Account
EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

ቅዱሳት መጻሕፍትን እንለዋወጥበት ዘንድ እንዲሁም አዳዲስ የሚወጡ መንፈሳዊ መጻሕፍትን እንድንተዋወቅበት ተከፈተ

Username
@ethiopian_orthodox_tewahdo_books
Category
Religion
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers4,576
Avg views per post, 7d433last 7 days
ERR9.45%last 7 days

Latest posts

#765Photo

Forwarded from EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

ሀምሌ 4 በግፍ የተገደሉት ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ ሰማዕት የተባሉበትና ቀብራቸው በጎፋ ገብርኤል የተፈጸመበትን በማስመልከት የህይወት ታሪካቸውን ከያዘው መጽሐፍ የተቀነጨበ ..." አባታችን ምነው ደህና አይደሉም?" "ጸጥ ብለው ከቆዩ በኋላ ሰዎች እየመጡ ከአገር ውጣ ወይም ሸፍት ይሉኛል። እኔ መነኩሴ ነኝ። እንግዲህ የመነኩሴ ሽፍታ ይታይህ -የመነኩሴ ሽፍታ። እኔስ አንገቴ ከብረት ላይ ተጋድሞ ከላይ ስለት እየወረደበት መሆኑ ይታየኛል። የምጠብቀው ስለቱ አንገቴ ላይ አርፎ አንገቴ ከአካሌ እስኪለይ ነው።" ገጽ 244 "... የእስር ቤት ኑሯቸው የቅዱስነታቸው አብዛኛው ጊዜአቸው በጾም በጸሎት በማስተማር የተጠመደ ነበር። ሌሊት ለተወሰነ ጊዜ ሲጸልዩ ያድራሉ። ጧትና ማታ በማኅበር ጸሎት ይካፈላሉ። አንዳንድ ጊዜም አጠር ያለ የማጽናኛ ምክር ይሰጣሉ። እሁድ እሁድ በንቡረዕድ ኤርምያስ ከበደ ረዳትነት ሥርዓተ ቅዳሴ ያደርሳሉ።..." ገጽ 280 " ... በሰሞነ ሕማማት እስረኞች ጧት ከሁለት እስከ ሰባት ሰዓት ይሰግዳሉ። ፓትርያርኩ ደሞ ከጧቱ ሁለት ሰዓት እስከ ሰባት ሰዓት አንድም ግዜ እንኳ ሳያቋርጡ ይሰግዳሉ።" ገጽ 282 ምንጭ ቀዳማዊ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ከታምራት አበራ

Open in Telegram
Views2,900+571%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#763Text

​ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ተርጓሚዎቹ በመጽሐፉ ላይ ያሳዩት ትጋት እና የታሪክ ማመሳከር እጅግ አስደናቂ ነው። በተለይም ደግሞ የምዕራባውያንን ትችት ውድቅ በማድረግ የቅዱስ ዲዮናስዮስን ድርሳናት ትክክለኛነት ከምሥራቃዊ ኦርቶዶክስ ክርስቶሎጂ አንጻር ለመከላከል ያቀረቡት መከራከሪያ፣ ዓለም አቀፍ ምሁራዊ ደረጃውን የጠበቀና የሚያኮራ ነው። ​በመሆኑም፣ መላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን፣ መምህራንና ወጣቶች ይህንን መጽሐፍ ገዝተው የግላቸው በማድረግ የቀደምት ሐዋርያት አበውን ንጹሕ ትምህርት፣ ሥርዓትና ተጋድሎ በጥልቀት እንዲያጠኑ በአክብሮት እመክራለሁ። ​በመጨረሻምይህንን ታላቅ መንፈሳዊ ሥራ ለቤተ ክርስቲያናችን በማበርከት፣ ሌሊት ተቀን በብዙ ድካም ለዋላችሁ ኦርቶዶክሳውያን ወንድሞችና እህቶች፣ አባቶቻችን የደከሙላት ቤተ ክርስቲያን ዛሬም በእናንተ ትጋት ስትበራ ማየት ታላቅ ደስታ ነው። የሐዋርያት አበው በረከትና ረድኤት አይለያችሁ፤ ድካማችሁን ፍሬያማ ያድርግላችሁ። ​ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን። ... እንደ ተጨማሪ ሀሳብ "ሐዋርያነ አበው" የሚባል ቃል ትርጉሙ ምንድነው? '' ሐዋርያውያን አበው'' አልያም '' አርድእተ ሐዋርያት'' የሚለው ቢተካ ትክክለኛ አይመስላችሁም? .... መጽሐፉን ከ አርጋኖን መጽሐፍት መደብር ወይንም Abrham Hailu በማናገር ማግኘት ትችላላችሁ።

Open in Telegram
Views3,480+705%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#762Text

​ሰ. መዓርገ ቤተ ክርስቲያን በሰማይ ያለው መለኮታዊ ሥርዓት በምድር ባለችው ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንደሚገለጥ ያሳያል። ሦስቱ ምሥጢራት ማለትም ጥምቀት፣ ቁርባን፣ ሜሮን እና ሦስቱ መዓርጋተ ክህነት ኤጲስ ቆጶስ፣ ካህናት፣ ዲያቆን ተተንትነዋል። ዲዮናስዮስ ኤጲስ ቆጶስን የብርሃን ምንጭና የምሥጢራት ሁሉ ፈጻሚ አድርጎ ያቀርበዋል። መጽሐፉ የጥንቷን ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። በተለይም ሥርዓተ ምሥጢረ ሜሮን ላይ የሰጠው ክፍል፣ ሜሮን በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ያለውን ከፍተኛ ስፍራ የሚያረጋግጥና ከካቶሊክ/ፕሮቴስታንት ተጽዕኖ የጸዳ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ነው። ​ሸ. በእንተ አስማተ መለኮት እግዚአብሔር አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብርሃን፣ ፍቅር፣ ሕይወት፣ ጥበብ እየተባለ የሚጠራባቸውን ስሞች ምስጢር ይተነትናል። እዚህ ጋር ዲዮናስዮስ እግዚአብሔር ከስሞች ሁሉ በላይ ነው የሚለውን ሐሳብ ያነሳል። እግዚአብሔርን ጥሩ ስንለው፣ ከእኛ መልካምነት ጋር የሚነጻጸር ሳይሆን የቸርነት ሁሉ ምንጭ መሆኑን ለመግለጽ ስለመሆኑ ነው። ይህ ክፍል ከቅዱስ ያሬድ አንቀጸ ብርሃን እና ከቅዱስ ኤፍሬም ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ጋር ይመሳሰላል። እግዚአብሔርን በባሕርዩ ሳይሆን በሥራው ማወቅ እንደሚቻል የሚያትተው ትምህርቱ፣ የቤተ ክርስቲያናችንን ምስጢራዊ ሕይወት ያጠናክራል። ​3. የትርጉም ጥራት የተርጓሚዎቹ ቡድን የቃላት አቻ እና የሐሳብ አቻ ስልቶችን አጣምሮ መጠቀም መቻሉ ታላቅ ብቃት ነው። ጽሑፉ ለምዕራባውያን ፈላስፎች እነ ሎሬንዞ ቫላ የሚሰጠው ምላሽ የተዘጋጀበት የአማርኛ ቋንቋ ስነ አመኮኗዊ ፍሰት ያለው ነው። ጥልቅ የሆኑ የግሪክ ፍልስፍናና ቴዎሎጂያዊ ቃላትን ወደ አማርኛ/ግዕዝ ለመመለስ የተደረገው ጥረት እጅግ የሚያስመሰግን ነው። ለምሳሌ፡- • ​Parhypostasis ~ ጥገኛ ህላዌ / ተውሳከ አካል • ​Agnosia ~ አለማወቅ - ከእውቀት በላይ የሆነ ምስጢራዊ መረዳት • ​Hierarchy (ሥርዓተ መዓርግ / መዓርገ ሰማይ) • ​Apophatic / Cataphatic ~ ኢይትበሃላዊ / ይትበሃላዊ ዐረፍተ ነገሮቹ ረዣዥም ቢሆኑም የዲዮናስዮስን ጠጣር የቃላት አጠቃቀም ወደ አማርኛ ለማምጣት የተመረጠው ስልት ተገቢ ነው። ይሁን እንጂ፣ በአንዳንድ ስፍራዎች በተለይ በእንተ አስማተ መለኮት የአማርኛው ፍሰት ከእንግሊዝኛ ሰዋሰው መዋቅር ጋር ስለሚመሳሰል ለአማካኝ አንባቢ ሊከብድ ይችላል።። ​4. ጠንካራ ጎኖች ▪️ ከሐዋርያት ቀጥሎ የነበሩትንና የቤተ ክርስቲያንን መሠረት ያጸኑትን የሐዋርያት አበው ጽሑፎች ለዘመኑ አማርኛ አንባቢ ተደራሽ ለማድረግ መሞከሩ በራሱ የሚደነቅ ተግባር ነው። ይህም ምእመናን የጥንቷን ቤተ ክርስቲያን የጸሎትና የሥርዓት ሕይወት 1ኛአስከ 3ኛ መ.ክ.ዘ እንዲረዱ በር ይከፍታል። መጽሐፉ የክህነት መዓርግ እና የምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን አፈጻጸምን በጽሑፍ ማስረጃ በማቅረብ የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ሐዋርያዊነት በጽኑ ይሞግታል። ▪️እንደ መልእክተ ዲዮግኔጦስ ያሉትንና ድርሳናት ውስጥ በስፋት የማይታወቁ ጽሑፎችን ማካተቱ ለነገረ መለኮት ተማሪዎችና ተመራማሪዎች እንደ ታላቅ ግብዓት ያገለግላል። ▪️ ትርጉሙ የዛሬውን ትውልድ የአማርኛ አጠቃቀም ግምት ውስጥ ያስገባ፣ ለማንበብ የማይከብድና ፍሰቱ የተጠበቀ መሆኑ አንባቢያን ሳይሰለቹ መጽሐፉን እንዲጨርሱ ይረዳል። ▪️ ​ለእያንዳንዱ አባት የሰጠው የታሪክ መግቢያ አንባቢያን አባቶቹ የነበሩበትን ዘመንና የደረሰባቸውን መከራ እንዲረዱ በማድረግ ረገድ ጠቃሚ ነው። ▪️የቅዱስ ዲዮናስዮስን ጽሑፎች ሐሰተኛ ከሚሉ የምዕራባውያን ትችቶች ለመከላከል የቀረበው ሰፊ ትንተና ለኦርቶዶክሳዊያን ተከራካሪዎች ትልቅ ግብዓት ነው። ​5. ድክመቶችና መሻሻል የሚገባቸው ▪️ ​መጽሐፉ በቀጥታ ከእደክታባቱ ወይም ከቤተ ክርስቲያናችን የግዕዝ ድርሳናት አልያም ከኣሓት አብያተ ክርስቲያናት ምንጮች ከመተርጎም ይልቅ፣ በምዕራባውያን ፕሮቴስታንት ምሁራን (ፊሊፕ ሻፍ፣ ላይትፉት፣ ኳስተን) የእንግሊዝኛ ትርጉም ላይ መመስረቱ ትልቁ ድክመት ነው። በእርግጥ ይሄ በሁሉም የትርጉም ስራዎች ላይ ያለ ክፍተት ነው። ለመረዳት የሚቀርበን እንግሊዘኛው ነውና ሀሁሉም ነገር መሰረት ይህንን ቋንቋ አደርገናል። ችግሩ ከቋንቋው ሳይሆን ከቀደመት ዋና ቅጂዎች ወደ እንግሊዘኛ የሚተረጉሙት ካቶሊኮችና ፕሮቴስታንቶች መሆናቸው ነው። ▪️ ሌላው ከላይ እንደተገለጸው፣ የፓፒያስ የሺህ ዓመት የምድር መንግሥት ትምህርት በኦርቶዶክስ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በግልጽ አላብራሩም። "ቅዱስ ሄሬኔዎስም ይህንኑ ያስተምራል" በሚል የግርጌ ማስታወሻ ገጽ 160 ማለፋቸው አንባቢውን ወደ ተሳሳተ መደምደሚያ ሊወስደው ይችላል። ይወስደዋልም። ይህ የሺህ ዓመቱ የምድር ንግሥና የአንዳንድ አበው የግል አመለካከት እንጂ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እንዳልሆነ በግልጽ የሚያብራራ ሰፊ የግርጌ ማስታወሻ መግባት ይኖርበታል። ▪️በእንተ አስማተ መለኮት እና ምስጢራዊ ነገረ መለኮት ክፍሎች ላይ የተተረጎመው አማርኛ እጅግ ፍልስፍናዊ በመሆኑ ለ ተራ አንባቢ በቀላሉ ለመረዳት አዳጋች ነው። ▪️አንዳንድ አንቀጾች እስከ አንድ ገጽ ይረዝማሉ። ይህ ደግሞ አንባቢው ሐሳቡን በቀላሉ እንዳይከታተል ያደርገዋል። ▪️ በመጽሐፉ መጨረሻ ላይ ያለው ዋቢ መጽሐፍት ገጽ 512-513 አብዛኛው በምዕራባውያን ምሁራን (የፕሮቴስታንትና ካቶሊካዊያን) ላይ የተመሰረተ ነው። ምንም እንኳን እነዚህ ምሁራን ታላላቅ ቢሆኑም፣ በእኛ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት የተጻፉ ትንታኔዎች ቢካተቱ ኖሮ የበለጠ ጥሩ ይሆን ነበር። (በነገራችን ላይ በነዚህ ምዕራባዊያን ተርጓሚዎች ላይ ሙሉ እምነት የለኝም ምክንያቱም ብቸኛ ማረጋገጫዎቻችን እነሱ እየሆነ መጥተዋለሸ በዚህም ላሉበት ቤተ እምንት በማድላት የትርጉም አልያም የትንታኔ ግድፈት ሊፈጽሙ ይችላሉ የሚል ሀሳብ ውስጤ አለ) በመጽሐፉ ዋቢ ዝርዝር ውስጥ ከመነኩሴው አባ ታድሮስ ማላቲ በስተቀር፣ የሌሎች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አባቶች ትንታኔዎች አልተካተቱም። በተለይም በኢትዮጵያ ገዳማትና በሊቃውንት እጅ የሚገኙ ጥንታዊ የግዕዝ ትርጓሜዎችና የብራና መጻሕፍት እንደ ዋቢ አለመጠቀማቸው መጽሐፉን በምዕራባውያን አስተሳሰብ ላይ ብቻ ጥገኛ ያደርገዋል። ይህ ነገር ለሌሎችም ተርጓሚዎች ማሳሰቢያ ቢሆን እልፍ በግዕዝ የተቀመጡና ያልተተረጎሙ ድርሳናት አሉ፤ ለግዕዙ ባይተዋር መሆናችን ካልሆነ በስተቀረ ጥንታዊያንና ተአማኒ የሆኑ ናቸው። 6. አጠቃላይ መደምደሚያ እና የማጠቃለያ ሐሳብ ​በአጠቃላይ ሲመዘን፣ ይህሐዋርያነ አበው የተሰሰኘ መጽሐፍ በይዘት ስፋቱና በምርምር ጥልቀቱ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን፣ ለቴዎሎጂ ተማሪዎች እንዲሁም ለአንባብያን እጅግ አስፈላጊና ብዙ ጥያቄዎችን የሚመልስ ታላቅ ሥራ ነው። መጽሐፉ የጥንቷን ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ታሪክና ትምህርት አሁን ያለው ትውልድ ሊረዳው በሚችለው ለማቅረብ ያደረገው ጥረት ከፍተኛ አድናቆት የሚገባው ነው። ​ምንም እንኳን ይህ ጅምር ትልቅ ሰሰራ ቢሆንም መጽሐፉ በቀጣይ ዕትሞቹ ይበልጥ ኦርቶዶክሳዊ ለዛና ምሉዕነት እንዲኖረው መታረምና መስተካከል የሚገባቸው ነጥቦች በልዩ ትኩረት ሊታሰቡባቸው ይገባል።

Open in Telegram
Views2,290+429%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#761Text

የሐዋርያነ አበው መጽሐፍ ዳሰሳ ©ማርያማዊት ሄኖክ ለሜሳ ....... ንዌጥን በረድኤተ እግዚአብሔር ጽሒፈ ዘንተ መጽሐፈ ገቢረ ፍካሬ በእንተ ሐዋርያነ አበው። ​ይህ ሐዋርያነ አበው የተሰኘ መጽሐፍ ከመሰራጨቱ በፊት እጄ ከገባና እንደ አንዲት ኦርቶዶክሳዊ የሰንበት ተማሪ እይታዬን ከተጠየቅኩ የሳምንታታ ያህል ጊዜ ይሆነዋል። መጽሐፉንበዚህ ጊዜ ውስጥ ሁለቴ ለማንበብ ሞከሪያለሁ። የመጀመሪያው ንባቤ ለብለብ በሆነና በፈጠነ መልኩ ይዘቱን ለመረዳትና የቱጋር ማተኮር እንዳለብኝ ለማወቅ የተጠቀምኩበት ሲሆን፤ በሁለተኛው ንባቤ ግን በመጀመሪያው ምልከታዬ ላይ በመመሥረት መጽሐፉን በዝርዝር ለመመርመርና ነገረ መለኮታዊ ይዘቱን ለመፈተሽ ሞክሬአለሁ። ..... ​1. የመጽሐፉ አጠቃላይ መግለጫ ▪️​ርዕስ፦ ሐዋርያነ አበው | ቅዱስ ዲዮናስዮስ እና ሌሎች… ▪️አሳታሚ፦ አርጋኖን መጻሕፍት ▪️ተርጓሚዎች፦ 50 ሆነው የጀመሩ፣ ነገር ግን በጽናት የጨረሱ ጥቂት የማኅበረ ቅዱሳን ጊቢ ጉባኤ ተማሪዎች (ዲያቆንዘሚካኤል ሐጎስ፣ ዮናታን ገነነ እና ሌሎችም)። በአባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ (የአራቱ ጉባኤያት መምህር) የታረመ። ▪️የታተመበት ዘመን ፦መጋቢት 2018 ዓ.ም. ▪️የመጽሐፉ ዓላማ፦ ምእመናንና የነገረ መለኮት ተማሪዎች ከሁለተኛና ሦስተኛ ምንጮች ላይ ጥገኛ ሳይሆኑ፣ የጥንታውያን አበውን ትምህርት ከዋናው ምንጭ በራሳቸው ቋንቋ በቀጥታ እንዲያገኙ ማስቻል የሚል ነው። ▪️ ዳራ፦፦ መጽሐፉ የ1ኛውን እና የ2ኛውን መቶ ክፍለ ዘመን አበው (ቀሌምንጦስ ዘሮሜ፣ አግናጥዮስ፣ ፖሊካርፐስ፣ ፓፒያስ፣ ዲዮግኔጦስ) መልእክታት፣ እንዲሁም በምሥራቃውያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ መሠረት የሆነውን የቅዱስ ዲዮናስዮስ ዘአርዮስፋጎስን ሥራዎች በአንድ ላይ አጠቃልሏል። በተለይም ዲዮናስዮስን በተመለከተ በምዕራባውያን እነ ሎሬንዞ ቫላ እና ኤራስሞስ የሚነሳውን ሐሳዊው ዲዮናስዮስ የሚል ትችት ውድቅ በማድረግ፣ ሐዋርያዊነቱንና ኦርቶዶክሳዊ ትክክለኛነቱን በሰፊው ይሞግታል። ▪️ የትርጉም ምንጭ፦ በመጽሐፉ ማብቂያ ላይ የተዘረዘሩትን ዋቢ መጻሕፍት መሰረት በማድረግ የትርጉም ሰንሰለቱን ስንመለከት መጽሐፉ በቀጥታ ከዋናው እደ ክታብ ግሪክ ወይም ሱርስት ፣ አሊያም ከጥንታዊው የቅብጥ ቅጂዎች የተተረጎመ አይደለም (ካልተሳሳትኩ)። የትርጉም ሰንሰለቱ ግሪክ/ላቲን ➔ እንግሊዝኛ ➔ አማርኛ ነው። ይህ ማለት መጽሐፉ የሁለተኛ ደረጃ ትርጉም ያደርገዋል። ​2. አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት ​በመጽሐፉ በስፋት ጠብሰቅ ያለ ከመሆኑ የተነሳ፣ ዋና ዋናዎቹን የትምህርት ክፍሎችና ምዕራፎች አበይት ጭብጦች ብቻ በሚከተለው መልኩ አስቀምጫቸዋለሁ፡- ​ሀ. የቅዱስ ቀሌምንጦስ መልእክት ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ▪️መልልእክቱ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በካህናት ላይ የተነሳውን አመጽ ለማብረድ የተጻፈ ኔው። ቀሌምንጦስ ለቤተ ክርስቲያን መዋቅርና ለሐዋርያዊ ቅብብሎሽ መገዛት ቅድመ ሁኔታ የሌለው ክርስቲያናዊ ግዴታ መሆኑን ያብራራል። ▪️ትምህርቱ ከብሉይ ኪዳን ታሪኮች እነ ቃየል፣ አቤል፣ ዳታንና አቤሮን ጋር በማያያዝ ቅንዓት የሚያመጣውን ጥፋት ይተነትናል። በምዕራፍ 25 ላይ የፊኒክስ አፈ ታሪካዊ ወፍ ለትንሣኤ ሙታን ምሳሌ አድርጎ ያቀረበበት መንገድ የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ምሳሌያዊ አተረጓጎምን ያሳያል። ​ለ. የቅዱስ አግናጥዮስ ምጥዉ ለአንበሳ መልእክታት ▪️ 7ቱ የአግናጥዮስ መልእክታት (ወደ ኤፌሶን፣ ማግኔስያ፣ ጥራሊያ፣ ሮሜ፣ ፊላደልፊያ፣ ሰርሞኔሳውያን እና ፖሊካርፐስ) በዋናነት ሦስት ነገሮች ላይ ያተኩራሉ፡- 1) ክርስቶስ በእውነት ሥጋን ለብሷል ጸረ ዶሴቲዝም 2) ያለ ኤጲስ ቆጶሱ ፈቃድ ምንም ሥርዓተ አምልኮ አይፈጸምም፣ እና 3) ሰማዕትነትን መናፈቅ ▪️ አግናጥዮስ ሮማውያን ክርስቲያኖች ከሞት ሊያድኑት እንዳይሞክሩ የሚለምንበት ወደ ሮሜ ሰዎች የተላከው መልእክቱ ምዕራፍ 4 እና 5 የክርስትናን የሰማዕትነት የሞራል ልዕልና ጥግ ያሳያል። እኔ የእግዚአብሔር ስንዴ ነኝ... የክርስቶስ ንጹሕ ኅብስት እሆን ዘንድ የሚለው ንግግሩ የቅዱስ ቁርባንን አማናዊነት ከራሱ ሕይወት ጋር አዋሕዶ ያሳያል። በዘህ ክፍል ያለው ትርጉሙ እጅግ መንፈሳዊ ጉልበት ያለው ልብን የመገዛ ነው። ​ሐ. የቅዱስ ፖሊካርፐስ መልእክትና ዜና ስምዑ ▪️ ወደ ፊልጵስዩስ የጻፈው መልእክት በፍቅረ ንዋይ እና በመNaFቃን ላይ የሚያተኩር ሲሆን ዜና ስምዑ ምዕራፍ 13-16ፖሊካርፐስ በእሳት ተቃጥሎ ሰማዕትነትን ሲቀበል እሳቱ እንደ ሸራ ከቦት እንደዳነና በመጨረሻም በሾተል ሲወጋ ርግብ ወጥታ ደም መፍሰሱን ይተርካል። በዚህ ክፍል በተለይ ሰማዕትነቱን በሚገልጹበት ወቅት እጅግ ስሜት የሚነኩና ሰማዕታትን ቤተክርስቲያናችንለማክበር ለምታስተምረው ትምህርት በተጨማሪም የቅዱሳን አጽም ከከበሩ ዕንቁዎች ይልቅ እንደሚበልጥ የተገለጸበት ምዕራፍ 18 ጥሩ ነው። ​መ. መልእክት ኀበ ዲዮግኔጦስ እና የፓፒያስ ትምህርት ▪️ ​የዲዮግኔጦስ መልእክት ክርስቲያኖች ለዓለም እንደ "ነፍስ ለሥጋ" መሆናቸውን ይሞግታል። የፓፒያስ ክፍል ደግሞ የሐዋርያት ተውፊት ያብራራል። ▪️ ​ፓፒያስ በምዕራፍ 4 ላይ ስለ ሺህ ዓመት የክርስቶስ የምድር ንግሥና ያስተማረው ትምህርት አለ። አዘጋጆቹ በመግቢያው ላይ ይህ ትምህርት በኦርቶዶክስ ተቀባይነት እንዳለው አድርገው ማቅረባቸው (ምንም እንኳን ሄሬኔዎስ ቢቀበለውም) ጥንቃቄ ይሻል። ​ሠ. የቅዱስ ዲዮናስዮስ ዘአርዮስፋጎስ ሥራዎች ▪️ ይህህ ክፍል የመጽሐፉ የጀርባ አጥንት ነው። በመግቢያው ላይ ጽሑፉ ሐሳዊ አይደለም ብለው አዘጋጆቹ በሰፊው ተከራክረዋል። የቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ እና የዮሐንስ ተአቃቢ ድርሳናትን ጠቅሰው ዲዮናስዮስ ከፕሮቅለስ አልኮረጀም፣ ይልቁኑ አረማውያን ከእሱ ኮረጁ እንጂ በማለት ይሞግታሉ። መጽሐፎቹም በእንተ አስማተ መለኮት ፣ መዓርገ ሰማይ ፣ መዓርገ ቤተክርስቲያን እና ምስጢራዊ ነገረ መለኮት ናቸው። ▪️ ​ዲዮናስዮስ የአሉታዊ ነገረ መለኮት ኢይትበሃላዊ እና የአዎንታዊ ነገረ መለኮት ይትበሃላዊ አባት ነው ። መጽሐፉ እግዚአብሔርን ከእውቀት በላይ በሆነ አለማወቅ ማወቅን በጥልቀት ያስተምራል። የክፋትን ምንነት ሲገልጽ ክፋት ራሱን የቻለ ህላዌ የሌለው የመልካምነት መጉደል ቊስለ ሠናይ መሆኑን በሚገባ አስቀምጧል። ረ. መዓርገ ሰማይ በቅዱስ ዲዮናስዮስ ይህ ክፍል በሰማይ ያሉ ረቂቃን መላእክት በሦስት መዓርጋት እና በዘጠኝ ነገዶች እንዴት እንደተከፈሉ ይተነትናል። • ​የመጀመሪያው መዓርግ፦ ሱራፌል፣ ኪሩቤል፣ መናብርት፤ • ​ሁለተኛው መዓርግ፦ ኩነናት፣ ኃይላት፣ ሥልጣናት፤ • ​ሦስተኛው መዓርግ፦ መኳንንት፣ ሊቃነ መላእክት፣ መላእክት፤ ቅዱስ ዲዮናስዮስ መላእክትን መለኮታዊ ብርሃንን ተቀብለው ለታችኞቹ የሚያስተላልፉ መስተዋቶች አድርጎ ይስላቸዋል። ይህ ትምህርት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ድርሳነ መላእክት እና መጽሐፈ አክሲማሮስ ላይ ካለው ትምህርት ጋር ተመሳሳየ ነው። ሆኖም ዲዮናስዮስ መላእክትን ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን ሲላቸው፣ የእኛ ሊቃውንት ግን እምነ ሐመድ ወእምነ ነፋስ ከእሳትና ከነፋስ የተፈጠሩ መሆናቸውን ያሰምሩበታል። መጽሐፉ ይህንን ልዩነት በግርጌ ማስታወሻ ቢተነትነው ለተማሪዎች ጠቃሚ ነበር።

Open in Telegram
Views1,850+328%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—

All posts

Connections