የእስራኤል የብሔራዊ ደኅንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን ግቪር፣ በክርስቲያን ቀሳውስትና አብያተ ክርስቲያናት ላይ መትፋትን «ጥንታዊ የአይሁድ ባህል» ብለው የገለጹበት ንግግር፣ በኢየሩሳሌም በክርስቲያን አማኞች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ተከትሎ ዳግም ከፍተኛ ትችት ቀስቅሷል። ሚኒስትሩ ቀደም ሲል ለእስራኤሉ የሕዝብ ሚዲያ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ አንዳንድ አይሁዳውያን በገዳማት ወይም በቀሳውስት አጠገብ ሲያልፉ እንደሚተፉ በመጥቀስ፣ ድርጊቱ የግድ እንደ ሕግ መጣስ እንደማይቆጠር ተከራክረው ነበር። አይሁዶቹ ክርስቲያኖችን እንደ ጣኦት አምላኪ የሚመለከቷቸው ሲሆን ሙስሊሙን በተመለከተ የጥላቻው ሁኔታ እንዳለ ቢሆንም ጣኦት አምላኪ ናቸው የሚል ፍርጃ ግን የላቸውም። ሙስሊሙ የቀደምት ነቢያትን ንጹህ ተውሒድ እንደሚያምን አበክረው ይመሰክራሉ! የሕያ ኢብኑ ኑህ
Открыть в TelegramПосты канала የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
የቀድሞው የካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ከ1992 እስከ 2024 ዓ.ል ድረስ በግል ማስታወሻቸው ላይ ያሰፈሯቸው አስደንጋጭ ምሥጢሮች በቅርቡ በመጽሐፍ መልክ ይፋ ሆነዋል። ታዋቂው የዜና አውታር ሲኤንኤን ባወጣው ዘገባ መሠረት፣ ፖፕ ፍራንሲስ በመሪነት ዘመናቸው ለሁለት ዓመታት የዘለቀ ከባድ መንፈሳዊ ቀውስ ውስጥ ገብተው እንደነበርና «የእሳት ዓይን» ያለውን ሰይጣንን ሦስት ጊዜ በራዕይ እንደተጋፈጡት በገዛ እጃቸው ጽፈዋል። በተለይም እ.ኤ.አ. በ2018 በቺሊ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመውን የቀሳውስት የወሲብ ጥቃት ቅሌት ጎብኝተው ወደ ሮም ከተመለሱ በኋላ፣ በአንድ ስብሰባ ላይ ሰይጣንን አይተውት ጎርናና በሆነ የድል አድራጊነት ድምፅ «አሁን የፈለግኩትን ሁሉ አግኝቻለሁ» ሲላቸው እንደሰሙ በማስታወሻቸው አስፍረዋል። ከዚህም በላይ ከመኝታቸው በፊት ከጣዖት አምልኮ ጋር የተያያዘውን «የገሃነም መግቢያ በር» በራዕይ ተመልክተው በታላቅ ድንጋጤ እንደተሸበሩ ገልጸዋል። በተጨማሪም በ2021 እና 2022 ዓ.ል መካከል የሥልጣን ፈተናና «ሁሉንም በራሴ መፍታት እችላለሁ» የሚል የትዕቢት ስሜት «እስከ ገሃነም ደጃፍ ድረስ» አድርሷቸው እንደነበር ተናዝዘዋል። በሚሊዮኖች ዘንድ ታላቅ መንፈሳዊ መሪ ተደርገው ይታዩ የነበሩት ፖፕ ፍራንሲስ፣ በውስጣቸው ይህን ያህል የሰይጣን ጥቃት፣ የገሃነም ፍርሃትና መንፈሳዊ ቀውስ ተሸክመው ማለፋቸውን የገዛ የእጅ ጽሑፋቸው በይፋ አጋልጧል! ይህንን ታሪክ እንደ አንድ ሙስሊም ያጋራሁት በሰው ድካም ለመደሰት ሳይሆን፣ ሃይማኖታዊ ተቋማት ለሰው ልጆች የሚሰጡትን የተጋነነ መንፈሳዊ ካባና በውስጡ ያለውን እውነተኛ ቀውስ ሚዛናዊ በሆነ መነጽር እንድንመለከተው ነው። በሚሊዮኖች ዘንድ «እንከን የለሽ መንፈሳዊ መሪ» ተብሎ የሚታይ አካል እንኳን፣ ከጣዖት አምልኮ ጋር የተያያዘውን «የገሃነም መግቢያ በር» እና የሰይጣንን ጥቃት በገዛ እጁ መመስከሩ፤ በሰው ሠራሽ ሥርዓትና አማላጅነት ላይ የተመሠረተ መንገድ የት ድረስ እንደሚያደርስ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ይህም እስልምና ሰውን ከሰው ጥገኝነት አላቆ፣ ያለ ምንም ጳጳስና አማላጅ ወይንም የንስሀ አባት ከአንዱ ፈጣሪ ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ ንጹሕ የተውሒድ ብርሃን መሆኑን ይበልጥ እንድናደንቅ ያደርገናል። የሕያ ኢብኑ ኑህ
Открыть в Telegramየግ*ድያ ቅስቀሳን ማውገዝ ወንጀል የሆነበት የጽንፈኝነት ዘመን! የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ቶማስ፣ ከሰሞኑ ሙስሊሞችን ስለ መግደል ሲናገር የነበረውን ወጣት መነኩሴ (አባ ፍቅረ ማርያምን) በማውገዛቸው ምክንያት በጽንፈኞች ከፍተኛ ዘመቻ ተከፍቶባቸዋል። እጅግ አሳዛኙ ነገር የጽንፈኞቹ የተገለበጠ ሚዛን ነው፤ በአደባባይ ሙስሊሞችን ስለ መ*ግደል ያወራን ሰው «ተበደለ» እያሉ ሲከላከሉለት፣ ይህንን አደገኛ የጥላቻ ንግግር ያወገዙትን ሊቀ ጳጳስ ግን «አባ ፍቅረ ማርያምን እያስፈራሩ ነው» በሚል ዘመቻ እያዋከቧቸው ይገኛሉ። ግድያን የሚሰብክ የሚወደስበት፣ ግድያን ያወገዘ ግን በጽንፈኞች ዘመቻ የሚከፈትበት ይህ ድርጊት የጥላቻ ፖለቲካው ምን ያህል አደገኛ ደረጃ ላይ እንደደረሰ በግልጽ ያሳያል። ለሀገር ሰላምና ለሕዝብ አብሮነት የሚያስብ ሁሉ፣ ከግድያ ሰባኪዎች ሳይሆን ጽንፈኝነትን በድፍረት ከሚያወግዙ የሃይማኖት አባቶች ጎን መቆም ይኖርበታል! የሕያ ኢብኑ ኑህ
Открыть в TelegramПереслано из አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ
«መጽሐፉ የሚለውን ነው የተናገርነው»! - ከግብጹ ዘካርያስ ቡትሮስ እስከ ዛሬ የቲክቶክ ተሳዳቢዎች፤ ራሳቸው የቀሰቀሱት የዕውቀት ማዕበል! ታሪክ ራሱን ይደግማል፤ ሞኞች ግን ከታሪክ አይማሩም! ከዓመታት በፊት በግብፅ ምድር ዘካርያስ ቡትሮስ የተባለ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቄስ ተነሥቶ ነበር። እስከዚያን ጊዜ ድረስ የግብፅ ሙስሊሞች ጠንካራ የኦርቶዶክስ ማኅበረሰብ ባለበት ሀገር ውስጥ ቢኖሩም፣ በንጽጽራዊ ሃይማኖት ጥናት ላይ ብዙም ገፍተው የሚታወቁ አልነበሩም። ዘካርያስ ቡትሮስ ግን በቴሌቪዥን መስኮት እየወጣ እስልምናን እጅግ ጸያፍና ባለጌ በሆነ መንገድ መሳደብ ጀመረ። የግብፅ ሙስሊም ምሁራንና የሀገር ሽማግሌዎች ወደ ቤተክርስቲያኗ አባቶች ሄደው «ይህንን ሰውዬ ሥርዓት አስይዙት» በሚል ሲጠይቁ የቤተ ክርስቲያኗ ሰው የሰጡት ትዕቢት የተሞላበት ምላሽ አንድ ነበር፦ «እርሱ መጽሐፉ የሚለውን ነው የተናገረው እንጂ አዲስ ነገር አልተናገረም፤ መልስ ስጡት!» ያቺ ቀን በግብፅ ታሪክ ውስጥ ትልቅ የዕውቀት አብዮት የፈነዳባት ዕለት ሆነች! በዚያ ትዕቢት የተቀሰቀሱት የግብፅ ሙስሊሞች ከቋንቋቸው ተሻግረው መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎበታል የሚባልበትን ጥንታዊ ቋንቋ ዕብራይስጥን እና ግሪክን ጭምር አጥንተው በመውጣት፣ የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እያንዳንዱን ድርሳናት በማጥናት ቃል በቃል በትነው አደባባይ ላይ አሰጡት! ዛሬ በግብፅ ምድር አንድም የኦርቶዶክስ ሰባኪ በሙለ የራስ መተማመን ስለ እስልምና መተንፈስ ወደ ሚቸገርበት ደረጃ ተሸጋገሩ። በምዕራቡ ዓለም (በአሜሪካና በእንግሊዝ) የታየውም ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለም። እንደ ዴቪድ ዉድ እና ጄይ ስሚዝ ያሉ የምዕራቡ ዓለም ጸረ-ኢስላም ሰባኪያን በአብያተ ክርስቲያናት ድጋፍ «መረጃውን ነው የጠቀስነው» እያሉ እስልምናን ሲያንቋሽሹ፣ ምላሹ የሆነው በዓለም አቀፍ መድረኮች (እንደ Speakers' Corner ባሉ) የመጽሐፍ ቅዱስን ቴክስችዋል ክሪቲሲዝም እና የሥላሴን መሠረት-አልባነት የሚያጋልጡ ኃያላን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዳዒዎችና ተመራማሪዎች መፍለቅ ነው! ዛሬ በሀገራችን እየሆነ ያለውም የዚሁ ታሪክ ግልባጭ ነው! ጥቂት መድረኩ ላይ የተኮለኮሉ የቤተ ክርስቲያኗ ሰዎች እስልምናን በጸያፍ ቃላት ሲሳደቡ፣ ተከላካዮቻቸው የሚሰጡት ምላሽ ያው የግብጾቹን ቃል የኮረጀ ነው፦ «መጽሐፉን ነው የተናገረው እንጂ አዲስ ነገር አልተናገረም!» እውነቱን ለመናገር ይህንን የምጽፈው ስለ ጥቂት ተራ ባለጌ ግለሰቦች ተጨንቄ አይደለም፤ ነገር ግን እኛ የነዚህን ግለሰቦች ብልግና ችላ ብለን ባለፍንበት ሰዓት፣ የእነርሱ አክቲቪስትና መንጋ ግን ይህንን ጸያፍ ተግባር እንደ ታላቅ ጀግና አንሥቶ ሲወራጭበት አይቼ በመደመሜ ነው! የቤተክርስቲያኗ ምእመናን ምን ያህል በጥልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እየኖሩ እንዳሉ የሚያሳብቀውም ይኸው ነው፤ ተስፋ ከመቁረጣቸው የተነሣ ያገኙትን ይህንን የብልግና ዕድል ላለማባከን መከራቸውን እየበሉ መሆኑ በግልጽ ያስታውቃል። ነገር ግን እነዚህ ወገኖች የቀሰቀሱትን እሳት አላወቁትም! እኛ ወደ ኋላ የምንልበት አንዳችም ምክንያት የለም። ከዚህ በኋላ የቤተክርስቲያኗን ሥርዓተ ትምህርትና ጥንታዊ ድርሳናት (ከግእዝ የተተረጎሙትንም ያልተተረጎሙትንም) አደባባይ ላይ በማውጣት፣ ለተራ ስብከት ሳይሆን ከጥልቅ ምርምር ጋር አያይዞ ለምእመኑ እውነቱን የሚገልጥ፣ በእስልምና ዙሪያ የሚነሣውንም ማንኛውንም የሐሰት ክስ ቃል በቃል በትኖ መልስ የሚሰጥ ኃያል ትውልድ የሚነሣበት ዘመን ይመጣ ዘንድ ግን መደላድል እየፈተጠረ ነው! ከዚያ በኋላ ራሳቸው ያስነሡትን ይህንን የዕውቀት ማዕበል በደንብ መቋቋም ከቻሉ አብረን የምንመለከተው ይሆናል። ለወገኖቻችን የምነግራችሁ ትልቁ እውነት ግን አንድ ነው፦ ይህ የዛሬው ሁካታ ለመጪው ጊዜ እጅግ ትልቅ መደላደል፣ መነሻና የማንቂያ ደወል መሆኑን ፈጽሞ እንዳትረሱ! https://t.me/Abuyusra3
Открыть в Telegramሰሞኑን ታዋቂው ዓለም አቀፍ የምርምር ተቋም ፒው ሪሰርች ሴንተር ባወጣው አዲስ ጥናት መሠረት፣ እስልምና እ.ኤ.አ. በ2035 ክርስትናን በመብለጥ በዓለም ላይ ትልቁ ሃይማኖት (ቁጥር አንድ) እንደሚሆን ይፋ አድርጓል። ይህንን ታሪካዊ ሪፖርት ተከትሎ ብዙ ትልልቅ የሀገራችን ሚዲያዎች ዜናውን ሲዘግቡ፣ ሆን ብለው አንድ የተዛባ ትርክት ለመፍጠር ሲሞክሩ ተስተውሏል። እርሱም፦ «እስልምና ቁጥር አንድ የሚሆነው ሙስሊሞች ብዙ ልጆችን ስለሚወልዱ ብቻ ነው» የሚል ግማሽ እውነት ነው! ነገር ግን እነዚህ ሚዲያዎች ከዚያው ከፒው ሪሰርች ጥናት ውስጥ ቆርጠው የደበቁትን ሌላኛውን አስገራሚ እውነታ ስንመለከት፣ የእስልምና የበላይነት ሚስጥር ከመወለድ ባለፈ የአስተምህሮው ጥንካሬ፣ ለሰው ልጅ አእምሮ መስማማትና የመሳብ አቅም መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦ በምዕራቡ ዓለም ክርስትናን በገፍ እየለቀቁ የሚወጡ ሚሊዮኖች! በዚሁ የፒው ሪሰርች ጥናት መሠረት፣ ከ2020 እስከ 2070 ባለው ጊዜ ውስጥ ክርስትና በሃይማኖት ለውጥ ምክንያት ብቻ የ105 ሚሊዮን ተከታዮች "የተጣራ ኪሳራ" ያጋጥመዋል! በተለይ በምዕራቡ ዓለም፣ ለምሳሌ በአሜሪካ ብቻ የክርስቲያኖች ቁጥር ከ217 ሚሊዮን ወደ 174 ሚሊዮን ቁልቁል ይወርዳል። ለምን? ምክንያቱም ቆም ብሎ የሚያስብና ምክንያታዊ የሆነ አካል፣ ከአእምሮ ጋር የሚጋጩ አስተምህሮቶችን መሸከም አቅቶት ክርስትናን በገፍ እየለቀቀ ወደ እስልምና አልያም ሃይማኖት-የለሽነት እየጎረፈ ስለሆነ ነው። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ወግ አጥባቂ አካባቢዎች፣ አንዳንድ ሚዲያዎችና የጥላቻ አራማጆች የእስልምናን መስፋፋት ለማሳነስና ለማድበስበስ ቢሞክሩም፣ የመረጃ ዘመን የፈጠረው የአስተሳሰብ መነቃቃት ግን እዚህም ደርሷል። ልቡንና አእምሮውን ከፍቶ እውነትን የሚመረምር ማንኛውም ሰው፣ ከጭፍን ትርክት ወጥቶ የእስልምናን ንጹሕ የአንድ አምላክ አምልኮ ተውሒድ እና ምክንያታዊ አስተምህሮ ሲያይ በጎ ምልከታ ማዳበሩና ወደ እውነቱ መሳቡ የማይቀር ሐቅ ነው። እስልምና የዓለም ቁጥር አንድ ሃይማኖት ሆኖ የሚወጣው በሕዝብ ብዛት (በመወለድ) ብቻ ሳይሆን፣ የሰውን ልጅ ተፈጥሮና አእምሮ በሚማርክ ንጹሕ መልእክቱ፣ በተከታዮቹ ጽናትና ወደ እርሱ በሚጎርፉ አዳዲስ አማኞች ኃያልነት ጭምር ነው! ሚዲያዎች ዜናውን ቢቆራርጡትም፣ እውነታውን ግን መቀየር አይችሉም። https://t.me/Yahyanuhe
Открыть в Telegramከሰሞኑ ጌታቸው ሽፈራው ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ለመወንጀል የያዘው የፕሮፓጋንዳ ስልት፣ ከምሬት ይልቅ ሳቅ የሚያጭር አስገራሚ ድራማ ሆኗል። እንደ ጌታቸው ትርክት ከሆነ፣ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በመላው አማራ ክልል እየተዘዋወረ የጦርነት ሥልጠና እየሰጠ ነው! የጌታቸውን የከተሞች ዝርዝር ስትመለከቱ፣ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ልክ እንደ ሆሊውድ ፊልም ገጸ-ባሕርይ በአንድ ቀን ውስጥ ከቦታ ቦታ የመብረር ልዩ ተዓምር ያለው ይመስላል። ጠዋት ባቲ ላይ ሲያሰለጥን ውሎ፣ ረፋድ ላይ ጎጃም ይከሰታል፤ ከሰዓት በኋላ ጎንደር ገብቶ ሥልጠናውን ይቀጥልና፣ ማታ ላይ ደግሞ ሸዋ ድረስ ወርዶ ያሰለጥናል! በዚህ ፍጥነትና የቦታ ሽፋን ከሄደማ፣ ጌታቸው ሽፈራው አህመዲን ጀበልን ከኢማም አሕመድ (ግራኝ) የበለጠ ታሪካዊ ገድል እየሰጠው ነው ማለት ነው! እርግጥ ነው፤ ጌታቸው ከብአዴን ጀምሮ ያደገበት ሙያ በመሆኑ ፕሮፓጋንዳ መፍጠር አዲሱ አይደለም። ትላንት ጎንደር ላይ በንጹሐን ሙስሊሞች ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግፍ ለመሸፈን ሲል፣ በአህመዲን ጀበል ላይ ዓይን ያወጣ ሐሰት ሲቀባጥር የነበረ «የፕሮፓጋንዳ ኪላኪል» መሆኑን የሚያውቅ ያውቀዋል። ዛሬም ያንኑ የተለመደ የቅጥፈት ካሴቱን ገልብጦ እያጫወተው ይገኛል። ከቀልዱና ከፕሮፓጋንዳው ወጣ ብለን ቁምነገሩን ስንመለከት ግን ጉዳዩ እጅግ አደገኛና አሳሳቢ ነው! ጌታቸው ሽፈራው እስራኤል ውስጥ ሞቅ ባለ ቤቱ ተቀምጦ የሚጽፋቸው እነዚህ ጽሑፎች ተራ የፌስቡክ ወሬዎች አይደሉም። በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሙስሊሞችን ፎቶ እዚህው ፌስቡክ ላይ የከተማ ስም ሰርች ሲያደርግ ያገኘውን ሁሉ እየለጠፈ፣ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችና ስሜታዊ ታዳጊዎች በእነዚህ ንጹሐን ዜጎች ላይ እርምጃ እንዲወስዱ በቀጥታ የግድያ ጥሪ (Hit-list) እያስተላለፈ ይገኛል። እዚህ ላይ መላው የኢትዮጵያ ሙስሊም፣ በተለይም በአማራ ክልል የሚኖረው ማኅበረሰብ ሊያጤነው የሚገባ ወሳኝ ነጥብ አለ፦ ከጌታቸው ሽፈራው ጀርባ ያለው «ጋላቢ» ማነው? ጌታቸው ሽፈራው ማን እንደሆነ ታሪኩ ምስክር ነው። እርሱ ራሱን ችሎ የሚቆም የፖለቲካም ሆነ የሃሳብ ባለቤት አይደለም፤ ከብአዴን ዘመን አንስቶ ሥጋ ሲወረወርለት ያንን ይዞ የሚጮህ፣ የከፈለው አካል እንደፈለገ የሚጋልበው ቅጥረኛ ፈረስ ነው። ከዚህ ቀደም ከሀገር ያስወጡት የቀድሞ የብአዴን አለቆቹ ተጠራርገው ሲባረሩና የሚጋልበውና የሚከፍለው አካል ሲጠፋ ለአንድ ዓመት ሙሉ ድምፁን አጥፍቶ ጠፍቶ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። አሁን ድንገት ተመልሶ ይህንን ሁሉ የጥላቻና የፍረጃ ዘመቻ በሙስሊሙ ላይ የከፈተው አዲስ ጋላቢ ስላገኘ ነው! ይህ ጋላቢ በሆነ መዋቅር ውስጥ ያለ ሴረኛ ቡድን ሊሆን ይችላል፣ ወይም በክልሉ ያለውን ውጥረት ወደ ሃይማኖት ግጭት ለመቀየር የሚፈልግ ሌላ ኃይልም ሊሆን ይችላል። ስለሆነም፦ • በአማራ ክልል የሚገኙ የመጅሊስ አመራሮችና ንቁ ሙስሊሞች ይህንን የጌታቸውን የዒላማ ማድረግ ዘመቻ በቀላሉ ሳይመለከቱት ለራሳቸው ደህንነት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። • ሁላችንም ጩኸቱን ብቻ ሳይሆን ጋላቢውን ማጥናትና መለየት ይኖርብናል። ምክንያቱም ነገ በአማራ ክልል በሚገኙ ንጹሐን ሙስሊሞች ላይ አንዳችም ጉዳት ቢደርስ፣ ተጠያቂው እስራኤል ተቀምጦ የሚጮኸው ቅጥረኛ ብቻ ሳይሆን፣ ከጀርባ ሆኖ የጋለበውና እንዲጽፍ የሚያዘው አካል ጭምር መሆኑን ለታሪክም ለፍትሕም መዝግቦ መያዝ የግድ ይላል!
Открыть в Telegramአልሐምዱሊላህ! በአላህ ፈቃድ በነቢዩ (ﷺ) ስብዕና ላይ ለሚነሱ ብዥታዎች ምላሽ ለመስጠት ያዘጋጀነው «ጽልመቱን የገፈፈው ብርሃን» መጽሐፍ፣ ለንባብ ይበልጥ ምቹ እንዲሆን ታስቦ ሳይዙ ተቀንሶ በሞባይል አፕሊኬሽን ቀርቧል። በኪስዎ ይዘው በቀላሉ እንዲጠቀሙበት ተደርጎ የተዘጋጀው ይህ አፕሊኬሽን፦ • መጠኑ አነስተኛ የሆነ፦ በስልክዎ ላይ ብዙ ቦታ ሳይዝ በፍጥነት የሚጫን። • ያለ ኢንተርኔት የሚሠራ፦ አንዴ ካወረዱት በኋላ በማንኛውም ቦታ ዳታ ሳይፈጅ የሚያገለግል። • ለንባብ ምቹ፦ ከማውጫው ላይ የሚፈልጉትን ርዕስ ነክተው በቀጥታ ወደ ገጹ የሚወስድና ቃላትን ለመፈለግ (Search) የሚያስችል። • አጋዥ አማራጮች ያሉት፦ ያቆሙበትን ገጽ ራሱ የሚያስታውስና ቁልፍ ነጥቦችን ማስታወሻ መጻፍ የሚያስችል። ይህንን ሥራ አውርደው እንዲያነቡትና ለሌሎችም በማጋራት የአጅሩ ተቋዳሽ እንዲሆኑ በትህትና እንጋብዛለን። አፑን የሰራው ወንድማችንንም አላህ መልካም ስራውን ይቀበለው! ⬇️ አፑን ለማውረድ ይህንን ይጫኑ፦ 🔗 https://t.me/kasimApp/173 #ጽልመቱን_የገፈፈው_ብርሃን #ንጽጽር #ኢስላም
Открыть в Telegramእንግዲህ እውነታው ይህ ነው! ችግሩ ያለው ታሪክ ላይ ሳይሆን፣ የምዕራባውያን ሚዲያ በፈጠረው የደብል ስታንደርድ መነጽር ውስጥ ነው። አንድ ሙስሊም ነኝ የሚል ግለሰብ ወይም ቡድን በየትኛውም ቦታ ራሱን ለመከላከል የሚያደርገውም ትግልም ይሁን ሌላ አካል ደግሞ መስመር ስቶ ጥፋት ሲሠራ ወዲያውኑ ጣቱ ወደ እስልምናና ወደ 2 ቢሊዮን ሙስሊሞች ይቀሰራል፤ ከላይ የዘረዘርናቸው ቡድኖች በመጽሐፍ ቅዱስና በመስቀል ስም ዓለምን የሚያንቀጠቅጥ ጭፍጨፋ ሲፈጽሙ ግን «የግለሰብ ጥፋት ነው፣ የአእምሮ ሕመምተኛ ነው» ተብሎ ይታለፋል። በእምነቱ ውስጥ የተዘረዘሩ እልፍ የግድያ ትምህርቶች ሁሉ ይሸፋፈናሉ። ለሌላው እምነት ሲሆን ግን ያለ አውድም ጭምር ይመዘዛሉ። ወንጀልና ሽብርን ሆን ብሎ ከሙስሊሙ ጋር ማያያዝ ያለፈበት ፕሮፓጋንዳ ነው፤ ታሪክን ሳያነቡ በምዕራባውያን ፕሮፓጋንዳ ተገፋፍቶ «ሙስሊም ብቻ ገዳይ ነው» እያሉ መለፈፍ ግን ከዕውቀት ድህነትና ራስን ለትዝብት ከመዳረግ ውጪ ሌላ ትርጉም የለውም። https://t.me/Yahyanuhe https://whatsapp.com/channel/0029Vb8AsW52UPB7oGE0mw1d
Открыть в Telegramበዘመናችን ለምዕራባውያን ሚዲያ ፕሮፓጋንዳ በእጅጉ የተጋለጡ ብዙ ሰዎች፣ እንዲያውም እዚሁ በገዛ ሀገራችን ጭምር፣ ያለ አንዳች ሐፍረት «ሽብርተኝነትና ታጥቆ ሰው መግደል የሙስሊሞች ብቻ መገለጫ ነው፤ እምነቱ እንዲገድል የሚያዘውም ሙስሊሙን ብቻ ነው» የሚል እጅግ አስቂኝና ከታሪክ ጋር የተጣላ ሙግት ሲያቀርቡ ይስተዋላሉ። እስልምና ስለ ጂሃድ ጽንሰ-ሐሳብ ያስተማራቸውን ትክክለኛ ሕግጋትና መርሆዎች፣ እንዲሁም በዚህ ዙሪያ ለሚነሱ ብዥታዎች የተሰጡ ሰፋፊ ምላሾችን ማንኛውም አንባቢ በቀላሉ ሊረዳው በሚችል ደረጃ በቴሌግራም ቻናሌ ላይ ላለፉት አመታት መልስ በመስጠት አስቀምጫለሁ፤ እዚያ ገብታችሁ መመልከት ትችላላችሁ። ዛሬ ግን እንደ መነሻ አንድ መሠረታዊ ጥያቄ እንፈትሽ፦ እውነት እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት «ለክርስትና ጥብቅና እቆማለሁ፣ ክርስትናን አስፋፋለሁ» ብሎ የታጠቀና ንጹሐንን የጨፈጨፈ አካል የለም ወይ? ይህንን ካነሳን አይቀር መዘርዘሩ አስፈላጊ ስለሆነ ከዚህ በታች እንዳሰው። እንዲያው በቅርብ ጊዜ እዚሁ በሀገራችን ግዙፍ መስቀል አንገታቸው ላይ አንጠልጥለውና በቤተክርስቲያን አባቶች ተባርከው መሣሪያ ይዘው፣ አንዳንዶቹ በገዳማት ሳይቀር መሽገው የሚዋጉትን ወደ ጎን እናድርጋቸውና፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የቅርብ ጊዜ ታሪክን ብቻ ገረፍ ገረፍ አድርገን ስንመለከት የሚከተሉትን ተጨባጭ እውነታዎች አንድ ሁለት እያልን መጥቀስ እንችላለን፦ 1. የሎርድ ሪዚስታንስ አርሚ በ1986–1987 ዓ.ል (እ.ኤ.አ) አካባቢ በጆሴፍ ኮኒ የተመሠረተው ይህ አሸባሪ ቡድን፣ ዋና ዓላማው የኡጋንዳን መንግሥት ገልብጦ «በመጽሐፍ ቅዱሱ አሥርቱ ትእዛዛት የሚመራ መንግሥት መመሥረት» እንደሆነ በይፋ ያወጀ ድርጅት ነው። ይህ ቡድን በኡጋንዳ፣ በደቡብ ሱዳን፣ በኮንጎ እና በመካከለኛው አፍሪካ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሐንን ገድሏል፣ አካል አጉድሏል፣ በርካታ ሕፃናትንም አግቶ ለውትድርና ዳርጓል። 🔗 ምንጭ (Britannica)፦ https://www.britannica.com/topic/Lords-Resistance-Army 2. ኩ ክሉክስ ክላን - አሜሪካ መጀመሪያ በ1865፣ በሁለተኛው ዙር ደግሞ በ1915 ዓ.ል በሰባኪው ዊሊያም ጄ. ሲመንስ እንደ «የፕሮቴስታንት ክርስቲያን ወንድማማችነት ድርጅት» ተመሥርቶ የሚንቀሳቀስ የሽብር ቡድን ነው። የሚነድ መስቀልን እንደ ዋነኛ ዓርማው በመጠቀምና ክርስቲያናዊ ማንነትን ሽፋን በማድረግ፣ በጥቁሮች፣ በአይሁዶችና በሌሎች አናሳ ማኅበረሰቦች ላይ አሰቃቂ ግድያዎችንና የቦምብ ጥቃቶችን (እንደ 1963ቱ የበርሚንግሃም ፍንዳታ) ፈጽሟል። 🔗 ምንጭ (Britannica)፦ https://www.britannica.com/topic/Ku-Klux-Klan 3. አንቲ-ባላካ - መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ በ2013–2014 ዓ.ል በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የተደራጁት እነዚህ የክርስቲያን ሚሊሻዎች፣ በሀገሪቱ በሚኖሩ ንጹሐን ሙስሊሞች ላይ የዘር ማጽዳት ዘመቻ ከፍተዋል። በርካታ መስጂዶችን ሙሉ በሙሉ አውድመዋል፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞችንም ከቀያቸው አፈናቅለው ከሀገር አባርረዋል፤ ይህንንም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት በሰነድ አረጋግጠውታል። 🔗 ምንጭ (Human Rights Watch)፦ https://www.hrw.org/news/2014/02/12/central-african-republic-muslims-forced-flee 🔗 ምንጭ (The Guardian)፦ https://www.theguardian.com/world/2014/mar/10/central-african-republic-christian-militias-revenge 4. የትሪፑራ ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (NLFT) - ሕንድ በ1989 ዓ.ል በሕንድ ትሪፑራ ግዛት የተመሠረተና በሕንድ መንግሥት በአሸባሪነት የተፈረጀ ክርስቲያን ታጣቂ ቡድን ነው። በማኒፌስቶው ላይ ዋና ዓላማው «የእግዚአብሔርንና የኢየሱስ ክርስቶስን መንግሥት በትሪፑራ ማስፋፋት» እንደሆነ ያስቀመጠ ሲሆን፣ ለአሥርት ዓመታት በንጹሐን ዜጎችና በጸጥታ ኃይሎች ላይ በፈጸማቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ጥቃቶች የብዙዎችን ሕይወት ቀጥፏል፤ ነዋሪዎችንም በኃይል ወደ ክርስትና እንዲቀየሩ ጫና ሲያደርግ ቆይቷል። 🔗 ምንጭ፦ https://en.wikipedia.org/wiki/National_Liberation_Front_of_Tripura 5. የእግዚአብሔር ሠራዊት (Army of God) እና «ክርስቲያን አይደንቲቲ» (Christian Identity) - አሜሪካ በአሜሪካ ውስጥ አክራሪ የክርስትና ትርጓሜን መሠረት በማድረግ የተደራጁ የሽብር ቡድኖች ናቸው። ለምሳሌ በ1996ቱ የአትላንታ ኦሊምፒክ ፓርክ የቦምብ ፍንዳታና በተለያዩ ተቋማት ላይ የቦምብ ጥቃት በመፈጸም በFBI በቀዳሚነት ሲፈለግ የነበረው ኤሪክ ሩዶልፍ፣ በ«ክርስቲያን አይደንቲቲ» አስተሳሰብ ተኮትኩቶ ያደገና ጥቃቶቹንም በ«Army of God» ስም ኃላፊነት የወሰደ ክርስቲያን አሸባሪ ነበር። ይህ ርዕዮተ ዓለም ዛሬም ለበርካታ የኒዮ-ናዚና የነጭ የበላይነት አቀንቃኝ አሸባሪዎች ዋነኛ ነዳጅ ሆኖ ያገለግላል። 🔗 ምንጭ (Britannica)፦ https://www.britannica.com/biography/Eric-Rudolph 🔗 ምንጭ (Middlebury Institute - CTEC)፦ https://www.middlebury.edu/institute/academics/centers-initiatives/ctec/ctec-publications/christian-identitys-new-role-extreme-right 6. የቦስኒያ ሰርብ ታጣቂዎች - የስሬብሬኒካው ጭፍጨፋ (1995) በጁላይ 1995 ዓ.ል በቦስኒያ በተፈጸመው የስሬብሬኒካ የዘር ማጥፋት ወቅት፣ «ስኮርፒዮንስ» የተባለው የሰርብ ኦርቶዶክስ ታጣቂ ክፍል ወደ ግድያው ከመሰማራቱ በፊት በኦርቶዶክስ ቄስ ተባርኮና ተጸልዮለት፣ ታጣቂዎቹም እጅ የሌላቸውን ንጹሐን ሙስሊም ታዳጊዎችና ወንዶች በግፍ ሲረሽኑ የሚያሳየው ቪዲዮ በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት (ICTY) ቀርቦ ዓለምን አስደንግጧል። 🔗 ምንጭ (RFE/RL)፦ https://www.rferl.org/a/1059192.html 7. የሊባኖስ ፋላንጂስት ሚሊሻዎች - የሳብራና ሻቲላ ጭፍጨፋ (1982) በሴፕቴምበር 1982 ዓ.ል በሊባኖስ የማሮናይት ክርስቲያን ታጣቂ ኃይል (ፋላንጂስቶች)፣ በቤይሩት በሚገኙት የሳብራና ሻቲላ የስደተኞች ካምፖች ውስጥ በመግባት ሴቶችንና ሕፃናትን ጨምሮ ከመቶዎች እስከ ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን ፍልስጤማውያን ሙስሊሞችን በአሰቃቂ ሁኔታ ጨፍጭፈዋል። 🔗 ምንጭ (Britannica)፦ https://www.britannica.com/event/1983-Beirut-barracks-bombings 8. የዘመናዊው «የመስቀል ጦረኛ» ሽብርተኝነት - አንደርስ ብሬቪክ (ኖርዌይ፣ 2011) በኖርዌይ 77 ንጹሐን ዜጎችን በቦምብና በጥይት የጨፈጨፈው አንደርስ ቤህሪንግ ብሬቪክ፣ ድርጊቱን የፈጸመው ራሱን «የክርስቲያን አውሮፓ ጠባቂ (Knights Templar)» አድርጎ በመቁጠርና በእስልምና ላይ ጦርነት በማወጅ ነው። 🔗 ምንጭ (West Point Combating Terrorism Center)፦ https://ctc.westpoint.edu/a-post-trial-profile-of-anders-behring-breivik/
Открыть в Telegramበኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ያለው የንጹሐን ግድያና መፈናቀል እጅግ ዘግናኝና አደገኛ ነው። ከዚህም በላይ የሚያሳዝነው ግን፣ በንጹሐን ደም ላይ ቁጭ ብለው በስሌት የሚነግዱ የፖለቲካና የሚዲያ ልሂቃን የሚከተሉት «የነጠላ መጣልና ማንሳት ፖለቲካ» ነው፤ እንደ ፖለቲካዊ አዋጭነቱ እየመረጡ ሀይማኖት ሲፈለግ ነጠላቸውን ሲያነሱ የብሄሩ ሲፈለግ ደግሞ ነጠላቸውን በመጣል የሚሄዱበት አስቀያሚ አካሄድ! ይህንን የመረጣ አካሄድ በተጨባጭ ክስተቶች ለመመልከት የሚከተሉትን ጥቂት ምሳሌዎች ብቻ እናንሳ፦ 1. በወለጋ እና በቤኒሻንጉል፦ በወለጋ የሚገደሉት የአማራ ክልል ተወላጅ ሙስሊሞች ሲሆኑ፣ ስለ ሙስሊምነታቸው ማንሳት ለፖለቲካ ፍጆታ ስለማያዋጣ ሃይማኖታዊ ማንነታቸው ተሸፍኖ የብሔር ካባ ብቻ ይለብሳሉ። በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል የተገደሉት አማሮች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ብሔሮችም (እንደ አገው ያሉ) ጭምር ቢሆኑም፣ እዚያም ቦታ ላይ ሙስሊሞች ስለሚገደሉ ሃይማኖታዊ ትርክቱን ትተው የተሻለ ያሉትን የብሔር ትርክት ብቻ ይመርጣሉ። ያውም ሌላውን ብሄር ያላካተተ አንድ ትርክት ብቻ ወስደው ለሚፈልጉት አላማ ይጠቀሙበታል። 2. በጎንደር፦ በሌላ አካባቢ «በብሔር ወገናችን ናቸው» ብለው የጮኹላቸውን እነዚያኑ ሙስሊሞች፣ በገዛ ክልላቸው በጎንደር በሃይማኖታቸው ምክንያት ሲገደሉ ግን ገዳዮቹን ማውገዝ አልቻሉም። ይልቁንም ገዳዩ «በሃይማኖት ወገናችን ነው» ብለው የሚያስቡት አካል ስለሆነ፣ ለገዳዮቹ ጥብቅና ቆመው ጥቃቱን ከሌላ ጠረፍ የመጣ አካል እንደፈጸመው በማስመሰል የወገኖቻቸውን ሞት ሙስሊሞች ስለሆኑ ብቻ መሳለቂያ አደረጉት። 3. በአርሲ፦ አርሲ ላይ ንጹሐን ተገደሉ ሲባል ደግሞ እነዚሁ ልሂቃን ወዲያውኑ ስሌታቸውን ይቀይራሉ። የአርሲውን ጥቃት በብሔር መነጽር መውሰድ «ፖለቲካዊ ትርፍ የለውም» ብለው ስለሚያስቡ፣ የብሔር ካባውን አውልቀው ነጠላቸውን ይደርቡና ጉዳዩን ሙሉ በሙሉ ወደ ቤተክርስቲያንና ወደ ሃይማኖት አጀንዳ ይጠመዝዙታል። በጣም የሚያሳዝነው እውነታ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በሚፈጸሙ ጥቃቶች ውስጥ የመስጂዱም ሆነ የቤተክርስቲያኑ ሰዎች፣ ሁሉም ንጹሐን ዜጎች ሰለባ እየሆኑ መሆኑ ነው። ነገር ግን ከጀርባ ሆነው ሕዝቡን የሚመሩት ልሂቃን በብሔር በኩል ሲፈልጉት ነጠላቸውን አውልቀው መግለጫ ይሰጣሉ፤ በሃይማኖት ሊነግዱበት ሲፈልጉ ደግሞ ነጠላቸውን አንስተው ተሸፍነው «በሃይማኖቴ ምክንያት» የሚለውን ትርክት በመምዘዝ በደፈናው ሌላውን ሁሉ በማጠልሸት ጉዳዩን በፈለጉበት አቆጣጫ ሊመሩት ይታገላሉ። ይህ ትችት በስሜት የሚነዳውን ተራ ተከታይ የሚመለከት ሳይሆን፣ ከጀርባ ሆኖ ይህንን መርዝ የሚቀምመውን ልሂቅ የሚመለከት ነው። የንጹሐንን ሞት ለፖለቲካ መነገጃ ማድረግ ፈጽሞ ግድያውን አያስቆመውም፤ ትርፉ የሐዘን ነጋዴዎችን ኪስና የፖለቲካ ፍላጎት ማርካት ብቻ ነው። ሚስኪኖች በሞቱ ቅጽበት ቀድመው የተዘጋጁ በሚመስል መልኩ በመላ ሀገሪቱ የሚገኘውን ሙስሊም በመፈረጅ ቅስቀሳ ማድረግ ሌላ አላማ ከሌለው በስተቀር ፈጽሞ ለሟቾቹ ማዘን አይደለም! https://t.me/Yahyanuhe https://whatsapp.com/channel/0029Vb8AsW52UPB7oGE0mw1d
Открыть в Telegramየኢትዮጵያ ሙስሊም ዕጣ ፈንታ እጅግ ያሳዝናል! ላለፉት ሳምንታት በዋና ዋና የኦርቶዶክስ መምህራንና ሚዲያዎች ጭምር መላው የኢትዮጵያ ሙስሊም እንደ ገዳይና ኦርቶዶክሶችን እንደሚፈጅ ተደርጎ ከፍተኛ የስም ማጥፋትና የፍረጃ ዘመቻ ሲካሄድበት ቆይቷል። በጣም የሚያሳዝነው ግን፣ በአርሲ ያ አሰቃቂ ግድያ በተፈጸመበት በዚያው ሰሞን፣ በወለጋ ታላቅ ዑለማን ጨምሮ በርካታ ሙስሊሞች በግፍ ተገድለዋል፤ በጎንደርም እንዲሁ የለመደው ገዳይ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ንጹሐን ሙስሊሞችን ጨፍጭፏል። ነገር ግን ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የአርሲው ጉዳይ በኦርቶዶክሱ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣና ሐዘን በፈጠረበት ወቅት ላይ ስለነበረ፣ ከጥቂት አክቲቪስቶች በቀር ሌላው ምናልባት «ሞት ያወዳድራሉ» የሚል አስቀያሚ ትርክት እንዳይሰጠው በመጠንቀቅ ብቻ በገዛ ወገኖቹ ሞት ላይ እንኳን ድምፁን አጥፍቶ ዝምታን መረጠ። ይሁን እንጂ ይህንን ዝምታና ትዕግሥት በክብር የወሰደለት አልነበረም። ይልቁንም የአርሲውን ጥቃት ሙሉ በሙሉ በሙስሊሙ ላይ በመለጠፍ፣ መላውን የኢትዮጵያ ሙስሊም በጅምላ «ገዳይ» ብሎ የመወንጀልና አስጸያፊ ፍረጃ የመስጠት ዘመቻው ተጧጧፈ። እነሆ ዛሬ ደግሞ እውነታው ፍንትው ብሎ ወጥቷል! በኦሮሚያ ክልል ለተፈጸመው ጥቃት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ / በተለምዶ ሸኔ) «እርምጃውን የወሰድኩት እኔ ነኝ» ሲል በይፋ ኃላፊነቱን መውሰዱን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። እዚህ ላይ ትልቁ አስገራሚና አሳዛኝ እውነታ ምንድነው? ትላንት ሙስሊሙን «ገዳይ» እያሉ ሲወነጅሉና የጥላቻ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩት አካላት፣ ሲያሻቸው ነጠላ ለብሰው የሃይማኖት ሰባኪ የሚሆኑ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ነጠላውን ሲያወልቁ የብሔር አክቲቪስትና ታጣቂዎች ዋነኛ ደጋፊዎች ናቸው። የሚገርመው ደግሞ ዛሬ የአርሲውን ጥቃት ፈጸምኩ ብሎ ኃላፊነት ከወሰደው ታጣቂ ቡድን ጋር በፖለቲካና በወታደራዊ ስሌት ጥምረት ፈጥረው ሲሠሩ የነበሩት እነዚሁ አካላት መሆናቸው ነው! በዚህ ሁሉ መካከል የኢትዮጵያ ሙስሊም ማኅበረሰብ እጅግ ልብ በሚሰብር አጣብቂኝ ውስጥ ወድቋል፤ በአንድ በኩል በየአካባቢው በግፍ ይገደላል፣ ሐዘኑን እንኳን በነጻነት መግለጽ አይችልም፤ በሌላ በኩል ደግሞ ምንም ባላጠፋበትና እጁ በሌለበት ጉዳይ በጅምላ «ገዳይ» ተብሎ ይፈረጃል! https://t.me/Yahyanuhe
Открыть в Telegramእንዲህ ዓይነት የጅምላ ፍረጃዎች እጅግ አደገኛ ናቸው! እስቲ አስቡት፤ አንድ ሙስሊም ዳዒ መስጂድ መሃል ቆሞ «የሀገራችንን ክርስቲያኖች ባጎረስን ነከሱን፤ በሏቸው!» የሚል ስብከት ቢያደርግ ኖሮ፣ የሚፈጠረውን የሚዲያ ጩኸት፣ ውግዘትና ውጥንቅጥ ገምቱት! በኦርቶዶክሱ በኩል ግን የአክቲቪስቶች ግፊት አስተውሎታቸውን የነጠቃቸው አንዳንድ ሰባኪዎች በጀብደኝነት የሚናገሯቸው መሰል ኃላፊነት የጎደላቸው ንግግሮች በዝምታ መታለፍ የለባቸውም፤ እጅግ ጥብቅ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል። ሙስሊሙን በጅምላ የመፈረጅና የጅምላ ጥቃት እንዲፈጸምበት እየተደረገ ያለው ቅስቀሳ፣ ሀገሪቱን ወደ አስከፊ የደም አፋሳሽ ቀጠና ለመቀየር ባቀዱ አካላት በተጠና መልኩ እየተሠራ ያለ ሴራ ነው። መገደልንና መገፋትን መታገል እንዲሁም ራስን መከላከል ሌላ ጉዳይ ነው፤ ንጹሑን ሙስሊም ሕዝብ በጅምላ እንዲገደል መቀስቀስ ግን ፈጽሞ ሌላ ወንጀል ነው። እንዲህ ዓይነት የጥላቻና የግድያ ቅስቀሳዎች (Incitement) ተገቢው ሕጋዊና ሞራላዊ እርምት ካልተሰጣቸው፣ ዳፋቸው ለሀገርም ለሕዝብም እጅግ አደገኛና ከባድ ነው። https://vt.tiktok.com/ZSpsHwMdN/
Открыть в Telegramበየትኛውም የሀገራችን ክፍል፣ በአርሲም ሆነ በጎንደር፣ በወለጋም ሆነ በሌላ ስፍራ የንጹሐን ዜጎች ደም መፍሰስና ሕይወት መቀጠፍ እጅግ የሚያሳዝን፣ ልብ የሚሰብርና በማንኛውም መመዘኛ ሊወገዝ የሚገባው አረመኔያዊ ተግባር ነው። የሰው ልጅ ሕይወት ክቡር ነው፤ ንጹሕ ሰው ሲገደል ሰብዓዊነት ያለው ሁሉ ያዝናል፣ ፍትሕንም ይጠይቃል። ነገር ግን፣ ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ባለ አንድ ቪዲዮ ላይ አንድ መነኩሴ በአርሲ የተፈጸመውን ግድያ መነሻ በማድረግ ያሰሙት ንግግር፣ ከሃይማኖት አባት ይቅርና ከአንድ ተራ ዜጋ እንኳን የማይጠበቅ የጥላቻ ቅስቀሳና የታሪክ ዝባዝንኬ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። በቪዲዮው ላይ ግለሰቡ ንጹሐንን የገደሉት ታጣቂዎች ለሕግ ይቅረቡ ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ፣ በጅምላ የኢትዮጵያን ሙስሊም ማኅበረሰብ «አረመኔ፣ ጅል ጅላጅል፣ እስላም» እያሉ በጸያፍ ቃላት ሲዘልፉ፣ ታሪክን አጣምመው (አድዋ ላይ ከጣሊያን ጋር የተደረገውን ጦርነት ሳይቀር «እስላሞችን አባሮ» በማለት በሐሰት ሲተርኩ) እና ምዕመናንን «ወገብህ ላይ ያለውን ክላሽ አውጥተህ ልቀቅበት፣ በገደለህ ልክ ግደል» በማለት ለእርስ በርስ እልቂት ሲቀሰቅሱ ይደመጣሉ። የገደለህ ወይም ያጠቃህ ታጣቂ ላይ፣ መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ መጠየቅ ወይም ራስን ከታጣቂው መከላከል አንድ ነገር ነው፤ ነገር ግን ጉዳዩ በፍጹም የማይመለከተውን፣ በሰላም ወጥቶ የሚገባውን ሚሊዮን ሙስሊም ማኅበረሰብ ያለ አንዳች ማስረጃ ጎትቶ በማስገባት መሳደብና መፈረጅ ዓይን ያወጣ ብልግናና በንጹሐን ደም መነገድ ነው። https://t.me/Yahyanuhe
Открыть в Telegram