Account
@Book for all

@Book for all

ማንበብ ማንበብ ማንበብ ‹‹ሰፊ ይለበሳል ጠባብ ይቀደዳል›› @መባ ለማንኛውም አስተያየት @Dasolo

Username
@bookfor
Category
Religion
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers4,880
Avg views per post, 7d462last 7 days
ERR9.47%last 7 days

Latest posts

#1407Text

እናንተዬ Spiritual Manipulation እንዳለ ስንቶቻችሁ ታዉቃላችሁ ? Controlling people in the name of God 😉 አሁን አሁን ደግሞ manipulation sound like ministry / ተልዕኮ፣ control ማድረግ እንደ spiritual guidance እየተቆጠረ መቷል። ሰዎች በጓደኝነት፣ Relationships ፣ በቤተሰብ፣ በትዳር፣ በBusiness አልፎ ተርፎም በቤተክርስቲያን ውስጥ እኛን ሰዎችን manipulate ለማድረግ የእግዚአብሔርን ቃል / መጽሐፍ ቅዱስን ሊጠቀሙ ይችላሉ። ለምሳሌ አንድ ሰው ሲዋሸን ወይም ሲጎዳን እግዚአብሔር ስለሚያዘን ይቅር እንላለን። ነገር ግን ይቅር ማለት ደግሞ የራሳችንን ደህንነት (well-being) አሳልፈን መስጠት ወይም እኛም ሆነ እርሱ/God Treat እንድንደረግ በማይፈልገዉ በማይገባን መንገድ እንዲያስተናግዱን መፍቀድ ማለት አይደለም። እግዚአብሔር በስሜት፣በአዕምሮ፣ በመንፈስ እና በአካል ጤናማ (emotionally, mentally, physically and spiritually healthy)እንድንሆን ፣ እራሳችንን preserve እንድናደርግ እና የተወደድን እንድንሆን ይፈልጋል። ሰዎች manipulate ለማድረግ ጥቅሶችን ከContext ውጪ ሲጠቀሙ 👇🏽 ❗️Toxic በሆነ ግንኙነት ውስጥ እንድትቆዩ ሲፈልጉ፡ “ሰባ ጊዜ ሰባት ይቅር በል" (ማቴ 18:22) ይላል ይላሉ But They ignore: ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ የማይቀበሏቸውን ሰዎች ትተው የእግራቸውን ትቢያ አራግፈው እንዲሄዱ ማዘዙን (ማቴ 10:14) ❗️ተደጋጋሚ ንቀትን (disrespect) እንድትታገሱ ሲፈልጉ፡ "ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናል" (1 ጴጥ 4:8) ይሉሀል But They ignore: "ክፉ ባልንጀራ መልካምን አመል ያጠፋል" እንደሚል (1 ቆሮ 15:33) ❗️ ጭፍን Obedient እንድትሆኚ ሲፈልጉ፡ " ተገዛዙ" ይላል ይሉሻል But They ignore: "ባሎች ሆይ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እንደወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ" የሚለውን (ኤፌ 5:21-25) ❗️ ዝም ለማሰኘት or Challenge ላለመደረግ፡ "የቀባኋቸውን አትንኩ" ይላል ይሉናል But They ignore: "ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ" የሚለውን ትዕዛዝ (1 ተሰ 5:21) ❗️ ያለምንም ጥያቄ እንድትታዘዙ ሲፈልጉ፡ "አባትህንና እናትህን አክብር" ይላል ይላሉ But They ignore: "አባቶች ሆይ ልጆቻችሁን አታስመርሩ" የሚለውን (ኤፌ 6:1-4) ❗️ ተደጋጋሚ በደልን (mistreatment) ለመሸፈን፡ "እርስ በርሳችሁ ታገሱ" ይላል ይላሉ But They ignore: "እውነትን በፍቅር መናገርን" የሚለውን (ኤፌ 4:15) ❗️ በገንዘብ (financially) ጫና ለመፍጠር ሲፈልጉ፡ "ስጡ ይሰጣችሁማል" ይላል ይሉናል But They ignore: "እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳል" የሚለውን (2 ቆሮ 9:7) ❗️ በደልን (abuse) እንድትታገሱ፡ "ፍቅር ይታገሳል" ይላል ይላሉ But They ignore: ፍቅር "ስለ ዓመፃ ደስ አይሰኝም፣ ከእውነት ጋር ግን ደስ ይሰኛል" የሚለውን ነው (1 ቆሮ 13:4-6) ❗️ ዝም ለማስባል (silent እንድትሆኑ) ለማድረግ፡ "ሰላም ፈጣሪዎች ሁኑ" ይላል ይላሉ But They ignore: "ለራሳቸው መናገር ለማይችሉ ተናገር" የሚለውን (ምሳሌ 31:8) ❗️ ተገቢውን ክፍያ ላለመክፈል ሲፈልጉ፡ "ገንዘብን አትውደዱ" ይላል ይሉሀል But They ignore: "ትክክለኛ ሚዛን የእግዚአብሔር ነው" የሚለውን (ምሳሌ 16:11) ❗️ ለእነሱ ብላችሁ የገንዘብ Risk እንድትወስዱ ሲፈልጉ፡ "በገንዘብ ሳይሆን በእግዚአብሔር ታመን" ይሉናል But They ignore: "የትጉ ሰው ዕቅድ ወደ ትርፍ ይመራል" የሚለውን (ምሳሌ 21:5) ❗️ ተጠያቂነት (accountability) ለመሸሽ፡ "Forgive and forget ይቅር በሉና እርሱት" ይሉናል But They ignore: ዘኬዎስ የበደለውን ካሳ መክፈሉን (ሉቃስ 19:8)። ወዳጆቼ፣ አንድ ነገር አስታውሱ! ሰይጣንም መጽሐፍ ቅዱስን አሳምሮ ያውቃል። In fact, ከብዙዎቻችን በተሻለ ያውቃል። ኢየሱስን በምድረ በዳ ሲፈትነው ውሸት ተናግሮ ሳይሆን ቃሉን ከContext ውጪ ጠቅሶ ነበር። Devil ራሱ የእግዚአብሔርን ልጅ ለመፈተን የእግዚአብሔርን ቃል ከተጠቀመ፣ ሰዎች እኛን manipulate / ለማታለልና ለመቆጣጠር ያንኑ ቃል የማይጠቀሙበት ምክንያት የለም? አንዳንዶች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ዝም ለማሰኘት፣ የማትፈልጉትን ነገር እንድታደርጉ Trick አድርጐ ለማስገደድ እና የራሳቸውን ባህሪ እንድትታገሱ ይጠቀማሉ። በዚህም ላይ የጥፋተኝነት ስሜት (Guilt) እንዲሰማችሁ በማድረግ ይቆጣጠሯችኋል። 💡 በእግዚአብሔር ቃል መመራት እና በእግዚአብሔር ስም control መደረግ በጣም የተለያየ ነገር ነው! Manipulation የሚሳካው እኛ በቂ Awareness ወይም ግንዛቤ ሳይኖረን ስንቀር ነው። ስለዚህ ድንበራችንን (Boundaries) የሚጥሱትን፣ ድምፃችንን የሚያፍኑትን እና በመንፈሳዊ ስም የሚበድሉንን (Spiritual Abuse) ለመለየት፣ ለመቋቋምና ራሳችንን ለመጠበቅ ግንዛቤ (Awareness) ያስፈልገናል። የእግዚአብሔርን ቃል እና የሰዎችን የግል ጥቅም መለየት እና መገንዘብ እጅጉን አስፈላጊ ነው እላለሁ! 💬 እናንተስ በሕይወታችሁ ወይም በአካባቢያችሁ እንዲህ አይነት ሁኔታ አጋጥሟችሁ ያውቃል? ሀሳባችሁን Comment ላይ አጋሩ። @Bookfor

Open in Telegram
Views4620%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1406Photo
Views4,660×10vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1404Text

ዛሬም ሆዳቸው አምላካቸው የሆኑ ጥቂቶች የብላቴናው የእውነት ሰይፍ ገና ከአፎቱ ሳይወጣ የሚርዱት ወደው አይደለም። የሚጠሉት ከሚወዱት በላይ የጥበቡን ጉልበትና ልክ አውቀውታል። ወዶ ገቢውም ሆነ በብር የተሸጠው ሁሉ ከመቅለል የዘለለ እጣ ሳይኖራቸው ቢቅበዘበዙም እውነት ሰፋሪው ህዝብ ግን የነገሰውን ሊያነግስ የቀናት ምጥ ይዞታል። በአስራዎቹ እድሜያችን የምናውቀው ቴዲ እሱ ወደ ሃምሳ እየገሰገሰ እኛም ወደ አርባ እየቀረብን ነው። እጅግ በጣም የተወደደ። ያለማቋረጥ ያወዛገበ። በገሚስ የተጠላ ፣ ምርቃትና እርግማን የጠገበ... የጠሉት ቢጠሉት እንኳን በዜማው ከመቆዘምም ሆነ በምቱ ከመወዛዘዝ አላመለጡም። መወደድና ዝና አረቄ ያልሆነበት ብላቴና ከስራው ይልቅ መወደዱን የያዘበት መንገድ ጠቢብነቱን ይመሰክራል። እሱ ወልዶ ከብዶ ቢጎለምስም በመወደድ ብዛት ብላቴናነቱን ሳይለቅ ከፊታችን እየገዘፈ ነው። ሁሌም በኩራት እንደምለው ቴዲ ሽበት ነው በቀለም ልታጠፋው ልትደብቀው ብትሞክር? ከስር በጥበብ በርጋታ ይፈካል! ተደብቆ መጉላት ይችልበታል! በምላጭ ልታጠፋው ስትለፋ ጭራሹን ይበዛል! በጥቁር ሻሽ የማታስረው የሀገር ሽበት! ሳንዘራው ያጨድነው, ያለጊዜው የበቀለ ሽበት! ብቻ አትልፋ ቴዲ ወጣት መሳይ ሽማግሌ ነው ለመጥፋት ስንቃረብ በግጥም መክሮ በዜማ አራርቶ ከልባችን የሚያስታርቀን ወጣት መሳይ ሽማግሌ ነው! ከፍቅር አስከ ሃገር ልብና አድማሱ ለሰፋለት ፣ አኗኗሩ ምሳሌ ፣ አንደበቱ ፈዋሽ ለሆነለት የዘመናችን መልክ ጥበብና እድሜ ይትረፍለፍለት! #ኢቶሪካ ✍🏽 ሙሉቃል ቃል @Bookfor

Open in Telegram
Views3,440+645%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1403Text

ተከብሮ ማርጀትና የዘመኔ ፍፁም መልክ! ፍቅር ጭራሽ አልገባንም። እድሜያችን ለጋ በጣም ለጋ ነበር ! ፊታችን ፂም አያቅም! እህቶቻችን ጉብ ጉብ አላበቀሉም። በመኖር ብዛት ባልቆሸሸ ልባችን ፈፅሞ ትዝታ በማያቀው እድሜያችን .... የዛሬ 25 አመት አንድ መልከ መልካም ወጣት በማናውቀው አለም ውስጥ በምዕናብ አምነሸነሸን። የወደድኳት በማለዳ.. በልጅነት በአቡጊዳ... የፍቅር ቃል መጠሪያዬ... የመጀመሪያዬ... እያለ.... እየተስረቀረቀ ሆድ በሚበላ ድምፅ በአዲስ የግጥም አፃፃፍ ፣ ስራ ነገሩ ሁሉ የተለየና ትውልዳችንን ያነሆለለ ግሩም ሰው ተከሰተ። በዘመነ ካሴት አንድም ዘፈኑ የማይዘለል ዘፋኝ ተገኝቶ የልጅነት አፋችንን አሟሸው። ሳናፈቅር አፈቀርን ፣ የልብ መደላደል ሳይገባን ፣ የስም መጥፋት ህመም ሳያገኘን ያልኖረውን ዘመን ኖርን። ብላቴናው.... "ተረታና ልቤ ለፍቅርሽ ተገዛ በልቤ ቤት ሰራሽ ሄዋን እንደዋዛ" ን እያቀነቀነ ዛሬም ዘመን ተሻግሮ ያላረጀ ቤቱን በህዝብ ውስጥ ሰርቶ ቁጭ አለ። ወጣትና ህፃናት ጎልማሳና ሽማግሌው አንድ ላይ አበደለት። በየ ቤቱ ፣ ሱቁና ፀጉር ቤቱ ፣ ጫት ቤቱና ካፌው ፣ ታክሲና ባሱ አስፋልቱና መንገዱ አረገዱለት። ሁሉም ነገር ቀጥ ብሎ ፣ ሁሉም የወሬ ጉልበት ዝሎ ሃገር ጆሮውን ሰጥቶ እየሰማው ተደመመ። 'ልቤ መሸነፉን እንዳይነግራት ሰጋ' ን እያዜመ ልጃገረዶች ሁሉ ተሸነፉለት። ተማሪዎች ከደብተራቸው ጠርዝ ስሙን ፃፉት ፣ ጋዜጦች ተነተኑት! መፅሄቶች የየእትማቸው መልክ አረጉት። በዘመን ውስጥ ብዙ ሰው ተወዷል ፣ ብዙ ሰው ገኖ ብዙ ሰው ቀሏል። አንድ የ 23 አመት ወጣት በድንገት መጥቶ የሃገሩ ዜማ ሆነ። ተራው ህዝብ ብቻ አይደለም አንጋፎች ሳይቀር ለውዳሴ ተሽቀዳደሙለት። 1993 እንደ ሃገር የነበሩ የፖለቲካ ትኩሳቶች አመፅና ግርግሮች ሳይቀር በብላቴናው አልበም ደበዘዙ። ሃገር ቆም ብሎ አንድ ነገር ሰማ! ስለ አንድ ነገር አወራ። የመወደዱ ብዛት የፈጠረው የወሬ ግምት ገኖ ገኖ... ቴዲ ከቆነጃጅቶች ጡት ላይ ፈርሟል የሚል ወሬ ሃገሩ ላይ ተዛመተ። ያኔ ልክ እንደዛሬው ጡት በአደባባይ አልዋለም። መሸፋፈን ክብር አለመገለጥ ውበት ነበር። እንደዛሬው ወሬ የሚያዛምት Internet ወለድ የወሬ ማሽን ሳይኖር " እከሌ አበደችለት" "እከሌ በሱ ፍቅር ትዳሯን ፈታች"... የሚሉ አሉባልታዎች አየሩን ሞሉት። ብላቴናው ሃገር እንደ ጉድ ቢያብደለትም መወደዱ አላሰከረውም። አልበሙን ባወጣ በወራት ጊዜ ውስጥ በወቅቱ በነበረው አንድ ለናቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርቦ ጡት ላይ ስለመፈረሙ ተጠየቀ " ጨዋ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ ነው ያሳደገኝ" አለ... ሲዘፍን የሰማው ሁሉ አፉን ከፍቶ አይኑን ሰክቶ ሲያወራ ሰማው። አንገቱን የሰበረ አይኖቹ በትህትና የሚንከባለሉ ሆኖ ተገኘ። ሃገር በስስት አየው። አንጋፋዎቹ ልጄ ልጄ እያሉ ተሻሙበት። አትሌት ሃይሌ ገብረ ስላሴ "እኔ ሩጫ እንጂ ወሬ አልችልበትም" ብሎ ቴዲን ማድነቂያ ቃል አጣ። የዘመኑ አንጋፋዎች እነ ውብሸት ወርቃለማው ቢዘፍንልን ብለው ተመኙ። ቴዲ ከዘመኑ የሚነፃፀር ባለሙያ ታጥቶለት ተንታኞች ከቀደሙት ገናኖች ጋር አወዳደሩት። በብዙዎች ለቴዲ የራሱ አለም ተሰጠው! ብቻውን የሚዳኝ እኩያ የማይገኝለት ሆኖ ማርሽ ቀያሪነት የዜማ ሊቅነት የገጣሚነት ጫፍ ላይ ተቀመጠ! ገና በ 23 አመቱ መሸከም የሚከብድ ፍቅር ፣ አንገዳግዶ የሚጥልን አድናቆት ቢቀበልም ብላቴናው ከአደባባዮች ጠፍቶ ከግርግሩ እርቆ ከአራት አመታት በኋላ "ያስተሰርያል" በተሰኘ ታሪካዊ አልበም ተከሰተ። በመጀመሪያ አልበሙ አቡጊዳ እያለ የሃገሬውን ሆድ የበላው ሰው አሁን በአልበሙ ጥግጋት "ብልህ ሰው ታናሹንም ይሰማል" እያለ በትህትና ዝቅ ብሎ ሃገር በጥላቻ እያባከኑ ያሉ ሽማግሌዎችን የሚመክርበትን ግጥምና ዜማ ጠምቆ ሃገሩን እንደ አዲስ አሰከረው! ቴዲ በዚህ አልበም በእያንዳንዱ ስንኝ ውስጥ ተከድኖ የሚነደውን መተንፈሻ ያጣውን የሃገሬውን ህመም ከሰው በማይመስሉ ጌጠኛ ቃላትና ልብ በሚያርዱ ዜማዎች ቀምሞ ሃገሩን አስቆዘመው። ብላቴናው "ያስተሰርያል" በሚለው አልበሙ ለሃገሩ የቃተተበት ዜማዊ ፀሎት ነው። ፍቅር ማጣታችን የመራባችን ምንጭ መሆኑን ተናገረ። እየዘፈነ ሰበከ ፣ እየወቀሰ መከረ ፣ እየመከረ ምህረት ለመነ። በሚጣሉ ወላጆች መሃል ቆሞ ግራ እንደገባው ህፃን "መለየት አቃተን የሚበጀንን ሰው" እያለ የነፍሱን ጭንቀት አስረዳበት። ግጥሙ ከዜማው ዜማው ከግጥሙ የተዛመዱበትን መንገድ ብዙዎች በእንባ ሰሙት። ቴዲ የብዙዎችን የልብ ህመም እየፈታ የህልማቸውን ሃገር በጥበብ መስኮት ከሰተላቸው። ኸረ አይነጋም ወይ አይነጋም ወይ ሌቱ..... ቴዲ ለሃገሩ ቃተተላት ቴዲ ከመርቀቁ ብዛት እንኳን በሸውራራ አይናቸው የሚያዩት አብዝተው የሚወዱትም በቅጡ የሚረዱት አይደለም። ከጥቂቶች በቀር የሚወዱትም የሚያወራውን ፍቅር አያወሩም። የሚጠሉትም ያለውን በፈለጉት መንገድ ተረጎሙ እንጂ በልቡ ልክ አልሰሙትም! ያስተሰርያል ፍቅርና አድናቆት ብቻ ሳይሆን የመከራ መስቀል ይዞበት የመጣው ቴዲ የውሸት ክስ ተቀምሞለት በገዢዎች ጉልበት ዘብጥያ ወረደ። ወጣቶች ከፖሊስ ጋር ተፋለሙለት። ቆነነጃጅት ማልደው ከፍርድ ቤት እየተገኙ እናቶች አገልግላቸውን አስረው ተሰለፉለት። በዚህ ሃገር ታሪክ ታስሮ በቅፅበት ያልተረሳ ጉምቱ የለም። ብላቴናው ግን ከክርክር እስከ ፍርድ ከፍርድ እስከ መፈታት ከሰው አፍ ሳይጎድል የመንግስት ራስ ምታት ሆኖ ከወህኒ ቤት ተፈታ። ወትሮም እንኳን ዘፈኑ ቃለ መጠይቁ የሚናፈቅለት ጥበበኛ 'ከእስሩ በኋላ ምን ይል ይሆን?' በሚል ብዙዎች ጆሯቸውን ቀስረው ቢጠብቁትም ለአመታት እስር የዳረገውን የተከሸነ ክስና በቀል " ፍቅር ግን ሁሉን ያሸንፈል በሚል ከደነው። ቴዲ እየደመቀ እንጂ እየበሰለ ያልሄደ ተዐምረኛ ሰው ሰው! ሲጀመር ቃላቶቹ የጣፈጡ ሃሳቦቹ የረቀቁ ናቸው። ባሰበት የሚያስብል እንጂ እዚች ጋር ተወነጨፈ የሚያስብል ክፍተት አሳይቶ አያውቅም። በመሃል ከአልበም በላይ የሚንጡ ነጠላ ዜማዎችን እየለቀቀ ሲለው ተሰርቆና አምልጦ የሚወጣው ስራው ሁሉ የሰው ጆሮ እያጠገበና ልብን እያረሰረሰ ቀጠለ። በዚህ ሁሉ ስኬቱ መሃል ኩራት ከአጠገቡ የለም። ስራው አንግሶት በግርማ ፀጥ ያለ አንበሳን መስሎ ይኖራል። አይንና ጆሮ በበዛበት ልክ "ከአይን ያውጣህ" ብለው የማይመርቁት የረጋ ጥበብ ሆኖ ኖረ። ከዛ በኋላ የለቀቃቸው ሁለት አልበሞቹ የፈጠሩት ድባብ እንዲህ ነበር ማለት የማይፈታቸው የመፃፍንም ሆነ የማስታወስን ልክ የሚፈታተኑ ሃገራዊ ድባቦች ነበሩ። በተለይም ከጥቁር ሰው በኋላ ያወጣው ኢትዮጵያ የተሰኘው አልበም ሲለቀቅ እያንዳንዱ ቤት ሰርግ ያለ እስኪመስል እያንዳንዱ ገበያና ነጋዴ ሳር ጎዝጉዞ የጠበቀው የአውዳመት ዋዜማ ይመስል ነበር። በጊዜና በቦታው ከነበረ ካየና ካልሰማ በቀር ለታሪክ ነገሪ የማይመች አስደናቂ ድባብ። ስለ ብላቴናው ብዙ ከመፃፍ ብዙ አይባልም። ብዙ ተፅፎም ጥቂት አይገለፅም! ልባም ሰው ግን ቴዲን እና ስፋቱን በስራዎቹ ውስጥ ዞሮ ለማየት ጆሮዎቹን ከፍቶ በግጥምና ዜማዎቹ ውስጥ ቢውል የበለጠ ይረዳዋል።

Open in Telegram
Views2,880+523%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1402Photo
Views4,790×10vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1400Text

የጋብቻው ዋጋ ከሠርጉ ድግስ ይበልጣል — ብዙዎች ግን ለጭፈራው እንጂ ለህይወቱ አያስቡም ሁሉም ሰው የተረት ህይወትን ይመኛል። ማንም ግን ለሚመጣው መዘዝ/ውድቀት አይዘጋጅም ወይም አያስብም። ለማሳየት፣ ለማስመሰል አይዞኝ ብለሃል። ለቀናት የአፍ ወሬ ሆንክ። በረራ አደረግክ፤ ብርህን በተንክ። ግን መሠረት ጥለሃል ወይ? የገዛኸው ጥበብን ነው — ወይስ ጊዜያዊ ጌጥና ውጫዊ ውበትን? ብዙዎች የሚያገቡት ድግሱን/ጭፈራውን ነው፣ ሰዉን አይደለም። እናም የእውነተኛው ዋጋ ሲመጣ ይደናገጣሉ። ነገሩን እንየው እስኪ፦ 1. ሠርጉ የአንድ ቀን ነው — ትዳሩ ግን የአርባ ዓመት ለፎቶ አንሺዎች በጀት መድበሃል። ለትዳር ምክርስ በጀት ይዘሃል? አበባ መርጠሃል። የሕይወት እሴቶችንስ መርጠሃል? ቅፅበቱን አግብተህ — ላላሰብከው ረጅም የህይወት ዘመን እስረኛ ሆንክ። ድግስ ለስድስት ሰዓት ነው። ትዳር ግን ስልሳ ዓመታትን ይጠይቃል። በዚያ ልክ ተዘጋጅ። 2. የውሸት የፍቅር ናዳ አታሎህ እድሜ ልክህን በብቸኝነት እንድትማቅቅ አትፍቀድ አንዳንድ ሰዎች ፍፁም መስለው መታየት ላይ የተካኑ ናቸው — እስክታገባቸው ድረስ። ያቆላምጡሃል። በሐሰት ፍቅር ያጥለቀልቁሃል። ይዘውህ ይዞራሉ፣ ያሳዩሃል። እናም የደስታው ጊዜ ሲያልፍና ሲበርድስ? በሚያምር ልብስ የተሸፈነ እንግዳ እንዳገባህ ትረዳለህ። ጊዜያዊ መፈላለግ እውነታውን እንዳይጋርድብህ ተጠንቀቅ። በፈተናው ጊዜ አጥናቸው — የፈገግታ ፎቷቸውን ብቻ አይደለም። ምክንያቱም በራስህ ቤት ብቸኝነት እየተሰማህ 'ለዘላለም' መኖር በጣም ረጅም ጊዜ ነው። 3. ቤተሰብህና ጓደኞችህ የሚገፉህ ከሆነ — ቆም ብለህ አስብ! ሁሉም ትውውቅ ከፈጣሪ የተሰጠ አይደለም። አንዳንድ ቤተሰቦች "ሸክማቸውን ለማራገፍ" ይቸኩላሉ። አንዳንድ ጓደኞች በሰርግህ ለመጨፈር የቋመጡ ናቸው። አንተ ግን? የተሳሳተ ሰዉ ሆኖ ነገር ግን ውብ ፊት ወይም አንደበት ያለው ሰው አይተህ፤ ካመንክ፣ ጥልቁ ውስጥ የምትሰምጠው አንተ ነህ። የትውልድን መሰረት የሚጥል ራዕይ ከሌላት፣ 'ይሆናል'ን ወይም ጸሎትን ብቻ አታግባ። ትዳር የማገገሚያ ወይም የመልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል አይደለም። አንቺም ለማድለብና ለመራባት የታጨሽ እንስሳ አይደለሽም። ንቃ! ባክህ/ባክሽ! 4. መውጫውም ቢሆን ቀላል አይደለም "ካልተሳካ እፈታለሁ/እፈታታለሁ።" እውነት? ፍቺ ቀላል መውጫ መንገድ እንዳይመስልህ። ልብህን አስቀድሜ ልስበርልህ፦ ፍቺ የስም ማጥፋትና የነውር ምልክት ይዞ ይመጣል። የተፋቱ አባቶች በህብረተሰቡ ዘንድ ብዙም አይታዩም፣ ድምፃቸው አይሰማም። ብቸኛ እናቶች ይገለላሉ፣ የህብረተሰቡን ነቀፋ ይሸከማሉ። የተፋቱ ሰዎች ሁልጊዜ ራሳቸውን ማስረዳትና ማብራራት ይጠበቅባቸዋል። በዚህ ላይ ልጆች ካሉበትስ? ለዓመታት ለሚቆይ የጠበቃ ክፍያ፣ የልጅ የማሳደግ መብት ክርክር እና ለስሜት ፈንጂዎች ተዘጋጅ። የትዳር አጋርህን ብቻ አይደለም የምታጣው። ጊዜ፣ ገንዘብ፣ የዋህነት — አንዳንዴም ራስህን ታጣለህ። 5. የምታገባው ፀባይን ነው — መልክን አይደለም የወገቧ ቅጥነት የሰመጠች መርከብህን አያድንም። የቁመቱ ርዝመት አመፀኛ ልጅህን አይገስፅም። ፀባይ ግዛትን ይገነባል። ውበትና አንደበት ግን በአየር ላይ ግንብ ይሠራል። በእያንዳንዱ የፈተና ሀሩር የምትቀልጥ ሻማ ካገባህ፣ በጨለማ ለመኖር ተዘጋጅ። ምክንያቱም የሕይወት ማዕበልና ፈተና አይቀሬ ነው። 6. ሸክም የሆነን ሰው ማግባት የትውልድ አሻራህን ዋጋ ያስከፍልሃል መጥፎ ጋብቻ፦ ህልምህን ያዘገያል። ገንዘብህን ያሟጥጣል። ስምህን ያጠፋል። የእጣ ፈንታህን መንገድ ያስታል። አንድ የተሳሳተ ፊርማ የአስር ዓመት ልፋትህን ሊያጠፋ ይችላል። በጥንቃቄ ምረጥ። በጤናማ አእምሮ ምረጥ። ምክንያቱም የምትመርጠው የሠርግ ልብስ አይደለም — ሕይወት ለምትባለው አስቸጋሪ ጉዞ አብሮህ መሪ የሚሆንህን እንጂ። 7. ቅፅበቱን ሳይሆን — የጋራ ዓላማችሁን አግቡ የምታገቡት አስተሳሰብን ነው። ቅፅበታዊ ስሜትን አይደለም። የምታገቡት መላ አካባቢውን፣ ስነ-ምህዳሩን ነው። የማህበራዊ ሚዲያ ገፅን አይደለም። ከባባድ ጥያቄዎችን ጠይቁ። ያለፈ ታሪካቸውን መርምሩ። አማካሪዎቻቸውንና የቅርብ ሰዎቻቸውን አጣሩ። ታማኝነታቸውን ፈትኑ። ምክንያቱም አሁን ያላጣራችሁት ነገር — በኋላ ዋጋ ያስከፍላችኋል፤ ታለቅሱበታላችሁ። 8. ስርዓት የሌለው ፍቅር ለመፍረስ የተዘጋጀ ስሜት ብቻ ነው ስርዓት ልጆችን ያሳድጋል። ስርዓት የቤት ብድር ይከፍላል። ስርዓት ህመምን፣ ክህደትን፣ መሰልቸትንና እርጅናን ለመቋቋም ያግዛል። የጋብቻህ መመሪያና እቅድ "ፍቅር በራሱ መላ ያበጃል" የሚል ከሆነ… ፍቅር በእውነተኛው የህይወት ውጣ ውረድና ግፊያ ውስጥ ለመጥፋት ይዘጋጅ። ስሜቶች ተሳፋሪዎች ናቸው። ስርዓት ነው መኪናውን የሚነዳው። አንዱን ያዝ — ወይም ትሰባበራለህ። የመጨረሻ ቃል፦ እንደ ቤት ሰሪ አግቡ — እንደ ሸማች ሳይሆን ከራዕይ ይልቅ ጊዜያዊ ስሜትን ከመረጥክ — ለጥፋትና ለህመም ተዘጋጅ። ከመዋቅርና እቅድ ይልቅ ቅፅበታዊነትን ከመረጥክ — ለሀዘን ተዘጋጅ። ሠርጉ ማጥመጃው ነው። ጋብቻው ሂሳቡና ዋጋው ነው። እናም ማንም የከፈልከውን ዋጋ አይመልስልህም። አስተዋይ ሁን። በእሴቶችህ ፅና። ራስህን መገንባትህን አታቋርጥ። @Bookfor @Bookfor

Open in Telegram
Views9,490×21vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1398Photo

". . . .ወንጌለ ውዴ የልቤ ማህደር፤ እንዴት ይዞሻል? የገና በአል ስለደረሰ ነው መሰለኝ፡ ሸገር ድምቅ ድምቅ ምቅ ብላለች። ሸገርን እንዲያው ዝም ብዬ ሣያት አለ አይደል ያኔ እማመይ ልጅ ሆነን የገናን በአል ለማድመቅ ስትል ከገበያ ሄዳ የምታትገዛውን የጥድ ዛፍ ታስታውሰኛለች! ወንጌለ ውዴ የልቤ ማህደር ነገሩ እንዲህ ነው። ልጅ አያለን ትዝ የሚልሽ ከሆነ አባቢ አኛን የ ሀገር ባህል ልብስ (ነጭ በነጭ) አልብሶ እንደሚያዚያ ጠሃይ ፍክት ድምቅ ሲደርገን፤ እማመይ ደግሞ የጥዱን ዛፍ በትልቅ ጣሣ ውስጥ አፈርና ድንጋይ ሞልታ ታቆመውና ፊኛውን ነፍታ ፤ አንድም ዛፉን ለማሣመር ሁለትም ከበአሉ ማግስት እኛው ከዛፉ ላይ እየበጠስን እድንበላው በገና ዛፍ መብራት አሽንቆጥቁጣው፤ ከረሜላና ቸኮሌት በክር ታንጠለጥልልን ነበር።..... ወንጌለ ውዴ የልቤ ማህደር ግና ኑሮም ሲከፋ ጊዜም ሲነጉድ የገና ጥዱ ከነ ብልጭልጭ መብራቱ እንደነበረ ትዝ የሚልሽ ከሆነ ከረሜለዉና ቸኮሌቹ ቀርቶ በአሱ ፋንታ ወጉ እንዳይቀር በሚያብለጨልጭ ወረቀት ድንጋይ ታንጠለጥልልን ነበር። .. . . ወንጌለ ውዴ የልቤ ማህደር ሸገርም አሁን እንደዚያ በሚያብረቀርቀው ወረቀት የተጠቀለለውን የማይበላውን ድንጋይ ያንጠለጠለች ውብ የገና ጥድ መሰለችኝ።. . .ውዴ እንዲው እየራበኝ እየሞረሞረኝ፤ አብረቅርቄ፤ ደምቄ፤ ልሞት ነው መሰለኝ፡፡ " ____ ምንተስኖት @Bookfor @Bookfor

Open in Telegram
Views8,770×19vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—

All posts

Connections