እስረኞች እየተከፈላቸው ስራ ጀምረዋል - ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተገናኘ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ በበርካታ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ የሠራተኛ እጥረት በማጋጠሙ ምክንያት እስረኞችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መጀመሩን አስታውቀዋል። እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ፣ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ በቂ የሰው ኃይል ማግኘት አስቸጋሪ በመሆኑ እስረኞች ተገቢው ክፍያ እየተፈጸመላቸው በልማት ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ እየተደረገ ይገኛል። በተለይም በሹፍርና፣ በቀለም ቅብ፣ በጽዳት፣ በወለል ንጣፍ እና በሌሎችም መሰል የሙያ መስኮች ላይ ሠራተኛ ማግኘት ፈታኝ መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ዜጎች ሥራን ሳይንቁ የተገኙትን የሥራ ዕድሎች በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባቸው አሳስበዋል። @Seledadotio @Seledadotio
Open in Telegram
ሰሌዳ | Seleda
የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ! ምርት እና አገልግሎታችሁን ገጻችን ላይ ለማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን @Seledanewsbot
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 25, 2026 | 6,595 |
| Nov 26, 2026 | 3,336 |
Most viewed this month
- 01Views8.54KForwards363Reactions68Comments—
- 02Views7.7KForwards85Reactions92Comments—
- 03Views7.65KForwards142Reactions44Comments—
- 04Views7.55KForwards44Reactions32Comments—
Latest posts
«የተዘረፈውን የሕዝብ ሀብት በማስመለስ ተጠያቂነት ሊሰፍን ይገባል» – የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የ7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ሲሆን፣ ከቀረቡት ጉዳዮች መካከል ብልሹ አሠራር እና ሙስና ዋነኛው መሆኑ ተገልጿል። የምክር ቤቱ አባላት በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የግል ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ፣ ዜጎችን የሚያስለቅሱ እና ሥልጣናቸውን ለበደል የሚጠቀሙ አካላት መኖራቸው በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለውን እምነት እየሸረሸረ ይገኛል። እነዚህ ጥቂት ሙሰኞች የሕዝብን ሀብት ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ እንደሚገኙ የጠቆሙት አባላቱ፣ ችግሩን ለመቅረፍ በዲጂታል ሥርዓት ላይ እንደ ሀገር እየተሠራ ቢሆንም ሙስና አሁንም ስጋት ሆኖ መቀጠሉን አመላክተዋል። ለሀገር ልማት መዋል የሚገባው ሀብት በጥቂት ሙሰኞች ኪስ መግባቱ የትውልዱን ሞራል እየገደለ መሆኑን ያነሱት የምክር ቤቱ አባላት፣ ችግሩን ማውገዝ ብቻ በቂ ባለመሆኑ ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ እና የዘረፉትን የሕዝብ ሀብት እንዲመልሱ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል። @Seledadotio @Seledadotio
Open in Telegramቡርኪናፋሶ በ61.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የገነባችውን ግዙፍ የቴክኖሎጂ አካዳሚ መርቃ ከፈተች የቡርኪናፋሶው ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ በ61.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በ11 ወራት ጊዜ ውስጥ የተገነባውን «አካዳሚ ቴክኖሎጂክ ዱ ፋሶ» የተሰኘ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋም ኅዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. ኅዳር 23 ቀን 2026) መርቀው ከፈቱ። በ60 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ የትምህርትና ምርምር ተቋም፣ የሀገሪቱን ሳይንሳዊ ራስን መቻልና የኢንዱስትሪ ዕድገት ለማፋጠን ታልሞ የተገነባ መሆኑ ተገልጿል። አካዳሚው በመጀመሪያው ዙር 250 ተማሪዎችን ተቀብሎ የኒውክሌር ምሕንድስና፣ አቪዬሽን፣ ማዕድን እና የሳይበር ደኅንነትን ጨምሮ በ11 ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ሥልጠና እንደሚሰጥ ተመላክቷል። @Seledadotio @Seledadotio
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 1,773 |
| 4 h | 4,090 |
- After 1 hour1,773
- Total to date4,090
የደረት ማቃጠል የደረት ማቃጠል በተለያዩ የጤና ችግሮች ምክንያት ሊከሰት የሚችል ምልክት ነው። ከሆድ አሲድ ወደ ምግብ ቧንቧ በመመለስ (Acid Reflux) ምክንያት ሲከሰት፥ በሌላ ጊዜ ከልብ በሽታዎች ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። ምክንያቶች የሆድ አሲድ መመለስ (Acid Reflux)፦ የሆድ አሲድ ወደ ምግብ ቧንቧ ሲመለስ በደረት አካባቢ የማቃጠል ስሜት ይፈጥራል። የልብ ችግር፦ ወደ ልብ ጡንቻ የሚደርሰው ደም ሲቀንስ ወይም ሲቋረጥ የደረት ማቃጠልና ጫና ሊሰማ ይችላል። የጡንቻ ችግር፦ በደረት አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች ሲጎዱ ወይም ሲወጠሩ ሕመም ሊከሰት ይችላል። የሳንባ ችግር፦ አንዳንድ የሳንባ በሽታዎችም በደረት አካባቢ ሕመምና ማቃጠል ሊያስከትሉ ይችላሉ። የደረት ማቃጠል መቼ አደገኛ ይሆናል? የደረት ማቃጠል በራሱ ሁልጊዜ የልብ ድካም ምልክት አይደለም። ነገር ግን ከሚከተሉት ሁኔታዎች ጋር ከተያያዘ አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ያስፈልጋል። @Seledadotio @Seledadotio
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 3 h | 3,557 |
| 5 h | 5,100 |
- After 6 hours5,100
- Total to date5,100
በጎፋ ዞን ዑባ ጌዞ ቤቶ ከተማ አምስት እግር ያለው የፍየል ግልገል ተወለደ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጎፋ ዞን፣ ዑባ ጌዞ ቤቶ ከተማ ሆሼለ ቀጠና ውስጥ አምስት እግር ያለው የፍየል ግልገል በመወለዱ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ትኩረት መሳቡን በአካባቢው የተደረገ ምልከታ ያሳያል። ግልገሉ አምስት እግሮችን ከመያዙ በተጨማሪ በርካታ ያልተለመዱ የአካል ገጽታዎች ታይተውበታል። በምልከታ ከተለዩት ዋና ዋና ባህሪያት መካከል፦ * በታችኛው የሆድ እና የቆለጥ ክፍል አካባቢ የሚገኘው ተጨማሪ እግር ወደ ጎን ወይም ዞሮ የሚታይ ሲሆን፣ ቅርጹም እንደ ቀስት የተጠማዘዘ መስሎ ይታያል። * አጠቃላይ የእግሮቹ ቅርጽ ከተለመደው የፍየል እግር አወቃቀር የተለየና የተዛባ ነው። * ሁለት ቆለጦች በግልጽ ይታያሉ። * በጭንቅላቱ አካባቢ የተለመደ ያልሆነ ቀዳዳ ተስተውሏል። * በዓይኖቹ ላይ ብርሃን ሲያርፍ እንደ ባትሪ ብርሃን የሚያንጸባርቅ ይመስላል። ተጨማሪ እግር ይዞ የመወለድ ሁኔታ በእንስሳት ሕክምና Polymelia ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን፣ በፅንስ እድገት ወቅት በሚከሰት የአካል እድገት መዛባት ሊፈጠር እንደሚችል ይገለጻል። ይሁን እንጂ በግልገሉ ላይ የሚታዩትን የተለያዩ የአካል ለውጦችና ገጽታዎች ዝርዝር ሁኔታ በእርግጠኝነት ለመለየት የእንስሳት ሐኪም ምርመራ ማድረግ ይጠይቃል። የባለሙያ ክትትልና ተገቢ እንክብካቤ መስጠትም ግልገሉን ለመከታተል አስፈላጊ መሆኑ ተመላክቷል። Via Duki DM @Seledadotio @Seledadotio
Open in TelegramለChatGPT ወይም ለGemini "ሰላም" ስትለው፣ እሱ በዚያው ቅጽበት አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውኃ ጭልጥ አድርጎ እንደሚጠጣ ታውቃለህ? 😂💧 የምንጠቀምበትን ኢንተርኔት፣ ክላውድ (Cloud) እና ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የሚያንቀሳቅሱት ግዙፍ የዳታ ማዕከላት (Data Centers) ጉሮሯቸው በጣም ደረቅ ነው! ሰርቨሮቻቸው ከመጠን በላይ ግለው እንዳይቃጠሉ ለማቀዝቀዝ በቀን እስከ 5 ሚሊዮን ጋሎን ንጹሕ ውኃ ይጠጣሉ። እስቲ ይህንን አስቡት አንድ ትልቅ የዳታ ማዕከል በቀን ከ1 እስከ 5 ሚሊዮን ጋሎን ውኃ ይጠቀማል። ይህ ማለት 50,000 ሕዝብ ያላትን አንዲት ሙሉ ከተማ የውኃ ፍጆታ ብቻውን ይጨርሳል ማለት ነው፤ ከእነዚህ ጋር ውኃ መጋራት ራሱ ይከብዳል! ዋናው ችግር ደግሞ የተጠቀሙት ውኃ ተመልሶ አለመገኘቱ ነው። "የጠጡት" ውኃ በትነት መልክ ወደ ሰማይ ስለሚወጣ፣ ተመልሶ ወደ ወንዙም ሆነ ወደ ቧንቧችን አይገባም። የሚገርመው ደግሞ ከ2022 ወዲህ ከተገነቡት አዳዲስ ማዕከላት መካከል ሁለት ሦስተኛው የተተከሉት ቀድሞውኑ ከፍተኛ የውኃ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች መሆኑ ነው። በዚህም ምክንያት የአካባቢው ገበሬ ቤተሰቡና እንስሳቱ በውኃ ጥም እየተቸገሩ፣ ሰርቨሮቹ ግን "ውኃ አምጡ" ይላሉ። ይበልጥ አሳሳቢው ግን የወደፊቱ ስጋት ነው! በቴክሳስ ብቻ በ2025 ወደ 49 ቢሊዮን ጋሎን ውኃ የጠጡት እነዚህ ማዕከላት፣ በ2030 ጥማታቸው ጨምሮ 399 ቢሊዮን ጋሎን ሊደርስ እንደሚችል ተተንብዮአል። ቴክኖሎጂው መልካም ነው፤ ሕይወታችንንም አቅልሎልናል። ሆኖም የሰው ልጅንና የተፈጥሮን ጉሮሮ እያደረቀ መሆን የለበትም አይደል? አዳዲስ የዳታ ማዕከላት ከመገንባታቸው በፊት "ውኃውን ከየት ነው የምታመጡት? ስንትስ ትጠቀማላችሁ?" ተብለው ሊጠየቁ ይገባል። @Seledadotio @Seledadotio
Open in TelegramConnections
Similar channels
Zehabesha@zehabeshanewsNews and media53.5K
BBC News Afaan Oromoo@bbcafaanoromooNews and media51.5K
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ@sputnik_ethiopiaNews and media50.8K
DW Amharic@dw_amharicNews and media56.8K
4-3-3 World News@ethionews433News and media49.8K
Muktarovich Ousmanova@muktarovichousmanovaNews and media59.5K
"ኡማ ቲቪ " Tv@ethioomahtvchannleNews and media44.3K
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal@zena24nowNews and media40.8K