Переслано из አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
እንዲሁ : ያልቀረችው : የቅዱስ : እስጢፋኖስ : ጸሎት ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለክርስቶስ በመመስከሩ አይሁድ ‹‹ ወንጀለኛ ነው ሕጋችንን ተላልፏል ሰድቦናል ›› በማለት በሐሰት መስክረው እንዲሞት ፈረዱበት ፡፡ በሕጋቸው ወንጀለኛ ነው የሚሉትን ሰው የሚፈርዱበት በድንጋይ ተወግሮ እንዲሞት ነበር በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይም እውነትን በማስተማሩ ፍርዱን አጸኑበት ። ከከተማው በስተውጭ አውጥተው ድንጋይ እያነሱ ይወግሩት ጀመር እርሱ ግን ‹‹ ጌታ ሆይ ይህንኃጢአትአትቁጠርባቸው ›› እያለ ስለእነርሱ ይጸልይ ነበር ። የቅዱስ እስጢፋኖስ ጸሎት እንዲሁ አልቀረም ባለማወቅ ከሚያጠፉት መካከል አንዱ የነበረው በቀደመ ስሙ ሳኦል በኋላ ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስን ከዚህ ስሕተቱ ተመልሶ ክርስቲያን በመሆን ወንጌልን አስተምሮ ብዙ መልእክታትን እንዲጽፍ የታደገች ጸሎት ናት ።
Открыть в Telegram







