🌹 ስጦታ የፍቅር መግለጫ ነው! የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «ተዠስጦታ ተሰጣጡ፤ እርስ በርሳችሁም ትዋደዳላችሁ።» ማለትም ስጦታን እርስ በርሳችሁ ተለዋወጡ፤ ይህም በልባችሁ ውስጥ ፍቅርን፣ መተሳሰብንና መቀራረብን ያበዛል። ምክንያቱም ስጦታ የሚለካው በዋጋው ሳይሆን በሚያስተላልፈው የፍቅር መልዕክት ነው። አንዳንድ ጊዜ ስጦታ ትልቅ ደስታን ይፈጥራል፤ ስጦታ የተራራቁ ልቦችን ያቀራርባል። ስጦታ በእጅ ይሰጣል፤ ግን ከልብ ይደርሳል! አላህ የዱንያን የሀብትና የበረከት በር የከፈተላችሁ ሆይ! ከተሰጣችሁ ስጡ፤ ለሌሎችም የደስታና የእፎይታ ምክንያት ሁኑ። አላህ የሰጣችሁን በረከት ለሌሎች የምታካፍሉበትን ልበ ሰፊነትና ሰጪ እጅ ይወፍቃችሁ። እኛንም ከሚለምኑ ሳይሆን ከሚሰጡ፣ ከሚጠብቁ ሳይሆን ከሚያካፍሉ ባሮቹ ያድርገን። የሀብት ትልቁ ውበት በማከማቸት ሳይሆን፣ በማካፈል ይገለጣል። አሚን! 🤲 ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba
Open in Telegram
አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ
قال الإمام مالك ((لايصلح آخر هذه الأمة إلا بماصلح به أولها))
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 13, 2026 | 1,640 |
| Nov 14, 2026 | 1,090 |
| Nov 15, 2026 | 1,140 |
| Nov 17, 2026 | 1,206 |
| Nov 18, 2026 | 943 |
| Nov 19, 2026 | 1,305 |
| Nov 24, 2026 | 723 |
| Nov 25, 2026 | 601 |
Most viewed this month
- 01Views1.64KForwards—Reactions—Comments—
- 02Views1.39KForwards—Reactions—Comments—
- 03Views1.35KForwards—Reactions—Comments—
- 04Views1.35KForwards—Reactions—Comments—
Latest posts
የደስታህ ሚስጥር ፣ ደስታህን ሚስጥር ማድረግህ ነው! 📍ሁሉንም ነገር ለሁሉም አታጋራ፤ የሕይወትህን ደስታ፣ የልብህን እርካታና የኑሮህን ሰላም በዝምታ ጠብቅ። ሁሉም ሰው ደስታህን ማወቅ አይጠበቅበትም፤ ሁሉም ሰው የሕይወትህን ዝርዝር ማወቅም አያስፈልገውም። አንዳንድ ደስታዎች ሲደበቁ ያብባሉ፤ አንዳንድ በረከቶችም በዝምታ ሲጠበቁ ይቆያሉ። ደስታህን ኑረው እንጂ ለሁሉም ለማሳየት አትጣር! ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba
Open in Telegram🤲 አሚን በሉ! ከሚያሰቃይና ከሚያስጨንቅ ከባድ ሕመም፣ ከሰው እጅ ላይ ከመውደቅና ለሌሎች ሸክም ከመሆን አላህ ይጠብቃችሁ። ጤናችሁን ይጠብቅላችሁ፣ ዕድሜያችሁን በበጎ ሥራ ያስረዝምላችሁ፣ በራሳችሁ እግር ቆማችሁ ለሌሎች የምትጠቅሙ ያድርጋችሁ። ከሕመም ያርቀን፣ ከሰው እጅ ነፃ አድርጎ በጤናና በክብር ያኑረን። አሚን ያ ረበል ዓለሚን! 🤲 ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba
Open in Telegramየአንዳንድ ሰዎችን ትልቅነት የምንረዳው ከጎናችን ሲለዩ ነው! 📍ከእኛ ጋር ሳሉ የሚያደርጉልንን መልካምነት፣ የሚሰጡንን ምቾት፣ የሚያሳዩንን ፍቅርና ቅንነት አንዳንዴ እንደ ተራ ነገር እንቆጥራለን። ነገር ግን ከሕይወታችን ሲርቁ የተዉት ቦታ ብቻ ሳይሆን የሰጡንን የልብ ሰላም እና የማይደገም ደስታ እንናፍቃለን። 📍አንዳንድ ሰዎች የሚኖራቸው ዋጋ በአጠገባችን ሳሉ አይታወቅም፤ በሌሉበት ጊዜ ግን በልባችን ውስጥ የነበራቸው ቦታ ይገለጣል። 📌ሰውን ከማጣትህ በፊት ዋጋውን እወቅ፤ አንዳንድ ኪሳራዎች ከተፈጠሩ በኋላ በምንም ነገር አይተኩም! ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba
Open in Telegram📌ክፍል ሰባት 📖 مختصر علم التجويد تأليف :الشيخ مصطفى عبد الرحمن الطيار 🎙 ደርሱን የሚሰጠው፦ አቡ አዩብ ሙሐመድ የኪታቡ pdf https://t.me/abutoiba/6245 https://t.me/abutoiba/6245 🌐ለመርከዝ አቢ አዩብ የቁርዐን ሂፍዝ እና መሰረታዊ የሸሪዓ ዱሩሶች ማዕከል ተማሪዎች መሰጠት የያዘ ተከታታይ ትምህርት https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba
Open in Telegramወሬን ከማመንህ በፊት አረጋግጥ፤ ሰው ላይ ከመፍረድህ በፊት አስብ! 📍አንድ ቀን እንኳን አግኝተኸው የማታውቀውን፣ ፊት ለፊት ተገናኝተህ የማታውቀውን ሰው፣ እንዴት ስለ እሱ በእርግጠኝነት ማውራት ቻልክ? «ሰምቼ ነው!» ትላለህ። እሺ፣ ሰምተሃል፤ ግን የሰማኸውን አረጋግጠሃል? የነገረህን ሰው እውነተኛነት መርምረሃል? ወይስ የሰዎችን ንግግር ሳታጣራ እንዳለ ተቀብለህ የሌላውን ክብር ለማጥፋት ተቻኩለሃል? ወንድሜ! የሰማኸው ሁሉ እውነት አይደለም፤ እውነት ቢሆንም ሁሉንም ማውራት ግዴታህ አይደለም። 📍አንድን ሰው ሳታውቀው አትፍረድበት፤ ሳታጣራ አትክሰሰው፤ የሌሎችን አንደበት መሠረት አድርገህ የሰውን ስምና ክብር አታፍርስ። ምክንያቱም አንድ የተሳሳተ ወሬ የሰውን የአመታት ጥረት፣ መልካም ስምና ክብር በአፍታ ሊያጠፋ ይችላል። አላህ እንዲህ ይላል፦ ﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنْ جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا﴾ «እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አመፀኛ ሰው በዜና ቢመጣላችሁ አጣሩ።» [الحجرات: 6] 📌አስታውስ! የሰማኸውን ሁሉ ማውራት አንደበትህን አይከብድም፤ ነገር ግን በዚያ ወሬ የሚጎዳውን ሰው ልብ ሊሰብር ይችላል። የሌሎችን ጉድለት ከመፈለግህ በፊት የራስህን አስተካክል፤ የሌሎችን ክብር ከማፍረስህ በፊት የራስህን አንደበት ጠብቅ። አላህ አንደበታችንን ከውሸትና ከሐሜት፣ ልባችንንም ከጥርጣሬና ከጥላቻ ይጠብቅልን። አሚን‼️ ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba
Open in Telegramይህን ምስል ስታይ መጀመሪያ ያስታወስከው ሰው ማን ነው? https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba
Open in Telegramሕይወታችንን ለምናልባት እስከ መቼ እንተዋለን? 🎙አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba
Open in TelegramConnections
Similar channels
🇮ዲን መመካከር ነው-الدين النصيحة🇮@ibnyahya7Religion8.66K
የቅዱሳን ታሪክ@sihela_adhnoReligion8.51K
Meleket Tube@meleket_tubeReligion8.82K
قناة دروس أبي قتادة حفظه الله የአቡ ቀታዳህ አጠቃላይ ትምህርቶች@qanathabuqetadaReligion9K
በረከተ እስጢፋኖስ | Saint Stephen's blessings@ststephenblessingsReligion8.18K
Daily Injera@dailyinjeraofficialReligion7.81K
ኢስላማዊ ግጥም@abdul_fettahReligion7.57K
ኢስላማዊ እውነታ@islamictruethReligion9.92K