ፈንድቃ ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! (ሼር በማድረግ የጥበብ ግብዣውን ለሌሎችም አድርሱልን።) የ67ኛ ምሽት እንግዳችን፤ በዳንስ ጥበቡ የዓለምን መድረኮች ያደመቀ፣ የኢትዮጵያን ብዝኃ ባህላዊ ውዝዋዜዎች ከዘመናዊ የፈጠራ ጥበብ ጋር ያዋሐደ፣ ለወጣት ከያኒያን የጥበብ መድረክ የፈጠረ፣ የፈንድቃ የባህል ማዕከል መሥራች፣ የበርካታ ዓለም አቀፍ ሽልማቶች ባለቤት፣ የኢትዮጵያ ባህል አምባሳደር፣ መላኩ በላይ ነው! 🔥 ፈንድቃ ምሽት! ሰውነት ቋንቋ ሲሆን፣ ዳንስስ ምን ይናገራል?... ከአዲስ አበባ ጎዳናዎች እስከ ዓለም አቀፍ የጥበብ መድረኮች፣ ከአዝማሪ ቤት ውዝዋዜ እስከ ፈንድቃ የባህል ማዕከል ምሥረታ፣ ከፈንድቃ እስከ ኢትዮከለር፣ ከእስክስታ እስከ TED መድረክ፣ በአጠቃላይ የሕይወትና የጥበብ ጉዞው ላይ እንወያያለን። 🎭 የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል። 📅 ረቡዕ፣ ኅዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም 🕠 11:30 ሰዓት 📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ አንድ መድረክ፣ ብዙ ታሪኮች! አንድ መድረክ፣ ሺ ስሜቶች! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል! #ፈንድቃምሽት #መላኩበላይ #አንጋፋየኪነጥበብምሽት #MelakuBelay #Fendika #Ethiocolor #EthiopianDance #Eskista #AAUCulturalCenter #WeeklyArtsNight
Открыть в Telegram
AAU-Official
Addis Ababa University
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 30 окт. 2026 г. | 33 200 |
| 31 окт. 2026 г. | 18 200 |
| 1 нояб. 2026 г. | 36 600 |
| 3 нояб. 2026 г. | 19 700 |
| 4 нояб. 2026 г. | 17 200 |
| 6 нояб. 2026 г. | 33 900 |
| 7 нояб. 2026 г. | 21 000 |
| 10 нояб. 2026 г. | 19 000 |
| 20 нояб. 2026 г. | 11 300 |
| 21 нояб. 2026 г. | 8 550 |
| 28 нояб. 2026 г. | 2 140 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры36,6 тыс.Пересылки—Реакции35Комментарии—
- 02Просмотры33,9 тыс.Пересылки—Реакции19Комментарии—
- 03Просмотры33,2 тыс.Пересылки—Реакции18Комментарии—
- 04Просмотры21 тыс.Пересылки—Реакции46Комментарии—
Новые посты
🌟🎭 ኮከብ ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! (ሼር በማድረግ የጥበብ ግብዣውን ለሌሎችም አድርሱልን።) የ66ኛ ምሽት እንግዳችን፤ በትወና ጥበቡ የተመልካቾችን ልብ የገዛ፣ በመድረክ፣ በሬዲዮ፣ በፊልምና በተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች የጥበብ አሻራውን ያሳረፈ፣ በአንድ የትወና ዘውግም ሆነ በአንድ ዓይነት ገጸ ባሕርይ ያልተገደበ፣ ከንጉሥ አጫዎች እስከ ንጉሥ የተለያዩ ገጸ ባሕርያትን በአስደናቂ ብቃት የተጫወተ፣ በእያንዳንዱ ገጸ ባሕርይ ውስጥ እንደልብ የሚገለጥ የኢትዮጵያ የትወና ጥበብ ደማቅ ኮከብ፣ አለማየሁ ታደሰ ነው! 🌟 ኮከብ ምሽት! ኮከብ የሚወለደው እንዴት ነው?... ከሐረር የልጅነት ትዝታዎቹ እስከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከመጀመሪያ የትወና ሙከራዎቹ እስከ ታላላቅ የቴአትር መድረኮች፣ ከ"አንቲጎን" እስከ "ባቢሎን በሳሎን"፣ ከሬዲዮ እስከ የቴሌቪዥን ድራማ፣በአጠቃላይ የጥበብ ጉዞውን... ከዝናው ጀርባ ባሉ ትግሎቹ፣ ፈተናዎቹና ስኬቶቹ ዙሪያ እንወያያለን። 🎭 የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል። 📅 ረቡዕ፣ ኅዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም 🕠 11:30 ሰዓት 📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ 🌟 አንድ ኮከብ፣ ብዙ ገጸ ባሕርያት! 🎭 አንድ መድረክ፣ ሺ ስሜቶች! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
Открыть в TelegramTo All Members of the AAU Community, It is with great sadness that we announce the passing of Dr. László Samodi, Associate Professor of Surgery, who served as a urology surgeon in the Department of Surgery at the College of Health Sciences (CHS). Dr. Samodi began serving the Department of Surgery since 2004 GC. Over nearly two decades of service prior to his recent retirement, he played a vital role in modernizing urology surgery in Ethiopia and was instrumental in establishing postgraduate training within the Department of Surgery at CHS. He will be remembered as a humble and dedicated teacher who was always eager to share his knowledge and skills with his students and colleagues. We extend our deepest condolences and wish strength to his family, colleagues, and friends during this difficult time. The funeral service will take place today, November 20, 2026, at 2:00 PM at Yeka Michael Church
Открыть в Telegram🎬 ሲኒማ ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! (ሼር በማድረግ የጥበብ ግብዣውን ለሌሎችም አድርሱልን።) የ64ኛ ምሽት እንግዳችን፤ ታሪክን በምስል፣ ስሜትን በብርሃንና በጥላ፣ ሕይወትን በሲኒማ ቋንቋ የመተረክ ጥበብን የተካነ፤ ከፎቶግራፍ ተነስቶ በኢትዮጵያ ሲኒማ ውስጥ የራሱን አሻራ ያሳረፈው የፊልም ዳይሬክተር፣ ሲኒማቶግራፈርና ፕሮዲዩሰር ሰውመሆን ይስማው (ሶሚክ) ነው! 🎬 ሲኒማ ምሽት! ከልጅነት ሕልሙ፣ ከመጀመሪያዎቹ የፎቶግራፍና የፊልም ሙከራዎቹ፣ ከሲኒማቶግራፊ ተሞክሮው፣ ከዳይሬክተርነትና ከፕሮዲዩሰርነት ጉዞው፣ ከፊልም ሥራ ፈተናዎችና ድሎች ጋር የተሰፋውን ማንነቱን በስፋት ይተርክልናል። ከዚህም ባሻገር፣ ስለ ኢትዮጵያ ሲኒማ ትናንት፣ ዛሬና ነገ፤ ስለ ፊልም አሠራር፣ ስለ ፈጠራ፣ ስለ ትረካ ጥበብና ስለ አዲሱ የፊልም ትውልድ በስፋት እንወያያለን። የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል። 📅 ረቡዕ፣ ህዳር 2፣ 2019 ዓ.ም. 🕠 11:30 ሰዓት 📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ አንድ ምሽት፣ ብዙ ታሪኮች! አንድ መድረክ፣ ሺ ስሜቶች! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
Открыть в TelegramCISI examinations are now available at AAU School of Commerce The School has become an accredited testing center for the Chartered Institute for Securities & Investment (CISI). If you are pursuing a professional qualification in financial services, you can now sit your CISI exams at AAU. Visit the CISI website for available exams, dates, fees and registration.
Открыть в TelegramThe John F. Kennedy Memorial Library @ Addis Ababa University: A Landmark Place that has served generations of learners and thinkers for over Six decades.
Открыть в Telegram"የአፍሪካ ቀጠናዊ ትስስር ማዕከል" ማቋቋም የሚያስችል ስምምነት ተደረገ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ(Expertise France) በጋራ በመሆን "የአፍሪካ ቀጠናዊ ትስስር ማዕከልን ማቋቋም የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ማዕከሉም በቀጠናዊ ትስስርና ልማት ላይ ያተኮረ የማስተርስ ፕሮግራም በመክፈት፣ ብቁ የንግድ ተደራዳሪዎችን እና የፖሊሲ ተንታኞችን እንደሚያፈራ ተጠቁሟል። በስምምነቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ላይ የኢትዮጵያን ስኬት ለማረጋገጥ ለተደረሰው የሶስትዮሽ የጋራ ስምምነት ስኬት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። ዶ/ር ሳሙኤል አያይዘውም ፤ ዩኒቨርሲቲው በግል እና በህዝብ ዘርፍ የሚገኙ ባለሙያዎችን አቅም በመገንባት የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ግቡን እንዲመታ የማድረግ ስራዎችን እንደሚሰራ ገልፀዋል። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ በበኩላቸው ፤ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ(Expertise France) በጋራ የሚመሰርተው "የአፍሪካ ቀጠናዊ ትስስር ማዕከል (ARIC)" በቀጠናዊ ትስስር እና ልማት ላይ ያተኮረ የማስተርስ ፕሮግራም በመክፈት፣ ብቁ የንግድ ተደራዳሪዎችንና የፖሊሲ ተንታኞችን እንደሚያፈራ ተናግረዋል። ስምምነቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ፣የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እና የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ(Expertise France) የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጄን ባፕቲስት ፈርመውታል፡፡
Открыть в Telegramጉዞ ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! (ሼር በማድረግ የጥበብ ግብዣውን ለሌሎችም አድርሱልን።) የ63ኛ ምሽት እንግዳችን፤ ሕልምን ወደ እውነት፣ ሐሳብን ወደ ተግባር፣ ፈተናን ወደ ዕድል መቀየርን ያሳየች፤ በቴክኖሎጂና በሥራ ፈጠራ ዓለም የራሷን መንገድ የቀየሰች፤ በድፍረቷና በተነሳሽነቷ ለብዙዎች መነሳሳት ምክንያት የሆነችው ሥራ ፈጣሪ ሳምራዊት ፍቅሩ ናት! ጉዞ ምሽት! ከሕይወት አጋጣሚዎች፣ ከችግሮች መፍትሔ የመፍጠር፣ ከሕልም ተነስቶ የራስን መንገድ የመጥረግ ታሪክ ይዛ ወደ መድረካችን ትመጣለች! ከልጅነት ሕልሟ፣ ከትምህርትና ከሕይወት ጉዞዋ፣ ከመጀመሪያዎቹ የሥራ ፈጠራ ሙከራዎቿ፣ ከስኬትና ከውድቀት ትምህርቶቿ፣ ከቴክኖሎጂ ዓለም ተሞክሮዋ፣ እስከ ራይድ (RIDE) የሥራ ፈጠራ ጉዞዋ ድረስ በስፋት ትተርክልናለች። የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል። 📅 ረቡዕ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 ዓ.ም. 🕠 11:30 ሰዓት 📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ አንድ ምሽት፣ ብዙ ታሪኮች አንድ መድረክ፣ ሺ ስሜቶች ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
Yeka Education@dam76Образование48 тыс.
Jimma University Official@jimmauniversityofficialОбразование51,3 тыс.
Havan Academy@havanacademyofficialОбразование43,4 тыс.
Campus Handout@campus_handoutОбразование39 тыс.
Advanced Freshman@advanced_freshmanОбразование36,9 тыс.
Maraki English With abi@marakiengОбразование63,5 тыс.
Matric Fetena@matric_fetenaОбразование34,5 тыс.
Oromia Education Bureau@oromiaeducationbureaudotcomОбразование75,6 тыс.