AI ChatbetaAccount
አትሮኖስ

አትሮኖስ

╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗ ║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣ ╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩ ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል። Contact @atronosebot please dont touch the leave button.😔😳😳

Username
@atronosee
Category
Books
Country
EthiopiaEthiopia
Created
, 8 years
Subscribers258,961−7,581, −2.8% in 30 days−1,992 last week
Avg views per post, 7d855−18.2% vs prev 7d
ERR0.33%last 7 days

Subscribers, 30 days

Oct 25 – Nov 24−7,581 (−2.8%)

Show as table
DateSubscribers
Oct 25, 2026266,542
Oct 26, 2026266,441
Oct 27, 2026266,418
Oct 28, 2026266,311
Oct 29, 2026266,189
Oct 30, 2026266,397
Oct 31, 2026266,088
Nov 1, 2026265,636
Nov 2, 2026265,335
Nov 3, 2026265,073
Nov 4, 2026264,680
Nov 5, 2026264,421
Nov 6, 2026264,157
Nov 7, 2026263,933
Nov 8, 2026263,500
Nov 9, 2026263,201
Nov 10, 2026262,995
Nov 11, 2026262,700
Nov 12, 2026262,185
Nov 13, 2026261,957
Nov 14, 2026261,546
Nov 15, 2026261,324
Nov 17, 2026260,953
Nov 18, 2026260,624
Nov 19, 2026260,339
Nov 20, 2026260,098
Nov 21, 2026259,818
Nov 22, 2026259,581
Nov 24, 2026258,961

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Oct 25, 20261,153
Oct 26, 20261,071
Oct 27, 2026375
Oct 28, 2026964
Oct 29, 2026922
Oct 30, 2026944
Oct 31, 2026736
Nov 1, 2026827
Nov 2, 2026896
Nov 3, 20261,118
Nov 4, 20261,230
Nov 6, 20261,036
Nov 7, 2026934
Nov 8, 20261,029
Nov 9, 20261,151
Nov 10, 20261,036
Nov 11, 20261,148
Nov 12, 20261,093
Nov 13, 2026955
Nov 14, 20261,033
Nov 15, 20261,197
Nov 16, 2026981
Nov 17, 20261,006
Nov 18, 2026920
Nov 19, 2026988
Nov 21, 2026944
Nov 22, 2026784
Nov 23, 2026709

Advertising

Ad posts, 30 days88 removed · latest
Avg views per ad post87−90.5% vs other posts
  1. ቤቲንግ ይጫወታሉ መበላትስ ሰልችቶታል እንግዲያውንሱ በነፃ ያለምንም ክፍያ በቀን ከ 50-150 odd የሚለቀቅበት ቻናል ልጠቁማቹ ይጠቀሙበታል ቻናሉን ከስር ያሉትን በመንካት ቶሎ ይቀላቀላሉdeleted18
  2. ◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በለው ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝗝𝗢𝗶𝗻👇👇deleted153
  3. ሁሌ ቤቴንግ መበላት ከሰለቸህ ይሄን ቻናል ተቀላቀል ሁሌ ነው አሸናፊ እምትሆነው Ethiopia ውስጥ ይሄ ብቻ ነው እውነተኛ ቻናል ስለዚ ሳያመልጣህ አሁኑኑ ተቀላቀልdeleted134
  4. 🎧🎵የማንን ሙዚቃ ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇 👤 Mikaya Behailu 👤 Minyeshu Kifle 👤 Muluken Melesse 👤 Neway Debebe 👤 Nati Haile 👤 Nhatty Man 👤 Sami Dan 👤 Sayat…deleted49
  5. ❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️ እንዴዴዴዴዴዴዴ ኧረ ፍጠኑ ጥያቄና መልስ ጀምረናል🔥🔥 ✔️ ቀድሞ ለመለሱ 5 ሰዎች የካርድ ሽልማት አለ Request to Join ያድርጉ 🟣 የአለማችን ብዙ ህዝብ ያላት ሀገር ማን ነች ❓deleted31

Most viewed this month

  1. 01

    📖 አንባቢ ለመሆን የሚረዱ 6 ቀላልና ተግባራዊ ሕጎች! «ማንበብ እፈልጋለሁ ግን ጊዜ የለኝም» ወይም «አንድ መጽሐፍ ጀምሬ መጨረስ አልቻልኩም» ብለው ያውቃሉ? እንግዲያውስ እነዚህ 6 ቀላል ሕጎች የንባብ ህይወትዎን ሙሉ በሙሉ ይቀይሩታል! 👇 1️⃣ The 10-Pages a Day Rule (የ10 ገጽ ሕግ) በአንድ ጊዜ 100 ገጽ ለማንበብ አትሞክሩ። በቀን 10 ገጽ ብቻ አንብቡ—ይህ ከ15 እስከ 20 ደቂቃ ብቻ ነው የሚወስደው! 💡 በቀን 10 ገጽ = በወር 300 ገጽ (1 ሙሉ መጽሐፍ) = በዓመት 12 መጻሕፍት ያለምንም ድካም! 2️⃣ Habit Stacking (ልማድን ከልማድ ጋር ማያያዝ) ንባብን ሁልጊዜ ከሚያደርጉት ቋሚ ልማድ ጋር አያይዙት። ☕️ «የጠዋት ቡናዬን ስጠጣ 5 ገጽ አነባለሁ» 🛌 «ማታ ከመተኛቴ በፊት አልጋ ላይ ሆኜ ለ10 ደቂቃ አነባለሁ» ይህ ዘዴ አእምሮአችሁ ሳያመነታ ንባብን ልማድ እንዲያደርግ ይረዳዋል። 3️⃣ The 50-Page Rule (የ50 ገጽ ሕግ) አንድን መጽሐፍ እስከ 50 ገጽ አንብባችሁ ካልጣማችሁ በግድ መጨረስ የለባችሁም፤ አስቀምጡትና ወደ ሌላ ይለፉ! የማይስብን መጽሐፍ በግድ ለማንበብ መሞከር የንባብ ፍላጎትን ይገድላል። 4️⃣ Replace Scroll with Page (ስክሮልን በገጽ መተካት) በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምናጠፋውን ጊዜ መጽሐፍ ለማንበብ እንጠቀምበት! ስልካችሁን አንስታችሁ ፌስቡክ ወይም ቲክቶክ ከመክፈታችሁ በፊት፣ መጽሐፋችሁን ገልጣችሁ 2 ገጽ ብቻ የማንበብ ልማድ ይኑራችሁ። 5️⃣ Always Carry a Book (ሁልጊዜ መጽሐፍ መያዝ) ቦርሳችሁ ውስጥ ሁልጊዜ አንድ መጽሐፍ (ወይም በስልካችሁ PDF/e-book) ይኑራችሁ። ታክሲ እየጠበቃችሁ፣ ተሰልፋችሁ ወይም ሰው ስትጠብቁ ለጥቂት ደቂቃዎች ማንበብ ከንባብ ጋር በቀላሉ ያላምዳችኋል። 6️⃣ Read What You Love (የሚወዱትን ያንብቡ) ሰዎች ስለወደዱት ብቻ ለእርስዎ የማይመች መጽሐፍ አያንቡ ታሪክ፣ እድገት (Self-help)፣ ሳይንስ ወይም ልብወለድ ደስ የሚልዎትን ዘውግ በመምረጥ ይጀምሩ! 💡 «ዛሬ የምታነበው ነገር ነገ የምትሆነውን ሰው ይወስናል!» 🔄 ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ @atronosee

    Text
    Views1.27K
    Forwards4
    Reactions5
    Comments1
  2. 02
    Views1.23K
    Forwards2
    Reactions15
    Comments2
  3. 03
    Views1.23K
    Forwards3
    Reactions17
    Comments13
  4. 04

    🐘እርግጠኛ ነሽ አርግዘሻል? አንድ ውሻና አንዲት ዝሆን በተመሳሳይ ጊዜ ፀነሱ ከሦስት ወራት በኋላ ውሻዋ ስድስት ቡችሎችን ወለደች ዝሆኗ ግን ገና ነፍሰ ጡር ነበረች ከዚያም ወራት አለፉ ውሻዋ እንደገና ፀነሰች በድጋሚም ቡችሎችን ወለደች ይህ ሁኔታ በተደጋጋሚ ቀጠለ ውሻዋ በየጥቂት ወራቱ ትወልድ ነበር ዝሆኗ ግን አሁንም ጽንሷን በማህፀኗ ተሸክማ ትጠብቅ ነበር በአንድ ወቅት ውሻዋ ወደ ዝሆኗ ቀርባ በጉጉት ጠየቀቻት ✨እርግጠኛ ነሽ ነፍሰ ጡር እንደሆንሽ? በሆድሽ ውስጥ በእርግጥ ጽንስ አለ? ተመሳሳይ ጊዜ ነው የፀነስነው እኔ ግን ከ16 በላይ ቡችሎችን ወልጄ አንዳንዶቹም አድገው ትልቅ ውሾች ሆነዋል አንቺ ግን አሁንም እርጉዝ ነኝ ትያለሽ ምን እየሆነ ነው? ዝሆኗም በረጋ መንፈስ እንዲህ ስትል መለሰች 🐘 «እኔ እንድትረጂ የምፈልገው አንድ ነገር አለ በማህፀኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነው እኔ ለረጅም ጊዜ እጠብቃለሁ ግን የምወልደው አንድ ብቻ ቢሆንም ተራ አይደለም ልጄ መሬት ላይ ሲረግጥ ኃይሉ ይታያል በመንገድ ላይ ሲሄድ ሰዎች ቆመው ያደንቁታል የእርሱ መኖር የሰዎችን ትኩረት ይስባል ስለዚህ የእኔ ጉዞ ከአንቺ ጋር ተመሳሳይ ባይሆንም የራሴ ጊዜና የራሴ ዓላማ አለኝ» ✨የሕይወት ትምህርት ወዳጄ ሌሎች ከአንተ በፊት ስኬታቸውን ሲያገኙ ሕይወታቸው ሲቀየርና የሚፈልጉትን ሲያሳኩ በእነርሱ አትቅና የአንተም ተስፋ እንዲጠፋ አትፍቀድ የሌላው ሰው ፍጥነት የአንተን መድረሻ አይወስንም ሁሉም ሰው የራሱ ጊዜ የራሱ መንገድና የራሱ ፈተና አለው 🌱 የአንተ ስኬት ዘግይቶ መምጣቱ ፈጽሞ እንደማይመጣ አያመለክትም 💎 ትዕግሥትህን አታጣ ጥረትህን አታቋርጥ የራስህን ጉዞ ከሌላ ሰው ጋር አታነጻጽር የራስህ ጊዜ ሲደርስ የራስህ ታሪክ ይጻፋል @atronosee

    Photo
    Views1.2K
    Forwards6
    Reactions21
    Comments3

Latest posts

#98284Text
Views641−30%vs avg
Forwards5
Reactions22
Comments1
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h64
2 h174
3 h197
6 h217
22 h641
  1. After 1 hour174
  2. After 6 hours217
  3. After 24 hours641
  4. Total to date641
#98283Text

​​የፀባቸው መነሻ ከአዳም ማታ ሲለፈልፍ እንደተረዱት ሲፈን ናት ይህን በመረዳታቸው ክፉኛ አዝነዋል ፣መንትዮች ፍላጎታቸው ይመሳሰላል ሲባል ሰምተዋል በነአዳም ላይ ግን ከመልክ መመሳሰል ውጪ እስከዛሬ ፍፁም የሚያመሳስል ነገር አላዩም አዳም አስቸጋሪና ጉልበተኛ የፈለገውን ከማድረግ የማይመለስ እንቢተኛ ነው ።ኤዶም ሰው አክባሪ ብዙም የማያወራ ቤተሰቦቹን አክባሪ ከቃላቸው የማይወጣ ትሁት ፣ ከስራ መልስ ወደቤት ፣ከቤት ወደስራ ከማለት በስተቀር ምንም አይነት አመል የሌለበት ነው ።  እስከዛሬም አዳም የተለያዩ ሴቶችን በፍቅር ሰበብ እየቀረበ ሲያሳዝን የቆየ ነው ፣እትዬ ፅጌ እንኳ የሚያውቋት ቤት ድረስ የምትመጣ ምስኪን ልጅ ነበረች ለምናው ለምናው ፍቃደኛ ሳይሆንላት ሲቀር ፣ እናትየው ያውቋት ስለነበር ቤት ድረስ በመምጣት እንዲያማልዷት ተማፅና ነበር ፣ አዳም ግን የፈለገውን ቀድሞ አግኝቷልና ወደሌላዋ ለመሻገር ስለፈለገ ፣ የሷነገር እንደሰለቸው  ያለምንም አዘኔታ በመንገር ፣ እርሺኝ ላይሽ አልፈልግም ብሎ አቃሎ አባሯታል ፣ እትዬ ፅጌ ከነስሟ ያውቋት ስለነበር 'የእየሩስ ግፍ አንድ ቀን ያገኝሃል' ብለውትም ነበር። ምናልባትም የግፉን ክፍያ በሲፈን እያገኘም ይሆናል......... ===-==-==- አዳም እንደተነሳ እያዛጋ በድብርት እየተንገላታ ሳሎን ገባ ፣ እናም ለመታጠብ ወደ አስቦ መታጠቢያ ክፍል ሊያመራ ሲል ። አባት "አንታይህም ደና አደራችሁም አይባልም "አሉት "ውይ አባዬ  ራሴን አሞኛል አይኔን እንኳ መክፈት አልቻልኩም "አለ "አይንህን ያጥፋው ፣ለነገሩ አጥፍቶልሃል !"ብለው ቱግ አሉ እትዬ ፅጌ ደነገጡ ባላቸው እንዲ አምርረው ሲራገሙ ሰምተው አያውቁም፣ ውስጣቸው ተላወሰ ፣ ለአዳም አዘኑ የአዳም ፊት አባብጧል በኤዶም ቦክስ ፣ክፉኛ እንዳገኘው ያወቁት አሁን ሲያዩት ነው ። እሱ ሰለማታው ሁኔታ ብዙም ያስታወሰ አይመስልም "ወይኔ ልጄ እስኪ ፊትህ ኧረ ምን ጉድ ነው ፣እንዴት እንዴት ነው ያገኘው በል "ብለው ወደባላቸው ዞሩ "እሰይ ጥሩ አደረገ ሁሌ እሱን ብቻ ማን ጉልበተኛ አደረገው ይሄ ክፉ አሉ ከንዴታቸው ሳይበርዱ "እንዴ አባዬ ምን ሆነሃል ለምንድነው የምትሰድበኝ "አለ አዳም ቆጣ ብሎ "ምክንያቱም እኩይ ስለሆንክ ፣ባንተ የተነሳ ከቤት ወጥቶ የማያውቅ ልጅ ወጥቶ አደረ  እንዴት አንተ በወንድምህ ሴት ትቀናለህ ፣ አንተ ባለጌ ! ያንተን ሴት ተኛዋት ብለህ ወንድምህን ታሳብደዋለህ እንዴት ስርሃት ብታጣ ነው ! የስከዛሬው ጥጋብህ አልበቃ ብሎ ዛሬ ደሞ በብቸኛ ወንድምህ ላይ ተነሳህ ፣ "አሉት ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው "ምን እኔ ......"ብሎ አዳም በአንድ እጁ ጭንቅላቱን ይዞ የማታውን ሁኔታውን ለማስታወስ ሞከረ "ኧረ ባክህን ተው እንጂ አይደለም መነጋገር ያለብን የአዳም አባት ሁለቱም ልጆቻችን ናቸው ፣ማስማማት ነው ያለብን እባክህ ተረጋጋ"አሉ እትዬ ፅጌ አዳም በፍጥነት መፀዳጃ ቤት ሄዶ እራሱን አየ ፣ፊቱ አባብጧል አይኑንን የከለለው ለካ እብጠቱ ነው ። በጣም ተናደደ ኤዶም ሰክሮ ስላገኘው እንዳጠቃው አይነት ስሜት ተሰማው ። ፊቱን ተጣጥቦ ልብሱን ቀያይሮ የሹራብ ኮፍያና መነፅር አድርጎ እየተጣደፈ ወጣ። እልህኝነቱ አገረሸበት ፣ኤዶምን ፊለፊቱ ቢያገኘው የሚለቀው አይመስልም .....እትዬ ፅጌ ተከትለውት ቢሮጡም አልደረሱበትም ፣ አባት ተይው ቢያገኘው ለሱ የሚያንስ ጉልበት ያለው ይመስልሻል ዝም ያለሰው አይነሳ ብቻ "አሉ እትዬ ፅጌ ዛሬ የባላቸው ማምረር ደስ አላላቸውም  ሁለቱንም ከመገሰፅ ይልቅ ለአንዱ ማዳላት ምንድነው  ብለው ተቀየሙ ...... ======== ኤዶም አብዲ ጋር የሄደው ንዴቱ ሲበርድለት ነበር ። እናቱንም ማሳዘን ስላልፈለገ ነው አብዲን ደውሎ እኔ ጋር ነው እንዲል ያደረገው ፣ ከአብዲጋር ሰለሆነው ሁሉ ሲነግረው አዲስ አልሆነበትም ፣ ምክንያቱም አብዲም ከአዳም ጋር ብዙ ተጨቃጭቆበታል ፣ አይሆንም ተው ብሎ አዳምን መክሮታል ግን አዳም ሞገደኛ ሆነበት በቀላሉ የሚያምን አይነት ሰው አይደለም ፣ የትላንትናው ግን በጣም መብዛቱን እሱም አውቋል በዚም ተናግሮት ተጣልተው ነው  የተለያዩት ። ኤዶምን ለማብሸቅ ግን በዚ መጠን ይናገራል ብሎ አልገመተም ፣ አዳም ላይ ተናደደ ፣ ይበልጥ ግን ያሳሰበው ኤዶም ሲፈን እንዴት አልነገረችኝም ፣ደጋግሜ ጠይቄያት ነበረ መከፋቷን አይቼ ። ብሎ ሲፈንን ካሁን በዋላ አላናግራትም ፣እኔላይ እያሾፈች ነው ምናልባትም ወንድሜን ትወደው ይሆናል ብሎ ሲያመር ነው።  ኤዶምን ለማሳመን ብዙ አወራ  ብትፈልገው ማን ያግዳታል ያንተን ስልክ ነው ተጠቅሞ ያሞኛት ፣ ነገርግን እሱ እንዳለው አይደለም አልነካትም ፣ ብሎ ብዙ አስረዳው  ኤዶም ንዴቱ አልበርድ አለው የተከዳ መሰለው  ከነ አብዲ ቤት ወጥቶ በቀጥታ እግሩ እንደመራው ተጓዘ ብስጭቱ እንዲተወው ፈጣሪ እንዲያረጋጋው ለመነ .....  እንዲ እየተጓዘ ሳለ ፣አንዲት ሴት እየሮጠች ወደሱ ስትመጣ አያት ፣ እራሱን አዘጋጀ ሊከላከላት ፣ፊቷላይ የደሰታ ስሜት ይነበባል የናፈቁትን ሰው ድንገት የገኙ አይነት ነው አመጣጧ ..... "አዳም ወይኔ .....ፈጣሪዬ......አዳም  ሰሎሜ እኮነኝ አላስታወስከኝም ...አዳምዬዬ..."ወገቡን ይዛ በደስታ ተፍለቀለቀች "ቆይ ቆይ ....."አለ ኤዶም እራሱን ለማስለቀቅ እየታገለ  .. #Share እና #Reaction..❤️ 👍 ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ። 👇Sebscribe YouTube link👇 https://www.youtube.com/@atronose

Open in Telegram
Views720−21%vs avg
Forwards2
Reactions30
Comments0
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h113
4 h389
7 h463
25 h703
26 h720
  1. After 1 hour113
  2. After 6 hours463
  3. After 24 hours703
  4. Total to date720
#98282Text

#ባለ_ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ ፡ ፡ ...ሲፈን በኤዶም እቅፍ ውስጥ ሙቀት ተሰማት የተለየ መረጋጋት የተለየ ሰላም ተሰማት ከነገሮች ሁሉ ሰውሮ የሚያስቀራት የሚከላከልላት እቅፍ ጠንካራ እቅፍ  ለአክስቱ ዝግጅት ሲባል የተቀባው ሽቶ ጠረኑ ተመቻት ያለችበትን ቦታ ለጊዜው አስረሳት ኤዶም ከቁጣ በርዶ  ሲፈንን ደረቱ ላይ እንደለጠፈ አፍንጫውን በፀጉሯ መሃል እያርመሰመሰ  ሽታዋን ሳበ ። የፍቅሩን ሐይል የሚገልፅበት መንገድ እያነሰበት ተቸገረ ለሲፈን የሚበቃት ምን ይሆን  .... "ኤዱ በቃ  !እንዴ ምን እያደረከኝ እንደሆን ተመልከት  "ብላ በኤዶም ዙሪያ የጠመጠመቻቸውን እጆቿን አላቃ እራቅ አለችው ። ኤዶም በደከመ እይታ አስተዋላት  ፈራች ደሞ ሊጀምረኝ ነው ይሄ ሽንፈቴ ብላ ከራሷጋር ተነጋገረች "ኤዶም በቃ ወደቤት ሂድ ማሚ ድንገት ልትወጣ ትችላለች ፣ ነገ እንገናኛለን "አለችው "እሺ ግን እኮ ልክ አይደለሽም ፊትሽ ላይ የማየው ነገር ይረብሻል ፣ አዳም በኔ ስልክ ደውሎልሽ ነበር ፣ነገርግን በትክክል ምን እንዳለሽ አላውቅም ፣ ምክንያቱም በግልፅ አልነገርሽኝም ፣  ወንድሜ አስቀይሞሽ ነው ?"አላት በጥርጣሬ "ልትሰማኝ የፈለክ አልመሰለኝም ምንድነው ። እንዲ ያሳሰበህ ? አዳም ልክ ያልሆነ ነገር ቢናገረኝስ ምን አዲስ ነገር አለ ፣ትክክል ተናግሮ ያውቃል እንዴ ?"ብላ ቆጣ አለች "እሺ በቃ አትናደጂብኝ  እሄዳለው አንዴ የመንገዴን  ብቻ "ብሏት ፈገግ አለ ።ሲፈን ፈገግ ለማለት እየሞከረች "መቼም አትሸነፍም አይደል "ብላ በመጠጋት ከንፈሩን ሳም አደረገችው በስሱ.... "በስሱ ደረስ መለስ ይሁን ጣፋጭ ነው "ብሎ ሳቀ ። እናም እጇን ያዝ አድርጎ በመሳም ተሰናበታት ። ሲፈን በዚመንገድ ከኤዶም ጋር ከተለያየች በኋላ ወደ ጊቢዋ ስትመለስ ሊያን ቆማ ስታይ እንደነበር አስተዋለች። "ምንድነው ተደብቀሽ ስታይኝ ነበር?"አለቻት እንደማፈርም እንደመቆጣትም ብላ "በጣም ቆንጆ ነው!"አለች እየሳቀች "ስርአት ይኑርሽ ሂጂ ግቢ በቃ "አለቻት.. ሊያ እየሳቀች ወደሳሎን ያየችውን ለእህቶቿ ልታጋራ ፈጠነች ሲፈን ስለገባት ልታስቆማት ተከተለቻት ግን ስትደርስ በከፊል አውርታ ጨርሳለች ። እህቶቿ ምን አሳፈረሽ በሚል ሳቁ ።ሲፈን ሳትቀመጥ ወደ ክፍሏ ገባች ፣የእህቶቿን ሁኔታ ቶሎ እረሳች ሃሳቧ በሙሉ ኤዶም ጋር እና አዳም ጋር ሄደ ፣  ወደፊት ምን ሊፈጠር ይችላል የሚለው አሳብ ጭንቅላቷን አዞረው ፣ አዳም በዚ ሁኔታው ከቀጠለ አብዶ ያሳብዳታል ፣  ከእነሱ አካባቢ እንዳትርቅ ትታ የማትተወው የኤዶም ፍቅር አለባት  ምርጫዋ ከባድ ነው ።  ወይ በድፍረት  ከኤዶም ጋር በመቀጠል በወንድማማቾች መሃከል መግባት አለበለዚያ ፣ ኤዶምን በማስቀየም ከሁለቱም መሃል እራሷን በማውጣት ፣ ከነሱ መሰወር !!...ግን እንዴት ፍቅሯስ ኤዶምስ የልቧ ጥያቄስ ...........? ====== ኤዶም ቤት ሲገባ ቡና ቀራርቦ እራት ተዘገጃጅቶ  እሱንና ወንድሙን ጥበቃ ላይ ነበር ። እናትና አባት  መትዮቹን እኩል ቤት ሲገቡ አብረዋቸው ቢጨዋወቱ ደስ ይላቸዋል ነገር ግን ሁሌም በአዳም በኩል አይሳካም ፣ የነሱ አጫዋች ትህዛዝ አክባሪ ኤዶም ነው።  ሰብሰብ ብለው መጫወቱ በፊት ቀረ አዳም ከመጎርመሱ በፊት ። ከጎረመሱ በዋላ አዳም  ተቀይሯል ከወንድሙ ጋር በመልክ ብቻ እንጂ በፀባይ ተራርቀዋል አዳም ደጅ ደጁን ነው የሚወደው ብዙ ጓደኞች አሉት የሴትም የወንድም የተለያዩ ፍቅረኞችም ነበሩት ብዙ ሴቶች ላይ በፍቅር መቀለድ ደስ ይለውም ነበር  ። በአንፃሩ ኤዶም የናትና የአባቱ ታዛዥ ልጅ ነው  እስካሁንም ድረስ እነሱ እንዳይቀየሙ ሁሉንም እሺ ከማለት ሌላ ቃል አይወጣውም ።  እናት ኤዶምን ሲያዩ ደስ አላቸው ሲቆይባቸው ተጨንቀው ነበር ። እሱን ሲያዩ ምግቡንም ቀረብ ቀረብ አድርገው ። እየበሉ መጨዋወት ጀመሩ ። አዳም ስላስለመዳቸው ያው ሲመጣ ይምጣ ብለው ነው የሚያልፉት ፣  እየተጫወቱ ስለነበራቸው የክፍለሃገሩ ቆይታ ሲያነሱ ሲጥሉ  ሰአት ሄደ  አዳም ከሚጠበቅበት ሰአት ሲያልፍ እናት መጨነቅ ጀመሩ  ኤዶም እኔ ወጥቼ አየዋለው ብሎ ተነስቶ ወጣ .......የእናቱን ጭንቀት ላለማየት እንጂ አዳምን የመፈለግ ስሜቱ እንደድሮው አይደለም ሰልችቶታል ... የሰፈራቸው ሱቅ ጋር ቆሞ ጠበቀው  ። በመጨረሻ ከርቀት እየተወለጋገደ እና እየተራገመ ሲመጣ አየው ፣ሰክሯል  ኤዶም ተበሳጨ ፣ ይሄንን ድርጊቱን አንድጊዜ ነበር ያየው ድጋሚ በዚ መልኩ ሲያየው ደስ አላለውም አጠገቡ ሲደርስ አዳም በስካር መንፈስ ይሰድበው ጀመር "እእሺ ወንድሜ ጠላቴ ልትፈልገኝ ወጣህ  አንተ አጭበረበርከኝ በላኽኝ ! አሁን ደሞ ከኔ ምንድነው የምትፈልገው ?!"ብሎ ጮኽበት የሚያውቋቸው የሰፈር ሰዎች ቆም ቆም አሉ ። "ምንድነው የምትቀባጥረው አፍህን ዘግተህ ናወደቤት እንግባ "አለው "ማ አንተ ነህ እኔን ቤቴን የምትመራኝ ዞር በል እንዳትነካኝ ። ስልክህን ያዝ ይሄ የማይረባ ስልክህን ስልኬን ስጠኝ ከዛ ዞርበል አንተ ቀማኛ"አለው እየጮኽ "የምን ቀማኛ ነው ያምሃል እንዴ "ብሎ እየጎተተ የቤታቸው በር አደረሰው "ልቀቀኝ ሰክሯል ብለህ ነው አቅም የምታይብኝ  አፈር ነው የማስበላ ከፈለኩ አንተ ቀማኛ "አለው ደግሞ "ምንድነው ቀማኛ አፍህን አትክፈት"አለው ኤዶም "ቀማኛ ነህ ሲፈንን ቀማኽኝ ሲፈን የኔ ነበረች  "አለው ኤዶም በፍጥነት አፉን ያዘው "ዝም በል አንተ ሰው ይሰማል በስካር መንፈስ የምትናገረው ነገ ይቆጭሃል "አለው "ልቀቀኝ ሲፈንን ከኔ ወሰድካት ግን አትችልም መልሼ እወስዳታለው ታያለህ " አለው "አፍህን አትክፈት  ያንተ ያልሆነ ነገር አይደለም በቃ በግድ የሚሆን ነገር የለም ይበቃል  እንዴት በወንድምህ ትመቀኛለህ ሲፈን እንደፈለክ እንደምታረጋቸው ሴቶች አይደለችም ፣ በቃ እልህን ተው "አለው ጎትቶ እያስገባው ። "አይ ተሳስተሃል በሃይልማ እንደሚያዋጣኝ አሳየዋት አልነገረችህም ኪኪኪኪኪ ዛሬ አቅሜን አሳይቻታለው !እዚ ቤት ውስጥ !!!እዚ ቤት ውስጥ...........!!"እያለ አዳም በተደጋጋሚ ኤዶምን ለማብሸቅ ጮኽ እናትና አባት ወጥተው ጊቢውስጥ የሚጓተቱትን ልጆቿቸውን ተመለከቱና ተሯሯጡ ፣ኤዶም አዳም የተናገረው ን ሲሰማ አበደ አይለኛ ቦክስ ሰነዘረበት ......እትዬ ፅጌ በጩኽት አስነኩት ኡኡኡኡኡ ኤዶም መሰንዘሩን አላቆመም ባሰበት አዳም እራሱን ሊከላከል ሞከረ  ግን አልቻለውም መሬት ላይ ወደቀ ...አባት ዱላ ይዘው በመምጣት ኤዶምን ትንሽ ሸንቆጥ አድርገው  እንዲያቆም በቁጣ ጮሁ ፣ ኤዶም መሬት ላይ ተኝቶ የሚንፈራፈረውን ወንድሙን ረግጦት ወጥቶ ሄደ እትዬ ፅጌ እንዲመለስ ተማፀኑ ኤዶም በጣም ከፋው በንዴት ወደፊት ገሰገሰ ==== ...አይነጋ የለ ነጋ የምሽቱ ሁኔታ እትዬ ፅጌን አላስተኛ እንዳለ የአዳም አባት ደጋግመው እንደተብሰለሰሉ ፣ አዳም እንዳንኮራፋ ፣ ኤዶም ወጥቶ እንደቀረ ነጋ ፣ ጠዋት ላይ ሁሉም አርፍደው ነበር የተነሱት ፣ እትዬ ፅጌ እስኪ በጤናው እናናግረዋለን ብለው ከባላቸው ጋር በተማከሩት መሰረት አዳም እስኪነሳ ጠበቁት ኤዶም አብዲ ጋር ማደሩን ስለተረዱ አሳብ ቀሎላቸዋል ፣

Open in Telegram
Views695−24%vs avg
Forwards2
Reactions19
Comments1
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h112
4 h396
7 h464
25 h678
26 h695
  1. After 1 hour112
  2. After 6 hours464
  3. After 24 hours678
  4. Total to date695
#98281Text

🏥 የዛሬዋ ቀን ንጉሥ ማነው? ሁሌም ወደ ሥራዬ ስሄድም ሆነ ወደ ቤቴ ስመለስ፣ ከኮሪያ ሆስፒታል አጥር አጠገብ አልፋለሁ። በየቀኑ በሕመምተኞች የተሞላውን ያንን ሆስፒታል አጥር በተሻገርኩ ቁጥር፣ አንድ ሐሳብ በአእምሮዬ ይመላለሳል። ብዙ ጊዜም ያንን እያሰብኩ ቢሮዬ እደርሳለሁ። ከሆስፒታሉ አጥር ውስጥ ያለውን የሕመምና የሥቃይ ዓለም፣ እኔ ከምኖርበት ሁሉን እንደዘነጋ ከሚታየው የሁካታና የደስታ ዓለም ጋር አነጻጽራለሁ። በዚያ ቅጽበት፣ አሁን ካለሁበት ስፍራ ይልቅ ከአጥሩ ውስጥ ባለው የሕክምና አልጋ ላይ ብገኝ ኖሮ፣ ቀኔን በሙሉ «አድነኝ፣ ድረስልኝ» እያልኩ አምላኬን በምለምንበት፣ ወዳጅ ዘመዶቼንም በጭንቀት በማዋትትበት ሁኔታ ውስጥ በተገኘሁ ነበር። «ነግቶ መምሸቱን፣ ፀሐይ ወጥታ መጥለቋን፣ አየር ሞቆ መቀዝቀዙን በጤና ማየቴ ለእኔ ተራ ነገር ሆኖ ሳለ፣ ለሕሙማን ግን የየዕለት ምኞት መሆኑን እንዴት ማሰብ ተሳነኝ? አምላኬንስ እንዴት አብዝቼ ማመስገን ተውኩ?» ብዬ ራሴን እወቅሳለሁ።፣ ወዳጆቼ! የተሰጠችን እያንዳንዷ ቀን ቁጥር የማይዘልቅ በረከት የተሞላባት ናት። ጠዋት ከተኛንበት መንቃት ትልቅ በረከት ነው። ከእንቅልፍ ነቅተን በአቅማችን ያለውን መብላትና መጠጣት፣ «ደህና ዋሉ» ብለን ከቤት በሰላም መውጣት፣ በጤና ወደምንፈልግበት ስፍራ መድረስ፣ ሠርተን መመለስ፣ ፀሐይ ስትጠልቅ ማየት፣ ጠዋት ተሰናብተናቸው የወጣንባቸውን ቤተሰቦቻችንና ወዳጆቻችንን ማታ በሰላም እንደገና ማግኘት... እነዚህ ሁሉ በረከቶች አይደሉምን? እኔ በየዕለቱ ከማልፈው የሆስፒታሉ አጥር ውስጥ፣ በሕክምና አልጋዎች ላይ የተኙት ሕሙማን የሚናፍቁት ይህንኑ አይደለምን? እኛ እንደ ተራ ነገር የምንወስደውን አየር፣ እነርሱ በማሽን እርዳታ ወደ ሳንባቸው ለማስገባት ሲታገሉ አይታዩምን? ከተኙበት አልጋ ቀና ማለት ያልቻሉ፣ ቁጭ ማለትን የሚናፍቁ፤ ቁጭ ማለት የቻሉትም በእግራቸው ወዲህና ወዲያ የሚንቀሳቀሱበትን ቀን የሚጠብቁ፤ ወደ መስኮት ሄደው የውጭውን ዓለም ለማየት የሚጓጉ፤ ከሕመማቸው ሥቃይ ትንፋሽ የሚያገኙበትን ደቂቃ በጉጉት የሚጠብቁ፤ እንደልባቸው መብላት፣ መሳቅና ጮክ ብለው ማውራት የማይችሉ ብዙ ሰዎች አሉ። ከሥቃዩ ብዛት የተነሳ ተስፋ የቆረጡ፣ ሁሉን ትተው ቀናቸውን የሚቆጥሩ፣ ከሕመማቸው የተነሳ ሞትን እስከሚመኙ የደረሱ ሰዎችም አሉ። እነዚህ ሰዎች እኛ የምንመኘው ሀብት፣ እኛ ቢኖረን ብለን የምንጓጓለት ንብረት፣ ለእኛ ሕልም የሆነብን ሥራ ሊኖራቸው ይችላል። እኛ ልንደርስበት የምንሻውን ደረጃ፣ ምናልባትም ከዚያ በላይ የሆነ ስፍራ ደርሰው ይሆናል። ዝና፣ ሀብትና ክብርም ከእነርሱ ጋር ዘመናቸውን ሙሉ ኖረው ይሆናል። በዚህች ቅጽበት ግን እነርሱ የሚመኙት አንድና ብቸኛ ነገር ምን መሰላችሁ? እንደኛ ጤነኛ መሆን ብቻ! ቀኑን ማየት፣ የጠዋት ወፎችን ዝማሬ መስማት፣ የማለዳውን ቀዝቃዛ አየር መተንፈስ፣ ሥራ መሥራት፣ ከጓደኛ ጋር መጫወት፣ መሳቅ... በጤና ሆኖ ጤናማ ቀን ማሳለፍ። እኛ እጅግ የምንፈልጋቸው፣ በእነርሱ ሕይወት ውስጥ ተሟልተው የነበሩ ብዙ ነገሮች፣ በዚህ የሕመምና የጭንቅ ወቅት ለእነርሱ ምንም ፋይዳ የላቸውም። ምኞታቸው አንድ ነገር ብቻ ነው፤ እንደኛ ጤነኛ መሆን፣ ከሆስፒታሉ አጥር ውጭ በነፃነት መገኘት። እናመስግን!🙏 ጤና ስላለን፣ በእግራችን ስለምንራመድ፣ በአፋችን ምግብ ስለምንመገብ፣ ሰኞንና ማክሰኞን እያልን ቀናትን ስለምንቆጥር፣ ጊዜን ኖረንበት «እንዴት ይሮጣል?» ስለምንል፣ ስለምንስቅ፣ ስለምንተነፍስ፣ ራሳችንን ችለን የዕለት ተዕለት ፍላጎቶቻችንን ስለምናሟላ፣ በእጆቻችን ስለምንሠራ... ዘርዝረን በማንጨርሰው የፈጣሪ ስጦታ ሁሉ እናመስግን። በእጃችን ያለው ጤና ውድና ብርቅ መሆኑ የሚገለጥልን በሆስፒታል አጥር ውስጥ ስንገባ ብቻ አይሁን። እናስ፣ የዛሬዋ ቀን ንጉሥ ማነው? ታሞ ከሚማቅቅ ናጠጠ ቱጃር ይልቅ፣ በማለዳ ከላስቲክ መጠለያው በጤና እየሳቀ የሚወጣው አንድ ጎዳና አዳሪ ይበልጥ ባለጸጋ አይደለምን? ንግሥና ማለት ዛሬን በጤና መኖር መቻል ነው! ወዳጆቼ! ሀብትን ከሕመም ጋር የሚመኝ ማንም የለም። ሙሉ ጤናን ከድህነት ጋር የሚለምን ግን እጅግ ብዙ ነው። ከቤቱ ወጥቶ መመለስ ባልቻለበት ዘመን፣ እኛ በጤና ወጥተን በሰላም የምንመለስ መሆናችንን እንደ ትልቅ በረከት እናመስግን። ቀሪውን የሕይወታችንን ክፍተት መሙላት ደግሞ የፈጣሪ ሥራ ይሁን። ሕይወታችሁ በጤና፣ አንደበታችሁም በምስጋና ይሙላ! 🙏 እስቲ የዛሬዋን ቀን በሰላም ከመኝታቹ የተነሳቹ በኮመንት እናመሰግናለን በሉ🙏 ✍️ መላኩ ብርሃኑ @atronosee

Open in Telegram
Views797−13%vs avg
Forwards2
Reactions16
Comments6
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h120
6 h340
24 h712
35 h797
  1. After 1 hour120
  2. After 6 hours340
  3. After 24 hours712
  4. Total to date797
#98280Photo
Views692−24%vs avg
Forwards0
Reactions—
Comments0
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h107
6 h286
24 h612
35 h692
  1. After 1 hour107
  2. After 6 hours286
  3. After 24 hours612
  4. Total to date692
#98277Text
Views855−6%vs avg
Forwards0
Reactions15
Comments1
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
12 h460
25 h749
46 h855
  1. After 24 hours749
  2. Total to date855
#98276Text
Views832−9%vs avg
Forwards1
Reactions14
Comments1
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
12 h484
24 h713
46 h832
  1. After 24 hours713
  2. Total to date832
#98275Link preview

​​ነው ለራሴ ክብር ያጣውት ምን ያክል ብደነዝዝ ነው የሰው ቤት ሄጄ ክብሬን የማጣው ... ኤዶምስ ቢሆን ፣እራሴን መቆጣጠር የለብኝም ...ምን እያደረኩ ነው ያለውት ....ፍቅር እውር አድርጎኛል እንዴ .....ለምን ለራሴ ክብር አጣለው ..የማያባራ ወቀሳ በራሷ ላይ አካሄደች ስልኳ ያለማቋረጥ ቢጮህም ማንሳት ከበዳት ሳይለንት አደረገችው ፣ በዚ ስሜት ውስጥ ሆና ከኤዶም ጋር ካወራች እንደምትረበሽ እና ዕንባዋን እንደምትዘረግፈው ተሰምቷታል ፣ ስልኳ መጥራቱን አላቋረጠም .... === ኤዶም ከሄደበት ሲመጣ ቤት ለመግባት እንኳ አልፈለገም የሲፈን ስልክ ያለማንሳት ሊያሳብደው ደርሷል እንኳን ቤት ገብቶ ሊቀመጥ ፣ ቀርቶ እናትና አባቱን እንኳ ከመንገድ ነው የተለያቸው የተሳፈሩበት መኪና ልክ የነ ሲፈን ሰፈር መግቢያ ሲደርስ ነበር የምደርስበት ቦታ አለ ብሎ ተሰናብቷቸው የወረደው ፣አባቱ ቢደናገራቸውም እናትየው ግን ገብቷቸዋል ውይ ልጄ ቀልቡ ሁሉ ሲፈኒ ጋር ነው ፈጣሪ ይጠብቀው ብለው በልባቸው ሸኙት.... አይምሮው እረፍት አጥቷል ሆነብዬ ስልኬን ቀይሬ መስሏት ይሆን ፣በጭራሽ ግን እሱን አዳም የኔን ስልክ እስካላነሳ በምን ታውቃለች ፣ ካወቀችስ በአዳም ስልክ ስደውል አንስታ አታናግረኝም ነበር ፣ አሄሄሄ ይሄማ ነገር አለው ፣ ምን ሆናብኝ ይሆን በአባቷ ምክንያት ተናዳ ይሆን ፣ እሱ ደሞ አልፏል ፣ከዚ በኋላ ፍርዳቸውን እንደሚጠብቁ አውቃለች ፣ ኡፍፍፍፍ ሲፈን ስልክ ማንሳት ነበረብሽ ፣ .....እያለ የነሲፈን ሰፈር ተጉዞ ጊቢያቸው ጋር ደረሰ ከምሽቱ አስራሁለት ተኩል ነው ። ገና ነው አለ ለራሱ ። እናም በሩን አንኳኳ ከትንሽ ቆይታ በዋላ በሩ ተከፍቶ ዘበኛው በምን ፈለክ አይነት አፈጠጠበት ትህትና የጎደለው አስተያየቱ ቢያናድደውም ፣ በተረጋጋ መንፈስ "ይቅርታ ወይዘሪት ሲፈን ትኖራለች "አለው በጥርጣሬ አይን ከገረመመው በኋላ "አለች ..."ብሎት ተገትሮ ቀረ "እሺ ትጠራልኛለህ እባክህ በስራ ጉዳይ ላወራት ፈልጌ ነው "አለው በትህትና ። ትንሽ ያለምንም ቃል ከቆየ በዋላ ቅር እያለው እዚው ጠብቅ ብሎት በሩን በላዩ ላይ ዘግቶ ተመለሰ.... ከቆይታ በዋላ ሲፈን መጥታ ፊቱ ገጭ አለች ነጭ ቢጃማ ለብሳ በላዩላይ ፒንክ ፎጣ ጣል አድርጋለች ፀጉሯ ወደኋላ ሰብሰብ ብሎ በፀጉር ማስያዢያ ተይዟል ፊቷላይ ጭንቀት ነገር ቢነበብም ውበቷ ግን ልብን ይሰርቃል ለቁጣ ያዘጋጀው ቃላት ተበታትነው ጠፉበት ፣ጭራሽ ያልፈለጋቸው እርጥበቶች በአይኖቹ ዙሪያ ተጋረዱበት ፣ ዝምብሎ ብቻ በእይታ ሊቀጣት ሞከረ ፣ "ኤዶ ምነው እዚ ድረስ ...."ብላ መቀጠል አቃታት እሷም የቀኑ ሁኔታ አንድ በአንድ መጥተው ተደቀኑባት ፣ "እዚ ድረስ ? ሲፍ እንዴት ነው ነገሩ "አለ ና መልሶ ዝም አለ "ማለቴ ...."ብላ መልሳ ተወችው ለምን አልደወልክልኝም ማለት አጉል ነገር መነካካት ነው የሚሆንባት ፣ ለጊዜው ዝም ማለቱ እንደሚሻላት አሰበች "ሲፍ ስልኬን ቤት ረስቼው ነው የወጣሁት ምን አልባት ደውለሽ ከሆነ?! ከአዳም ጋር የሞባይል ቀፎ አችን መመሳሰሉን ታውቂ የለ ፣ ጠዋት ቸኩዬ ለካ የሱን ነው ይዤ የሄድኩት ፣ እና ይሄን ደሞ ያወኩት አክስቴ ጋር ደርሼ ስልኩን ቻርጅ ሳደርግ ነው ። እና የአዳም መሆኑን ሳውቅ ላብድ ነበር የደረስኩት ፣ ለሱ ብደውል ይጠራል አያነሳም ላንቺ ብደውል አይነሳም ፣ በጣም ነበር የተጨነኩት ...ይበልጥ ደሞ የፈራውት አብዲጋር ስደውል እሱም አጥጋቢ ምላሽ ሳይሰጠኝ ስልኩን ዘጋብኝ ፣ አንድ ቀን ከከተማ ምን ተፈጠረ ብዬ እንዴት እንደሆንኩ እኔነኝ የማውቀው !!ግን በሰላም ነው ?"አላት አይን አይኗን በስስት እያየ። ሲፈን በዝምታ አይምሮዋን አሰራች ምክንያት ፍለጋ ተሯሯጠች ...... "ሲፍ ችግር አለ "አላት እየተጠጋት "አይ ምንም ችግር የለም ፣ ደውዬልህ ነበር ደና መሆንህን ነግረኽኛል እኮ በቃ ከዛ በኋላ ደሞ እኔ በአባቴ ጉዳይ ላይ ነበርኩ "አለችው "አይ አይደለም እየነገርኩሽ እኮ ነው ፣ስልኬ ተቀያይሮ ነው "አላት እና መልሶ "ያናገረሽ አዳም ነው! እኔ የምልሽ ምን ብሎሽ ነው ?"አላት በጥርጣሬ ። "ምንም አላለኝም ደና ነኝ አክስቴ ጋር እየሄድኩ ነው ስመለስ እንገናኛለን ነው ያለኝ አንተን ተመስሎ ስላወራኝ አልጠረጠርኩም ። እና ደሞ አንተ በአዳም ስልክ እንደምትደውል በምን አውቃለው የአዳምን ስልክ እንደማላነሳ ደሞ ታውቃለህ በቃ ተረጋጋ አሁን "አለችው በጭንቀት ሳይታወቃት እየጮኽች ።ኤዶም ስላስቆጣት እየተ ፀፀተ ወደራሱ አስጠግቶ እያቀፋት "በቃ በቃ ይቅር የኔ ቆንጆ ጥፋቱ የኔ ነው በቃ የኔ ፍቅር ተረጋጊልኝ ፣ ምን ላድርግ የራቅሺኝ ሲመስለኝ ላብድ ነው የምደርሰው ባላይሽ እንኳ ድምፅሽ ያስፈልገኛል ደና ነኝ የሚለውን ድምፅሽን ስሰማ ደንነት ይሰማኛል እወድሻለው ሲፍ "አላት በስሜት ደረቱላይ ውሽቅ አለች ሳታውቀው ዕንባዋ በጉንጯ አልፎ ኮለል ሲል ተሰማት ፀፀት አቃጠላት በኤዶም እቅፍ ውስጥ ሆና አዳምን እረገመች ........ #Share እና #Reaction.. በጣም ያንሳል ሁለቱንም እያረጋቹ ቤተሰብ ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ። 👇Sebscribe YouTube link👇 https://www.youtube.com/@atronose

Open in Telegram
Views745−18%vs avg
Forwards2
Reactions31
Comments0
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h101
16 h653
25 h745
  1. After 1 hour101
  2. After 24 hours745
  3. Total to date745
#98274Text

#ባለ_ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ዘጠኝ ፡ ፡ ...ሲፈን ባለፈው  እነ ኤዶም ቤት የገጠማትን እያሰበች ብክን አለች በዛ ቀን እን ኤዶም ቤት ስትደርስ አዳም ኤዶምን በመምሰል በትህትና ተቀበላት ሶፋው ላይ እንድትቀመጥ እየጋበዘ ጠብ እርግፍ አለ ሲፈን በትላልቅ አይኖቿ ሁኔታውን ሁሉ እየተከታተለች እንደመሳቅም እንደመገረምም ብላ ታየዋለች አዳም ኤዶምን የመምሰሉ ትወና እንደተሳካለት ቆይቶ ተረዳ "ኤዶ ለምን ወዲ ወዲያ ትላለህ ቁጭ ብለህ አታጫውተኝም?"አለች ሲፈን ቀረብ አላት እና ተቀመጠ አጠገቧ አይኖቹ ውስጥ በፍቅር ተመልከተችው አዳም ልቡ መቅለጥ ጀመረ ጭንቅ አለው ሲፈን ጣቶቿን ጉንጩ ላይ በማሳረፍ "የኔ ፍቅር ሰሞኑን ተረብሼ ችላ አልኩህ አይደል ይቅርታ አድርግልኝ ግራ ገብቶኝ ነበር!" አዳም በፀጥታ የእጇን ሙቀት ያዳምጣል ሰውነቱ በአንዳች ፍላጎት መንደድ ጀምሯል አትናገርም ስትለው ጉንጩላይ የሚርመሰመሰውን ጣቷን ያዝ አደረገው አሻሸው ሲፈን ጠጋ አለችው እሱም ቀረባት ከንፈሯን አቀበለችው ተቀበላት ተስገበገበ ፡ሳማት ደጋግሞ ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ አለ አዳም እጆቹን ወደ ጡቶቿ ሰነዘራቸው ያዝ ጨመቅ አሸት ሲያደርግላት እንደማቀሰት አይነት ድምፅ አወጣች አዳም ድምፁ የባስ ተግ አደረገው ወደራሱ አሰጠግቶ በደንብ ያዛት ሳማት "ኤኤዶ እ አልቻል ኩም አአንድ ነገረ አድርግ የየኔ ፍቅር በበጣም አእወድድሃለው ..."አለች በስሜት ተውጣ አዳም ወንድሙ ይህን የመሰለ ፍቅር እንደነጠቀው ሲረዳ የባስ ተቃጠለ ከበፊቱ በበለጠ ፡ያጣድፋት ጀመር እናም ከሶፋው ላይ በሁለት እጁ ብድግ አድርጓት ወደመኝታ ክፍሉ ይዟት ገባ ሲፈን በሰመመን "ኤኤዶ ለለምን የአዳም ክክፍል ታታስገባኛለህ?"አለች አዳም ተሸወደ ደነገጠ እንዳት ነቃበት፡የመጣለትን ተናገረ "ሲፍ ስለቸኮልኩ አእሱ አልታየኝም ናናፍቀሽኛል !"አለ ከመናገሯ በፊት፡አልጋው ላይ በጀርባዋ አንጋለላት እናም ልብሱን አንድ በአንድ አውልቆ ጣለው ፡ሲፈን እርቃኑን ስታይ በፍላጎት ተንገበገበች አዳም ቀረብ ብሎ የለበሰችውን ልብስ በፍጥነት አውልቆ ጣለባት ሲፈን አፋን ከፍታ አየችው አያት አዳም እራሱን መቆጣጠር አቃተው በፍጥነት ተጣበቀባት ሲፈን ተቀበለችው "ኤዶ ፍፍቅሬሬሬ እእወድድ ሀሀለውው እእእእኤዶዶ....."ሲፈን በደስታ ቀባጠረች፡ አዳም፡በዝምታ ፡ ወደሷ ወደ ወደ ወደ.....   ስልኩ መጮህ ጀመረ ደጋግሞ እንደገና እሪ ስልኩ የሲፈን ስልክ .....  አዳም ስልኩን እንዴት ያስቁመው ፣እንደምቀኛ ቆጠረው ፣ ልቡ ሁለት ቦታ የሚመታ መሰለው ሲፈን ጋር በፍቅር ...ኤዶም ጋር በፍርሃት እላይዋላይ እየ እንደተጣበቀ ፣ ጭንቅላቱ እዚ እዛ ተደበላለቀበት ፣ ሲፈን ሞባይሏ ደጋግሞ ሲጠራ እርብሽ አለች ፣ "ቆይ ኤኤ ዶ ...ከቤት ይይሆናል"አለች በሚቆራረጥ ድምፅ "አይ ሲፍ እንዲ ባለ ሁኔታማ ማንንም ጣልቃ አናስገባ ማቆም አልችልም "አላት ትንፋሹን ለመሰብሰብ እየሞከረ "አይ ችችግር ባይኖር በአንደኛው ጥሪ ይቆም ነነበር "አለችው ። "የኔ ፍቅር አአይታይሽም ስሜቴን መግታት እንደማልችል  !ተይው ስልኩን በኋዋላ ትደውይላቸዋለሽ "አላት እየተስገበገበ ከጉዳዩ ለመድረስ ፣ሲፈን ድርቅ ሲልባት ትህትናውን ሲያጣ ፣ ትንሽ ቆጣ አለች "ኤዶ ተው በቃ የት ይሄድብሃል መርማሪው አንድ ፍንጭ አግኝቶ ይሆናል ወይም ደሞ ከቤት አንድ ነገር ተፈጥሮ ይሆናል" ብላ ገፋ አደረገችው ። አዳም ወደትክክለኛ ማንነቱ ድንገት ተመለሰ ፣ልትነሳ ስትል እዛው መልሶ አጋደማት ፣ሲፈን ደነገጠች ፣ ያልጠበቀችው ምላሽ ነበር ። በጉልበት የሚደረግ ማንኛውም ነገር የማትቀበለው ነው ይህንን ደሞ ኤዶም ጠንቅቆ ያውቃል ምነክቶት ነው በሚል አፈጠጠችበት "ምንድነው የምታካብጂው ስልክ ነው እንጂ የጮኽው ይጩሃ !አላት ከቁጥጥሩ ውጪ የሆነውን ስሜቱን በግድ ለማስታገስ አይል እየተጠቀመ ። ሲፈን ድንገት ከእንቅልፉ እንደነቃ ሰው አይልጨምራ አዳምን በመገፍተር ከስሩ ሾልካ ወጣች ፣ እናም አልጋው ላይ የምታየውን ሰው አፍጥጣ እያየች "አአንተ ማማ ነህ ኤዶ አአንተ አይደለህም !...አይ አይ አይሆንም ..."ብላ ጮኽች አዳም በመጨረሻ እንዳወቀችው ሲረዳ ፣ ያበጠው ይፈንዳ ብሎ አስገድዶ ጉዳዩን ሊጨርስ ከአልጋው በመነሳ በድንጋጤ በሩ ላይ የደረሰችውን ሲፈንን አፈፍ አድርጎ "ሲፈን አታካብጂ በቃ እኔ አዳም ነኝ በቃ ልትረጂኝ ስላልቻልሽ ነው እንዲ የሆንኩት ፣እና ምን ያክል እንደማፈቅርሽ እንድትረጂ ስሜቴን በግልፅ ላሳይሽ ስለፈለኩ ነው ። በቃ ሁሉንም በፍቅር እናርገው ጥሩ ስሜት ላይ ነበርን እኮ ፣ምን ያክል ውስጥሽ እንዳለው የተረዳውት ሰውነትሽን ስነካው እንኳ አልቀፈፈሽም ፣ነይ የኔ.... "ሲፈን አላስጨረሰችውም "እንዳትነካኝ እጮሃለው አልፈልግም አንተ አረመኔ  እንዴት እንዲ ጉድ ትሰራኛለህ አንተ ልክስክስ ነህ ውሻ ነህ ......"ብላ የመጣላትን ሁሉ ቃላት አውጥታ ተሳደበችው ። አዳም ጠጋ ብሎ ተሸክሞ አልጋው ላይ ለመጣል በማሰብ ሲንቀሳቀስ ሲፈን በጉልበቷ የአዳምን ብሽሽት በሀይል መታችው አዳም በአይለኛው አቃስቶ ተንበረከከ ሲፈን  በፍጥነት ከመኝታ ክፍሉ ልብሷንንና ስልኳን ይዛ በመውጣት  ፣ከውጪ በኩል የመኝታ ክፍሉን ቀረቀረችበት ከዛምልብሷን በፍጥነት በመልበስ ፣ ለአዳም ጩኽት ምላሽ ሳትሰጥ በድንጋጤ እየተደናበረች  ከነአዳም ቤት በሩጫ ተፈተለከች ፣ነገሩ ከምትሸከመው በላይ ነው የሆነባት ፣በየመንገዱ እራሷን እየረገመች ነበር ፣ እንዴት  እንዴት............. ============ ...ሲፈን ቤት ስትገባ እህቶቿ ተሰብስበው ሲያወሩ አገኘቻቸው ፣ እንደዛ ሁና ማንንም ማየት አልፈለገችም ነበር ፣ ወደክፍሏ ለመግባት ደሞ ሳሎኑን ማቋረጥ አለባት ፣እናቷም የጨዋታቸው ተካፋይ ስለነበሩ  አብረው ተቀምጠዋል ፣ ሲፈን እራሷን አረጋጋች ፣ ሰሞኑን በባላቸው ስራ ተጨናንቀው ከርመዋል ፣እና ትንሽ ነገር ነው የሚበቃቸው ፣ለዛ ስትል ሰላም መፍጠር አለባት ፀጉሯን ወደኋላዋ ገፋ ገፋ አድርጋ እያስተካከለች  ....ሶፋው ላይ ቁጭ አለች ሁሉም በአንዴ አይኖቻቸውን ተከሉባት ...... "ምነው እንዴ ጨዋታችሁን ቀጥሉ እንጂ"አለች ፈገግ ለማለት እየሞከረች "እኛስ ጨዋታችንን እንቀጥላለን ያንቺ አጫዋች ግን ማነበረ ዛሬ"አለቻት ሮዛ "እንዴት ምን ለማለት ነው "አለች ደንገጥ ብላ "አይ ልብስሽን እንኳ ገልብጠሽ እስክትለብሺ ድረስ የሆንሽበት ጨዋታ ...."ብላ ዝም አለች እናትና ልጆች እርስ በእርስ በፍርሃት ተያዩ "እእ አይ ...ልብ አላልኩትም ነበር  አይገርምሽም አሁን እኮ ቡቲክ ገብቼ ለብርድ የሚሆን ሹራብ ለመግዛት ስለካ ነበር ። ልጅቷ ግን የምትገርም ናት  ገልብጬ መልበሴን አልነገረችኝም አለች ሲፈን በፍጥነት የመጣላትን የፈጠራ ወሬ እየተጠቀመችበት ። "ውይ ነው እንዴ እኔ ደሞ ምን ተፈጠረ ብዬ !ታዲያ የታል ሹራቡ "አሉ እናት "ምን በጣም ሰፋኝ አላማረብኝም ተውኩት "አለች ሲፈን "ለዛ ነዋ ልብስሽን ገልብጠሽ ስትለብሺው ዝም ያለችሽ !ስላልገዛሻት "አለችና ሊያ ሳቀች ሁሉም ሳቁ ፣ ሳቅ የራቀው ቤት በሲፈን የፈጠራ ሽወዳ ደመቅ ስላለ ፣ለጊዜውም ቢሆን ሲፈን አዳም ካደረሰባት የሚያሳቅቅ በደል  አገገመች  ፣አይምሮዋ በርግጥ እረፍት አጥቷል ኤዶም ነው ክፍለ ሀገር የሄደው ፣እንዴት ስልካቸው ተቀያየረ ፣ አዳም ፍፁም እንደ ኤዶም ሆኖ ነበር የቀረበኝ በዚመጠን እንዴት ተሸወድኩ ፣ ...ብዙ ብዙ ጥያቄዎች ጭንቅላቷን ሞልተው ተንጫጩባት እራሷን ደጋግማ ወቀሰች ....እኔስ ብሆን ከመቼ ወዲ

Open in Telegram
Views741−19%vs avg
Forwards2
Reactions16
Comments0
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h97
16 h632
25 h741
  1. After 1 hour97
  2. After 24 hours741
  3. Total to date741
#98273Photo

🌱 ተስፋ እስካለ ድረስ... ✨ 📍 በሰዎች ዘንድ ተስፋ የሌለን ብንመስልም፣ ዋናው ነገር በፈጣሪ ዘንድ ያለን ተስፋ ነው። ሕይወት ጠመዝማዛ መንገድ ብትሆንም፣ ውብና በተስፋ የተሞላች ናት። 💡 በዚህ ዓለም ሁሉም ነገር አበቃ፣ ተፈጸመ ብለን በምናስብበት ቅጽበት እንኳን፣ የተሻለ አጋጣሚ ከፊታችን ሊጠብቀን ይችላል። የምናውቀውና የተለመደው በር ተዘግቶብን ቢመስልም፣ ሌላ በር በድንገት ሊከፈት ይችላል። ዙሪያችን ደረቅ በረሃ ቢመስልም፣ ከዚያ ባሻገር የለመለመ መስክ ሊኖር ይችላል። 📍 ሕይወት እንደ ሳንቲም ናት፤ ሁለት ገጽታዎች አሏት። ተቃራኒ ቢሆኑም እርስ በርሳቸው የማይነጣጠሉ ገጽታዎች። በሕይወት እስካለን ድረስ ከአንዱ ገጽታ ብቻ ተለይተን መኖር አንችልም። እያንዳንዱ ሁኔታ ተቃራኒ ገጽታ አለው። ሳንቲም ያለ ጀርባው ገጽታ ሙሉ እንደማይሆን ሁሉ፣ ያለ ሐዘን ደስታን፣ ያለ ሞት ሕይወትን፣ ያለ ለቅሶ ሳቅን፣ ያለ ድህነት ሀብትንj በሙሉ ልንረዳ አንችልም። ስለዚህ ሕይወትን ከነሕብረ ቀለሟ መቀበል አለብን። 💡 እድል ፊቷን ያዞረችብን በመሰለን ጊዜ እንኳን፣ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ በትጋት መጓዝን እንምረጥ። ትጋት የተስፋ ልጅ ናት፤ ተስፋ ደግሞ በእኛና በፈጣሪ መካከል ያለው የእምነት ድልድይ ነው። 📖 ቃሉም እንዲህ ይላል፦ «ዛፍ ቢቆረጥ ደግሞ ያቆጠቁጥ ዘንድ፣ ቅርንጫፉም እንዳያልቅ ተስፋ አለው።» — ኢዮብ 14፥7 ━━━━━━━━━━━━━━ 🌿 አስታውስ! የተዘጋ በር የጉዞህ መጨረሻ ላይሆን ይችላል። የደረቀ ዛፍም አዲስ ቡቃያ ሊያወጣ ይችላል። የዛሬ ሐዘንህ የነገ ደስታህን አይከለክልም። ተስፋህን አታጥፋ፤ ፈጣሪ አንተ ያላየኸውን መንገድ ሊከፍትልህ ይችላል! 🤲 ✍️ አለማየሁ ዋሴ @Atronosee

Open in Telegram
Views746−18%vs avg
Forwards2
Reactions11
Comments0
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
9 h443
25 h746
  1. After 24 hours746
  2. Total to date746

All posts

Connections