Кабинет
Zelalem Mengistu

Zelalem Mengistu

Zelalem Mengistu YouTube:-https://www.youtube.com/channel/UCLVOIQaz_Qws6Vkiq2cjX1g/videos FB:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100009781051944

Юзернейм
@zelalemmengistu
Категория
Религия
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики8 611−1 за 1 день
Просмотров на пост, 7 дн.183−91,8% к пред. 7 дн.
ERR2,13 %за 7 дней

Подписчики, 30 дней

28 нояб. – 29 нояб.−1 (0%)

Показать таблицей
ДатаПодписчики
28 нояб. 2026 г.8 612
29 нояб. 2026 г.8 611

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
30 окт. 2026 г.4 475
11 нояб. 2026 г.3 110
13 нояб. 2026 г.2 925
16 нояб. 2026 г.2 240
28 нояб. 2026 г.183

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01
    Просмотры4,56 тыс.
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—
  2. 02

    መስቀል ዙፋን አይደለም። የክርስቶስ መስቀል ከንቱ እንዳይሆን በቃል ጥበብ አይደለም። 1ቆሮ. 1፥17 የክርስቶስ መስቀል ከንቱ መሆን ይችላል። ዓላማው የእግዚአብሔር ክብር ሳይሆን የራስ ጥቅም ከሆነ ከንቱ መሆን ይችላል። ግቡ ወንጌልና የቤተ ክርስቲያን ጥቅም ካልሆነ ከንቱ ሊሆን ይችላል። ጳውሎስ ይህን ጥቅስ የጻፈው ግቡ ወንጌልን መስበክ እንጂ ሌላው ቀርቶ ማጥመቅ እንኳ እንዳልሆነ ሲናገር ነው። ከክርስቶስ የማዳን ወንጌል፥ ከመስቀሉ ቃል፥ ቀጥሎ ያለ ማናቸውም ነገር መስቀሉን ከንቱ ያደርገዋል። ጥምቀትም እንኳ ቢሆን። ጥምቀት አያድነንማ! ሌላውስ? ሌላውማ ምን ቦታ እንዳለው መገመት አይከብድም። ጉደኛው ቆንስላ አቶ ጌትነትን ማጣራት ከጀመረ በኋላ አሁን ሥራው መጠናቀቂያ ጊዜው ነው። ማጣራት ከማለት ማጣሪያ ወይም የማጣሪያ ግጥሚያ ቢባል የተሻለ ይመስለኛል። ማጣሪያው የሚሆነው እርሱ በቢሮውና በቆንስላው ላይ ተንፈራጥጦ ተቀምጦ ነው። ይህ ምርመራ መደረግ የነበረበት በቤተ ክርስቲያን መሆኑ በራሱ ስላቅ ነው። ይህ እኮ የመንግሥት ሥራ ነው መሆን የነበረበት። ቤተ ክርስቲያን ወንጀል አጣሪ የሆነችበት ዘመን ላይ መሆናችን ራሱ ቤተ ክርስቲያን የመንግሥትን ሚና እየተጫወተች መሆኗን እና መንግሥትም ለዜጎች እንግልት ደንታ የሌለው መሆኑን አመልካች ይመስለኛል። ስለ አቶ ጌትነት ለማ ወንጀሎች ዛሬ አንድ ብቻ ምሳሌ ልስጥ። ርኆቦት አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የሚባለው ኅብረት የአቶ ጌትነትንን የስልክ ድምጽ ቅጂ ባወጣንበት ማግሥት ተሽቀዳድመው የai ድምጽ ነው ብለው ካወጡት ማኅበሮች አንዱ ነው። ያንን ደብዳቤ የፈረመው በስፍራው ሄዳችሁ ልትመለከቱት እንደምትችሉት ፓስተር ካሳሁን እምሩ የተባለው ፕሬዚደንት ነው። ደብዳቤው የተጻፈው ነሐሴ 19፥ 2018 ነው። ሌተርሄዱ አዲስ ማኅተሙም አዲስ ነው። ለምን? ያ ሰው ከማኅበሩ ፕሬዚደንትነት ከ5 ቀናት በፊት በማኅበሩ መተዳደሪያ አንቀጽ 17 መሠረት ታግዶአል። የታገደባቸው ወንጀሎችም በጥቅሉ በግልጽ በማገጃው ላይ ተጽፈዋል። በዝርዝር በሌላ ሰነድ ይገኛሉ፤ ደብዳቤውን በአስተያየት መስጫ አስቀምጣለሁ። ይህ የታገደው ሰው ለአቶ ጌትነት ወንጀሎች ቁልፍ ተባባሪ ነው፤ የአንድ አካባቢ ሰዎችም ናቸው። ይህ ሰው ወንጀሉ እንዲታጠብለት ተብሎ ከቆንስላው አሻንጉሊት ኮሚሽኖች አንዱ የሰላምና እርቅ ኮሚሽን የሚባል አካል ክሱ ለስልሶ እንዲታገድለት ሚናውን ይጫወታል። እርሱ በዚያ ሥልጣን መቆየት እንዲኖርበት በአስቸኳይ በጥቂት ቀናት ውስጥ ሌላ ተመሳሳይ ስም የያዘ ማኅበር ይቋቋማል። ልብ በሉ፤ ማኅበር ለማቋቋም የሚወስደው ቆንስላዊ ውጣ ውረድ በሙሉ በአንድ ዝላይ ተዘሎ ማለት ነው። ይህ ሰው ነው የአቶ ጌትነትን ድምጽ የai ነው ብሎ ወዲያው የጻፈው። እነዚያ ደብዳቤዎች የተጻፉትም በአቶ ጌትነት ትእዛዝ እንደሆነ መገመት አይከብድም። ያ ብቻ አይደለም፤ የርኆቦት ኅብረት ፕሬዚደንቱን አስወግዶ ሌላ (ፓስተር አዲስ አዳነ) ሲመርጥ፥ አመራረጣችሁ የቆንስላውን መዋቅር ያልተከተለ ነው ብለው ረብሻ ተፈጠረ። ኅብረቱ በደንቡ መሠረት ፕሬዚደንቱን መሻር ይችላል። ቆንስላው ደግሞ ያንን ነው ሊራመድበት የሞከረው። የማጣሪያው ሥራ ሲጀመር አቶ ጌትነት ራሱ የፈለጋቸው ሰዎች በአጣሪው ውስጥ እንዲገቡ አንዳንዶችን በማዘዝ የሚፈልጋቸው ሰዎች እንዲወከሉ፥ ሌሎቹን ደግሞ በመለመንና በማማለድ የሚደግፉት ሰዎች እንዲገቡ ጥረት አድርጓል። በዚህ ተሳክቶለታል። ከወከለችውና ካገደችው ከቃለ ሕይወት እንኳ ለአቶ ጌትነት ወንጀሎች የሚራሩ ሰዎች መኖራቸውን መስማት ያሳፍራል። በውክልናው ጊዜ ከርኆቦት (አሁን ሁለት ሆነዋል) ሁለት አጣሪ መወከል ስለማይችሉ የሚወከለው አንድ ሰው በአቶ ጌትነት የተፈለገው ፓስተር ደሳለኝ ተፈራ የተባለው ከፓስተር ካሳሁን እምሩ ጋር በአጋሮ የአንዲት አጥቢያ ሰው የሆነ ተወከለ። የተወከለው በአዲሱ ፕሬዘደንት ሲሆን ለዚህኛው ውክልና የአዲሱን ፕሬዚደንት ወካይነት ተቀብሎአል። ይህ ሰው ፓስተር ደሳለኝ ከዚህ በፊት በማኅበራዊ ሚድያ እዚያ አጣሪ ኮሚቴ ውስጥ መገኘት እንደሌለበት በግልጽ የተጻፈበት ሰው ነው። እንግዲህ አቶ ጌትነት እቢሮው ተቀምጦ እየተመረመረ የሚሠራቸው ነገሮች፥ የሚያጠፋቸውና ገድሎ የሚቀብራቸው ሰነዶች፥ እዚያው ሆኖ እርሱን እንዲመረምሩ የሚያስመርጣቸው እና የሚያባብላቸው ሰዎች፥ ቀጥሎም እዚያው የሚቆይ ከሆነ ደግሞ (መቼም ቅሌታችን አያልቅምና ሊቀጥል ይችል ይሆናል) ገና ለገና የሚሆንባቸውን ፈርተው የሚሸማቀቁ ሰዎች እየተወኑ ባሉበት በዚህ ሂደት ፍትህ ድል ነሥታ ትወጣለች ማለት የመነመነ ተስፋ ነው። አቶ ጌትነትም ዓይኑን በጨው ታጥቦ እዚያ ቢሮ ይቀመጥ ይሆናል። እኛም ወንጀሎቹን ከመናገር፥ ጉዳዩ በእርግጥም ወንጀል ነውና መንግሥት ጣልቃ እስኪገባ ድረስ፥ ዝም ማለት አንችልም። መስቀል ዙፋን አይደለም። ዘላለም ነኝ።

    Текст
    Просмотры4,39 тыс.
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—
  3. 03

    የዚህን ሰው አንዱን የአምልኮ ወይም የቴሌቪዥን ስርጭቱን (አሁን የከሰረ ነጋዴ ከሆነ በኋላ ብሶበታል፤ ግን የቀድሞውንም ቢሆን) ብታዩት፥ የሚስቡ ልብሶች ለብሶ ስብከት ሲቀነስ ክርስቶስ፥ ዲስኩር ሲቀነስ መስቀል ደስኳሪና ሰባኪ ነው። ይህ አንድ ምሳሌ ነው። ወደ አገራችን ሐሰተኛ ነቢያት እና ሐሰተኛ ሐዋርያት ስንመጣም፥ ሁሉም ክርስቶስንና መስቀሉን ወይም ደሙን አይሰብኩትም። የማይሰብኩት ስለሚኮንናቸው ነው። እርሱን ሰብከው መቅጠፍና መዋሸት አይችሉም፤ ገንዘብ መዝረፍና መበዝበዝ አይችሉም። ክርስቶስን ሰብከው ራሳቸውን ማሳየት አይችሉም። ከሁሉም በላይ ክርስቶስን የማይሰብኩት ክርስቶስን ስለማያውቁት ነው። ድነትን አያውቋትም፤ የደሙን የማዳን ሥራ አያውቁትም፤ የማያውቁትን እንዲሰብኩ መጠበቅም የለብንም። ሐሰተኛ ነቢይ ኢዩ ጩፋ ሃቻምና በዲላ ያደረገው ዘረፋ ጆሮ ጭው የሚያደርግ ነበር። በጆንያዎችና ከረጢቶች የታጨቁት ብሮች ባንክ እንዲገቡ የባንክ ሠራተኞች ትርፍ ሰዓት እና ባንክም ከሥራ ሰዓት ውጪ ለሊሎች ሳይሆን ለእርሱ ሰዎች ብቻ ክፍት ሆኖ ቆይቶ ነበር። አምና ተመሳሳይ ነገር ሊያደርግ ሲል አሠራሩ ሕገ ወጥ ነው ተብሎ ታገደ። ጩፋ ዘንድሮ ማባበያዎችንና ማስፈራሪያዎችን በመጠቀም፥ በዞንም በክልልም ውስጥ የሚገኙ፥ (ለምሳሌ፥ እንደ የመካነ የሱሱን ቄስ ወልዴ አየለ እና የቃለ ሕይወቱ አቶ በጸጋ ጂላ የመሰሉ) የቆንስላ መሪዎችን መጠቀሚያ በማድረግ እንደገና የቡና ምርት ገንዘብ ዝርፊያ ለማድረግ እየታገለ ነው። የመካነ ኢየሱስ እና የቃለ ሕይወት አብያተ ክርስቲያናት በሐሰተኛ ነቢያት ላይ ቆራጥ አቋም ቢኖራቸውም እነዚህ የቆንስላ መሪዎች ለቤተ ክርስቲያናቸው አስተምህሮና አቋም ሳይሆን ለቆንስላው አባል ሐሰተኛ ነቢይ ወግነው መቆማቸው ያስደነግጣል። በዚህ መልኩ አስተምህሮ ገበያ ላይ ለልዋጭ ትቀርባለች ማለት ነው። ሌሎችም አሉ፤ ሁለቱን ብቻ በስም የጠቀስኩት የመካነ የሱስ እና የቃለ ሕይወት ሰዎች ስለሆኑ እና ሁለቱም በሐሰተኞች ላይ በቅርቡ አቋማቸውን ስለገለጡ ነው። የዲላ ከተማ ቃለ ሕይወት አጥቢያዎች ኅብረት በአቋም የኢዩ ጩፋን እንቅስቃሴ በግልጽ ተቃውሞ ሲጽፍ፥ ቆንስላው ውስጥ ያሉ የቃለ ሕይወት ሰዎች ደግሞ ሲደግፉ፥ ይህ ቆንስላ በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናው ላይ ምን እየሠራ እንዳለ ደማቅ ማሳያ ነው። ቆንስላው በአገር አቀፍ ደረጃ መበከል ብቻ ሳይሆን እላይ የሚሠራው የነጌትነት ለማ መንፈስ አሠራር በተዋረድ እስከ ታች ድረስ ወንጌላዊ ክርስትና ላይ የሚሠራው እኩይ ሥራይ ቀላል አይደለም። ሙስናና ጉቦ እላይም እታችም አለ። ማስፈራራትና ባለ ሥልጣናትን መጠቀም እላይም እታችም አለ። ለዲላ ቅዱሳን የምለው ይህ ነው። 1. ሐሰተኛ ነቢይ ኢዩ ጩፋ ሐሰተኛ ነቢይ ነው። ክርስቶስ ስላልተቀበለ ክርስቶስን መስበክ አይችልም። ክርስቶስን የት ተቀብሎ በማን እግር ስር ደቀ መዝሙሮ ሆኖ ተኮትኩቶ እንዳደገ፥ የት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ቅዱስ እንደተማረ ጠይቁት። ልክ እንደ ቲ ቢ ጆሽዋ ማለት ነው። ቲ ቢ የት ጌታን ተቀበልክ? ማን በጌታ ትምህርት አሳደገህ? ወዘተ ሲባል እናቱ ማኅፀን ሆኖ ጌታን እንደተቀበለ እንደተናገረው ማለት ነው። ጌታን የማያውቅ ሰው ጌታን አይሰብክምና ራሱን አይስበካችሁ። 2. ሐሰተኛ ነቢይ ኢዩ ጩፋ ዲላ ቢመጣና እስቴዲየም ቢሰብክ መስቀሉ (የመስቀሉ ቃል) ያለው ከእስቴዲየሙ ውጪ በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኖቻችሁ እንደሆነ እወቁ። 3. ሐሰተኛ ነቢይ ኢዩ ጩፋ እና መሰሎቹ የቡና ጊዜ እየጠበቁ ወደ ቡና አምራች ዞኖች የሚመጡት ለምንም ሳይሆን ለገንዘብ ጠረጋ ብቻ እንደሆነ እወቁ። ጌታ ማስተዋልን ይስጣችሁ። ዘላለም ነኝ።

    Текст
    Просмотры3,63 тыс.
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—
  4. 04
    Просмотры3 тыс.
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—

Новые посты

#1160Текст

Открыть в Telegram
Просмотры3 630+27%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#1159Фото

መስቀሉ ያለው ከእስቴዲየሙ ውጪ ነው። ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን። 2ቆሮ. 4፥5 በዚህ ጥቅስ ጳውሎስ ሁለት ዋና ነገሮችን ተናገረ፤ አንዱ ራሱን ሳይሆን ክርስቶስን መስበክ ነው። ሌላው ራሱን ላገለገላቸው ሰዎች ባሪያ ማድረግ ነው። ሁለቱንም አስቧቸው። ጳውሎስ ክርስቶስን ሰባኪ ነበረ፤ የተጠራበትን ምስክርነቶች ሲመሰክር እንኳ፥ (ለምሳሌ፥ ሐዋ. 22 እና 26) ስለ ራሱ እና በእጁ ስለተደረጉትን ድንቆች ሳይሆን ክርስቶስን ነበር የመሰከረው። መታወቂያውን ማሳየትና አርማውን ማውለብለብ ሳይሆን ያዳነውን ጌታ ነበር ያሳየው። በመካከላቸው መከፋፈልና አምልኮተ ሰብእ በነበራቸው፥ ‘እኔ የእገሌ ነኝ!’ ለሚሉት የቆሮንቶስ ሰዎች ሲጽፍ፥ ‘ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን? . . . ለማጥመቅ ክርስቶስ አልላከኝምና፥ ወንጌልን ልሰብክ እንጂ፤ የክርስቶስ መስቀል ከንቱ እንዳይሆን በቃል ጥበብ አይደለም። . . . አጵሎስ እንግዲህ ምንድር ነው? ጳውሎስስ ምንድር ነው? በእነርሱ እጅ ያመናችሁ አገልጋዮች ናቸው፤ ለእያንዳንዳቸውም ጌታ እንደ ሰጣቸው ያገለግላሉ።’ ነበር ያላቸው። 1ቆሮ 1፥13-16 እና 3፥5። ራሱን ቢሰብክ ጳውሎስ ራሱን የሚሰብክባቸው ርእሶች ነበሩት፥ ልደቱ፥ እድገቱ፥ ትምህርቱ፥ የውሸት ያልሆኑ ዶክትሬቶቹ፥ አይሁዳዊነቱ፥ ሃይማኖታዊ ቅንዓቱ፥ ያለ ነቀፋ የሆነ ሃይማኖታዊ ጽድቁ፥ የሚያውለበልባቸው ብዙ ባርኔጣዎች አሉት። አድርጎ አያውቅም። የዘመናችን ሐሰተኞች ክርስቶስን ሲጠሩ ለንግድ ማስታወቂያነት ብቻ መሆኑን ማወቅ ከተሳነንን ቆይተናል። ለምሳሌ፥ ቤኒ ሂንን በቅርብ ደጋግሜ ጽፌበታለሁ፤ የዚህን ሰው አንዱን የአምልኮ . . .

Открыть в Telegram
Просмотры2 590−9%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#1157Текст

መስቀል ዙፋን አይደለም። የክርስቶስ መስቀል ከንቱ እንዳይሆን በቃል ጥበብ አይደለም። 1ቆሮ. 1፥17 የክርስቶስ መስቀል ከንቱ መሆን ይችላል። ዓላማው የእግዚአብሔር ክብር ሳይሆን የራስ ጥቅም ከሆነ ከንቱ መሆን ይችላል። ግቡ ወንጌልና የቤተ ክርስቲያን ጥቅም ካልሆነ ከንቱ ሊሆን ይችላል። ጳውሎስ ይህን ጥቅስ የጻፈው ግቡ ወንጌልን መስበክ እንጂ ሌላው ቀርቶ ማጥመቅ እንኳ እንዳልሆነ ሲናገር ነው። ከክርስቶስ የማዳን ወንጌል፥ ከመስቀሉ ቃል፥ ቀጥሎ ያለ ማናቸውም ነገር መስቀሉን ከንቱ ያደርገዋል። ጥምቀትም እንኳ ቢሆን። ጥምቀት አያድነንማ! ሌላውስ? ሌላውማ ምን ቦታ እንዳለው መገመት አይከብድም። ጉደኛው ቆንስላ አቶ ጌትነትን ማጣራት ከጀመረ በኋላ አሁን ሥራው መጠናቀቂያ ጊዜው ነው። ማጣራት ከማለት ማጣሪያ ወይም የማጣሪያ ግጥሚያ ቢባል የተሻለ ይመስለኛል። ማጣሪያው የሚሆነው እርሱ በቢሮውና በቆንስላው ላይ ተንፈራጥጦ ተቀምጦ ነው። ይህ ምርመራ መደረግ የነበረበት በቤተ ክርስቲያን መሆኑ በራሱ ስላቅ ነው። ይህ እኮ የመንግሥት ሥራ ነው መሆን የነበረበት። ቤተ ክርስቲያን ወንጀል አጣሪ የሆነችበት ዘመን ላይ መሆናችን ራሱ ቤተ ክርስቲያን የመንግሥትን ሚና እየተጫወተች መሆኗን እና መንግሥትም ለዜጎች እንግልት ደንታ የሌለው መሆኑን አመልካች ይመስለኛል። ስለ አቶ ጌትነት ለማ ወንጀሎች ዛሬ አንድ ብቻ ምሳሌ ልስጥ። ርኆቦት አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የሚባለው ኅብረት የአቶ ጌትነትንን የስልክ ድምጽ ቅጂ ባወጣንበት ማግሥት ተሽቀዳድመው የai ድምጽ ነው ብለው ካወጡት ማኅበሮች አንዱ ነው። ያንን ደብዳቤ የፈረመው በስፍራው ሄዳችሁ ልትመለከቱት እንደምትችሉት ፓስተር ካሳሁን እምሩ የተባለው ፕሬዚደንት ነው። ደብዳቤው የተጻፈው ነሐሴ 19፥ 2018 ነው። ሌተርሄዱ አዲስ ማኅተሙም አዲስ ነው። ለምን? ያ ሰው ከማኅበሩ ፕሬዚደንትነት ከ5 ቀናት በፊት በማኅበሩ መተዳደሪያ አንቀጽ 17 መሠረት ታግዶአል። የታገደባቸው ወንጀሎችም በጥቅሉ በግልጽ በማገጃው ላይ ተጽፈዋል። በዝርዝር በሌላ ሰነድ ይገኛሉ፤ ደብዳቤውን በአስተያየት መስጫ አስቀምጣለሁ። ይህ የታገደው ሰው ለአቶ ጌትነት ወንጀሎች ቁልፍ ተባባሪ ነው፤ የአንድ አካባቢ ሰዎችም ናቸው። ይህ ሰው ወንጀሉ እንዲታጠብለት ተብሎ ከቆንስላው አሻንጉሊት ኮሚሽኖች አንዱ የሰላምና እርቅ ኮሚሽን የሚባል አካል ክሱ ለስልሶ እንዲታገድለት ሚናውን ይጫወታል። እርሱ በዚያ ሥልጣን መቆየት እንዲኖርበት በአስቸኳይ በጥቂት ቀናት ውስጥ ሌላ ተመሳሳይ ስም የያዘ ማኅበር ይቋቋማል። ልብ በሉ፤ ማኅበር ለማቋቋም የሚወስደው ቆንስላዊ ውጣ ውረድ በሙሉ በአንድ ዝላይ ተዘሎ ማለት ነው። ይህ ሰው ነው የአቶ ጌትነትን ድምጽ የai ነው ብሎ ወዲያው የጻፈው። እነዚያ ደብዳቤዎች የተጻፉትም በአቶ ጌትነት ትእዛዝ እንደሆነ መገመት አይከብድም። ያ ብቻ አይደለም፤ የርኆቦት ኅብረት ፕሬዚደንቱን አስወግዶ ሌላ (ፓስተር አዲስ አዳነ) ሲመርጥ፥ አመራረጣችሁ የቆንስላውን መዋቅር ያልተከተለ ነው ብለው ረብሻ ተፈጠረ። ኅብረቱ በደንቡ መሠረት ፕሬዚደንቱን መሻር ይችላል። ቆንስላው ደግሞ ያንን ነው ሊራመድበት የሞከረው። የማጣሪያው ሥራ ሲጀመር አቶ ጌትነት ራሱ የፈለጋቸው ሰዎች በአጣሪው ውስጥ እንዲገቡ አንዳንዶችን በማዘዝ የሚፈልጋቸው ሰዎች እንዲወከሉ፥ ሌሎቹን ደግሞ በመለመንና በማማለድ የሚደግፉት ሰዎች እንዲገቡ ጥረት አድርጓል። በዚህ ተሳክቶለታል። ከወከለችውና ካገደችው ከቃለ ሕይወት እንኳ ለአቶ ጌትነት ወንጀሎች የሚራሩ ሰዎች መኖራቸውን መስማት ያሳፍራል። በውክልናው ጊዜ ከርኆቦት (አሁን ሁለት ሆነዋል) ሁለት አጣሪ መወከል ስለማይችሉ የሚወከለው አንድ ሰው በአቶ ጌትነት የተፈለገው ፓስተር ደሳለኝ ተፈራ የተባለው ከፓስተር ካሳሁን እምሩ ጋር በአጋሮ የአንዲት አጥቢያ ሰው የሆነ ተወከለ። የተወከለው በአዲሱ ፕሬዘደንት ሲሆን ለዚህኛው ውክልና የአዲሱን ፕሬዚደንት ወካይነት ተቀብሎአል። ይህ ሰው ፓስተር ደሳለኝ ከዚህ በፊት በማኅበራዊ ሚድያ እዚያ አጣሪ ኮሚቴ ውስጥ መገኘት እንደሌለበት በግልጽ የተጻፈበት ሰው ነው። እንግዲህ አቶ ጌትነት እቢሮው ተቀምጦ እየተመረመረ የሚሠራቸው ነገሮች፥ የሚያጠፋቸውና ገድሎ የሚቀብራቸው ሰነዶች፥ እዚያው ሆኖ እርሱን እንዲመረምሩ የሚያስመርጣቸው እና የሚያባብላቸው ሰዎች፥ ቀጥሎም እዚያው የሚቆይ ከሆነ ደግሞ (መቼም ቅሌታችን አያልቅምና ሊቀጥል ይችል ይሆናል) ገና ለገና የሚሆንባቸውን ፈርተው የሚሸማቀቁ ሰዎች እየተወኑ ባሉበት በዚህ ሂደት ፍትህ ድል ነሥታ ትወጣለች ማለት የመነመነ ተስፋ ነው። አቶ ጌትነትም ዓይኑን በጨው ታጥቦ እዚያ ቢሮ ይቀመጥ ይሆናል። እኛም ወንጀሎቹን ከመናገር፥ ጉዳዩ በእርግጥም ወንጀል ነውና መንግሥት ጣልቃ እስኪገባ ድረስ፥ ዝም ማለት አንችልም። መስቀል ዙፋን አይደለም። ዘላለም ነኝ።

Открыть в Telegram
Просмотры4 390+54%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—

Все посты

Связи