ኅዳር 19 - 25 10ኛ ትምህርት Nov 28 - Dec 4 ትንቢታዊ ስልጣንና ጠቃሚነቱ። ሰንበት ከሰዓት በኋላ ለዚህ ሳምንት ጥናት እነዚህን ጥቅሶች ያንብቡ። ዘፀ 4፥10-16፣ ሉቃ 8፥22-25፣ ዮሐ 3፥1-10፣ የሐዋ 16፥25-34፣ 1ኛ ቆሮ 5፥1-5፣ ሉቃ 7፥28። የመታሰቢያ ጥቅስ፡”የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል” (ዕብራውያን 4፡12)። በህዳር ወር 1989 ዓም በኮሙኒከት ምስራቅ ጀርመን ጉንተር ስቻቦዊስኪ በቴሌቪዥን ያስተላለፈው ቀጥታ ንግግር ለበርሊን ግንብ መውደቅ ዋዜማ ሆነ። የምስራቅ ጀርመን ዜና ማሰራጫዎች ወኪል ሆኖ ሲናገር ማስታወቂያውን በትክክል አላስተላለፈም ነበር። የምስራቅ ጀርመን ነዋሪዎች አስቸጋሪና አስፈላጊ የሆነውን ተገቢ ቪዛ ካገኙ በኋላ ምዕራብ አውሮፓን መጎብኘት ይችላሉ በማለት ፋንታ እንዲሁ በደፈናው የምስራቅ ጀርመን ነዋሪዎች ምዕራብ አውሮፓን መጎብኘት ይችላሉ አለ። አንድ ጋዜጠኛ የፖሊሲ ለውጡ መቼ ይጀምራል ብሎ ሲጠይቀው ስቻቦዊስኪ “እኔ እንደማውቀው ከሆነ ከአሁን ጀምሮ ምንም ሳይዘገይ” አለ። ታዲያ ህዝቡ ይህን ሲሰማ መንግስት ባሳወቀው መሰረት ወደ ድንበሩ ኬላ በመጉረፍ ለማለፍ ፈለገ። ሰዎች ለተቋማትና ለሀገራት እንዲናገሩ ይወከላሉ። ለእግዚአብሔር የሚናገሩትስ? በዚህ ሳምንት ነቢያት ምን አይነት ስልጣን እንዳላቸው እንመረምራለን። መጽሐፍ ያልፃፉት ነቢያት እንደነ ናታን እና እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት፣ ኤለን ጂ ዋይት ሳትቀር ምን ስልጣን አላቸው? @SabbathSchool @TekalignSorato
Open in Telegram
SABBATH SCHOOL (ሰንበት ትምህርት)
@TekalignSorato +251913070430 Daily Spiritual & Religious Education. Live Q&A Sessions & Daily Training. YouTube Content & Livestreams!
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 22, 2026 | 1,980 |
| Nov 23, 2026 | 1,740 |
| Nov 24, 2026 | 1,510 |
| Nov 25, 2026 | 1,350 |
| Nov 26, 2026 | 1,300 |
| Nov 27, 2026 | 1,243 |
| Nov 28, 2026 | 314 |
Most viewed this month
- 01Views2.05KForwards—Reactions21Comments—
- 02Views1.97KForwards—Reactions3Comments—
- 03Views1.92KForwards—Reactions—Comments—
- 04Views1.74KForwards—Reactions17Comments—
Latest posts
Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 11 h | 541 |
| 26 h | 1,290 |
- After 24 hours1,290
- Total to date1,290
Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 11 h | 661 |
| 27 h | 1,370 |
- After 24 hours1,370
- Total to date1,370
ዓርብ ህዳር 18 Nov 27 “ቅመሱና እዩ ቅመሱና እዩ” የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን የኤለን ጂ ዋይትን ትንቢታዊ ስጦታ መቀበልን በተመለከተ፣ ከመጀመሪያ አንስቶ እስካሁን ድረስ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ነቢያት የገጠማቸውን የሚመስል የአቀባበል ችግር ገጥሟታል። ኤለን ጂ ዋይት በታኅሳስ ወር 1844 የመጀመሪያ ራእይዋን ስትቀበል አንዳንድ ሰዎች ነቢይነቷን ሊቀበሉ አልፈለጉም። ይህ ሁኔታ ሰንበት ጠባቂዎች አድቬንቲስቶችን (በኋላ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት የተባሉትን) የኤለን ጂ ዋይትን የነቢይነት ስጦታ የሚደግፍ መከራከሪያ (ማስረጃ) ወደ ማዘጋጀት መራቸው። መጀመሪያ፣ ትንቢታዊ ስጦታ እስከ ዘመን መጨረሻ ድረስ እንደሚቀጥል የሚያሳይ ሥነ መለኮታዊ መረጃ አቀረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ ዘመናዊ የትንቢት ስጦታ እንደሚኖር ይደግፋል እያሉ ተከራከሩ። ኢዩኤል 2ን፣ ራዕይ 12፥17ን እና ሌሎችን ጥቅሶች በመጥቀስ “በመጨረሻ ጊዜ” የትንቢት ስጦታ እንደሚኖር ማስረጃ አቀረቡ። እንዲያውም የቅሬታዋ ቤተ ክርስቲያን እንዱ መለየዋ የትንቢት መንፈስ ስጦታ መሆኑን ተከራከሩ። (Gerald ___, “The gift of prophecy and God’s Remenant church” The gift of prophecy chapter 4)። ሁለተኛ፣ ቀደምት አድቬንቲስቶች የኤለን ጂ ዋይት ስጦታ በአማኞች ላይ መልካም ተጽኖ አስገኝቷል ብለው ዘገቡ። ለምሳሌ በ1840ዎቹ መጨረሻ ላይ የተደረገውን የሰንበት ጉባዔ (ኮንፍራንስ) ይከታተሉ የነበሩ አማኞች በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮዎች ላይ ባልተስማሙ ጊዜ አንድ እንዲሆኑ ረድቷቸዋል። በሚቀጥሉት አያሌ አስርት ዓመታትም ስጦታዋ “መልካም ፍሬ” ማፍራቱን ቀጥሏል። ጽሑፎቿም በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት የእምነት ማህበረሰብ ውስጥ ተጽእኖ ማሳደሩን ቀጥለዋል። ሦስተኛ፣ ኤለን ጂ ዋይትን ከጥቃት ለመከላከል ያቀረቡት መከራከሪያቸው (ማስረጃቸው) ደግሞ ራእይ በምታይበት ጊዜ ከተፈጥሯዊ ውጪ የሆኑ ሁኔታዎችን መለማመዷ ነው። ባለፈው እንደጠቀስነው በራዕይ ላይ ስትሆን ኤለን ጂ ዋይት ከተፈጥሮ ውጪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ሆና ከዚህ በፊት ያላወቀቻቸው የወደፊቱ ክስተቶች እንደተገለጡላት፣ ከተፈጥሮ ውጪ የሆነ የአካል ብርታት እንዳገኘች፣ ራእይ የምታይበትን ጊዜና ሁኔታ መቆጣጠር እንደማትችል መናገራቸው ከተጠቀሱት ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው። 7ኛ ቀን አድቬንቲስቶች ዛሬም የኤለን ጂ ዋይትን ነቢይነት ይቀበላሉ፣ ይደግፋሉም። እነዚህ መከራከሪያዎች (መረጃዎች) ሁሉ መልካም ሳሉ ለኤለን ጂ ዋይት ሰጦታ ዋናው ማስረጃ ግን በጽሑፎችዋ የተገለጠው የራሷ የህይወት ተሞክሮ ነው። ባለመዝሙሩ ዳዊት እንደሚለው “እግዚአብሔር መልካም እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም” (መዝ 34፥8)። ነቢይነቷን መገምገም የምንችለው ጽሑፎቿን በጸሎት ስንመረምር ብቻ ነው። ንባባችንን ወይም ምርመራችንን ለመጀመር አንዱ ቦታ ሀይለኛ የሆነችውን ትንሿን ወደ “ክርስቶስ የሚያደርስ መንገድ” የምትለውን መጽሐፍ ማንበብ ነው። ከዚያም 5 ጥራዝ ያለውን “Conflict of the Ages” የሚለውን መጽሐፍ በማንበብ ግምገማችንን ብንቀጥል ይመረጣል። ይህ መጽሐፍ ታላቁን ተጋድሎ ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ዮሐንስ ይዘረዝራል። መጽሐፍቷ በወረቀትም ሆነ በኤሌክትሮኒክ መረጃ ማሰራጫዎች በቀላሉ ይገኛሉ (EG writings. Org ይመልከቱ)። መጽሐፍቷም ወደ ብዙ ልዩ ልዩ ቋንቋዎች ተተርጉመዋል። @SabbathSchool @TekalignSorato
Open in Telegramሐሙስ ህዳር 17 Nov 26 የተፈጸሙ ትንቢቶች። ሰዎች ነቢይ የወደፊቱን የሚተነቢይ ነው ብለው ያስባሉ። ይህ የነቢይ አንዱ ሥራ ነው። የነቢይ ስራ ሌላም ብዙ ነገሮችን ያካትታል። ነቢያት ሰዎች ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ ይመራሉ፤ ምክርን፣ ማስጠንቀቂያንና ማደፋፈርንም ያበረክታሉ (ይሰጣሉ)። ሰዎች ወደፊት የሚሆኑ ክስተቶችን እንዲያውቁና እንዲዘጋጁ ከማድረግ አልፎ፣ ነቢያት የወደፊቱን ለምን ይተነብያሉ? ኤርምያስ 28፥9፣ 15- 27ን ይመልከቱ። Save Notes ነቢይ የሚፈተንበት አንዱ ሌላው መስፈርት ትንቢቱ መፈፀሙ ነው። የእውነተኛ ነቢይ ትንቢት ልክ እንደተናገረው መፈጸም አለበት። “ነቢይ በእግዚአብሔር ስም በተናገረ ጊዜ የተናገረው ነገር ባይሆን ባይመጣም ያ ነገር እግዚአብሔር ያልተናገረው ነው፣ ነብዩ በድፍረቱ ተናግሮታል እሱን አትፍራው (ዘዳ 18፥22)። ይህ ፈተና አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም አንዳንዶቹ ትንቢቶች ቅድመ ሁኔታ ያዘሉ ናቸው። ቅድመ ሁኔታዎቹ ካልሆኑ ትንቢቶቹ ላይፈጸሙ ይችላሉ። ይህን መርህ በዮናስና ለነነዌ በሰጠው ማስጠንቀቂያ ውስጥ እናያለን። የዮናስ መልዕክት እጥር ምጥን ያለችና ግልጽ ነበረች። “በአርባ ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች” (ዮናስ 3፥4)። ነገር ግን ትንቢቱ አልተፈጸመም። ለምን? ኤርምያስ 18፥7-10ን ያንብቡ። ይህ በሁኔታዎች ስላሚደገፈው ትንቢት ምን ያስተምረናል? Save Notes ቅድመ ሁኔታን ያዘሉ ትንቢቶች ህዝቡ ለእግዚአብሔር መልእክት በሚመልሱት መልስ ላይ ይተማመናል። ህዝቡ ሀሳባቸውንና ስራቸውን ከቀየሩ የተነገረው ትንቢት ላይፈፀም ይችላል። የነነዌ ሰዎች የዮናስን ትንቢት ሰሙና መንገዳቸውን ቀየሩ። ስለዚህ እግዚአብሔር አላጠፋቸውም። ቀጣዮቹ ትውልዶች ግን እንደገና ወደ ክፋታቸው ሲመለሱና ነነዌ እንደገና ክፉ እና ጨካኝ ስትሆን እግዚአብሔር አጠፋት። እግዚአብሔር ወደፊት የሚሆነውን ያውቃል። እኛ ግን አናውቅም። ምርጫዎቻችን ወደፊት ምን እንደሚደርስብን ወሳኝ ናቸው። ቅድመ ሁኔታዎችን ያዘለ የትንቢት ሀሳብ ማስተዋል ለምን ይጠቅማል? ይህ ግንዛቤ የመጽሀፍ ቅዱሳዊውን እውነት በበለጠ ለማስተዋል እንዴት ይረዳናል? @SabbathSchool @TekalignSorato
Open in Telegramረቡዕ ህዳር 16 Nov 25 መልካም ፍሬዎች። በተራራው ስብከት ላይ (ማቴ ምዕራፍ 5-7) ክርስቶስ የክርስቲያን ቤተ ክርስቲያንን መሰረት ጣለ። የዚያ መሠረት አንዱ ክፍል ትንቢታዊ አገልግሎት ነበር። ታድያ ስለ ሐተኛ ነቢያት አስጠነቀቀ። “በፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ” አለ (ማቴ 7፥20)። የፍሬ ጥራቱን ለማወቅ ጊዜ ይወስዳል። ፀባዩን (ባህርዩን) ወይም ፀባይዋን በመመልከት መልዕክቱ ወይም መልእክቷ ምን ውጤት እንደሚያስገኝ በመመልከት ነብዩ ወይም ነቢይቱ ሰዎችን ወደ ክርስቶስ እያቀረቡ ወይም ከእርሱ እያራቁ እንደሆነ ማየት ይቻላል። ዮሐ 1፥1-3፣ የሐዋ 15፥36-39 እና ገላትያ 2፥11-14ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ ነቢያት ምን ያስተምሩናል? Save Notes ሆኖም ነቢይ መሆን አንድን ሰው ኃጢአት የለሽ ወይም የማይሳሳት አያደርገውም። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌ የሚሆኑትን እነ ዮሐንስን፣ እነ ጳውሎስንና እነ ጴጥሮስን እናያለን። እንከን የለሽ እግዚአብሔር ብቻ ነው። መልእክተኞቹ ግን ጉድለት አይታጣባቸውም። ነገር ግን አቅጣጫቸው ወደ እግዚአብሔር ነው። ነቢያት በአኗኗሯቸው መልዕክቱን የሚፃረር ፀባይ በማሳየት መልዕክቱን ማበላሸት የለባቸውም። ማንኛውም ነቢይ ክርስቶስ የኖረውን አይነት ፍጹም ኑሮ መኖር አይችልም። ነገር ግን እውነተኛ ነቢያት የእግዚአብሔርን መንግስት ደንብና አኗኗር ይከተላል (ማቴ 7፥16-20)። የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነኝ እያለ አኗኗሩ ግን ሲያስተላልፈው የነበረውን መልዕክት በጭፍን ከተፃረረ ያ አይነት ሰው ሊታመን አይገባውም። የነቢይነት ስራ ከባድ ቢሆንም,ብዙ ነቢያት “መልካም ፍሬ” አሳይተዋል። ለምሳሌ ሙሴ እስራኤላውያንን በምድረ በዳ በጥሩ ስኬት መራቸው (ዘዳ 34፥10-12)። ሀጌ 19 ዓመት ተቋርጦ የነበረውን ሁለተኛውን ቤተ መቅደስ እንዲሰሩ የይሁዳን ነዋሪዎች አደፋፍራቸው (ሐጌ 1፥12)። የኢሳይያስ የማያፈገፍግ መልዕክት አራት ነግስታትን በአስቸጋሪ ጊዜያት መራ። መልእክቱም ወደ መሲሁ ያመላክት ነበር (ኢሳ 39፥5ና ኢሳ 53፥4-6)። የዳንኤልን ከልብ የመነጨ ኑዛዜ (ዳንኤል 9፥15)፣ የኤርምያስንም ልባዊ ቆራጥነት ልንረሳ አንችልም (ኤርምያስ 9፥1)። የእግዚአብሔር ነቢያት ቢሰደዱና ቢበደሉም የእውነተኛ ነቢያት ዋና መስፈርት የሆነውን ለእግዚአብሔር እና ለህዝቡ ፍቅራቸውን ያሳዩ ነበር። የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮች በስራቸው እና በፀባያቸው ስንት ጊዜ አሳዝነዎታል? ከዚያ ልምምድ ምን አይነት ጠቃሚ ትምህርት ምማር ይችላሉ? @SabbathSchool @TekalignSorato
Open in Telegramሰላም ለእናንተ ይሁን ዛሬ የSabbathSchool Live ፕሮግራም ባለመኖሩ ይቅርታ እንጠይቃለን ። @SabbathSchool @TekalignSorato
Open in Telegramማክሰኞ ህዳር 15 Nov 24 የክርስቶስ ስጋ መልበስ 1ኛ ዮሐንስ 4፥1-3 የሚነግረን ክርስቶስ ስጋ ለብሶ መምጣቱን የማመን ፈተና ከሌሎች ታላላቅ ሃይማኖቶች የመጡ ነቢያት እንደሆኑ የሚናገሩትን ወይም ከማንኛውም ሃይማኖት ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው ከመንፈሳዊው ዓለም ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የሚናገሩ ሰዎች ክርስቶስ ሥጋ ለብሶ መምጣቱን ሳያምኑ ነቢያት ነን ቢሉ ተቀባይነት እንደሌላቸው እናውቃለን። “ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም” (1ኛ ዮሐ 4፥3)። ዮሐንስ ይህን ጥቅስ ሲጽፍ ክርስቶስ ሰው ነኝ ይላል እንጂ ሰው አይደለም እያሉ ስለሚያስተምሩ ሀሰተኛ መምህራን እያሰበ ነበር። ይህ ፈተና ከዚህም ያልፋል። መፈተኛው ነቢይ ነኝ የሚለው ሰው ክርስቶስ ስጋ ለብሶ በምድር ላይ የኖረ ትክክለኛ ሰው ነው ብሎ ማመኑ ብቻ እውነተኛ ነቢይ አያደርገውም። አብዛኞች ክርስቲያኖች ስለ ኢየሱስ ይህን ያምናሉ። የዮሐንስ ትንቢታዊ ማስጠንቀቂያ፣ ለአንድ የተወሰነ ሁኔታ የተፈለገ ቢሆንም፣ ለኋለኞቹ ትውልዶች የሚያስፈልጉ አስፈላጊ (ወሳኝ) እውነቶችን የያዘ ነው። የሚከተሉት ጥቅሶች ስለ ኢየሱስ ምን ይነግሩናል? ዮሐ. 3:16፤ 2ኛ ቆሮ. 5:21፤ ዮሐ. 11:25፤ ዕብ. 4:14፣ 15፤ ዮሐ. 14:1-3። Save Notes እውነተኛ ነቢያት ክርስቶስ ስጋ የለበሰ መለኮትና በርግጥም ሰው መሆኑን ማመንና ማስተማር አለባቸው። ስለ ክርስቶስ ሙሉ እውነት--ስለ ተልዕኮው፣ ስለ ኃጢአት የለሽ ሕይወቱ፣ ስለ የስርየት ሞቱ፣ ስለ ትንሳኤው፣ በሰማይ ስለሚያከናውነው የሊቀ ክህነት አገልግሎቱና ስለ ዳግም ምጻአቱ የተሟላ እውነት ማቅፍ አለባቸው። ይህ ክርስቶስ በምድር ላይ ስለ መኖሩ በሀሳብ ተስማምቶ ብቻ የሚታለፍ ነገር አይደለም። የነቢይ መልእክት ዋናው ትኩረቱ ኢየሱስ ላይ ነው እንጂ እንዲሁ እግረ መንገዱን ነካ አድርጎ የሚያልፈው ርዕሰ አይደለም። መልእክቱ ወይም መልዕክቷ ሰዎችን ከክርስቶስ ጋር የሚያድን ግንኙነት ወደ መፍጠር መምራት አለበት። በመንፈስ ቅዱስ የተመራ ትንቢታዊ የእግዚአብሔር ቃል የንጋት ኮክብ የሆነው ኢየሱስ በውስጣችን ያለውን ጨለማ እስኪያስወግድ ድረስ በልባችን ውስጥ እንዲነጋና ትንቢታዊው ስጦታው ከእርሱ ጋር አቆራኝቶን በቀጣይነት ወደ እርሱ እንዲያመለክተን ማድረግ ነው። ክርስቶስን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ነቢያት የራሳቸውን ተከታዮች አይሰበስቡም፣ ወይም ራሳቸውን ከፍ ከፍ አያደርጉም (የሐዋ 4፥12)። መልእክቱን እንዲያደርሱ የተላኩባቸውን ሰዎች ያገለግላሉ እንጂ ሰዎቹ እንዲያገለግሏቸው አያደርጉም። ይህ እንዳለ ሆኖ በነገው ክፍል እንደምናየው፣ የእግዚአብሔር ነቢያት እንደ እኛ ሰዎች ነበሩ። እንደ ሁላችንም ወንጌሉ የሚያስፈልጋቸው ኃጢአተኞች ነበሩ። ክርስቶስ፣ ሙሉ በሙሉ አምላክ፣ በእኛ ምትክ የሀጥያታችንን ሸክም ተሸክሞ መሞቱን ማስተዋል የእምነታችን ማዕከል የሆነው ለምንድን ነው? ይህን አስተምሮ ካላስተዋልነው ምን ይቀርብናል? @SabbathSchool @TekalignSorato
Open in Telegramሰኞ ህዳር 14 Nov 23 ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር መጣጣም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር መጣጣም/መስማማት መስማማት እኛ ሰዎች በቃላችን ባንቆምም እግዚአብሔር ግን አይዋሽም (ዘሁ 23፥19ን ይመልከቱ)። በነቢያት በኩል የሚሰጣቸው ትንቢታዊ መልዕክቶች ይህኑ የማይዛነፍ እውነተኛነቱን ያሳያሉ። ኢሳያስ 8፥20ን ያንብቡ። ምን ወሳኝ ነጥብ ይጠቁማል? Save Notes የትንቢታዊ ስጦታ መመዘኛ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። ነቢያት የሚናገሩት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር መስማማት አለመስማማቱ መፈተን አለበት። እውነተኛ ነቢይ መጽሐፍ ቅዱስን አይቃረንም፣ አያጣጥልም ወይም ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ሰዎችን አያወናብድም። በሀሰተኛ ነቢያት እንዳይታለሉ ወይም እነርሱን እንዳይከተሉ ነገር ግን እግዚአብሔርን እንዲከተሉ እንዲረዳቸው ሰዎች ቃሉን ጠንቅቀው ማወቅ አለባቸው። በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን ነቢያት ትንቢታዊ መልእክታቸውን ለማጠናከር ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ነቢያት ይጠቅሳሉ። እነዚህ ነቢያት ካለፉት ትንቢቶች አዲስ ማብራሪያዎችን ያክላሉ እንጂ በፍጹም ተቃራኒ መልዕክት አያስተላልፉም። ባለፉት ምዕተ-አመታት እግዚአብሔር ስለሰጠን ትንቢታዊ መልዕክቶች እነዚህ ጥቅሶች ምን ያስተምሩናል? 2ኛ ጴጥ 1፥19-21፣ ሮሜ 15፥4፣ ያዕ 1፥17። Save Notes የድነት ዕቅድን ለመረዳት የብሉይ ኪዳን መሠረት ያለው እገዚአብሔር ራሱ በዘፍጥረት 3፥15 ላይ በሰጠው የመጀመሪያው ተስፋ ውስጥ ነው። የመስዋዕቱ ስነ- ስርአት የዚያ የማዳን ዕቅድ ምሳሌያዊ መግለጫ ነበር። ነገር ግን የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ ከሰዎች መካከል በመኖሩ፣ በመሞቱና በመነሳቱ ተስፋ እንዴት እንደሚፈጽም በተከታታይ ለነቢያት ተብራርቷል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዘገባ የሚያሳየው ደግሞ እግዚአብሔር እውነቱን የሚገልጠው ሰዎች ሊያስተውሉት በሚችሉት መንገድ መሆኑን ነው። በተከታታይ ትውልዶች ሰዎች ቃሉን የማስተዋል ችሎታቸው ጠለቅ እያለ ይሄዳል። “የእውነቱ መገለጥ” ወይም “የእውነት እድገት” የሚባለው ለዚህ ነው። ይህ ማለት አዲስ ትውልድ ካለፈው ትውልድ ይልቅ እውነቱን በበለጠ ለመረዳት ይችላል ማለት ነው። ነገር ግን አንድ መገንዘብ የሚገባን ወሳኝ ነገር አለ። አዲሱ እውቀት የቀድመውን እውቀት የሚቃረን መሆን የለበትም። @SabbathSchool @TekalignSorato
Open in TelegramConnections
Similar channels
🎧Nashiidaalee Islaamaa Channel🎼🎼🎼🎼🎧@nashiidaa_islaamaa_channelReligion9.72K
ኢስላማዊ እውነታ@islamictruethReligion9.92K
Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ@fantahun_wakieReligion9.38K
ISLAMIC SCHOOL@islam_and_scienceReligion10.2K
እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net@ewnetlehuluReligion10.2K
ፍቁረ እግዚእ ሚዲያ Fikure Egzi Media – FEM@fikureegzi4Religion10.2K
ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል@dania_islamicReligion10.3K
Dr. Tesfaye Robele@tesfayerobeleReligion10.4K