራይ ጨምሪ...እንትና መቶ ብር...እንትና ስልሳ ብር ... አንተ አብርሃም ሰባ ብር ፣ የውሃም እኛ መክፈል አለብን.....(በቃ ይሄ ሰው ራሱን ሊያጠፋ ወስኗል ማለት ነው ብየ አሰብኩ) አከራያችን ጋቢያቸውን ለብሰው ብቅ አሉና እንደወትሮው "እንዲህ ከረበሽክ ከነገ ጀምሮ ቤት ፈልግ" ይሉታል ብለን ስንጠብቅ ፍቅር በሆነ ድምፅ "መምህር ና እራት ብላ እስቲ... " ወሬ ልመለከት ስንወጣ አከራየ ጋር እንደመጋኛ ተገጣጠምን። ወደእኔ እያዮ "የሚጠጣ ሰውኮ በሆዱ ክፋት የለም..." 🤔 እና ልጠጣልወት?
Open in Telegramበችግር ጊዜ የሚሸሹ የዞዲያክ ኮከቦችና ምክንያቶቻቸው እነዚህ ኮከቦች በተፈጥሯቸው አሉታዊነትን፣ ድብርትን ወይም ከባድ ሸክምን መሸከም አይችሉም። ማህበራዊ ክብራቸውን፣ ደስታቸውን ወይም ነፃነታቸውን ስለሚመርጡ ችግርህን ሲያዩ ሮጠው ያመልጣሉ። Gemini (ጀሚናይ) እና Sagittarius (ሳጁታሪየስ): ችግርህን መስማት አሰልቺና ነፃነታቸውን የሚነጥቅ ስለሚመስላቸው፣ Libra (ሊብራ) እና Leo (ሊዮ): ስምህ እና ክብርህ ሲወድቅ አብረው እንዳይጠለሹ በመፍራት፣
Open in Telegramበዚህ ሰዓት የሐይማኖት ሰወች ከአምላካቸው በላይ መንጋቸውን ያመልካሉ። ይህን ለማረጋገጥ ከፈለክ ብዙ መንጋ ያለውንና የሌለውን አነፃፅር። ባለብዙው የበዛ ኮንፊደንስ ሲኖረው ትንሽ መንጋ ያለው አንገቱን ደፍቶ ይቅለሰለሳል። መንጋው ሲበዛለት ተነስቶ ይደነፋል። መንጋ ያድናል፣ መንጋ ሀይል ነው፣ የሚመካ በመንጋው ይመካ ነው መንፈሱ። በዚህ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ የመንጋ እንጅ የሐይማኖት ፀብ አለ ብሎ ለማመን ይቸግራል። ሐይማኖት ከብሔርና ፖለቲካ ተዳቅሎ ዲቃላ ሐይማኖተኞችን ወልዷል።ዲቃላ በባህሪው መንገደኛው ሁሉ አባቱ ይመስለዋል። እናቱን ያገባ ሁሉ አባቱ ይመስለዋል። መንጋ የሐይል፣ መንጋ የገቢ ምንጭ ነው። አማኝ ሳይሆን መንጋ ማብዛት የሐይማኖቶች ዋና ስራ ሁኗል!! ((መንጋ)) በአምላኩ ስም ወደየትም የሚነዳ ግዑዝ የሰው ስብስብ ሲሆን ፣((አማኝ)) ግን በእምነት ወደአምላኩ ብቻ የሚራመድ ሰው ነው!
Open in Telegramአባ (በእውቀቱ ስዩም) አባ ገብረማርያም የአምሳ ስምንት አመት መነኩሴ ናቸው፤ አንድ ማታ፣ ከምሽቱ አምስት ሰአት ተኩል ላይ፣ የንስሀ ልጃቸው ለሆነቸው ወይንሸት ደወሉ፤ “ሀሎ! ወለተማርያም” “አቤት አባ” “ይቅርታ ተመሸ ደወልኩ” “በሰላም ነው አባ?” “ባለቤትሽ ቤት አለ፤? “የለም ፊልድ ወጥትዋል” “ልጆችስ ?” “ተኝተዋል” “በይ ያለሸበትን ክፍል በር ዝጊው” “እ! ዘጋሁት” “ስልክሽን በምን እጅሽ ነው የያዝሽው?” “በቀኝ እጄ ” “ወደ ግራ እጅሽ አዛውሪው” “ማለት ?” “በማንኩሳው ሚካኤል፤ በውስጠጉልቱ ጊዮርጊስ የምልሽን አድርጊ” “እሺ አንዳሉት አድርጊያለሁ” “በቀኝ እጅሽ እስኪብርቶ ይዘሽ ማስታወሻ ትመዘግቢልኛለሽ” “ምንድነው ?” “የሆነ ጊዜ ላይ ሎንዶን የመሄድ እድል ገጥሞኝ፣ ብሪትሽ ላይብራሪ ላይ ከመቅደላ የተዘረፉ ብራናዎችን ሳገላብጥ አንድ ጥንታዊ መጽሀፍ አገኘሁ፤ የመጽሀፉ አስራ ሰባተኛ ገጽ ተገንጥሎ ስመለከት ከነከነኝ ፤ አገር ቤት ስመለስ የብራናውን ቅጂ በየገዳሙ ማፈላለግ ጀመርኩ፤ በመጨረሻ ዲማ ውስጥ አገኘሁት፤ የሚገርምሽ መጽሀፉ በግእዝ የተጻፈ ቢሆንም የተገነጠለው ክፍል ለብቻው በጋፋትኛ ነበር የተጻፈው፤ ታድያ እኔ አባትሽ ጋፋትኛን ለአምሳት አመት አጥንቸ፤ ትርጉሙን ደረስኩበት” “ይቀጥሉ” “ያ ገጽ ታላቅ ምስጢር አዝሉዋል፤ ንጉስ ላሊበላ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሳጥን ሙሉ ወርቅ አልማዝ፤ ዩራኒየም ታንታለም እና ሌሎች የከበሩ ማእድኖችን አንድ ዋሻ ውስጥ አንደደበቀ ይጠቁማል ፤ ይህ ብቻ አይደለም ፤መቅደሶቹን የፈለፈለበት ማሽን ሳይቀር በዚያ ይገኛል፤ ማሽኑ ትልልቅ አለቶችን በቀላሉ አንደ እርሳስ መቅረጽ የሚችል ነው፤ እየሰማሽኝ ነው ?” “አዎ! ይቀጥሉ አባ!” “የብራናውን ጥቆማ መሰረት አድርጌ ስሄድ አገኘሁት፤ ዋሻው ተደብቆ የሚገኘው በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ የሚገኝ ተራራ ግርጌ ነው፤ ” “ይህንን ለኔ ለምንድነው የሚነግሩኝ አባ” አለች ወይንሸት፤ “ሰሞኑን ትንሽ ሲያመኝ አልነበር፤ አንድ የታወቀ ዶክተር ጋር ሂጄ ነበር ዛሬ ጠዋት! በቅርቡ! በሰአታት ጊዜ ውስጥ የመዘንጋት በሽታ አእምሮህን ይቆጣጠረዋል ብሎ አረዳኝ፤ እናም ትውስታየ ሳይከዳኝ ይህንን አገራችንን ከድህነት መንጥቆ የሚያወጣ ሚስጥር አንቺ ጋር ባደራ ላስቀረው ብየ ነው” አሉ አባ ትካዜ በተላበሰ ድምጽ፤ “እሺ የተራራው ስም ምንድነው አባ ?” አለች ወይንሸት፤ አባ በረጅሙ ተነፈሱና መለሱ፤ “የምን ተራራ;?” (ከምናለሽ ተራ እስከ ምንትሴ ተራራ ከሚለው ልብ ሰቃይ መፅሐፍ የተቀነጨበ)
Open in Telegramየምታውቁት እና የምወደው " ሲሪየስ"ቀልድ (አሌክስ አብርሃም) ፖይለቱ ሶስት ሰወችን አሳፍሮ በበረራ ላይ እያለ የአውሮፕላኑ ሞተር ስራ አቆመ። እና ለተሳፋሪወቹ "አዝናለሁ አውሮፕላኑ መከስከሱ ነው፣ እኛ አራት ነን፣ ያለን ግን ሶስት ፖራሹት ብቻ ነው፣ ስለዚህ አንድ ሰው መሞቱ ግድ ነው" አለና አንዱን ፓራሹት አዝሎ ዘለለ። ከሶስቱ አንዷ ተወርውራ አንዱን ፓራሹት አፈፍ አድርጋ በጀርባዋ አዘለችና "አዝናለሁ አገራችን ካሏት ጂኒየስና ስማርት ሰወች አንዷ እኔ ነኝ መሞት የለብኝም" ብላ ዘለለች። ቀሪወቹ አባትና የአስር አመት ልጁ ነበሩ። አባት በሐዘንና በፍቅር እንዲህ አለ " ልጀ እኔ በቂ ኑሪያለሁ አንተ ፓራሹቱን ይዘህ ሂድ ይቅናህ" ልጅ "ዳዲ ሁለት ፓራሹትኮነው ያለን ተመልከት" እውነትም ሁለት ነበር። አባት ተገርሞ "አንዱ ከየት መጣ? ሶስት ብቻ አልነበር ያለው ፓይለቱ?" ልጅ እየሳቀ " ልክነው ዳዲ! ሶስት ብቻ ነው፣ ግን ያች 'ጂኒየስና ስማርት' ሴትዮ ፓራሹት መስሏት የእኔን የትምህርት ቤት ቦርሳ ነው አዝላ የዘለለችው"😀 በእነዚህ ጥቂት ዓመታት ስንቱ ፓራሹት መስሎት ቦርሳችንን እየያዘ ዘለለ! ቦርሳችን ውስጥ የነበረ ፍቅርና እምነት አብሮ ቢወሰድም መሬት ያረፍን ቀን ተፈጥፍጦ የምናገኘው ብዛቱ። መቸስ ቦርሳችን አይፈጠፈጥ አቧራውን አራግፈን እናነሳዋለን። አሁን ሁላችንም አየር ላይ ነን! #Share
Open in Telegramዘመም ይላል እንጂ (በእውቀቱ ስዩም) እንደ ጊዜው መክፋት እንደ ግፉ መስፋት እንዳገሩ ክስመት እንዳገሬው ጥመት እንደሰው ጭካኔ፥እንደ ልቡ ፍሬ ታምር ነው መትረፍሽ፥ ታምር ነው መኖሬ:: የበጎ ሰው ሀሳብ፥ ሲካድ እለት በእለት ጉድጓድ ተምሶለት፥ ሰብእና ሲቀበር በዚህ ዓለም መኖር፥አያስመኝም ነበር :: ምድሩ ሳር ቅጠሉ፥ በስጋት ተሞልቶ የማለዳው ሰማይ፥ እንዳንቀልባ ቀልቶ ታረደ ነደደ ከዘብጥያ ወጥቶ ዘብጥያ ወረደ የሚል ዜና ብቻ ፥ አየሩን ሲሞላው ሰው በገዛ ጥላው ፥ በርግጎ ሲሸበር በዚህ ምድር መኖር፥ አያስመኝም ነበር ፤ አዎ ለጊዜውም ቢሆን ግፍ ያደነዝዛል በደል ያስተክዛል ጊዜም ጠብን ሽሮ፥ ወደ ፊት ይጓዛል በልብ ሰሌዳ ላይ፤ ቂም ይደበዝዛል በነገ ያመነ ልጁን ቀብሮ መጥቶ ፥ ሚስቱን ያስረግዛል :: ይቅርታና ምህረት ፍቅርና ህብረት ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው፥ ቢሆን የሞት ሽረት ዳገት ይወጣሉ፥ በንጥፍጣፊ አቅም የመኖር ፍላጎት ዘመም ይላል እንጂ ፥ተገርስሶ አይወድቅም :: ( አዳምኤል )
Open in Telegram👁️በድብቅ የህይወትህን አስከፊ ድራማ የሚያቀነባብሩልህ 4 አደገኛ ኮከቦች "እኔ ማስመሰል አልወድም..." ይህን ንግግር ስንት ጊዜ ሰምተኸዋል? ምናልባትም ከቅርብ ጓደኛህ፣ ከፍቅረኛህ፣ ወይም አብሮህ ከሚሠራው ሰው? በ Dark Psychology ጥናት መሠረት፣ "ድራማ እጠላለሁ! ማስመሰል አይመቸኝም!" ብለው ጮክ ብለው የሚናገሩ ሰዎች፣ ብዙውን ጊዜ ራሳቸው የፈጠሩትን እሳት እያቀጣጠሉ ከጀርባ ሆነው የሚስቁ አደገኛ የስነ-ልቦና መሐንዲሶች ናቸው። አንዳንድ ሰዎች ደም አያፈሱም። ነገር ግን በስውር የሰዎችን ስሜት እርስ በእርስ በማጋጨትና እሳት በመፍጠር ሙቀቱን የሚመገቡ የአዕምሮ ጥገኛ (Emotional Vampires) ናቸው። አንተን በውጥረት ውስጥ ዘፍቀው፣ አንተ ሰላምህን ስታጣ፣ እነሱ ግን በዚያ ሁከት ውስጥ የህይወታቸውን ትርጉም ያገኛሉ። በኮከብ ቆጠራው አለም ከ12ቱ ኮከቦች መካከል አራቱ በዚህ ባህርያቸው ይታወቃሉ... ውጫዊ ገጻቸው መልአክ፣ ውስጣቸው ግን የረቀቀ የስሜት ጦርነት ሜዳ ነው። ከአራቱ ውስጥ ምናልባት የምትወደው ሰው እንዳለ ስትረዳ ማመን ሊከብድህ ይችላል። የከፋው ደግሞ... ምናልባት ያ አራተኛው ሰው ራስህ ልትሆን መቻልህ ነው? 👇 ሙሉውን አስደናቂ ትንታኔ ለማንበብ 👇 https://mistre-kewakbt.blogspot.com/2026/11/4.html
Open in Telegram😱 ቪርጎ፣ ሊዮ እና ጀሚኒ በውድ ሬስቶራንት ውስጥ 🍽️** ቪርጎ፣ ሊዮ እና ጀሚኒ በውድ ሬስቶራንት ውስጥ በሊዮ መሪነት ገቡ። ሊዩ ክብሩን የሚመጥን ከዚህ የተሻለ ሬስቶራንት አላገኘም። ችግሩ ግን በማን ኪስ ውስጥ ምን ያህል ገንዘብ እንዳለ ሶስቱም አያውቁም። በሁሉም ልብ ውስጥ ከፋይ ማን እንደሆነ አልተወሰነም። በቀላል ገንዘብም የሚገላገሉ መስሏቸው ነበር። ከበሉ ከጠጡ በኋላ አስተናጋጁ 5,000 ብር ሂሳብ ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦ ሄደ። --- Virgo 📋፦ (ሂሳቡን አይቶ ዓይኑ ፈጠጠ) "አምስት ሺህ ብር?! እኔ የጠጣሁት አንድ ማኪያቶ ብቻ ነው! የናንተን በርገርና ቁርጥ አልከፍልም!" Leo 🦁፦ (ደረቱን ነፍቶ) "ተረጋጋ ቪርጎ! ይህ ንግግርህ የእኔን ክብር አይመጥንም፤ ለ5000 ብር ብለህ እንዲህ ትሆናለህ?! ሂሳቡን ሙሉውን እኔ እከፍላለሁ!" Virgo 📋፦ "ደስ ይለኛል። ክፈለው!" Leo 🦁፦ (ኪሱን እየዳበሰ… በድንጋጤ አይኑ ፈጠጠ) "ወይኔ! ቦርሳዬ… ቦርሳዬ የለም! ወይኔ ተዋረድኩ ዛሬ!" Virgo 📋፦ (ጠረጴዛውን በእጁ ከመታ በኋላ) "ድራማህን ተው ሊዮ! ኪስህ ባዶ እንደሆነ እያወቅክ ነው እዚህ ውድ ቦታ ያመጣኸን?!" Gemini 🌪️፦ (እስካሁን በርገሩን ሲያላምጥ ከቆየ በኋላ ስልኩን ጆሮው ላይ ለጥፎ እየተጣደፈ) "ሄሎ አባዬ?… ምን?! አክስቴ ሆስፒታል ገባች?! ወይኔ መጣሁ!!" (ወደ ሁለቱ ዞሮ) "ይቅርታ አጣዳፊ ጉዳይ ገጠመኝ! ቶሎ መሔድ አለብኝ!" 🏃♂️💨 Leo 🦁፦ (የጀሚኒን ጃኬት ይዞ) "አትሄድም! ስልክህ እኮ አልጠራም… ባዶ ስክሪን ነው ጆሮህ ላይ የለጠፍከው!" Virgo 📋፦ (አስተናጋጁ ወደነሱ ሲመጣ አይቶ) "አስተናጋጁ እየመጣ ነው! የበላችሁበትን ክፈሉና በሰላም ከዚህ እንውጣ!" Leo 🦁፦ (ድንገት ወንበሩ ላይ ተዘርሮ)* "እያመመኝ ነው… ትንፋሽ አጠረኝ … እባካችሁ አምቡላንስ ጥሩልኝ!" 😵 Gemini 🌪️፦ (ለአስተናጋጁ ፈገግ እያለ) "ወንድም… የወጥ ቤት ሳህን ማጠቢያ ክፍላችሁ በየት በኩል ነው?" 🧼🧽😁😂 *** ✨ ኮከባችሁን ወደ ዌብሳይታችን ግቡና "ኮከብዎን ይወቁ" የሚለው ፎርም ላይ የተወለዳችሁበትን ቀን በትክክል በማስገባት ማወቅ ትችላላችሁ። የዌብሳይታችን ሊንክ 👉 https://mistre-kewakbt.blogspot.com
Open in Telegram🌌 12ቱ የዞዲያክ ምልክቶች እና የተሰሩባቸው ዋና ንጥረ ነገሮች [Elements]🔮 በኮከብ ቆጠራ ዓለም ውስጥ እያንዳንዱ ሰው የተፈጠረበት ዋና የተፈጥሮ ንጥረ ነገር (Element) አለ። ስሜታችን፣ ውሳኔያችን እና ከሰዎች ጋር ያለን መስተጋብር የሚመራው በዚህ የተፈጥሮ ኃይል ነው። 👇 --- 🔥 የእሳት ኮከቦች (Fire Signs) (ጠንካራ፣ በራስ መተማመን ያላቸው እና የማይበገሩ) ♈ አሪስ (Aries)፡ በቀላሉ ይናደዳሉ ነገር ግን ቂም መያዝ አይችሉም፤ ውስጣቸው እንደ ህፃን የዋህ እና ቅን ነው። ♌ ሊዮ (Leo)፡ የትኩረት ማዕከል መሆን ይወዳሉ፤ ነገር ግን አንዴ ካፈቀሩ ላፈቀሩት ሰው ያላቸው ታማኝነት እና ጥበቃ ወደር የለውም። ♐ ሳጂታሪየስ (Sagittarius)፡ ነፃነታቸውን ከምንም በላይ ይወዳሉ፤ ሰዎች ሲያዟቸው አይወዱም፤ ሁልጊዜም የህይወትን ጥልቅ ትርጉም አሳዳጅ ናቸው። ⚠️ የሶስቱ የጋራ ድክመት፡ ትዕግስት ማጣት፣ የችኮላ ውሳኔ እና ቶሎ መበሳጨት። --- 🌍 የመሬት ኮከቦች (Earth Signs) (በህይወት ውስጥ እጅግ በጣም የረጋ፣ አስተማማኝ እና መሬት የነካ ህይወት የሚመሩ ናቸው።) ♉ ቶረስ (Taurus)፡ ሰላምን እና የቅንጦት ኑሮን ይወዳሉ፤ እጅግ በጣም ግትር (Stubborn) ሊሆኑ ይችላሉ፤ አንዴ ያመኑበትን ነገር ማንም ሊያስቀይራቸው አይችልም። ♍ ቪርጎ (Virgo)፡ ጥቃቅን ስህተቶች ያበሳጯቸዋል፤ ሁሉንም ነገር 'Perfect' ማድረግ ይፈልጋሉ፤ ራሳቸውንም ሆነ ሌላውን ከመጠን በላይ ይወቅሳሉ። ♑ ካፕሪኮርን (Capricorn)፡ ለስኬት እና ለስራ ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ፤ ስሜታቸውን ለሰው ማሳየት እንደ ትልቅ ድክመት ይቆጥሩታል። ⚠️ የሶስቱ የጋራ ድክመት፡ ለውጥን አለመፈለግ፣ ከመጠን በላይ መጨነቅ እና ግትርነት። --- 💨 የአየር ኮከቦች (Air Signs) (የሚኖሩት በአእምሮአቸው፣ በሃሳባቸው እና በማያልቀው ምናባቸው ውስጥ ነው) ♊ ጄሚኒ (Gemini)፡ ሁለት ዓይነት ስብዕና አላቸው፤ አሁን ደስተኛ የነበሩት በቅጽበት ሊደብራቸው ይችላል። እጅግ በጣም ብልህ እና ተግባቢ ናቸው። ♎ ሊብራ (Libra)፡ ሰላምን፣ ውበትን እና ፍትህን ይወዳሉ፤ ትልቁ ድክመታቸው ቶሎ ውሳኔ መወሰን አለመቻል (Overthinking) ነው። ♒ አኳሪየስ (Aquarius)፡ ከማንም ጋር የማይመሳሰል የተለየ አስተሳሰብ አላቸው፤ ከሰዎች ጋር በቀላሉ አይቀራረቡም፤ ነፃነታቸውን የሚነካ ማንኛውንም ግንኙነት ያቋርጣሉ። ⚠️ የሶስቱ የጋራ ድክመት፡ በስሜት አለመርጋት፣ በቀላሉ መሰልቸት እና ከመጠን በላይ ማሰብ። --- 💧 የውሃ ኮከቦች (Water Signs) (በጣም አደገኛው፣ ጥልቁ እና ስሜታዊው ዓለም የሚገኘው በእነዚህ ኮከቦች ውስጥ ነው።) ♋ ካንሰር (Cancer)፡ ያለፈውን ነገር መርሳት አይችሉም፤ በጣም አፍቃሪ እና ቤተሰባዊ ናቸው፤ ነገር ግን ከተጎዱ ድጋሚ በጭራሽ አያምኑዎትም። ♏ ስኮርፒዮ (Scorpio)፡ የዞዲያኩ ትልቁ ምስጢረኛ! ውሸትን የማሽተት ልዩ የተፈጥሮ ስጦታ አላቸው፤ በቀል እና ጥላቻቸው ልክ እንደ ፍቅራቸው እጅግ ኃይለኛ ነው። ♓ ፓይሲስ (Pisces)፡ የህልም ዓለም ነዋሪዎች ናቸው፤ የሰውን ህመም እንደ ራሳቸው አድርገው ይሰማቸዋል፤ በቅዠትና በእውነታ መሀል ይዋትታሉ። ⚠️ የሶስቱ የጋራ ድክመት፡ ከመጠን በላይ ስሜታዊ መሆን፣ ቂም መያዝ እና ያለፈውን አለመርሳት። --- ✨ የእርስዎ ኮከብ የትኛው እንደሆነ ማወቅ ይፈልጋሉ? ወደ ዌብሳይታችን በመግባት "ኮከብዎን ይወቁ" የሚለው ፎርም ላይ የተወለዱበትን ቀንና ወር በትክክል በማስገባት ኮከብዎን እና ዝርዝር ባህሪዎን ማወቅ ይችላሉ! 👉 የዌብሳይታችን ሊንክ፦ https://mistre-kewakbt.blogspot.com
Open in Telegram🪐 ኮከብ ቆጠራ (Astrology) ምንድነው?🔮 ብዙ ሰው ኮከብ ቆጠራን እንደ ቀላል "ሟርት" ፣ እንደ አስማት(ጥንቁልና) ወይም እንደ ተራ ወሬ ይመለከተዋል። እውነታው ግን ከዚህ ፍጹም የራቀ ነው! በቀላል ቋንቋ፦ ኮከብ ቆጠራ የሰው ልጆች የተፈጥሮ ጠባይ እና ስነ-ልቦና (Psychology) መፍቻ ቁልፍ ነው። እስኪ ቆም ብላችሁ ራሳችሁን እና በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎችን በደንብ አስተውሉ፦ 👑🔥 አንዳንድ ሰዎች ምንም ሳይጥሩ የተፈጥሮ መሪ፣ ደፋር እና የትኩረት ማዕከል ናቸው፣ 🤍🩹 አንዳንዶቹ ደግሞ በጣም ሩህሩህ፣ ለሰው አሳቢ ነገር ግን ውስጣቸው በቀላሉ የሚጎዳ ነው፣ 🧊🤫 ሌሎች ምንም ቢፈጠር የማይደናገጡ፣ የተረጋጉ እና ሚስጥራቸውን ለማንም የማያወሩ ናቸው፣ 🧠🌪️ አንዳንዶቹ አእምሯቸው ሳያቋርጥ የሚያስብ (Overthinkers)፣ በአንድ ቦታ መርጋት የማይችሉ እና አዳዲስ ነገሮችን የሚናፍቁ ናቸው፣ 🎯🔍 ጥቃቅን ስህተቶች የሚያበሳጯቸው፣ ሁሉ ነገር በስርዓት እና እንከን-አልባ (Perfect) እንዲሆን የሚጥሩ አሉ፣ 🕵️♂️👁️ የሰውን ስሜትና ውሸት ገና ከሩቅ የማሽተት ልዩ የተፈጥሮ ስጦታ ያላቸው አሉ፤ ነገር ግን ምንም እንዳላወቁ ሆነው ዝም ይላሉ፣ 🦅🔓 በማንም ህግና ትዕዛዝ መመራት የማይፈልጉ፣ ነፃነታቸውን ከምንም በላይ የሚወዱ አሉ፣ 🎭🌧️ በሰው መሀል በጣም ተጫዋች ሆነው፣ ብቻቸውን ሲሆኑ ግን ጥልቅ የብቸኝነት ስሜት የሚያጠቃቸው አሉ፣ ይህ ሁሉ በአጋጣሚ የመጣ ይመስላችኋል? ፍጹም አይደለም! ወደዚህች ምድር ስንመጣ ተፈጥሮ ያደለችን የተለየ ኃይል፣ የተፈጥሮ ጠባይ፣ ጥንካሬ እና ድክመት አለ። ያንን ማንነታችንን እና ከጀርባ ያለውን ምስጢር ነው የኮከብ ቆጠራ የሚተነትንልን። 🧩 ለምን እንደዚህ ዓይነት የተለየ ጠባይ እንዳላችሁ፣ ❤️🩹 ፍቅር ላይ ደጋግማችሁ ለምን እንደምትጎዱ እና ማንስ እንደሚስማማችሁ፣ 💼✨ ድብቅ የተፈጥሮ ተሰጥዖአችሁ እና ለእናንተ የሚስማማውና ስኬታማ የሚያደርጋችሁ የስራ/የትምህርት መስክ የትኛው እንደሆነ፣ 🧘♂️🔥 ቁጣችሁን እና ስሜታችሁን እንዴት መቆጣጠር እንደምትችሉ፣ 🤝 ከሰዎች ጋር (ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ፣ ከፍቅረኛ) ያላችሁን ግንኙነት እንዴት ማሳመር እንደምትችሉ፣ 🪞 እና ከሁሉ በላይ በውስጣችሁ ተደብቆ ስላለው ትክክለኛ ማንነታችሁ ነው! ✨ አብራችሁን ከቆያችሁ... ማንም ያልነገራችሁን፣ ምናልባትም እናንተም ጭምር የማታውቋቸውን የራሳችሁን አስገራሚ ድብቅ የስነ ልቦና ምስጢሮች ትረዳላችሁ ! 👁️ ✨ ኮከባችሁን ወደ ዌብሳይታችን ግቡና "ኮከብዎን ይወቁ" የሚለው ፎርም ላይ የተወለዳችሁበትን ቀን በትክክል በማስገባት ማወቅ ትችላላችሁ። የዌብሳይታችን ሊንክ 👇 https://mistre-kewakbt.blogspot.com
Open in Telegram