🌟🎭 ኮከብ ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! (ሼር በማድረግ የጥበብ ግብዣውን ለሌሎችም አድርሱልን።) የ66ኛ ምሽት እንግዳችን፤ በትወና ጥበቡ የተመልካቾችን ልብ የገዛ፣ በመድረክ፣ በሬዲዮ፣ በፊልምና በተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች የጥበብ አሻራውን ያሳረፈ፣ በአንድ የትወና ዘውግም ሆነ በአንድ ዓይነት ገጸ ባሕርይ ያልተገደበ፣ ከንጉሥ አጫዎች እስከ ንጉሥ የተለያዩ ገጸ ባሕርያትን በአስደናቂ ብቃት የተጫወተ፣ በእያንዳንዱ ገጸ ባሕርይ ውስጥ እንደልብ የሚገለጥ የኢትዮጵያ የትወና ጥበብ ደማቅ ኮከብ፣ አለማየሁ ታደሰ ነው! 🌟 ኮከብ ምሽት! ኮከብ የሚወለደው እንዴት ነው?... ከሐረር የልጅነት ትዝታዎቹ እስከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከመጀመሪያ የትወና ሙከራዎቹ እስከ ታላላቅ የቴአትር መድረኮች፣ ከ"አንቲጎን" እስከ "ባቢሎን በሳሎን"፣ ከሬዲዮ እስከ የቴሌቪዥን ድራማ፣በአጠቃላይ የጥበብ ጉዞውን... ከዝናው ጀርባ ባሉ ትግሎቹ፣ ፈተናዎቹና ስኬቶቹ ዙሪያ እንወያያለን። 🎭 የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል። 📅 ረቡዕ፣ ኅዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም 🕠 11:30 ሰዓት 📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ 🌟 አንድ ኮከብ፣ ብዙ ገጸ ባሕርያት! 🎭 አንድ መድረክ፣ ሺ ስሜቶች! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
Open in TelegramPosts of AAU-Official
To All Members of the AAU Community, It is with great sadness that we announce the passing of Dr. László Samodi, Associate Professor of Surgery, who served as a urology surgeon in the Department of Surgery at the College of Health Sciences (CHS). Dr. Samodi began serving the Department of Surgery since 2004 GC. Over nearly two decades of service prior to his recent retirement, he played a vital role in modernizing urology surgery in Ethiopia and was instrumental in establishing postgraduate training within the Department of Surgery at CHS. He will be remembered as a humble and dedicated teacher who was always eager to share his knowledge and skills with his students and colleagues. We extend our deepest condolences and wish strength to his family, colleagues, and friends during this difficult time. The funeral service will take place today, November 20, 2026, at 2:00 PM at Yeka Michael Church
Open in Telegram🎬 ሲኒማ ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! (ሼር በማድረግ የጥበብ ግብዣውን ለሌሎችም አድርሱልን።) የ64ኛ ምሽት እንግዳችን፤ ታሪክን በምስል፣ ስሜትን በብርሃንና በጥላ፣ ሕይወትን በሲኒማ ቋንቋ የመተረክ ጥበብን የተካነ፤ ከፎቶግራፍ ተነስቶ በኢትዮጵያ ሲኒማ ውስጥ የራሱን አሻራ ያሳረፈው የፊልም ዳይሬክተር፣ ሲኒማቶግራፈርና ፕሮዲዩሰር ሰውመሆን ይስማው (ሶሚክ) ነው! 🎬 ሲኒማ ምሽት! ከልጅነት ሕልሙ፣ ከመጀመሪያዎቹ የፎቶግራፍና የፊልም ሙከራዎቹ፣ ከሲኒማቶግራፊ ተሞክሮው፣ ከዳይሬክተርነትና ከፕሮዲዩሰርነት ጉዞው፣ ከፊልም ሥራ ፈተናዎችና ድሎች ጋር የተሰፋውን ማንነቱን በስፋት ይተርክልናል። ከዚህም ባሻገር፣ ስለ ኢትዮጵያ ሲኒማ ትናንት፣ ዛሬና ነገ፤ ስለ ፊልም አሠራር፣ ስለ ፈጠራ፣ ስለ ትረካ ጥበብና ስለ አዲሱ የፊልም ትውልድ በስፋት እንወያያለን። የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል። 📅 ረቡዕ፣ ህዳር 2፣ 2019 ዓ.ም. 🕠 11:30 ሰዓት 📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ አንድ ምሽት፣ ብዙ ታሪኮች! አንድ መድረክ፣ ሺ ስሜቶች! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
Open in TelegramCISI examinations are now available at AAU School of Commerce The School has become an accredited testing center for the Chartered Institute for Securities & Investment (CISI). If you are pursuing a professional qualification in financial services, you can now sit your CISI exams at AAU. Visit the CISI website for available exams, dates, fees and registration.
Open in TelegramThe John F. Kennedy Memorial Library @ Addis Ababa University: A Landmark Place that has served generations of learners and thinkers for over Six decades.
Open in Telegram"የአፍሪካ ቀጠናዊ ትስስር ማዕከል" ማቋቋም የሚያስችል ስምምነት ተደረገ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ(Expertise France) በጋራ በመሆን "የአፍሪካ ቀጠናዊ ትስስር ማዕከልን ማቋቋም የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ማዕከሉም በቀጠናዊ ትስስርና ልማት ላይ ያተኮረ የማስተርስ ፕሮግራም በመክፈት፣ ብቁ የንግድ ተደራዳሪዎችን እና የፖሊሲ ተንታኞችን እንደሚያፈራ ተጠቁሟል። በስምምነቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ላይ የኢትዮጵያን ስኬት ለማረጋገጥ ለተደረሰው የሶስትዮሽ የጋራ ስምምነት ስኬት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። ዶ/ር ሳሙኤል አያይዘውም ፤ ዩኒቨርሲቲው በግል እና በህዝብ ዘርፍ የሚገኙ ባለሙያዎችን አቅም በመገንባት የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ግቡን እንዲመታ የማድረግ ስራዎችን እንደሚሰራ ገልፀዋል። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ በበኩላቸው ፤ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ(Expertise France) በጋራ የሚመሰርተው "የአፍሪካ ቀጠናዊ ትስስር ማዕከል (ARIC)" በቀጠናዊ ትስስር እና ልማት ላይ ያተኮረ የማስተርስ ፕሮግራም በመክፈት፣ ብቁ የንግድ ተደራዳሪዎችንና የፖሊሲ ተንታኞችን እንደሚያፈራ ተናግረዋል። ስምምነቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ፣የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እና የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ(Expertise France) የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጄን ባፕቲስት ፈርመውታል፡፡
Open in Telegramጉዞ ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! (ሼር በማድረግ የጥበብ ግብዣውን ለሌሎችም አድርሱልን።) የ63ኛ ምሽት እንግዳችን፤ ሕልምን ወደ እውነት፣ ሐሳብን ወደ ተግባር፣ ፈተናን ወደ ዕድል መቀየርን ያሳየች፤ በቴክኖሎጂና በሥራ ፈጠራ ዓለም የራሷን መንገድ የቀየሰች፤ በድፍረቷና በተነሳሽነቷ ለብዙዎች መነሳሳት ምክንያት የሆነችው ሥራ ፈጣሪ ሳምራዊት ፍቅሩ ናት! ጉዞ ምሽት! ከሕይወት አጋጣሚዎች፣ ከችግሮች መፍትሔ የመፍጠር፣ ከሕልም ተነስቶ የራስን መንገድ የመጥረግ ታሪክ ይዛ ወደ መድረካችን ትመጣለች! ከልጅነት ሕልሟ፣ ከትምህርትና ከሕይወት ጉዞዋ፣ ከመጀመሪያዎቹ የሥራ ፈጠራ ሙከራዎቿ፣ ከስኬትና ከውድቀት ትምህርቶቿ፣ ከቴክኖሎጂ ዓለም ተሞክሮዋ፣ እስከ ራይድ (RIDE) የሥራ ፈጠራ ጉዞዋ ድረስ በስፋት ትተርክልናለች። የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል። 📅 ረቡዕ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 ዓ.ም. 🕠 11:30 ሰዓት 📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ አንድ ምሽት፣ ብዙ ታሪኮች አንድ መድረክ፣ ሺ ስሜቶች ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
Open in Telegramየአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል በ62ኛ ሳምንቱ የክብር እንግዳ የነበረችው አንጋፋዋ የሚዲያ ባለሙያ ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ ልምዷን አካፈለች ለዓመታት ብዙ ሺዎችን ስታነጋግር፣ የታሪክ ጓዳቸውን ስትበረብር፤ የሕይወት መንገዳቸውን ስትፈትሽ የኖረችው ልሳነ-ርቱዋ መዓዛ ብሩ በዚህ ታሪካዊ ምሽት የእርሷን የራሷን ታሪክ አውግታለች! ጠያቂዋ ተጠይቃለች! እንግዳ አክባሪዋ በታላቅ ድምቀት ተከብራለች! በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስም ካላቸው እና አንጋፋ ከሆኑት የጋዜጠኝነት ባለሙያዎች አንዷ ለሆነችው መዓዛ ብሩ የምስጋና መርሃግብር ተካሂዷል። በኢትዮጵያ የግል የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች አነሳስና እድገት ውስጥ ቀዳሚውን ሚና ከተጫወቱት መካከል የምትጠቀሰው መዓዛ ብሩ፥ ከባህል ማዕከሉ ሽልማትም ተበርክቶላታል። ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ "መርሃ ስፖርት" በተባለ ጋዜጣ ላይ የስፖርት ዘጋቢ በመሆን የሰራች ሲሆን በብሔራዊ ባንክ "ብሪቱ" የተባለውን የባንኩን ወርሃዊ መጽሔት በዋና አዘጋጅነት መምራቷ የሚታወስ ነው። ከሕይወት ጉዞዋ፤ ከሙያዊ ፍልስፍናዋ፤ ከ"ጨዋታ" እስከ "ሸገር" ተረማምዳ ካለፈቻቸው የሚዲያ ሙያዊ ጉዞዋ፤ ከድልና ከፈተና የሕይወት አጋጣሚዎቿ በጥልቀት ያካፈለችበት፤ በቃለ መጠይቋም ልቧን እና አእምሮዋን ግልጽ አድርጋ በልዩ ትህትና ትልቅ መልእክት ያካፈለችበት ግሩም ምሽት ነበር። ዘወትር ረቡህ ምሽት 11፡30 የሚካሄደው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል ፕሮግራም በተለያዩ እንግዶች የሚቀጥል ይሆናል፡፡
Open in TelegramAAU Connect | Volume XIX | September 2026 Continental Recognition! Edition XIX celebrates AAU’s Mastercard Foundation AHEFT Prize recognition and looks ahead to the opportunities it brings for strengthening clinical excellence. Also, inside are the President’s message as we welcome the new academic year, exploration of AAU’s vibrant activities, and spotlight of its distinguished alumni, community-oriented research and strong partnerships. Join us in celebrating our University community’s achievements and aspirations. Read and share “Continental Recognition” here https://volume.aau.edu.et/2,3d9ea044a47e5d
Open in TelegramNOTICE Gate Digital Access Control and Library Photo Submission See More here https://aau.edu.et/announcements/detail?title=Gate~Digital~Access~Control~and~Library~Pphoto~Submission
Open in Telegramያገር መዓዛ ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! የ62ኛ ምሽት እንግዳችን፤ በኢትዮጵያ የሬዲዮ ጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ የማይፋቅ አሻራዋን ያኖረች፤ በቃል ጥበቧ ትውልድን ያነጋገረች፤ የሰዎችን የሕይወት ታሪክ በጥበብ የምትፈታ፤ አንጋፋዋ የሚዲያ ባለሟል መዓዛ ብሩ ናት! ያገር መዓዛ ምሽት! ለዓመታት ብዙ ሺዎችን ስታነጋግር፣ የታሪክ ጓዳቸውን ስትበረብር፤ የሕይወት መንገዳቸውን ስትፈትሽ የኖረችው ልሳነ-ርቱዋ መዓዛ ብሩ በዚህ ታሪካዊ ምሽት የእርሷን የራሷን ታሪክ ታወጋናለች! ጠያቂዋ ትጠየቃለች! እንግዳ አክባሪዋ ትከበራለች! ከሕይወት ጉዞዋ፤ ከሙያዊ ፍልስፍናዋ፤ ከ"ጨዋታ" እስከ "ሸገር" ተረማምዳ ካለፈቻቸውና ካሳለፈቻቸው የሚዲያ ሙያዊ ጉዞዋ፤ ከማይረሱ የስቱዲዮ ትዝታዎቿ፤ ከድልና ከፈተና የሕይወት አጋጣሚዎቿ ያለስስት ጠልቀን እየቀዳን እንጎነጭ ዘንድ ልቧን፣ አእምሮዋን፣ መንፈሷን፣...ግልጽ አድርጋ በልዩ እመቤታዊ ትህትና ትቀርብልናለች፡፡ እኛም ከአየር ሞገድ እመቤቲቱ ፍቅር የተሞላበት ደግ ልቧ ጠልቀን በነጻነት እንዋኛለን፡፡ ያለገደብ እናወጋታለን፡፡ በፍቅር እናዳምጣታለን! የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል። 📅 ረቡዕ፣ ጥቅምት 17፣ 2019 ዓ.ም. 🕠 11:30 ሰዓት 📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ አንድ ምሽት፣ ብዙ ታሪኮች! አንድ መድረክ፣ ሺህ ስሜቶች! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
Open in Telegramየአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ የ10 ምሁራንን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ደረጃ እድገት አፀደቀ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የ10 ምሁራንን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ደረጃ እድገት አፅድቋል። እድገቱ ምሁራኑ በትምህርትና አካዳሚያዊ አገልግሎት፣ በምርምር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት ያስመዘገቧቸውን የላቀ ውጤቶችና አስተዋፅዖዎች መሠረት ያደረገ ነው። ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ያደጉት ምሁራን፦ 1. ዶ/ር አብርሃም ገብሬ ታረቀኝ - በስትራክቸራል ኢንጂነሪንግ ፕሮፌሰር 2. ዶ/ር አዳነ ቢተው ተገኘ- በሜዲካል ማይክሮባዮሎጂ ፕሮፌሰር 3. ዶ/ር አደይ ፈለቀ ደስታ- በኢንቫይሮሜንታል ማይክሮባዮሎጂ ፕሮፌሰር 4. ዶ/ር ደሳለኝ ያየህ አያል- በዲሳስተር ሪስክ ማኔጂሜንት ፕሮፌሰር 5. ዶ/ር ኃይለልዑል ንጉሴ ዱባለ- በቨተርነሪ ኢፒዲሞሎጂ ፕሮፌሰር 6. ዶ/ር ካሳ ሚካኤል ወ/የሱስ- በማቲማቲክስ ኢጁኬሽን ፕሮፌሰር 7. ዶ/ር ሰለሞን ገነት ገብሬ- በባዮኬሚስትሪ ፕሮፌሰር 8. ዶ/ር ሰለሞን አረዓያ ካሳ- በጀነራል ኢዱኬሽን ፕሮፌሰር 9. ዶ/ር ያረጋል አሳቤ ላቀ- በአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ፕሮፌሰር 10. ዶ/ር የድልፋና ሰጣርጌ መኮንን- በፊዚካል ኬሚስትሪ ፕሮፌሰር ይህ ስኬት ዩኒቨርሲቲው ለአካዳሚያዊ ልህቀት፣ ለምርምርና ፈጠራ እንዲሁም ለማኅበረሰብ አገልግሎት ያበረከተውንና እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለዚህ ከፍተኛው የአካዳሚክ ማዕረግ ለበቃችሁ ምሁራን እንኳን ደስ አላችሁ እያለ፣ በቀጣይ የጀመርነውን የአካዳሚክ፣ ምርምርና አገልግሎት ልቀት ለማምጣት ከመቼውም በላይ እንደምትተጉ በማመን ነው፡፡
Open in Telegram