የፀባቸው መነሻ ከአዳም ማታ ሲለፈልፍ እንደተረዱት ሲፈን ናት ይህን በመረዳታቸው ክፉኛ አዝነዋል ፣መንትዮች ፍላጎታቸው ይመሳሰላል ሲባል ሰምተዋል በነአዳም ላይ ግን ከመልክ መመሳሰል ውጪ እስከዛሬ ፍፁም የሚያመሳስል ነገር አላዩም አዳም አስቸጋሪና ጉልበተኛ የፈለገውን ከማድረግ የማይመለስ እንቢተኛ ነው ።ኤዶም ሰው አክባሪ ብዙም የማያወራ ቤተሰቦቹን አክባሪ ከቃላቸው የማይወጣ ትሁት ፣ ከስራ መልስ ወደቤት ፣ከቤት ወደስራ ከማለት በስተቀር ምንም አይነት አመል የሌለበት ነው ። እስከዛሬም አዳም የተለያዩ ሴቶችን በፍቅር ሰበብ እየቀረበ ሲያሳዝን የቆየ ነው ፣እትዬ ፅጌ እንኳ የሚያውቋት ቤት ድረስ የምትመጣ ምስኪን ልጅ ነበረች ለምናው ለምናው ፍቃደኛ ሳይሆንላት ሲቀር ፣ እናትየው ያውቋት ስለነበር ቤት ድረስ በመምጣት እንዲያማልዷት ተማፅና ነበር ፣ አዳም ግን የፈለገውን ቀድሞ አግኝቷልና ወደሌላዋ ለመሻገር ስለፈለገ ፣ የሷነገር እንደሰለቸው ያለምንም አዘኔታ በመንገር ፣ እርሺኝ ላይሽ አልፈልግም ብሎ አቃሎ አባሯታል ፣ እትዬ ፅጌ ከነስሟ ያውቋት ስለነበር 'የእየሩስ ግፍ አንድ ቀን ያገኝሃል' ብለውትም ነበር። ምናልባትም የግፉን ክፍያ በሲፈን እያገኘም ይሆናል.........
===-==-==-
አዳም እንደተነሳ እያዛጋ በድብርት እየተንገላታ ሳሎን ገባ ፣ እናም ለመታጠብ ወደ አስቦ መታጠቢያ ክፍል ሊያመራ ሲል ። አባት
"አንታይህም ደና አደራችሁም አይባልም "አሉት
"ውይ አባዬ ራሴን አሞኛል አይኔን እንኳ መክፈት አልቻልኩም "አለ
"አይንህን ያጥፋው ፣ለነገሩ አጥፍቶልሃል !"ብለው ቱግ አሉ እትዬ ፅጌ ደነገጡ ባላቸው እንዲ አምርረው ሲራገሙ ሰምተው አያውቁም፣ ውስጣቸው ተላወሰ ፣ ለአዳም አዘኑ የአዳም ፊት አባብጧል በኤዶም ቦክስ ፣ክፉኛ እንዳገኘው ያወቁት አሁን ሲያዩት ነው ። እሱ ሰለማታው ሁኔታ ብዙም ያስታወሰ አይመስልም
"ወይኔ ልጄ እስኪ ፊትህ ኧረ ምን ጉድ ነው ፣እንዴት እንዴት ነው ያገኘው በል "ብለው ወደባላቸው ዞሩ
"እሰይ ጥሩ አደረገ ሁሌ እሱን ብቻ ማን ጉልበተኛ አደረገው ይሄ ክፉ አሉ ከንዴታቸው ሳይበርዱ
"እንዴ አባዬ ምን ሆነሃል ለምንድነው የምትሰድበኝ "አለ አዳም ቆጣ ብሎ
"ምክንያቱም እኩይ ስለሆንክ ፣ባንተ የተነሳ ከቤት ወጥቶ የማያውቅ ልጅ ወጥቶ አደረ እንዴት አንተ በወንድምህ ሴት ትቀናለህ ፣ አንተ ባለጌ ! ያንተን ሴት ተኛዋት ብለህ ወንድምህን ታሳብደዋለህ እንዴት ስርሃት ብታጣ ነው ! የስከዛሬው ጥጋብህ አልበቃ ብሎ ዛሬ ደሞ በብቸኛ ወንድምህ ላይ ተነሳህ ፣ "አሉት ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው
"ምን እኔ ......"ብሎ አዳም በአንድ እጁ ጭንቅላቱን ይዞ የማታውን ሁኔታውን ለማስታወስ ሞከረ
"ኧረ ባክህን ተው እንጂ አይደለም መነጋገር ያለብን የአዳም አባት ሁለቱም ልጆቻችን ናቸው ፣ማስማማት ነው ያለብን እባክህ ተረጋጋ"አሉ እትዬ ፅጌ
አዳም በፍጥነት መፀዳጃ ቤት ሄዶ እራሱን አየ ፣ፊቱ አባብጧል አይኑንን የከለለው ለካ እብጠቱ ነው ። በጣም ተናደደ ኤዶም ሰክሮ ስላገኘው እንዳጠቃው አይነት ስሜት ተሰማው ። ፊቱን ተጣጥቦ ልብሱን ቀያይሮ የሹራብ ኮፍያና መነፅር አድርጎ እየተጣደፈ ወጣ። እልህኝነቱ አገረሸበት ፣ኤዶምን ፊለፊቱ ቢያገኘው የሚለቀው አይመስልም .....እትዬ ፅጌ ተከትለውት ቢሮጡም አልደረሱበትም ፣ አባት ተይው ቢያገኘው ለሱ የሚያንስ ጉልበት ያለው ይመስልሻል ዝም ያለሰው አይነሳ ብቻ "አሉ እትዬ ፅጌ ዛሬ የባላቸው ማምረር ደስ አላላቸውም ሁለቱንም ከመገሰፅ ይልቅ ለአንዱ ማዳላት ምንድነው ብለው ተቀየሙ ......
========
ኤዶም አብዲ ጋር የሄደው ንዴቱ ሲበርድለት ነበር ። እናቱንም ማሳዘን ስላልፈለገ ነው አብዲን ደውሎ እኔ ጋር ነው እንዲል ያደረገው ፣ ከአብዲጋር ሰለሆነው ሁሉ ሲነግረው አዲስ አልሆነበትም ፣ ምክንያቱም አብዲም ከአዳም ጋር ብዙ ተጨቃጭቆበታል ፣ አይሆንም ተው ብሎ አዳምን መክሮታል ግን አዳም ሞገደኛ ሆነበት በቀላሉ የሚያምን አይነት ሰው አይደለም ፣ የትላንትናው ግን በጣም መብዛቱን እሱም አውቋል በዚም ተናግሮት ተጣልተው ነው የተለያዩት ። ኤዶምን ለማብሸቅ ግን በዚ መጠን ይናገራል ብሎ አልገመተም ፣ አዳም ላይ ተናደደ ፣ ይበልጥ ግን ያሳሰበው ኤዶም ሲፈን እንዴት አልነገረችኝም ፣ደጋግሜ ጠይቄያት ነበረ መከፋቷን አይቼ ። ብሎ ሲፈንን ካሁን በዋላ አላናግራትም ፣እኔላይ እያሾፈች ነው ምናልባትም ወንድሜን ትወደው ይሆናል ብሎ ሲያመር ነው። ኤዶምን ለማሳመን ብዙ አወራ ብትፈልገው ማን ያግዳታል ያንተን ስልክ ነው ተጠቅሞ ያሞኛት ፣ ነገርግን እሱ እንዳለው አይደለም አልነካትም ፣ ብሎ ብዙ አስረዳው ኤዶም ንዴቱ አልበርድ አለው የተከዳ መሰለው
ከነ አብዲ ቤት ወጥቶ በቀጥታ እግሩ እንደመራው ተጓዘ ብስጭቱ እንዲተወው ፈጣሪ እንዲያረጋጋው ለመነ ..... እንዲ እየተጓዘ ሳለ ፣አንዲት ሴት እየሮጠች ወደሱ ስትመጣ አያት ፣ እራሱን አዘጋጀ ሊከላከላት ፣ፊቷላይ የደሰታ ስሜት ይነበባል የናፈቁትን ሰው ድንገት የገኙ አይነት ነው አመጣጧ .....
"አዳም ወይኔ .....ፈጣሪዬ......አዳም ሰሎሜ እኮነኝ አላስታወስከኝም ...አዳምዬዬ..."ወገቡን ይዛ በደስታ ተፍለቀለቀች
"ቆይ ቆይ ....."አለ ኤዶም እራሱን ለማስለቀቅ እየታገለ ..
#Share እና #Reaction..❤️ 👍
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose