Account
AAU-Official

AAU-Official

Verified

Addis Ababa University

Username
@aau_official
Category
Education
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers48,075
Avg views per post, 7d—last 7 days
ERR45.48%30-day average

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Oct 30, 202633,200
Oct 31, 202618,200
Nov 1, 202636,600
Nov 3, 202619,700
Nov 4, 202617,200
Nov 6, 202633,900
Nov 7, 202621,000
Nov 10, 202619,000
Nov 20, 202611,300
Nov 21, 20268,550

Most viewed this month

  1. 01

    ጉዞ ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! (ሼር በማድረግ የጥበብ ግብዣውን ለሌሎችም አድርሱልን።) የ63ኛ ምሽት እንግዳችን፤ ሕልምን ወደ እውነት፣ ሐሳብን ወደ ተግባር፣ ፈተናን ወደ ዕድል መቀየርን ያሳየች፤ በቴክኖሎጂና በሥራ ፈጠራ ዓለም የራሷን መንገድ የቀየሰች፤ በድፍረቷና በተነሳሽነቷ ለብዙዎች መነሳሳት ምክንያት የሆነችው ሥራ ፈጣሪ ሳምራዊት ፍቅሩ ናት! ጉዞ ምሽት! ከሕይወት አጋጣሚዎች፣ ከችግሮች መፍትሔ የመፍጠር፣ ከሕልም ተነስቶ የራስን መንገድ የመጥረግ ታሪክ ይዛ ወደ መድረካችን ትመጣለች! ከልጅነት ሕልሟ፣ ከትምህርትና ከሕይወት ጉዞዋ፣ ከመጀመሪያዎቹ የሥራ ፈጠራ ሙከራዎቿ፣ ከስኬትና ከውድቀት ትምህርቶቿ፣ ከቴክኖሎጂ ዓለም ተሞክሮዋ፣ እስከ ራይድ (RIDE) የሥራ ፈጠራ ጉዞዋ ድረስ በስፋት ትተርክልናለች። የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል። 📅 ረቡዕ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 ዓ.ም. 🕠 11:30 ሰዓት 📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ አንድ ምሽት፣ ብዙ ታሪኮች አንድ መድረክ፣ ሺ ስሜቶች ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

    Photo
    Views36.6K
    Forwards—
    Reactions35
    Comments—
  2. 02
    Views33.9K
    Forwards—
    Reactions19
    Comments—
  3. 03
    Views33.2K
    Forwards—
    Reactions18
    Comments—
  4. 04

    🎬 ሲኒማ ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! (ሼር በማድረግ የጥበብ ግብዣውን ለሌሎችም አድርሱልን።) የ64ኛ ምሽት እንግዳችን፤ ታሪክን በምስል፣ ስሜትን በብርሃንና በጥላ፣ ሕይወትን በሲኒማ ቋንቋ የመተረክ ጥበብን የተካነ፤ ከፎቶግራፍ ተነስቶ በኢትዮጵያ ሲኒማ ውስጥ የራሱን አሻራ ያሳረፈው የፊልም ዳይሬክተር፣ ሲኒማቶግራፈርና ፕሮዲዩሰር ሰውመሆን ይስማው (ሶሚክ) ነው! 🎬 ሲኒማ ምሽት! ከልጅነት ሕልሙ፣ ከመጀመሪያዎቹ የፎቶግራፍና የፊልም ሙከራዎቹ፣ ከሲኒማቶግራፊ ተሞክሮው፣ ከዳይሬክተርነትና ከፕሮዲዩሰርነት ጉዞው፣ ከፊልም ሥራ ፈተናዎችና ድሎች ጋር የተሰፋውን ማንነቱን በስፋት ይተርክልናል። ከዚህም ባሻገር፣ ስለ ኢትዮጵያ ሲኒማ ትናንት፣ ዛሬና ነገ፤ ስለ ፊልም አሠራር፣ ስለ ፈጠራ፣ ስለ ትረካ ጥበብና ስለ አዲሱ የፊልም ትውልድ በስፋት እንወያያለን። የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል። 📅 ረቡዕ፣ ህዳር 2፣ 2019 ዓ.ም. 🕠 11:30 ሰዓት 📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ አንድ ምሽት፣ ብዙ ታሪኮች! አንድ መድረክ፣ ሺ ስሜቶች! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

    Photo
    Views21K
    Forwards—
    Reactions46
    Comments—

Latest posts

#1774Photo

🌟🎭 ኮከብ ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! (ሼር በማድረግ የጥበብ ግብዣውን ለሌሎችም አድርሱልን።) የ66ኛ ምሽት እንግዳችን፤ በትወና ጥበቡ የተመልካቾችን ልብ የገዛ፣ በመድረክ፣ በሬዲዮ፣ በፊልምና በተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች የጥበብ አሻራውን ያሳረፈ፣ በአንድ የትወና ዘውግም ሆነ በአንድ ዓይነት ገጸ ባሕርይ ያልተገደበ፣ ከንጉሥ አጫዎች እስከ ንጉሥ የተለያዩ ገጸ ባሕርያትን በአስደናቂ ብቃት የተጫወተ፣ በእያንዳንዱ ገጸ ባሕርይ ውስጥ እንደልብ የሚገለጥ የኢትዮጵያ የትወና ጥበብ ደማቅ ኮከብ፣ አለማየሁ ታደሰ ነው! 🌟 ኮከብ ምሽት! ኮከብ የሚወለደው እንዴት ነው?... ከሐረር የልጅነት ትዝታዎቹ እስከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከመጀመሪያ የትወና ሙከራዎቹ እስከ ታላላቅ የቴአትር መድረኮች፣ ከ"አንቲጎን" እስከ "ባቢሎን በሳሎን"፣ ከሬዲዮ እስከ የቴሌቪዥን ድራማ፣በአጠቃላይ የጥበብ ጉዞውን... ከዝናው ጀርባ ባሉ ትግሎቹ፣ ፈተናዎቹና ስኬቶቹ ዙሪያ እንወያያለን። 🎭 የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል። 📅 ረቡዕ፣ ኅዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም 🕠 11:30 ሰዓት 📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ 🌟 አንድ ኮከብ፣ ብዙ ገጸ ባሕርያት! 🎭 አንድ መድረክ፣ ሺ ስሜቶች! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

Open in Telegram
Views8,550−61%vs avg
Forwards—
Reactions86
Comments—
#1773File
Views11,300−48%vs avg
Forwards—
Reactions131
Comments—
#1771Photo

🎬 ሲኒማ ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! (ሼር በማድረግ የጥበብ ግብዣውን ለሌሎችም አድርሱልን።) የ64ኛ ምሽት እንግዳችን፤ ታሪክን በምስል፣ ስሜትን በብርሃንና በጥላ፣ ሕይወትን በሲኒማ ቋንቋ የመተረክ ጥበብን የተካነ፤ ከፎቶግራፍ ተነስቶ በኢትዮጵያ ሲኒማ ውስጥ የራሱን አሻራ ያሳረፈው የፊልም ዳይሬክተር፣ ሲኒማቶግራፈርና ፕሮዲዩሰር ሰውመሆን ይስማው (ሶሚክ) ነው! 🎬 ሲኒማ ምሽት! ከልጅነት ሕልሙ፣ ከመጀመሪያዎቹ የፎቶግራፍና የፊልም ሙከራዎቹ፣ ከሲኒማቶግራፊ ተሞክሮው፣ ከዳይሬክተርነትና ከፕሮዲዩሰርነት ጉዞው፣ ከፊልም ሥራ ፈተናዎችና ድሎች ጋር የተሰፋውን ማንነቱን በስፋት ይተርክልናል። ከዚህም ባሻገር፣ ስለ ኢትዮጵያ ሲኒማ ትናንት፣ ዛሬና ነገ፤ ስለ ፊልም አሠራር፣ ስለ ፈጠራ፣ ስለ ትረካ ጥበብና ስለ አዲሱ የፊልም ትውልድ በስፋት እንወያያለን። የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል። 📅 ረቡዕ፣ ህዳር 2፣ 2019 ዓ.ም. 🕠 11:30 ሰዓት 📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ አንድ ምሽት፣ ብዙ ታሪኮች! አንድ መድረክ፣ ሺ ስሜቶች! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

Open in Telegram
Views21,000−4%vs avg
Forwards—
Reactions46
Comments—
#1765Photo

"የአፍሪካ ቀጠናዊ ትስስር ማዕከል" ማቋቋም የሚያስችል ስምምነት ተደረገ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ(Expertise France) በጋራ በመሆን "የአፍሪካ ቀጠናዊ ትስስር ማዕከልን ማቋቋም የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ማዕከሉም በቀጠናዊ ትስስርና ልማት ላይ ያተኮረ የማስተርስ ፕሮግራም በመክፈት፣ ብቁ የንግድ ተደራዳሪዎችን እና የፖሊሲ ተንታኞችን እንደሚያፈራ ተጠቁሟል። በስምምነቱ ላይ  ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ  አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ላይ የኢትዮጵያን ስኬት ለማረጋገጥ ለተደረሰው የሶስትዮሽ የጋራ ስምምነት ስኬት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። ዶ/ር ሳሙኤል አያይዘውም ፤ ዩኒቨርሲቲው በግል እና በህዝብ ዘርፍ የሚገኙ ባለሙያዎችን አቅም በመገንባት የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ግቡን እንዲመታ የማድረግ ስራዎችን እንደሚሰራ ገልፀዋል። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ በበኩላቸው ፤ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ(Expertise France) በጋራ የሚመሰርተው "የአፍሪካ ቀጠናዊ ትስስር ማዕከል (ARIC)" በቀጠናዊ ትስስር እና ልማት ላይ ያተኮረ የማስተርስ ፕሮግራም በመክፈት፣ ብቁ የንግድ ተደራዳሪዎችንና የፖሊሲ ተንታኞችን እንደሚያፈራ ተናግረዋል። ስምምነቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ፣የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ  እና የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ(Expertise France) የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጄን ባፕቲስት ፈርመውታል፡፡

Open in Telegram
Views19,700−10%vs avg
Forwards—
Reactions15
Comments—
#1764Photo

ጉዞ ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! (ሼር በማድረግ የጥበብ ግብዣውን ለሌሎችም አድርሱልን።) የ63ኛ ምሽት እንግዳችን፤ ሕልምን ወደ እውነት፣ ሐሳብን ወደ ተግባር፣ ፈተናን ወደ ዕድል መቀየርን ያሳየች፤ በቴክኖሎጂና በሥራ ፈጠራ ዓለም የራሷን መንገድ የቀየሰች፤ በድፍረቷና በተነሳሽነቷ ለብዙዎች መነሳሳት ምክንያት የሆነችው ሥራ ፈጣሪ ሳምራዊት ፍቅሩ ናት! ጉዞ ምሽት! ከሕይወት አጋጣሚዎች፣ ከችግሮች መፍትሔ የመፍጠር፣ ከሕልም ተነስቶ የራስን መንገድ የመጥረግ ታሪክ ይዛ ወደ መድረካችን ትመጣለች! ከልጅነት ሕልሟ፣ ከትምህርትና ከሕይወት ጉዞዋ፣ ከመጀመሪያዎቹ የሥራ ፈጠራ ሙከራዎቿ፣ ከስኬትና ከውድቀት ትምህርቶቿ፣ ከቴክኖሎጂ ዓለም ተሞክሮዋ፣ እስከ ራይድ (RIDE) የሥራ ፈጠራ ጉዞዋ ድረስ በስፋት ትተርክልናለች። የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል። 📅 ረቡዕ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 ዓ.ም. 🕠 11:30 ሰዓት 📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ አንድ ምሽት፣ ብዙ ታሪኮች አንድ መድረክ፣ ሺ ስሜቶች ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

Open in Telegram
Views36,600+67%vs avg
Forwards—
Reactions35
Comments—
#1760Photo

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል በ62ኛ ሳምንቱ የክብር እንግዳ የነበረችው አንጋፋዋ የሚዲያ ባለሙያ ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ ልምዷን አካፈለች ለዓመታት ብዙ ሺዎችን ስታነጋግር፣ የታሪክ ጓዳቸውን ስትበረብር፤ የሕይወት መንገዳቸውን ስትፈትሽ የኖረችው ልሳነ-ርቱዋ መዓዛ ብሩ በዚህ ታሪካዊ ምሽት የእርሷን የራሷን ታሪክ አውግታለች! ጠያቂዋ ተጠይቃለች! እንግዳ አክባሪዋ በታላቅ ድምቀት ተከብራለች! በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስም ካላቸው እና አንጋፋ ከሆኑት የጋዜጠኝነት ባለሙያዎች አንዷ ለሆነችው መዓዛ ብሩ የምስጋና መርሃግብር ተካሂዷል። በኢትዮጵያ የግል የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች አነሳስና እድገት ውስጥ ቀዳሚውን ሚና ከተጫወቱት መካከል የምትጠቀሰው መዓዛ ብሩ፥ ከባህል ማዕከሉ ሽልማትም ተበርክቶላታል። ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ "መርሃ ስፖርት" በተባለ ጋዜጣ ላይ የስፖርት ዘጋቢ በመሆን የሰራች ሲሆን በብሔራዊ ባንክ "ብሪቱ" የተባለውን የባንኩን ወርሃዊ መጽሔት በዋና አዘጋጅነት መምራቷ የሚታወስ ነው። ከሕይወት ጉዞዋ፤ ከሙያዊ ፍልስፍናዋ፤ ከ"ጨዋታ" እስከ "ሸገር" ተረማምዳ ካለፈቻቸው የሚዲያ ሙያዊ ጉዞዋ፤ ከድልና ከፈተና የሕይወት አጋጣሚዎቿ በጥልቀት ያካፈለችበት፤ በቃለ መጠይቋም ልቧን እና አእምሮዋን ግልጽ አድርጋ በልዩ ትህትና ትልቅ መልእክት ያካፈለችበት ግሩም ምሽት ነበር። ዘወትር ረቡህ ምሽት 11፡30 የሚካሄደው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል ፕሮግራም በተለያዩ እንግዶች የሚቀጥል ይሆናል፡፡

Open in Telegram
Views18,200−17%vs avg
Forwards—
Reactions36
Comments—
#1759Photo
Views33,200+52%vs avg
Forwards—
Reactions18
Comments—

All posts

Connections