Forwarded from Christ Life Reflection || የክርስቶስ ሕይወት ነጸብራቅ
❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓ ✨በቅርቡ ከተለቀቁ የመዝሙር አልበሞች ውስጥ የትኛው የመዝሙር አልበም እናድርሳቹ የምትፈልጉትን መርጣቹ የሚመጣላቹሁን መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ
Open in Telegram
ወደ ቻናላችን እንኳን በደህና መጣችሁ በዚህ ቻናል ኢየሱስን ከፍ የሚያደርጉ ግጥሞች ፅሁፎች መዝሙሮችና ላይቭ ፕሮግራሞች ይኖሩናል አብረውን ይቆዩ
By publication day
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Oct 30, 2026 | 5,750 |
| Nov 2, 2026 | 4,340 |
| Nov 7, 2026 | 3,100 |
| Nov 10, 2026 | 3,430 |
| Nov 15, 2026 | 2,410 |
| Nov 17, 2026 | 2,920 |
| Nov 20, 2026 | 2,110 |
| Nov 27, 2026 | 199 |
Forwarded from Christ Life Reflection || የክርስቶስ ሕይወት ነጸብራቅ
❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓ ✨በቅርቡ ከተለቀቁ የመዝሙር አልበሞች ውስጥ የትኛው የመዝሙር አልበም እናድርሳቹ የምትፈልጉትን መርጣቹ የሚመጣላቹሁን መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ
Open in Telegram7 እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አምላኬም ይሰማኛል። * 8 ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ። * ት/ሚክ 7:7
Open in Telegramእንደገና ተነስ *-*-*-*-*-*-*-*-*-* በትጋት ውስጥ ነበርክ መውደቅ አልፈለክም ግና በማታውቀው ምክንያት መውደቅ አላቆምክም በድውይ ብትያዝ ሺ ብትታመምም ህይወት እንዲቀጥል መብላት አታቆምም መብላት ባትፈልግም ምን ባትሆን ደህና ታግለህ ትበላለህ ነገህ እንዲቃና መፀለይ ባትፈልግ መንፈስህ ተዳክሞ ህይወትህ ቢደክም ዳግም ባይመስልህም የምታየው ቆሞ ቃል ለማሰላሰል ባይኖርህ ፍላጎት መንፈሳዊ ስርዓት ማድረግህ አታቁም በቁም እንዳትሞት በቃ ወድቅያለው ዳግም አልነሳም ብለህ እንዳትቆርጥ ተስፋ ማረኝ ከምትልበት ከፀጋው ዙፋን ስር በፍፁም አትጥፋ በርትተህ እንደደከምክ ስትደክምም ለመበርታት በድጋሚ ተነስ በርከክ በልና ከቸሩ አባትህ የምህረት ልብስ ልበስ መፀለይ አታቁም ቃሉን ዙውትር አጥና ጠፍተህ ቢሆን እንኳን ምታመልከው አምላክ አለው እንደገና ✍ኤርሚያስ ክፍሌ react And Share @Kegetemku_leyesus
Open in Telegramአለምን አምኜ አለምን አምኜ አምላኬን ፈትኜ እንዲህ አድርግ ብዬ ከትዛዝ ባላነሰ ውርርድ ካላረከውማ ብዬ ፎክሬበት ከሰማይ ካልወረድክ መልሴ የዘገዬ የቀረ ሲመስለኝ ዓለም ደግሞ መጥታ ነይ እኔጋ ስትለኝ ባየው አንጋጥጬ ሰማይ ዝም ብሎአል ዓለም ደጃፌ ላይ ደስታ ሳቅ ክብር ተሰብስቦአል ታዲያ ያኔ ስለምነው ዝም ካለኝ ጩኼ ጩኼ ካልመለሰ ከሱ ጋራ እኔ ምን አለኝ ብዬ አለምን ተከትዬ ከቤት ወጣሁ በብር በወርቅ በመጠጡ ጮቤ ረገትኩ ማን እንደኔ ደስተኛ ማለት ጀመርኩ በከበቡኝ እልፍ ሰዎች ባሳዬችኝ ክብር ሰከርኩ መች ገብቶኝ በሰው ምሃል ለብቻዬ እንደቀረሁ መች አወቄ በሳኩ ቁጥር እልፍ ለቅሶ እንዳፈራሁ ዓለም ሆዬ በጉብዝናዬ ወራት ለአምላኬ ቃል እንዳልገዛ በ ብልጭልጭ ሽፍና ሬቱን በማር ቀብታ አጠፋችኝ እንደ ዋዛ እልፍ አበባ ይዛ አዱኛ ሰብስባ እንደከበበችኝ አበባው ሲረግፍ አዱኛው ሲደርቅ ባዶ አደረገችኝ እንዲህ ነበር ዓለም ከ እግዜር የለዬችኝ ግን እዉነት ሲገባኝ የዓለም ማንነት በልቤ ታወሰኝ ያ የአባቴ ቤት ሁሉ የሞላበት የምወደድበት እንደ ሎሌ ሳይሆን ልጅ የምሆንበት መጣሁ ወደ ደጅ ፈራ ተባ ብዬ ገና ከሩቅ ሲያየኝ እጆቹን ዘርግቶ እቅፍ አረገና ሳመኝ አባብዬ. ✍Tesfa Degu ✍✍ React And Share @Kegetemku_Ieyesus
Open in Telegramእምባ ለካስ ያምራል😭😭 እምባ ለካ ያምራል ሲታይ ያስደስታል ከ አይን እየወጣ ልብን የሚያፅናና ከምድር አርቆ ሚያስብል አየሱስ ና ለካስ ልቅሶ አለ ልብ ዉስጥ ሚገባ ስምህን እየጠራደግሞ ወደሌላው ረሃብን ሚያጋባ ስላንተ ሚለቀስ ፍቅርህ አይሎበት ክብርህ መገለጡ እጅግ እጅግ ናፍቆት ክብርህ ከላይ ወርዶ በምድር ላይ ከብዶ ትዉልድ ሁሉ አንተን አይቶ ጌትነትህን ሁሉም አዉቆ ማራናታ ማለታችን አንተን ናፍቀን የከበደ ያንተን ክብር ተመልክተን አንተን አንተን እንድንል ጌታ እየሱስ ያንን የጥንቱን ዘመን ክብር መልስ ደግሞ በኛ ዘመን ክብርህ ብቻ ይስራ ስምህን ብቻ ሰምቶ ፍጥረት ሁሉ አንተን ይፍራ. ✍✍✍Tesfa Degu✍✍✍ React And Share @Kegetemku_leyesus
Open in Telegramጊዜ የለንም እንጂ *-*-*-*-*-* ቃልህን ለመስማት፣ከእግርህ ስር መቀመጥ በመንፈስ ለመሞላት ለመዋል ለመስመጥ በምድራችን እንዲሆን የክብርህ ደመና ሪቫይቫል ሊሆን ዛሬም እንደገና መንፈስ ሲሰራ በልጆችህ ጎልቶ እኛ እንመኛለን ትጋታችን ጠፍቶ ጊዜ የለንም እንጂ ታውቃለህ ልባችን የተገለጠ ነው አንተ መውደዳችን የኑሮው ሁኔታ ባይለን ኖሮ ግድ ላንተ መገኘት ነው ምንሻው የነፍሳችን ውድ ቃልህ ማሰላሰል ስንፀልይ ለመዋል እኛ እንወዳለን ሁሉን ታውቀዋለህ ጌታ ሆይ ጊዜ የለን ጊዜ እኮ የለንም እንላለን ግብዞች ጊዜን የሚሻሙ አበጅተን ጣዖቶች ላንተ ቦታ የለንም ፍቅራችን ቀንሷል ደባል ጣዖታችን መኖርያ ቀልሷል ላንተ የለንም እንጂ ጊዜ እኮ አናጣም ለሳቅ ለጨዋታ በህይወታችን ላይ እየሆኑብን ነው ሚዲያዎች ጌታ ጊዜ የለኝም በዝቷል ለቃልህ እና ፀሎት ውድ የሆነው ጊዜ ለጠላቱ ሰጥቶት ላንተ ጊዜ ሳይሆን ያጣነው ፍቅር ነው አብልጠን እንድንወድህ ልባችን ፈውሰው ላንተ ያለኝ ፍቅር ስለጠፋ ከውስጤ ስለቀነሰብኝ ድምፅህን ማድመጤ ስለከበደብኝ ላንተ መገዛቴ በማይጠቅሙ ጣዖት ስለሞላ ቤቴ በዚህ ከቀጠልኩኝ ስለማልሆን ደህና ፍቅርህ በልቤ ይፍሰስ ዛሬም እንደገና ልቤን ፈውስልኝ ልውደድህ አብዝቼ ፊትህን ልፈልግ ደጆቼ ዘግቼ ጣዖቶች አይኑሩኝ አንተ ብቻ ግዛኝ ሌላ እስካያምረኝ በመንፈስህ ንካኝ ፍቅርህ ይንካኝ እንጂ የትም የሚባክን ብዙ ጊዜ አለኝ ልክ የወደድኩህ ቀን ሁሉን ነገር ትቼ ካንተ ጋር ነው ምገኝ ✍ኤርሚያስ ክፍሌ react And Share @Kegetemku_leyesus
Open in TelegramForwarded from Hebron Evangelical Ministry🔥
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟 ★እናቴን የምወዳትና የምኖርላት በቅርበት ስለማውቃት ነው፡፡ ይህም፦ የመጀመሪያው ማን እንደሆነች፣ ሲቀጥል ምን ያህል እንደምትወደኝና ለኔ ምን ያህል እንዳደረገች ስለማውቅ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ የማደርገውን ሁሉ የማደርግላት ከፍቅር❤️ የተነሳና እንዲሁም ደስ😊 እያለኝ ነው፡፡ 👉ክርስትናም እንዲሁ ነው👈 ክርስትና የሚጀምረው ክርስቶስ ኢየሱስን ከማወቅ እና ለእኛ ካለው ፍቅር የተነሳ ምን ያህል ዋጋ እንደከፈለ እንዲሁም ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት እንዴት እንዳገባን ስንረዳ ነው፡፡ ይህ ሲገባን ነው ለእግዚአብሄር እንደሚገባ መኖር የምንጀምረው፡፡ ክርስትና ከስራ አይጀምርም ከእምነት እንጂ ፤ ነገር ግን እምነት ውስጥ ባለ ስራ ይገለጣል፡፡ (ያቆ 2፥26) አንድ ጊዜ ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ በተናገረው ምሣሌ ላስደግፍላችሁ፦ "አንድ ልብሱ የቆሸሸበት ሰው ልብሱን ለማፅዳት ብዙ ይታገላል ፣ የተቻለውንም ሁሉ አድርጎ ለማፅዳት ቢሞክርም ከልብሱ የበዛ ማደፍ የተነሳ ሊያፀዳ አልተቻለውም። በዚህ አጋጣሚ አንድ ሰው ሲታገል ያየውና የራሱን ንፁህ ልብስ ሰጥቶት፤ የእርሱን ቆሻሻውን ልብስ ያስወግደዋል፡፡" ከዚህ በሗላ ይህ ሰው👈......... ልብሱን ለማፅዳት መታገል ነው ያለበት🤔?ወይስ..... እንዳይቆሽሽበት ጥንቃቄ ማድረግ ነው ያለበት🤔🤔??? ምላሹ ግልፅ ነው🤗 👉 እንዳይቆሽሽ ጥንቃቄ ማድረግ ነው ያለበት! እንዳንረክስ ከሚያደርጉን ነገሮች ባለን ጥንቃቄ ስራችን ይገለጣል እንጂ ለፅድቅ ነው ብሎ መመፃደቅ በታላቁ አምላክ የተደረገልንን ታላቅ ስራ እንደማናናቅ ነው፡፡ ስለዚህ ክርስትና 1. ታላቅ አምላክ -እርሱን ስናውቅ (ቆላ 1፥15-20) 2. ታላቅ ስራ - በእርሱ የሆንነውንና የተደረገልንን ስናውቅ (ቆላ 2፥9-23) 3. ታላቅ ኑሮ- ለእርሱ የሚመጥን ኑሮ ስንኖር ነው፡፡(ቆላስይስ 3 ፤ 4፥1-2) ክርስትናችን በእነዚህ ቅደም ተከተል ካልሆነ በቀር ፍሬአልባ ፣ የማስመሠልና የግዳጅ ነው የሚሆንብን፡፡( እናትህን ሳታውቃት ውደዳትና ኑርላት ማለት በርግጥ ይከብዳል፡፡ ምንም እናትህ እንኳን ብትሆን አብረሃት ካልኖርክና ካላወቃት ምክንያታዊ ፍቅር አይኖርህም፡፡ ነገር ግን አብረሃት ከኖርክ በደንብ ታውቃታለህ ፤ ማንም ስላለህ ሳይሆን ደስ እያለህ ትወዳታለህ ደስ እያለህም ትኖርላታለህ፡፡ ክርስትናም ልክ እንዲሁ ነው፡፡ ያመንከውንና ያወቅከውን እግዚአብሔር ስትኖርለት ለእርሱ በመኖር ውስጥ በሚገጥሙህ በማናቸውም ውጣ ውረዶች ደስተኛ ትሆናለህ😊 ምክንያቱም ያመንከውን ታውቀዋለህ😎፡፡(ቆላ 1፥24 ፤ ሐዋ 5፥41) ያላወከውን እግዚአብሔር በምን ሒሳብ ትወደዋለህ?😱 በምንስ ሁኔታ ትኖርለታለህ?🤔) እግዚአብሔርን እንወደዋለን እንላለን ግን አንወደውም ፣ እናውቀዋለን እንላለን ግን አናውቀውም ፣ በአንደበታችን እናከብረዋለን ግን ከልባችን አይደለም፡፡ ከዚህም የተነሳ እኛና ክርስትናችን ለየቅል ናቸው፡፡🙅♂ ስለዚህ እግዚአብሔርን እንወቀው እናውቀውም ዘንድ እንፈልግ ፤ <እርሱ ያለምክንያት ወዶናልና እኛ ደግሞ በምክንያት እንውደደው> " እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።" (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:19) ✍በረከት ተስፋዬ 👇Join to channal 👇 https://t.me/Holiness_unto_lord
Open in Telegram
CHRIST TUBE - ETH🇪🇹@christ_tubeReligion25.5K
⚓️ሐመረ ኖኅ⚓️@orthotekReligion24.5K
የገጣሚያን ማኅበር@ye_getamian_mahiberReligion24.1K
ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት@bibleztewahidoReligion26.1K
☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA@huda4ethReligion26.2K
የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe@yahyanuheReligion23.2K
ተስፋ በኢየሱስ Channel@hopeofjesuschannelReligion27.4K
ምክረ አበው@mekra_abawReligion27.5K