AI-чатbetaКабинет

Посты канала አትሮኖስ

сначала новые

#98284Текст
Просмотры641−30%к среднему
Пересылки5
Реакции22
Комментарии1
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч64
2 ч174
3 ч197
6 ч217
22 ч641
  1. Через 1 час174
  2. Через 6 часов217
  3. Через 24 часа641
  4. Всего сейчас641
#98283Текст

​​የፀባቸው መነሻ ከአዳም ማታ ሲለፈልፍ እንደተረዱት ሲፈን ናት ይህን በመረዳታቸው ክፉኛ አዝነዋል ፣መንትዮች ፍላጎታቸው ይመሳሰላል ሲባል ሰምተዋል በነአዳም ላይ ግን ከመልክ መመሳሰል ውጪ እስከዛሬ ፍፁም የሚያመሳስል ነገር አላዩም አዳም አስቸጋሪና ጉልበተኛ የፈለገውን ከማድረግ የማይመለስ እንቢተኛ ነው ።ኤዶም ሰው አክባሪ ብዙም የማያወራ ቤተሰቦቹን አክባሪ ከቃላቸው የማይወጣ ትሁት ፣ ከስራ መልስ ወደቤት ፣ከቤት ወደስራ ከማለት በስተቀር ምንም አይነት አመል የሌለበት ነው ።  እስከዛሬም አዳም የተለያዩ ሴቶችን በፍቅር ሰበብ እየቀረበ ሲያሳዝን የቆየ ነው ፣እትዬ ፅጌ እንኳ የሚያውቋት ቤት ድረስ የምትመጣ ምስኪን ልጅ ነበረች ለምናው ለምናው ፍቃደኛ ሳይሆንላት ሲቀር ፣ እናትየው ያውቋት ስለነበር ቤት ድረስ በመምጣት እንዲያማልዷት ተማፅና ነበር ፣ አዳም ግን የፈለገውን ቀድሞ አግኝቷልና ወደሌላዋ ለመሻገር ስለፈለገ ፣ የሷነገር እንደሰለቸው  ያለምንም አዘኔታ በመንገር ፣ እርሺኝ ላይሽ አልፈልግም ብሎ አቃሎ አባሯታል ፣ እትዬ ፅጌ ከነስሟ ያውቋት ስለነበር 'የእየሩስ ግፍ አንድ ቀን ያገኝሃል' ብለውትም ነበር። ምናልባትም የግፉን ክፍያ በሲፈን እያገኘም ይሆናል......... ===-==-==- አዳም እንደተነሳ እያዛጋ በድብርት እየተንገላታ ሳሎን ገባ ፣ እናም ለመታጠብ ወደ አስቦ መታጠቢያ ክፍል ሊያመራ ሲል ። አባት "አንታይህም ደና አደራችሁም አይባልም "አሉት "ውይ አባዬ  ራሴን አሞኛል አይኔን እንኳ መክፈት አልቻልኩም "አለ "አይንህን ያጥፋው ፣ለነገሩ አጥፍቶልሃል !"ብለው ቱግ አሉ እትዬ ፅጌ ደነገጡ ባላቸው እንዲ አምርረው ሲራገሙ ሰምተው አያውቁም፣ ውስጣቸው ተላወሰ ፣ ለአዳም አዘኑ የአዳም ፊት አባብጧል በኤዶም ቦክስ ፣ክፉኛ እንዳገኘው ያወቁት አሁን ሲያዩት ነው ። እሱ ሰለማታው ሁኔታ ብዙም ያስታወሰ አይመስልም "ወይኔ ልጄ እስኪ ፊትህ ኧረ ምን ጉድ ነው ፣እንዴት እንዴት ነው ያገኘው በል "ብለው ወደባላቸው ዞሩ "እሰይ ጥሩ አደረገ ሁሌ እሱን ብቻ ማን ጉልበተኛ አደረገው ይሄ ክፉ አሉ ከንዴታቸው ሳይበርዱ "እንዴ አባዬ ምን ሆነሃል ለምንድነው የምትሰድበኝ "አለ አዳም ቆጣ ብሎ "ምክንያቱም እኩይ ስለሆንክ ፣ባንተ የተነሳ ከቤት ወጥቶ የማያውቅ ልጅ ወጥቶ አደረ  እንዴት አንተ በወንድምህ ሴት ትቀናለህ ፣ አንተ ባለጌ ! ያንተን ሴት ተኛዋት ብለህ ወንድምህን ታሳብደዋለህ እንዴት ስርሃት ብታጣ ነው ! የስከዛሬው ጥጋብህ አልበቃ ብሎ ዛሬ ደሞ በብቸኛ ወንድምህ ላይ ተነሳህ ፣ "አሉት ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው "ምን እኔ ......"ብሎ አዳም በአንድ እጁ ጭንቅላቱን ይዞ የማታውን ሁኔታውን ለማስታወስ ሞከረ "ኧረ ባክህን ተው እንጂ አይደለም መነጋገር ያለብን የአዳም አባት ሁለቱም ልጆቻችን ናቸው ፣ማስማማት ነው ያለብን እባክህ ተረጋጋ"አሉ እትዬ ፅጌ አዳም በፍጥነት መፀዳጃ ቤት ሄዶ እራሱን አየ ፣ፊቱ አባብጧል አይኑንን የከለለው ለካ እብጠቱ ነው ። በጣም ተናደደ ኤዶም ሰክሮ ስላገኘው እንዳጠቃው አይነት ስሜት ተሰማው ። ፊቱን ተጣጥቦ ልብሱን ቀያይሮ የሹራብ ኮፍያና መነፅር አድርጎ እየተጣደፈ ወጣ። እልህኝነቱ አገረሸበት ፣ኤዶምን ፊለፊቱ ቢያገኘው የሚለቀው አይመስልም .....እትዬ ፅጌ ተከትለውት ቢሮጡም አልደረሱበትም ፣ አባት ተይው ቢያገኘው ለሱ የሚያንስ ጉልበት ያለው ይመስልሻል ዝም ያለሰው አይነሳ ብቻ "አሉ እትዬ ፅጌ ዛሬ የባላቸው ማምረር ደስ አላላቸውም  ሁለቱንም ከመገሰፅ ይልቅ ለአንዱ ማዳላት ምንድነው  ብለው ተቀየሙ ...... ======== ኤዶም አብዲ ጋር የሄደው ንዴቱ ሲበርድለት ነበር ። እናቱንም ማሳዘን ስላልፈለገ ነው አብዲን ደውሎ እኔ ጋር ነው እንዲል ያደረገው ፣ ከአብዲጋር ሰለሆነው ሁሉ ሲነግረው አዲስ አልሆነበትም ፣ ምክንያቱም አብዲም ከአዳም ጋር ብዙ ተጨቃጭቆበታል ፣ አይሆንም ተው ብሎ አዳምን መክሮታል ግን አዳም ሞገደኛ ሆነበት በቀላሉ የሚያምን አይነት ሰው አይደለም ፣ የትላንትናው ግን በጣም መብዛቱን እሱም አውቋል በዚም ተናግሮት ተጣልተው ነው  የተለያዩት ። ኤዶምን ለማብሸቅ ግን በዚ መጠን ይናገራል ብሎ አልገመተም ፣ አዳም ላይ ተናደደ ፣ ይበልጥ ግን ያሳሰበው ኤዶም ሲፈን እንዴት አልነገረችኝም ፣ደጋግሜ ጠይቄያት ነበረ መከፋቷን አይቼ ። ብሎ ሲፈንን ካሁን በዋላ አላናግራትም ፣እኔላይ እያሾፈች ነው ምናልባትም ወንድሜን ትወደው ይሆናል ብሎ ሲያመር ነው።  ኤዶምን ለማሳመን ብዙ አወራ  ብትፈልገው ማን ያግዳታል ያንተን ስልክ ነው ተጠቅሞ ያሞኛት ፣ ነገርግን እሱ እንዳለው አይደለም አልነካትም ፣ ብሎ ብዙ አስረዳው  ኤዶም ንዴቱ አልበርድ አለው የተከዳ መሰለው  ከነ አብዲ ቤት ወጥቶ በቀጥታ እግሩ እንደመራው ተጓዘ ብስጭቱ እንዲተወው ፈጣሪ እንዲያረጋጋው ለመነ .....  እንዲ እየተጓዘ ሳለ ፣አንዲት ሴት እየሮጠች ወደሱ ስትመጣ አያት ፣ እራሱን አዘጋጀ ሊከላከላት ፣ፊቷላይ የደሰታ ስሜት ይነበባል የናፈቁትን ሰው ድንገት የገኙ አይነት ነው አመጣጧ ..... "አዳም ወይኔ .....ፈጣሪዬ......አዳም  ሰሎሜ እኮነኝ አላስታወስከኝም ...አዳምዬዬ..."ወገቡን ይዛ በደስታ ተፍለቀለቀች "ቆይ ቆይ ....."አለ ኤዶም እራሱን ለማስለቀቅ እየታገለ  .. #Share እና #Reaction..❤️ 👍 ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ። 👇Sebscribe YouTube link👇 https://www.youtube.com/@atronose

Открыть в Telegram
Просмотры720−21%к среднему
Пересылки2
Реакции30
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч113
4 ч389
7 ч463
25 ч703
26 ч720
  1. Через 1 час113
  2. Через 6 часов463
  3. Через 24 часа703
  4. Всего сейчас720
#98282Текст

#ባለ_ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ ፡ ፡ ...ሲፈን በኤዶም እቅፍ ውስጥ ሙቀት ተሰማት የተለየ መረጋጋት የተለየ ሰላም ተሰማት ከነገሮች ሁሉ ሰውሮ የሚያስቀራት የሚከላከልላት እቅፍ ጠንካራ እቅፍ  ለአክስቱ ዝግጅት ሲባል የተቀባው ሽቶ ጠረኑ ተመቻት ያለችበትን ቦታ ለጊዜው አስረሳት ኤዶም ከቁጣ በርዶ  ሲፈንን ደረቱ ላይ እንደለጠፈ አፍንጫውን በፀጉሯ መሃል እያርመሰመሰ  ሽታዋን ሳበ ። የፍቅሩን ሐይል የሚገልፅበት መንገድ እያነሰበት ተቸገረ ለሲፈን የሚበቃት ምን ይሆን  .... "ኤዱ በቃ  !እንዴ ምን እያደረከኝ እንደሆን ተመልከት  "ብላ በኤዶም ዙሪያ የጠመጠመቻቸውን እጆቿን አላቃ እራቅ አለችው ። ኤዶም በደከመ እይታ አስተዋላት  ፈራች ደሞ ሊጀምረኝ ነው ይሄ ሽንፈቴ ብላ ከራሷጋር ተነጋገረች "ኤዶም በቃ ወደቤት ሂድ ማሚ ድንገት ልትወጣ ትችላለች ፣ ነገ እንገናኛለን "አለችው "እሺ ግን እኮ ልክ አይደለሽም ፊትሽ ላይ የማየው ነገር ይረብሻል ፣ አዳም በኔ ስልክ ደውሎልሽ ነበር ፣ነገርግን በትክክል ምን እንዳለሽ አላውቅም ፣ ምክንያቱም በግልፅ አልነገርሽኝም ፣  ወንድሜ አስቀይሞሽ ነው ?"አላት በጥርጣሬ "ልትሰማኝ የፈለክ አልመሰለኝም ምንድነው ። እንዲ ያሳሰበህ ? አዳም ልክ ያልሆነ ነገር ቢናገረኝስ ምን አዲስ ነገር አለ ፣ትክክል ተናግሮ ያውቃል እንዴ ?"ብላ ቆጣ አለች "እሺ በቃ አትናደጂብኝ  እሄዳለው አንዴ የመንገዴን  ብቻ "ብሏት ፈገግ አለ ።ሲፈን ፈገግ ለማለት እየሞከረች "መቼም አትሸነፍም አይደል "ብላ በመጠጋት ከንፈሩን ሳም አደረገችው በስሱ.... "በስሱ ደረስ መለስ ይሁን ጣፋጭ ነው "ብሎ ሳቀ ። እናም እጇን ያዝ አድርጎ በመሳም ተሰናበታት ። ሲፈን በዚመንገድ ከኤዶም ጋር ከተለያየች በኋላ ወደ ጊቢዋ ስትመለስ ሊያን ቆማ ስታይ እንደነበር አስተዋለች። "ምንድነው ተደብቀሽ ስታይኝ ነበር?"አለቻት እንደማፈርም እንደመቆጣትም ብላ "በጣም ቆንጆ ነው!"አለች እየሳቀች "ስርአት ይኑርሽ ሂጂ ግቢ በቃ "አለቻት.. ሊያ እየሳቀች ወደሳሎን ያየችውን ለእህቶቿ ልታጋራ ፈጠነች ሲፈን ስለገባት ልታስቆማት ተከተለቻት ግን ስትደርስ በከፊል አውርታ ጨርሳለች ። እህቶቿ ምን አሳፈረሽ በሚል ሳቁ ።ሲፈን ሳትቀመጥ ወደ ክፍሏ ገባች ፣የእህቶቿን ሁኔታ ቶሎ እረሳች ሃሳቧ በሙሉ ኤዶም ጋር እና አዳም ጋር ሄደ ፣  ወደፊት ምን ሊፈጠር ይችላል የሚለው አሳብ ጭንቅላቷን አዞረው ፣ አዳም በዚ ሁኔታው ከቀጠለ አብዶ ያሳብዳታል ፣  ከእነሱ አካባቢ እንዳትርቅ ትታ የማትተወው የኤዶም ፍቅር አለባት  ምርጫዋ ከባድ ነው ።  ወይ በድፍረት  ከኤዶም ጋር በመቀጠል በወንድማማቾች መሃከል መግባት አለበለዚያ ፣ ኤዶምን በማስቀየም ከሁለቱም መሃል እራሷን በማውጣት ፣ ከነሱ መሰወር !!...ግን እንዴት ፍቅሯስ ኤዶምስ የልቧ ጥያቄስ ...........? ====== ኤዶም ቤት ሲገባ ቡና ቀራርቦ እራት ተዘገጃጅቶ  እሱንና ወንድሙን ጥበቃ ላይ ነበር ። እናትና አባት  መትዮቹን እኩል ቤት ሲገቡ አብረዋቸው ቢጨዋወቱ ደስ ይላቸዋል ነገር ግን ሁሌም በአዳም በኩል አይሳካም ፣ የነሱ አጫዋች ትህዛዝ አክባሪ ኤዶም ነው።  ሰብሰብ ብለው መጫወቱ በፊት ቀረ አዳም ከመጎርመሱ በፊት ። ከጎረመሱ በዋላ አዳም  ተቀይሯል ከወንድሙ ጋር በመልክ ብቻ እንጂ በፀባይ ተራርቀዋል አዳም ደጅ ደጁን ነው የሚወደው ብዙ ጓደኞች አሉት የሴትም የወንድም የተለያዩ ፍቅረኞችም ነበሩት ብዙ ሴቶች ላይ በፍቅር መቀለድ ደስ ይለውም ነበር  ። በአንፃሩ ኤዶም የናትና የአባቱ ታዛዥ ልጅ ነው  እስካሁንም ድረስ እነሱ እንዳይቀየሙ ሁሉንም እሺ ከማለት ሌላ ቃል አይወጣውም ።  እናት ኤዶምን ሲያዩ ደስ አላቸው ሲቆይባቸው ተጨንቀው ነበር ። እሱን ሲያዩ ምግቡንም ቀረብ ቀረብ አድርገው ። እየበሉ መጨዋወት ጀመሩ ። አዳም ስላስለመዳቸው ያው ሲመጣ ይምጣ ብለው ነው የሚያልፉት ፣  እየተጫወቱ ስለነበራቸው የክፍለሃገሩ ቆይታ ሲያነሱ ሲጥሉ  ሰአት ሄደ  አዳም ከሚጠበቅበት ሰአት ሲያልፍ እናት መጨነቅ ጀመሩ  ኤዶም እኔ ወጥቼ አየዋለው ብሎ ተነስቶ ወጣ .......የእናቱን ጭንቀት ላለማየት እንጂ አዳምን የመፈለግ ስሜቱ እንደድሮው አይደለም ሰልችቶታል ... የሰፈራቸው ሱቅ ጋር ቆሞ ጠበቀው  ። በመጨረሻ ከርቀት እየተወለጋገደ እና እየተራገመ ሲመጣ አየው ፣ሰክሯል  ኤዶም ተበሳጨ ፣ ይሄንን ድርጊቱን አንድጊዜ ነበር ያየው ድጋሚ በዚ መልኩ ሲያየው ደስ አላለውም አጠገቡ ሲደርስ አዳም በስካር መንፈስ ይሰድበው ጀመር "እእሺ ወንድሜ ጠላቴ ልትፈልገኝ ወጣህ  አንተ አጭበረበርከኝ በላኽኝ ! አሁን ደሞ ከኔ ምንድነው የምትፈልገው ?!"ብሎ ጮኽበት የሚያውቋቸው የሰፈር ሰዎች ቆም ቆም አሉ ። "ምንድነው የምትቀባጥረው አፍህን ዘግተህ ናወደቤት እንግባ "አለው "ማ አንተ ነህ እኔን ቤቴን የምትመራኝ ዞር በል እንዳትነካኝ ። ስልክህን ያዝ ይሄ የማይረባ ስልክህን ስልኬን ስጠኝ ከዛ ዞርበል አንተ ቀማኛ"አለው እየጮኽ "የምን ቀማኛ ነው ያምሃል እንዴ "ብሎ እየጎተተ የቤታቸው በር አደረሰው "ልቀቀኝ ሰክሯል ብለህ ነው አቅም የምታይብኝ  አፈር ነው የማስበላ ከፈለኩ አንተ ቀማኛ "አለው ደግሞ "ምንድነው ቀማኛ አፍህን አትክፈት"አለው ኤዶም "ቀማኛ ነህ ሲፈንን ቀማኽኝ ሲፈን የኔ ነበረች  "አለው ኤዶም በፍጥነት አፉን ያዘው "ዝም በል አንተ ሰው ይሰማል በስካር መንፈስ የምትናገረው ነገ ይቆጭሃል "አለው "ልቀቀኝ ሲፈንን ከኔ ወሰድካት ግን አትችልም መልሼ እወስዳታለው ታያለህ " አለው "አፍህን አትክፈት  ያንተ ያልሆነ ነገር አይደለም በቃ በግድ የሚሆን ነገር የለም ይበቃል  እንዴት በወንድምህ ትመቀኛለህ ሲፈን እንደፈለክ እንደምታረጋቸው ሴቶች አይደለችም ፣ በቃ እልህን ተው "አለው ጎትቶ እያስገባው ። "አይ ተሳስተሃል በሃይልማ እንደሚያዋጣኝ አሳየዋት አልነገረችህም ኪኪኪኪኪ ዛሬ አቅሜን አሳይቻታለው !እዚ ቤት ውስጥ !!!እዚ ቤት ውስጥ...........!!"እያለ አዳም በተደጋጋሚ ኤዶምን ለማብሸቅ ጮኽ እናትና አባት ወጥተው ጊቢውስጥ የሚጓተቱትን ልጆቿቸውን ተመለከቱና ተሯሯጡ ፣ኤዶም አዳም የተናገረው ን ሲሰማ አበደ አይለኛ ቦክስ ሰነዘረበት ......እትዬ ፅጌ በጩኽት አስነኩት ኡኡኡኡኡ ኤዶም መሰንዘሩን አላቆመም ባሰበት አዳም እራሱን ሊከላከል ሞከረ  ግን አልቻለውም መሬት ላይ ወደቀ ...አባት ዱላ ይዘው በመምጣት ኤዶምን ትንሽ ሸንቆጥ አድርገው  እንዲያቆም በቁጣ ጮሁ ፣ ኤዶም መሬት ላይ ተኝቶ የሚንፈራፈረውን ወንድሙን ረግጦት ወጥቶ ሄደ እትዬ ፅጌ እንዲመለስ ተማፀኑ ኤዶም በጣም ከፋው በንዴት ወደፊት ገሰገሰ ==== ...አይነጋ የለ ነጋ የምሽቱ ሁኔታ እትዬ ፅጌን አላስተኛ እንዳለ የአዳም አባት ደጋግመው እንደተብሰለሰሉ ፣ አዳም እንዳንኮራፋ ፣ ኤዶም ወጥቶ እንደቀረ ነጋ ፣ ጠዋት ላይ ሁሉም አርፍደው ነበር የተነሱት ፣ እትዬ ፅጌ እስኪ በጤናው እናናግረዋለን ብለው ከባላቸው ጋር በተማከሩት መሰረት አዳም እስኪነሳ ጠበቁት ኤዶም አብዲ ጋር ማደሩን ስለተረዱ አሳብ ቀሎላቸዋል ፣

Открыть в Telegram
Просмотры695−24%к среднему
Пересылки2
Реакции19
Комментарии1
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч112
4 ч396
7 ч464
25 ч678
26 ч695
  1. Через 1 час112
  2. Через 6 часов464
  3. Через 24 часа678
  4. Всего сейчас695
#98281Текст

🏥 የዛሬዋ ቀን ንጉሥ ማነው? ሁሌም ወደ ሥራዬ ስሄድም ሆነ ወደ ቤቴ ስመለስ፣ ከኮሪያ ሆስፒታል አጥር አጠገብ አልፋለሁ። በየቀኑ በሕመምተኞች የተሞላውን ያንን ሆስፒታል አጥር በተሻገርኩ ቁጥር፣ አንድ ሐሳብ በአእምሮዬ ይመላለሳል። ብዙ ጊዜም ያንን እያሰብኩ ቢሮዬ እደርሳለሁ። ከሆስፒታሉ አጥር ውስጥ ያለውን የሕመምና የሥቃይ ዓለም፣ እኔ ከምኖርበት ሁሉን እንደዘነጋ ከሚታየው የሁካታና የደስታ ዓለም ጋር አነጻጽራለሁ። በዚያ ቅጽበት፣ አሁን ካለሁበት ስፍራ ይልቅ ከአጥሩ ውስጥ ባለው የሕክምና አልጋ ላይ ብገኝ ኖሮ፣ ቀኔን በሙሉ «አድነኝ፣ ድረስልኝ» እያልኩ አምላኬን በምለምንበት፣ ወዳጅ ዘመዶቼንም በጭንቀት በማዋትትበት ሁኔታ ውስጥ በተገኘሁ ነበር። «ነግቶ መምሸቱን፣ ፀሐይ ወጥታ መጥለቋን፣ አየር ሞቆ መቀዝቀዙን በጤና ማየቴ ለእኔ ተራ ነገር ሆኖ ሳለ፣ ለሕሙማን ግን የየዕለት ምኞት መሆኑን እንዴት ማሰብ ተሳነኝ? አምላኬንስ እንዴት አብዝቼ ማመስገን ተውኩ?» ብዬ ራሴን እወቅሳለሁ።፣ ወዳጆቼ! የተሰጠችን እያንዳንዷ ቀን ቁጥር የማይዘልቅ በረከት የተሞላባት ናት። ጠዋት ከተኛንበት መንቃት ትልቅ በረከት ነው። ከእንቅልፍ ነቅተን በአቅማችን ያለውን መብላትና መጠጣት፣ «ደህና ዋሉ» ብለን ከቤት በሰላም መውጣት፣ በጤና ወደምንፈልግበት ስፍራ መድረስ፣ ሠርተን መመለስ፣ ፀሐይ ስትጠልቅ ማየት፣ ጠዋት ተሰናብተናቸው የወጣንባቸውን ቤተሰቦቻችንና ወዳጆቻችንን ማታ በሰላም እንደገና ማግኘት... እነዚህ ሁሉ በረከቶች አይደሉምን? እኔ በየዕለቱ ከማልፈው የሆስፒታሉ አጥር ውስጥ፣ በሕክምና አልጋዎች ላይ የተኙት ሕሙማን የሚናፍቁት ይህንኑ አይደለምን? እኛ እንደ ተራ ነገር የምንወስደውን አየር፣ እነርሱ በማሽን እርዳታ ወደ ሳንባቸው ለማስገባት ሲታገሉ አይታዩምን? ከተኙበት አልጋ ቀና ማለት ያልቻሉ፣ ቁጭ ማለትን የሚናፍቁ፤ ቁጭ ማለት የቻሉትም በእግራቸው ወዲህና ወዲያ የሚንቀሳቀሱበትን ቀን የሚጠብቁ፤ ወደ መስኮት ሄደው የውጭውን ዓለም ለማየት የሚጓጉ፤ ከሕመማቸው ሥቃይ ትንፋሽ የሚያገኙበትን ደቂቃ በጉጉት የሚጠብቁ፤ እንደልባቸው መብላት፣ መሳቅና ጮክ ብለው ማውራት የማይችሉ ብዙ ሰዎች አሉ። ከሥቃዩ ብዛት የተነሳ ተስፋ የቆረጡ፣ ሁሉን ትተው ቀናቸውን የሚቆጥሩ፣ ከሕመማቸው የተነሳ ሞትን እስከሚመኙ የደረሱ ሰዎችም አሉ። እነዚህ ሰዎች እኛ የምንመኘው ሀብት፣ እኛ ቢኖረን ብለን የምንጓጓለት ንብረት፣ ለእኛ ሕልም የሆነብን ሥራ ሊኖራቸው ይችላል። እኛ ልንደርስበት የምንሻውን ደረጃ፣ ምናልባትም ከዚያ በላይ የሆነ ስፍራ ደርሰው ይሆናል። ዝና፣ ሀብትና ክብርም ከእነርሱ ጋር ዘመናቸውን ሙሉ ኖረው ይሆናል። በዚህች ቅጽበት ግን እነርሱ የሚመኙት አንድና ብቸኛ ነገር ምን መሰላችሁ? እንደኛ ጤነኛ መሆን ብቻ! ቀኑን ማየት፣ የጠዋት ወፎችን ዝማሬ መስማት፣ የማለዳውን ቀዝቃዛ አየር መተንፈስ፣ ሥራ መሥራት፣ ከጓደኛ ጋር መጫወት፣ መሳቅ... በጤና ሆኖ ጤናማ ቀን ማሳለፍ። እኛ እጅግ የምንፈልጋቸው፣ በእነርሱ ሕይወት ውስጥ ተሟልተው የነበሩ ብዙ ነገሮች፣ በዚህ የሕመምና የጭንቅ ወቅት ለእነርሱ ምንም ፋይዳ የላቸውም። ምኞታቸው አንድ ነገር ብቻ ነው፤ እንደኛ ጤነኛ መሆን፣ ከሆስፒታሉ አጥር ውጭ በነፃነት መገኘት። እናመስግን!🙏 ጤና ስላለን፣ በእግራችን ስለምንራመድ፣ በአፋችን ምግብ ስለምንመገብ፣ ሰኞንና ማክሰኞን እያልን ቀናትን ስለምንቆጥር፣ ጊዜን ኖረንበት «እንዴት ይሮጣል?» ስለምንል፣ ስለምንስቅ፣ ስለምንተነፍስ፣ ራሳችንን ችለን የዕለት ተዕለት ፍላጎቶቻችንን ስለምናሟላ፣ በእጆቻችን ስለምንሠራ... ዘርዝረን በማንጨርሰው የፈጣሪ ስጦታ ሁሉ እናመስግን። በእጃችን ያለው ጤና ውድና ብርቅ መሆኑ የሚገለጥልን በሆስፒታል አጥር ውስጥ ስንገባ ብቻ አይሁን። እናስ፣ የዛሬዋ ቀን ንጉሥ ማነው? ታሞ ከሚማቅቅ ናጠጠ ቱጃር ይልቅ፣ በማለዳ ከላስቲክ መጠለያው በጤና እየሳቀ የሚወጣው አንድ ጎዳና አዳሪ ይበልጥ ባለጸጋ አይደለምን? ንግሥና ማለት ዛሬን በጤና መኖር መቻል ነው! ወዳጆቼ! ሀብትን ከሕመም ጋር የሚመኝ ማንም የለም። ሙሉ ጤናን ከድህነት ጋር የሚለምን ግን እጅግ ብዙ ነው። ከቤቱ ወጥቶ መመለስ ባልቻለበት ዘመን፣ እኛ በጤና ወጥተን በሰላም የምንመለስ መሆናችንን እንደ ትልቅ በረከት እናመስግን። ቀሪውን የሕይወታችንን ክፍተት መሙላት ደግሞ የፈጣሪ ሥራ ይሁን። ሕይወታችሁ በጤና፣ አንደበታችሁም በምስጋና ይሙላ! 🙏 እስቲ የዛሬዋን ቀን በሰላም ከመኝታቹ የተነሳቹ በኮመንት እናመሰግናለን በሉ🙏 ✍️ መላኩ ብርሃኑ @atronosee

Открыть в Telegram
Просмотры797−13%к среднему
Пересылки2
Реакции16
Комментарии6
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч120
6 ч340
24 ч712
35 ч797
  1. Через 1 час120
  2. Через 6 часов340
  3. Через 24 часа712
  4. Всего сейчас797
#98280Фото
Просмотры692−24%к среднему
Пересылки0
Реакции—
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч107
6 ч286
24 ч612
35 ч692
  1. Через 1 час107
  2. Через 6 часов286
  3. Через 24 часа612
  4. Всего сейчас692
#98277Текст
Просмотры855−6%к среднему
Пересылки0
Реакции15
Комментарии1
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
12 ч460
25 ч749
46 ч855
  1. Через 24 часа749
  2. Всего сейчас855
#98276Текст
Просмотры832−9%к среднему
Пересылки1
Реакции14
Комментарии1
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
12 ч484
24 ч713
46 ч832
  1. Через 24 часа713
  2. Всего сейчас832
#98275Превью ссылки

​​ነው ለራሴ ክብር ያጣውት ምን ያክል ብደነዝዝ ነው የሰው ቤት ሄጄ ክብሬን የማጣው ... ኤዶምስ ቢሆን ፣እራሴን መቆጣጠር የለብኝም ...ምን እያደረኩ ነው ያለውት ....ፍቅር እውር አድርጎኛል እንዴ .....ለምን ለራሴ ክብር አጣለው ..የማያባራ ወቀሳ በራሷ ላይ አካሄደች ስልኳ ያለማቋረጥ ቢጮህም ማንሳት ከበዳት ሳይለንት አደረገችው ፣ በዚ ስሜት ውስጥ ሆና ከኤዶም ጋር ካወራች እንደምትረበሽ እና ዕንባዋን እንደምትዘረግፈው ተሰምቷታል ፣ ስልኳ መጥራቱን አላቋረጠም .... === ኤዶም ከሄደበት ሲመጣ ቤት ለመግባት እንኳ አልፈለገም የሲፈን ስልክ ያለማንሳት ሊያሳብደው ደርሷል እንኳን ቤት ገብቶ ሊቀመጥ ፣ ቀርቶ እናትና አባቱን እንኳ ከመንገድ ነው የተለያቸው የተሳፈሩበት መኪና ልክ የነ ሲፈን ሰፈር መግቢያ ሲደርስ ነበር የምደርስበት ቦታ አለ ብሎ ተሰናብቷቸው የወረደው ፣አባቱ ቢደናገራቸውም እናትየው ግን ገብቷቸዋል ውይ ልጄ ቀልቡ ሁሉ ሲፈኒ ጋር ነው ፈጣሪ ይጠብቀው ብለው በልባቸው ሸኙት.... አይምሮው እረፍት አጥቷል ሆነብዬ ስልኬን ቀይሬ መስሏት ይሆን ፣በጭራሽ ግን እሱን አዳም የኔን ስልክ እስካላነሳ በምን ታውቃለች ፣ ካወቀችስ በአዳም ስልክ ስደውል አንስታ አታናግረኝም ነበር ፣ አሄሄሄ ይሄማ ነገር አለው ፣ ምን ሆናብኝ ይሆን በአባቷ ምክንያት ተናዳ ይሆን ፣ እሱ ደሞ አልፏል ፣ከዚ በኋላ ፍርዳቸውን እንደሚጠብቁ አውቃለች ፣ ኡፍፍፍፍ ሲፈን ስልክ ማንሳት ነበረብሽ ፣ .....እያለ የነሲፈን ሰፈር ተጉዞ ጊቢያቸው ጋር ደረሰ ከምሽቱ አስራሁለት ተኩል ነው ። ገና ነው አለ ለራሱ ። እናም በሩን አንኳኳ ከትንሽ ቆይታ በዋላ በሩ ተከፍቶ ዘበኛው በምን ፈለክ አይነት አፈጠጠበት ትህትና የጎደለው አስተያየቱ ቢያናድደውም ፣ በተረጋጋ መንፈስ "ይቅርታ ወይዘሪት ሲፈን ትኖራለች "አለው በጥርጣሬ አይን ከገረመመው በኋላ "አለች ..."ብሎት ተገትሮ ቀረ "እሺ ትጠራልኛለህ እባክህ በስራ ጉዳይ ላወራት ፈልጌ ነው "አለው በትህትና ። ትንሽ ያለምንም ቃል ከቆየ በዋላ ቅር እያለው እዚው ጠብቅ ብሎት በሩን በላዩ ላይ ዘግቶ ተመለሰ.... ከቆይታ በዋላ ሲፈን መጥታ ፊቱ ገጭ አለች ነጭ ቢጃማ ለብሳ በላዩላይ ፒንክ ፎጣ ጣል አድርጋለች ፀጉሯ ወደኋላ ሰብሰብ ብሎ በፀጉር ማስያዢያ ተይዟል ፊቷላይ ጭንቀት ነገር ቢነበብም ውበቷ ግን ልብን ይሰርቃል ለቁጣ ያዘጋጀው ቃላት ተበታትነው ጠፉበት ፣ጭራሽ ያልፈለጋቸው እርጥበቶች በአይኖቹ ዙሪያ ተጋረዱበት ፣ ዝምብሎ ብቻ በእይታ ሊቀጣት ሞከረ ፣ "ኤዶ ምነው እዚ ድረስ ...."ብላ መቀጠል አቃታት እሷም የቀኑ ሁኔታ አንድ በአንድ መጥተው ተደቀኑባት ፣ "እዚ ድረስ ? ሲፍ እንዴት ነው ነገሩ "አለ ና መልሶ ዝም አለ "ማለቴ ...."ብላ መልሳ ተወችው ለምን አልደወልክልኝም ማለት አጉል ነገር መነካካት ነው የሚሆንባት ፣ ለጊዜው ዝም ማለቱ እንደሚሻላት አሰበች "ሲፍ ስልኬን ቤት ረስቼው ነው የወጣሁት ምን አልባት ደውለሽ ከሆነ?! ከአዳም ጋር የሞባይል ቀፎ አችን መመሳሰሉን ታውቂ የለ ፣ ጠዋት ቸኩዬ ለካ የሱን ነው ይዤ የሄድኩት ፣ እና ይሄን ደሞ ያወኩት አክስቴ ጋር ደርሼ ስልኩን ቻርጅ ሳደርግ ነው ። እና የአዳም መሆኑን ሳውቅ ላብድ ነበር የደረስኩት ፣ ለሱ ብደውል ይጠራል አያነሳም ላንቺ ብደውል አይነሳም ፣ በጣም ነበር የተጨነኩት ...ይበልጥ ደሞ የፈራውት አብዲጋር ስደውል እሱም አጥጋቢ ምላሽ ሳይሰጠኝ ስልኩን ዘጋብኝ ፣ አንድ ቀን ከከተማ ምን ተፈጠረ ብዬ እንዴት እንደሆንኩ እኔነኝ የማውቀው !!ግን በሰላም ነው ?"አላት አይን አይኗን በስስት እያየ። ሲፈን በዝምታ አይምሮዋን አሰራች ምክንያት ፍለጋ ተሯሯጠች ...... "ሲፍ ችግር አለ "አላት እየተጠጋት "አይ ምንም ችግር የለም ፣ ደውዬልህ ነበር ደና መሆንህን ነግረኽኛል እኮ በቃ ከዛ በኋላ ደሞ እኔ በአባቴ ጉዳይ ላይ ነበርኩ "አለችው "አይ አይደለም እየነገርኩሽ እኮ ነው ፣ስልኬ ተቀያይሮ ነው "አላት እና መልሶ "ያናገረሽ አዳም ነው! እኔ የምልሽ ምን ብሎሽ ነው ?"አላት በጥርጣሬ ። "ምንም አላለኝም ደና ነኝ አክስቴ ጋር እየሄድኩ ነው ስመለስ እንገናኛለን ነው ያለኝ አንተን ተመስሎ ስላወራኝ አልጠረጠርኩም ። እና ደሞ አንተ በአዳም ስልክ እንደምትደውል በምን አውቃለው የአዳምን ስልክ እንደማላነሳ ደሞ ታውቃለህ በቃ ተረጋጋ አሁን "አለችው በጭንቀት ሳይታወቃት እየጮኽች ።ኤዶም ስላስቆጣት እየተ ፀፀተ ወደራሱ አስጠግቶ እያቀፋት "በቃ በቃ ይቅር የኔ ቆንጆ ጥፋቱ የኔ ነው በቃ የኔ ፍቅር ተረጋጊልኝ ፣ ምን ላድርግ የራቅሺኝ ሲመስለኝ ላብድ ነው የምደርሰው ባላይሽ እንኳ ድምፅሽ ያስፈልገኛል ደና ነኝ የሚለውን ድምፅሽን ስሰማ ደንነት ይሰማኛል እወድሻለው ሲፍ "አላት በስሜት ደረቱላይ ውሽቅ አለች ሳታውቀው ዕንባዋ በጉንጯ አልፎ ኮለል ሲል ተሰማት ፀፀት አቃጠላት በኤዶም እቅፍ ውስጥ ሆና አዳምን እረገመች ........ #Share እና #Reaction.. በጣም ያንሳል ሁለቱንም እያረጋቹ ቤተሰብ ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ። 👇Sebscribe YouTube link👇 https://www.youtube.com/@atronose

Открыть в Telegram
Просмотры745−18%к среднему
Пересылки2
Реакции31
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч101
16 ч653
25 ч745
  1. Через 1 час101
  2. Через 24 часа745
  3. Всего сейчас745
#98274Текст

#ባለ_ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ዘጠኝ ፡ ፡ ...ሲፈን ባለፈው  እነ ኤዶም ቤት የገጠማትን እያሰበች ብክን አለች በዛ ቀን እን ኤዶም ቤት ስትደርስ አዳም ኤዶምን በመምሰል በትህትና ተቀበላት ሶፋው ላይ እንድትቀመጥ እየጋበዘ ጠብ እርግፍ አለ ሲፈን በትላልቅ አይኖቿ ሁኔታውን ሁሉ እየተከታተለች እንደመሳቅም እንደመገረምም ብላ ታየዋለች አዳም ኤዶምን የመምሰሉ ትወና እንደተሳካለት ቆይቶ ተረዳ "ኤዶ ለምን ወዲ ወዲያ ትላለህ ቁጭ ብለህ አታጫውተኝም?"አለች ሲፈን ቀረብ አላት እና ተቀመጠ አጠገቧ አይኖቹ ውስጥ በፍቅር ተመልከተችው አዳም ልቡ መቅለጥ ጀመረ ጭንቅ አለው ሲፈን ጣቶቿን ጉንጩ ላይ በማሳረፍ "የኔ ፍቅር ሰሞኑን ተረብሼ ችላ አልኩህ አይደል ይቅርታ አድርግልኝ ግራ ገብቶኝ ነበር!" አዳም በፀጥታ የእጇን ሙቀት ያዳምጣል ሰውነቱ በአንዳች ፍላጎት መንደድ ጀምሯል አትናገርም ስትለው ጉንጩላይ የሚርመሰመሰውን ጣቷን ያዝ አደረገው አሻሸው ሲፈን ጠጋ አለችው እሱም ቀረባት ከንፈሯን አቀበለችው ተቀበላት ተስገበገበ ፡ሳማት ደጋግሞ ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ አለ አዳም እጆቹን ወደ ጡቶቿ ሰነዘራቸው ያዝ ጨመቅ አሸት ሲያደርግላት እንደማቀሰት አይነት ድምፅ አወጣች አዳም ድምፁ የባስ ተግ አደረገው ወደራሱ አሰጠግቶ በደንብ ያዛት ሳማት "ኤኤዶ እ አልቻል ኩም አአንድ ነገረ አድርግ የየኔ ፍቅር በበጣም አእወድድሃለው ..."አለች በስሜት ተውጣ አዳም ወንድሙ ይህን የመሰለ ፍቅር እንደነጠቀው ሲረዳ የባስ ተቃጠለ ከበፊቱ በበለጠ ፡ያጣድፋት ጀመር እናም ከሶፋው ላይ በሁለት እጁ ብድግ አድርጓት ወደመኝታ ክፍሉ ይዟት ገባ ሲፈን በሰመመን "ኤኤዶ ለለምን የአዳም ክክፍል ታታስገባኛለህ?"አለች አዳም ተሸወደ ደነገጠ እንዳት ነቃበት፡የመጣለትን ተናገረ "ሲፍ ስለቸኮልኩ አእሱ አልታየኝም ናናፍቀሽኛል !"አለ ከመናገሯ በፊት፡አልጋው ላይ በጀርባዋ አንጋለላት እናም ልብሱን አንድ በአንድ አውልቆ ጣለው ፡ሲፈን እርቃኑን ስታይ በፍላጎት ተንገበገበች አዳም ቀረብ ብሎ የለበሰችውን ልብስ በፍጥነት አውልቆ ጣለባት ሲፈን አፋን ከፍታ አየችው አያት አዳም እራሱን መቆጣጠር አቃተው በፍጥነት ተጣበቀባት ሲፈን ተቀበለችው "ኤዶ ፍፍቅሬሬሬ እእወድድ ሀሀለውው እእእእኤዶዶ....."ሲፈን በደስታ ቀባጠረች፡ አዳም፡በዝምታ ፡ ወደሷ ወደ ወደ ወደ.....   ስልኩ መጮህ ጀመረ ደጋግሞ እንደገና እሪ ስልኩ የሲፈን ስልክ .....  አዳም ስልኩን እንዴት ያስቁመው ፣እንደምቀኛ ቆጠረው ፣ ልቡ ሁለት ቦታ የሚመታ መሰለው ሲፈን ጋር በፍቅር ...ኤዶም ጋር በፍርሃት እላይዋላይ እየ እንደተጣበቀ ፣ ጭንቅላቱ እዚ እዛ ተደበላለቀበት ፣ ሲፈን ሞባይሏ ደጋግሞ ሲጠራ እርብሽ አለች ፣ "ቆይ ኤኤ ዶ ...ከቤት ይይሆናል"አለች በሚቆራረጥ ድምፅ "አይ ሲፍ እንዲ ባለ ሁኔታማ ማንንም ጣልቃ አናስገባ ማቆም አልችልም "አላት ትንፋሹን ለመሰብሰብ እየሞከረ "አይ ችችግር ባይኖር በአንደኛው ጥሪ ይቆም ነነበር "አለችው ። "የኔ ፍቅር አአይታይሽም ስሜቴን መግታት እንደማልችል  !ተይው ስልኩን በኋዋላ ትደውይላቸዋለሽ "አላት እየተስገበገበ ከጉዳዩ ለመድረስ ፣ሲፈን ድርቅ ሲልባት ትህትናውን ሲያጣ ፣ ትንሽ ቆጣ አለች "ኤዶ ተው በቃ የት ይሄድብሃል መርማሪው አንድ ፍንጭ አግኝቶ ይሆናል ወይም ደሞ ከቤት አንድ ነገር ተፈጥሮ ይሆናል" ብላ ገፋ አደረገችው ። አዳም ወደትክክለኛ ማንነቱ ድንገት ተመለሰ ፣ልትነሳ ስትል እዛው መልሶ አጋደማት ፣ሲፈን ደነገጠች ፣ ያልጠበቀችው ምላሽ ነበር ። በጉልበት የሚደረግ ማንኛውም ነገር የማትቀበለው ነው ይህንን ደሞ ኤዶም ጠንቅቆ ያውቃል ምነክቶት ነው በሚል አፈጠጠችበት "ምንድነው የምታካብጂው ስልክ ነው እንጂ የጮኽው ይጩሃ !አላት ከቁጥጥሩ ውጪ የሆነውን ስሜቱን በግድ ለማስታገስ አይል እየተጠቀመ ። ሲፈን ድንገት ከእንቅልፉ እንደነቃ ሰው አይልጨምራ አዳምን በመገፍተር ከስሩ ሾልካ ወጣች ፣ እናም አልጋው ላይ የምታየውን ሰው አፍጥጣ እያየች "አአንተ ማማ ነህ ኤዶ አአንተ አይደለህም !...አይ አይ አይሆንም ..."ብላ ጮኽች አዳም በመጨረሻ እንዳወቀችው ሲረዳ ፣ ያበጠው ይፈንዳ ብሎ አስገድዶ ጉዳዩን ሊጨርስ ከአልጋው በመነሳ በድንጋጤ በሩ ላይ የደረሰችውን ሲፈንን አፈፍ አድርጎ "ሲፈን አታካብጂ በቃ እኔ አዳም ነኝ በቃ ልትረጂኝ ስላልቻልሽ ነው እንዲ የሆንኩት ፣እና ምን ያክል እንደማፈቅርሽ እንድትረጂ ስሜቴን በግልፅ ላሳይሽ ስለፈለኩ ነው ። በቃ ሁሉንም በፍቅር እናርገው ጥሩ ስሜት ላይ ነበርን እኮ ፣ምን ያክል ውስጥሽ እንዳለው የተረዳውት ሰውነትሽን ስነካው እንኳ አልቀፈፈሽም ፣ነይ የኔ.... "ሲፈን አላስጨረሰችውም "እንዳትነካኝ እጮሃለው አልፈልግም አንተ አረመኔ  እንዴት እንዲ ጉድ ትሰራኛለህ አንተ ልክስክስ ነህ ውሻ ነህ ......"ብላ የመጣላትን ሁሉ ቃላት አውጥታ ተሳደበችው ። አዳም ጠጋ ብሎ ተሸክሞ አልጋው ላይ ለመጣል በማሰብ ሲንቀሳቀስ ሲፈን በጉልበቷ የአዳምን ብሽሽት በሀይል መታችው አዳም በአይለኛው አቃስቶ ተንበረከከ ሲፈን  በፍጥነት ከመኝታ ክፍሉ ልብሷንንና ስልኳን ይዛ በመውጣት  ፣ከውጪ በኩል የመኝታ ክፍሉን ቀረቀረችበት ከዛምልብሷን በፍጥነት በመልበስ ፣ ለአዳም ጩኽት ምላሽ ሳትሰጥ በድንጋጤ እየተደናበረች  ከነአዳም ቤት በሩጫ ተፈተለከች ፣ነገሩ ከምትሸከመው በላይ ነው የሆነባት ፣በየመንገዱ እራሷን እየረገመች ነበር ፣ እንዴት  እንዴት............. ============ ...ሲፈን ቤት ስትገባ እህቶቿ ተሰብስበው ሲያወሩ አገኘቻቸው ፣ እንደዛ ሁና ማንንም ማየት አልፈለገችም ነበር ፣ ወደክፍሏ ለመግባት ደሞ ሳሎኑን ማቋረጥ አለባት ፣እናቷም የጨዋታቸው ተካፋይ ስለነበሩ  አብረው ተቀምጠዋል ፣ ሲፈን እራሷን አረጋጋች ፣ ሰሞኑን በባላቸው ስራ ተጨናንቀው ከርመዋል ፣እና ትንሽ ነገር ነው የሚበቃቸው ፣ለዛ ስትል ሰላም መፍጠር አለባት ፀጉሯን ወደኋላዋ ገፋ ገፋ አድርጋ እያስተካከለች  ....ሶፋው ላይ ቁጭ አለች ሁሉም በአንዴ አይኖቻቸውን ተከሉባት ...... "ምነው እንዴ ጨዋታችሁን ቀጥሉ እንጂ"አለች ፈገግ ለማለት እየሞከረች "እኛስ ጨዋታችንን እንቀጥላለን ያንቺ አጫዋች ግን ማነበረ ዛሬ"አለቻት ሮዛ "እንዴት ምን ለማለት ነው "አለች ደንገጥ ብላ "አይ ልብስሽን እንኳ ገልብጠሽ እስክትለብሺ ድረስ የሆንሽበት ጨዋታ ...."ብላ ዝም አለች እናትና ልጆች እርስ በእርስ በፍርሃት ተያዩ "እእ አይ ...ልብ አላልኩትም ነበር  አይገርምሽም አሁን እኮ ቡቲክ ገብቼ ለብርድ የሚሆን ሹራብ ለመግዛት ስለካ ነበር ። ልጅቷ ግን የምትገርም ናት  ገልብጬ መልበሴን አልነገረችኝም አለች ሲፈን በፍጥነት የመጣላትን የፈጠራ ወሬ እየተጠቀመችበት ። "ውይ ነው እንዴ እኔ ደሞ ምን ተፈጠረ ብዬ !ታዲያ የታል ሹራቡ "አሉ እናት "ምን በጣም ሰፋኝ አላማረብኝም ተውኩት "አለች ሲፈን "ለዛ ነዋ ልብስሽን ገልብጠሽ ስትለብሺው ዝም ያለችሽ !ስላልገዛሻት "አለችና ሊያ ሳቀች ሁሉም ሳቁ ፣ ሳቅ የራቀው ቤት በሲፈን የፈጠራ ሽወዳ ደመቅ ስላለ ፣ለጊዜውም ቢሆን ሲፈን አዳም ካደረሰባት የሚያሳቅቅ በደል  አገገመች  ፣አይምሮዋ በርግጥ እረፍት አጥቷል ኤዶም ነው ክፍለ ሀገር የሄደው ፣እንዴት ስልካቸው ተቀያየረ ፣ አዳም ፍፁም እንደ ኤዶም ሆኖ ነበር የቀረበኝ በዚመጠን እንዴት ተሸወድኩ ፣ ...ብዙ ብዙ ጥያቄዎች ጭንቅላቷን ሞልተው ተንጫጩባት እራሷን ደጋግማ ወቀሰች ....እኔስ ብሆን ከመቼ ወዲ

Открыть в Telegram
Просмотры741−19%к среднему
Пересылки2
Реакции16
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч97
16 ч632
25 ч741
  1. Через 1 час97
  2. Через 24 часа741
  3. Всего сейчас741
#98273Фото

🌱 ተስፋ እስካለ ድረስ... ✨ 📍 በሰዎች ዘንድ ተስፋ የሌለን ብንመስልም፣ ዋናው ነገር በፈጣሪ ዘንድ ያለን ተስፋ ነው። ሕይወት ጠመዝማዛ መንገድ ብትሆንም፣ ውብና በተስፋ የተሞላች ናት። 💡 በዚህ ዓለም ሁሉም ነገር አበቃ፣ ተፈጸመ ብለን በምናስብበት ቅጽበት እንኳን፣ የተሻለ አጋጣሚ ከፊታችን ሊጠብቀን ይችላል። የምናውቀውና የተለመደው በር ተዘግቶብን ቢመስልም፣ ሌላ በር በድንገት ሊከፈት ይችላል። ዙሪያችን ደረቅ በረሃ ቢመስልም፣ ከዚያ ባሻገር የለመለመ መስክ ሊኖር ይችላል። 📍 ሕይወት እንደ ሳንቲም ናት፤ ሁለት ገጽታዎች አሏት። ተቃራኒ ቢሆኑም እርስ በርሳቸው የማይነጣጠሉ ገጽታዎች። በሕይወት እስካለን ድረስ ከአንዱ ገጽታ ብቻ ተለይተን መኖር አንችልም። እያንዳንዱ ሁኔታ ተቃራኒ ገጽታ አለው። ሳንቲም ያለ ጀርባው ገጽታ ሙሉ እንደማይሆን ሁሉ፣ ያለ ሐዘን ደስታን፣ ያለ ሞት ሕይወትን፣ ያለ ለቅሶ ሳቅን፣ ያለ ድህነት ሀብትንj በሙሉ ልንረዳ አንችልም። ስለዚህ ሕይወትን ከነሕብረ ቀለሟ መቀበል አለብን። 💡 እድል ፊቷን ያዞረችብን በመሰለን ጊዜ እንኳን፣ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ በትጋት መጓዝን እንምረጥ። ትጋት የተስፋ ልጅ ናት፤ ተስፋ ደግሞ በእኛና በፈጣሪ መካከል ያለው የእምነት ድልድይ ነው። 📖 ቃሉም እንዲህ ይላል፦ «ዛፍ ቢቆረጥ ደግሞ ያቆጠቁጥ ዘንድ፣ ቅርንጫፉም እንዳያልቅ ተስፋ አለው።» — ኢዮብ 14፥7 ━━━━━━━━━━━━━━ 🌿 አስታውስ! የተዘጋ በር የጉዞህ መጨረሻ ላይሆን ይችላል። የደረቀ ዛፍም አዲስ ቡቃያ ሊያወጣ ይችላል። የዛሬ ሐዘንህ የነገ ደስታህን አይከለክልም። ተስፋህን አታጥፋ፤ ፈጣሪ አንተ ያላየኸውን መንገድ ሊከፍትልህ ይችላል! 🤲 ✍️ አለማየሁ ዋሴ @Atronosee

Открыть в Telegram
Просмотры746−18%к среднему
Пересылки2
Реакции11
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
9 ч443
25 ч746
  1. Через 24 часа746
  2. Всего сейчас746
#98272Превью ссылки

​​ነካው........... ==== አብዲ እነ አዳም ቤት ሲደርስ አዳም በሩን ዘግቶ ሲወጣ ደረሰበት ፣ሁኔታው እንደተበሳጨ ያሳብቅበታል በሩን የሚዘጋው የመወርወር ያክል ነው አብዲ ሲፈንን በአይኖቹ ዙሪያውን ፈለገ የለችም ፣ አለመኖሯን እርግጠኛ ለመሆን ግን ወደ አዳም ቀረብ ብሎ ማረጋገጥ አለበት ይሄ እብድ ልጅ ቆልፎባትም ሊሆን ይችላል ብሎ አሰበ ፣ ... አዳም በሩን ዘግቶ ዞር ሲል አብዲን አየው ፣እና በመገረም አፍጥጦበት ቀረ  .. አብዲ ለፀብ የሚጋበዝ ሰው ነው የሚመስለው ፣ የሁኔታውን መለዋወጥ አይቶ ፣ "ምነው አብዲ ሰላም አይደለም እንዴ ምን ተፈጥሮነው የመጣኽው ? ችግር አለ ?" አለው   በሀሳቡ ቀጥታ የመጣለት  የአብዲ አባት ሞት ጉዳይ ነው በወንጀሉ ተባባሪ አድርገው በሐሰት የመሰከሩበትም መሰለው እንደ አዲስ ፣ "ችግር አለወይ ትላለህ እንዴ ? አንተ ባለህበት ሁሉ ችግር ጠፍቶ ያውቃል ፣ኧረ ምን አይነት የማትታረም ሰው ነክ ግን ፣ "አለው "እንዴ ምን ነካህ ፣ምን ሆነሃል "አለ ቁጣው ግንፍል ብሎ "ቆይ አሁን ሲፈን የት አለች ምን አደረካት  ?የትነው ያለችው "አለአብዲ ከቁጣው ሳይበርድ " ኦኬ ኪኪኪኪኪኪ አዳም መሆኔን ደረስክበት ኪኪኪኪ አይዞህ ጓደኛህ አምልጣለች "አለው ሳቁ ውስጥ እልህ እንዳለበት በግልፅ ያስታውቃል "አንተግን ያምሃል ምንድነው አላማህ ?" "ምን አላማ አለኝ ሲፈንን አፈቅራታለው ደጋግሜ ነገሬሃለው ፣እንደ መጥፎ ሰው አትየኝ ፣ እየሞከርኩ ያለውት ፍቅሬን ለማሳየት ነው "አለ ድርቅ ብሎ ። አብዲ ጓደኛውን እንደማያውቀው ሁሉ  ትኩር ብሎ ተመለከተው ጤነኝነቱንም ተጠራጠረ ፣  "ግንኮ እንደማትፈልግህ ደጋግማ ነግራሃለች ፣ ወንድምህን ደሞ ታፈቅረዋለች ፣ ሲፈንኮ ፣እያመጣህ እንደምትሸኛቸው ሴቶች አይደለችም ለምን አይገባህም ፣ "አለው በተሰላቸ አንደበት "ድንገት እኮ ነው ከእጄ ያመለጠችው ፣እኔና እሷ እየተፋቀርን ነበር እኮ ፣ድንገት ወንድሜ በመሃል ባይገባብን "አለ በቁጭት "አዳም ደጋግሜ ሲፈንን ጠይቄያታለው  ኤዶምን ከማንም ጋር አታወዳድረውም ፣ ላንተ ደሞ አንተ ባሰብከው መንገድ ተሰምቷት እንደማያውቅ ደጋግማ ነግራኛለች ፣ እባክህን በገዛ ወንድምህ ቅናት አይደርብህ ፣  አንተ ስለፍቅር ምንም የምታውቀው ነገር የለም ። ብታውቅ ኖሮ የምታፈቅራትን ልጅ በዚመልኩ ፀፀት ውስጥ ልትከታት አትጣደፍም ነበር ፣  ፍቅር አልያዘህም አዳም !እልህ ነው ሲፈንን እንደጓደኛ እኔም እወዳታለው ፣ ነገርግን ደስ ትለኛለች ማለት አፈቅራታለው ማለት አይደለም ፣ ሲፈን ለኔና ላንተ  ጓደኛ እህት ብቻ ነው መሆን የምትፈልገው ፣ ፍቅሯ ልቧ ግን የሄዶም ነው ይህን ተቀበል አለበለዚያ ግን ከዚህም በላይ ትጎዳለህ እንጂ ሲፈንን አታገኛትም ፣ ተው በቃ !! "አለው አብዲ ምርር ባለ አነጋገር ። አዳም ዝም አለ መናገር አቃተው  እራሱን ፈተሸ ፣እውነት እኔ እልህ ነው የያዘኝ....... #Mute ያረጋቹ  የሚለቀቀው አይደርሳችሁም #Unmute እያረጋቹ የንባብ አፍቃሪ ለሆናቹ ብቻ....ሌላው #React እያደረጋቹ #Share እያደረጋቹ አያስከፍልም ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ። 👇Sebscribe YouTube link👇 https://www.youtube.com/@atronose

Открыть в Telegram
Просмотры867−5%к среднему
Пересылки3
Реакции41
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
6 ч380
37 ч774
66 ч854
71 ч867
  1. Через 6 часов380
  2. Всего сейчас867
#98271Текст

#ባለ_ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ስምንት ፡ ፡ ...አዳም ከወዲያ ወዲ እያለ ቤቱን ያስተካክላል ዛሬ በራሱ መንገድ በጣም ተደስቷል ቤት ማንም የለም ምክንያቱ ደሞ ወላጆቹ እንዲሁም ኤዶም ናዝሪት የምትገኘው አክስቱ ጋር የሰርግ ስነስርሃት ስላለ ለሱ በመጠራታቸው ነበር  አዳም ያለ የሌለ ምክንያት ፈጥሮ ቤት ቀርቷል ስለዚህም ነበር ቤቱን የማስተካከሉን ድርሻ የወሰደው ግን ከዛም ከዛም በላይ ከማታ ጀምሮ እንቅልፍ ሳይተኛ ያሰበበት ነገር አለው አዎ የኤዶምና የአዳም የሞባይል ቀፎ ተመሳሳይ ነው እናም አዳም  ለነገ የኤዶምን ቀፎ በራሱ ቀፎ መቀየር ፈለገ  ስለዚህም ጠዋት ቤተሰቡ ለጉዞ ሲነሱ አዳም እንዳሰበው ለኤዶም የራሱን ቀፎ ቀይሮ አስቀመጠለት፡በዛላይ ምንም ቻርጅ አልነበረውም ኤዶም ወላጆቹን ላለ ማስጠበቅ  በጥድፊያ ውስጥ ሆኖ የአዳምን፡ተንኮል ሳይረዳ የራሱ ያልሆነውን ቀፎ ይዞ ወጣ በልቡ ለሲፈን መንገድ ላይ ሆኜ እደውልላታለው፡መቼም እንዴት ሳትነግረኝ ትለኛለች ያው እማዬ በድንገት ያመጣችው፡አሳብ ነው ብዬ አስረዳታለው፡ብሎ ሃሰበ አዳም ወንድሙ ብዙ ልብ ሳይል በመሄዱ ተገላገለ እናም በተንኮል ፈገግ በማለት ሲፈን አሳይሻለው ማንነቴን! ከዛ ማን ወንድ እንደሆነ ታረጋግጫለሽ ቱ እኔ አዳም አደለውም ንቀትሽን ባላወጣልሽ!'አለ አዳም እራሱን ኤዶምን ለማስመሰል ብዙ አልተቸገረም ወትሮም ብዙም፡ባይለያዩም በመልክ የወንድሙን የትህትና አነጋገር ለማምጣት ግን ትንሽ ደጋግሞ መሞከር ነበረበት እናም ወዲ ወዲያ እያለ  እንደ ወንድሙ አክት አደረገ በራሱ አሳብ እንደመሳቅ አለ ውስጡ ለበቀል፡ተነሳስቷል ሲፈን የኔ ነበረች፡ወንድሜ የኔ !ስልኩ ጮህ አዳም፡ድንግጥ አለ ኤዶም እንዳይሆን ፀለየ  አነሳው አብዲ ነበር አዳም ለመረጋጋት ሞከረ  እንዴት ለኤዶም ደወለ ብሎም አሰበ"ሄሎ አብዲ"አለ አዳም፡እንደ ወንድሙ ረጋ ብሎ "ኤዶ እንዴት ነህ ሰላም ነው?" "ደናነኘ አብዲ እንዴት ነህ አንተ በሰላም?" "አዎ በሰላም ነው ኤዶ የአዳም ስልክ ዝግ ሆኖብኝ ነው እኮ መርማሪው ጋር ቀጠሮ ይዘን ነበር፡ሲፈን አልነገረችህም ሦስታችንንም አንድ ላይ ሊያናግረን ነበር "አለው አብዲ "እህ ውይ ማታ እኮ... እማዬ የእህቷ ልጅ ታገባለች እና ብታይ ከሳምንት በፊት ይሆናል ከተነገራት ግን እኛ አንሄድም ብለናት ቆይተን ድንገት ማታ እንዴት የወላድ ማህን ታረጉኛላቹህ ብላ ስታማርር አዳም ያለውድ በግዱ እሺ አላቸውና አብረው ሄዱ ዛሬን ሳያድሩ አይቀርም ደሞስልኩ ሳይዘጋ አይቀርም እኔም ስደውልለት ነበር!" ብሎ ዋሸ አዳም "ኧረ ይገርማል ይህን ሲያውቅ ማታ አይደውልልኝም ነበር እሺ በቃ ኤዶ ከሲፈን ጋር አገኘዋለው መርማሪውን ቻዎ!"አለ አብዲ  እየተነጫነጨ "እሺ አብዲ ሲሲፈን አብራህ ናት እእ..." "እህ አፍቃሪው አሁን አብራኝ አደለችም ቆይቼ ግን አገኛታለው ካላስቻለ ደውልላት ሀሀ!ሀሀሀ አይ ኤዶ በርታ ወንድሜ!"አለ አብዲ፡በአብዲ ንግግር አዳም ተናደደ ፡ለምንድነው የኔ ስሜት የማይታየው፡ብሎ "አይ እሺ በዋላ አገኛታለው መልካም ቀን አብዲ ቻዎ "ብሎ ስልኩን ዘጋው በቃ ሲፈንን ለማግኘት ቢያንስ ለሦስት ሰአታቶች መጠበቅ ሊኖርብኝ ነው እስከዛ በቃ እንዴት ተውኔቴን እንደምጫወት ልለማመድ ፍፁም አዳም መሆኔን መንቃት የለባትም አዎ እሰራልሻለው ሲፈን! አለ ======= የሲፈን እናት በሲፈን የማፅናኛ ንግግር እርጋታን አግኝተዋል የሰሞኑ ጭንቀት ውጥረታቸው ሁሉ ሲተዋቸው ተሰምቷቸዋል እንዲሁም ልጆቻቸውን ከማበርታት ይልቅ እሳቸው ብሰው መገኘታቸው፡አሁን ላይ አሳፍሯቸዋል እሱንም ለመካስ ይመስላል ቡናውን፡እራሴው ነኝ የማፈላው ብለው ጉድ ጉድ ሲሉ ልጆቹም በደስታ መፍለቅለቅ ጀምረዋል ሲፈን የሊያ የቀልድ ወሬ የራሄል የማያቋርጥ ከትከት የሚል ሳቅ የሮዛ የውሸት ቁጣ የእናት ወዲወዲያ ማለት የሰሞኑን ውጥረት በረድ ስላደረገው ተደስታ ታያቸው ጀመር ሁሉም ነገር እንዲ ቢሆን ሁሌ ወይኔ አባዬ ይህን ፍልቅልቅ ቤተሰብ ለማይሞላው ፍላጎትህ ብለህ ምን እንዳደረክ ታውቃለህ ግን እሺ አሁን ምን አይነት ፍርድ ይሆን የሚገባህ አንተ የሕገወጥ ነጋዴ አንተ የጓደኛህ አስገዳይ፡ሌላም ሌላም ምን አይነት ፍርድ ይሆን የሚጠብቅህ አባባ ምን ያክል እንደጠላሁህ ባወክ ዳግም እማዬም አብራህ ትኖራለች ብዬም አልጠብቅ እምቢም ብትል ይገባታል ትላለች በሀሳብ ጭልጥ ብላ እናት ቡና አፍልተው ምሳም ከልጆቻቸው ጋር በልተው ደስ የሚል ቤተሰባዊ ሰላም ፍቅር ፈጥረው ዋሉ ሲፈን ከሰአት ላይ መርማሪውን ለማግኘት ብላ ወጣች አብዲን ሱቅ ድረስ በመሄድ አገኘችውና ተያይዘው ወደመርማሪው ሄዱ ያው ግን፡እንደዎትሮው ነበር ጥያቄው፡ብዙም የተለየ ስላልነበረ አብዲ ተሰላችቷል ሲፈን የመርማሪውን ክፍል ለቀው ሲወጡ የአብዲን መሰላቸት አይታ "አብዲ ታውቃለህ ለነሱ አንዲት ቃል እንኳን ልትጠቅማቸው ትችላለች አትበሳጭ በወነ ድግግሞሽ አንድ ፍንጭ አገኛለው ብሎ ነው ያው እኛም ትክክለኛ ፍትህ እስከፈለግን ድረስ መተባበር አለብን !"አለችው "እሱስ ልክ ነሽ ከተያዙ በኋላ የማጣራቱን ጉዳይ እኛን ከማንገላታት እነሱው ቢበረቱበት ብዬ ነው ተይ ለማንኛውም ቤት ላድርስሽ ወይስ?" "አይ ቅድም ውስጥ ሆነህ እኮ ኤዶ ደውሎቤት ብቻዬን ነኝ ነይ ብሎኝ ነበር ወደዛው መሄዴ ነው"አለች "እሺ ኤዶም ጋር ላድርስሻ ?" "እ ግን" "ምን ግን አለው እኔም እማ ጋር ደርሼ ነው ወደሱቅ የምሄደው ግዴለሽም ጊቢ ወይ መኪናሽን ይዘሽ አልወጣሽ አትግደርደሪ!"አለ አብዲ "እሺ እንግዲ "አለች ሲፈን ኤዶም ናፍቋታል ቶሎ ደርሳ ልታቅፈው ቸኩላለች ማንም የለም እሷና እሱ ብቻ...... ...ኤዶም አክስቱ ጋር ከገባ በኋላ ነበር ስልኩን ቻርጅ ሲያደርግ እናም ከፍቶ ሲያይ የራሱን የሞባይል ቀፎ አለመያዙን የተረዳው እናም በቀጥታ ለሲፈን መደወል እንዳለበት ተሰምቶት ደጋግሞ የደወለው ነገርግን አታነሳም በጣም ተጨነቀ ግራ ገባው ፣ የሰርጉ ቤት ጭፈራና ሆሆታ ምንም ስሜት አልሰጠውም ሁሉም ነገር ቶሎ ተጠናቆ ወደ አዲስአበባ የሚመለሱበት ጊዜ ናፈቀው ለረጅም ሰአት ደወለ እየጠራ የማታነሳው ለምን ይሆን  አሳብ ገባው.. ለረጅም ሰአት ሲወዛገብ ከቆየ በዋላ አብዲ ትዝ አለው ምን አልባት አግኝቷት ይሆናል ዛሬ ከመርማሪው ጋር ቀጠሮ ስላላቸው ብሎ  በማሰብ ወደ አብዲ ደወለ ..........ሁለቴ ጠርቶ ተነሳ "እሺ ጋሼ ሰርገኛ "አለው አብዲ ከሳምታው በፊት ከአዳም ጋር በዚ መልኩ ነው የሚያወሩት "አብዲ እንዴት ዋልክ "አለው ኤዶም "እንዴ ትህትና ደሞ እንደሄዶም ማውራት ጀመርክ"ብሎ እንደመሳቅ አለ "አብዲ ባክህ ኤዶም ነኝ ፣ከአዳም ጋር ጠዋት ስወጣ ስልኬ ተቀያይሮብኛል ለካ"አለው አብዲ ጉሮሮው ደረቀበት "እየቀለድክ ነው አዳም?!"አለው በጥርጣሬ "ኧረ የምን ቀልድ ነው ኤዶም ነኝ ይልቅ አዳምም ሲፈንም ስልክ አያነሱልኝም ፣አዳምስ እሺ ካልመሰለው እንዲ ነው ።ወይም ስልኩ መቀየሩን ሲያቅ ተናዶብኝ ቤት ጥሎት ይሆናል ። የጨነቀኝ ሲፈን ስልክ አለማንሳቷ ነው ።"አለው አብዲ ድንጋጤው ጨመረ ፣አዳም ሆነብሎ እንዲ አይነት የወረደ ነገር ያደርጋል ፣እኔ ይህን አላምንም አለ ለራሱ እሺ ሲፈንስ ኤዶም ነኝ ብሎ ሸውዶነው እቤት የጠራት ማለት ነው አብዲ ድንገት ባነነ የጓደኛው ተንኮል ገባው ...ኤዶም ላይ ስልኩን ዘግቶ በፍጥነት ወደነ አዳም ቤት እሮጠ ...........ሲፈንን አዳም ጉድ ከማድረጉ በፊት ሊደርስላት ሊያስጥላት ሊከላከልላት ፣የጓደኛውን መርዝ የሆነ አሳብ ሊያጋልጥ  ኤዶም ግራ ገባው ዛሬ ሰውን ሁሉ ምን

Открыть в Telegram
Просмотры993+9%к среднему
Пересылки2
Реакции12
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
6 ч355
37 ч828
66 ч976
71 ч993
  1. Через 6 часов355
  2. Всего сейчас993
#98270Текст
Просмотры971+7%к среднему
Пересылки1
Реакции16
Комментарии1
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
9 ч487
24 ч697
67 ч949
74 ч971
  1. Через 24 часа697
  2. Всего сейчас971
#98268Превью ссылки

​​===========           ...አብዲ ጓደኛውን እየጎተተ ወደፊት ሄደ በጣም ተናዶበታል እንዴት በዚ መጠን እራሱን ያስገምታል እንዴት ነው ሁሌም ስሜቱን መቆጣጠር የማይችለው ድንገት ፈጣን የሆነ እርምጃ ወስዶ ሲያድር መፀፀት! ለሲፈን አዘነላት፡በድንጋጤ ውስጥ እያለች የአዳም ጥፊ መጨመር ምን ያክል እንደሚጎዳት አሰበ ምን አይነት ነገር ነው፡...ዝናብ ማንጠባጠብ ጀመረ አብዲ ግንባሩ ላይ አንዲት፡የዝናብ ጠብታ አረፈችበት ቀና አለ ወደ ሰማይ ጉም አዝሏል ያን ያክል አይለኛ ዝናብ ግን የሚዘንብ አይመስልም ወደጰአዳም ዞረ በፀጥታ እየተከተለው ነው የትም ቢወስደው ግድ የሚሰጠው አይመስልም "አዳም ዝናብ ሊዘንብ ነው እንፍጠንና አንድ ቦታ እንቀመጥ" አለው "እእ ምን አልከኝ?"አለ አዳም እንደመባነን ብሎ "ዝናብ ሊዘነብ ነው አንድ ቦታ እንግባ በዛው መክሰስ እንቀማምሳለን  እርምጃህን ጨምር" "እእ እሺ እንደውም መጠጣት ፈልጌአለው!"አለ አዳም በግዴለሽነት "አትቀባጥር እንግዲ ይሄ አንድ ነገር ኮሽ ባለብህ ቁጥር መደበቂያ አትፈልግ በቃ ይበቃሃል እንዴ!"አለ አብዲ ተናዶ "ባክህ አብዲ ዝም በለኝ! እንደውም እዚ እንግባ ጥሩ ምግብ አላቸው!"አለ አዳም ከፊትለፊቱ የሚታየውን አነስተኛ ሆቴል በእጁ ለአብዲ እያመላከተው "እእ አጅሬው መጠጥ አለ አትልም!! በልሺ ዝናሙ ሊያደራው ነው ፈጥነን እንግባ"ብሎ አብዲ ወደሆቴሉ አቀና አዳም ተከተለው ውስጡ ተረባብሾበታል ደንግጧል ተጨንቋል እንዴት ነው ሲፈን ላይ መሰንዘር የቻልኩት ተገቢ ነበር እንዴ ከዚ በፊት ሴት ልጅ ላይ፡ሰንዝሬ አውቅ ነበር? ኧረ...አዎ አዎ ኤልሳ ላይ ግን ያ በጣም በልጅነቴ ነው እንዴት ነው የማፈቅራት ልጅ ላይ እጄ የተነሳው መቼም ይቅር አትለኝም በቃ ግንኮ ንግግሯ አጥንት ይሰብራል ሲፈን ለምን ለምን ወደ እውነታው አትመለሺም እንደምታፈቅሪኝ አውቃለው ችላ ስላልኩሽ ነው ወደ ወንድሜ የዞርሺው አውቃለው ለምን፡አይበቃሽም አዳም ላለመሸነፍ፡ጣረ... "እህ በዝምታህ ትቀጥላለህ ወይስ ቅድም ስላረከው እብደት፡ታስረዳኛለህ?!"አለ አብዲ ሆቴሉ ገብተው ከተቀመጡ በዋላ የአዳም ዝምታ ሲረዝም "ምንም የማስረዳህ ነገር የለም አብዲ እንዴት እንዴት እንደምታናግረኝ አይተሃል!" "በፈጠረህ ምን ነክቶሃል አንተ !ለምን አትተዋትም ተወኝ አለች እኮ በግልፅ አማርኛ እኔ የምወደው ኤዶምን ነው አለች እኮ!" "አይ አይ አብዲ ይህን መቀበል አልችልም  ሲፈንን መተው አልችልም!" "በጣም ጥሩ !በዚው ከቀጠልክ እንግዲህ በፍቅር ሰበብ ጥበባቸውን እንደሚያፈሱቱ እንደ አንዳንድ ወፈፌዎች ወይ አሲድ ወይ ጩቤ መጠቀምህ፡አይቀርማ!! ?"አለ አብዲ የአዳም ድርቀት ነው የታየው እናም ተናደደበት "ምን ለማለት ነው?!"አለ አዳም ቀና ብሎ እያየው I "አሃ ልክ ነኛ አየህ እንደማትፈልግህ ስትነግርህ ጥፊ አቀበልካት ነገ ተነገወዲያ  ካልሆንሽ ይገባሻል ጩቤ ይገባሻል ማለት አይቀርም ብዬ ነው ልንገርህ ይሄ አስገድዶ ፍቅር ውጤቱ ጥሩ አይሆንም ተው እሷ ኤዶምን አንተ እንደ ተሰማህ ለበቀል ወይም፡አንተን ለማናደድ ብላ አይደለም የምትወደው ፍቅሯ የእውነት ነው፡ይህን መቀበል አለብህ ተዋቸው፡የራስህን ሴት ታገኛለህ ታገስ ፍቅር፡ማለት ያፈቀርከውን ሰው ስሜት፡ማክበር ነው ለዛሰው ደስታ፡መጨነቅ ማለት ነው መንገዱን፡ማክበርም ጭምር ነው! የኔ ካልሆንሽ መደሰት መሳቅ፡መተንፈስ አትቺይም ማለት እራስ፡ወዳድነት ነው አዳም እሷን ብቻ፡አደለም ወንድምህንም እራስህንም ነው የምትጎዳው በዚ ከቀጠልክ ተው ጓደኛዬ!!"አለ አብዲ አዳምን እንዴት ከዚ ሁሉ ጥፋት እንደሚጠብቀው ግራ እየገባው አዳም ምንም ሳይመልስለት አቀርቅሮ ቀረ የተሸናፊነት ስሜት፡ተሰማው ክፉኛ አዘነ አብዲ ያለው ነገር ትክክል ቢሆንም እንዴት፡ይቀበል አመመው በጣም አመመው አዳም ሲፈንን መተው.... ==== ዝናቡ ዘንቦ ዘንቦ ማባራት ጀምሯል ካፌው ዝናብ ተጠልለው የገቡ ሰዎች አጨናንቀዋታል የረጠቡ ጨርሶ ያልነካቸው ወንድናሴት በጥንድ በተናጥል እየሆኑ ተቀምጠዋል ሁሉም የዝናቡን፡ማባራት በጉጉት የሚጠብቁ ነው ሚመስሉት ኤዶም ካፌውስጥ ከተቀመጠ ቆይቷል ለብቻው፡እንደገና ሲፈን ከመጣች በዋላ፡እረዥም ሰአት ! "የኔ ቆንጆ አሁንም አትነግሪኝም፡ማነው ፊትሽ ላይ የመሰንዘሩን አቅም ያገኘው?" "ኤዶ እወድሃለው በጣም ይህን የምልህ ለሽንገላ አይደለም ከልቤ ነው ካላየውሁ ለሁለት ቀን እንኳ መቆየት አልች እያልኩ ነው! እያንዳንዷ የልቤ ምት ውስጥ አንተ አለህ፡ኤዶ.." "ሲፍ እርህስ አትቀይሪ ማነው የመታሽ ለምንድነው የመታሽ አባትሽ እንዳልሆኑ እርግጠኛ ነኝ!" "ኤዶ በምን እርግጠኛ ሆንክ?!"ቆጣ አለች ሲያስጨንቃት፡እንዴ አዳም መታኝማ አይባልም፡እንዴ ወንድማማች ተጋደሉሃ!አይ በጭራሽ አለች በውስጧ "ምን አባትሽ ናቸው?" "አዎ!" "ለምን ?" "በጣም ስላናደደኝ ብዙ ነገር ተናገርኩት እንደምጠላው እና፡የማይረባ ሰው መሆኑን ብቻ በጣም ስለሰደብኩት ድንገት ሰነዘረብኝ በቃ!"አለች ሲፈን ውሸቱ እንደተሳካላት ኤዶም በረድ ብሎ፡ጉንጯን ቀስ እያለ ሲደባብስላት፡ተረዳች እናም የሚዳስሳት እጁላይ እጇን አሳረፈች አይኖቹን በፍቅር ስሜት ተሞልታ አየቻቸው እንዴት ነው ኤዶምን የማልወደው ኧረ ከመውደድም በላይ እየሆነብኝ ነው ስሜቴ አዳም ተሳስተሃል! ወንድምህ አንተ የያዝከውን ገፅታ፡ይዟል ከዛም በላይ ደሞ አንተጋር የሌሉ ብዙ የሚፈቀሩ ነገሮች አሉት፡እና እንዴት ብዬ ነው ከዚ የፍቅር ሙቀት ውስጥ የምወጣው በጭራሽ "ሲፍ በቃ አባርቷል እንሂድ እንዴ፡ከስንት ሰአት ጀምሮ ተቀመጥኩ ኪኪኪ ኧረ ቂጤ ደነዘ!" "ሀሀሀ መቀመጫዬ ነው የሚባለው!" "ያው ነው ሲፍ ቂጥ መቀመጫ ባይባል ከየት አመጣዋለው ኪኪኪኪ" "አይ እንግዲ እቆነጥጥሀለው፡ስርሃት!"የውሸት ኮስተር አለች ሲፈን "እሺ እንዳትቆነጥጪኝ ባለፈው እእ እዛ እእ ኪኪኪኪ አይ ሲፍ አይለኛ ተቧጨሪ አይደለሽ እንዴ !"ብሎ ሳቀ ደስተኛ ነው ኤዶም "በል ዝም በል አን! "አለች እንደማፈር ብላ "እሺ ኪኪኪ የኔ ቆንጆ ስወድሽ እኮ፡ሲ ሲፍ ዛሬ አብረን እንደር በጣም ናፍቀሺኛል እእእ ፕሊስ?" "አይ ኤዶ ዛሬ ከመቼውም በበለጠ ቤተሰቦቼ ይፈልጉኛል !" "እእ  ይቅርታ ሲፍ ልክ ነሽ  ልታረጋጊያቸው ይገባል የኔ አስተዋይ ስወድሽ ልዩ እኮ ነሽ የኔ ልዩ "ብሎ እጇን ሳም አደረጋት "አመሰግናለው ኤዶ !በቃ እንነሳ አባርቷል ለዚ ዝናም የሚሆን ጥላ አለኝ !"ብላ እየተነሳች ፈገግ አለች፡ኤዶም አብሯት ተነሳ ከካፌው ሲወጡ ችፍቸፍ ለሚለው ሳሳ ያለዝናም ጥላዋን ዘረጋች ኤዶም ተጠለለ መልሶ ተቀበላትና እራሱ በመያዝ አቅፏት መሄድ ጀመረ ፡ሲፈን ቀለል አላት የአዳም ጉዳይ ግን ውስጥ ውስጧን እያስፈራት ነበር በዚው ከቀጠለ እንዴት ብላ ልታስቆመው እንደምትችል አሳቡ የላትም ተገርማለች በጣም በጥፊ መታኝ እኮ ማንም ሰው ፊቴላይ ሰንዝሮ አያውቅም አዳም እኔን ፡እንዴት ነው ይህን ነገር፡ማስቆም የምችለው አረስንት ጉድ ነው የመጣብኝ፡ወይኔ ሲፈን !!!!! ❗️አንብበው ሲጨርሱ ❤️ እንዳይረሳ ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ። 👇Sebscribe YouTube link👇 https://www.youtube.com/@atronose

Открыть в Telegram
Просмотры1 021+12%к среднему
Пересылки5
Реакции94
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
12 ч437
27 ч703
72 ч1 021
  1. Через 24 часа703
  2. Всего сейчас1 021
#98267Текст

#ባለ_ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሰባት ፡ ፡ ...የሲፈን እናት ከወዲያ ወዲ እያሉ ያነባሉ የሚይዙት የሚጨብጡት ጠፍቷቸዋል ሁሉም ነገር ድንገት በአንዴ ከብርሃን ወደጨለማ ተቀይሮባቸዋል ስለ ባላቸው ሐይለኝነት በስተቀር ሌላ አጉል ነገር ይኖራቸዋል ብለው አስበው አያውቁም ፖሊስ በራቸውን አንኳኩቶ ሲመጣም የመጀመሪያ ነው አቶይፍሩን ለመውሰድ፡ለማመን ተቸግረዋል የኔ ይፍሩ ሕገወጥ ነጋዴ ሊያውም ሰውን ሊጎዳ የሚችል ነገር በፈጣሪ ምን ሲል አሰበው እንዴት የዚህን ያክል ጨካኝ ሆነ እያሉ ይጮሃሉ በመሃል በመሃል እሮዛ ሽብሽብ ብላ ተቀምጣለች አንገቷን ደፍታ....፡ራሄልም ከሷ ትይዩ ተቀምጣ እናቷን በእንባ ታግዛለች ወይኔ አባዬ አዋረደን አሳፈረን እንዴት ብለን ነው በሰፈርተኛው አይን የምንታየው ወይኔ አባ ምነድነው ያደረከው እንዴት ? ትላለች በፍርሃት .....ሊያ እናቷን ለማፅናናት እየሞከረች አብራ ወዲያ ወዲ ትላለች በውስጧ አብዲን ትረግማለች የልጅ ነገር ሆኖባት ትዝታለች እሱ ነው አባቴ ላይ ጠቁሞ የሚበጠብጠን ይሄ የማይረባ በሞተ ይሄ ከሃዲ በአባቴ እጅ በልቶ ደሞ መልሶ እንዲ ያደርገናል ደሞ ያባቴ ገዳይ ናቸው፡ይላል የማይረባ ቤተሰቤን እንደበጠበጠ  እኔም በተራዬ ባልበጠብጠው ሊያ አደለውም ሲያስጠላ እያለች እናቷን ያዝ ለቀቅ ታደርጋለች እናት በለቅሶ ድምፅ እንዴት እንዴት እንዲ ያለ አስነዋሪ ነገር ይሰራል እንዴት ለሰው ጤና ጠንቅ የሆነ ነገር እያመጡ ልክ፡ጥሩ ስራ እንደሚሰራ ሰው መጋዘን እያስገቡ ያከፋፍላሉ ተውት እሱን፡አቶ የሱፍን ማስገደል እእእእ አውሬነት ነው ምን ያክል ነው ባሌን የማላውቀው ወይኔ ወይኔ አምሳል የአጢያት ገንዘብ አስበላኝ እእእእ"ብለው በምሬት እንደመጮህ አሉ ሊያ ደነገጠች "እማዬ እንዳያምሽ እባክሽ፡ለዚሁሉ ተጠያቂው አብዲ ነው የጠቆመባቸው አንቺ ግን በቃ ይበቃሻል!"አለች እናቷን እያቀፈች "የአብዲን ስሞ አትጥሪ አንቺ ትንሽ ልጅ ሂጂ ወደክፍልሽ ቶሎ "አለች ሮዛ እህቷ ላይ እየ ተቆጣች፡ሊያ እያልጎመጎመች እናቷን ለቃ ወደ ክፍሏ ገባች ሮዛ ወደ እናቷ በመጠጋት እንዲቀመጡ ወተወተች ተቀመጡ ነገሮችን ተረጋግተው ማሰብ እንዳለባቸው መከረች ተረጋጉ ራሄል ወደ ሲፈን ደወለች እዚያው ጣቢያ እንደሆነች፡እና አባቷን እንዳወራቻቸው በደከመ ድምፅ ነገረቻት ራሄል ሲፈን ስትዳከም ፍርሃት ፍርሃት አላት ወይ ጉዳችን ምን ይውጠን !. =========== ከእስርቤት መልስ ብቻዋን በእግሯ እየተጓዘች አባቷ ያወሯትን የጭካኔ ስራ አንድ በአንድ አይምሮዋ ውስጥ እያመላለሰች ድጋሚ ድጋሚ ትሰማዋለች በጣም ተገርማለች አባቷን ከዚ በፊት እንደማታውቃቸው ሆኖነው የተሰማት እንዴት አባቴ በዚህ መጠን አውሬ ይሆናል እንዴት ገና ለገና በፍርሃት ተመርቶ ውድ ጓደኛውን እሰከማስገደል ይደርሳል እንዴት አስመሳይ ሰው መሆን ቻለበት የፈለገውን ያክል ያቶ ይርጋ ግፊት ቢኖረው እንዴት አባቴ እንደ ተራ አስተሳሰብ እንዳለው ሰው ተራ ይሆናል በዚ ጥፋቱ የስንት ሰው የሕይወት መስመር እንደሚጠፋ አያውቅም አባቴ ጠላሁ በጣም ጠላሁ  አጭበርባሪና ነብሰ ገዳይ ነህ ጥይቱን ማንም ተኮሰ ማን አንተና ጓደኛህ ግን ገዳይ ናቹ የእጃችሁን ታገኛላቹ እጠላችዋለው አውሬውች!!.. "ሲፈን ሲፈን....."ሲፈን የጥሪውን ድምፅ ሰምታ ዞረች  አዳም ነበር የሚጠራት ቆመች አዳም ደርሶ እጂን ለሰላምታ እየዘረጋላት "እንዴ እንዴት ነው የምትፈጥኚው፡እዛ እስርቤት ውስጥ አይቼሽ ነበር ተሰወርሺብኝ!"አለ አዳም በናፍቆት እያያት እናም እያዘነላት "እእ አላየውህም ነበር ለምን መጣህ አባቴ ላይ ለመሳቅ ነው?" "ምን ማለት ነው ደሞ ለምን አባትሽላይ እስቃለሁ? " "ምን አልባት ብዬ ነው እሺ ምን ታደርጋለህ?" "ብቻዬን አይደለሁም መርማሪው ሊያናግረን ስለፈለገ ከአብዲ ጋር ነው የመጣነው ያው እንደውም አብዲም እየመጣነው!"አለ አዳም እያመላከታት አብዲ እየተጎተተ ወደነሱ ሲመጣ አየችው ሲፈን ጭንቅ አላት መሄድ ፈለገች እንዴት ብላ ነው የአብዲን አይን ማየት የሚቻላት አባቷ እኮ ነው አባቱን ያስገደሉበት አፈረች ተሸማቀቀች"አዳም እኔ ልሂድ!"አለች "አይ አብዲ እያየሽ ነው ይደብራል በነገራችን ላይ አብዲ እንደውም፡ስለሁሉም ነገር ሲፈን ስታውቅ በጣም ታዝናለች ብሎ ጉዳዩን ካወቅነው ጀምሮ ስላንቺ ነበር ሲጨነቅ የነበረው ስለዚህ አሳብ አይግባሽ "አላት አዳም አብዲ አጠገባቸው ሲደርስ እጁን ለሰላምታ ወደሲፈን ዘረጋ "ሲፍ እንዴት ነሽ?"አለ አዝኖላታል ለሷም ዱብዳ እንደሚሆንባት ገብቶታል "ደደና ነኝ አብዲ እንዴት ነህ አንተ እእ ማለት አዝናለው አብዲ ይህ አይገባም ነበር እእኔ...." "ሲፍ ተይ በቃ መሆን ስላለበት ነው እኔም ጉዳዩን ይፋ ያደረኩት የግድ አሁን ላይ ካላስቆምኳቸው ግድያው መቀጠሉ አይቀርም ነበር አዳምን አባትሽ ባይሆኑም አቶይርጋ ግን ከመግደል ወደኋላ አይሉም ነበር ዞሮዞሮ መቀጣት አለባቸው አንቺ ግን ለመፅናናት ሞክሪ!"አለ አብዲ እያዘነላት "እእሺ አብዲ በጣም ነው አባቴን የጠላሁት ለአቶ የሱፍ በጭራሽ እንዲ ያለ ነገር አይገባቸውም ነበር አዝናለሁ "ብላ አቅፋ አፅናናችው አብዲ ሲፈን ስላልተቀየመችው ደስ አለው አዳም ሲፈንን በአዘን ስሜት እያያት "ሲፍ ልሸኝሽ በቃ ነይ አብዲ ወደ ሱቅ ነው የሚሄደው"አላት "አይ እኔም ብዙ አልሄድም ኤዶምን ሳም ካፌ ጠብቀኝ ብዬዋለው እዛ እየጠበቀኝ ነው አመሰግናለሁ አዳም መሄድ ትችላለህ ከአብዲ ጋር!"አለችው አዳም አንጀቱ ተቆረጠ ፊቱ ተቀያየረ "ነው ለምን አብሮሽ አልመጣም ነበር ታዲያ!" "ስማ ባለ ጭንብሉ አባቴን ላወረው እኮ ነው የመጣሁት አባቴ ኤዶምን ቢያየው ምን የሚል ይመስልሃል በል ቻዎ እንዳወራ አታድርገኝ!"አለች የሰላችታ "አውሪ ከዚም በባሰ ማውራት ትቺያለሽ እንዴ ምን ቀረሽ ስሚ ይሄ ግትር የምትይው ነገር ይብቃሽ ሆነብለሽ እንደምታደርጊው አውቃለው አቁሚ ከወንድሜ ጋር ያለሽን ነገር እኔን ማናደዱ ይበቃል!"አለ አዳም በስጨት ብሎ አብዲ ነካ አድርጎ ጠቀሰው በእንሂድ ተዋት አይነት ሲፈን ተበሳጨች "አንተ ደነዝ እኔ እንዳንተ ጭንብል አጥልቄ አደለም ሰዎችን የምቀርበው አይገባህም ኩራትህን ቀቅለ ብላው እንዴት አልተወደድኩም በሚል ክብርህ የተነካ ከመሰለህ የራስህ ጉዳይ!! ኤ  ዶ  ም ን እ ወ ደ ዋ ለ ሁሁ ለምን አትሰማም ይህው በአብዲ ፊት እነግርሃለው አልፈልግህም፡እንደውም ለተራ ጓደኝነትም አልፈለግህም ገደል ግባ!"ከማለቷ የአዳም ጥፊ ተቀበላት ጯ ዋ..ሲል ሲፈን ተንገዳገደች እናም ፊቷን ያዘች አይኖቿ እምባ አቀረሩ አዳም ፈዘዘ ጥፊው ከሱ የተሰነዘረ እሰስከማይመስለው ሆነ አብዲ በድንጋጤ አፉን ከፈተ ..ወዲያው እጁን ይዞ ጎተተው "አንተ በሽተኛ የማትረባ በልና ና ከኔጋር!ሲፈን ሂጂ ይቅርታ በጣም!"አለ አብዲ ስለ ጓደኛው፡አዳም ይቅርታም ሳይጠይቅ እየተጎተተ ሄደ ሲፈን በአንድ በኩል ብቻ የወረደውን እንባዋን ጠረግ እያደረገች ወደ ኤዶም ሄደች ስትደርስ ኤዶም በትህግስት እየጠበቃት አገኘችው ስታየው እምባ እምባ አላት ግን ተቆጣጠረችው ኤዶም ተነስቶ ተቀበላ እናም ፊቷን ሲያየው ግን፡ደነገጠ ጠጋ አደረጋት የግራ ጉንጯ ላይ የታተመው ሰንበር ፈጧል ኤዶም ፊቱ ተቀያየረ ምንድ ነው ተርበተበተ ምን አደረጉብኝ?????

Открыть в Telegram
Просмотры977+7%к среднему
Пересылки4
Реакции17
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
12 ч452
27 ч692
72 ч977
  1. Через 24 часа692
  2. Всего сейчас977
#98266Фото

✨ ደስታ እንደ ቢራቢሮ ናት... 🦋 ደስታ ቢራቢሮ ብትሆን፣ ለመያዝ በሞከርን ቁጥር ከእጃችን የምትርቅ፤ ነገር ግን ፀጥ ብለን ስንቀመጥ በአጠገባችን ብልጭ ብላ የምትታይ ናት። 🦋 ደስተኛ ለመሆን ከሚረዱን መንገዶች አንዱ፣ ከአቅማችን በላይ በሆኑ ነገሮች ላይ መጨነቅን ማቆም ነው። እጅህ ላይ ያለው ካላስደሰተህ፣ ሊመጣ ያለውም ቢሆን ሙሉ በሙሉ ሊያረካህ እንደማይችል አስብ። በረሃ ላይ ያለችን አበባ ተመልክተህ መደሰት ካልቻልክ፣ የገነትን ውበት ብቻ በማሰብ ልብህን ማርካት አትችልም። የፍላጎትህን ስሌት ለጥቂት ጊዜ ወደ ጎን አድርገህ፣ ያለህን በምስጋና ተመልከት። 🌅 በንጋት ፀሐይ ሙቀት ተደሰት። ☀️ በቀኑ ብርሃን ተደሰት። 🌿 በነፃ በምትተነፍሰው ውድ አየር ተደሰት። ❤️ ደክመህ እንኳን ሳትደክም በምትሠራው ልብህ አመስግን። 🤝 በዙሪያህ ስላሉት ወገኖችና ወዳጆች አመስግን። 👁️ ይህንን ጽሑፍ ማንበብ ስላስቻለህ ዓይንህም አመስግን። በደንብ ስታስተውል፣ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ብዙ እንደሆነ ትረዳለህ። ያኔ ዕድለኛ መሆንህ ይሰማሃል፤ ያልጎደለብህንም ታውቃለህ። ያኔ አመስጋኝ ትሆናለህ። 💎 ደስታ ከውስጥ ይጀምራል! የአንተ አመለካከት ሲጠራ፣ ደስታህና ፊትህ እንደ ፀሐይ ያበራሉ። በቁሳዊ ነገሮች ላይ ያልተመሠረተ ደስታ ውስጥህን ይሞላዋል። ነገ ራሱ የብዙ ዛሬዎች ድምር ነውና፣ ለደስታህ ቀጠሮ አትያዝለት። ሁሉም ነገር ሲሟላልህ ደስተኛ እሆናለሁ ብለህ አትጠብቅ። የደስታህ ጊዜ አሁን ነው! 🌸 ━━━━━━━━━━━━━━ 💭 አናንተስ ዛሬ ደስተኛ እንድትሆኑ ያደረጋቹ ትንሽ ነገር ምንድን ነው? 👇 ሐሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን! 🔄 ለብዙ ሰው ተጀራሽ እንዲሆን ይህን መልዕክት አጋሩ። @atronosee

Открыть в Telegram
Просмотры965+6%к среднему
Пересылки5
Реакции23
Комментарии1
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
8 ч415
37 ч832
67 ч965
  1. Через 6 часов415
  2. Всего сейчас965
#98265Превью ссылки

​​"ሲፈን አስጠልቼሻለው!?አሁን ይህን ምን አመጣው አዳም! በፈጠረ ልታስወራኝ እንዳይሆን! አለች እንዳይጀምረኝ ብቻ እያለች በሆዷ ፀለየች "አይ ወደኔ አታይም ወሬዬም አይጥምሽም እሺ ምን ልሁን "አለ ድንገት አምልጦት "ምንድነው ምታወራው!? "አለች ሲፈን ኤዶም በዝምታ የሁለቱን ምልልስ ያዳምጥ ጀመር፡ "ታውቂያለሽ የማወራውን ለምንድነው የጠላሽኝ?" "መስሎህ ነው ማንንም የምጠላ ሰው አይደለውም አንተ በምትፈልገው መንገድ ግን ሊሆን አይችልም ይህን ደጋግሜ ነገሬሃለው  አዳም በፈጠረህ ድጋሚ አትጀምረኝ!" አለች ሲፈን ኮስተር ብላ አዳም እየሞተ ያለ መሰለው ከውስጡ የሆነ ነገር ሲጎድል ተሰማው "ሲፈን ወንድሜን እስካገኘሽበት ድረስ የነበረው ለኔ ያለሽ ስሜትስ የት ሄደ!" "አዳም እያለፍክ ነው! በዛ ሰአትም ቢሆን ልረዳህ ብቻ ነው የሞከርኩት ስራህን ትረሳዋለህ እንዴ? ይኽውልህ ከኔጋር መልካም የሆነ ግንኙነት እንዲኖረን ከፈለክ፡በውስጥህ የያስከውን አሳብ እርሳው፡በቃ" "አልቻልኩም !" "በቃህ ወንድሜ እኔን ሰው አላደረከኝም ለምንድነው የዚን ያክል እራስ ወዳድ የሆንከው? ነይ ሲፍ እንሂድ!"አለ ኤዶም በአዳም ተናዶ ሲፈን ቃላት ሳተነፍስ ተከተለችው እጇን ያዝ አደረጋት እጆቹ ይንቀጠቀጣሉ ሲፈን ተጨነቀች "ኤዶ የኔ ፍቅር አትናደድ ለጊዜው እልህ ስለያዘው ነው ይረሳኛል እሺ"አለችው ኤዶምን በስስት እያየችው ኤዶም አቀፋት፡ጭምቅ አደርጎ አዳም በቆመበት ደርቆ ቀረ ፍቅር ይሉንታውን አሳጥቶ አስቀባጥሮ አሳፍሮና አሸማቆ አስቀረው ከኋላ እያያቸው ከአይኖቹ እስኪርቁ ድረስ እንባ ባቀረሩ አይኖቹ ተከተላቸው ሲፈን አፈቅርሻለው ከልቤ ነው የፍቅርሽ ሀይል አቅሜን እያሳጣኝ ነው በትክክል ማሰብ አልቻልኩም የት ልሂድ ይህን ሁሉ የማላይበት፡የማልሰማበት ኧረ ጨነቀኝ ኤዶም ሲፈንን እንዳቀፈ ብዙ ነገር ማሰብ ጀመረ አዳም እውነት ከምሩ ነው ለሲፈን ያለው ፍቅር ወይስ ሲፈን እንደምትለው እልህ ይዞት ነው እልሁ በማን ነው በኔ ነው በሲፈን፡ምን ይሻላል"ሲፍ ታፈቅሪኛለሽ ከልብሽ?"አለ ኤዶም "ምን ማለት ነው ኤዶ ?!"ብላ ቆመች "አይ ካንቺ አፍ ሲወጣ ስለሚጣፍጠኝ ነው በዛላይ ወንድሜ አወዛግቦኛል ጨነቀኝ መሰለኝ!" "አትጨነቅ አዳም ይረሳኛል እሺ ኤዶ "ብላ ወገቡን አቀፈች "በጣም አፈቅርሻለው አንቺን ባጣ ምን እንደምሆን አላውቅም"ብሎ ከንፈሯን ጉርስ አደረገው  ሲፈን ከእግሯ ጀምሮ ነዘራት ወገቡን ጭምቅ አደረገችው መልሳ ቶሎ ተላቀቀችውና አካባቢዋን ቃኘች ፊቷ ቅልት አለ "ኤዶ ሰው ቢያየን ደስ አይልም፡በየመንገዱ መሳሳም እንደማልወድ ነግሬሃለው እንዳትደግመው"አለች ሲፈን ድንገት የተፈጠረባት የስሜት ወጀብ ስርሃት እያስያዘች "ይቅርታ አንዳንዴ አጠገቤ ስቶኚ ልቆጣጠረው የማልችለው ስሜት ወዳንቺ ይገፋኛል የኔ ቆንጆ ስስቴ ነሽ"አለ ኤዶም እቅፍ አድርጓት መንገዱን እየቀጠለ "አውቃለው የኔ ፍቅር ግን እኛ ኢትዮጲያዊ ነን በየመንገዱ የመሳሳም ባህል የፈረንሳዮች ነው እሺ "ብላ ፈገግ አለች ሲፈን "እሺ የኔ አስተዋይ፡አይደገምም"አለ ኤዶም አዳም መሬቱ ላይ ቁጢጥ ብሎ ተቀምጦ በስንጥር ይጫጭራል፡በሀሳቡ ግን የሲፈን ገፅታ የአወራሯ ሁኔታ እየመጣ ድቅን ይልበታል፡እንደመሳቅ አለ በራሱ ላይ እእ ለካ ፍቅር ይህ ነው ወይኔ አዳም ..... ❗️አንብበው ሲጨርሱ 👍 እንዳይረሳ ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ። 👇Sebscribe YouTube link👇 https://www.youtube.com/@atronose

Открыть в Telegram
Просмотры882−3%к среднему
Пересылки2
Реакции60
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
4 ч303
19 ч601
33 ч734
78 ч882
  1. Через 6 часов303
  2. Через 24 часа601
  3. Всего сейчас882
#98264Текст

#ባለ_ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ስድስት ፡ ፡ ...አዳም ከልቡ ከራሱ ጋር አልነበረም ደመነፍሱን ነው ያለው አጠገቡ ሆኖ እንኳ አብዲንም ጭምር እርስት አድርጎ እርቆ ይሄዳል ሰሞኑን በተለይ ኤዶም፡ሲፈንን ይዞ ከከተማ መውጣት ትልቅ እራስምታት ሆኖበታል ተጎድቷል በጣም ከመደበሩ የተነሳ ዝምብሎ ሲተኛ ነበር የሚውለው ዛሬም አብዲ እንገናኝ ባይለው፡መውጣት አልፈለገም "አብዲ እሺ ምንድነው ነገሩ ?" "የሲፈን አባት ... "የሲፈን አባት ምን?" "በጉዳዩ እንዳሉበት አቶ ይርጋ ተናገሩ!" "ኪኪኪአንተ ልጅ እና ምን ይገርማል ይህን እንዴት መገመት ያቅትሃል አየህ አባትህን እና እኔን ችግር ውስጥ ለመክተት አቶ ይርጋ ምንም ምክንያት የላቸውም እራሳቸውን በተመለከተ የሳቸው መሪ ተዋናይ አቶ ይፍሩ ናቸው በቃ እንዴት ይሄ ይጠፋሃል!አብዲ አትናደድ አውቃለው ለዚሁሉ ነገር መፈጠር ምክንያት እኔ ነኝ ነገር ግን አሁን ላይ ባይሆንም በሚሰሩት ሕገወጥ ስራ እርስ በእርሳቸው የሆነ ሰአት ላይ መወነጃጀላቸው አይቀርም ነበር አዝናለው ስለ አባትህ እድሜ ልኬን የምፀፀትበት ጉዳይ ነው !"አለ አዳም በቁጭት "አዳም አውቃለው አቶ ይፍሩ እጃቸው እንዳለበት ነገርግን አቶ ይርጋ ለአባቴ ሞት ተጠያቂ ነው እሱ ሰውዬ ምን ያክል የኔን ሆድ እንኳ በአንተና በአቶ ይፍሩ ላይ ነገር እያወሳሰበ እያገነኛኘ ለማሻከር አንዴ ቤቴ አንዴ ሱቅ ድረስ በመምጣት ጥረት እንዳረገ ታውቃለህ ስለዚ አቶ ይፍሩ ተባባሪ ቢሆኑም የእቅዱ ባለቤት ግን አቶ ይርጋ ነው !"አለአብዲ በእልህ፡ጥርሱን እየነከሰ "በርግጥ ልክ ነህ !እሺ እና አሁን ምን ልታረግ ነው?" "ስለመጋዘኑ አውቃለው እነሱም ልብ ያላሉት ነገር ይሄንን ነው ሰሞኑን የገባ እቃ አለ ጊዜው ያለፈበት የታሸጉ ምግቦች በብዛት እንዲሁም ሌሎች ሌሎች፡ያለፈባቸው መዳኒቶች እናም እሱን ለመርማሪው አስረድቼ እጅ ከፍንጅ እንዲያዙ አደርጋለው እነሱ የአንድ ሰው  ሳይሆን የብዙ ሰዎችን ነብስ የበሉ መሆናቸውን አጋልጣለው፡አባቴም ቢሆን ይቅር ይበለው መጨረሻው አላማረም ያው የፈጣሪ ስራ ነው እናም እነሱም ቅጣታቸውን ይቀበሏታል በቃ!"አለ አብዲ "እርግጠኛነህ አብዲ? "አዎ አዳም መሆን ያለበት ይህ ነው በፍፁም በቀላል እስር እንዲቀጡ አላደርግም በተደራራቢ ጥፋት ወንጀል እስርቤት ባይማቅቋት እኔ አብዲ አደለውም!!" "እሺ እንዳልክ እራስህን ጠብቅ ግን ሚስጢር አድርገው" "አደርገዋለው እሺ የሲፈን ጉዳይስ እንዴት ነው ማለት እንዴት ብላ ነው ስለ አባቷ ሀጥያት መቀበል የምትችለው? ሰሞኑ አላገኘሃትም?" "እእ እኔ እንጃ እእ እሷ ..." "እሷ ምን?ምን ሆነች ችግር አለ አዳም? "አዎ ከኤዶም ጋር ከከተማ ውጪ ተዝናንተው አድረው መጡ!"አለ አዳም ቃላቱ እየከበደው "ኦኬ ይሄነው ችግሩ ኧረ አዳም ይሄ ነገር ወዴት እያመራ ነው?በወንድምህ ላይ እያቄምክ ነው እንዴ?ኧረ ተው ምን ነካህ ፍቅር እኮ ለሌሎች ማሰብ የሌላውን ሰው እውነት ማክበር ነው የሌላውን ደስታ መጠበቅም ጭምር ነው፡ሲፈንን ከወደድካት የምትወደውን፡እንድታደርግ ዕድል ስጣት በማስገደድ የሚሆን አንዳች ነገር የለም በዛላይ ኤዶም ማለት ግማሽ አንተ ነህ አስበው በሕይወቱ አንዲት ሴት መቅረቡ ነው አንተ በሴት ጉዳይ ላይ ብዙ ልምድ አለህ መውጫውን አታጣውም ነገሮችን ለማርገብ ከሱ ይልቅ ላንተ ይቀልሃል በዛላይ ሲፈን ልቧ ለሱ ካደላ ምን ማድረግ ትችላለህ ለመተው ሞክር መልካም ጓደኝነቷን አስብ በቃ!"አለ አብዲ በጓደኛው ተጨንቆ "አብዲ አልቻልኩም ...ልቤን ተው ማለት አልቻልኩም....ሲፈንን ማሰብ የጀመርኩት ከሱ በፊት ነው ....ሆስፒታል አስገብታኝ ያዳነችኝ ሰሞን...ከሰመመን ነቅቼ ያየዋት ሰሞን.....እሷናት ሕይወትህን ያተረፈችልህ ብሎ ደክተሩ ያስተዋወቀኝ ሰሞን....ባለጭንብሉ ልጅ ነቅተሃል ለማስታወስ ሞክር እያለችኝ ስትወተውተኝ የነበረ ሰሞን....!አብዲ ድንገት አደለም ልቤውስጥ የገባችው ...በድንገት ላወጣት አልችልም በድንገት ያፈቀራት ወንድሜ ነው!" "አሃ ምን እያልክ ነው እና ኤዶምን ተዋት እባክህ ለኔ ስትል ልትለው ነው? ኧረ አዳም ምንሆነሃል?"አለ አብዲ ደስ ባላለው ስሜት "አብዲ እራስ ወዳድ በለኝ የፈለገህን በለኝ በቃ ስሜቴን ነው እየነገርኩ ያለሁት አፈቅራታለው ፍቅርህን ለማንም ለምንም ብለ መተው አትችልም አቅም የለኝም አቅቶኛል አልቻልኩም አፈቅራታለሁ.....!" "አይ እንግዲ ይሄ ለኔ ብቻ የምትለው ነገር አይመቸኝም እኔ ዞሮዞሮ ውሳኔው ያንተም የኤዶምም አይደለም የሲፈን እንጂ በቃ የሷ ብቻ እና እንዳየነው ደሞ መርጣለች። ማስገደድ አትችልም አለቀ !አሁን ተነስ እንሂድ ብዙ ቆየን"አለ አብዲ እየተሰላቸ ደስ አላለውም በሁለት ወንድማማቾች የሚፈጠረው ፀብ እየታየው ምን አይነት ዓለም ነው? ግራ የገባው ========                              ...አዳም ከአብዲ እንደተለየ ወደ ቤቱ ነው የሄደው መንፈሱ ስብር እንዳለ ከመሬቱ ላይ አንዳች  ነገር ጠብ ይልለት ይመስል አንገቱን እንዳቀረቀረ ነበር የሚጓዘው ማንንም ለማየትም ሆነ ለማናገር ምንም ፍላጎት አይታይበትም ቤታቸው አካባቢ ሲደርስ ግን ድንገት ቀና አለ እናም በርቀት እናቱን ወንድሙን እንዲሁም፡አንዲት ሴት ቆመው አየ  ለማጣራት ሞከረ እናትየው እጃቸውን ለሰላምታ ዘረጉላት ለሴቲቱ ወንድምየው እጁን ከትከሻዋላይ አሳረፈው አሁን ገባው አዎ የቆሙት ከሲፈን ጋር ነው አዳም እርምጃውን በመግታት አንድ ጥግ ይዞ ቆመ ልቡ ፍስስስ አለችበት የፍቅር ስሜቱ አየለበት እዛው ባለበት ሆኖ መጮህ አማረው በቅናት ተቃጠለ በቀኝ እጁ ሆዱን ጭምቅ አደረገው እንዴት ነው የምችለው ኧረ ፈጣሪዬ እርዳኝ ይሄንን ስሜት አጥፋልኝ እባክህ ካልሆነ ብዙ ነገረ ነው የሚጠፋው ውስጤ የሚቀጣጠለውን የፍቅር እሳት አንተ አዳፍንልኝ ጌታዬ አልቻልኩም በርቀት እናትዬው ሲፈንን ተሰናብተው ወደ ጊቢያቸው ሲገቡ አየ ቀጥሎ ኤዶምና ሲፈን፡እየተላፉ እየተቃቀፉ ወደሱው አቅጣጫ ሲመጡ ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ገባው ወደዋላ ለመመለስ አሰበ እንዳላየ ለመሆንም ፈለገ ግን አልቻለም፡ሲፈን ናፍቃዋለች ሊያያት ፈለገ ፡እዛው በቆመበት ፈዞ ቀረ እነሱም እየቀረቡ መጡ መጀመሪያ ያየችው ሲፈን ነበረች እናም ድንግጥ ብላ ለኤዶም አሳየችው ኤዶም ሲያየው ተረበሸ ደሞ እዚ ምን የሚያስቆመው ነገር አገኘ ድጋሚ ከነታዲዮስ ጋር ገጥሞ እንዳይሆን ብቻ እነሱ እንደሆን የወንድሜን ሀይለኝነት ተጠቅመው የአሳባቸውን ለመፈፀም ነው ሁሌም የሚጥሩት በነሱ ምክንያት ነው አንድ ሰሞን በለሊት እየወጣ ችግር ሲፈጥር የነበረው ብቻ እኔ አይመቹኝም፡አሁን ደሞ፡ለምን፡............. "እህ ወንድሜ ምን ታረጋለህ እዚ?"አለ ኤዶም በጥርጣሬ "እእ ...ምንም ዝምብዬ ነው የቆምኩት"አለ አዳም ወደሲፈን እያየ ሲፈን ሲያፈጥባት አይኖቹን መቋቋም አቃታት ፊቷን ወደሌላ አቅጣጫ አዞረች "ግን እዚ መቆም ያለብህ አይመስለኝም ደሞ ሰፈር ከደረስክ ወዲያ ወደቤት አትገባም?"አለ ኤዶም "እእ አይ ሰው እየጠበኩ ነው" "ታዲዮስን እንዳይሆን ብቻ!"አለ ኤዶም፡ "አደለም ሲሲፈን ...ምምነው ዝም አልሽ የዚን ያህል አስጠልቼሻለው ?"አለት በቅሬታ ወደሷው እያየ ኤዶም የወሬው መቀየር አስፈራው ሲፈን ወደ አዳም ዞራ አስተዋለችው አስተያየቱ አስጨነቃት ምን እንደምትል ግራ ገባት አዳም ተለውጧል ፊቱ ከሳ ገርጣ ብሏል አይኖቹ ወደውስጥ የገቡም መሰላት ከንፈሮቹ ደርቀዋል ቃላቶቹም ተዳክመዋል፡እርብሽ አለች

Открыть в Telegram
Просмотры957+5%к среднему
Пересылки5
Реакции19
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
4 ч295
19 ч590
33 ч737
78 ч957
  1. Через 6 часов295
  2. Через 24 часа590
  3. Всего сейчас957
#98263Превью ссылки

​​"ላንተ መንገር አለብኝ እንዴ ?!" "ንገሪኛ የእውነትሽን ከሆ!" "ከኤዶም ጋር የምንሄድበት ቦታ አለ ከከተማ ልንወጣ አስበናል አዝናለው አዳም ያው የነገርኩህ መስማትህ አይቀርም ብዬ ነው ባይሆን በስልክ የማትነግረኝ ከሆነ ስመለስ ነገ ..." "ምን አልሽ እንዴት ነው ከሰአት በዋላ ከከተማ ውጪ !አዳር ነው እንዴ!"አዳም ተቆጣ "አይመለከትህም እንድትጮህብኝ ፍቃድ አልሰጠውህም ደሞ ደናደር!"ብላ ስልኩን ጆሮው ላይ ዘጋችው አዳም አበደ ደግሞ ደወለ ይጠራል አታነሳም ደጋገመ በመጨረሻ ከአገልግሎት መሰጫ ክልል ውጪ ሆነ ስልኳ አዳም ተንቀጠቀጠ የፍቅር እንባ አይኖቹ አቀረሩ እራሱን ጠላ ውስጡ ተሰቃየበት ጥላቻዋ ተሰማው ሲፈን አሳመምሺኝ አሳመምሺኝ እእእእእእ..... ====== ደስ የሚል የፍቅር ሕይወት፡እያጣጣመነው ኤዶም አሳቡ ሁሉ አንድና አንድ ሰው ላይ ሆኗል ሲፈን ሲፈን ሲፈን አብራው ስትሆን ልቡ በሀሴት ይሞላል ስለፍቅር ያዜማል ስለፍቅር ይሰብካል ስለፍቅር ቃላትን ያስውባል በእውነት ስለእውነት ፍቅርን ከላይ ከላይ ሳይሆን ከልቡ ይሆንበታል ደስታን ሰቶ ደስታን ይቀበላል ሁሌም ለወንድሙ ይፀልያል ሲፈንን ከልቡ እንዲያወጣለት መርሳት እንዲችል እና የሁለቱን ግንኙነት በሰላም እንዲቀበል ኤዶም በፍቅሩ በሲፈን ምንም ጥርጥር የለውም የሱ ፍርሃት ወንድሙ ብቻ ነው እኔ ያልኩት ካልሆነ ባዩ አይለኛና፡ንዴተኛ ወንድሙ ነው ችግሩ ===== ካፌው በሰው ስለተጣበበ በረንዳው ላይ ለመቀመጥ አዳም ወደአንድ ጥግ እየሄደ ጓደኛውን፡አብዲን እንዲከተለው ጋበዘ ፡አስተናጋጁ ጠረቤዛው አጠገብ ያለው ወንበር አንድ መሆኑን አስተውሎ ተጨማሪ ለማምጣት፡ተጣደፈ አብዲ እየተከተለው "የዚ ቤት ገበያ ምሳ ሰአት ላይ ነው፡መቼም ይሄ ሁሉ ለቡናቸው ነው!"አለ "አሃ ማኪያቶ አቸውም አሪፍ ነው ደንበኛ መያዝ ያውቁበታል አግባብ ያለው ስራ መስራት እንግዲ ትርፍ አለው ደንበኛ ማፍራቱ ሲያልፍ የተጠቃሚ የእርካታ ምስጋና ቀላል አይደለም እያለ ወንበሯን ሳብ አድርጎ ተቀመጠ አብዲ እንደመሳቅ ብሎ "አጅሬ ትንሽ እንኳ ተቀመጥ ብለህ አታግደረድረኝም በቃ ጉብ ነው!"አለው አዳም ቀናብሎ እያየው "ያው ከመጣህ ቆመህ እንደማትቀር ስለማውቅ ነው" ብሎ ሳቀ...አብዲ ወንበር ይዞለት የመጣውን አስተናጋጁን አመስግኖ እየተቀመጠ "ተናግረህ ሞተሃል"አለው ከነሱ ቲንሽ ፈቀቅ ብሎ ሦስት ጎረምሶች ቁጭ ብለው ማኪያቶ አቸውን እየጠጡ..ያስካካሉ አብዲ ሁከት ባይመቸውም ቤቱ ስለተጨናነቀ ለመታገስ ሞከረ ደሞ ያው ቀስ እያለ መቀነሳቸው አይቀርምብሎም አሰበ አዳም ከልቡ ከራሱጋር አልነበረም ደመነፍሱን ነው ያለው አጠገቡ ሆኖ እንኳ አብዲንም ጭምር እርስት አድርጎ እርቆ ይሄዳል ሰሞኑን በተለይ ኤዶም ሲፈንን ይዞ ከከተማ መውጣት ትልቅ እራስምታት ሆኖበታል ተጎድቶሃል፡በጣም ከመደበሩ የተነሳ ዝምብሎ ሲተኛ ነበር የሚውለው ዛሬም፡አብዲ እንገናኝ ባይለው፡መውጣት አልፈለገም አንብቦ የጨረሰ ቢያንስ reactions እየሰጣቹ❤️ ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ። 👇Sebscribe YouTube link👇 https://www.youtube.com/@atronose

Открыть в Telegram
Просмотры992+9%к среднему
Пересылки2
Реакции98
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
14 ч518
29 ч815
73 ч992
  1. Через 24 часа815
  2. Всего сейчас992
#98262Текст

#ባለ_ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አምስት ፡ ፡ ...ነገሮች አንዳንዴ ከግምትህ ውጭ ሲሆኑ ለሕይወት ያለህ አመለካከት ባዶ ይሆንና በምድረበዳ ላይ ብቻህን የምትዳክር በጨለማ ውስጥ ብቻህን የምትደናበር ይመስልሃል የአንድ ከልብህ የምትወደው ሰው ጥላቻ ዓለም ሁሉ የጠላህ እስኪመስልህ ድረስ ይሰማሃል!! አዳም ብቻውን እንደተጣለ ሰው ይሰማው ጀምሯል ውስጡ ሰላም አጥቷል ነገሮች ሊያሳብዱት ደርሰዋል ዘግይቶአል በጣም ዘግይቷል በሲፈን ጉዳይ ላይ  አዎ የዚህን ያክል እንዳፈቀራት ያወቀው በገዛ መንትያ ወንድሙ ፍቅር ስትሳብ ነው በተለይ በሰሞኑ የኤዶም የግድያ ሙከራን ተከትሎ የመጣው የሲፈንና የወንድሙ ቅርበት ጤና ነስቶታል እውነቱን ለመቀበል አቅቶታል ኩራቱን አስጥሎ ያለ ይሉኝታ ባደባባይ እንዲያወራ አድርጎታል ጓደኞቹ እንኳ እስኪታዘቡት በወንድሙ መናደዱን አሳውቋል የፍቅር ሀይል ለብቻው ያስቀዋል እንደ ተነካ ሰው ያስለቅሰዋል ያበሳጨዋል ያነጫንጨዋል ያስቆጣዋል ብቻ የሚያረገውን አሳጥቶታል አዳም ከተለያዩ ሴቶች የፍቅር ጥያቄዎች ቀርበውለት ያውቃል አንዳንዶቹን በግዴለሽነት አብሯቸው ሆኖም፡ያውቃል ዛሬ ነው ምንያክል ማፍቀር እንደሚጎዳ የተረዳው፡እያንዳንዳቸውን ተፈጥሮ በለገሰችው ውበት ተመክቶ ተመፃድቆባቸዋል በዕንባቸው አሹፏል ቅጣቱ ክፉኛ እየደረሰው እንደሆነ ተሰማው የለም ያለው፡ፍቅር አለው ብሎ መጥቷል ግን አታገኘኝም  ያለውም ይመስለዋል፡ አዳም ተሰቃየ ! ========= አብዲ እንደ እብድ እያደረገው ብቻውን እያወራ እየተበሳጨ እያለቀሰም ጭምር ጥድፍ ጥድፍ እያለ አዳምን ሊያገኘው ወደቤታቸው ይገሰግሳል ቀጥታ የመጣው ከፖሊስ ጣቢያ ነው መርማሪው ላግኝህ ባለው መሰረት አግኝቶት ነበር እናም ባባቱ ግድያ  እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩት ሁለቱ ወጠምሻ ፡ጎረምሶች ተይዘው ከስንት የምርመራ ስልት በዋላ ኤዶምን ለመግደል ሙከራ ከማድረጋቸውም ባሻገር የአቶ የሱፍም ገዳይ እንደሆኑ ቃላቸውን፡ሰጥተው ትዕዛዝ ይቀበሉ የነበረው፡ግን ከአቶ ይርጋ መሆኑን ገልፀው መናገራቸውን ነበር ያሳወቀው አብዲ አብዲ አቶይርጋን ማመን ቢያቅተውም እንዲ እውነታውን ሲያውቅ ግን አዞረው የሰውልጅ የክፋት መጠን ከፍ ብሎታየው፡ እንዴት አባቴን እንዴት ጓደኛውን፡ለምን በምን ወይኔ የሰውልጅ ክፋት ከአስፈሪም አውሬ ይበልጣል አውሬስ የሚገድልህ የሆዱን እርሃብ ሊያስታግስብህ ነው የሰው ልጅ ሲከፋ ግን ላይበላህ ያርድሃል ይገድልሃል ወይኔ አባቴን ብቻህን፡አገኙህ ወይኔ እያለ አብዲ ዳግም፡እንደአዲስ ለአባቱ እያለቀሰ ወደአዳም ፈጠነ እስኪነግረው ጨንቆታል አባቴ በገዛ ጓደኛው ወይኔ.... ========== ሲፈን ከእህቶቿጋር እየተሳሳቀች ምሳ ላይ ተሰይማለች እሁድ እሁድ ቡዙ ጊዜ አንድ ላይ ሰብሰብ ማለቱን ለምደውታል እቤት እንኳን ባይሆን ተያይዘው ይወጣሉ እንጂ ብቻለብቻ ብሎ ነገር የለም በፍቃድ ካልሆነ እሱንም ለሮዛ ነው እንደታላቅነቷ አንዳንድ ጉዳይ ይኖራታል ተብሎ ስለሚታሰብ በተረፈ ከእናትና ከአባታቸው ጋር ነው በደስታ የሚያሳልፉት "እማ አባቢስ ዛሬ ወጥቷል ወይስ ምንድነው አላየሁትም?"ሊያ ነበረች ችኩል ችኩል እያለች የጠየቀችው "ተኝቶ ይሆናል ማታስ መች በጊዜ ገባ!"አለች ሲፈን ወደእናቷ እያየች እራሄል ፈገግ አለች እናም "ውይ ማሚ ቺክ ምናምን ጠብሶ ይሆን እንዴ?"ስትል ሁሉም ሳቁ እናት "አንዳች ይጥበስሽ!"ብለው አብረው ሳቁ እና አባታቹ በለሊት ነው የወጣው የሆነ ስራ አለብኝ ብሏል አላውቅም የሱ ስራ ብዙ ነው!'አሉ አንድ ጉርሻ ጠቅልለው፡ወደ ሊያ እየዘረጉ  ሊያ አፋን ከፍታ ተቀበለች  ሲፈን ለእናቷ ማስጠንቀቂያ ሰጠች "እማ ይቺ ልጅ ጉርሻ ለምዳ ሁሌም ከሰው ጠባቂ አድርገሽ እንዳታስቀሪያት እንደዚ አይነት ነገር ተፅህኖ ያሳድራል ጥሩ አደለም፡!"አለች እህቶቿ በመስማማት አነገታቸውን ነቀነቁ ሊያ እንደመናደድ አለች "አይ እንግዲ ከኔ ከናቷ ጎረሰችና ምን እንዳይመጣ ነው?አንቺ ደሞ ሁሌ አንዱን ነገር ከአንዱ ማዛመድ ትወጃለሽ በተለይ በዚች ልጅ ላይ!. አሉ በቅሬታ ሊያ ደስስ አላት ሲፈን እናቷን ኮስተር ብላ አየች ሮዛ ጣልቃ ገባች "እማዬ..እማዬ ተይ እንጂ የእናት ፍቅር ሆኖብሽ እንጂ ሲፈን ለማለት የፈለገችው ጠፍቶሽ አደለም መቼም ለዚች ትንሽ ልጅም የልብልብ አትስጫት ታውቂያለሽ፡ትንሽ ለቀቅ ስናደረጋት አገር እንደምትገዛ አደል እንዴ ትንሿ ፡ሁላችንም እንወድሻለን ስስታችን ነሽ ነገርግን አንዳንዴ መስተካከል ያለበት ጉዳይ ካለ ለማስተካከል፡ትንሽ ቁንጥጫ እንጠቀማለን፡ይህ ደሞ አንቺን ይጠቅምሻል እሺ ሆዴ ደሞ አብዝቶ ጎርሻ መውደድ ጥሩ አይደለም አጉራሽ የታጣቀን ስለሚቸግር !"አለች እሮዛ "አሃ እናቴን መቼም አላጣትም እሺ!"አለች ሊያ "እንደዛ ለማለት ሳይሆን ይህ የመስጠትና የመቀበል ልምድ ይፈጥራል ባንቺላይ ተፅህኖ ሊፈጥር ይችላል ነው አሳቡ ለማጠቃለል ያህል"አለች እራሄል ክርክሩ እንዲቆም በመፈለግ "እሺ እህቶቼ፡አመሰግናለው ስለ ቁርቆራቹ !"አለች እንደማሾፍ ብላ ሦስቱም ኮስተር አሉባት ፊታቸውን አይታ ሊያ ዝም አለች በሩ የሳሎኑ እንደ መከፈት ሲል እናት ቀና አሉ አቶ ይፍሩ ነበሩ ሁሉም ኖር ብለው ተነሱ አባት በዝጌር ብለው ገብተው ወንበር ስበው እየተቀመጡ፡በድካም መንፈስ እንደሆኑ "ስንቴ ነው ከምግብ ላይ አትነሱ ብዬ የምናገረው!"አሉ ሚስት ምግቡን ወደፊታቸው ጠጋ እያደረጉ"የሄድክበት ጉዳይ ተሳካልህ "አሉ "እእ አዎ ምንም አይል"አሉ በተሰላቸ መንፈስ አሳብ ገብቷቸዋል ከትላንት ጀምሮ ጤና አላገኙም በተለይ አቶ ይርጋ ፖሊስ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብለው በዛው መቅረት አስጨንቋቸው ነበር ካሁን አሁን በኔስ ምን ይፈጠር ይሆን እያሉ ነበር ያደሩት ዛሬም እዛው እንዳሳደሯቸውና እነዳለቀቋቸው በመስማታቸው ተደናግጠዋል ፈርተዋል በጣም ወይ ልጆቼ ጉድ ላመጣባቸው ነው ልጆቼ አበቦቼ ጌጦቼ አሂሂሂሂሂ. የሲፈን ስልክ ሲጮህ ሁሉም ብንን ያሉ መሰሉ ሲፈን ተነስታ ወደስልኳ ሄደች ሊያ ይሄን ድምፅ መቀነስ እንድትችዪ ልርዳሽ እህቴ በጣም፡ይጮሃል "አለች "አመሰግናለሁ በራሴ አደርገዋለው"ብላ ስልኳን ይዛ ወጣች  ሊያ ቆየብሽ!"አለች፡ሮዛ ታላቅ ይከበር እሺ!"አለች ሲፈን ስልኩን ስታየው አዳም ይላል ለማንሳት ዘገየች እራሷን እንደምንም አረጋግታ አነሳች "ሄሄሎ" "አቤት " "ሲፈን እኔ ነኝ አዳም" "አይቼዋለው እሺ አዳም ሰላም ነህ?" "ሰላም ነኝ ካንቺ ናፍቆት በቀር!" "እሺ" "እሺ ነው የሚባለው?" "ምን እንድል ጠበክ ይቅርታ አዳም ልትጨቃጨቀኝ ከሆነ አታድርገው እባክህ?" "ኧረ እንደዛ አደለም እኔ ላወራሽ ስለፈለኩ ነው እህ ሲፈን ንገሪኝ፡ምምን ላድርግ በፍፁም እረፍት ማግኘት አልቻልኩም!" "ስለምኑ ?!" "ሲፈን እባክሽ ግራ ገባኝ ባዶ የሆንኩ ያህል ይሰማኛል አልቻልኩም አንቺን መተው ሞክሪያለው ግን አልሆን አለኝ፡እወድሻለው ሲፈን!" "ተነጋግረን የጨረስን መስሎኝ ፡አዳም እርሳኝ አንተ ከኔ ፍቅር፡አልያዘህም እልህ እንጂ ተወኝ በቃ ተወኝ!" ሲፈን በፈጠረሽ ተረጂኝ በጣም እፈልግሻለው ፕሊስ እናውራ ላግኝሽና ዛሬ በዛውም ስለ አብዲ አባት አቶ የሱፍ ገዳይ ማንነት የታወቀ ይመስለኛል ስለሱና ስሌሎች ጉዳዮች በሰፊው እንድናወራ እንገናኝ እባክሽ!" አለ ሊያገኛት ስለፈለገ  በአብዲም አሳበበ "ምን ተገኘ ገዳዩ ?! ከሆነ አሁን ንገረኝ!"አለች ሲፈን ድንግጥ ብላ ተደስታም ጭምር "አይ መገናኘት አለብን" "መገናኘቱን እንኳን እርሳው በዋላ ቀጠሮ አለብኝ አልችልም " "የት ትሄጃለሽ ሲፈን "

Открыть в Telegram
Просмотры1 004+10%к среднему
Пересылки4
Реакции21
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
14 ч502
29 ч792
73 ч1 004
  1. Через 24 часа792
  2. Всего сейчас1 004
#98261Текст

🕯️ከ150 ዓመት በኋላ 📍 ከ150 ዓመት በኋላ ዛሬ በሕይወት ካሉት ሰዎች መካከል አንዳችንም በዚህ ምድር ላይ አንገኝም ዛሬ ለምንታገልላቸውና እጅግ ዋጋ ለምንሰጣቸው ነገሮች አብዛኞቹ በዚያን ጊዜ ይረሳሉ ይጠፋሉም። 🕯️ ሆኖም ዛሬ ለእኛ ትልቅ ጉዳይ የሆኑት ነገሮች በወቅቱ ለሰው ልጅ የሞትና የሕይወት ያህል አስፈላጊ ነበሩ ጤናችንን እንኳን እንመልከት ዛሬ የዘረጋነውን እጃችንን ነገ ማጠፍ ሊያቅተን ይችላል በሀብታችን በእውቀታችንና በዝናችን መመካት ከንቱ ነው፤ የዘረጋነውን እጃችንን እንኳን የምናጥፈው በፈጣሪ ቸርነት ነው 💡የታላቁ እስክንድር ታሪክ በብዙ ቦታ የሚነገር ታሪክ እንዲህ ይላል ታላቁ እስክንድር ወደ ሞት አፋፍ መቃረቡን ሲያውቅ ወዳጆቹን ሰብስቦ «ስትቀብሩኝ እጆቼን ከሬሳዬ ውጭ አድርጋችሁ ቅበሩኝ» አላቸው። ምክንያቱን ሲጠይቁትም «ከዚህ ዓለም ስሄድ ምንም ይዤ እንደማልሄድ ሰዎች እንዲያዩ ነው» ብሎ መለሰ ይባላል የታሪኩ መልዕክት ግልጽ ነው ሰው ምንም ያህል ሀብትና ሥልጣን ቢኖረው በመጨረሻ ባዶ እጁን ይሄዳል። 🔷 ዓለም አላፊ ናት በዚህ አላፊ ዓለም መጥፊያው ሰፊ መልሚያው ጠባብ በሆነው ኑሮ በዙፋን ላይ ካለ ንጉሥ ይልቅ በፈጣሪው የታመነ አማኝ ይበልጣል የዓለምን አላፊነት ብዙ እያየንም እንኳን ከእሱ መማር ይሳነናል ብዙ እናነባለን ብዙ እናውቃለን ሆኖም ይህች ዓለም ዘላለማዊ መኖሪያችን እንዳልሆነች እንዘነጋለን 📍 ማጠቃለያ ሕይወትን ቀለል አድርገን እንኑር ከማንም ጋር መወዳደርና ከሌሎች በልጠን ለመታየት መጣር የሕይወት ዓላማ አይደለም ስለዚህ ❤️ ፍቅር ይግዛን 🤝 መከባበርን እናስቀድም 🕊️ ይቅርታን እንለማመድ 🚫 መጠላለፍን ከጀርባ መወጋጋትንና በቅናት መኖርን እንተው ኑሮ በውልደትና በሞት መካከል ያለ አጭር ጉዞ ነው በድንገት ተጀምሮ በማይታወቅ ሰዓት የሚያበቃ 📖 ቃሉም እንዲህ ይላል «ሕይወታችሁ ምንድን ናት? ጥቂት ጊዜ ታይታ ኋላ እንደምትጠፋ እንፋሎት ናችሁና» ያዕቆብ 4፥14 📜 ሐዲሱም እንዲህ ይመክራል «በዚህ ዓለም እንደ እንግዳ ወይም እንደ መንገደኛ ሁን» ነቢዩ ሙሐመድ 🤲 ፈጣሪ መልካም ሥራን እንድንሠራ ልባችንንም ከከንቱ ኩራትና ከጥላቻ እንዲያጸዳ ይርዳን  አሜን። @atronosee

Открыть в Telegram
Просмотры1 061+16%к среднему
Пересылки4
Реакции19
Комментарии1
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
12 ч580
27 ч812
70 ч1 061
  1. Через 24 часа812
  2. Всего сейчас1 061
#98260Фото
Просмотры966+6%к среднему
Пересылки0
Реакции—
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
12 ч483
27 ч697
70 ч966
  1. Через 24 часа697
  2. Всего сейчас966
#98257Текст
Просмотры1 011+11%к среднему
Пересылки3
Реакции23
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
9 ч286
37 ч828
66 ч1 011
  1. Всего сейчас1 011
#98256Текст
Просмотры981+8%к среднему
Пересылки1
Реакции13
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
9 ч376
38 ч810
67 ч981
  1. Всего сейчас981
#98254Превью ссылки

​​ዛሬ አዳምና አብዲ እዛች በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው የአቶ ይርጋና የአቶ ይፍሩን የእውነት የሚመስል የውሸት ጓደኝነት አስተውለዋል፡ሁለቱም እዚ ቤት መምጣት ከጀመሩ ሦስት ቀን ሆኗቸዋል፡ይህንም የሚያደርጉት ሆን ብለው፡ነው እነ አቶ ይፍሩ ያጫሩባቸውን፡ጥርጣሬ እየተከታተሉ ለማጥራት በማሰብ! አዳም ከቤት ሲወጣ በንዴት ቢሆንም አብዲን ድጋሚ ሊያገኘው የፈለገው ግን እነ አቶ ይፍሩ የሚጠቀሙበት ግሮሰሪ ነው፡ያን ያክል ድባቡ የሚመች፡ባይሆንም ለአላማቸው ሲሉ ነበር እየሄዱ በጊዜ በረንዳላይ መሰየም የጀመሩት አብዲ እንደ አባቱ መጠጥ ባይጠጣም ውሃ ወይም ለስላሳ ይዞ ከአዳም ጋር ሲጫወት ይቆያል መንገድ ዳር በመሆኑ ምክንያት አልፎ አልፎ የሰፈራቸው ሰዎችም ከታክሲ ወርደው ወደ ቤታቸው ለመግባት ሲጣደፉ ያዩአቸዋል አዳም ሦስተኛ ቢራውን ሲደግም አብዲ ቆጣ አለ "ምንድነው አረጋጋው እንጂ ሰአቱ ገና እኮ ነው !"አለው "ባክህ ጠጣ ትንሽ ያለዛ ድብርቱ አይለቀኝም ስለነሱ ማሰብ አልችልም!"አለ አሁንም በወንድሙ እና በሲፈን አሳብ እንደተወጠረ ነው "ኧረባክህ መጠጣት መፍትሄ አያመጣም ይልቅ እኔን ያሳሰበኝ፡ነገር አለ እእ..."አለ አብዲ "ምንድነው ?"አለ አዳም እያስተዋለው "ማለት የአንተ ሲፈንን መቅረብ ያሳስበኛል!" "አልገባኝም !ለምን?"አለ አዳም፡ "እንዴ አሁን እኛ ከጀመርነው፡ክትትል ጋር በጭራሽ አይሄድማ!" "ማለት ምን አገናኘው?"አለ አዳም ኮስተር ብሎ "እንዴት አይገናኝም አንተ ደሞ ስለአንድ ነገር እያሰብክ ከሆነ ሌላ በዙሪያው ስላለ ነገር በጭራሽ አታስተውልም ዝምብለህ ፊት ፊቱን ብቻነው የምትጋልበው አይታይህም እንዴ የምታፈቅረው እኮ ሲፈንን ነው ሲፈን ደሞ እኛ የምንከታተለው ሰው ልጅ ናት ይህን መንገር ይጠበቅብኛል አስበው እስኪ?!"አለ አብዲ ድንገት ንዴት ንዴት እያለ "እህ አባቷ በሰራው ስራነው የሚጠየቀው ወንጀለኛ ሆኖ ከተገኘ ሲፈንም ብትሆን የአባቷን ማንነት ስታውቅ የሆነው ነገር ትቀበላለች፡አሁንስ ቢሆን እየረዳችን አደል ደሞ ባለፈው ጊዜ አባቷ በኔላይ ከጓደኛቸው ጋር ስለኔ አንዳች ነገር ሲያሴሩ ሰምታ አስጠንቅቃኛለች የኤዶምንም ጉዳይ እነሱው ሰፈር ስለተጠቃም ጭምር በመጠኑ የጠረጠረችው ነገር እንዳለ ገምቻለው፡!"አለ አዳም እየተከራከረ "አይ አይ በጭራሽ አቶ ይፍሩ ታስረው እንኳ ቢሆን ወይም አንዳች ነገር ቢፈጠር ሲፈን አባቷን ከድታ ላንተ ስሜት የምትገዛ አይመስለኝም ዞሮ ዞሮ ከገዳይህ ልጅ ጋር መሆኑ የሚዋጥ ነገር አደለም ጉዳዩ እስኪጣራ ተረጋጋ!"አለ አብዲ እያስጠነቀቀ "አልገባኝም ኤዶምስ? እያልክ ያለኽው ሲፈን ከኔጋር መሆን አይገባትም ነው?" "እንደኔ ከሁለታችሁም ጋር ባትሆን ጥሩ ነበር በተለይ ግን ካንተ ጋር!"ኮስተር አለ አብዲ "ተው ተው በቃ አብዲ አንተደሞ የባስ አታናደኝ !"አለ አዳም እሱም ቆጣ ብሎ እናም መጠጣት ጀመረ በአንድ ትንፋሽ እንደገና ደገመ ፡አብዲ ሊከላከል ሞከረ ፍቃደኛ አልሆነም አዳም በቅናት ተቃጥሏል አብዲ ደሞ ሲያጣጥልበት ብስጭቱ ባሰ አይ አብዲ አፍቅረህ አታውቅም ፍቅር ስንት ነገር እንደሚያስጥል መቼ ገባህ ላላፈቀረሰው ተው እርሳ አትሆንህም ቀላልነው በፍቅር ውስጥ ብዙ ነገር ታልፋለህ ብዙ ነገር ታሳልፋለህ ፍቅር ከዚ በፊት እያየሃት ያለፍካትን አለም ደግመህ እንደ አዲስ እንድታያት ታደርግሃለች ፍቅር ፍቅር..አዳም መስከር ጀመረ ብዥ ብዥዥዥ እያለበት መጣ አብዲ ተነስ እንሂድ በቃ አለው እየጎተተው ገና መጨለሙ ነው አዳም ግን በጊዜ ፡ሰከረ መጠጡ ነገሩ  የአብዲ ማስጠንቀቂያ ተዳምረው አዞሩበት፡ዘወርርርር..... ====== "ኤዶ በቃ ይበቃል እኔ ልሂድ !"አለች ሲፈን ከኤዶም እቅፍ ውስጥ ለመውጣት እየሞከረች "ፕሊስ ትንሽ ብቻ ትትንሽ ቆቆይልኝ እእ በጣም እእወድሻለው?!"አለ ኤዶም ሲፈንን ደጋግሞ እየሳማት "ኤዶ አታስጨንቀኝ ያለዛሬ የማንገናኝ አስመሰልከው እኮ ደሞ አዳም ከመጣ ዳግም በክርክር መወጠር አልፈልግም በዛላይ መሽቷል "አለች ሲፈን ከእቅፉ ተላቃ በመውጣት "እእሺ የኔ ቆንጆ በቃ ግን ብቻሽን..." "አይ ቅርብ የሆነ ቦታነው መኪናዬን ያቆምኳት ይልቅ እራስህን ዘና አድርግ ቶሎ ከዚ አልጋ ላይ እንድትነሳ እፈልጋለው እሺ!" "እሺ የኔ ውብ !"አለ ኤዶም በፍቅር እያያት "በቃ ደናደር ቻዎ ፈጣሪ ይማርህ!!!" አለችውና ሲፈን ተሰናብታው ልትሄድ ስትል"ሲፍ እንዲ ነው ቻዎ የምትይኝ የመሰናበቻ አልሳምም እእ?" ሲፈን ቀረብ ብላ ሳም አደረገችው ደስስስስ አለው ኤዶ ከነ አልጋው በአየር ላይ እየተንሳፈፈ መሰለው "ሲፍ እወድሻለው" አለ በስሜት አዙሪት እየተሽከረከረ ሲፈን መልስ ሳትሰጠው አይኖቹን በትኩረት አየችው ፀጉሩን በቀስታ ወደኋላ መለስ መለስ በማድረግ አሻሽታው "በቃ ደናደር እደውላለው !"ብላው ተነስታ ወጣች እትዬ ፅጌንም ሳሎን ገብታ አፈር አፈር እያለች ተሰናብታቸው ሄደች ሲፈን በሁለት፡ወንድማማቾች ሕይወት ውስጥ ድንገት ገብታ መውጫ አጥታ እንደተጣበቀች ተሰማት!ጉድ ነው መጨረሻዬ ምን ሊሆን ነው ፈጣሪዬ እርዳኝ ምንድነው፡ያደረኩት ምንድነው....? 📌መልክት አለኝ ውድ ቤተሰቦች፣ እዚህ የምንጋራቸው ጽሑፎች የሚኖሩት እናንተ ስታነቧቸው፣ ስትጋሯቸውና ሐሳባችሁን ስትገልጹባቸው ነው። እናም ከእያንዳንዳችሁ የምጠይቀው ትልቅ ነገር ሳይሆን ትንሽ ትብብር ብቻ ነው። 📌 የምትወዱትን ጽሑፍ ለአንድ ጓደኛችሁ አጋሩ። 📌 የሚስማማችሁን Reaction አድርጉ። 📌 Unmute🔔 በማድረግ 📌 ሐሳባችሁን በComment ወይም በMessage አጋሩን። #አትሮኖስ በእኔ ጥረት ብቻ አይደለም የሚያድገው፤ በእናንተ ተሳትፎም ነው። ❤️ 🙏 አብረን እንደግፈው! አብረን እናሳድገው! ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ። 👇Subscribe YouTube link👇 https://www.youtube.com/@atronose

Открыть в Telegram
Просмотры895−2%к среднему
Пересылки2
Реакции72
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
10 ч402
24 ч632
67 ч895
  1. Через 24 часа632
  2. Всего сейчас895
#98253Текст

#ባለ_ጭንብሉ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አራት ፡ ፡ ...አቶ ይርጋ አቶ ይፍሩን በንቀት እያስተዋሉ በነገር ይሸነቁጧቸዋል በወሬአቸውም መሃል ላንተብዬ ባደረኩት የዚህን ያህል ትችት አይገባኝም ይሏቸዋል አቶይፍሩ አቶይርጋ እየሰሯቸው ያሉት የጅል ስራ አልተመቻቸውም ሽጉጥ እያስያዙ መንደር ለመንደር ሰው ማስገደል ብቃት አለኝ ከሚል ሰው የሚጠበቅ አይደለም በየቦታው አሻራ እየተው ትክክለኛ ስራ ይባልልኛል ነው ይርጋ ምንድነው፡አሳቡ በዛላይ የተያዘው ወጠምሻ፡ነብሰገዳይ ምርመራው ሲበዛበት፡ይርጋ ነው የቀጠረን ቢልስ እንዴ እስከመቼ በውሸቱ ይቀጥላል ደሞ አብዲም ቢሆን የአባቱን ገዳይ ለማወቅ እስካሁን መርማሪውን እያስጨነቀ ነው አዳምም ትውስታው ስለተመለሰ በወንድሙ የግድያ ሙከራ እኔን መጠርጠሩ አይቀርም ጭራሽ የራሴው ሰፈር ነው ወንድሙን ያጠቁት ምን አይነት ዝርክርክነት ነው ይርጋ የሚያካሂደው  ዘንድሮ ጉድ ሊያፈላብኝ ነው ይህ ሰው ለነገሩ እኔ አንድም ነገር ውስጥ አልገባውም ይህ የራሱ አሳብ ነው እኔ ገዳዮቹንም አናግሬም ሆነ አይቻቸው አላውቅ ዞሮ ዞሮ እራሱ ይወጣው ፡፡ "ምን እያሰብክ ነው ?"አሉ ይርጋ ፡አቶይፍሩን በጎን እያዩ ከቢራቸው ጎንጨት እያደረጉ "ምን አስባለው አንተ አስብ እንጂ!" "እንዴት ምን የሚያሳስበኝ ነገር አለ?" "ስማ ነብስ እኮነው ያስጠፋኽው ያውም የጓደኛህን ቀጥለህ ደሞ የሌላን ጎረምሳ ሞከርክ ምን እየሰራህ እንደሆነ ይታወቅሃል?!"አሉ ይፍሩ አቶ ይርጋ ተበሳጩ "ምን እያልክ ነው ለማን ብዬነው እዚ ነገር ውስጥ የገባውት ?ላንተ ስል መስሎኝ ሁለቱም ባንተ ሕይወት መጡ እንጂ በኔ ሕይወት አልመጡም!ለምንድነው ነገሩን ሁሉ በኔ ላይ የምትደፈድፈው !"ተናደዱ "ሲጀመር እኔ አላመንኩህም ያንተ ስራ ነው እንዲነው እንዲያ ነው እያልክ እኔንም ጭንቀት ውስጥ የከትከኝ መንደር ለመንደር ሽጉጥ የምታስተኩሰው ተራ ነገር የምታጠፋ መስሎህ ነው እንዴ?ያንተ ረቀቅ ያለው ስራ ይሄነው በቃነው ሌላ አላማ አለህ ጭራሽ ብለህ ብለህ የአዳምን ወንድም ሰፈሬ አምጥተህ ለማስገደል መሞከር ምን ይሉታል ምን አስበህ ነው!?"ቆጣ አሉ ይፍሩ አቶ ይርጋ ሊናገሩ ሲሉ አስተናጋጁ መጥቶ ባዶ ጠርሙስ መሰብሰብ ጀመረ አቶ ይፍሩ የጓደኛቸው ነገር ስለሰለቻቸው ገና ሰአቱ 11: 30 ቢሆንም  አስተናጋጁን "ሂሳብ አምጣ፡"አሉት አቶ ይርጋ "ወዴት ለመሄድ ነው፡አሳባችንን ሳንጨርሰው የልብህን ተናግረህ ሳንተማመን እማ አንላቀቅም!"አሉ "ምንም መተማመን አያስፈልግም እራስህን አስተካክል!ሂሳብ አምጣ አንተ!"አሉ መልሰው አስተናጋጁን፡"እእ አይ ተተከፍሏል !"አለ ወደበረንዳው ከውጭ በኩል ከተቀመጡት ሁለት ጎረምሶች እየዞረ "ማን አባቱ ነው የሚከፍልልን እርቆ ከሚከፍልልን አብሮን አይጠጣም፡ማነው እሱ !"አሉ ይፍሩ ኮስተር ብለው፡"እእህ ምን አገባህ ይክፈል ካስደሰተው ማነው አስተናጋጅ "አሉ ይርጋ አስተናጋጁ ወደጎረምሶቹ ጠቆመ  ሁለቱም አንድላይ ዞሩ አቶ ይርጋም አቶ ይፍሩም የሚያዩትን ማመን አቃታቸው አዳምና አብዲ ነበሩ ሁለቱም እጃቸውን አውለበለቡላቸው በሰላምታ በተለይ አዳም እንደመነሳት ብሎና፡እያለመጠ በሚመስል ሁኔታ ጎንበስ እያለ አቶይፍሩ ደንግጠው፡አመሰግናለው አሉ በጭንቅላታቸው ንቅናቄ ይርጋ ግራ በመጋባት ስሜት ወደ አብዲ ያያሉ፡አብዲ ጭንቅላት ውስጥ የሆነ ነገር ከትቻለው ብለው አስበው ነበር ስለ አዳም ተጠራጠሩ  አቶ ይፍሩ ከፈለክ ተቀመጥ ብለው ተነሱ እናም ወደውጭ ወጡ ይርጋ ተከተሏቸው እራቅ እንዳሉ አብዲን ብቻ ተሰናብተው ሄዱ አዳም ሳቀ ዝምብሎ ስሜት የሌለው ሳቅ ነበር፡አቶይፍሩ ሰምተው ፊታቸውን ሳይመልሱ እንደ ተሳቀቁ እየፈጠኑ መኪናቸው ውስጥ ገብተው አበረሩ  ይርጋም በራሳቸው መኪና ተንቀሳቀሱ አዳምና አብዲ ከአስባልቱ ፊትለፊት ስለተቀመጡ በግልፅ ይታዩአቸው ነበር በሁኔታቸው ተገርመዋል ጥርጣሬአቸውም እየጨመረላቸው መጣ አብዲ የሚጠጣውን ኮካ አንስቶ ብርጭቆ ውስጥ እየጨመረ "እሺ ምን ይታይሃል፡!?"አለው አዳምን "ለጊዜው እኛን በማየት ተረብሸዋል ቀጣይ ደሞ የምናየው ይሆናል አለው በተሰላቸ ስሜት "ምን ሆነሃል አዳም?ከቅድም ጀምሮ ልክ አይደለህም ደሞ ከተለያየን በዋላ መልሼ ላግኝህ ያልከኝስ ለምንድነው?!"አለው አብዲ "እእ ባክህ፡የሆነ ልክ ያልሆነ ነገር በዙሪያዬ እያንዣበበ ነው!" "የምን ልክ ያልሆነ ? "ወንድሜ ወንድሜ ነው!" "ማ !ኤዶ !" "አዎ ሲፈንን ያፈቅራታል!" "ሀሀሀሀሀ ብራቮ ኤዶ !" "ምንድነው ብራቮ ?!"ተናደደ አዳም "እእህ ኤዶን ከሴት ጋር አይቼው አላውቅም ነበር ይሄ ለውጥ ነው ያልገባኝ አንተን ያሳሰበህ ምንድነው?"አለ አብዲ "እ አብዲ እኔና ሲፈን ጓደኞች ነን እእና..."አለ መልሶ የተናገረውን የተጠራጠረ መሰለ "ምምን !? ማማለት ፍቅረኞች ሆናቹሃል እንዴ ከሲፈን ጋር ይህን ነገረኽኝ አታውቅም!"አለ አብዲ ድንገት አሳብ እየገባው ወንድማማች አንድ ሴት ላይ! "ማለቴ እኔ ለሷ ጥሩ ስሜት አለኝ እሷም እንደዛው ይመስለኝ ነበረ ፡አሁን ግን ግራ ገብቶኛል በጣም እየተቀራረቡ ይመስለኛል እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም፡እሱ በርግጥ ፍቅር ውስጥ ነው እሷ ግን ልቧ እኔጋር እንደሆነ ይሰማኛል እልኽኛ ናት እኔ ችላ ስላልኳት ወደሱ እየቀረበች ነው፡ወንድሜ እንዲጎዳም አልፈልግም ፍቅሬንም ማጣት አልፈልግም፡ምን እንደማደርግ ግራ ገብቶኛል!አለ አዳም፡በጭንቀት "አሃ እሱን በምን ታውቃለህ የምርስ እሱን አፍቅራውስ ቢሆን ጓደኛዬ ሴትን ልጅ ማወቅ ይከብዳል አንተ የሚመስልህ ነገር ሁሉ እሷጋር የሌለ ሊሆን ይችላል ፡ሴቶች አዝነው ሲቀርቡ እንኳን እኮ ያፈቀሩ ነው የሚመስሉት በቀላሉ የማይፈቱ ቅኔ ናቸው! እንዲናት እንዲያ ናት ብለህ ልትገልፃቸው አትችልም እራሷን እስካልገለፀች ድረስ!ስለዚህ ልቧ ከሱጋርም ሊሆን ይችል ይሆናል ብለህም ጠርጥር ከሆነ ደሞ ጓደኛዬ ለሚፈጠረው ነገር እራስህን አዘጋጅ ፍቃደኝነቱ ይኑርህ መሆን ያለበት ነው ሁሌም የሚሆነው መታገል አያስፈልግም ፡ውጤቱ ጥሩ ስለማይሆን!!!"አለ አብዲ የጓደኛው ስሜት እየረበሸው፡አዳም ፊቱን በሁለት እጆቹ ሸፈነ ፡ሲፈንን መተው ሲፈንን እንዴት አድርጌ ?አፈቅራታለሁ.....አፈቅራታለሁ ....ወንድሜ ...ወንድሜ...... ===== ...እቤቱ አነስተኛ ግሮሰሪ ነው ሁልጊዜም ከስራ ሰአት ውጪ አቶ ይፍሩ ጓደኞቻቸውን የሚያገኙት እዚሁ ነው፡የአሁኑን አያድርገውና፡አቶ የሱፍ በአቶ ይርጋ አቀነባባሪነት፡ከመሞታቸው በፊት ሰብሰብ፡ብለው ስለ የጋራ ስራቸውም ሆነ ስለ ግል ሕይወታቸው እያወሩ እየተጨዋወቱ የሚያመሹበት ቤት ነው የዛቤት፡አስተናጋጆችም ሆኑ ባለቤቱ ጭምር እንደቤተሰብ ተላምደዋቸዋል ያቶ የሱፍን፡ባልታወቀሰው መገደል ሰምተው ከላይ እስከታች አዝነውም ነበር፡የጓደኞቹን መቀራረብ ላየ እንዲ በቀላሉ ይረሳሳሉ ብሎ የገመተም ሰው አልነበረም ምን ይደረግ አንዳንድ ጓደኝነት ከላይ ከላይ ነው፡!! ብዙ ወዳጆች ሳይግባቡ የተግባቡ ! ሳይዋደዱ የተዋደዱ !ሳይስማሙ የተስማሙ!.....ይመስላሉ ፡ያስመስላሉ !!

Открыть в Telegram
Просмотры1 036+14%к среднему
Пересылки2
Реакции16
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
10 ч418
24 ч698
67 ч1 036
  1. Через 24 часа698
  2. Всего сейчас1 036
#98252Фото

🐘እርግጠኛ ነሽ አርግዘሻል? አንድ ውሻና አንዲት ዝሆን በተመሳሳይ ጊዜ ፀነሱ ከሦስት ወራት በኋላ ውሻዋ ስድስት ቡችሎችን ወለደች ዝሆኗ ግን ገና ነፍሰ ጡር ነበረች ከዚያም ወራት አለፉ ውሻዋ እንደገና ፀነሰች በድጋሚም ቡችሎችን ወለደች ይህ ሁኔታ በተደጋጋሚ ቀጠለ ውሻዋ በየጥቂት ወራቱ ትወልድ ነበር ዝሆኗ ግን አሁንም ጽንሷን በማህፀኗ ተሸክማ ትጠብቅ ነበር በአንድ ወቅት ውሻዋ ወደ ዝሆኗ ቀርባ በጉጉት ጠየቀቻት ✨እርግጠኛ ነሽ ነፍሰ ጡር እንደሆንሽ? በሆድሽ ውስጥ በእርግጥ ጽንስ አለ? ተመሳሳይ ጊዜ ነው የፀነስነው እኔ ግን ከ16 በላይ ቡችሎችን ወልጄ አንዳንዶቹም አድገው ትልቅ ውሾች ሆነዋል አንቺ ግን አሁንም እርጉዝ ነኝ ትያለሽ ምን እየሆነ ነው? ዝሆኗም በረጋ መንፈስ እንዲህ ስትል መለሰች 🐘 «እኔ እንድትረጂ የምፈልገው አንድ ነገር አለ በማህፀኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነው እኔ ለረጅም ጊዜ እጠብቃለሁ ግን የምወልደው አንድ ብቻ ቢሆንም ተራ አይደለም ልጄ መሬት ላይ ሲረግጥ ኃይሉ ይታያል በመንገድ ላይ ሲሄድ ሰዎች ቆመው ያደንቁታል የእርሱ መኖር የሰዎችን ትኩረት ይስባል ስለዚህ የእኔ ጉዞ ከአንቺ ጋር ተመሳሳይ ባይሆንም የራሴ ጊዜና የራሴ ዓላማ አለኝ» ✨የሕይወት ትምህርት ወዳጄ ሌሎች ከአንተ በፊት ስኬታቸውን ሲያገኙ ሕይወታቸው ሲቀየርና የሚፈልጉትን ሲያሳኩ በእነርሱ አትቅና የአንተም ተስፋ እንዲጠፋ አትፍቀድ የሌላው ሰው ፍጥነት የአንተን መድረሻ አይወስንም ሁሉም ሰው የራሱ ጊዜ የራሱ መንገድና የራሱ ፈተና አለው 🌱 የአንተ ስኬት ዘግይቶ መምጣቱ ፈጽሞ እንደማይመጣ አያመለክትም 💎 ትዕግሥትህን አታጣ ጥረትህን አታቋርጥ የራስህን ጉዞ ከሌላ ሰው ጋር አታነጻጽር የራስህ ጊዜ ሲደርስ የራስህ ታሪክ ይጻፋል @atronosee

Открыть в Telegram
Просмотры1 197+31%к среднему
Пересылки6
Реакции21
Комментарии3
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
14 ч601
28 ч777
71 ч1 197
  1. Через 24 часа777
  2. Всего сейчас1 197
#98251Текст
Просмотры1 121+23%к среднему
Пересылки3
Реакции11
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
14 ч457
28 ч807
71 ч1 121
  1. Через 24 часа807
  2. Всего сейчас1 121
#98250Текст
Просмотры1 087+19%к среднему
Пересылки3
Реакции9
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
14 ч484
29 ч776
71 ч1 087
  1. Через 24 часа776
  2. Всего сейчас1 087
#98248Превью ссылки

​​ኤዶም ሰውነቱ ይንቀጠቀጣል፡ሁሉም ነገር ጭንቀት ለቀቀበት የአዳም እንደዛ መሆን የሲፈን መረበሽ የእናቱ የምን ሆናችዋል ጥያቄ የሚጠዘጥዘው የእግሩ ቁስል አይኑን ጨፈነ የቀኝ እጁን ግንባሩ ላይ አደረገው ፡፡ሲፈን የትዬ ፅጌን ጥያቄ መመለስ አቃታት እንደው እንደነገሩ አይ እንደው በሆነ ነገር ተናዶ ነው አለች በደፈናው እትዬ ፅጌ ከሁለቱም አጥጋቢ መልስ ባያገኙም፡ይሁን በዋላ እራሱን እጠይቀዋለው፡በማለት ነገሩን በመተው ወደልጃቸው ጠጋብለው ብርድ ልብሱን እንደማልበስ አድርገው በስስት እያዩት፡"ኤዶሜ የኔ አለም እራስህን አታስጨንቅ ወንድምህ፡እንደው ድንገት ምን እንደሚያስቆጣው አይታወቅም ያው ታውቀዋለህ ቆይቶ መለስ ይላል ልጅቷንም አታስጨንቋት!ቁጭበይ እናቴ!ቁጭበይ!"አሉ  ጭንቅ ጥብብ ብለው ሲፈን ግራ በመጋባ መንፈስ ውስጥ ሆና፡ቦርሳዋን አነሳች መልሳ ቁጭ አለች፡  እትዬ ፅጌ ወደጓደኞቻቸው ተመለሱ.. ኤዶም ግንባሩን ማሻሸቱን አቁሞ አይኖቹን በመግለፅ ሲፈንን አያት እና የፍቅሩን መጠን መለካት ጀመረ ሲፈን አቀርቅራለች ፀጉሯን የቀይ ዳማ ፊቷን እረዣዥም የሚያማምሩ እግሮቿን ከላይ እስከታች አንድ በአንድ አስተዋለ ሲፈን ልዩ ናት በተለይ ደሞ የሚወደድ አስተዋይ ባህሪዋ ኤዶም ለኔ የሚገባኝ ማንነት ነው ያላት የሆነ ንቃት የሕይወት ውበት የተሰማኝ ሲፈንን ካገኘው ጀምሮ ነው !!ምን ላድርግ ለዚች የልቤ ገዢ ለሆነች ሴት ስል የመንትያ ወንድሜን ስሜት መግፋት ይጠበቅብኝ ይሆን ?የሱ ፍቅር፡ከኔ የበለጠ ይሆን እንዴ ፍቅርስ መበላለጥ አለው ይሆን? ግራ ገባው ኤዶም ከጭንቀቱ የተነሳ ቀስ እያለ ከአልጋው ተነሳ ጥርሱን ነከስ አድርጎ ቆመ ሲፈን እንደመባነን ብላ አብራው ቆመች፡ "ኤዶ ወዴት ነው፡ኧረ ያምሃል፡ለምን ተነሳህ?!"አለች ልትይዘው እየሞከረች "አይ ተይው ብዙ አይሰማኝም ያን ያህል ካባበልኩትማ ተኝቼ መቅረቴ ነው፡"አለ "እሺ ለምን ተነሳህ?" "ሽንት ቤት ልሂድ "አለ "ኧረ ውሃሽንት ከሆነ ለማዘር ልንገራቸው እዚሁ ያምጡልህ ፡እባክህ ኤዶ ያምሃል በዋላ!"አለች ሲፈን "ሲፍ ምንም አልሆንም "አለ ኤዶም እናም ቀስ እያለ ሄደ ሲፈን ደገፈችው ከጎኑ ስትቆም ደስ የሚል ስሜት ተሰማው "ሲፍ አንዴ እእ አንዴ ብብቻ....."አለና ተወው "ምን አንዴ ምን ልስጥህ ?"አለች ሲፈን አንጋጣ በጥያቄ እያየችው "አይ እ እእኔ..." "አንተ ምን?" "አንዴ ልሳምሽ ?" "እእ ማለት..እሺ "አለች ሲፈን ገርሟት ኤዶም መልሶ እንደማፈር አለ፡"እሺ ብያለው ..."አለች ሲፈን ቀና ብላ እያየችው ኤዶም ቀስ ብሎ ሳምምምም አደረጋት የሆነ የሚጣፍጥ ነገር እንደ ጎረሰ ሰው ደስስስስ አለው አጣጣመ አይኖቿን በፍቅር አስተዋላቸው፡እናም አረጋገጠ መቼም ቢሆን፡ከዚ ደስ የሚል የሚጣፍጥ ፍቅር፡ለወንድሙ ብሎ መውጣት እንደማይችል፡አልችልም፡ወንድሜ አልችልም...... ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ። 👇Sebscribe YouTube link👇 https://www.youtube.com/@atronose

Открыть в Telegram
Просмотры1 026+13%к среднему
Пересылки5
Реакции17
Комментарии0
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч110
16 ч532
30 ч742
72 ч1 026
  1. Через 1 час110
  2. Через 24 часа742
  3. Всего сейчас1 026