1. 01
    Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻAyu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ@ayuzehabeshanews,
    Просмотры5,44 тыс.
    Пересылки1
    Реакции42
    Комментарии—
  2. 02

    የማሪን ኮማንዶና ባህረኞች በህዳሴው ግድብ ሀይቅ ላይ የሚያደርጉት የንጋት ቅኝት። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ባህረኞች ሙያዊ አቅምን ለማረጋገጥ የሚያስችል የስልጠናና የዝግጁነት ተግባራትን ከማከናወን በተጨማሪ በወንዞች ላይ የሚደርስን የደህንነት ስጋት ለመከላከል አሰሳና ቅኝት ያካሂዳሉ። ኢትዮጵያ የባዕዳንን ከንቱ ቅዥት ሰብራ በዜጎቿ የተባበረ ክንድ በመገደብ የጠላቶቿን አፍ ያዘጋጀችበት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚገኙት የባህር ሀይል አባላት በሀይቅ ላይ የንጋት አሰሳና ቅኝት በማድረግ የሀይቁን ዙሪያ ደህንነት በማረጋገጥ ህዳሴ ግድቡን ከአደጋ ይከላከላሉ። ይህ የተለመደ የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ነው። በዚህ አሰሳና ቅኝት በሀይቁ ወደሚገኙ ደሴቶችና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች ፈጣን የጀልባ እንቅስቃሴ በማድረግ ያላቸውን አቅምና ቁርጠኝነት እያረጋገጡ የህዳሴውን ሰላም አስተማማኝ የማድረግ ተግባራቸው ከሌሎች የሰራዊት ክፍሎችና የፀጥታ አካላት ጋር መረጃ በመለዋወጥ እያስጠበቁም ይገኛሉ ። ሀገራችን ያጣችውን የባህር በር ለማግኝት አሁን ላይ የዲፕሎማሲ ስራዎችን እየሰራች ባለችበት ታሪካዊ ወቅት ባህር ሀይሏም የተቀናጀ የባህር ደህንነት ስራዎችን በማከናወንና የሙያተኞችን አቅም በማሳደግ ዝግጁነቱን በማረጋገጥ ላይ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የቀጠናውን ሠላም በማረጋገጥ አይተኬ ተግባር ከመፈፀሙ ባሻገር ቦንድ በመግዛትና ቀጠተኛ የልማት ተሳታፊ በመሆን አጋርነቱን ያረጋገጠ የሠላምና የልማት ኃይል ነው። ዘጋቢ ሜሮን ጌታነህ ፎቶ ግራፍ ኤርሚያስ ተስፋ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

    Превью ссылки
    Просмотры3,14 тыс.
    Пересылки1
    Реакции43
    Комментарии—

Новостные телеграм-каналы Эфиопии