Категории
Все категории
Страны
Все страны
Список каналовВсе категории и страны
ከአሰሪዋ ጥቃት ለማምለጥ‼ በሀዋሳ ከተማ ታቦር ክፍለ ከተማ (ሲሲሊያ አካባቢ) በአሠሪዋ ድብደባና እገታ ተፈጽሞብኛል ስትል ከአጥር ለመውጣት የሞከረች የቤት ሠራተኛ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ። በአሠሪዋ ተደብድባ ግቢ ውስጥ ተቆልፎባት የነበረችው ተጎጂዋ ከግቢው ለማምለጥ ስትሞክር በብረት አጥር በመወጋቷ በፊቷ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል። የአካባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ ባደረጉት ጥቆማ መሠረት የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጉዳዩን በመመርመር ላይ ይገኛል። ድርጊቱ የሰብዓዊ መብትና የሠራተኛ ክብር ጥሰት በመሆኑ በሕግ አግባብ ተጣርቶ ፍትሕ እንዲሰጠውና አሠሪዎች በሠራተኞች ላይ ከሚፈጽሙት ሕገ-ወጥ እገታና ጥቃት እንዲቆጠቡ አጽንዖት ተሰጥቷል። ዋሱመሐመድ ========== ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
Телеграм-каналы Эфиопии о бизнесе и стартапах