የእስራኤል የብሔራዊ ደኅንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን ግቪር፣ በክርስቲያን ቀሳውስትና አብያተ ክርስቲያናት ላይ መትፋትን «ጥንታዊ የአይሁድ ባህል» ብለው የገለጹበት ንግግር፣ በኢየሩሳሌም በክርስቲያን አማኞች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ተከትሎ ዳግም ከፍተኛ ትችት ቀስቅሷል። ሚኒስትሩ ቀደም ሲል ለእስራኤሉ የሕዝብ ሚዲያ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ አንዳንድ አይሁዳውያን በገዳማት ወይም በቀሳውስት አጠገብ ሲያልፉ እንደሚተፉ በመጥቀስ፣ ድርጊቱ የግድ እንደ ሕግ መጣስ እንደማይቆጠር ተከራክረው ነበር። አይሁዶቹ ክርስቲያኖችን እንደ ጣኦት አምላኪ የሚመለከቷቸው ሲሆን ሙስሊሙን በተመለከተ የጥላቻው ሁኔታ እንዳለ ቢሆንም ጣኦት አምላኪ ናቸው የሚል ፍርጃ ግን የላቸውም። ሙስሊሙ የቀደምት ነቢያትን ንጹህ ተውሒድ እንደሚያምን አበክረው ይመሰክራሉ! የሕያ ኢብኑ ኑህ
Открыть в Telegram
የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | ለንግድ፣ ለህክምና ወይም ለጉብኝት ወደ ቱርክ፣ ዱባይ እና የተለያዩ ሀገራት ለመጓዝ ካሰባችሁ ፈሲሩ ትራቭል የትኬት ጉዳያችሁን በኃላፊነት ያጠናቅቃል። እንግልት የሌለበት ጉዞ ለማድረግ ስትፈልጉ በዋትስአፕ አግኙን፦ https://wa.me/qr/5CWCIMYBZLCJB1
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 16 нояб. 2026 г. | 4 625 |
| 17 нояб. 2026 г. | 4 195 |
| 18 нояб. 2026 г. | 3 673 |
| 19 нояб. 2026 г. | 5 390 |
| 20 нояб. 2026 г. | 3 800 |
| 21 нояб. 2026 г. | 3 320 |
| 22 нояб. 2026 г. | 3 720 |
| 24 нояб. 2026 г. | 2 440 |
| 26 нояб. 2026 г. | 1 360 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры5,39 тыс.Пересылки—Реакции135Комментарии—
- 02Просмотры5 тыс.Пересылки—Реакции134Комментарии—
- 03Просмотры4,81 тыс.Пересылки—Реакции91Комментарии—
- 04Просмотры4,44 тыс.Пересылки—Реакции141Комментарии—
Новые посты
የቀድሞው የካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ከ1992 እስከ 2024 ዓ.ል ድረስ በግል ማስታወሻቸው ላይ ያሰፈሯቸው አስደንጋጭ ምሥጢሮች በቅርቡ በመጽሐፍ መልክ ይፋ ሆነዋል። ታዋቂው የዜና አውታር ሲኤንኤን ባወጣው ዘገባ መሠረት፣ ፖፕ ፍራንሲስ በመሪነት ዘመናቸው ለሁለት ዓመታት የዘለቀ ከባድ መንፈሳዊ ቀውስ ውስጥ ገብተው እንደነበርና «የእሳት ዓይን» ያለውን ሰይጣንን ሦስት ጊዜ በራዕይ እንደተጋፈጡት በገዛ እጃቸው ጽፈዋል። በተለይም እ.ኤ.አ. በ2018 በቺሊ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመውን የቀሳውስት የወሲብ ጥቃት ቅሌት ጎብኝተው ወደ ሮም ከተመለሱ በኋላ፣ በአንድ ስብሰባ ላይ ሰይጣንን አይተውት ጎርናና በሆነ የድል አድራጊነት ድምፅ «አሁን የፈለግኩትን ሁሉ አግኝቻለሁ» ሲላቸው እንደሰሙ በማስታወሻቸው አስፍረዋል። ከዚህም በላይ ከመኝታቸው በፊት ከጣዖት አምልኮ ጋር የተያያዘውን «የገሃነም መግቢያ በር» በራዕይ ተመልክተው በታላቅ ድንጋጤ እንደተሸበሩ ገልጸዋል። በተጨማሪም በ2021 እና 2022 ዓ.ል መካከል የሥልጣን ፈተናና «ሁሉንም በራሴ መፍታት እችላለሁ» የሚል የትዕቢት ስሜት «እስከ ገሃነም ደጃፍ ድረስ» አድርሷቸው እንደነበር ተናዝዘዋል። በሚሊዮኖች ዘንድ ታላቅ መንፈሳዊ መሪ ተደርገው ይታዩ የነበሩት ፖፕ ፍራንሲስ፣ በውስጣቸው ይህን ያህል የሰይጣን ጥቃት፣ የገሃነም ፍርሃትና መንፈሳዊ ቀውስ ተሸክመው ማለፋቸውን የገዛ የእጅ ጽሑፋቸው በይፋ አጋልጧል! ይህንን ታሪክ እንደ አንድ ሙስሊም ያጋራሁት በሰው ድካም ለመደሰት ሳይሆን፣ ሃይማኖታዊ ተቋማት ለሰው ልጆች የሚሰጡትን የተጋነነ መንፈሳዊ ካባና በውስጡ ያለውን እውነተኛ ቀውስ ሚዛናዊ በሆነ መነጽር እንድንመለከተው ነው። በሚሊዮኖች ዘንድ «እንከን የለሽ መንፈሳዊ መሪ» ተብሎ የሚታይ አካል እንኳን፣ ከጣዖት አምልኮ ጋር የተያያዘውን «የገሃነም መግቢያ በር» እና የሰይጣንን ጥቃት በገዛ እጁ መመስከሩ፤ በሰው ሠራሽ ሥርዓትና አማላጅነት ላይ የተመሠረተ መንገድ የት ድረስ እንደሚያደርስ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ይህም እስልምና ሰውን ከሰው ጥገኝነት አላቆ፣ ያለ ምንም ጳጳስና አማላጅ ወይንም የንስሀ አባት ከአንዱ ፈጣሪ ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ ንጹሕ የተውሒድ ብርሃን መሆኑን ይበልጥ እንድናደንቅ ያደርገናል። የሕያ ኢብኑ ኑህ
Открыть в Telegramየግ*ድያ ቅስቀሳን ማውገዝ ወንጀል የሆነበት የጽንፈኝነት ዘመን! የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ቶማስ፣ ከሰሞኑ ሙስሊሞችን ስለ መግደል ሲናገር የነበረውን ወጣት መነኩሴ (አባ ፍቅረ ማርያምን) በማውገዛቸው ምክንያት በጽንፈኞች ከፍተኛ ዘመቻ ተከፍቶባቸዋል። እጅግ አሳዛኙ ነገር የጽንፈኞቹ የተገለበጠ ሚዛን ነው፤ በአደባባይ ሙስሊሞችን ስለ መ*ግደል ያወራን ሰው «ተበደለ» እያሉ ሲከላከሉለት፣ ይህንን አደገኛ የጥላቻ ንግግር ያወገዙትን ሊቀ ጳጳስ ግን «አባ ፍቅረ ማርያምን እያስፈራሩ ነው» በሚል ዘመቻ እያዋከቧቸው ይገኛሉ። ግድያን የሚሰብክ የሚወደስበት፣ ግድያን ያወገዘ ግን በጽንፈኞች ዘመቻ የሚከፈትበት ይህ ድርጊት የጥላቻ ፖለቲካው ምን ያህል አደገኛ ደረጃ ላይ እንደደረሰ በግልጽ ያሳያል። ለሀገር ሰላምና ለሕዝብ አብሮነት የሚያስብ ሁሉ፣ ከግድያ ሰባኪዎች ሳይሆን ጽንፈኝነትን በድፍረት ከሚያወግዙ የሃይማኖት አባቶች ጎን መቆም ይኖርበታል! የሕያ ኢብኑ ኑህ
Открыть в TelegramПереслано из አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ
«መጽሐፉ የሚለውን ነው የተናገርነው»! - ከግብጹ ዘካርያስ ቡትሮስ እስከ ዛሬ የቲክቶክ ተሳዳቢዎች፤ ራሳቸው የቀሰቀሱት የዕውቀት ማዕበል! ታሪክ ራሱን ይደግማል፤ ሞኞች ግን ከታሪክ አይማሩም! ከዓመታት በፊት በግብፅ ምድር ዘካርያስ ቡትሮስ የተባለ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቄስ ተነሥቶ ነበር። እስከዚያን ጊዜ ድረስ የግብፅ ሙስሊሞች ጠንካራ የኦርቶዶክስ ማኅበረሰብ ባለበት ሀገር ውስጥ ቢኖሩም፣ በንጽጽራዊ ሃይማኖት ጥናት ላይ ብዙም ገፍተው የሚታወቁ አልነበሩም። ዘካርያስ ቡትሮስ ግን በቴሌቪዥን መስኮት እየወጣ እስልምናን እጅግ ጸያፍና ባለጌ በሆነ መንገድ መሳደብ ጀመረ። የግብፅ ሙስሊም ምሁራንና የሀገር ሽማግሌዎች ወደ ቤተክርስቲያኗ አባቶች ሄደው «ይህንን ሰውዬ ሥርዓት አስይዙት» በሚል ሲጠይቁ የቤተ ክርስቲያኗ ሰው የሰጡት ትዕቢት የተሞላበት ምላሽ አንድ ነበር፦ «እርሱ መጽሐፉ የሚለውን ነው የተናገረው እንጂ አዲስ ነገር አልተናገረም፤ መልስ ስጡት!» ያቺ ቀን በግብፅ ታሪክ ውስጥ ትልቅ የዕውቀት አብዮት የፈነዳባት ዕለት ሆነች! በዚያ ትዕቢት የተቀሰቀሱት የግብፅ ሙስሊሞች ከቋንቋቸው ተሻግረው መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎበታል የሚባልበትን ጥንታዊ ቋንቋ ዕብራይስጥን እና ግሪክን ጭምር አጥንተው በመውጣት፣ የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እያንዳንዱን ድርሳናት በማጥናት ቃል በቃል በትነው አደባባይ ላይ አሰጡት! ዛሬ በግብፅ ምድር አንድም የኦርቶዶክስ ሰባኪ በሙለ የራስ መተማመን ስለ እስልምና መተንፈስ ወደ ሚቸገርበት ደረጃ ተሸጋገሩ። በምዕራቡ ዓለም (በአሜሪካና በእንግሊዝ) የታየውም ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለም። እንደ ዴቪድ ዉድ እና ጄይ ስሚዝ ያሉ የምዕራቡ ዓለም ጸረ-ኢስላም ሰባኪያን በአብያተ ክርስቲያናት ድጋፍ «መረጃውን ነው የጠቀስነው» እያሉ እስልምናን ሲያንቋሽሹ፣ ምላሹ የሆነው በዓለም አቀፍ መድረኮች (እንደ Speakers' Corner ባሉ) የመጽሐፍ ቅዱስን ቴክስችዋል ክሪቲሲዝም እና የሥላሴን መሠረት-አልባነት የሚያጋልጡ ኃያላን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዳዒዎችና ተመራማሪዎች መፍለቅ ነው! ዛሬ በሀገራችን እየሆነ ያለውም የዚሁ ታሪክ ግልባጭ ነው! ጥቂት መድረኩ ላይ የተኮለኮሉ የቤተ ክርስቲያኗ ሰዎች እስልምናን በጸያፍ ቃላት ሲሳደቡ፣ ተከላካዮቻቸው የሚሰጡት ምላሽ ያው የግብጾቹን ቃል የኮረጀ ነው፦ «መጽሐፉን ነው የተናገረው እንጂ አዲስ ነገር አልተናገረም!» እውነቱን ለመናገር ይህንን የምጽፈው ስለ ጥቂት ተራ ባለጌ ግለሰቦች ተጨንቄ አይደለም፤ ነገር ግን እኛ የነዚህን ግለሰቦች ብልግና ችላ ብለን ባለፍንበት ሰዓት፣ የእነርሱ አክቲቪስትና መንጋ ግን ይህንን ጸያፍ ተግባር እንደ ታላቅ ጀግና አንሥቶ ሲወራጭበት አይቼ በመደመሜ ነው! የቤተክርስቲያኗ ምእመናን ምን ያህል በጥልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እየኖሩ እንዳሉ የሚያሳብቀውም ይኸው ነው፤ ተስፋ ከመቁረጣቸው የተነሣ ያገኙትን ይህንን የብልግና ዕድል ላለማባከን መከራቸውን እየበሉ መሆኑ በግልጽ ያስታውቃል። ነገር ግን እነዚህ ወገኖች የቀሰቀሱትን እሳት አላወቁትም! እኛ ወደ ኋላ የምንልበት አንዳችም ምክንያት የለም። ከዚህ በኋላ የቤተክርስቲያኗን ሥርዓተ ትምህርትና ጥንታዊ ድርሳናት (ከግእዝ የተተረጎሙትንም ያልተተረጎሙትንም) አደባባይ ላይ በማውጣት፣ ለተራ ስብከት ሳይሆን ከጥልቅ ምርምር ጋር አያይዞ ለምእመኑ እውነቱን የሚገልጥ፣ በእስልምና ዙሪያ የሚነሣውንም ማንኛውንም የሐሰት ክስ ቃል በቃል በትኖ መልስ የሚሰጥ ኃያል ትውልድ የሚነሣበት ዘመን ይመጣ ዘንድ ግን መደላድል እየፈተጠረ ነው! ከዚያ በኋላ ራሳቸው ያስነሡትን ይህንን የዕውቀት ማዕበል በደንብ መቋቋም ከቻሉ አብረን የምንመለከተው ይሆናል። ለወገኖቻችን የምነግራችሁ ትልቁ እውነት ግን አንድ ነው፦ ይህ የዛሬው ሁካታ ለመጪው ጊዜ እጅግ ትልቅ መደላደል፣ መነሻና የማንቂያ ደወል መሆኑን ፈጽሞ እንዳትረሱ! https://t.me/Abuyusra3
Открыть в Telegramሰሞኑን ታዋቂው ዓለም አቀፍ የምርምር ተቋም ፒው ሪሰርች ሴንተር ባወጣው አዲስ ጥናት መሠረት፣ እስልምና እ.ኤ.አ. በ2035 ክርስትናን በመብለጥ በዓለም ላይ ትልቁ ሃይማኖት (ቁጥር አንድ) እንደሚሆን ይፋ አድርጓል። ይህንን ታሪካዊ ሪፖርት ተከትሎ ብዙ ትልልቅ የሀገራችን ሚዲያዎች ዜናውን ሲዘግቡ፣ ሆን ብለው አንድ የተዛባ ትርክት ለመፍጠር ሲሞክሩ ተስተውሏል። እርሱም፦ «እስልምና ቁጥር አንድ የሚሆነው ሙስሊሞች ብዙ ልጆችን ስለሚወልዱ ብቻ ነው» የሚል ግማሽ እውነት ነው! ነገር ግን እነዚህ ሚዲያዎች ከዚያው ከፒው ሪሰርች ጥናት ውስጥ ቆርጠው የደበቁትን ሌላኛውን አስገራሚ እውነታ ስንመለከት፣ የእስልምና የበላይነት ሚስጥር ከመወለድ ባለፈ የአስተምህሮው ጥንካሬ፣ ለሰው ልጅ አእምሮ መስማማትና የመሳብ አቅም መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦ በምዕራቡ ዓለም ክርስትናን በገፍ እየለቀቁ የሚወጡ ሚሊዮኖች! በዚሁ የፒው ሪሰርች ጥናት መሠረት፣ ከ2020 እስከ 2070 ባለው ጊዜ ውስጥ ክርስትና በሃይማኖት ለውጥ ምክንያት ብቻ የ105 ሚሊዮን ተከታዮች "የተጣራ ኪሳራ" ያጋጥመዋል! በተለይ በምዕራቡ ዓለም፣ ለምሳሌ በአሜሪካ ብቻ የክርስቲያኖች ቁጥር ከ217 ሚሊዮን ወደ 174 ሚሊዮን ቁልቁል ይወርዳል። ለምን? ምክንያቱም ቆም ብሎ የሚያስብና ምክንያታዊ የሆነ አካል፣ ከአእምሮ ጋር የሚጋጩ አስተምህሮቶችን መሸከም አቅቶት ክርስትናን በገፍ እየለቀቀ ወደ እስልምና አልያም ሃይማኖት-የለሽነት እየጎረፈ ስለሆነ ነው። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ወግ አጥባቂ አካባቢዎች፣ አንዳንድ ሚዲያዎችና የጥላቻ አራማጆች የእስልምናን መስፋፋት ለማሳነስና ለማድበስበስ ቢሞክሩም፣ የመረጃ ዘመን የፈጠረው የአስተሳሰብ መነቃቃት ግን እዚህም ደርሷል። ልቡንና አእምሮውን ከፍቶ እውነትን የሚመረምር ማንኛውም ሰው፣ ከጭፍን ትርክት ወጥቶ የእስልምናን ንጹሕ የአንድ አምላክ አምልኮ ተውሒድ እና ምክንያታዊ አስተምህሮ ሲያይ በጎ ምልከታ ማዳበሩና ወደ እውነቱ መሳቡ የማይቀር ሐቅ ነው። እስልምና የዓለም ቁጥር አንድ ሃይማኖት ሆኖ የሚወጣው በሕዝብ ብዛት (በመወለድ) ብቻ ሳይሆን፣ የሰውን ልጅ ተፈጥሮና አእምሮ በሚማርክ ንጹሕ መልእክቱ፣ በተከታዮቹ ጽናትና ወደ እርሱ በሚጎርፉ አዳዲስ አማኞች ኃያልነት ጭምር ነው! ሚዲያዎች ዜናውን ቢቆራርጡትም፣ እውነታውን ግን መቀየር አይችሉም። https://t.me/Yahyanuhe
Открыть в Telegramከሰሞኑ ጌታቸው ሽፈራው ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ለመወንጀል የያዘው የፕሮፓጋንዳ ስልት፣ ከምሬት ይልቅ ሳቅ የሚያጭር አስገራሚ ድራማ ሆኗል። እንደ ጌታቸው ትርክት ከሆነ፣ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በመላው አማራ ክልል እየተዘዋወረ የጦርነት ሥልጠና እየሰጠ ነው! የጌታቸውን የከተሞች ዝርዝር ስትመለከቱ፣ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ልክ እንደ ሆሊውድ ፊልም ገጸ-ባሕርይ በአንድ ቀን ውስጥ ከቦታ ቦታ የመብረር ልዩ ተዓምር ያለው ይመስላል። ጠዋት ባቲ ላይ ሲያሰለጥን ውሎ፣ ረፋድ ላይ ጎጃም ይከሰታል፤ ከሰዓት በኋላ ጎንደር ገብቶ ሥልጠናውን ይቀጥልና፣ ማታ ላይ ደግሞ ሸዋ ድረስ ወርዶ ያሰለጥናል! በዚህ ፍጥነትና የቦታ ሽፋን ከሄደማ፣ ጌታቸው ሽፈራው አህመዲን ጀበልን ከኢማም አሕመድ (ግራኝ) የበለጠ ታሪካዊ ገድል እየሰጠው ነው ማለት ነው! እርግጥ ነው፤ ጌታቸው ከብአዴን ጀምሮ ያደገበት ሙያ በመሆኑ ፕሮፓጋንዳ መፍጠር አዲሱ አይደለም። ትላንት ጎንደር ላይ በንጹሐን ሙስሊሞች ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግፍ ለመሸፈን ሲል፣ በአህመዲን ጀበል ላይ ዓይን ያወጣ ሐሰት ሲቀባጥር የነበረ «የፕሮፓጋንዳ ኪላኪል» መሆኑን የሚያውቅ ያውቀዋል። ዛሬም ያንኑ የተለመደ የቅጥፈት ካሴቱን ገልብጦ እያጫወተው ይገኛል። ከቀልዱና ከፕሮፓጋንዳው ወጣ ብለን ቁምነገሩን ስንመለከት ግን ጉዳዩ እጅግ አደገኛና አሳሳቢ ነው! ጌታቸው ሽፈራው እስራኤል ውስጥ ሞቅ ባለ ቤቱ ተቀምጦ የሚጽፋቸው እነዚህ ጽሑፎች ተራ የፌስቡክ ወሬዎች አይደሉም። በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሙስሊሞችን ፎቶ እዚህው ፌስቡክ ላይ የከተማ ስም ሰርች ሲያደርግ ያገኘውን ሁሉ እየለጠፈ፣ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችና ስሜታዊ ታዳጊዎች በእነዚህ ንጹሐን ዜጎች ላይ እርምጃ እንዲወስዱ በቀጥታ የግድያ ጥሪ (Hit-list) እያስተላለፈ ይገኛል። እዚህ ላይ መላው የኢትዮጵያ ሙስሊም፣ በተለይም በአማራ ክልል የሚኖረው ማኅበረሰብ ሊያጤነው የሚገባ ወሳኝ ነጥብ አለ፦ ከጌታቸው ሽፈራው ጀርባ ያለው «ጋላቢ» ማነው? ጌታቸው ሽፈራው ማን እንደሆነ ታሪኩ ምስክር ነው። እርሱ ራሱን ችሎ የሚቆም የፖለቲካም ሆነ የሃሳብ ባለቤት አይደለም፤ ከብአዴን ዘመን አንስቶ ሥጋ ሲወረወርለት ያንን ይዞ የሚጮህ፣ የከፈለው አካል እንደፈለገ የሚጋልበው ቅጥረኛ ፈረስ ነው። ከዚህ ቀደም ከሀገር ያስወጡት የቀድሞ የብአዴን አለቆቹ ተጠራርገው ሲባረሩና የሚጋልበውና የሚከፍለው አካል ሲጠፋ ለአንድ ዓመት ሙሉ ድምፁን አጥፍቶ ጠፍቶ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። አሁን ድንገት ተመልሶ ይህንን ሁሉ የጥላቻና የፍረጃ ዘመቻ በሙስሊሙ ላይ የከፈተው አዲስ ጋላቢ ስላገኘ ነው! ይህ ጋላቢ በሆነ መዋቅር ውስጥ ያለ ሴረኛ ቡድን ሊሆን ይችላል፣ ወይም በክልሉ ያለውን ውጥረት ወደ ሃይማኖት ግጭት ለመቀየር የሚፈልግ ሌላ ኃይልም ሊሆን ይችላል። ስለሆነም፦ • በአማራ ክልል የሚገኙ የመጅሊስ አመራሮችና ንቁ ሙስሊሞች ይህንን የጌታቸውን የዒላማ ማድረግ ዘመቻ በቀላሉ ሳይመለከቱት ለራሳቸው ደህንነት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። • ሁላችንም ጩኸቱን ብቻ ሳይሆን ጋላቢውን ማጥናትና መለየት ይኖርብናል። ምክንያቱም ነገ በአማራ ክልል በሚገኙ ንጹሐን ሙስሊሞች ላይ አንዳችም ጉዳት ቢደርስ፣ ተጠያቂው እስራኤል ተቀምጦ የሚጮኸው ቅጥረኛ ብቻ ሳይሆን፣ ከጀርባ ሆኖ የጋለበውና እንዲጽፍ የሚያዘው አካል ጭምር መሆኑን ለታሪክም ለፍትሕም መዝግቦ መያዝ የግድ ይላል!
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
⚓️ሐመረ ኖኅ⚓️@orthotekРелигия24,5 тыс.
አፍሪካ ቲቪ | Africa TV1@africatv1Религия22 тыс.
CHRIST TUBE - ETH🇪🇹@christ_tubeРелигия25,5 тыс.
S֮t֮r֮o֮n֮g֮ I֮m֮a֮n֮🇵🇸@strong_imanРелигия21,1 тыс.- ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት@bibleztewahidoРелигия26,1 тыс.
ኢስላሚክ ጥያቄዎች እና ሐዲሶች 📚@islamic_picture_wallpaperРелигия20,6 тыс.
የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ@alateriqilhaqРелигия20,6 тыс.- ☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA@huda4ethРелигия26,2 тыс.