1. 01
    MikeMike@mike_endale,
    Views673
    Forwards3
    Reactions17
    Comments0
  2. 02
    4-3-3 Tech4-3-3 Tech@tech_433et,

    ኤአይ ኤአይን የሚገነባበት ዘመን እየመጣ ነው አንድ ቀን አንድ ኤአይ ሞዴል የራሱን ተተኪ ቢሠራስ? ይህ ከሳይንሳዊ ልብ ወለድ የወጣ ሀሳብ ሳይሆን፤ የዘርፉ ባለሙያዎች አሁን በቁም ነገር የሚወያዩበት ጉዳይ ሆኗል። Claudeን ያበለጸገው አንትሮፒክ 2026 ላይ When AI Builds Itself በሚል ርዕስ ባወጣው ማብራሪያ ይህንኑ አመልክቷል። እንደ ኩባንያው ገለጻ የኤአይ ሞዴሎች ኮድ መጻፍ ብቻ አይደለም የሚችሉት። አዳዲ ነገሮችን ይሞክራሉ፣ ምርምርን ያፋጥናሉ፣ ውስብስብ የልማት ችግሮችንም ይፈታሉ። ራሱን የሚያሻሽል ኤአይ ምን ማለት ነው? በቴክኖሎጂው ዓለም ይህ ሂደት Recursive Self-Improvement ይባላል። ዘዴው አንድ ተማሪ ከስህተቱ እንደሚማር ነው። ኤአይ የራሱን አፈጻጸም ይመረምራል፣ ድክመቱን ይለያል፣ የተሻለ መንገድም ይቀይሳል። ይህ ዑደት ደጋግሞ ሲሠራ አቅሙ እየጨመረ ይሄዳል። ሂደቱ ሙሉ በሙሉ በራስ የሚመራ ከሆነ አንድ ሞዴል ቀጣዩን፤ የበለጠ አቅም ያለውን ሞዴል ለመፍጠር የሚያስፈልገውን ብዙ የምርምርና ልማት ሥራ ራሱ ሊሠራ ይችላል። ውጤቱም እጅግ የፈጠነ ይሆናል። ጊዜው መቼ ነው? አንትሮፒክ እንደሚገምተው እ.አ.አ በ2027 መጀመሪያ አካባቢ አንዳንድ የኤአይ ሥርዓቶች ትላልቅ የምርምር ቡድኖች የሚሠሯቸውን ሥራዎች በራሳቸው ማከናወን ወይም በእጅጉ ማፋጠን ይችሉ ይሆናል። https://t.me/+-odCEJs1e505ODZi

    Photo
    Views1.29K
    Forwards3
    Reactions14
    Comments—

Tech Telegram channels in Ethiopia